Category Archives: tongue

መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ

conscious1.jpg

ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡10-11

ሰው እንደፈለገ እየኖረ ህይወትን ማየት አይችልም፡፡ ሰው ያመጣለትን እየተናገረ የህይወትን ደስታ ማየት አይችልም፡፡ ሰው እንደልቡ እያደረገ የህይወትን እርካታ ማየት አይችልም፡፡

በህይወት መልካም ቀኖች የሚባሉ ቀኖች አሉ፡፡ በህይወት የእርካታና የደስታ ቀኖች አሉ፡፡ በህይወት የእረፍት ቀኖች አሉ፡፡ ሰው እነዚህን ነገሮች ካደረገ ህይወትን ያጣጥማል፡፡ ሰው አነዚህን ነገሮች ካላደረገ ህይወትን አያይም፡፡

ሁላችንም እግዚአብሄርን ተስፋ እናደርጋለን፡፡  እነዚህን የሚያድርግ ሰው ግን ካልተመለሰ በስተቀር ህይወትንና መልካሞችን ቀኖች ሊያይ አይችልም፡፡ እነዚህን ነገሮችን በማድረግ የሚቀጥል ሰው ካለተመለሰ በስተቀር ህይወትንና መልካሞችን ቀኖች ከማየት ተስፋ መቁረጥ አለበት፡፡ ሁሉም ሰው መልካምን ቀኖች ለማየት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን መልካምን ቀኖች ለማየት የሚያስችሉትን ነገሮች የሚያደርገው ሁሉም ሰው አይደለም፡፡

በህይወቱ እርካታን ማየት የሚወድ ሰው ሊያደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ በህይወት እርካታ የሚገኘው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡

  1. መላሱን ከክፉ ይከልክል

ለህይወቱ ዋጋ የሚሰጥ ህይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው መላሱን ክፉ ከመናገር መከልከል አለበት፡፡ ክፉ ነገርን ዋጥ ማድረግ አለበት፡፡ ክፉን እንዳይናገር ራሱን መግዛት አለበት፡፡ ክፉን እንዳይናገር ትሁት መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለሌላወ ሰው የሚናገረው መልካም ነገር ከሌለ ዝም ማለት አለበት፡፡ ክፉ መናገር ራሳነ ያቆሽሻል፡፡ ክፉ መናገር መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል፡፡ ክፉ መናገር እግዚአብሄ ከእኛ ጋር እዝንዳይሆን ደርጋል፡፡ ክፉ መናገር ከህይወት ያጎድለናለናል፡፡

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡29-30

  1. ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤

በልቡ አንድን ነገር ይዞ ሌላን ነገር የሚናገር ሰው መልካም ቀኖችን ማየት አይችልም፡፡ በልቡ የሚፈልገው ነገር ሸፍኖ በተልኮል በማሳሳት ሌላ ነገር የሚናገር ሰው መልካምን ቀኖች ማየት አይችልም፡፡ ግልፅ ያልሆነ ሰውና ክፋትን ሽፍኖ እውነተኛ መስሎ ሰዎችን የሚያሳስት ሰው መልካም ቀኖችን ማየት አይችልም፡፡

ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡2

እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡1

  1. ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥

ሰው ከእግዚአብሄር የሚመጡትን መልካሞቹን ቀኖች ተስፋ ካደረገ ከከፉ ፈቀቅ ማለይት አለበት፡፡ በክፋት እየዋኘ የእግዚአብሄርን መልካምነት መጠበቅ ዘበት ነው፡፡ ሰው ክፋትን እያሰበ ፣ ክፋትን እየተናገረና ክፋትን እያደረገ እግዚአብሄር ከእኔ ጋር ነው ማለት አይችልም፡፡ ሰው ከክፋት ጋር አለመተባበር አለበት፡፡ መልካሞችን ቀኖች ማየት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ክፋትን መጸየፍ አለበት፡፡

ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡9

  1. መልካምንም ያድርግ

ለህይወቱ ዋጋ ያለውና መልካሙን ቀኖች ማየት የፈለገ ሰው የየትኛውም ችግር አካል መሆን አይፈልግም፡፡ መልካም ቀኖችን ማየት ሚፈልግ ሰው የመፍትሄ አካል መሆን ይፈልጋል፡፡ መልካሞችን ቀኖች ማየት የሚፈልግ ሰው ስለሰው መልካም ያስባል መልካመ ይናገራል መልካምን ያደርጋል፡፡ መልካሞችን ቀኖች ማየት የሚፈክልግ ሰው ከመልካምነት ውጭ ክፉ በማድረግ በእግዚአብሄ አምሳል የተፈጠረን ሰው በመራገም ከእግዚአብሄር ጋር አይጣላም፡፡

በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤  የያዕቆብ መልእክት 3፡9

ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡16-17

  1. ሰላምን ይሻ ይከተለውም

መልካችን ቀኖች ማየት የሚፈለግ ሰው ረብሻን አይመርጥም ሰላምንም ግን ይከተላል፡፡ ሰው ሰላምን የማይመርጠውና ረብሻን የሚመርጠው በህይወቱ ሰላም ሳይኖረው ሲቀር ነው፡፡ መልካሞቹን ቀኖች ማየት የሚፈልግ ሰው በጥላቻና በረብሻ ውስጥ የሚመጣውን መቆሳሰል አይፈልገውም፡፡ ለህይወቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው ግን ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ለማድረግ ይጥራል፡፡

ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡18

በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡3

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ባርኩ #ክፉ #መልካም #በረከት #ልትወርሱ #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንደበት #ከንፈር #ስድብ

ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ

tongue.jpgእኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ማቴዎስ 12፡36

ዝም ብሎ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ሰው የንግግርን ሃይል በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡

ንግግር ታላቅ ሃይል ያለው ነገር ነው፡፡ የንግግር ቃል ያፈርሳልም ይገነባልም፡፡

ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ። ምሳሌ 18፡21

የንግግር ቃል ይባርካል ይረግማል፡፡

በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። ያዕቆብ 3፡9-10

ሰው በንግግር ሰውን ያንፃል ፣ ይገነባል ፣ ያሻግራልና ይፈውሳል፡፡ መልካም ቃል ይፈውሳል ጤንነትን ይሰጣል፡፡

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ኤፌሶን 4፡29

ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል። ምሳሌ 15፡4

ሰው ደግሞ በንግግር ሰውን ያፈርሳል ያጠፋል የፍጥረትን ሩጫ ያቃጥላል፡፡

እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፤ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፤ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው። ምሳሌ 12፡17-18

አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። ያእቆብ 3፡6

እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ማቴዎስ 12፡36

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #አንደበት #ምላስ #አፍ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፀጋ #እሳት #መልካምቀኖች #ህይወት #በረከት #መርገም #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ስለ አንደበትዎ ማወቅ የሚገባዎ አምስት ነገሮች

tongue taming.jpgሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን። እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ። እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል። አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው። በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም። ያዕቆብ 3፡2-10

  1. አንደበት ከፍተኛ ተፅእኖ ያደርጋል፡፡

አንደበት በሚሰማው ላይ ከፍተኛ አዎንታዊም አሉታዊም ተፅእኖ አለው፡፡ አንደበት ያለው እምቅ ጉልበት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ናት፤ ምሳሌ 10፡11

  1. አንደበት ሊናቅ አይገባውም፡፡

አንደበት ትንሽ ክፍል ቢመስልም ነገር ግን ተፅእኖው እጅግ በጣም ታላቅ ነው፡፡ ትልቅን መርከብ አንድ ትንሽ መሪ እንደሚመራው ሁሉ የሰውን ህይወት የሚመራው አንድ ትንሽ የሰውነት ክፍል አንደበት ነው፡፡ አንድ ትንሽ እሳት ትልቅ ጫካን እንደምታቃጥል ሁሉ አንደበት ትንሽ ሆና ታላላቅ ነገሮችን ታበላሻለች፡፡

አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ። መዝሙር 141፡3

  1. አንደበት የስጋ ዋና ነው፡፡

የስጋ ምኞት ሃጢያተኛ ባህሪ በአንደበት ይገለፃል፡፡ የሰው የስጋ ምኞት ሁኔታ የሚታየው በአንደበት ነው፡፡ የስጋ ምኞት ዋናው አንደበት ነው፡፡ ስጋዊ ባህሪያችን በመናገር ይረካል፡፡ ስጋ የሚመካው በመናገር በመናገር በመናገር ነው፡፡  ስጋ ንግግርን ሲከለከል ይጮሃል፡፡

እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና። ማቴዎስ 12፡34

  1. አንደበትን ለመግራት ቀላል አይደለም፡፡

አንደበት ለመግራት ጥረትን ይጠይቃል፡፡ አንደበት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ አንደበት ከፍተኛ ክትትል ይጠይቃል፡፡ እያንዳንዱ የምንናገረው ነገር ከመነገሩ በፊት በራሳችን መቀመስና መመርመር አለበት፡፡ በንግግር ዘና የምንልበት ነገር የለም፡፡ አንደበት አጥብቆ የሚጠብቀው ሰው ይፈልጋል፡፡

የሰው አንደበቱን የመጠበቅ አቅሙ ውስን ስለሆነ እራሱ ቀምሶ አጣጥሞ የሚያሳልፈው ጥቂት ቃል ካልሆነ በስተቀር ብዙ ቃል መናገር የለበትም፡፡

ምላስ መብልን እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃልን የሚለይ አይደለምን? ኢዮብ 12፡11

በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። ምሳሌ 10፡19

  1. አንደበት ጥፋቱ ታላቅ ነው፡፡

አንደበት ሰውን ያነሳል ፡፡ አንደበት ሰውን ይጥላል፡፡ በአንደበት በአለም ችግር ላይ ችግር ልንጨምር እንችላለን፡፡ በአንደበት ለአለም ችግር መፍትሄ አንሰጣለን፡፡ በቃለዓችን ለሰዎች የእግዚአብሄርን ፀጋ እናካፍላለን፡፡ በእንደበታችን ሰዎችን እናፈርሳለን እናሰናክላለን፡፡

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ኤፌሶን 4፡29

ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ 1ኛ የጴጥሮስ  3፡10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #አንደበት #ምላስ #አፍ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፀጋ #እሳት #መልካምቀኖች #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: