Category Archives: God wonderful amazing

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም

your willአቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው። ኤርሚያስ 10፡6

እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። 1ኛ ዜና 16፡25-27

እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ። ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ፤ እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና። መዝሙር 96፡2-4

አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ። ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው። 1ኛ ዜና 29፡11-12

እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። መዝሙር 47፡2

ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡15-16

አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን? እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ አለቆችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፥ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፥ እነርሱም ደረቁ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው። ኢሳያስ 40፡21-24

አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም። ኤርሚያስ 32፡17

እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ። ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም። ኢሳያስ 40፡25-26

ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? ኢሳያስ 40፡12

አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው። ኤርሚስ 10፡6

እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። ሊባኖስ ለማንደጃ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፥ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። ኢሳያስ 40፡15-17

አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንዳንተ ያለ ማን ነው? ዘፀአት 15፡11

ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33፡26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #ታላቅ #ድንቅ #ልዩ #ግሩም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ

3d-hd-wallpaper-0453-1024x768.jpgእኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከአርሱ ጋር ህብረት እንዲያደርግ ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ብቻ እንዲረካ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ ምንም እርካታ የሌለው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችል ክፍተት በህይወቱ ያለው፡፡

መዝሙረኛው የሚለው ይህንን ነው፡፡

ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል ብለው ወደ ብዙ ነገሮች ይሮጣሉ ብዙ ነገሮችን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል የሚሉትን ብዙ ነገሮችን ይሰበስባሉ ነገር ግን ሲያገኙዋቸው አይረኩም፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ለመርካት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

ለእኔ ግን ይላል መዝሙረኛው ሰዎች የሚፈልጉት ነገር ሁሉ አያረካኝም፡፡ እኔን የሚያረካኝ ግን ይህ ሁሉ ነገር አይደለም ይላል፡፡ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው አንተን እግዚአብሄርን ነው እያለው ነው መዝሙረኛው፡፡

እኔ ግን ትክክለኛነቴን ላለመተው ዋጋ እከፍላለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን የሚያሳዝን ነገር ላለማድረግ እጠነቀቃለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን አድረጋለሁ፡፡  እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን እንቃለሁ፡፡ እኔ ግን በእውነት ወደአንተ እቀርባለሁ፡፡

እኔን የሚያረካኝ ክብርህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ መገኘትህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ የአንተ አብሮነት ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተ ነህ፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተን መፈለግ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ ክብርህን ማየት ነው፡፡

እኔን ሊያጠግበኝ የሚችል ከአንተ ውጭ ከሰማይ በታች ምንም ነገር የለም፡፡ ሰዎች ለመርካት የሚፈልጉበት ነገር ሁሉ እኔን አያረካኝም፡፡ ሰዎች ለመጥገብ የሚጋደሉለት ነገር ሁሉ አያጠግበኝም፡፡

እኔን የምረካው ክብርህን ሳይ ብቻ ነው፡፡

እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ክብር #መልክ #አምሳል #ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #መፈለግ #መጠማት #መራብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው

DsuOreL.jpgበምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ። እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝሙር 66፡ 1-3

አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው። መዝሙር 92፡4-5

አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ። መዝሙር 40፡5

የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። ሮሜ 11፡33

በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ። ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፤ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው። መዝሙር 66፡4-5

አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች። መዝሙር 104፡24

አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና። መዝሙር 86፡10

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #ታላቅ #ድንቅ #ልዩ #ግሩም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

%d bloggers like this: