Category Archives: Rest

ከመመላለስ በፊት ማረፍ ይቀድማል

Photo to convey idea of restingለሰው የሚያስፈልገውን ማንኛውም ነገር ሁሉ በአምስት ቀን ውስጥ ከሰራ በኋላ ሰውን እግዚአብሔር የፈጠረው በስድስተኛ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኋላ በሰባተኛው ቀን ከሰው ጋር አረፈ፡፡ ሰው በስድስተኛ ቀን የተፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር በሰባተኛው ቀን እንዲያርፍ ነው፡፡

ሰው የተሰራው ለእረፍት ነው፡፡ ሰው ምንም ነገር ቢሰራ እንኳን የተሰራው በእረፍት እንዲሰራ ነው፡፡ እረፍት ማለት አለመስራት ማለት አይደለም፡፡ እረፍት ማለት አለመባዘን ፣ አለመባከን ፣ አለመጨነቅ ፣ አለመታሰር ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ነው እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ከከፈልልን በኋላ እረፉ የሚለን፡፡

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ማቴዎስ 11፡28-29

ከመስራት በፊት ማረፍ ይቀድማል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው አርፈን በራሱ ምሪትና ሃይል ብቻ እንድንሰራ  ነው፡፡ በራሳችን ሃይልና ጉልበትን እንድንፍጨረጨር አይፈልግም፡፡

ስለዚህ ነው በመንፈሴ እንጂ በሃይልና በብርታት አይደለም የሚለው፡፡

መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ዘካርያስ 4፡6

ሰው የሚያርፈው ተጨማሪ ገንዘብ ሲኖረው አይደለም፡፡ ሰው የሚያርፈው ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚርፈው እግዚአብሄርን ሲያይ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙር 46፡10

ሰው የሚያርፈው በራሱ ከመሮጥ ሲመለስ ነው፡፡ ሰው የማያርፈው በራሱ ከመፍጨር ሲያርፍ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በፀጥታ እግዚአብሄርን ሲመለከት ነው፡፡ ሰው ሃያል የሚሆነው በእግዚአብሄር ሲያርፍ ነው፡፡ ሰው የሚበረታው በእግዚአብሄር ሲታመን ነው፡፡

የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ ኢሳያስ 30፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል

peace.jpgየእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15

እግዚአብሄር እንዲሰራ ሰው ሊያርፍ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ካላረፈ እግዚአብሄር ወይም አይሰራም ቢሰራም ደግሞ እግዚአብሄ እንደሰራ አያስታውቅም፡፡ ሰው ካላረፈ እግዚአብሄር ብቻውን ክብሩን ሊወስድ አይችልም፡፡ ሰው ካላረፈ የሰውና የእግዚአብሄር ክብር ይደባለቃል፡፡

ሰው በእረፍት ሆኖ እግዚአብሄር ሲሰራ ብቻ ነው ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር ክብሩን መስጠት የሚችለው፡፡ ሰው ሳያርፍ ምንም ነገር ቢሆንለት እንኳን “እግዚአብሄር ረድቶኛል እኔም ግን ቀላል ሰው አይደለሁም” ነው የሚለው፡፡

እግዚአብሄር እንድንሰራ እንኳን የሚፈልገው በእረፍት ነው፡፡ ስራችንነን እንኳን አንድንጀምር የሚፈልገው በእርሱ ካረፍን በኋላ ነው፡፡ ከስራ በፊት አንኳን መጀመሪያ በእርሱ እንድናርፍ ይፈልጋል፡፡

ለእግዚአብሄር ምንም ነገር ካደረግንለት እግዚአብሄር አስቀድሞ ሰርቶ እንደጨረሰው በማመን መሆን አለበት፡፡ ወደምድር የመጣነው እንኳን እግዚአብሄር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለመስራት እንጂ ለስራ ፈጠራ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከመስራታችን በፊት በእግዚአብሄር ዘንድ አንደተሰራ አውቀን በምድር ላይ ለማስፈፀም ብቻ እንደሆነ ማወቅ ይገባናል፡፡

ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። ኤፌሶን 1፡4-6

ለእግዚአብሄር ምንም ከማድረጋችን በፊት እንድናርፍ መፈለጉ ብቻ ሳይሆን በስራ መካከል እንድናርፍ ይፈልጋል፡፡

ስንሰራም በእረፍት እንድንሰራ ነው እግዚአብሄር የሚፈልገው፡፡ ሳናርፍ የምንሰራውን ምንም ነገር እግዚአብሄር አይፈልገውም፡፡ ስለፀሎት አንኳን መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር ሳትለምኑት ምን እንምደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል ነው የሚለው፡፡

አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡7-8

ስለዚህ ስንፀልይ እንኳን አዲስን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ልንቆረቁር እንደሆነ ሊሰማን አይገባንም፡፡ በእውነት የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት ከፈለግን አስቀድሞ የተሰራውን ስራ መከተል ብቻ ነው፡፡

ሰለዚህ ነው ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ አባቴ ይሰራል እኔም እሰራለሁ በማለት ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ እነደሚሰራ የሚናገረው፡፡

ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17

እግዚአብሄር በትጋት እየሰራ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራውን ነገር ተረድተን ከእርሱ ጋር አብረን መስራት ከሁሉም የሚበልጥ የተሻለ ነገር ነው፡፡

በማረፍ ከብክነት እንድናለን፡፡ በማረክ አግዚአብሄር በማይዘራበት እንዳንዘራ እንጠበቃለን፡፡ በማረፍ እግዚአብሄር በሌለበት እንዳንሰራ እንጠበቃለን፡፡ በማረፍ ከከንቱ ድካም እንድናለን፡፡

እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ። መዝሙር 127፡1-2

የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እኔም አሳርፋችኋለሁ ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ

rest222.jpgእናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ማቴዎስ 11፡28-30

እግዚአብሄር ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ በአምስት ቀን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሄር በሰባተኛው ቀን ከማረፉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሰውን በስድስተኛው ቀን ፈጠረው፡፡ ሰው የተፈጠረው እንዲያርፍ ነው፡፡ ሰው ዲዛይን የተደረገውና የተሰራው ለእረፍት ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰው ካላረፈ የሚጨነቀውና ፣ የሚጎሳቆለውና የሚታመመው፡፡ አለማረፍ ጤና አይደለም፡፡ አለማረፍ የነገሮች መዛባት ምልክት ነው፡፡

ኢየሱስም ወደምድር ሲመጣ ቃል የገነባው እረፍት ነው፡፡ ወደ ኢየሱስ በመምጣት ከነፍስ ጭንቀትና ከሰቆቃ ህይወት ማረፍ ይቻላል፡፡

ሰው የሚያርፈው በእግዚአብሄር ላይ ሲታመን ብቻ ነው፡፡ ሰው እንዳያርፍ የሚነዘንዙት ነገሮች ዙሪያውን ሳላሉ ሰው በእግዚአብሄር ላይ ካልተደገፈ አያርፍም፡፡

ሰው ለማረፍ በእግአብሄር ላይ ቃል ላይ መታመን አለበት፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል የዋህ ያልሆነ የእግዚአብሄርን ቃል በሞኝነት የማይቀበል ሰው ሊያርፍ አይችልም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመን የሚቸግረው ሰው ሊያርፍ አይችልም፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ የተናገረውን እንዳለ የማይቀበል ሰው ከእረፍት ይጎድላል፡፡

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ማቴዎስ 25፡24-25

እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ያለው አላማ ፍቅር መሆኑ ያልተረዳ ሰው ካለ እረፍት ዘመኑን ይፈጃል፡፡

ወደ ወይን ጠጁም ቤት አገባኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ 2፡4

ለእናንተ የማስባትን ሃሳብ እኔ አውቃለሁና ያለውን እግዚአብሄርን በየዋህነት የማይቀበል ሰው ዘመኑ ይባክናል፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11

የሚያስጨንቃችሁን በእርሱ ላይ ጣሉት እርሱ ስለእናንተ ያስባልና ለሚለው ቃል የዋህ የማይሆን ሰው በዘመኑ ሊያርፍ በፍፁም አይችልም፡፡

ሰው ትሁት ካልሆነ ለእግዚአበሄር አሰራት ጊዜል ካልሰጠ ሊያርፍ አይችልም፡፡

ኢየሱስ የየዋህነትና የእረፍት ምሳሌ ነው፡፡ ኢየሱስ በአብ ተልኮ ራሱን ባዶ አደረገ፡፡ በምድር ላይ በአግዚአብሄር ፊት በሁሉ በሁሉ ትሁት ሆነ፡፡ ለእግዚአብሄር ሃሳብ ሁሉ የዋህ ሆነ፡፡ በእግዚአብሄር ስለታመነ በሁሉ እግዚአብሄርን ታዘዘ፡፡ እስከመስቀል ሞት ድረስ የታዘዘ ሆነ፡፡

ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ማቴዎስ 11፡29

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

እረፍት ከስራ ይቀድማል

rest.jpgሰውን የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው ለአላማው ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሰው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ነገር በአምስት ቀናት ውስጥ ፈጠረ ሰራና አዘጋጀ፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሊያርፍ ሲል በስድስተኛው ቀን ነው፡፡ የመጀመሪያው የሰው ስራ የነበረው እረፍት ነው፡፡ አሁንም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ የሰው የመጀመሪያውና በጣም አስፈላጊው ሃላፊነት ማረፍ ነው፡፡ ያላረፈ ሰው ምንም ሊሰራ አይችልም፡፡ የሰውም ፍሬያማነት የሚለካው በእረፍቱ መጠን ብቻ ነው፡፡

ሰው በህይወት ስኬታማ እንዲሆን ካስፈለገ ማረፍ አለበት፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ካረፈ ብቻ ነው ትርጉንም ያለው ስራ የሚሰራው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ከተደገፈ ብቻ ነው ፍሬያማ የሚሆነው፡፡

ስለዚህ ነው ገና ሃጢያተች ሆነንን ሳለን በሃጢያት ምክኒያት እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተቅበዝብዘን ሳለን ኢየሱስ የሃጢያታችን እዳ ለመክፈል ወደምድር መጣ፡፡ ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሙሉ ለሙሉ እንደከፈለ ተፈፀመ አለ፡፡

ማንም ሰው የእግዚአብሄር አላማ ውስጥ ለመግባት ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው የማዳን ስራ ላይ መደገፍ አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ለማስደሰት በእግዚአብሄር በሚያስችል ሃይሉ በፀጋው ላይ ማረፍ አለበት፡፡

ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። ዕብራውያን 4፡3

ከምንም ስራ ቀዳሚው ማረፍ ነው፡፡ ለምንም ስራ የጉልበት ምንጩ እረፍት ነው፡፡ የምንም የእግዚአብሄር ስራ መመዘኛው እረፍት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ የሚጀመረው ከማረፍ ነው፡፡  በራሳችን ምንም ማድረግ ስለማንችል ስራ ተሰርቶ ሳይሆን የሚታረፈው ታርፎ ነው የሚሰራው፡፡ ፍሬ ለማፍራ በቅርንጫፉ መታመን ይጠይቃል፡፡

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሃንስ 15፡5

ከመስራታችን በፊት እግዚአብሄር አስቀድሞ እየሰራ እንደሆነ ማወቅና ማረፍ አለብን፡፡ እኛ ብቻችንን እንደምንሰራ ካሰብን ስራው ውጤታማ እየሆንም፡፡

ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17

ከመፀለያችን በፊት የሚያስፈልገንን ሳንለምን በፊት እንደሚያውቅ በማመን ማረፍ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡8

የእግዚአብሄርን ስራ ከመስራታችን በፊት ወጪው ሁሉ በእርሱ እንደሆነ በመረዳት ማረፍ ይጠበቅብናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

ለጌታ ስለሰጠን እንደማይጎድልብን እርሱ እረኛችን እንደሆነ በማረፍ ነው፡፡

ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። ሉቃስ 6፡38

ሌላውን ይቅር የምንለውና የምንምረው እግዚአብሄር በእጅጉ እንደማረን ስላወቅንና በምህረቱ እርፍ ስላልን ነው፡፡

 

ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ማቴዎስ 18፡32-33

መልካም የምናደርገው ለመዳን ሳይሆን ስለዳንን መሆኑን በማወቅ ማረፍ ፍሬያማ ያደርገናል፡፡

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 28-10

ሌላውን የምንወደው በራሳችን ጉልበት እንዳይደለ ነገር ግን የእግዚአብሄ ፍቅር በልባችን እንደፈሰሰ በማመንና በማረፍ ካልሆነ አይሳካልንም፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡5

እውነተኛ ስራ እውነተኛ ውጤት እውነተኛ ፍሬ የሚፈራው በማረፍ ነው፡፡ ባረፍን መጠን ብቻ ነው የምንሰራው፡፡ ባረፍን መጠን ብቻ ነው የምናፈራው፡፡ በእምነት ባረፍን መጠን ብቻ ነው ውጤታማ የምንሆነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

 

%d bloggers like this: