Category Archives: Wisdom

የእውቀት ችግር የእግዚአብሔር ችግር ነው

conscious1.jpg

ሰው እውቀት ያስፈልገዋል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ነፍስ ያለእውቀት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም ይላል፡፡ ሰው እውቀት ከጎደለውቅ ሁሉ ነገር ይጎድለዋል፡፡

ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል። መጽሐፈ ምሳሌ 19፡2

ሰው በእግዚአብሄር የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከሚያስፈልገው ከሙሉ እውቀት ጋር ነው፡፡ ሰው ለኑሮ የሚያስፈልገው እውቀት ሁሉ ነበረው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በሚገባ ያውቀው ነበር፡፡ ሰው ስለ እግዚአብሄር የሚያስፈልገው እውቀት ሁሉ ነበረው፡፡

ሰው በሰይጣን ማታለል ምክንያት የማያስፈልገውን እውቀት ሲፈልግል ለኑሮና ለስኬት የሚያስፈልገውን ዋናውን እውቀት አጣው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን እውቀት ሲያጣው ስለሌላ ስለሁሉም ነገሮች ያሉት እውቀቶች ሁሉ ተዛቡበት፡፡ ሰው ስለ እግዚአብሄር ያለውን ትክክለኛውን እውቀት ሲያጣው ስለራሱ ያለውን ትክክለኛ እውቀት አጣው፡፡ ሰው ስለ እግዚአብሄር ያለውን ትክክለኛ እውቀት ሲያጣው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ስለተፈጠረው ሰው ትክክለኛውንና ንፁህን  እውቀት አጣው፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

የሰው የእውቀት ችግር የተጀመረው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ያለው እውቀት ሲዛባ ሌላ ሁሉ እውቀቱ ተዛባ፡፡

ሰው እውቀት ካስፈለገው መጀመሪያ ማወቅ ያለበት የእግዚአብሄርን እውቀት ነው፡፡ ሰው ወደ እውቀት ከተመለሰ መመለስ ያለበት ወደ እግዚአብሄር እውቀት ነው፡፡ ሰው እውቀት ካስፈለገው እውቀትን መጀመር ያለበት እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚኖር በማወቅ ነው፡፡

ሰው እውቀት አለኝ የሚለው መጀመሪያ ከፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር በማወቅ ነው፡፡ ሰው እውቀት አለኝ ማለት የሚችለው ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና በመስጠት ነው፡፡ ሰው እውቀት አለኝ ማለት የሚችለው እግዚአብሄርን በመፍራት ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡7

የሰው እውነተኛ እውቀት የሚጀምረው በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረውን እግዚአብሄርን እንደ አምላክነቱ አውቅና በመስጠት ነው፡፡

ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡20-21

ሰው ከፈጣሪው ጋር እንደት በትህትና እንደሚሄድ ካላወቅ ሌላው እውቀቱ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር ካላወቀ ሌላ እውቀትን መሰብሰብ ራስብን ማድከም ነው፡፡

ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፤ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል። የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። መጽሐፈ መክብብ 12፡12-13

ሰው እግዚአብሄርን የመፍራት ጥበብ ከሌለው ምንም ጥበብ እንደሌለው ይቆጠራል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የመፍራት ጥበብ ካለው ደግሞ ለኑሮ ለስኬትና ለክንውን የሚያስፈልገው ጥበብ ሁሉ እንዳለው ይቆጠራል፡፡

አሁን ያለው የሰው የእውቀት ችግር ሁሉ የእግዚአብሄር እውቀት ችግር ነው፡፡ የሰው የእውቀት ችግር ሁሉ የሚፈታው የእግዚአብሄር እውቀት ችግር ሲፈታ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ህዝቤ አውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቶዋል የሚለው፡፡

ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። ትንቢተ ሆሴዕ 4፡6

ሰው የእውቀት ችግሩ የሚፈታው የእግዚአብሄርን እውነት ሲያውቅ በነው፡፡ ሰው ራሱንና ሌላውን ሰው በትክክል የሚያውቅው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ የሰው የእውቀት ችግር የሚፈታው የእግዚአብሄር እውቀት ችግር በህይወቱ ሲፈታ ብቻ ነው፡፡

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 8፡32

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

seen by men.jpg

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

ክፉን በክፉ ላለመመለስ ህፃናተ ሁኑ እንጂ ስለህይወታችሁ እወቁ፡፡ ህይወታችሁን እንዳመጣላችሁ አትምሩት፡፡ ህይወታቸሁን ለመምራት አስቡ አቅዱ በእግዚአብሄር ቃል የታደሰ አእምሮዋችሁን ተጠቀሙ፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20

መውጫ መግቢያውን የምትቃኙ ንቁዎችና ብልሆች ሁኑ እንጂ ወደ ወሰዷችሁ የምትጎተቱ ሞኞች አትሁኑ፡፡

እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 10፡16

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

በእእምሮው ህፃን የሆነ ሰው የራሱ የህይወት መርህ የለውም የመጣው ነገር ሁሉ ይወስደዋል፡፡

ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡11

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

በአእምሮው የበሰለ ሰው የሰው የግል መጠቀሚያ አይሆንም፡፡ በአእምሮ የበሰለ ሰው ዘሎ ውሳኔን አይወስንም በአእመሮ ህፃን ያልሆነ ሰው አካሄድን ይመለከታል ይመዝናል፡፡

በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17

የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። መጽሐፈ ምሳሌ 14፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ህፃንነት #ብስለት #ጥበብ #ማስተዋል #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ

በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም

conscious.jpg

በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም

ሰው ከምንም ነገር በላይ በሚያደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሄር አብሮት እንዳለ የሚያደርገው ነገር እግዚአብሄር ያለውን ነገር መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

እግዚአብሔርም፦ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው። እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡14-15

ልዩነት የሚያመጣው የእኛ ብዛትና ማነስ አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ መበርታትና መድከም አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ አዋቂነትና አላዋቂነት አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ ዝናና አለመታወቅ አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው እግዚአብሄር ነው፡፡ ልዩነት የሚያመጣው እግዚአብሄር ከእኛ ጋር መሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሚሳነው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አያቅተውም፡፡

አሳም፦ አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14፡11

ወይም ልዩነት የሚያመጣው ምቹ ስፍራ መሆንህና አለመሆንህ አይደለም፡፡ የእስራኤል ህዝብን እግዚአብሄር ከምድረበዳ ስጋን እንዴት ሊያመጣ ይችላል ብለው አሙት፡፡ እግዚአብሄር በጊዜና በቦታ አይወሰንም፡፡ እግዚአብሄር ግን ጊዜና ቦታ አይገድበውም፡፡ ለእግዚአብሄር ግን የሚሳነው ነገር የለም፡፡

ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት። እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን? ዓለቱን መታ፤ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፤ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን? መዝሙረ ዳዊት 78፡18-20

እግዚአብሄር በሰው ነገር አይታመንም፡፡ እግዚአብሄር በሰው ችሎታ አይደገፈም፡፡ እግዚአብሄር የራሱ ክንድ መድሃኒት ታመጣለታለች፡፡

ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው። ትንቢተ ኢሳይያስ 59፡16

ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ። ትንቢተ ኢሳይያስ 63፡5

በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና፡፡ ሰው እግዚአብሄር የፈለገበትን ነገር እንደሚሰራ ካወቀ ስለብዛት መጨነቅ የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ደጋፊ ቲፎዞ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር በሰው በብዛት አይደገፍም፡፡

ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ጭፍራ እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ  14፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #አይሳነውም #ባለቤት #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ #በጥቂት #በብዙ #ማዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ለሰይጣን ሽንገላ ፍቱን መድሃኒቱ

kylo-ren-star-wars-the-4.jpgሰይጣን በትእቢት ምክንያት ከመውደቁ በፊት የእግዚአብሄር አገልጋይ ነበር፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄርን ቦታ ፈልጎ ከመዋረዱ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ይኖር ነበር፡፡ ሰይጣን በሃጢያት ምክንያት ሲወድቅ ነው ጥበብህን አረከስህ የተባለው፡፡

በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። ሕዝቅኤል 28፡17

ሰይጣን የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ አሁንም ጥበብ አለው፡፡ ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያሳምናል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያታልላል፡፡ ሰይጣን በረከሰው ጥበብ ተጠቅሞ ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ ሰዎችን በእግዚአብሄር ላይ ያሳምፃል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ የሰዎችን ህይወት ያጠፋል ያበላሻል፡፡

ሰይጣን ሰዎችን በማታለል ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ሄዋንን አስቶዋታል፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሄር ጥበብ በቀጣይነት የማይኖረውን ማንኛውንም ሰው ሊያስት ይችላል፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ሰይጣን አያታልለንም ብለን በከንቱ ብንፎክር ከሰይጣን ማታለል አናመልጥም፡፡ ሰይጣን የራሱ የማታለል ሃይለ አለው፡፡ ሰይጣን ምንም አያመጣም ብለን ብንኩራራ ራሳችን ምንም አናመጣም፡፡

የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ ሰይጣን የራሱ ጥበብ ስላለው ካለ እግዚአብሄር ጥበብ በስተቀር ከሰይጣን ማታለል ማምለጥ አንችልም፡፡ በሰይጣን ላለመሳት ከፈለግን የእግዚአብሄር ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወምበት የእግዚአብሄርን ጥበብ ማንሳይ አለብን፡፡ ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም አንችልም፡፡

ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወም ከመሰለን በራሱ በሰይጣን ተታልለናል ማለት ነው፡፡ በሰይጣን ላለመበለጥ  የሰይጣንን ማታለል የሚበልጥ ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የምንበረታው በራሳችን ሃይል ሳይሆን በጌታ ሃይል ብቻ ነው፡፡

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌሶን 6፡10-11

ከእግዚአብሄር ብቻ በምናገኘው ዘርፈ ብዙ ጥበብ በመታገዝ ብቻ ነው የሰይጣንን ሽንገላ እያለ በእኛ ላይ ምንም ሃይል እንዳይኖረው ማድረግ የምንችለው፡፡ በአለቆችና ስልጣናት ላይ በሃይል የምንገለጠው በእግዚአብሄር ጥበብ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 3፡10

በእግዚአብሄር ቃል ጥበብ ስንኖር ግን ኢየሱስ እንዳለው ሰይጣን በእኔ ላይ አንዳች የለውም ማለት እንችላለን፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ማስተዋል #ሽንገላ #አለቆች #ስልጣናት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰይጣን #ዲያብሎስ #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነታችሁም በሰው ጥበብ እንዳይሆን

kingdome.jpgእምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4-5

መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡13

ጥበብ ስለተባለ ብቻ ጥበብ ሁሉ አንድ አይደለም፡፡ በምድር ላይ የሰው ጥበብ አለ የእግዚአብሄር ጥበብ ደግሞ አለ፡፡ የሰው ጥብብና የእግዚአብሄር ጥብብ እጅግ የተለያዩ ጥበቦች ናቸው፡፡

የእግዚአብሄርና የሰው ጥበብ በሚያፈሩዋቸው ፍሬዎች ይታወቃሉ፡፡

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ያዕቆብ 3፡13

ከእግዚአብሄር ዘንድ የሆነው ጥበብ ንፁህ ፥ ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ፣ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለበት ነው፡፡

ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡17

የሰው የሆነው ጥበብ መራርነት ቅንአትንና አድመኝነትን ያፈራል፡፡

ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ያዕቆብ 3፡14-16

ከሚሰበኩት ስብከት የተነሳ እምነታቸው በሰው ጥበብ ላይ የሚሆን ሰዎች አሉ፡፡ ከሚሰበኩት ስብከት የተነሳ ደግሞ እምነታቸው በእግዚአብሄር ሃይል ላይ የሚሆን ሰዎች አሉ፡፡ በሚያባብል በጥበብ ቃል የሚሰበኩ ሰዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመግለጥ የሚሰበኩ ሰዎች አሉ፡፡ የሚያባብል በጥበብ ቃል የተሰበከ ሰው እምነቱ በሰው ጥበብ ላይ ነው የሚሆነው፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመግለጥ የሚሰበኩ ሰዎች እምነታቸው የሚሆነው በእግዚአብሄር ሃይል ላይ ነው፡፡

እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4-5

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #የሰውጥበብ #የእግዚአብሄርጥበብ #በሚያባብል #ተንኮል #መራራ #ቅንዓትና #አድመኛነት #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ

rebuke.jpgየጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ምሳሌ 1፡7

ነፍስ ያለእውቀት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፡፡ ጥበብና እውቀት ከሚገኝበት መንገድ አንዱ ተግሳፅ ነው፡፡ ተግሳፅ የሰው ሃብት ነው፡፡ ተግሳፅን የሚሰማ ሰው ደግሞ ተግሳፅ ከክፉ ይጠብቀዋል፡፡

ተግሳፅን የማይሰማ ሰው ግን ያንኑ ስንፍና ሲደግመው ሳያድግና ሳይለወጥ እንደተፀፀተ ይኖራል፡፡ ሰነፍ ሰው በተግሳፅ ለመታረም ከመትጋተ ይልቅ ስንፍናው በህይወት ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍል ያደርገዋል፡፡

እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። ምሳሌ 23፡23

ሰው ስለዘለፋ እና ተግሳፅ ጥቅም እውቀት ከሌለው ዘለፋንና ተግሳፅን ይንቃል፡፡ ዘለፋና ተግሳፅ ያላቸውን ዋጋ የተረዳ ሰው ያከብራቸዋል፡፡ የተግሳፅን አስፈላጊነት የተረዳ ሰው ለተግሳፅ ሙሉ ልቡን ይሰጣል፡፡ የዘለፋን ጥቅም ያወቀ ሰው የዘለፋን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ እስከሚጠቀምበት ድረስ ዘለፋን አያልፈውም፡፡

ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፤ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።ምሳሌ 4፡13

የዘለፋን ጥቅም የማያውቅ ሰው ግን የገሰፀው ሰው ጠላቱ ይመስለዋል፡፡ የተግሳፅን አስፈላጊነት ያልተረዳ ሰው ግን የሚገስፀው ሰው ያለአግባብ የሚጠቀምበት ይመስለዋል፡፡

በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ። ማቴዎስ 7፡6

ሰው ከተግሳፅ ምን እጠቀማለሁ ማለቱ ግን ወሳኝ ነው፡፡ ተግሳፅ ራሳችንን እንድናይ ያደርገናል፡፡ ተግሳፅ እኔ ሃላፊነት የመወስደው ስለየቱ ጥፋት ነው ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ተግሳፅ ራሳችንን እንድናነፃ እድልን ይሰጠናል፡፡ ተግሳፅ ትክክል ብንሆን እንኳን ትክክል መሆናችንን ያፀናልናል፡፡

ብልህ ሰው ህይወት ከሚገስፀው ሰው ቢገስፀው ይሻለዋል፡፡ ብልህ ሰው ውድቀት ከሚያዋርደው ዘለፋ ቢያዋርደው ይቀለዋል፡፡ ጠቢብ ሰው መከራ ከሚመክረው ሰው ቢመክረው ይሻለዋል፡፡

ዘለፋን የሚጠላ ገንዘቡ የማያደርግ ሰው ዘለፋን የሚንቅ ቸልተኛ ሰው በፍፃሜው እንዴት እንደሚፀፀት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ አትናገሩኝ የሚል ሰው በትእቢቱ ይፀፀታል፡፡

በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥ ትላለህም፦ እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ! የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም። ምሳሌ 5፡11-13

ዘለፋን የሚታገስ ፡ በተግሳፅ ራሱን የሚያይ በተግሳፅ ተጠቅሞ ራሱን የሚያሻሻል ሰው እየለመለመ ፣ እያበበና እያፈራ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #ተግሳፅ #ዘለፋ #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ

tahoepurewater-slide-2.jpgበውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።  ሕዝቅኤል 28፡17

ሰይጣን እግዚአብሄር ላይ በማመፅ ከመውደቁ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ነበር የሚኖረው፡፡ ሰይጣን ከክብሩ ሲወድቅ ግን የሰይጣን ጥበብ ረከሰ፡፡

ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚታለሉት ጥበበኛ የሆኑ እየመሰላቸው ነው፡፡ ጥበበሦች የሆኑ ሲመስላቸው የማያስተውሉ ይሆናሉ፡፡

ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ ሮሜ 1፡22

ሰዎች ጥበብ አለን ይላሉ ነገር ግን ያላቸው ጥበብ ምን አይነት ጥበብ እንደሆነ አያስተውሉም፡፡ ሰዎች በጥበብ እየኖሩ ይመስላቸዋል ነገር ግን ያላቸውን የጥበብ አይነት ለይተው አያውቁትም፡፡

ሰዎች በአግዚአብሄር ጥበብ እየኖሩ እየመሰላቸው በሰይጣን ጥበብ ይኖራሉ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ጥበብ ሁሉ እውነተኛ ጥበብ እንዳይደለ ያስተምራል፡፡ ጥበብ ሁሉ ንፁህ ጥበብ እንዳይደለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ ንፁህ ጥበብ እንዳለ ሁሉ የረከሰ ጥብብ እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ ያስተምረናል፡፡

ሰይጣን ጥበብ አለው፡፡ ነገር ግን የሰይጣን ጥበብና የእግዚአብሄር ጥበብ አንድ አይደሉም፡፡ የሰይጣን ጥበብ የረከሰ ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥብብ ቅዱስ ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የየዋህነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የተንኮል ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የይቅርታ ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የመራርነት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የፍቅር ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የቅንአት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የአንደነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የአድመኝነትና የመከፋፈል ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የሰላም ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የጥል ጥበብ ነው፡፡

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡13-17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #መራራ #ቅንዓትና #አድመኛነት #ንጽሕት #በኋላም #ታራቂ #ገር #እሺባይ #ጥርጥር #ግብዝነት  ##አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሔር በእኛ ላይ አይደለም ፣ እግዚአብሔር ለእኛ ነው

maxresdefault (4).jpgእግዚአብሄር ቸር አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የማንንም እድገት አይጠላም፡፡ እግዚአብሄር የማንንም ደስታ አይቃወምም፡፡ እግዚአብሄር የነጻነት አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ላይ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡

እግዚአብሄር የህግን ብዛት ዘርዝሮ ሰዎችን አሳስሮ የሚያስቀምጥ የስጋት አምላክ አይደለም፡፡

የእግዚአብሄር ትእዛዞች ከባዶች አይደሉም፡፡

ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3

ሰው በነፃነት እንዲሰራ ፣ እንዲያድግና እንዲለወጥ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር እጅግ ረቂቅ ከመሆኑ የተነሳ እግዚአብሄርን ለማስደሰት በስነመለኮት ዲግሪ ማግኘት ፣ ብዙ መፅሃፎችን ማንበብና ብዙ የምርምር ስራዎችን መስራት አይጠይቅም፡፡ እግዚአብሄርን ማስደሰት ሊደረስበት የማይቻል ውስብስብ ነገር አይደለም፡፡

ሰው እግዚአብሄር የሚፈልገውን ይህን አንድ ነገር ካደረገ ባለው እውቀት ተጠቅሞ እግዚአብሄርን ማስደሰት ይችላል፡፡

እግዚአብሄር አንድ የሚጠይቀው ነገር ግን አለ፡፡ ሰው ሌላ ምንም ነገር ባያደርግ ይህንን ነገር ግን እንዲያደርግ እግዚአብሄር ይጠብቃል፡፡

የትእዛዛት መደምደሚያ ይህ ነው፡፡ የትእዛዛት ሁሉ አላመ ሰው እግዚአብሄን በመፍራተ እንዲኖር ነው፡፡ የሰው ሃላፊነቱ ሁሉ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ትእዛዙን መጠበቅ፡፡

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መክብብ 12፡13-14

ምክኒያቱም እግዚአብሄር የሰውን ስራ ሁሉ ወደፍርድ ያመጣዋል፡፡ እግዚአብሄር የተሰወረውን መልካምም ይሁን ክፉ ስራ ወደፍርድ ያመጣዋል፡፡

ሰው እግዚአብሄርን በመፍራት እስካደረገው ድረስ በነጻነት መኖር መስራት መውጣትና መግባት ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ

seen by men.jpgለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ ማቴዎስ 23፡5

ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። ማቴዎስ 6፡1-2

ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ። ቆላስይስ 3፡22

ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። ማቴዎስ 6፡5

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ።  ኤፌሶን 6፡6

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ሃሳብ #መነሻሃሳብ #ልብ #ንፁህ #ፍቅር #ፉክክር #ቃል #ክብር #ለታይታ #የእግዚአብሔርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Survival of the fittest

servival of the fittest.jpgWhen I was in high school I was taught a Biology theory called the survival of the fittest. Here is the Wikipedia definition of Survival of the fittest copied for you.

“Survival of the fittest” is a phrase that originated from Darwinian evolutionary theory as a way of describing the mechanism of natural selection. The biological concept of fitness is defined as reproductive success. In Darwinian terms the phrase is best understood as “Survival of the form that will leave the most copies of itself in successive generations.”

In nature if you adapt the environment you can live longer, you can produce more offspring and you will dominate the earth and can continue by overcoming danger or hardship.

The purpose of this article isn’t to argue whether or not the theory is true or not.  I know God created the heavens and the earth and I know that those who give due respect to the creator survive.

But when I always think about the fear of the Lord the survival of the fittest theory comes to my mind.

Furthermore, just as they did not think it worthwhile to retain the knowledge of God, so God gave them over to a depraved mind, so that they do what ought not to be done. Romans 1:28

For although they knew God, they neither glorified him as God nor gave thanks to him, but their thinking became futile and their foolish hearts were darkened. Romans 1:21

God created the heavens and the earth. To survive on earth you need at least a wisdom. To survive on earth you need the wisdom of the fear of God.

The fear of God is the beginning of wisdom. If you don’t have this minimum requirement, you don’t survive on earth. You may live but not really live. You may exist but not be living.

The fear of the Lord is the beginning of wisdom, and knowledge of the Holy One is understanding. Proverbs 9:10

We can’t survive on earth and in life not fearing the Lord and not giving due respect for the God who has created us all and sustains the earth.

The fear of the LORD adds length to life, but the years of the wicked are cut short. Proverbs 10:27

Those who fear the Lord will survive having the goodness of God by their side.

How abundant are the good things that you have stored up for those who fear you, that you bestow in the sight of all, on those who take refuge in you. Psalm 31:19

Those who fear God survive evil by being delivered By God’s angels.

The angel of the Lord encamps around those who fear him, and he delivers them. Psalm 34:7

Those who fear the Lord are highly blessed and their generation survives by becoming blessed as well.

Praise the LORD. Blessed is the man who fears the LORD, who finds great delight in his commands. His children will be mighty in the land; the generation of the upright will be blessed psalms 112:2

According to the Bible, the best way of survival mechanism isn’t getting rich or being famous or being mighty but to fear the Lord.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#time #wisdom #fearofgod #might #money #fame #vapor #redeemtime #tomorrow #today #salvation #church #testimony #soulwinning #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

%d bloggers like this: