Category Archives: fear

አሸባሪው ማነው

conscious.jpg

ሰዎችን ተጠቅሞ የሚያሸብረው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የተፈረደበት ተስፋ የሌለው ጠላት ነው፡፡

ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 16፡11

ሰይጣን ፍቅርን አያውቅም፡፡ ሰይጣን ምህረት አይገባውም፡፡ ሰይጣን በፍቅርና በሰላም ምንም ነገር ማድረግ ስላይችል የሚችለው አንድ ነገር ውሸትን በመዋሸት ፍርሃትን በሰዎች ውስጥ በመጨመር ከመንገዳቸው ማስቆም ነው፡፡  ሰይጣን ውሸትን በማዛመት ማስፈራራት ስራው ነው፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44

ሰይጣን የሰዎችን ጉስቁልና እንጂ እድገት አይፈልግም፡፡ ሰይጣን የሰዎችን መቆም እንጂ መራመድ እና እድገት አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ራስ ወዳድ ምኞታቸውን ብቻ የሚከተሉ ፣ ለሌላው ምንም ፍቅር እና አክብሮት የሌላቸው ሰዎችን ለማስፈራሪያነት  እንደመሳሪያ ይጠቀማል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረ ፈቃድ ሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሲከፈት የሚከፈት ሲዘጋ የሚዘጋ የራሱ ፈቃድ የሌለው ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን አድርጎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በሙሉ ፈቃድ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚገዛው በፍቅር እና በፈቃደኝት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች እንዲገዙለት የሚፈልገው በፍቅርና በፈቃደኝነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው ሰውን ማሸነፍ የሚፈልገው በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡1

በፍርሃት ሊገዛ የሚፈልውገው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን የሚሰራው በጥላቻ ነው፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካላስገባ በስተቀር ሰይጣን መስራት አይችልም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካስገባ ደግሞ የማይሰራው ክፋት የለም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻ ካስገባ ሰውን ያስገድላል፡፡

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14-15

ሰይጣን ደግሞ ራስ ወዳድ ሰዎችን ለማረድ ለማጥፋትና ለመስረቅ አላማው ይጠቀማል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44

የአሸባሪነት አላማ ደግሞ ሰውን ከጉዞው ማስቆም ነው፡፡ ሰውን ዝም ካላሰኘና ከአላማው ካላስቆመው ፍርሃት አላማው ይከሽፋል፡፡ ሰውን ከመንገዱ ከላስቆመው አሸባሪነት ግቡን አይመታም፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ወደ ዕብራውያን 2፡14-15

ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ መታወስ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ የፍርሃት ዜናውን ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ የሰይጣን አላማ በፍርሃት ሽባ ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣነ አላማ በውስጣችን ያለውን እምቅ ጉልበት እንዳንጠቀም አሳስሮ ማስቀመጥ ነው፡፡

ሰይጣን አያስቆመንም፡፡ በፍቅር ፍርሃትን አሽቀንጥረን እንጥላለን፡፡ በፍቅር እንሄዳለን፡፡ በፍቅር እንወጣለን እንገባለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍትህ #ፍርድ #ዲያቢሎስ #ሰይጣን #ዲሞክራሲ #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #ፍርሃት #የውሸት አባት #ኢትዮጲያ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #ጥላቻ #ፍቅር #ፈቃድ #መሪ

Survival of the fittest

servival of the fittest.jpgWhen I was in high school I was taught a Biology theory called the survival of the fittest. Here is the Wikipedia definition of Survival of the fittest copied for you.

“Survival of the fittest” is a phrase that originated from Darwinian evolutionary theory as a way of describing the mechanism of natural selection. The biological concept of fitness is defined as reproductive success. In Darwinian terms the phrase is best understood as “Survival of the form that will leave the most copies of itself in successive generations.”

In nature if you adapt the environment you can live longer, you can produce more offspring and you will dominate the earth and can continue by overcoming danger or hardship.

The purpose of this article isn’t to argue whether or not the theory is true or not.  I know God created the heavens and the earth and I know that those who give due respect to the creator survive.

But when I always think about the fear of the Lord the survival of the fittest theory comes to my mind.

Furthermore, just as they did not think it worthwhile to retain the knowledge of God, so God gave them over to a depraved mind, so that they do what ought not to be done. Romans 1:28

For although they knew God, they neither glorified him as God nor gave thanks to him, but their thinking became futile and their foolish hearts were darkened. Romans 1:21

God created the heavens and the earth. To survive on earth you need at least a wisdom. To survive on earth you need the wisdom of the fear of God.

The fear of God is the beginning of wisdom. If you don’t have this minimum requirement, you don’t survive on earth. You may live but not really live. You may exist but not be living.

The fear of the Lord is the beginning of wisdom, and knowledge of the Holy One is understanding. Proverbs 9:10

We can’t survive on earth and in life not fearing the Lord and not giving due respect for the God who has created us all and sustains the earth.

The fear of the LORD adds length to life, but the years of the wicked are cut short. Proverbs 10:27

Those who fear the Lord will survive having the goodness of God by their side.

How abundant are the good things that you have stored up for those who fear you, that you bestow in the sight of all, on those who take refuge in you. Psalm 31:19

Those who fear God survive evil by being delivered By God’s angels.

The angel of the Lord encamps around those who fear him, and he delivers them. Psalm 34:7

Those who fear the Lord are highly blessed and their generation survives by becoming blessed as well.

Praise the LORD. Blessed is the man who fears the LORD, who finds great delight in his commands. His children will be mighty in the land; the generation of the upright will be blessed psalms 112:2

According to the Bible, the best way of survival mechanism isn’t getting rich or being famous or being mighty but to fear the Lord.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#time #wisdom #fearofgod #might #money #fame #vapor #redeemtime #tomorrow #today #salvation #church #testimony #soulwinning #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

እምነትና ጥርጥር

fear vs faith 22.jpgኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

ለእግዚአብሄር አንድን ነገር ማድረግ ከፈለግን በእምነት መሆን አለበት፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንገናኘው በእምነት ነው፡፡ ከእግዚአብሄር የምንቀበለው በእምነት ነው፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ጥርጥር ደግሞ እግዚአብሄርን አለማመን ነው፡፡ ጥርጥር የእምነት ተቃራኒ ነው፡፡ ጥርጥር የእምነት ጠላት ነው፡፡ ጥርጥር እጃችንን ዘርግተን አንድን ነገር ከእግዚአብሄር በእምነት እንዳንቀበል እጃችንን እንድንሰበስብ ይፈታተነናል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲያምን የእምነት ጠላት የሆነውን ጥርጥርን መዋጋት አለበት፡፡

እምነት የሚመጣው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ሲያምን ያመነው ነገር እስኪሆን ደርስ በእምነቱ ፀንቶ መጠበቅ አለበት፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

የሚታየው ነገር ሁሉ የሚመጣው ከማይታየው አለም ነው፡፡ ሰው በማይታየው አለም ውስጥ በእምነት ያየው ነገር ወደሚታየው ግኡዙ አለም እስኪመጣ መታገስ አለበት፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡1፣3

ሰው አንድን ነገር ሲያምን ያመነው ነገር ወደ ገሃዱ አለም አሰኪገለጥ ድረስ በጥርጥር ይፈተናል፡፡ ሰው ያመነው ነገር ትክክል እንዳይደለና እንዲተወው ጥርጥር ይፈትነዋል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የሚከፍለው በእምነቱ ብቻ ነው፡፡ የሚጠራጠር ሰው ከእግዚአብሄር አይቀበለም፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

መጠራጠር የለብንም ማለት ግን የጥርጥር ሃሳብ ወደ አእመሮዋችን አይመጣም ማለት አይደለም፡፡ ሰው ያመነው ነገር እንደማይሆን ሰይጣን የጥርጥርን ሃሳብ ይልካል፡፡ ሰው የጥርጥርን ሃሳብ ከተቃወመው በእምነቱ ከእግዚአብሄር ብድራትን ይቀበላል፡፡ ሰው ግን የጥርጥርን ሃሳብ ከተቀበለው እምነቱ ያለፍሬ ይቀራል፡፡

ሰው መጀመሪያ ማመኑ ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰው ሲያምን ጥርጥርን በሚገባ መቃወም አለበት፡፡

ጴጥሮስ የጌታን ቃል እምኖ በውሃ ላይ መራመድ ጀምሮ ነበር ፡፡ ነገር ግን ጥርጥር በውሃ ላይ መራመድ የጀመረውን ጴጥሮስን አሰመጠው፡፡ ጴጥሮስ አይኑን ና ከሚለው ከኢየሱስ ቃል ላይ እንስቶ ወደወጀቡ ላይ ሲያደርግ መስመጥ ጀመረ፡፡

እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ማቴዎስ 14፡29-30

ጥርጥርን የምንዋጋው የእግዚአብሄርን ቃል በቀጣይነት በመስማት በማሰላሰልና በመናገር ነው፡፡ ጥርጥርን የምንዋጋው ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ የሆነን ነገር ባለመስማትና ባለመከተል ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነትና ፍርሃት

fear vs faith 22.jpgከእግዚአብሄር ጋር ላለን የሰመረ ግንኙነት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

አንዱ የእምነት ጠላት ደግሞ ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው ከእምነት ጉዞ ልናቋርጥ እንችላለን፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ሳናከናውን እንቀራለን፡፡

እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እንድንሰማና እንድንከተል ያደርጋል፡፡ ፍርሃት ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳንሰማና እንዳንከተል ያደርጋል፡፡

እምነት አለን ማለት ግን ከፍርሃት ስሜት ነፃ እንሆናለን ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት የማይኖረን ወደሰማይ ስንሄድ ብቻ ነው፡፡ በምድር ላይ ይብዛም ይነስም የፍርሃት ስሜት አለ፡፡

የፍርሃት ስሜት አለን ማለት ግን እምነት የለንም ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም የማመን እድሉ አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም እምነት አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት  እምነታችንን ፍርሃት እየተፈታተነው ነው ማለት ነው፡፡ ፍርሃት የሚመጣው የሚያምንን ሰው ለማስቆም ነው፡፡

ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ በከንቱ ይደክማል፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ ስኬታማ አይደለም፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ አይከናወንለትም፡፡

የፍርሃትን ስሜት ካልተከተልነው በእምነታችን አሸናፊ እንሆናለን፡፡ ደፋር የሚባለው ሰው ምንም የፍርሃት ስሜት የማይሰማው ሰው አይደለም፡፡ ደፋር የሚባለው እንዲያውም በጣም የሚያስፈራ ነገር ውስጥ የሚያልፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር የፍርሃት ስሜት እንዳይገዛው የሚያደርግ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው በፍርሃት ስሜት የማይሸነፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር ስው የፍርሃት ስሜት የማይወሰደ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው ፍርሃትን ሰምቶ ከእምነት ጊዞ የማይቆም ነው፡፡

እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡35

ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡36

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ፍርሃት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት

ኤፕሪል ዘ ፉል

fool.jpgበየአመቱ ኤፕሪል 1 ቀን የማሞኛ ቀን ተብሎ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰውን ዋሽቶ ማታለል እንደመዝናኛ ይቆጠራል፡፡ አንዳንድ ሰው ሰውብ ማስደንገጥ ደስ የሚለው ሰው አለ፡፡ እኔ በበኩሌ ሰውን ማስደንገጥ በፍፁም አልወድም፡፡

ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር እንደ ዕብድ ሰው፥ ባልንጀራውን የሚያታልል፦ በጨዋታ አደረግሁት የሚል ሰውም እንዲሁ ነው። ምሳሌ 26፡18-19

ሰው ሰውን ሊያታልለው ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰው ግን ራሱን ያታልላል፡፡ በጣም በአስፈላጊ እና ወሳኝ ነገር ላይ ራሱን የሚያታልል ሰው እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። መዝሙር 14፡1

The fool says in his heart, “There is no God.” They are corrupt, their deeds are vile; there is no one who does. Psalm 14:1

የሚገርመው ነገር ሰነፍ በልቡ ነው እግዚአብሄር የለም የሚለው፡፡ እግዚአብሄር የለም ማለቱ የሚታወቀው በድርጊቱ ብቻ ነው፡፡ የሚኖረው ኑሮ ሁሉ እግዚአብሄር እንደሌለ ነው የሚያሳየው፡፡ እግዚአብሄር የለም ብሎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ እንደማይፈርድ አድርጎ ያስባል፡፡  እግዚአብሄር እንደሌለ እንደማይሰራ አድርጎ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል አድርጎ ይመላለሳል፡፡

ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። መዝሙር 53፡1

እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ተጠያቂነትን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ራሱን መግዛት አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ለማንም ተጠሪ መሆን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው እንደልቡ መኖር ነው የሚፈልገው፡፡

ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ እግዚአብሄርን በየእለቱ መፈለግ አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግና መከተል አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄር አለ ብሎ ካመነ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ መፍራት አለበት፡፡  ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ ለእግዚአብሄር ተጠያቂነት አለበት፡፡

ሰነፍ ወይም ሞኝ ለስንፍናው ማሳበቢያ የሚያገኘው እግዚአብሄር የለም በማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር የለም በማለቱ እግዚአብሄርን ከመፈለግ ፣ ፈቃዱን ከማድረግና ለእግዚአብሄር ካለ የህይወት ሃላፊነቶች ሁሉ የዳነ ይመስለዋል፡፡ በዚህም ራሱን ያታልላል፡፡

ሰው ጥበበኝነቱና ትጋቱ የሚታወቀው ለእግዚአብሄር መኖር እውቅና በመስጠቱ ብቻ ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ምሳሌ 1፡7

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #ሞኝ #ሰነፍ #በልቡ #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም

fearofdeath.jpgእግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡7

እግዚአብሄር የሰጠንን ማወቅ እንድንጠብቀው እንድንንከባከበው ያደርገናል፡፡ እግዚአብሄር ያልሰጠንን ማወቅ ደግሞ እንድንቃወመውና እንዳናስተናግደው ያደርገናል፡፡

በህይወታችን በምንም አጋጣሚ ማስተናገድ የሌለብን ነገር ፍርሃትን ነው፡፡ ፍርሃት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ ፍርሃት ከሰይጣን ነው፡፡ እግዚአብሄር የፍርሃትን መንፈስ አልሰጠንም፡፡

የፍርሃት አላማ ደግሞ እግዚአብሄር ከሰጠን ራእይ ማሰናከልና እና ጌታን ከመከተል ማስቆም ነው፡፡

እግዚአብሄር የሃይል መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

ፍርሃት እንደማንችል ፣ እንደማንበቃ ፣ እንደማይሳካልንና እንደማይከናወንልን ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን መንፈስ ግን የሃይል መንፈስ ነው፡፡ በምድር ላይ የምንኖረው በእግዚአብሄር በሚያስችል ሃይል ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠንን ማንኛውንም ሃላፊነት የምንፈፅምበት ሃይል አለን፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመፈፅም ከሚያስፈልገን አንድም ፀጋ አይጎድልብንም፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

እግዚአብሄር የፍቅር መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

የሰይጣን አለማ በፍርሃት ራስ ወዳድ እና ስግብግብ እንድንሆን ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣነ አላ በፍርሃት ማንንም እንዳንወድ ለማንም እንዳናካፍልና ለራሳችን ብቻ አግበስብሰን እንድንኖር ነው፡፡ የሰይጣነ የፍርሃት አላማው በስስት በማንም ላይ ተፅኖ ሳናደርግ እንድናልፍ ነው፡፡ ሰው ግን የተፈጠረው ሌላውን እንዲወድና እንዲያገለግል ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን መንፈስ ከራስ አልፎ ሌላውን የሚደርስ መንፈስ እንጂ በምስኪን እኔ አስተሳሰብ ለራሱ ብቻ ኖሮ የሚያልፍ አይደለም፡፡

እግዚአብሄር የራስን የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡

እግዚአብሄር ራሳችንን እንድንገዛ መንፈሱን ሰጥቶናል፡፡ ራሳችንን እንገዛ ይሆን ብለን በፍርሃት አንታሰርም፡፡ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሄር ፀጋ በእኛ ላይ በሃይል እንደሚሰራ እናምናለን፡፡ እግዚአብሄር ያቀደልንን የቅድስና ህይወት መኖር የሚያስችለን ሁሉም ነገር እንደተሰጠን እናምናል፡፡ በሆነው ባልሆነው በመፈራት በቅድስና ተስፋ እንቆርጥም፡፡ አንፈራም እግዚአብሄር የሰጠን ራስን የመግዛት መንፈስን እንጂ የፍርሃትን መንፈስ አይደለም፡፡

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡11-13

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ፍቅር #ፍርሃት #ሃይል #ራስንመግዛት #አላማ #መዳን #ነፃነት #ቅድስና #ሰላም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

12ቱ እግዚአብሄርን የመፍራት ጥቅሞች

fear of God.pngበምድር ላይ ተቋቁሞ ለማለፍ እንዲሁም ከማንኛውንም ክፋት ለመዳን እግዚአብሄርን መፍራት በጣም ወሳኝ ነው፡፡

እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ደግሞ እግዚአብሄርን እንደ እግዚአብሄርነቱ መጠን ማክበር እና መስማት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ለእግዚአብሄር ፈጣሪነትና አምላክነት እውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር መፍራት ማለት እኛ የእግዚአብሄር ፍጥረት እንደሆንን ለራሱ ለክብሩም እንደፈጠረን መረዳት ማለት ነው፡፡

እግዚአብሄርን አለመፍራት ማለት ደግሞ በሃሳባችን ፣ በንግግራችንና በድርጊታችን ለእርሱ ፈቃድ ቦታ አለመስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን አለመፍራት ማለት በህይወታችን ለእርሱ ሀሳብ ቅድሚያ አለመስጠት ማለት ነው፡፡  እግዚአብሄርን አለመፍራት ማለት ፍላጎቱን ከቁጥር አለማስገባት ማለት ነው፡፡

ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ሮሜ 1፡20-21

ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ስለተፈጠረ እግዚአብሄርን እንደ እግዚአብሄርነቱ ካላከበረው ህይወቱ ይወሳሰባል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካልፈራ ምንም ነገሩ ሊቃና አይችልም፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ከፈራ ደግሞ በህይወቱ ሁሉም ነገሩ መስራትና መሳካት ይችላል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ከፈራ ሌላ ሁሉ ነገሩ ትክክለኛ ቦታውን ይይዛል፡፡

 1. እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ጥበበኛ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ለህይወቱ ያውቅበታል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ከሰማይና ከምድር ፈጣሪ ጋር እንዴት እንደሚኖር የሚያውቅ አስተዋይ ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ምሳሌ 1፡7

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል። መዝሙር 111፡10

 1. እግዚአብሄርን የምትፈራ ሴት የተመሰገነች ነች፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው የሚደነቅ ሰው ነው፡፡

ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ምሳሌ 31፡30

 1. እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው መልካም ከሚባል ምንም ነገር አይጎድልም፡፡

የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት። መዝሙር 34፡9

 1. እግዚአብሄር የሚፈሩትን ፀሎታቸውን ይሰማል ምኞታቸውንም ያደርጋል፡፡

ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም። መዝሙር 145፡19

 1. የሚፈሩት ሰዎች ይበልጥ ረጅም እድሜ እንዲኖሩ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፤ የኀጥኣን ዕድሜ ግን ታጥራለች። ምሳሌ 10፡27

 1. እግዚአብሄርን መፍራት ገንዘብና ንብረት ከማያስጥለንን አደጋ ያስጥለናል፡፡

 

ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው። ምሳሌ 14፥27

 

 1. የሚፈሩ ሰዎች እግዚአብሄርን ያስደስቱታል፡፡

 

እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል። መዝሙር 147፡11

 

 1. እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሰዎች እግዚአብሄር በመላክቱ ይጠብቃቸዋል ያድናቸውማል፡፡

 

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። መዝሙር 34፡7

 

 1. እግዚአብሄር በሚፈሩትን ሰዎች ፋንታ ሃይሉን ይገልፃል፡፡ ራሱን እና ቃልኪዳኑን ይገልጥላቸዋል፡፡

እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። መዝሙር 25፡14

 1. እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ከራሱ አልፎ ለትውልዱ ጠንካራ መታመኛን ያዘጋጃል፡፡

እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል። ምሳሌ 14፡26

 1. ልጅ ለአባቱ እንደሚራራ እግዚአብሄር ለሚፈሩት ይራራል፡፡

አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ መዝሙር 103፡13

 1. እግዚአብሄርን ፈርቶ የሚስት ሰው የለም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በመፍራቱ ወደ ህይወት ይመራል፡፡

እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም። ምሳሌ 19፥23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የጥበብ መጀመሪያ ምንጭ

Siblings-in-the-countryside-in-the-Enderta-area-Tigray-Ethiopia.jpgሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ የሰው መረዳት ዝቅተኛው መመዘኛ እግዚአብሄርን መፍራቱ ነው፡፡ የሰው መረዳት የሚጀምረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደሚኖር በማወቁ ነው፡፡ የሰው እውቀቱ የሚለካው በትንሹ ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና መስጠቱ በማወቁ ነው፡፡ የሰው እውቀቱ የሚታየው ከእግዚአብሄር ከፈጣሪው ጋር ያለውን ግንኙነት በመረዳቱ ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ምሳሌ 1፡7

ሰው እጅግ የተዋጣለት የጠፈር ተመራማሪ ቢሆን ከእግዚአብሄር ጋር ግን እንዴት እንደሚኖር ካላወቀ ምንም አያውቅም፡፡ ሰው በሌላ በብዙ ነገር የተሳካለት አዋቂ ሆኖ ለፈጠረው ለእግዚአብሄር እውቅና መስጠት ካላወቀ ሀ ሁ አልቆጠረም ማለት ነው፡፡ ሰው በሌላ ነገር የተካነ ሆኖ ለክብሩ ከፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር ስላለው ግንኙነት መረዳቱ ከሌለው ምንም አያውቅም ማለት ነው፡፡ ሰው ምንም ቢያውቅ ለእግዚአብሄር ፈጣሪነትና ባለቤትነት እውቅና ካለሰጠ የእውቀት መጀመሪያ ላይ አልደረሰም ማለት ነው፡፡

እግዚአብሄን መፍራት ግን ከድርጊት አይጀመርም፡፡ በድርጊታችን እግዚአብሄርን ለመፍራት መፍጨርጨር የለብንም፡፡ በድርጊታችን አግዚአብሄርን ለመፍራት የድርጊታችንን ምንጩን ማስተካከል ይኖርብናል፡፡ በንግግራችን እና በድርጊታችን እግዚአብሄርን ለመፍራት ንግግራችንና ድርጊታችን የሚመጣበትን ምንጩ አስተሳሰባችንን ማስተካከል ይኖርብናል፡፡

መጽፅሃፍ ቅዱስ የማንኛውም ድርጊት ምንጩ ሃሳብ እንደሆነ ያስተምረናል፡፡ እንዲያውም ሰው በልቡ እንደሚያስበው እንደዚሁ እንደሆነ መፅሃፍ ያስተምረናል፡፡ በአስተሳሰብ ህይወቱ እግዚአንብሄርን የሚፈራ ሰው በንግግሩ እግዚአብሄርን ይፈራል፡፡ በአስተሳሰቡ እግዚአብሄርን የሚፈራ በራሱ በድርጊቱ እግዚአብሄርን ይፈራል፡፡

በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ምሳሌ 23፡7

ስለዚህ ነው ኢየሱስ ፈሪሳዊያንን እናንተን የሚያረክሳችሁ ድርጊት ሳይሆን የልባችሁ ሃሳብ ነው እያለ የሚወቅሳቸው፡፡

ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ማቴዎስ 15፡18-19

ሰው እግዚአብሄርን በእውነት የሚፈራው በሃሳብ ደረጃ ነው፡፡ ሰው በሃሳብ ደረጃ እግዚአብሄርን ከፈራ ከመቀፅበት በንግግርም ሆነ በድርጊት እግዚአብሄርን የመፍራት ህይወት ይኖረዋል፡፡ ሰው ግን በአስተሳሰብ ህይወቱ እግዚአብሄርን ካልፈራና ስርአት አልባ ከሆነ በድርጊቱ እግዚአብሄን መፍራት አይችልም፡፡ ሰው ሰው አያየኝም ብሎ ክፉን ቢያስብ በንግግሩና በድርጊቱ ሰው ያየዋል፡፡

ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል፡፡ ሉቃስ 11፡39

ስለዚህ በአስተሳሰባችን እግዚአብሄርን በመፍራት እግዚአብሄርን የመፍራት ህይወት ይኑረን፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ምሳሌ 1፡7

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ በአስተሳሰቤ አንተን እፈራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ወደ አእምሮዬ የመጣውን ሃሳብ ሁሉ አላስብም፡፡ እግዚአብሄር ሆይ የማስበውን ማንኛውንም ሃሳብ አንተን በመፍራት አስባለሁ፡፡ እግዚአብሄ ሆይ እንደቃልህ ያልሆነን ሃሳብ ከአእምሮዬ አሽቀንጥሬ እጥላለሁ፡፡ አንደ ቃልህ ያልሆነውን ሃሳብ በአእምሮዬ አላስተናገድም፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በአስተሳሰብ ህይወቴ አንተን በመፍራት ወዳዘጋጀህልኝ በረከት ውስጥ እገባለሁ፡፡ ስላስተማርከኝ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም ፡፡ አሜን

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #አእምሮ #ልብ #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Terrorism – Old trick of the Devil

london.jpgThe purpose of the Devil is to instill fear, steal our confidence and to cripple us and to stop us from doing the right thing and to destroy our lives.

For the Spirit God gave us does not make us timid, but gives us power, love and self-discipline. 2 Timothy 1:7

The Devil’s only mission is to steal, to kill and destroy.

The thief comes only to steal and kill and destroy; I have come that they may have life, and have it to the full. John 10:10

The Devil doesn’t want to be forgotten. He wants to be heard of his lies. The devil wants the spotlight.

The Devil knows we are winning. Terrorism is the sign of His defeat. Frightening is his last card. If we are not taken by the threat, we continue to enforce his defeat further. If we fight hatred and continue treating others with dignity, he fails.

The Devil is a liar. He wants us to believe what isn’t true. He wants to tell us that there is no hope. He wants to convince us that evil is winning. He tries his best to convince us we are losing the battle.

You are of your father the devil, and the desires of your father you want to do. He was a murderer from the beginning, and does not stand in the truth, because there is no truth in him. When he speaks a lie, he speaks from his own resources, for he is a liar and the father of it. John 8:44

If the Devil frightens us from doing what is in our hearts, He wins the battle. If we take the necessary security measures and continue doing what we have been doing, He will continue to fall.

If He doesn’t succeed to make panic us, he fails. If we continue even with the feeling of fear, we win.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#God #Jesus #fear #hatred #knowledge #destroy #trustGod #steal #kill #church #Satan #TheDevil #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #londonattack #scriptures #abiywakumadinsa

%d bloggers like this: