Category Archives: Devil

አሸባሪው ማነው

conscious.jpg

ሰዎችን ተጠቅሞ የሚያሸብረው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የተፈረደበት ተስፋ የሌለው ጠላት ነው፡፡

ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 16፡11

ሰይጣን ፍቅርን አያውቅም፡፡ ሰይጣን ምህረት አይገባውም፡፡ ሰይጣን በፍቅርና በሰላም ምንም ነገር ማድረግ ስላይችል የሚችለው አንድ ነገር ውሸትን በመዋሸት ፍርሃትን በሰዎች ውስጥ በመጨመር ከመንገዳቸው ማስቆም ነው፡፡  ሰይጣን ውሸትን በማዛመት ማስፈራራት ስራው ነው፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44

ሰይጣን የሰዎችን ጉስቁልና እንጂ እድገት አይፈልግም፡፡ ሰይጣን የሰዎችን መቆም እንጂ መራመድ እና እድገት አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ራስ ወዳድ ምኞታቸውን ብቻ የሚከተሉ ፣ ለሌላው ምንም ፍቅር እና አክብሮት የሌላቸው ሰዎችን ለማስፈራሪያነት  እንደመሳሪያ ይጠቀማል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረ ፈቃድ ሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሲከፈት የሚከፈት ሲዘጋ የሚዘጋ የራሱ ፈቃድ የሌለው ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን አድርጎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በሙሉ ፈቃድ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚገዛው በፍቅር እና በፈቃደኝት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች እንዲገዙለት የሚፈልገው በፍቅርና በፈቃደኝነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው ሰውን ማሸነፍ የሚፈልገው በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡1

በፍርሃት ሊገዛ የሚፈልውገው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን የሚሰራው በጥላቻ ነው፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካላስገባ በስተቀር ሰይጣን መስራት አይችልም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻን ካስገባ ደግሞ የማይሰራው ክፋት የለም፡፡ ሰው ውስጥ ጥላቻ ካስገባ ሰውን ያስገድላል፡፡

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14-15

ሰይጣን ደግሞ ራስ ወዳድ ሰዎችን ለማረድ ለማጥፋትና ለመስረቅ አላማው ይጠቀማል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። የዮሐንስ ወንጌል 8፡44

የአሸባሪነት አላማ ደግሞ ሰውን ከጉዞው ማስቆም ነው፡፡ ሰውን ዝም ካላሰኘና ከአላማው ካላስቆመው ፍርሃት አላማው ይከሽፋል፡፡ ሰውን ከመንገዱ ከላስቆመው አሸባሪነት ግቡን አይመታም፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ወደ ዕብራውያን 2፡14-15

ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ መታወስ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ባገኘው አጋጣሚ የፍርሃት ዜናውን ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ የሰይጣን አላማ በፍርሃት ሽባ ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣነ አላማ በውስጣችን ያለውን እምቅ ጉልበት እንዳንጠቀም አሳስሮ ማስቀመጥ ነው፡፡

ሰይጣን አያስቆመንም፡፡ በፍቅር ፍርሃትን አሽቀንጥረን እንጥላለን፡፡ በፍቅር እንሄዳለን፡፡ በፍቅር እንወጣለን እንገባለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍትህ #ፍርድ #ዲያቢሎስ #ሰይጣን #ዲሞክራሲ #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #ፍርሃት #የውሸት አባት #ኢትዮጲያ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #ጥላቻ #ፍቅር #ፈቃድ #መሪ

ለሰይጣን ሽንገላ ፍቱን መድሃኒቱ

kylo-ren-star-wars-the-4.jpgሰይጣን በትእቢት ምክንያት ከመውደቁ በፊት የእግዚአብሄር አገልጋይ ነበር፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄርን ቦታ ፈልጎ ከመዋረዱ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ይኖር ነበር፡፡ ሰይጣን በሃጢያት ምክንያት ሲወድቅ ነው ጥበብህን አረከስህ የተባለው፡፡

በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ። ሕዝቅኤል 28፡17

ሰይጣን የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ አሁንም ጥበብ አለው፡፡ ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያሳምናል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያታልላል፡፡ ሰይጣን በረከሰው ጥበብ ተጠቅሞ ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ ሰዎችን በእግዚአብሄር ላይ ያሳምፃል፡፡ ሰይጣን ጥበቡን ተጠቅሞ የሰዎችን ህይወት ያጠፋል ያበላሻል፡፡

ሰይጣን ሰዎችን በማታለል ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን ይዋሻል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን ያስታል፡፡ ሰይጣን ሄዋንን አስቶዋታል፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሄር ጥበብ በቀጣይነት የማይኖረውን ማንኛውንም ሰው ሊያስት ይችላል፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ሰይጣን አያታልለንም ብለን በከንቱ ብንፎክር ከሰይጣን ማታለል አናመልጥም፡፡ ሰይጣን የራሱ የማታለል ሃይለ አለው፡፡ ሰይጣን ምንም አያመጣም ብለን ብንኩራራ ራሳችን ምንም አናመጣም፡፡

የረከሰ ጥበብ ይሁን እንጂ ሰይጣን የራሱ ጥበብ ስላለው ካለ እግዚአብሄር ጥበብ በስተቀር ከሰይጣን ማታለል ማምለጥ አንችልም፡፡ በሰይጣን ላለመሳት ከፈለግን የእግዚአብሄር ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወምበት የእግዚአብሄርን ጥበብ ማንሳይ አለብን፡፡ ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም አንችልም፡፡

ካለ እግዚአብሄር ጥበብ የሰይጣንን ሽንገላ የምንቃወም ከመሰለን በራሱ በሰይጣን ተታልለናል ማለት ነው፡፡ በሰይጣን ላለመበለጥ  የሰይጣንን ማታለል የሚበልጥ ጥበብ ያስፈልገናል፡፡ የምንበረታው በራሳችን ሃይል ሳይሆን በጌታ ሃይል ብቻ ነው፡፡

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌሶን 6፡10-11

ከእግዚአብሄር ብቻ በምናገኘው ዘርፈ ብዙ ጥበብ በመታገዝ ብቻ ነው የሰይጣንን ሽንገላ እያለ በእኛ ላይ ምንም ሃይል እንዳይኖረው ማድረግ የምንችለው፡፡ በአለቆችና ስልጣናት ላይ በሃይል የምንገለጠው በእግዚአብሄር ጥበብ ስንንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 3፡10

በእግዚአብሄር ቃል ጥበብ ስንኖር ግን ኢየሱስ እንዳለው ሰይጣን በእኔ ላይ አንዳች የለውም ማለት እንችላለን፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ማስተዋል #ሽንገላ #አለቆች #ስልጣናት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰይጣን #ዲያብሎስ #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ተዘዋዋሪ የሰይጣን አምልኮ

throat stab 2 (1).PNGሰይጣን ከመውደቁ በፊት የእግዚአብሄር አገልጋይ ነበር፡፡ ሰይጣን የወደቀው በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ ነው፡፡ ሰይጣን የወደቀው እንደ እግዚአብሄር ለመመለክ በመፈልግ ምኞት ነው፡፡ ሰይጣን መመለክ ይፈልጋል፡፡

ሰይጣን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መመለክን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ኢየሱስን በግልፅ ብታመልከኝ ይህን ክብር ሁሉ አሰጥሃለሁ ብሎታል፡፡

ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው። ዲያብሎስም፦ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው። ሉቃስ 4፡5-7

ሰው ካመለከው እና ከተንበረከከለት ሰይጣን በየደረጃው የአለምን ክብር ለሰው ለመስጠት ዝግጁ ነው፡፡

አሁን ሰይጣን የሚመለከው እንደ ኢየሱስ በግልፅ ጠይቆ ላይሆን ይችላል፡፡ በግልፅም ይሁን በስውር ሰይጣን መመለክን ይፈልጋል፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሰይጣን መመለክን ይጠይቃል፡፡

የሰይጣን አምልኮ በጣም በታዋቂ ሰዎች ላይ ብቻ ያለ የሚመስላቸው ሰዎች ተሳስተዋል፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄር መልክና አምሳል ያለበትን ማንንም አይንቅም፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄር መልክና አምሳል ያለበትን ሰው ማስመለክ እግዚአብሄርን ራሱን ያገኘውና ያሸነፈው ይመሰለዋል፡፡

ሰይጣን ከማንም ሰው አምልኮን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ከተፈጠር ከማንም ሰው የሚመጣውን አምልኮ አይንቅም፡፡ ሰይጣን አንዳንድ ጊዜም ቢሆን የመስረቅ የማረድ የማጥፋት አላማውን የሚያሳካለትን ሰው ይፈልጋል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን ለማምለክ የሰይጣን ጉባኤ መሄድ አያስፈልግም፡፡ ሰይጣንን ለማምለክ የሰይጣን ስብሰባ አባል መሆንም አይጠይቅም፡፡ ሰይጣንን እምቢ ለማለት እግዚአብሄርን እምቢ ማለት ብቻ ይበቃል፡፡ ሰይጣንን ለመታዘን እግዚአብሄርን አለመታዘዝ ብቻ ይበቃል፡፡ ሰይጣንን ለመከተል በውሸት መመላለስና የሰይጣንን ምኞት ጥላቻንና ነፍሰ ገዳይነትን ማድረግ በቂ ነው፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ሰይጣንም ለማምለክ ሰይጣንን የሚያስደስተውንና ሰይጣን የሚበላውን ነገር ሃጢያትን መለማመድ ይበቃል፡፡ ሰይጣንን ለማምለክ እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን ነገር ማድረግ ይበቃል፡፡ ሰይጣንን ለማምለክ የእርሱን ጥበብ መከተል በቂ ነው፡፡

ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ያዕቆብ 3፡14-16

ሰይጣንን ለማምለክ ብልቶቻችንን የፅድቅ የጦር እቃ አድርጎ ለእግዚአብሄር አለማቅረብ ይበቃል፡፡ የሰይጣንን ስራ ለመስራት ብልቶችን የአመፅ የጦር እቃ አድርጎ ለሃጢያት ማቅረብ በቂ ነው፡፡

ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ሮሜ 6፡13

በሰይጣን አምልኮ ስር ለመውደቅ ጌታን ሳይሆን ራስን በህይወታችን ላይ ጌታ ማድረግና ማንገስ ይበቃል፡፡ ሰው ጌታ ጌታው ካልሆነ ከመቀፅበት ሰይጣን ጌታው ይሆናል፡፡ ሰው የጌታን ፈቃድ ካልሰማ የሰይጣንን ፈቃድ ይሰማል፡፡ ሰው ጌታን ሳይሆን ራሱን በላዩ ላይ ከሾመና ጌታ ካደረገ በሰይጣን ጌትነት ስር ይወድቃል፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2

በሰይጣን ለመዋጥ በእግዚአብሄር ነገር ንቁ አለመሆንና በመጠኑ አለመኖር በቂ ነው፡፡

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8

በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ የባለጠግነት መኞትን መከተል በቂ ነው፡፡

ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡9-10

ከሳይጣን ጋር ለማበር እና ሰይጣንን ለማምለክ የእግዚአብሄርን ስራ መቃወም በቂ ነው፡፡ ሰይጣንን ለማምለክ የእግዚአብሄር ስራ ላይ መነሳት በቂ ነው፡፡ በሰይጣን ወጥመድ ለመያዝ በአመፅ መቀጠልና ንስሃ አለመግባት በቂ ነው፡፡

ደግሞም፦ ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡25-26

በሰይጣን ሃሳብ ውስጥ ለመውደቅ መራርነትና ይቅር አለማለት በቂ ነው፡፡ በህይወታችን ለሰይጣን ስፍራ መስጠት በምህረት አለመመላለስ በቂ ነው፡፡

በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን ሰዎች 4፡27

የሰይጣንን ፈቃድ ለማድረግ የልቦናችንን ፈቃድ ማድረግ በቂ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ካላደረግን የስጋችንን ፈቃድ በማድረግ በተዘዋዋሪ የምናደርገው የሰይጣንን ፈቃድ ነው፡፡

በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ኤፌሶን 2፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #የስጋፈቃድ #የልቦናፈቃድ #ምኞት #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አምልኮ #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሰውና የሰይጣን ሃሳብ

temptation2 (1).jpgሰው ለእግዚአብሄር ክብር ስለተፈጠረ ለእግዚአብሄር ክብር ካልኖረ በሰይጣን ተገዝቷል ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚታለሉት ቀንድ ያበቀለ አውሬ አይነት ሰይጣን በህይወታቸው ካልመጣ ከሰይጣን ጥቃት ነፃ እንደሆኑ ስለሚመስላው ነው፡፡ ሰይጣን የሚሰራው በግልፅ አይደለም፡፡ ሰይጣን የሚሰራው በማታለል ነው፡፡ በሰው ስጋ የሚሰራው ሰይጣን ነው፡፡ በሰው ምኞት የሚሰራው ሰይጣን ነው፡፡ የስጋችንንና የልቦናችንን ፈቃድ ካደረግን በሰይጣን ፈቃድ እየተመላለስን ነው፡፡

በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን ኤፌሶን 2፡1-3

በምድር ላይ ሁለት አይነት ሃሳብ ብቻ ነው ያለው፡፡ የእግዚአብሄር ሃሳብ አለ፡፡ የእግዚአብሄር ያልሆነ ሃሳብ አለ፡፡ የእግዚአብሄር ያልሆነው ሃሳብ ሁሉ የሰው ሃሳብ ነው የሰይጣንም ሃሳብ ነው፡፡

በምድር ላይም ያለው ጥበብ ሁለት አይነት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ አለ፡፡ የእግዚአብሄር ያልሆነ ጥበብ አለ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ያልሆነው ጥበብ የሥጋና የአጋንንትም ጥበብ ነው፡፡

ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ያዕቆብ 3፡14-15

ሰይጣን እፃን ለማጥቃት የሚጠቀመው የስጋን ሃሳብ ተጠቅሞ ነው፡፡ ሰይጣን እኔ ሰይጣን ነኝ ብሎ ሳይሆን የሚመጣው ለሰው ስጋ በሚመች ሃሳብ ነው፡፡

ኢየሱስ ጴጥሮስን አንተ ሰይጣን ብሎ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ብሎ ሲገስፀው እናያለን፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ለመተላለፍ የሰይጣንን ሃሳብ ማሰብ የለበትም፡፡ ሰው የሰውን ሃሳብ ካሰበ በተዘዋዋሪ የሰይጣንን ሃሳብ አሰበ ማለት ነው፡፡ ሰይጣን እኔ ሰይጣን ነኝ አገልግሉኝ ብሎ ሳይሆን የሚመጣው የራስ ወዳድነትን ሰውኛን ሃሳብ እንድናስብ በማድረግ ነው፡፡

እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። ማቴዎስ 16፡23

እግዚአብሄር በፍጹም ልባችን በፍጹም ነፍሳችን በፍጹም ኃይላችን በፍጹም አሳባችን እንድንወደው ስለሚፈልግ ራስ ወዳድነት ካለብን በተዘዋዋሪ ሰይጣንን እያገለገልን ነው እንጂ እግዚአብሄርን እየወደድን አይደለም፡፡

ዓለምን በሚወድ ውስጥ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም የሚለው ለዚህ ነው፡፡ አለምን መውደድ በተዘዋዋሪ ሰይጣንን ማገልገል ነው፡፡

ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሐንስ 2፡15

በህይወታችን ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ ለመሳት የሰይጣን አምላኪ መሆን የለብንም ከእግዚአብሄር ጋር ለመተላለፍ እንደሰው ልማድ መመላለስ ይበቃናል፡፡

ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #የስጋፈቃድ #የልቦናፈቃድ #ምኞት #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: