Category Archives: excellence

የእውነተኛ ህይወት ብልጫ

excellence.jpgእንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1ኛ የጴጥሮስ 3:1-2

አኗኗር ያሳምናል፡፡ ህይወት ይሰብካል፡፡ ሰዎች ሲሰበክላቸው እውነት ነውን ብለው የሰዎችን ኑሮ ነው የሚያዩት፡፡ የሰዎቹ ህይወት ከሚናገሩት አብሮ ካልሄደ ሰዎች አይቀበሉም፡፡ የህይወት ብላጫ እንደንግግር ብልጫ የማያከራክር ብልጫ ነው፡፡

ክርስትና ህይወት ነው፡፡ ክርስትና ክርስቶስን መከተል ነው፡፡ ክርስትና ለሞተልን ለእርሱ መኖር ነው፡፡ ክርስትና ብልጫ አለው፡፡ ብልጫ የሌለው ነገር ባዶ ሃይማኖት እንጂ ክርስትና አይደለም፡፡

ይህ ሁሉ የሚሆነው በሚያስችል በእግዚአብሔር ፀጋ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር አብረን ለመስራት ግን አሰራሩን ማወቅ አለብን፡፡

 1. እውነተኛ የሚበልጥ መስጠት የሚለካው ከጉድለት ነው፡፡

በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤ እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና። 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡2-3

ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤ ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው። ማርቆስ ወንጌል 12፡43-44

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ፍቅር የሚለካው ጠላትን በመውደድ ነው፡፡

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ማቴዎስ 5፡44-45

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ትህትና የሚለካው ታናናሾችን በመቀበል ነው፡፡

እውነተኛ ትህትና ሰዎች በሚወድቁበትና በሚደክሙበት ጊዜ መሸከም እና መንከባከብ ነው፡፡

እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው። ማርቆስ 9፡37

 1. እውነተኛ የሚበልጥ እምነት የሚለካው የሚታይ ነገር በሌለ ጊዜ ነው፡፡

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። 2ኛ ነገሥት 3፡17

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ድፍረት የሚለካው በሞት ጥላ መካከል ነው፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡34-35

 1. እውነተኛ የሚበልጥ አምልኮ በእስርና በስቃይ መካከል ነው፡፡

በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ሐዋርያት 16፡23-25

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ጥንካሬ የሚለካው በፈተና ቀን ነው፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። ምሳሌ 24፡10

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ፀጋ የሚለካው በሁለተኛው ምእራፍ ነው

እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡40-41

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ምስጋና በወጀቡ መካከል ማመስገን ነው፡፡

ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡14፣23

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ደስታ በጌታ እንጂ በሁኔታ አይደለም፡፡

ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው። እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ ሐዋርያት 5፡40-41

ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና። ማቴዎስ 5፡11-12

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ሰላም በወጀብ መካከል ነው፡፡

ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ማርቆስ 4፡37-38

አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ፊልጵስዩስ 4፡7

 1. እውነተኛ የሚበልጥ ታላቅነት የሚለካው ለትንንሾች ያለ ዋጋ ከፍተኝነት ነው፡፡

ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ዝቅተኛ ኑሮ ወይም ዝቅተኛ ሥራ ለመሥራት ፍቀዱ ውስጥ ካሉ ጋር አብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ሮሜ 12፡16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #መስጠት #እረፍት #ሰላም #ትህትና #ድፍረት #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ብልጫ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #ፍቅር #መፅሃፍቅዱስ #በደስታ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: