Category Archives: Love

ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው

Clip-art-black-and-white-paint-clipart-kid-2.pngእንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና። ማቴዎስ 7፡12

የእግዚአብሄር ትእዛዞች ከባዶች አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄርን ትእዛዞች ማድረግ ከፈለግን ማድረግ እንችላለን፡፡ ማድረግ የማንችላቸው የእግዚአብሄር ትእዛዞች የሉም፡፡ እግዚአብሄር ካዘዘ ማድርገ እንችላለን ማለት ነው፡፡

ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3

የእግዚአብሄር ትእዛዞች ውስብስብና ለመረዳት አስቸጋሪ አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ለመረዳት እና እግዚአብሄርን ለማስደሰት አራት አመት ስነመለኮት መማር የለብንም፡፡

ማንም ሰው የእግዚአብሄርን ትእዛዝ መረዳት ይችላል፡፡

ለምሳሌ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ ማቴዎስ 22:39 የሚለውን ትእዛዝ ለመረዳት ሰው ብዙ ቦታ መውጣት መውረድ የለብንም፡፡ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደደ የሚለውን ትእዛዝ ለመረዳት ሰው ራሱን እንደ እንደሚወድ መመለከት በቂው ነው፡፡ ሰው ራሱን አይጠላም፡፡ ሰው ለራሱ ክብር አለው፡፡ ሰው ራሱን ይወዳል፡፡

ትእዛዙ ታዲያ ለራስህ ክብር እንዳለህ ለሌላው ክብር ይኑርህ ነው፡፡ ትእዛዙ ለራስህ ፍቅር እንዳለህ ለሌላው ፍቅር ይኑርህ ነው፡፡

ሰው እንዲያከብርህ እንደምትፈልገው ሁሉ ሰውን አክብር፡፡ ሰው እንዳይንቅህ እንድምትፈልገው ሁሉ ሰውን አትናቅ፡፡ ሰው እንዲሰማህ እንደምትፈልገው ሁሉ ሰውን ስማ፡፡ ሰው እንዲያዋርድህ እንደማትፈልገው ሁሉ ሰውን አታዋርድ፡፡ ሰው እንዲያማህ እንደማትፈልገው ሁሉ ሰውን አትማ፡፡ ሰው በችግርህ እንዲረዳህ እንደምትፈልግ ሰውን በችግሩ እርዳ፡፡ ሰው እስከድካምህ እንዲቀበልህ እንደምትፈልግ ሰውን እስከድካሙ ተቀበል፡፡ ሰው ሊያደርግልህ የምትፈልገውን ለሰው አድርግ፡፡

ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው። ሉቃስ 6፡31

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መውደድ #የህግፍፃሜ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዲዛይን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ራስንመውደድ #መንፈስቅዱስ #ራስንማክበር #ልብ #መሪ

Advertisements

ከጥላቻ ተጠበቁ

hate1.jpgእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው ዲዛይን የተደረገው ለፍቅር ህይወት ነው፡፡

ፍቅር ስለሰው መልካም ማሰብ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ነው፡፡

ሰው በፍቅር ሲኖር እግዚአብሄር የፈጠረውን አላማ ስለሚፈፅም ደስተኛ ይሆናል፡፡ ሰው በፍቅር ሲኖር እግዚአብሄር ስለሚረዳው በእግዚአብሄር እርዳታ መንገዱ ይቀልለታል፡፡

ሰው በጥላቻ ሲኖር ግን ህይወቱ ያልተነደፈበትንና ያልተሰራበትን ስራ ስለሚሰራ ህይወቱ ይጨልማል፡፡

ጥላቻ ከማንም በላይ የሚጎዳው የሚጠላውን ሰው ነው፡፡ እንዲያውም ጥላቻ ሌላውን ይገድልኛል ብሎ ራስ መርዝ እንደመጣጣት ነው የሚባለው፡፡

በጥላቻ የሚኖር ሰው በጨለማ ይሄዳል፡፡ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ። ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። 1ኛ ዮሐንስ 2፡9-11

ጥላቻ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ በጥላቻም የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ሰውን መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ሌላ አላማ የለውም፡፡ ሰይጣን ጥላቻ ውስጥ ካስገባን በቀላሉ አላማውን ይፈፅማል፡፡ ከጥላቻ ራሱን ያልጠበቀ ሰው ለዲያብሎስ ፈንታ ሰጥቶት ለምን ሰይጣን በህይወቴ ሰረቀ ፣ አረደና አጠፋ ማለት አይችልም፡፡

በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡27

ሰይጣን የመስረቅ የማረድና የማጥፋቱን አላማ የሚያሳካው በሰዎች ውስጥ ጥላቻን በመጨመር ነው፡፡ በሰው ውስጥ የጥላቻን ሃሳብ ካልጨመረ በስተቀር ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ አይችልም፡፡ ሰይጣን ከጥላቻ ራሱን በሚጠብውቅ ሰው ህይወት ውስጥ እንዳች እድል ፈንታ አይኖረውም፡፡

ኢየሱስ የበደሉትን እንኳን ይቅር በማለት ህይወቱን ከጥላቻ ይጠብቅ ስለነበር ይህንን አለ፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30

ሰይጣን በሰው ውስጥ ጥላን ከጨመረ ደግሞ የማያሰራው ክፋት የለም፡፡ ጥላቻ ላለበት ሰው መግደል ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ ነው መፅጽሃፍ ቅዱስ ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው የሚለው፡፡

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡14-15

ማንንም ሰው እንድንጠላ አልተፈቀደልንም፡፡ ልንጠላው የሚገባው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የሚመጣውን ሰይጣንነ ብቻ ነው፡፡ እንድንጠላው የሚገባው ሰዎችን ክፋት የሚያሰራውን ሰይጣንን ብቻ ነው፡፡ ልንጠላው የሚገባው ውሸታምና የውሸት አባት የሆነውን በውሸት ሰዎችን የሚያጠላላውን በጥላቻ የሚያገዳድለውን ሰይጣንን ብቻ ነው፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥላቻ #ውሸት #ግድያ #ሰይጣን #ሊሰርቅ #ሊያርድ #ሊያጠፋ #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ

LOVE GOD.jpgመምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማቴዎስ 22፡36-38

እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡

እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለአላማው ነው፡፡

እግዚአብሄር ከምንም ነገር በፊት እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንሰማው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንፈልገው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንፈራው ይፈልጋል፡፡

ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15

እግዚአብሄር ከራሳችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ራሳችንን ከእርሱ እንድናስቀድም አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ስለእርሱ ነፍሳችንን እንድንክድ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከደስታችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምኞታችን በላይ እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከፍላጎታችን በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡

ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡26

እግዚአብሄር በህይወታችን ሁለተኛ መሆን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ከሌላ ነገር ጋር መዳበል አይፈልግም፡፡

ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ማቴዎስ 10፡37

እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድናስቀድመው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ነገር በላይ እንድንወደው ይፈልጋል፡፡

መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማቴዎስ 22፡36-38

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #በፍፁምልብ #በፍፁምሃሳብ #በፍፁምነፍስ #በፍፁምሃይል #መውደድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የፍቅር ባርነት

LOVE ONE.jpgክርስቶስ በፍቅር ለእኛ መዳን እና መለወጥ የባሪያን መልክ ያዘ፡፡ ክርስቶስ በፍቅር ለመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ፡፡

ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡7-8

ክርስቶስ የፍቅርን ምሳሌ ትቶልናል፡፡ ክርስቶስ እንደወደደን በፍቅር ልንመላለስ ይገባል፡፡

ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፡2

ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠን እኛም ስለወንድሞቻችን ራሳችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባል፡፡

እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። 1ኛ ዮሐንስ 3፡16

ክርስቶስ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል፡፡

እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ። ዮሃንስ 13፡34

ጳውሎስ ለክርስቶስ ቤተክርስትያን አገልግሎት በፍቅር በሙሉ ፈቃደኝነት ራሱን ባሪያ አድርጎ ሰጠ፡፡

ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ሮሜ 1፡1-2

በታላቅ ፍቅር ተወደናል፡፡ እርሱ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባናል፡፡

እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሃንስ 15፡12-13

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ፋሲካ #ትንሳኤ #ስቅለት #በዓል #መስዋእት #ቤዛነት #መቤዠት #የሚበልጥ #ፍቅር #ተስፋ #ደስታ #መስዋእት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም

the cross.jpgነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐንስ 15፡13

ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡6-8

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡4-5

ስለዚህ ከዚህ በላይ የሚቀርብ መስዋእት የለም፡፡

የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም። ዕብራውያን 10፡18

ስለሃጢያታችን አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዋትን አድርጎዋል፡፡

እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ዕብራውያን 7፡27

ይህንን ታላቅ መዳን መዳን ቸል ብንለው፥ አናመልጥም፡፡

በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡2

ይህንን እውቀት ካወቅን በኋላ ወደን ሃጢያት ብናደርግ ከዚህ በኋላ የሃጢያተ መስዋእት አይኖርም፡፡

የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ ዕብራውያን 10፡26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ፋሲካ #ትንሳኤ #ስቅለት #በዓል #መስዋእት #ቤዛነት #መቤዠት #የሚበልጥ #ፍቅር #ተስፋ #ደስታ #መስዋእት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

የጐመን ወጥ በፍቅር

peace1.jpgየጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡17

ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለሰላም ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሰላም እብሮ እንዲኖር ነው፡፡ ስው የተፈጠረው በፍቅር ተጋግዞ እንዶኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሰላም ተረዳደቶ እንዶኖር ነው፡፡

ሰው ለጥል አልተፈጠረምን፡፡ ሰው ለረብሻ አልተፈጠረም፡፡ ሰው ለመነካከስ አልተፈጠረም፡፡

ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ ሰላምን ከረብሻ የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ ፍቅርን ከጥላቻ የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ

ፍቅር የሌለው ሰው ሃብት ቢኖረው ምንም አይጠቅመውም፡፡ ሰላም የሌለው ሰው ሃያል ቢሆን ምንም አይጠቅመውም፡፡ እረፍት የሌለው ሰው ጥበብ ቢኖረው ምንም አይጠቅመውም፡፡

ስለዚህ ነው ሰው ከረብሻ ከሃብታምነት ይልቅ ሰላምን የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ውዝግብ ዝና ይልቅ እረፍትን የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ከእረፍት የለሽ ጥበብ ይልቅ እርካታን የሚመርጠው፡፡

የእግዚአብሄር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች ሃዘንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም፡፡

የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም። ምሳሌ 10፡22

እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል። የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡16-17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ፍቅር #ጥል #በረከት #ጎመን #ፍሪዳ #ሰላም #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #እረፍት

ካለ ምክኒያት ወደህ በምክንያት አትጠላም

6360181766387696171264015521_image5.jpgእግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ። ኤርምያስ 31፡3

እግዚአብሄር ፍቅር ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የሚወደው ደግሞ እየመረጠ በምክኒያት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚወደን የምንወደድ መልካም ሰዎች ስለሆንን አይደለም፡፡

እግዚአብሄር የሚወደን ካለ ምክንያት ነው፡፡ ምኔን ነው የወደድከው? ምኔ ነው የሳበህ? የቱ ነገሬ ነው ደስ ያለህ እና የወደድከኝ? ተብሎ እግዚአብሄር ቢጠየቅ በዚህ ነው ብሎ የሚመልሰው ምንም ነገር የለም፡፡ ለምን ወደድከኝ ሲባል እንዲሁ ወደድኩህ ነው የሚለው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16

እግዚአብሄር የወደደን በማንወደድበት ጊዜ ነው፡፡ እግዚአብሄር የወደደን በንፅህናችንና በቅድስናችን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የወደደን ጠንካሮች ሆነን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የወደደን ደካሞች ሳለን ነው፡፡ እግዚአብሄር የወደደን ሃጢያተኞች ሆነን ነው፡፡

ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ሮሜ 5፡6

እግዚአብሄር የወደደን ጠላቶች ሆንነ ነው፡፡ እግዚአብሄር የወደደን እግዚአብሄርን የማንፈልግ ተሳዳቢዎች ሆነን ነው፡፡ (ሮሜ 3፡10-19)

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8

እግዚአብሄር ምንም የሚወደድ ነገር ሳይኖረን ካልጠላን እና ከወደደን አሁንም እኛን የሚጠላበት ምንም ምክኒያት አይኖረውም፡፡

የእግዚአብሄር ፍቅር በእኛ ሁኔታ ላይ የተደገፈ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር እንደፍቅር ተቀባዩ እና እንደ ተወደደው ሰው አይለዋወጥም፡፡

እግዚአብሄር ታማኝ አፍቃሪ ነው፡፡ ሰው ፍቅሩን ቢቀበለውም ባይቀበለውም እግዚአብሄር የዘላለም አፍቃሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር በፍቅር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ሰው ቢቀበልም ባይቀበለም ፍቅሩን ተቀብሎ ቢድንም ባይድንም የሰው ሃላፊነት እንጂ የእግዚአብሄር ሃላፊነት አይደለም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ፍቅር ተጠቅሞ ከዘላለም ጥፋት ቢያመልጥም ባያመልጥም የስው ጥፋት እንጂ የእግዚአበሄር አለመውደድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የዘላለም አፍቃሪ ነው፡፡

ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡13

ካለምክኒያት ከወደደ አሁን ደግሞ ሃሳቡን ለውጦ በምክኒያት አይጠላም፡፡ ስለዚህ ነው ዘማሪ ሃና_ተክሌ ካለ ምክኒያት ወደህ በምክኒያት አትጠላም በማለት በአራት ቃላት የእግዚአብሄርን የማይለወጥ ፍቅር በዝማሬ የገለጠችው፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምክንያት #ያለምክንያት #እንዲሁ #የዘላለም #ታማኝ #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ

የፍቅር ምንጭ

isnt love.jpgበተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡8

ስለ ፍቅር ክብር ስናጠና ፍቅር እጅግ የከበረ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሄር እንኳን ፍቅር ነው በሚል ነው የተገለፀው፡፡ ስለፍቅር ክብር ስናስብ ይህ ፍቅር የሚባለው ነገር ይቻል ይሆንን ብለን ልናስብ እንችላለን፡፡

ፍቅር ይቻላል፡፡ ፍቅር የሚቻለው በእኛ አይደለም፡፡ በራሳችን ፍቅርን ማድረግ አንችልም፡፡ በበራሳችን ጉልበት በፍቅር መኖር አይታሰብም፡፡

ፍቅር እግዚአብሄር ነው፡፡ የፍቅር ምንጩ እግዚአብሄር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተወደደ ሰው ብቻ ነው በፍቅር የሚኖረው፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር ያልተረዳ ሰው ፍቅር ሊኖረው አይችልም፡፡ በእግዚአብሄር እንደተወደደ የማያውቅ ሰው ፍቅር ለእርሱ እንግዳ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተወደደ ሰው ሰውን ሊወድ ይችላል፡፡ ከእግዚአብሄር ፍቅርን የተቀበለ ሰው ለሌላው ፍቅርን ሊሰጥ ይችላል፡፡ የተወደደ ሰው ለመውደድ ጉልበትን ያገኛል፡፡

በእግዚአብሄር የሚኖር በፍቅር ይኖራል ፡፡ በፍቅር የማይኖር እግዚአብሄርን አላየውም አላወቀውም፡፡

በእኛ ዘንድ ፍቅር ከተገኘ ምንጩ እግዚአብሄር ነው፡፡

ከእግዚአብሄር የሆነ ሰውና ከእግዚአብሄር ያልሆነ ሰው የሚለየው በፍቅር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተነካ ሰውና ያልተነካ ሰው የሚያስታውቀው በፍቅር ነው፡፡ በእግዚአብሄር የተለወጠ ሰውና ያልተለወጠ ሰው የሚታወቀው በፍቅር ነው፡፡

ማንኛውም አካሄዳችን ከእግዚአብሄር ይሁን አይሁን መመዘኛው በፍቅር መደረጉና አለመደረጉ ነው፡፡ በፍቅር የተደረገ ነገር ሁሉ ከእገዚአብሄር ነው በፍቅር ያልተደረገ ነገር ሁሉ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡8

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ

ፍቅር የሚፈተነው

love love.jpgሰው ሁሉ ፍቅር ያለው ይመስላዋል፡፡ በሰላም ጊዜ ፍቅር ይቀላል፡፡ ነገር ሲጠነክር ጥሎ የሚጠፋ ፍቅር ፍቅር አይደለም፡፡ ነገር ሳይመች የሚተው ፍቅር አይደለም፡፡ መንገድ ሲያስቸግር የሚለይ ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነትና ተራ ስሜት ነው፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። ምሳሌ 24፡10

ፍቅር ግን በሁኔታዎች ውስጥ ይፈተናል፡፡ ፍቅር የሚፈተንባቸው ሶስት መንገዶች፡-

  1. ፍቅር የሚፈተነው ለመውደድ ምክኒያት ስናጣ ነው፡፡

ፍቅር የሚፈተነው የምንወደው ሰው ሲለወጥ ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው የምንወደው ሰው ሲጠላን ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው ምንም ያህል ብንወደው የምንወደው ሰው ሳይረዳ ሲቀር ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው እየወደድነው ምንም እንዳልተፈጠረ ሲሆን ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው ለፍቅራችን ምላሽ ስናጣ ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው ለፍቅራችን ምላሽ ጥላቻ እና መገፋት ሲሆን ነው፡፡ የዚያን ጊዜ የሚጠፋ ፍቅር ፍቅር ሳይሆን ተራ ስሜት ነው፡፡ የዛን ጊዜ የሚቀጥል ፍቅር ተፈትኖ የወጣ እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡ ሁኔታዎችን ሳያይ መልካምን በማድረግ የሚቀጥል ፍቅር እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡ ሰው ክፉ አለመለካከቱን ሲያሳየን መልካም አመለካከትን የምናሳይ ከሆነ እውነተኛ ፍቅር አለን፡፡ በመልካም የምናሸንፍ እንጂ በክፉ የምንሸነፍ ካልሆነ ያ እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡

ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ሮሜ 12፡20-21

  1. ፍቅር የሚፈተነው ጊዜው እየሄደ ሲሄድ ነው

ስሜት ተለዋዋጭ ነው፡፡ ስሜት አይቆይም፡፡ ስሜት አይዘልቅም፡፡ ስሜት አይፀናም፡፡ ፍቅርንና ስሜትን ለመለየት ጊዜ መስጠት ወሳኝ ነው፡፡ ፍቅር የምንለው ነገር በራሱ እየቀነሰ ከሄደ ፍቅር ሳይሆን ስሜት ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር እየጨመረ እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡ እውነት ነው ፍቅር ትጋትን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ስራን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ማስተዋልና ጥበብን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር በየጊዜው መነቃቃትን ይጠይቃል፡፡ ይህ ሁኔታ ከተሟላ ፍቅር እየጨመረ እየጨመረ ነው የሚሄደው እንጂ እውነተኛ ፍቅር እየቀነሰ አይሄድም፡፡

ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፤ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል። መኃልየ መኃልይ 8፡7

  1. ፍቅር የሚፈተነው በችግር ጊዜ ነው፡፡

ፍቅር የሚፈተነው በዝቅታ ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው የምንወደው ሰው የምንወደው በአንድና በአንድ ምክኒያት ብቻ ሲሆን ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው የምንወደውን ሰው የምንወደው መውደድ ሃፊነታችን እንደሆነ ስንረዳ ብቻ ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው ከሌላው ወገን የምንጠቀመው ምንም ነገር ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው የምንወደው ሰው ሲደክም ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው በህይወቱ የምንወድለት ምክኒያት ሲጠፋ ነው፡፡ ፍቅር የሚፈተነው መግባባት ሲጠፋ ነው፡፡

በፍቅረኞች ቀን አካባቢ ሰውን መውደድ ሊቀል ይችላል ነገር ግን ሰውን በዝቅተኛ የህይወቱ ደረጃ ላይ መውደድ ግን እውነተኛ ፍቅርን ይጠይቃል፡፡ እውነተኛ ፍቅር ሌላውን በመረዳት መሸከም ይጠይቃል፡፡

ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። 1ኛ ዮሐንስ 4፡10

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ

ፍቅር አይደለም

isnt love.jpgእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በፍቅር ነው፡፡ የተፈጠርነው ለመውደድና ለመውደድ ነው፡፡ የተፈጠርነው በእግዚአብሄርና በሰው ለመወደድና እግዚአብሄርንና ሰውን ለመውደድ ነው፡፡ ፍቅር በህይወታችን በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ፍቅር የሚለው ቃል ለብዙ ነገሮች ስለሚጠቅም በጣም ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡

አንድን ነገር ምን እንደሆነ ለመግለፅ ምን እንዳልሆነ መግለፅ ይበልጥ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ፍቅር ምን እንደሆነ ለመግለፅ ፍቅር ምን እንዳይደለ መግለፅ ለፍቅር ትርጉም ይበልጥ ተጨማሪ መረዳት ይሰጠዋል፡፡

ብዙ ሰዎች ፍቅር የሚመስላቸው መልካም ነገር ማግኘት ሳይሆን መልካም ነገር ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር መልካም ለመጠቀም መልካም አጋጣሚ ሳይሆን ለመጥቀም መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

ፍቅር በሰው መጠቀም አይደለም፡፡

ፍቅር በሰው መጠቀም አይደለም፡፡ ፍቅር የሰውን ጥንካሬና እድል ተጠቅሞ መለወጥ አይደለም፡፡ ፍቅር ሰውን መጥቀም ነው፡፡ ፍቅር ሰውን ማነሳት ነው፡፡ ፍቅር ሰውን መርዳት ነው፡፡ ፍቅር ሰውን እድለኛ ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር ሰውን የተመረቀ ማድረግ ነው፡፡

ፍቅር ከሰው መውሰድ አይደለም፡፡

ፍቅር መውሰድ አይደለም፡፡ ከሰው የሆነ የሚጠቅም ነገር አይቶ ለመውሰድ መጠጋት ፍቅር አይደለም፡፡ ከሰው ለመውሰድ አላማ ሰውን መጠጋት ብልጠት እንጂ ፍቅር አይደልም፡፡

ፍቅር የራስ ፍላጎትን ማሟላት አይደለም፡፡

ፍቅር የራስን ፍላጎት ማሟያ አይደለም፡፡ ፍቅር የሌላውን ፍላጎት ያማከለ ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን መጥቀም ላይ ያተኩራል፡፡

ፍቅር የሰውን ድካም ተጠቅሞ መጠቀም አይደለም፡፡

ፍቅር የሰውን ድካም ይሸከማል፡፡ ፍቅር የሰውን ድካም ይሸፍናል፡፡ ፍቅር የስውን ድካም አያይም ያልፋል፡፡

ፍቅር ያጠፋን አውጥቶ መጣል አይደለም፡፡

ፍቅር የተሻለን ሰው መፈለግ አይደለም፡፡ ፍቅር ሲመች ሲመች አብሮ መሆን አይደለም፡፡ ፍቅር የደከመን አውጥቶ መጣል አይደለም፡፡ ፍቅር ከደካማ ጋር አብሮ መኖር ነው፡፡ ፍቅር ከማይመች ጋር አብሮ መሄድ ነው፡፡ ፍቅር የማይመስለንን ሰው መታገስ ነው፡፡

ፍቅር መታደል አይደለም፡፡

ፍቅር ሌላውን እድለኛ ማድረግ ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማንሳት ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማንሳት ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን ማሻገር ነው፡፡

ፍቅር ከሌላው ጋር ራስን በመረዳት ማስተባበር ነው፡፡

እግዚአብሄር በድካማችን ከእኛ ጋር ራሱን አስተባበረ፡፡

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መስጠት #ማካፈል #ልብ #መሪ

%d bloggers like this: