Category Archives: Marriage

እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው

Wallpaper-Wedding-Download-For-Free-1WC40010088-1024x576.jpg

እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። የማቴዎስ ወንጌል 19፡4-6

ትዳርን የሰራው እግዚአብሄር ነው ፡፡

እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡18

ባልን ለባልነት ሚስትን ለሚስትነት የሰራቸው እግዚአብሄር ነው፡፡

አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡20-24

ትዳርን የሚቃወም የእግዚአብሄርን ስርአት ይቃወማል፡፡

ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡2

እግዚአብሄር ክቡር ያለውን ሳያከብር የሚሳካለት ሰው የለም፡፡

መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ወደ ዕብራውያን 13፡4

በእግዚአብሄር እንታመንና እግዚአብሄርን እንታዘዝ፡፡

እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። የማርቆስ ወንጌል። 10:9

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #አንድስጋ #እውነት #ያጣመረውን #አንድስጋ #አይለየው #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የንጉሱና የባለትዳርዋ ሴት ታሪክ

king.jpgበድሮ ዘመን ነው አሉ አንድ ንጉስ ነበረ፡፡ ይህ ንጉስ ከውበትዋ የተነሳ ወደ አንድ ባለትዳር ሴት ይሳባል፡፡ እናም እርሱዋን ማግባት እፈልጋለሁ ይላል፡፡ ሰዎች ግን ተው እንጂ ይህች ባለትዳር ሴት ነች እርሷንና ባልዋን ተዋቸው ብለው ይለምኑታል፡፡ እርሱ ግን አይ አይሆንም እኔ አርሷን ነው የማገባው ብሎ በውሳኔው ይፀናል፡፡

ውሳኔውን ልታስለውጥ እንዳልቻለች ያወቀችውና ባልዋንና ቤትዋን የምትወደው ይህች ባለትዳር ሴት እሺ አገባሃልሁ ብላ ትስማማለች፡፡ ነገር ግን የማገባህ አንድ ቅድመ ሁኔታ ከተሟላ ብቻ ነው ትላለች፡፡ ንጉሱም ምንድነው አንቺን የማገባበት ቅድመ ሁኔታ ደግሞ ብሎ ሲጠይቅ አይ እኔን ማግባት ካለብህ የሰርጉን ድግስ ሁሉ የምደግሰው እኔ ነኝ ብላ ሃሳቡዋን ትገልፅለታለች፡፡ በዚህ ከተስማማህ አገባሃለሁ ትለዋለች፡፡ እርሱ ግን እኔ ንጉስ ነኝ እኔ ነበርኩ መደገስ የነበረብኝ አንቺ ግን ካልሽ ይሁን ብሎ እርስዋ እንድትደግስ ይስማማል፡፡

የሰርጉ ቀን ደረሰ፡፡ ምግብ ሁሉ ተዘጋጅቶ በመሶብ በመሶብ ተሸፍኖ ተቀምጦአል፡፡ ንጉሱ ከምግቡ እንዲያነሳ ቅድሚያ ተሰጠው፡፡ ከዚያም የመጀመሪያው ምግብ ሲታይ ተልባ ነው፡፡ ንጉሱ ከተልባው ጥቂት አነሳና ወደሚቀጥለው መሶብ ሄዶ ሲከፍተው ሁለተኛው መሶብ ተልባ ነው፡፡ ሶስተኛው አራተኛው አምስተኛው መሶቦች ሁሉ ሲከፈቱ ተልባ ናቸው፡፡ እንዲያውም ሁሉም መሶቦች ሲከፈቱ ተልባ ሆነው ተገኙ ፡፡

ንጉሱ ተናደደ፡፡ ለምንድነው እንደዚህ ያደረግሽው ብሎ ሲጠይቃት ተመልከት ሴት ሁሉ አንድ ነው፡፡ ይህንን ትምህርት ላስተምርህ ስለፈልኩ ነው አለችው ይባላል፡፡

የሰው ምኞት አንዴ ቀዩዋን ፣ አንዴ ጠይምዋን ፣ አንዴ ቀጭንዋን ፣ አንዴ ወፍራምዋን ፣ አንዴ ረጅምዋን አንዴ ደግሞ አጭርዋን ሊፈልግ ይችላል፡፡

አስተማሪዬ እንዲህ ይላል፡፡ ሴት ሁሉ ግን አንድ ነው፡፡ ለመርካት አንድ ሴት በቂ ነው፡፡ አንድ ወንድ በአንድ ሴት መርካት ካልቻለ ችግሩ እርሱ ጋር ነው ማለት ነው፡፡ በአንድ ሴት መርካተ ካለቻለ ያልገባው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ በአንድ ሴት መርካት ካልቻለ ራሱን ትሁት እድርጎ መማር እንጂ በብዙ ሴቶች ለመርካት መሞከር ከንቱ ድካም ራስን ማባከን ነው፡፡ ምክንያቱም የሴቶች ሁሉ መሰረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፡፡ አንድን ሴት መያዝ ካልቻለ በአጠቃላይ ሴትን መያዝ አልቻለም ማለት ነው፡፡

በአንድ ሴት መርካት ያልተቻለ ሰው በብዙ ሴቶች እረካለሁ ዘበት ነው፡፡ በእንድ ሴት የመርካት እድሉ እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡ በብዙ ሴቶች ለመርካት መሞከር እድሉን እያጠበበው ነው የሚሄደው፡፡

ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤ . . . ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡4-6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #አንድ #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ

single.jpgነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡32-34

ብናገባም ባናገባም ልባችን ለጌታ ያለን ፍቅር እንዲከፋፋል እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ እኛ በዋጋ የተገዛን ነን የራሳችን አይደለንም፡፡ ስለዚህ በሁለንተናችን እግዚአብሄርን ማክበር አለብን፡፡

ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20

ክርስቶስ ለእኛ ሞቷል፡፡ ክርስቶስ የሞተልን ወደፊት ለራሳችን እንዳንኖር ነው፡፡ ክርስቶስ የሞተልን ለሞተልን ለእርሱ እንድንኖርለት ነው፡፡ ስለዚህ ለእኛ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ወደፊት ለራሳችን መኖር የለብንም፡፡

በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡15

ጌታ ቀናተኛ አምላክ ነው፡፡ አግብተንም ይሁን ሳናገባ ለጌታ የምንሰጠውን ስፍራ ለሚስታችን ወይም ለባላችን እንድንሰጠው ጌታ አይፈልግም፡፡

እንዲያውም ጌታን ሙሉ ለሙሉ ለመከተል ሚስታችንንና ባላችንን መጥላት ይኖርብናል፡፡ መጥላት ማለት ለጌታ የምንስጠው ፍቅር ለባላችን ወይም ለሚስታችን አለመስጠት ማለት ነው፡፡ ወይም ለባላችን ወይም ለሚስታችን ለጌታ ከምንሰጠው ፍቅር ያነሰ መስጠት ማለት ነው፡፡ የባል ወይም የሚስታችንን ፍቅር ከጌታ ፍቅር ካስበለጥነው ጌታን በሙላት መከተል ያቅተናል፡፡

ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡26

ጌታን አንደኛ ስንወደው ነው ባላችንን ወይም ሚስታችንን በሚገባ መውደድ የምንችለው፡፡ እግዚአብሄርንም አንደኛ ካልወደድነው ወይም ለእግዚአብሄር መስጠት ያለብንን ፍቅር ለባላችን ወይም ለሚስታችን ከሰጠን ነገር ሁሉ በህይወታችን ይመሰቃቀላል፡፡

ጌታ ለእርሱ ያለንን ፍቅር ለማንም ስጋ ለባሽ እንዳንሰጥ ወይም እንዳናካፍል ይፈልጋል፡፡ ለእርሱ ያለን ፍቅር የሚገባው እርሱና እርሱ ብቻ ነው፡፡

ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15

መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማቴዎስ 22፡36-38

ስለዚህም ያገቡ ካገቡት ሰው በላይ የሚያስደስቱት ጌታ እንዳለ አድርገው ይኑሩ፡፡

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ያገባ #ያላገባ #ድንግል #ያገቡ #ያላገቡ #ፍቅር #ሚስት #ባል #ልብ #ተከፍሎአል #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ባል ሚስቱን እንዲወዳት የምታበረታታበት መንገድ

obessive-thoughts-of-ex.jpg

ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።  ኤፌሶን 5፡22-25

ሰውን አንዳንዴ መውደድ  ይቀላል፡፡ ሰውን ሁልጊዜ መውደድ ግን ቀላል አይደለም፡፡ ሰውን በብርታቱ መውደድ ይቀላል፡፡ ሰውን በድካሙ መውደድ ግን እንደዚያ ቀላል አይደለም፡፡ ሰውን መውደድ መውደድ ሲያሰኘን መውደድ ቀላል ነው፡፡ ሰውን መውደድ ሳይሰማን መውደድ ግን ቀላል አይደለም፡፡

አንዳንድ ሴቶች የወንድ የመውደድ ሃላፊነት ከሴት የመገዛት ሃላፊነት ይቀላል ይላሉ፡፡ እውነት ነው ሰው መውደድ መውደድ ሲሰማው መውደድ ይቀለዋል፡፡ ነገር ግን ባል መውደድ ሲሰማው ሳይሆን የወደው ባል ሚስቱን የሚወዳት ከየትኛውም ምክኒያት ጋር ተያይዞ አይደለም፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ክርስቶስ እኛን ጠላቶች ሳለን ካለምክኒያት እንደወደደን ባል ሚስቱን ካለምክኒያት እንዲወዳት ያዛል፡፡ ክርስቶስ ካለምክኒያት እንደማይወደን ፍቅሩ በሁኔታዎች እንደማይለወጥና እኛን ለመውደድ ራሱን እንደሰጠ ባል ሚስቱን እንዲወድ የመፅሃፍ ቅዱስ ትእዛዝ ነው፡፡

ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፡፡ ኤፌሶን 5፡25-26

የወንድ የመውደድ ሃላፊነት የሚቀልበት ጊዜ አለው፡፡ ነገር ግን ባል ሚስቱን መውደድ ያለበት ሚስቱ ስትደክምና የራስዋን ሃላፊነትም ሳትወጣ ነው፡፡ ባል ሚስቱ ባለችበት በምንም ሁኔታ ውስጥ ሊወዳትና ከምንም ምክኒያት ጋር ባለተያያዘ መልኩ የባልነት የመውደድ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባዋል፡፡

ፍቅር የውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር የስሜት ጉዳይ አይደለም፡፡ ፍቅር የመረዳት እርምጃ ነው፡፡ ባል ሚስቱን መውደድ ራስን የመስጠት ጉዳይ ነው፡፡

ነገር ግን ይህን ካለ ምክኒያይት የመውደድ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሚስት የምታደረገው ማበረታቻ አለ፡፡ ሚስት ባሌ እንዴት ሊወደኝ ይገባል በማለት በባል ሃላፊነት በጭንቀት ጊዜ ከምታጠፋ እንዴት ልታዘዝለት ብላ ብታስብ ባልዋ ሁልጊዜ እንዲወዳት በተዘዋዋሪ መንገድ ማበረታታት ትችላለች፡፡ ባል በምንም ሁኔታ ውስጥ ሚስቱን መውደድ ይገባዋል፡፡ ሚስት ግን በመታዘዝና ባለመታዘዝ ባልዋ እንዲወዳት ማበረታታትም አለማበረታታትም ትችላለች፡፡ ወይም እርስዋን መውደዱን ደስ ብሎት እንዳያደርገው ልታከብድበት ትችላለች፡፡

ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ዕብራዊያን 13፡17

ሚስት ትዳሬ ከእኔ ምን ይፈልጋል በሚለው ሃላፊነት ለባልዋ በመታተዝ ላይ ካተኮረች ባልዋ እርስዋን ሁልጊዜ እንዲወዳት ጉልበት ትጨምርለታለች፡፡ ሚስት ግን ባል ሚስቱን ይወደዳት ውደደኝ ብላ ብትጨቃጨቅ እንደ ብሉይ ኪዳን ህግ ባልዋ የሚያውቅውን ነገር ትነግረዋለች እንጂ የባልነት የመውደድ ሃላፊነቱን እንዲፈፅም አትረዳውም፡፡ ወይም ባሌ እንደሚገባው አይወደኝም ብለሽ ብታሚ ባልሽ ይበልጥ እንዲወድሽ ለእርሱ ይበልጥ በመታዘዝ ያደረግሽው አስተዋፅኦ ስለሌለ ከባልሽ አልፈሽ ህጉን ታሚያለሽ እንጂ ባልሽ ህጉን እንዲፈፅም ያደረግሽው አስተዋፅኦ የለም፡፡

በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ያዕቆብ 4፡10-11

ሚስት ሁሌ መጠየቅ ያለባት እኔ ለትዳሬ ምን አድርጌያለሁ? ትዳሬ ከእኔ ምን ይፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ እንጂ የራስዋን የመታዘዝ ሃላፊነት ትታ ባሌ ስለሃላፊነቱ ምን እያደረገ ነው? በሚለው ጥያቄ ላይ ካተኮረችና ባተሌ ከሆነች የሚለወጥ ነገር አይኖረም፡፡

ሚስት ለባልዋ በሁሉ በታዘዘች መጠን ባልዋ በሁሉ እንዲወዳት ካለ ንግግር እና ካለቃል ታበረታታዋለች፡፡

እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡1-2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #መታዘዝ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሚስትህ በደስታ እንድትታዘዝህ የምትረዳበት መንገድ

aid754343-v4-728px-Get-Your-Wife-to-Love-You-Again-Step-1-Version-2.jpgለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ። ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ኤፌሶን 5፡21-24

ባል የቤተሰቡን ለመምራት አገልግሎት ተጠርቷል፡፡ ቤተሰቡን የመምራት ሃላፊነትና ሸክም የወደቀበት እንደመሆኑ መጠን ለባል የሚስት መታዘዝ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠውን የራስነትን ሚና ለመጫወትና ቤተሰቡን እግዚአብሄር ወዳየለት የክብር ቦታ ለመምራት የሚስት በነገር ሁሉ መታዘዝ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ባል እግዚአብሄር የሰጠውን የመሪነት ሚና ለመጫወት  ከሚስት እንደመታዘዝ የሚያስፈልገው ነገር የለም፡፡ የባል እርካታ የቤተሰብ መሪነትን ሃላፊነት መወጣት እንደመሆኑ መጠን እንደ ሚስት አለመታዘዝ ተስፋ የሚያስቆርጠው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር የሰጠኝን የመሪነት አገልግሎቴን ስፈፅም ሚስቴ እንዴት ነው የምትታዘዝልኝ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ወሳኝ ነው፡፡

በክርስትና ስለምትበላውና ስለምትጠጣው መጨነቅ ካልፈልግክ አስቀድመህ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ፈልግ ሌላ ሁሉ ይጨመርልሃል፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33

ክርስትና አገልግሎት ነው፡፡ ክርስትና መስጠት ነው፡፡ ክርስትና መዝራት ነው፡፡ ያገለገልከው ይንከባከብሃል፡፡ የሰጠኸው ይሰጥሃል፡፡ የዘራህበት ያበቅልልሃል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ሚስቴ እንዴት ነው የምትገዛልኝ ብሎ መጨነቅና መጨቅጨቅ ሚስትህ በደስታ እንድትታዘዝህ ትክክለኛው መንገድ አይደለም፡፡ ሚስትህ እንድትታዘዝህ ያንተ የራስህ የመውደድ ሃላፊነት ላይ ከማተኮር የተሻለ መንገድ የለም፡፡ እግዚአብሄር በህይወትህ በሰጠህ የመውደድ ሃላፊነት ላይ ስታተኩር እግረ መንገድህን ሚስትህ እንድትታዘዝህ እያመቻቸህላት ነው፡፡ ለቤተሰቡ በምታደርገው የመውደድ ሃላፊነትህ ላይ ተጠንቀቅ ሌላው ነገር ለራሱ ይጠነቀቃል፡፡ ትዳሬ ከእኔ ምን ይፈልጋል በሚለው ላይ ስታተኩር ሃላፊነትህን እንድትወጣ የሚያስችልህን የሚስትህን መታዘዝ ታተርፋለህ፡፡

ሚስት ትገዛ ተብሎ ተፅፏል የሚለው ጭቅጭቅ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን ህግ መረጃ ይሰጥ ይሆናል እንጂ ትእዛዙን ለመፈፀም የሚያስችል ጉልበት አይሆንም፡፡

ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡6

ለቤተሰብ አንድነት እና ጥንካሬ ለባል የሚስት የመታዘዝን አስፈላጊነት የምትክድ ሴት አትገኝም፡፡ ባልን መታዘዝ ትክክል እንደሆነ ባላቸውን በሚታዘዙ ሰዎች የሚቀኑ ሴቶች ህያው ምስክር ናቸው፡፡ ባልን መታዘዝ የእግዚአብሄርን መታዘዝ በመሆኑ ባልዋን በመታዘዝ ጌታን ማስደሰት የማትፈልግ ሚስት አትገኝም፡፡ ባልን መታዘዝ እግዚአብሄር ለቤተሰብ ጥቅም ያስቀመጠውን ስልጣንን እንደመታዘዝ አስፈላጊ እንደሆነ የማትረዳ ሚስት አትገኝም፡፡

ሰውን መታዘዝ አንዳንዴ ሊቀል ይችላል፡፡ ሰውም ሁልጊዜ መታዘዝ ግን ቀላል አይደለም፡፡

ይህን ቀላል ያልሆነውን መታዘዝ ሚስትህ እንድታደርገው አንተም እንደባል የምታደርገው አስተዋፅኦ አለ፡፡ ትዳር የህብረት ስራ ነው፡፡ ሚስትህ ደስ ብሎዋት እንድትታዘዝ የምታግዛት አንተ ነህ፡፡ የሚስት መታዘዝ የሚስት ብቻ ሃላፊነት ቢሆንም ሚስትህ ደስ ብሎዋት እንድትታዘዝ አንተም የምታበረክተው አስተዋፅኦ እንዳለ አለመዘንጋት ይገባል፡፡ ያም ሆነ ይህ ሚስት መታዘዝ ቢኖርባትም መታዘዝዋን ለማቅለል ባል የሚወስደው ወሳኝ እርምጃ አለ፡፡

ሚስትህን ስትወዳት ሚስትህ እንድትታዘዝህ በተዘዋዋሪ እየጠየቅካት ነው፡፡ ሚስትህን ስትወድ ሚስትህ እንድትታዘዝህ እየረዳሃት ነው፡፡ ሚስትህ ስትወዳት እንድትታዘዝህ ሸክሟን እያገዝካት ነው፡፡ ሚስትህን ስትወድ እንድትታዘዝህ እያመቻቸህላትና እያቀለልክላት ነው፡፡

እግዚአብሄርን በእውነት ማስደሰት የምትፈልግ ሚስትህ ለእርስዋ ያለህን ፍቅርና መስዋእትነት ስታይ አንተን መታዘዝ ከአቅም በላይ ከባድ ሸክም አይሆንባትም፡፡ ሚስትህ ፍቅርህን ስታይ አንተን ለማስደሰት የማትሄደው መንገድ አይኖርም፡፡

ኢየሱስም እኛ እንድንታዘዘው በመጀመሪያ ያደረገው እኛን መውደድ ነው፡፡ ኢየሱስ እንድንታዘዘው የጠየቀው በፍቅር ነው፡፡ ኢየሱስ ራሳችንን እንድንሰጥ ከመጠየቁ በፊት ራሱን ሰጠን፡፡ ፍቅሩን በተረዳን ቁጥር መታዘዝ እየቀለለን ይሄዳል፡፡ ፍቅሩን በተረዳነውና ባወቅነው መጠን ምን ላድርግለት ፣ ምን ልሁንለንት ምኔን ልስጠው እንላለን፡፡

እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። 1ኛ ዮሐንስ 4፡19

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #መታዘዝ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሚስቶቻችሁን ውደዱ

love wife.jpgባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ኤፌሶን 5፡25-30

የመፅሃፍ ቅዱስ ትእዛዝ ኢየሱስ ተቀብሏችኋል ወዷችኋል ሚስቶቻችሁን ራሩላቸው ተቀበሏቸው ነው፡፡

ኦየሱስ የተቀበለን እንዳለን ነው፡፡ ኢየሱስ እኛን ከመቀበሉ በፊት አልለወጠንም አላሻሸለንም፡፡ ኢየሱስ አኛን የተቀበለን ባለንበት ቦታና ደረጃ ነው፡፡ ኢየሱስ ሲቀበለን እኛን ለመቀበል እና ለመውደድ የሚያበታታ ምንም ነገር አልነበረም፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡4-5

ኢየሱስ እኛን የተቀበለን በታላቅነታችን አይደለም፡፡ ኢየሱስ እኘዓን የተቀበለን በዝቅታቸን በማንወደድበት ጊዜ በድካማችን ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡26

ክርስቶስ ተረድቶናል፡፡ ክርስቶስ ሊወደን የቻለው ስለተረዳን ነው፡፡ ክርስቶስ ያለንበትን ደረጃ ተረድቶናል ክርስቶስ ራርቶልናል፡፡

ክርስቶስ እንዴት በጥንቃቄ እንደሚይዘን የታውቃል፡፡ ክርስቶስ አንደደረስንበት ደረጃ ይንከባከበናል፡፡ ክርስቶስ በደረስንበርት ደረከጃ ወርዶ የእኛን ቋንቋ ተናግሮ ከእኛ ጋር ኖሮ መስዋእት ሆኖልናል፡፡ ክርስቶስ ሁላችንንም በደረስንበት ደረጃ በፍቅር ይንከባከበናል፡፡

ክርስቶስ ጨካኝ አይደለም፡፡ ክርስቶስ አሳልፎ አይሰጠንም፡፡ ክርስቶስ በድካማችን ዞር አይልም፡፡ ክርስቶስ ርሁርሁ ነው፡፡ ክርስቶስ በድካማችን አይፈርድም፡፡ ክርስቶስ በድካማችንን ይራራልናል፡፡ ክርስቶስ በድካማችን ይሸከመናል፡፡ ክርስቶስ ድካማችንን በብርታቱ ይሸፍናል፡፡

ክርስቶስ ይመግበናል፡፡ ክርስቶስ ያስታጥቀናል፡፡ ክርስቶስ ያበረታታናል፡፡

ክርስቶስ ከእኛ ጋር ራሱ ያስተበናብራል፡፡ ክርስቶስ ለከእኛ ጋር አብሮ ለመጠራት ፈቃደኛ ነው፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር መቆጠርን ይፈልጋል፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ያብራል፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ይተባበራል፡፡

ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። ዕብራውያን 2፡13

ኢየሱስ ትሁት ነው፡፡ ኢየሱስ ስለእኛ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ስለእኛ ራሱን አልሰሰተም፡፡ ስለእኛ ያለውን ሁሉ ሰጠ፡፡ ስለእኛ የሆነውን ሁሉ ሆነ፡፡ ስለእኛ ክብሩን አጣ ተዋረደ፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ 2፡5-8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እኅት ሚስታችንን

marriage 22.jpgእንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡5

የጋብቻ ግንኙነት የሚጀመረው በእህትነትና በወንድምነት ነው፡፡ ወንድ የሚያጋባው በጌታ እህቱ የሆነችውን ሴት ነው፡፡ ሴት የምታገባው በጌታ ወንድሟ የሆነውን ወንድ ነው፡፡ የትዳር መሰረቱ በጌታ የእህትነትና የወንድምነት ዝምድና ነው፡፡

ትዳር ከትዳር የፍቅር ግንኙነት አይጀምርም፡፡ ትዳር የሚጀምረው ከወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ ትዳር የሚጀምረው ከእህትነት ፍቅር ነው፡፡ የትዳር የፍቅር ግንኙነት የሚጀመረው ከእህትነት የፍቅርና የርህራሔ ግንኘነት ነው፡፡ የትዳር የፍቅር ግንኙነት የሚጀምረው ከወንድምነት የፍቅርና የርህራሔ ግንኙነት ነው፡፡ ትዳር የሚጀምረው ከቤተሰብነት የፍቅር ግንኙነት ነው፡፡

የክርስትያናዊ ጋብቻ ግንኙነት መሰረቱ የእህትነትና የወንድምነት ግንኙነት ነው፡፡ የጋብቻ ግንኙነት መሰረቱ የቤተሰብነት ግንኙነት ነው፡፡ የትዳር የርህራሔና የፍቅር ግንኙነት የሚጀምረው ከወንድምነትና ከእህትነት የርህራሄና የፍቅር ግንኙነት ነው፡፡

ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡39

ባልና ሚስት ከመሆናቸው በፊት እህትነትና ወንድም መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የባልና የሚስት ፍቅር ከማሳየታቸው በፊት የወንድምና የእህት ፍቅር ሊያሳዩ ይገባቸዋል፡፡ እንዲያውም ለባልና ለሚስትነት ፍቅር መሰረት የሚሆነው የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ ለባልነትና ለሚስትነት ዝቅተኛው መመዘኛ የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር የሌላቸው የባልነትና  የሚስትነት ፍቅር ይኖራቸዋል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ከባልነቱ በፊት ወንድምነቱ ይቀድማል ከሚስትነትዋ በፊት እህትነትዋ ይቀድማል፡፡ ባልና ሚስትነቱ ወንድምና እህትነቱን በፍፁም አይሽረውም፡፡

በትዳር የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር እየጨመረ ሊሄድ ይገባዋል እንጂ ሊቀንስ አይገባውም፡፡ ባልና ሚስት በሆኑም ጊዜ ወንድምና እህትነቱ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ በትዳር የወንድምነትና የእህትነት ፍቅር እየጨመረ ሊሄድ ይገባዋል እንጂ በባልነትና በሚስትነት ፍቅር ሊተካ አይገባውም፡፡ በትዳር ባለቤትህ እህትህ ነች፡፡ በትዳር ባለቤትሽ ወንድምሽ ነው፡፡ በትዳርም የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ከባልነትና ከሚስትነት ፍቅር ይቀድማል፡፡ የወንድምና እህትነቱ ፍቅር ለባልና ለሚስትነቱ ፍቅር ጉልበት ይሰጠዋል፡፡

የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ከትዳር ፍቅር መቅደሙ በቻ ሳይሆን የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ለትዳር መሰረት ነው፡፡ ከትዳርም በኋላ እንዲሁ በሰማይ የሚዘልቀው የወንድምነትና የእህትነት ግንኙነት እንጂ የባልነትና የሚስትነት ግንኙነት አይደለም፡፡

በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም። ማቴዎስ 22፡30

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #አንድስጋ #እውነት #እህትነት #ወንድምነት #መውደድ #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል

one flesh.pngእርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። ማቴዎስ 19:4-6

ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል

ሰው ሁሉን ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ ሰው ውስን ነው፡፡ ሚስት ከባል ልዩ ፍቅር ትፈልጋለች፡፡ ሰው ከሚስቱ ጋር ለመጣበቅ  ልዩ ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡  ሰው አባቱንና እናቱን ሳይተው ከሚስቱ ጋር መጣበቅ አይችልም፡፡ ሰው አባቱንና እናቱን ካልተወ በስተቀር ከሚስቱ ጋር የሚጣበቅበት አቅም አይኖረውም፡፡ ሚስት ከምትፈልገው ልዩ እንክብካቤና ፍቅር አንፃር ሰው አባቱንና እናቱን ሳይተው በሚስቱ መጣበቅ አይችልም፡፡ ሰው አባቱንና እናቱን ሳይተው ከሚስቱ ጋር መጣበቅ የሚችልበት ትርፍ አቅም የለውም፡፡ ሰው ለሚስቱ ሙሉ ፍቅርና ትኩረት ለመስጠት እንዲችል እናቱንና አባቱን መተው ግዴታው ነው፡፡

ከሚስቱም ጋር ይተባበራል

ፍቅር በመረዳት ራስን ከሌላው ጋር ማስተባበር ነው፡፡ ፍቅር የሌላውን ድካም የራስ ድካም አድርጎ መሸከም ነው፡፡ ፍቅር የሌላውን ገመና እንደራሰ ገመና መሸፈን ነው፡፡ ፍቅር በሌላው ስም መጠራት ለመጠራት መፍቀድ ነው፡፡ ፍቅር ከሌላው ደረጃ ጋር ራስን ማስተባበር ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ሳያሻሽሉ እንዳለ መቀበል ነው፡፡ ፍቅር ከሌላው ጋር ለመቆጠር መፍቀድ ነው፡፡ ፍቅር ከሌላው ጋር ማበር ነው፡፡ ፍቅር  ሌላው ካለው ፣ ከሆነውና ከሚያደርገው ጋር ማበር ነው፡፡

ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፡፡  ሰው ከሚስቱ ጋር ራሱን ያስተባብራል፡፡ ሰው የሚስቱን ስም ይወስዳል፡፡ ሰው የሚስቱን ነገር እንደራሱ ይቀበላል፡፡ ሰው ለሚስቱ ሃላፊነትን ይወስዳል፡፡  ሰው ከሚስቱ ጋር ይቆጠራል፡፡ ሰው የሚስቱን ደረጃ ይወስዳል፡፡ ሰው ሚስቱ ካላት ፣ ከሆነችውንና ከምታደርገው ነገር ጋር ያብራል፡፡

ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ

አንድ ስጋ መሆን ማለት መዋሃድ ማለት ነው፡፡ አንድ ስጋ መሆን ማለት ሌላውን እንደራስ መውደድ ማለት ነው፡፡ አንድ ስጋ መሆን ማለት አለመለያየት አለመከፋፈል አንድ መሆን ማለት ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ስለፍቅር ሲናገር ሌላውን የመውደድ ደረጃ ራስን የመውደድ ደረጃ እንደሆነ ያሰተምራል፡፡ ሰው ግፋ ቢል ራሱን በሚያከብርበት አከባበር ብቻ ነው ሌላውን ሊያከብር የሚችለው፡፡ ሰው ራሱን በሚወድበት መውደድ ነው ሌላውን መውደድ የሚችለው፡፡ ሰው ለራሱ ዋጋ በሚሰጥበት ደረጃ ብቻ ነው ለሌላው ዋጋ ሊሰጥ የሚችለው፡፡ ሰው ለራሱ በሚሳሳበት መጠን ብቻ ነው ለሌላው ሊሳሳ የሚችለው፡፡ ሰው ነፍሱን ከሚወድበት መጠን በላይ የሌላውን ነፍስ አይወድም፡፡ ሰው ራሱን በሚንከባከብበት መጠን ብቻ ነው ሌላውን ሰው የሚንከባከበው፡፡

ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ማርቆስ 12፡31

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል ያለው፡፡

እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ኤፌሶን 5፡28-31

ሰው ለራሱ አክብሮት እንዳለው የሚታየው ለሚስቱ በሚያሳየው አክብሮት ነው፡፡ የገዛ ስጋውን የሚጠላ ሰው እንደሌለ ሁሉና ሰው ስጋውን እንደሚመግበውና እንደሚንከባከበው ሁሉ ሰውም ሚስቱን ይመግባል ይንከባከባል፡፡ ራሴን እወዳለሁ ስጋዬን አልወደውም የሚል ሰው እንደሌለ ሁሉ ለራሱ አክብሮትና ፍቅር ያለው ሰው ለሚስቱ አክብሮትና ፍቅር ይኖረዋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ዘፍጥረት 2፡22-24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም

alonehdr.jpgእግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ዘፍጥረት 2፡18

ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ሲል እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው ምን አይነት ሰው እንደነበር እንመልከት፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ስንመለከት ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለውን ሰው መመልከት እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው ማንኛውምንም ሰው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው ሙሉ የሆነን ሰው ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው ሙሉ ሰውን ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር የተሳካ ግንኙነት የነበረውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው በእግዚአብንሔር የረካን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው አንድ ሴትን ሊያስተዳድር የሚችል ሙሉ ብቃት ያለውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ጎዶሎን ሰው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው 50 % ሰውን አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው 100% ሰውን ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ቤተሰብ ሊመራ የሚችልን ሙሉ ሰውን ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ተለዋዋጭ ስሜቱን የሚከተልን ሰው ሳይሆን ሚስቱን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሊወድድ የሚችልን የውሳኔን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ለቤተሰቡ ሊያቀርብ የሚችል ጠንካራን ሰራተኛ ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ቤተሰብን ሊሸከም የሚችል ሙሉ ሰውን ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው ሙሉ የምታደርገኝን ሴት እፈልጋለሁ ብሎ በጉድለት የሚጮኽን ሰው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ተግዳሮት ሲመጣ የሚሸሽና በእርሱ ፋንታ የምታምንለትን ሴት የሚፈልግን ሰው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ተባርኮ ለበረከት የሚሆንን ወንድ እንጂ ከምስኪንነት የምታነሳውን ሴት የሚፈልግን ወንድ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው በእግዚአብሔር ግንኙነት የረካን ወንድ እንጂ የምታሳልፍለትን ሴት የሚጠብቅን ወንድ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ጎዶሎን ሰው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ባለ ራእይን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው በመስጠት በመባረክ በማካፈል ላይ ያተኮረን ሰው ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው ስልጣኑን ከማወቁ የተነሳ ሺን የሚያሳድድን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው እግዚአብሔር ባዘጋጀው አሰራር በትዳር ከአንድ ሴት ጋር አስር ሺን ሊያሳድድ የተዘጋጀን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው አንድን ሴት ሊባርክ የተዘጋጀን የተባረከን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው አንድን ሴት ሊመራትና የተሻለውን ከውስጥዋ ሊየወጣ የተዘጋጀን ሰው ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረው በራስዋ የረካች አንድን ባለራእይ ልትረዳ የተዘጋጀችን ሴት ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው የሚያነሳትን ባል የምትፈልግን ሴት ሳይሆን እግዚአብሔር ስለእኔ ምክኒያት ቤቱን ይባርካል ብላ የምታምንን የእምነትን ሴት ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው የሚያሳልፍላትን ባል የምትፈልግን ሴት ሳይሆን እንደ ልጅ ከአባት እንዴት በፀሎት እንደምትቀበል የምታውቅን ሴት ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው በመስጠት በመባረክ በማካፈል ላይ ያተኮረችን ሴት ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ስለግንኙነት በረከት ሲናገር አንዱ ሺህ ሁለቱ ደግሞ ሁለት ሺህ ያሳድዳሉ አይደለም የሚለው፡፡ እንደዚያ ከሆነማ ሁለቱም ጎዶሎ በመሆናቸው 50 % ሊያዋጡ ነው ማለት ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ግን በህብረት ውስጥ ስለተቀመጣው ታላቅ እምቅ ሃይልክ ሲናገር አንዱ ሺህ ሁለቱ ደግሞ አስር ሺህ ያሳድዳሉ ነው የሚለው፡፡

ወንድና ሴት ከመጋባታቸው በፊት ሁለቱም በጌታ ሙሉ መሆን አለባቸው፡፡ በጌታ ሙሉ የሆነውን ሰው ነው መፅሃፍ ቅዱስ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ያለው፡፡ ወንድ 100 % ሴትም መቶ % ሲሆኑ ነው ሲያብሩ አስር ሺህ የሚያሳድዱትና እግዚአብሔ በህብረት ውስጥ ያስቀመጠውን እምቅ ጉልበት የሚለቁት፡፡

ወንድና ሴት ግን ጎዶሎዎች ከሆኑና እርሱም በጎዶሎነት አስተሳሰብ ሙሉ የሚያደርገው ኢየሱስ ላይ ካላተኮረና የምትሞላውን ከፈለገ እርስዋም በዋናው በሚያረካው በእግዚአብሔር ካልረካችና በምስኪንነት አስተሳሰብ የሚሞላትን ከፈለገች ሁለቱም ሳይገናኙ መሃል ላይ ይቀራሉ፡፡ ሁለቱም ሙሉ የሚያደርጋቸውን ክርስቶስን ትተው በጎዶሎነት የሚሞላቸውን ሲፈልጉ እግዚአብሔር በትዳር ውስጥ ያስቀመጠው ታላቅ ሃይል ሳይገለጥ ይቀራል፡፡

ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም ያልሆነው ጎዶሎው እንዲሞላ ሳይሆን ሙላቱ እንዳይባክን ነው፡፡

ስለዚህ ነው ሰው ካገባም በኋላ አላግባብ በሚስቱ ላይ እንዳይደገፍ የእግዚአብሔር ቃል የሚመክረው፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ያላገባ ሰው በእግዚአብሔር ላይ መደገፉን እንዳይለውጥ የሚመክረው፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ሰው ለትዳሩ በሚሰጠው በሚያበረክተውና በሚያካፍለው ነገር ላይ እንጂ ከትዳሩ በሚጠቀመው ነገር ላይ ያለልክ እንዳይደገፍ የሚመክረው፡፡

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ትዳር የእግዚአብሔር ስርአት

Marriage-holding-hands (1).jpgትዳር የሰው ሃሳብ አይደለም፡፡ ትዳር የሰው ፈጠራ አይደለም፡፡ ትዳር የሰው እቅድ አይደለም፡፡ ትዳር የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡ ትዳር እግዚአብሔር ራሱ ያቋቋመው ተቋም ነው፡፡ ትዳር የእግዚአብሔር ስርአት ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ዘፍጥረት 2፡18

አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር። ዘፍጥረት 2፡20-25

ትዳርን አለመቃወም የእግዚአብሄርን መንግስት አለመቃወም ነው፡፡ ትዳርን አለመቃወም የእግዚአብሄርን አሰራር አለመቃወም ነው፡፡ ለትዳር መስራት ለእግዚአብሄር መንግስት መስራት ነው፡፡ ትዳርን ማክበር የእግዚአብሄርን ስርአት ማክበር ነው፡፡ ትዳርን መውደድ እግዚአብሔርን መውደድ ነው፡፡ ትዳርን ማክበር እግዚአብርን ማክበር ነው፡፡

መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ዕብራውያን 13፡4

ትዳርን መቃወም የእግዚአብሔርን ስርአት መቃወም ነው፡፡ ትዳርን መቃወም አግዚአብሔርን መቃወም ነው፡፡ የትዳር መጠንከር የእግዚአብሔር መንግስት መጠንከር አንዱ አካል ነው፡፡

ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ሮሜ 13፡2

ኢየሱስ ስለመጋባት ሲናገር በመጀመሪያ ግን እንደዚህ አልነበረም በማለት የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመረዳት የመጀመሪያውን የጥንቱን የእግዚአብሄርን ሃሳብ መረዳት ወሳኝ እንደሆነ ይነግረናል፡፡

እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። እነርሱም፦ እንኪያስ ሙሴ የፍችዋን ጽሕፈት ሰጥተው እንዲፈቱአት ስለ ምን አዘዘ? አሉት። እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። ማቴዎስ 19፡4-8

የመጀመሪያው ኦሪጂናል የእግዚአብሄር ሃሳብ እውነት ነው፡፡ ሰው የሚጠቀመው ከእውነት ጋር ሲስማማ ነው እንጂ ከእውነት ተቃራኒ ሲሆን አይደለም፡፡ ሰው ከእውነት ተቃራኒ ሲሆን ይጎዳል፡፡ እጅግ ጠቢብ ሰው ከእውነት ጋር ይወግናል እንጂ በእውነት ላይ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከእውነት ጋር መወገን እንጂ ከኦሪጂናል በእግዚአብሄር ሃሳብ ላይ ወይም በእውነት ላይ ምንም ማድረግ እንደማይችል የተናገረው፡፡

ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

ስለዚህ ነው ኢየሱስ እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው በማለት የሚያስጠነቅቀን፡፡

እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። ማርቆስ 10፡9

ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5-6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው

gallery-1473796416-child-marriage-knot.jpg21 ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

22 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

25-26 ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

27 እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

28 እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

29-30 ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

31 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።

33 ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን

ትፍራ።

ኤፌሶን 5፡21-33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል

finding-a-wife.pngአንድ አሳ አጥማጅ ነበር ይባላል፡፡ ብቻውን ሲኖር በቀን አንድ አሳ ያጠምዳል ይጠብሳ ይበላል ይተኛል፡፡ ሰዎች ሚስት አግባ ብለው መከሩት፡፡ ሚስት ካገባ በኋላ በቀን ሁለት አሳ ማጥመድ ጀመረ፡፡ ልጅ ሲወልድ ሶስት አራት አምስት አሳዎች ያጠምድ ጀመረ፡፡ እንደዚህ እያለ ሰባት ልጆች በመውለዱ ከሚስቱ ጋር የሚበቃውን በድምሩ ዘጠኝ አሳ ያጠምድ ጀመረ፡፡

ሳያገባ ሲያጠምድ ከነበረው አንድ ብቻ አሳ ጋር ሲያስተያየው ዘጠኝ አሳ ብዙ ነው፡፡ እና ምን አለ ይባላል? ሚስቴና ልጆቼ ባይኖሩ ኖ ዘጠኙም የእኔ ይሆኑ ነበር አለ ይባላል፡፡ ነገር ግን በውስጡ የተቀመጠው ዘጠኙ አሳዎች የመጡት ሚስት በማግባቱና ልጆች በመውለዱ መሆኑን ዘንግቶት ነበር፡፡

የዚህ አሳ አጥማጅ ታሪክና በመጨረሻ የተናገረው ንግግር ቢያስገርመንም እንደ አሳ አጥማጁ የሚያስቡ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሄር እንደ ቤተሰብ የባረካቸው በረከት የእነርሱ ብቻ አድርገው የሚያስቡ፡፡ እራሳቸውን ብቻ የተመረቁ ሰዎች አድርገው የሚያዩና ሌላውን ግን ዝቅ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች አሉ፡፡

ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል። ምሳሌ 18፡22

መፅሃፍ ሚስትን ያገኘ ከእግዚአብሄር ሞገስን ይቀበላል ይላል፡፡ ሰው ሚስት ሲያገባ በሚስቱ ስም የእግዚአብሄር አቅርቦት ይጨምራል፡፡ ሰው ሚስት ሲያገባ ካላገባው ሰው ይልቅ እንደ ቤተሰብ ሞገሱ ይበዛል፡፡ ሰው ልጅ ሲወልድ እንዲሁ ለተጨማሪ በጀት ሞገሱ ይጨምራል፡፡ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የራሱን በጀት ይዞ ነው ወደ ቤተሰቡ የሚመጣው፡፡

እግዚአብሄር መጀመሪያ ስለሚስቱ ከዚያም ስለልጆቹ ብሎ የባረከውን በረከት ሁሉ ወደ ራሱ ስም የሚያዞር ፣ ሁሉም በእርሱ ቅልጥፍና ምክኒያት እንደመጣ የሚቆጠር ሰው የተሳሳተ መረዳት ያለው ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ቤተሰብን የሚባርከው ሁሉንም የቤተሰብ አባላት አስቦ ነው፡፡ እግዚአብሄር አቅርቦቱ የሚጨምረው በቤተሰቡ ውስጥ ባሉት አጋሮች ብዛት ልክ ነው፡፡

አንድ በቅርብ የማውቃት እህት ከመስራ ቤት ደሞዝ ሲጨመርላት ለቤት ሰራተኛዋ ደሞዝ ትጨምራለች፡፡

እግዚአብሄር ስለንግድ ድርጅቱ አባላት የባረከውን በረከት ሁሉ ለመዋጥ የሚፈልግ ሰውና እግዚአብሄር ድርጅቱን የባረከው በድርጅቱ ስለሚሰሩት ሰዎች ሁሉ ምክኒያት እንደሆነ የማያስብ ሰው የእግዚአብሄርን የበረከት መንገድ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የምታገለግላቸውና የሚጠቅሙህን ደንበኞች የሚልከው ስለድርጅቱ አጋር ባለቤቶችና በድርጅቱ ውስጥ ስለሚሰሩት ሰዎች ሁሉ ምክኒያት ነው፡፡ ድርጅቱ ሲያድርግ ሁሉም አብሮ እንዲያድግ እንጂ አንድ ሰው ብቻ ተለይቶ እንደተመረቀ ሁሉንም ክብር ወደራስ ማድረግ የእግዚአብሄር አሰራር አይደለም፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች ሁሉ እንደ አጋር ሰራተኛ እንጂ ባለቤቱን ሊጠቅሙ ብቻ እንደቀመጡ ያልታደሉ ሰዎች መቁጠር አግባብ አይደለም፡፡

ቤተክርስትያንም ሆነ አገልግሎት ሲያድግ የእግዚአብሄር ሞገስ የመጣው በአገልጋዪችና በተጠቃዎቹ ሁሉ ፍላጎት ምክኒያት እንደሆነ ተረድቶ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ካልሆነ በረከቱ መሰረት አይኖረውም፡፡ አገልግሎቱን እንደ አጋርነት ካላየው አንድ ሰው ብቻውን እንደ ተመረቀ ሌሎች ለእርሱ እንዲሰሩ እንደተፈጠሩ መቁጠር ሞኝነት ነው፡፡ ሁላችንም አብረን እንድናድግ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ ስለ ህብረትና አጋርነት የመጣውን የእድገትን ክብር ለብቻ ጠቅልሎ መውሰድ ስህተት ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህብረት #አጋርነት #አብሮማደግ #የጋራ #ሚስት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው

MAN WOMAN.jpgእግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 1፡27

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር ወንድና ሴት እንዲሆኑ ነው በቤተሰብ ውስጥ የፈጠረው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን በመልኩ ፈጠረው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የእግዚአብሄር መልክ የሚታየው በወንድና በሴት ነው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ወንድ ብቻ እግዚአብሄርን መልክ ሙሉ ለሙሉ አይገልጠውም፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የሴት መልክ ብቻ እግዚአብሄርን ሙሉ ለሙሉ አያንፀባርቀውም፡፡

የእግዚአብሄርን ሙሉ መልክ እንዲያንፀባርቁ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡

በቤተሰብ ውስጥ የእግዚአብሄርን መልክ ሙሉ ለሙሉ ለማንፀባረቅ የሴት የርህራሄ ፣ የምህረት ፣ የፍቅርና የደግነት ባህሪ ያስፈልጋል፡፡

ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም። ምሳሌ 31፡12

እግዚአብሄር የፈጠራችሁን መልክ ለመኖር ለሁሉም ሰው ርህሩህ ፣ አፍቃሪ ፣ መሀሪ ፣ ደግ ይቅር ባይ የሆናችሁ ሴቶች ሁሉ መልካም የእናቶች ቀን ይሁንላችሁ፡፡

 

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ሴት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ #እግዚአብሔርንመምሰል #ቃል #ደግነት #ቸርነት #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

One of the best Christian Marriage Books Audio for free

One of the best Christian marriage books audio for free

Click here for You and me forever audio book

ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው

leaning-on-leanዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29፣31
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው ሙሉ አድርጎ ነው፡፡ አዳም ምንም የማይጎድለው ሙሉ ተደርጎ ነው የተፈጠረው፡፡ አዳም በምድር ላይ ተቋቁሞ ለመኖር ሚስት አላስፈለገውም፡፡ አዳም ካለሚስት በራሱ ሙሉ ነበረ፡፡ አዳም በራሱ ከእግዚአብሄር ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው፡፡ አዳም በራሱ እግዚአብሄርን የሚያምን ከእግዚአብሄር ጠይቆ የሚቀበል ነበረ፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሄርን ሰውን ከፈጠረ በኋላ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ የሚለው፡፡
እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። ዘፍጥረት 1፡31
ሰው ከማግባቱ በፊት ሙሉ እንደነበረና በእግዚአብሄር ላይ ሙሉ ለሙሉ ይደገፍ እንደነበረ ሁሉ ካገባም በኋላ ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ አለበት፡፡ ሰው ሚስት ሲያገባ በእግዚአብሄር ላይ ያለውን መደገፍ በሚስት ላይ ባለ መደገፍ መለወጥ የለበትም፡፡ እንዲሁም ሴት ማግባትዋ በእግዚአብሄር ላይ ያላትን መደገፍ ፣ ከእግዚአብሄር ጋር ያላትን ግንኙነትና በእግዚአብሄር ላይ ያላትን መታመን በፍፁም መተካት የለበትም፡፡
እንዲያውም እንደዚህ ሙሉ የሆነ ሰው ብቻ ነው ሚስትን ማግባት ያለበት፡፡ እንዲሁም ከጌታ ጋር የተሳካ ግንኙነት ያላት ሴት ነች ባል ማግባት ያለባት፡፡ ጎዶሎነት ተሰምቷት ጉድለቷን ለመሙላ ባል ማግባት የምትፈልግ ሴት ሳትሆን ጌታን የምታምነው ሴት ነች ባል ማግባት ያለባት ፡፡ ከጌታ እንዴት ጠይቃ እንደምትቀበል የምታውቅ የእምነት ሴት ነች ባል ማግባት ያለባት፡፡ ስለእኔ ብሎ ቤቱን ይባርካል ብላ በጌታ ላይ የምትታመን ሴት ነች ማግባት ያለባት፡፡
አላስፈላጊ የሆነ በባል ወይም በሚስት ላይ መደገፍ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነት ያበላሻል፡፡ ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ያገባ እንዳላገባ ይኑር በማለት ያገባ ሰው በሚስቱ ወይም ያገባች ሴት በባልዋ ላይ አላግባብ እንዳትደገፍና የሚመክርው፡፡
የዚህ አለም መልክ ጊዜዊና አላፊ በመሆኑ ከመጠን በላይ ልንደገፍበት የሚያስችል አይደለም፡፡ ስለዚህ ያገባ እንዳላገባ ወይም እንደ ብቸኛ ሰው እንዲኖር የተጠየቀው፡፡ ያገባ በማያልፈው በእግዚአብሄር ላይ ያለውን መደገፍ በሚያልፈው በሰው ላይ ባለ መደገፍ እንዳይለውጠው የሚያስጠነቅቀው፡፡
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
%d bloggers like this: