Category Archives: salvation

የማዳንህን ደስታ ስጠኝ

church leader.jpgየማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። መዝሙር 51፡12

እግዚአብሄር እኛን ለማዳን ሳይራራ አንድያ ልጁን ከፍሎዋል፡፡ ስለመዳናችን እጅግ ታላቅቅ ዋጋ ተከግፍሎዋል፡፡ መዳመናችንም ታላቅ ነው፡፡

ስለመዳናችን የምንሰማውን ነገር ልንጠነነቀቅ ይገባናል፡፡ መዳናችንን የሚያሳንስ ነገር የምንሰማ ከሆነ ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ነው፡፡ ከምንም ነገር በላይ መዳናችንን ቸል ለንለው አይገባንም፡፡ ስለመዳናችን እግዚአብሄርን በየጊዜው እንደ አዲስ ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል። በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡2

የዳንነው ከሞት ነው፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንስ 5፡24

የዳንነው ለዘላላም ከእግዚአብሄር ጋር ከመለያየት ነው፡፡

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ማቴዎስ 25፡41

የዳንነው ከጨለማው ስልጣን ነው፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2

የዳንነው የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ ከመኖርና ህይወትን ካለማየት አሰቃቂ ህይወት ነው፡፡ የፈለስነው ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት  ነው፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

ይህንን መዳን የሚገባውን ስፍራ ካልሰጠነው ፣ ይህን መዳን ስናቃልልና ይህ መዳን ሲያንስብን በክርስትና ህይወታችን ሁሉ ነገራችን ይዛባል፡፡

ይህን ታላቅ መዳን በራሱ እንደሃብት ሳይሆን ግን እንደ መተላለፊያ ብቻ ስንቆጥረው ህይወታችን ይዛባል፡፡ ይህን መዳን በራሱ ታላቅ እድል እንደሆነ ስንረሳና እንደ ማትረፊያ መንገድ ብቻ ስናየው ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡

በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡4-5

ይህን መዳን ስናከብረው በመዳናችን ደስ ስንሰኝ እግዚአብሄርን እንደሚገባው ማክበር እንችላለን፡፡ በዚህ መዳን ሳናቋርጥ ደስ ስንሰኝ ህይወታችን ሁሉ በምስጋና ይለመልማል፡፡ ይህን ታላቅ መዳን ስናከብረው በሁሉ ነገር እግዚአብሄርን በደስታ እንታዘዘዋለን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #ደስታ #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ

one way1.jpgኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15

የሰው መንገድ በምርጫ የተሞላ ነው፡፡ ዛሬ የምንኖረው ኑሮ ትላንት የመረጥነውን ምርጫ ውጤት ነው፡፡ ወደፊት የምንኖረው ኑሮ ዛሬ የመረጥነውን ምርጫ ውጤትን ነው፡፡

ሰው በህይወቱ ዘመን ሁሉ በምድር ላይ ብዙ ምርጫ መምረጥ ቢጠበቅበትም እንደዚህ ያለ የወደፊት ህይወቱን ሁሉ የሚወስን ምርጫ ግን የለም፡፡

አንዳንድ ምርጫ በገንዘባችን ላይ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሌላው ምርጫ በዝናችን ላይ ታላቅ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ሌላው ደግሞ በጥበባችን ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊን ተጽፅእኖን ያመጣል፡፡ ሌላውም በሃይላችን ላይ ተፅእኖ በማሳደር በምድር ላይ ሃያል እንድንሆን ወይም እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ምርጫዎች ተፅእኖ የሚያደርጉት የምድር ህይወታችንን ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን በምድርም ከምድር ህይወት በስቲያም ህይወታችን ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ወሳኝ ምርጫ አለ፡፡ ሰው በምድር ላይ ሲኖር በሌላ ምርጫዎች እንኳን ቢሳሳት በዚህ ምርጫ ግን መሳሳት የለበትም፡፡ ሰው በምድር ላይ ሲኖር በሌላ ምርጫዎች የሚሳተው መሳሳት በዚህ መርጫ እንደሚሳሳተው መሳሳት አይከፋም፡፡ ሰው በሌላ ምርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የምድር እጦት ብቻ ነው፡፡ ሰው በምድር ምርጫዎች ቢሳሳት የምርጫው ውጤት በምድር ላይ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡

ሰው ግን በዚህ መርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የምድርን ቢያጠቃልልም የምርጫው ውጤት በምድር ላይ ብቻ አያበቃም፡፡ ሰው በዚህ ምርጫ ቢሳሳት ውጤቱ በምድርና ከምድር ህይወት በኋላም ይቀጥላል፡፡ ሰው በዚህ መርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የማይቀለበስ የዘላለም ነው፡፡ ሰው በዚህ መርጫ ቢሳት ውጤቱ ለዘላለም ከእግዚአብሄር መለያየትን ያመጣል፡፡

ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #የታመነ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ኢየሱስ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

#ኢየሱስ

#ኢየሱስ.jpgየገና በአል ትርጉም የተረሳ ይመስላል፡፡ የገና በአል ሲታሰብ መብላት ከታሰበ ፣ የገና በአል ሲታሰብን መጠጣት ከታሰበ ፣ የገና በአል ሲታሰንብ መልበስ ከታሰበ ፣ የገና በአል ሲታሰብ የገና ዛፍ ከታሰበ የገና በአል ሲታሰብ ከረሜላ እና ቸኮሌት ከታሰበ ፣ የገና በአለ ሲታሰብ ጣፋጭ ብስኩትና ኬክ ከታሰበ ፣ የገና በአል ሲታሰብ እረፍትና መዝናናት ከታሰበ ፣ የገና በአልዕ ሲታሰብ ዘፈንና ዳንራ ከታሰበበ ፣ የገና በአል ሲታሰብ መጠጣትና መስከር ከታሰበ ምንም ሃይማኖተኛ ብንሆን የገናን ትርጉም አናውቀውም ማለት ነው፡፡

ገና የሚበላበት የሚጠጣበት የሚዘፈንበት የሚጨፈርበት አይደለም፡፡ ገና እግዚአብሄር ለሰዎች የሰጠው ስጦታ ኢየሱስ የሚዘከርበት እግዚአብሄር የሚመሰገንበትና በስጦታው ምክኒያት ያገኘነው የክርስትና ነፃነት በአል የሚደረግበት ጊዜ ነው፡፡ ገና የእግዚአብሄርን ስጦታ የማክበርበት ጊዜ ነው፡፡ ገና የእግዚአብሄርን ስጦታ የምናጣጥምበት ጊዜ ነው፡፡

የገና ምክኒያት ኢየሱስ ነው፡፡

ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ማቴዎስ 1፡21

የገና ምክኒያት እግዚአብሄር ለሰው ልጆች ስጦታ መስጠቱ ነው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16

የገና ምክኒያት ስጦታውን የተቀበሉ ከሃጢያት መዳናቸው ነው፡፡

እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ቲቶ 3፡5

የገና በአል በእግዚአብሄር ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃችን ነው፡፡

እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19

የገና በአል ኢየሱስን የተቀበልን የእግዚአብሄር ልጅ መሆናችን ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ገና #በዓል #ፍቅር #ተስፋ #ደስታ #መስዋእት #ሃጢያት #መዳን #ነፃነት ## #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #ኢየሱስ #ጌታ

ሰበብ የለም

excuse.jpgከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡6-10

እግዚአብሄር ሰውን ያውቀዋል፡፡ እግዚአብሄር የሃጢያትን እዳ ሁሉ በኢየሱስ ከከፈለ በኋላ ሰው ግን ላለመዳን ምክኒያት እንደሚፈልግ ያውቀዋል፡፡ ሰው ቀላል የሆነውን ነገር እንዴት እንደሚያወሳሰብና የማይቻል እንደሚያደርገው እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ስለዚህ ነው እንዲህ ተብሎ የተፃፈው፡፡

በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል ሮሜ 10፡6-7

ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ፣ ከዘላለም ፍርድ መዳን ፣ የዘላለም ህይወት ማግኘት ከባድ አይደለም፡፡ መዳን የአመታት ስራ አይጠይቅም፡፡ መዳን የአመታት ጥረት ፣ ትጋትና ጉስቁልና አይጠይቅም፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያት እዳችንን ሁሉ ስለከፈለ ለመዳን የሚጠበቅብን ነገር የደህንትን ነፃ ስጦታ በእምነት መቀበል ብቻ ነው፡፡

የቃሉ ማስጠንቀቂያ እነዲህ ይላል መዳን እንደ ሰማይ የራቀ ነው አትበል፡፡ እንዲሁም መዳን እንደ ጥልቅ ሩቅ ነውም አትበል፡፡ ለመዳን ሰበብ አይኑርህ፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው ማንኛውም ምክኒያት በቂ አይደለም፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው የቱም ምክኒያት ሰንካላ ምክኒያት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ፈፅሞ ከከፈለ በኋላ ላለመዳን ለምናቀርበው ማንኛውም ምክኒያት ጆሮ የለውም፡፡

እግዚአብሄር መዳንን እጅግ አቅርቦታል፡፡ ለመዳን እጅግ ዋጋ ቢከፈለምና መዳን እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው ቢሆንም እግዚአብሄር ለእኛ ግን መዳንን ቀላል አድርጎታል፡፡

በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ሮሜ 10፡8

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10

ኢየሱስን እንደአዳኝና ጌታ አሁኑኑ መቀበል ከፈለጉ ይህን ፀሎት አብረው ይፀልዩ

እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በኢየሱስ የሃጢያቴን እዳ ሁሉ ስለከፈለክ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለሰጠኸኝ የደህነት ነፃ ስጦታ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ከሙታን እንዳስነሳው በልቤ አምናለሁ፡፡ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #ነፃስጦታ #ፀጋ #ሞት #የዘላለምህይወት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ብትመሰክር #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ብታምን #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሰዎች ለምን መዳን አይፈልጉም?

question2.jpgብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ስለሃጢያታቸው በመስቀል ላይ የከፈለላቸውን ዋጋ ለእኔ ነው በማለት ጌታን ለመከተል ይወስናሉ፡፡ እግዚአብሔርም በኢየሱስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ስለተቀበሉ ልጆች አድርጎ ወደ ቤተሰቡ ይቀበላቸዋል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ግን ቢያንስ ቢያንስ እስካሁን ኢየሱስን አልተቀበሉም፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተቀብለው የማይድኑበትን ምክኒያቶች እንመልከት፡-

 1. ሰዎች የደህንነት ነፃ ስጦታነት ስለማይረዱት ነው፡፡

እግዚአብሄር በነፃ ሊያድናችሁ ይፈልጋል ሲባሉ በጣም የተጋነነ ከእውነት የራቀ አባባል ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ ነፃውን ስጦታ ከመቀበል ይልቅ በራሳቸው ስለሃጢያታቸው ዋጋን ለመክፈል መልካምን ለማድረግ በዚያም ደህንነትን ለማግኘት ይጥራሉ፡፡ ሃጢያተኛ ሰው በቅዱሱ በእግዚአብሄ ፊት መልካምን ነገር በማድረግ ስለሃጢያቱ ዋጋን ሊከፍል አይችልም፡፡ ሰዎች ግን በራሳቸው ለሃጢያታቸው ዋጋ ለመክፈል ከፈለጉ ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ነው የሚከፍሉት፡፡ ስለሃጢያት ሊከፍል የሚችለው ሰው ሃጢያት ያልሰራ ብቻ ነው፡፡ ሃጢያት የሌለበት ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ፈፅሞ ከፍሎዋል፡፡ እኛ መክፈል አንችልምም አይገባንምም፡፡ እኛ ማድርግ የሚገባን በእምነት ይህንን ስጦታ መቀበል ብቻ ነው፡፡

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9

 1. አንዳንድ ሰዎች የደህንነትን መልእክት የማይቀበሉት ለደህንነት የሃይማኖት ስርአትን መፈፀም የሚበቃ ስለሚመስላቸው ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ የማይቀበሉት የአንድ ሃይማኖት ተከታይ መሆን የሚያድን ስለሚመስላቸው ነው፡፡ እውነተኛ ሃይማኖት ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት መስዋእትነት የሚሰብክ ነው፡፡ ያንን እግዚአብሄር ያዘጋጀውን ብቸኛ የመዳኛ መንገድ መቀበል እንጂ የሃይማኖት ስርአትን መፈፀም ብቻ ማንንም ሊያድን አይችልም፡፡ የሃይማኖትን ስርአት መፈፀም የሚያድን ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ ወደ ሃይማኖተኞች መጥቶ ስለ ዳግመኛ መወለድ አይሰብክላቸውም ነበር፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3

በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ያለን ሰው ኢየሱስ ካላዳነው የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ በራሱ አያድነውም፡፡ የኢየሱስን አዳኝነት ከመቀበል ውጭ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይነት ለመዳን በቂ አይደለም፡፡

 1. አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት ሃጢያትን ስለሚወዱ ነው፡፡

ሰዎች ኢየሱስን መከተል የማይፈልጉት ሃጢያትን ስለሚወዱ ነው፡፡ በሃጢያት የሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ የዘላለም ህይወትን ያሳጣቸዋል፡፡ በሃጢያት ስለሚገኝ ደስታ በጌታ ኢየሱስ የሚገኘውን ሰላምና እረፍት ይለውጡታል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን እንዲቀበሉ ሲነገራቸው ብዙ ምክኒያት የሚዘረዝሩት በጨለማ ስለሚመላለሱና ወደብርሃን መውጣት ስለማይፈልጉ ነው፡፡

ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ዮሃንስ 3፡19-20

 1. አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት በመልካም ባህሪያቸው ስለሚመኩ ነው

አንዳንድ ሰዎች የደህንነትን መልእክት የማይቀበሉት ደህንነት የባህሪ ለውጥ ስለሚመስላቸው ነው፡፡ “እኔ በተቻለ ህሊናዬን ጠብቄ እኖራለሁ ስለዚህ ምንም አያስፈልገኝም” ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ደህንነት የባህሪ ለውጥ ሳይሆን የመጥፋትና የመዳን ጉዳይ ነው፡፡ ደህንነት ጥሩ ሰው የመሆን ጉዳይ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ለዘላለም መለያየትና ከእግዚአብሄር ጋር   የመታረቅ ጉዳይ ነው፡፡ ደህነንነት የመልካም ስነምግባር ጥሪ ሳይሆን የሞትና የህይወት ምርጫ ጥሪ ነው፡፡

ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 1ኛ ዮሃንስ 5፡12

ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ሮሜ 5፡10

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

 1. አንዳንድ ሰዎች መዳን የማይፈልጉት በቂ ጊዜ ያላቸው ስለሚመስላቸው ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች መዳን በኢየሱስ ብቻ እንዳለ ያምናሉ ነገር ግን በሌሎች ነገሮች በጣም ባተሌ ከመሆናቸው የተነሳ የደህንነታቸውን ነገር ሁሌ ለሌላ ጊዜ ያስተላልፉታል፡፡ አፍላ ህይወታቸውን ለጌታ መስጠት ይሳሳሉ፡፡ ህይወትን ለጌታ ከመስጠት በላይ አስፈላጊ ነገር እንዳለ ያስባሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የህይወታቸውን ጭላጭ ሊሰጡት ይቀጥራሉ፡፡

ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው። ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። ሉቃስ 9፡59-62

በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡2

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10

ፀሎት

አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ

እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የደህንነት ነፃ ስጦታ

free gift.jpgሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይቶዋል፡፡ ሰው በሃጢያቱ ሙት ሆኖዋል፡፡ ሰው ከዚህ ሞት መዳን አለበት፡፡ ሰው ካልዳነ በስተቀር ለዘላለም ከእግዚአብሄር ይላያያል፡፡

ደህንነት ደሞ ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ደህንነት እጅግ ውድ ከመሆኑ የተነሳ ደህንነትን በምንም ነገር ሊገዙት አይችሉም፡፡

ሰው በሃጢያት የተነሳ በእግዚአብሄር ዘንድ ሙት በመሆኑና ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት በመሆኑ በህይወት ዘመኑ ሁሉ መልካምን ስራ ቢሰራ መልካም ስራው ደህንነትን ሊገዛለት አይችልም፡፡

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9

መልካ ስራ ደህንትን ቢያስገኝልን ኖሮ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር፡፡

መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14

ሰው በአለም ላይ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ቢያፈስ የአንድ ሰውን ደህንነትን ለመግዛት አይበቃም፡፡ ደህንነት እንዳውም በገንዘብ ሊተመን የማይችል እጅግ ውድ ነገር ነው፡፡

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማርቆስ 8፡36-37

ከጥፋተ መዳን የምንችለው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን ያደረገው መስዋእትነት ለእኔ ነው ብለን በእምነት በመቀበል ብቻ ነው፡፡

ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።1ኛ ጴጥሮስ 1፡18-19

ሰው ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት የከፈለለትን የሃጢያት እዳ ክፍያ በእምነት ባይቀበል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይከፍለዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄ በክርስቶስ የሰጠውን ነፃ ስጦታ ቸል ቢል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይጠፋል፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16

እግዚአብሔር ሆይ ስለላክልኝ ስለደህነነት ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ ሊሰቀል ወደምድር ስለመጣ  ስለሞተልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአደፌ እመሰክራለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መልካም ስራን መስራት ለመዳን ለምን አይጠቅምም?

murder-7593.jpgብዙ ሰዎች ለመዳን በመልካም ስራቸው ላይ ይደገፋሉ፡፡ መዳንን ሲያስቡ መልካም ስራዬ ያድነኝ ይሆንን ብለው ስለመልካም ስራቸው ጥንካሬ ይጨነቃሉ፡፡ መልካም ስራ መስራት እንደማያድን እና ሰው ለመዳን መልካም ስራ እንደሚያስፈገው ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሰው ጋር ህብረት ማድረግ እንዲችል ሰውን በመልኩ ፈጠረው፡፡ ሰው የተፈጠረው ወደ እግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ ነበር ፡፡

እግዚአብሄር ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንዲኖር አስቦ ነው ሰውን የፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንዲኖር ፣ ከእርሱ ጋር ህብረት እንዲያደርግና እንዲታዘዘው ነበር፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሄር ሰውን እንዲታዘዘው ያዘዘው በእርሱ ላይ ባመፀ ጊዜ እንደሚሞት ያስጠነቀቀው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ባልታዘዘ በዚያው ቅፅበት ሞተ፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ ሳተ፡፡ ሰው በአመፁ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው የአባትና የልጅነት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ተቆራረጠ፡፡ ሰው በራሱ ሆነ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት ሆነ፡፡

ስለዚህ ምክኒያት ምንም አይነት ለመዳን ወይም ለመጽደቅ የሚደረግ መልካም ስራ ሊያፀድቅ የማይችልበትን ምክኒያቶች እንመልከት፡፡

 1. ሰው ከእግዚአብሄር ክብር ወድቆዋል

በእግዚአብሄር መልክና አምሳል በእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮ ነበር፡፡

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 2፡27

ሰው ሃጢያትን ሲሰራ ከለእግዚአብሄር ክብር ወድቆዋል፡፡ ሰው ሃጢያትን ሲሰራ የእግዚአብሄን መልክ አጥቶታል፡፡ ሰው ሃጢያት በመሰራቱ ከእግዚአብሄር ክብር ጎድሎዋል፡፡

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23

ሰው ሃጢያት ሲሰራ ከእግዚአብሄ ክብርት ደረጃ ወደ ሳርነትና አባባነት ደረጃ ተዋርዶዋል፡፡ እግዚአብሄር በክብሩ የፈጠረው ሰው ከወደቀ በኋላ በሳርነትና በአበባነት ክብር የሚሰራው ስራ እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡ እግዚአብሄር የአመፀኛ ምንም አይነት ስራ አያስደስተውም፡፡

ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡24

 1. ሰው ሃጢያት ሲሰራ ከእግዚአብሄር ቤተሰብ አባልነት ወጥቶዋል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለህብረት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመጀመሪያ የፈጠረው ለህብረት እንጂ ለስራ አይደለም፡፡ ሰው ወደ እግዚአብሄ ቤተሰብ ውስጥ ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ወንድና ሴት ልጅ እንዲሆን ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኘኙነት እንዲኖረው ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው የአባትና የልጅ ግንኙነት ሲቋረጥ ሰው አጣ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው ግንኙነት በሃጢያት ምክኒያት ሲቋረጥ ሰው እግዚአብሄርን የሚመስልበትን ባህሪ አጣው፡፡ እግዚአብሄር ያለመውን ህብረትና ግንኙነት ከሰው ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ሳይሆን ሰይጣንን በመስማቱ መልካም ባህሪ አጥቶ የሰይጣንን ባህሪ ተካፈለ፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን የልጅነት ግንኙነት ያቋረጠውና የእግዚአብሄን ባህሪ ያጣው ሰው  በመልካም ስራ እግዚአብሄርን ሊያስደስተው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ስራውን ሳይሆን ግንኙነቱና የራሱን ባህሪ በሰው ውስጥ ማየቱን ነው፡፡ ግንኙነቱንና ህብረቱን አቋርጦ ባህሪውን ጥሎ ስራውን ልስራ የሚል ሰው እግዚአብሄርን አይማርከውም፡፡

 1. ሰው አላማውን ስቶዋል፡፡

ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እየሰማና እየታዘዘ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው ሃጢያት ሲሰራ የተፈጠረበትን አላማውን ሁሉ ስቶዋል፡፡ ሰው የተፈጠረው መልካም በሚላቸው ነገሮች እግዚአብሄርን እንዲያስደስት አይደለም፡፡ ሰው የተሰራው ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት በማድረግ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር እንዲያደርግ ነው፡፡ ስለዚህ የተፈጠረበትን የህብረት አላማ የሳተ ሰው በራሱ አነሳሽነት ነገሮችን በማድረግ እግዚአብሄርን ሊያስደስተው አይችልም፡፡

በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። ሮሜ 8፡8

 1. ሰው በሃጢያቱ ምክኒያት ሞቶዋል፡፡

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ዘንድ ህያው ሆኖ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት እያደረገ ለዘላለም እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው የአባትነትና የልጅነት ግንኙነት ሲቋረጥ ሞተ፡፡ ንስሃ ያልገባና ኢየሱስን ያልተቀበለ በሃጢያት የሚኖር ሰው በእግዚአብሄር አይን ሙት ነው፡፡ ኢየሱስን የማይከተል ሰው ሰው ለእግዚአብሄር ህያው አይደለም፡፡ ሃጢያተኛ ሰው ይበላል ይጠጣል ይንቀሳቀሳል በእግዚአብሄር አይን ግን ሙት ነው፡፡ የሰው መንፈሱ ሞቶዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበት የመንፈስ ክፍሉ ሞቶዋል፡፡ የሞተ ወይም የተለየ ሰው ማንንም ማስደሰት እንደማይችል ሁሉ ሃጢያተኛ ሰው እግዚአብሄርን በመልካም ስራ በፅድቁ ሊያስደስተው አይችልም፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን  2፡1-2

ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ኢሳያስ 64፡6

 1. ሰው በሰይጣን ግዛት ውስጥ ውድቆዋል

ሰው እግዚአብሄርን እንቢ ሲል ሰይጣንን እሺ ብሎዋል፡፡ ሰው ለፈጠረው ለእግዚአብሄር ካልተገዛ ለሰይጣን ይገዛል፡፡ ሰው ወይ የኢየሱስ ተከታይ ይሆናል ወይም የሰይጣን ተከታይ ይሆናል፡፡ ከሁለቱም መካከል ነኝ የሚል ሰው የለም፡፡ ሰው በንስሃ ኢየሱስን ካልተቀበለ በሰይጣን ግዛት ውስጥ እያለ ኢየሱስን ሊያገለግል መልካምን ስራ ሊሰራ አይችልም፡፡  ሰው መልካምን ለመስራት መጀመሪያ ከተያዘበት ከዲያቢሎስ ግዛት ነፃ መውጣት አለበት፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን  2፡1-2

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14

 1. ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ሆኖዋል፡፡

ሰው እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን በማድረጉ በእግዚአብሄር ላይ አምፆአል፡፡ ስለዚህ አመፀኛ የሆነ ሰው ላመፀበት መልካምን ነገር ከማድረጉ በፊት ከአመፁ ንስሃ መግባት አለበት፡፡ ከአመፁ ንስሃ ሳይገባና ሳይመለስ ከእግዚአብሄር ጋር ሳይታረቅ በጠላትነት የሚያደርገው መልካም ስራ ሁሉ ለመዳን በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሰው መልካመነ ስራ ከመስራቱ በፊት መታረቅ ግዴታ ነው፡፡

ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ሮሜ 5፡10

መልካምን ስራ መስራት ምንም ጉዳት የለውን ለመፅደቅ ወይም ለመዳን ግን አይጠቅምም፡፡ ሰው የሚድነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራለትን ስራ ለእኔ ነው ብሎ በእምነት ሲቀበል ነው፡፡ መልካምን ስራ ለመስራት ከሞተ ስራ ንስሃ መግባትና እንደገና መመለድ ይጠይቃል፡፡ ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ሁሉ መልካምን መስራት አለበት፡፡ ነገር ግን መልካምን የሚሰራው ለመዳን ሳይሆን ስለዳነ ነው፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእግዚአብሔር ፍጥረት ወይስ የእግዚአብሔር ልጅ ?

cliff2.jpgሰውን ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰውን እግዚአብሔር የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው የእግዚአብሔር የቤተሰቡ አባል እንዲሆንና ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖረው ነው፡፡ ሰው ከእርሱ ጋር ለዘላለም በአባትና በልጅ ግንኙነት እንዲኖር ስለፈለገ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይበላሽ ስለፈለገ ሰውን ካልተፈቀደለት ፍሬ እንዳይበላና እንዳይሞት አዘዘው፡፡

እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡16-17

ሰው ግን በሰይጣን አማካኝነት አትብላ የተባለውን ፍሬ በላ፡፡ ሰው በበላም ቀን ሞተ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው የአባትነትና የልጅነት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው በመንፈሱ ከእግዚአብሔር ተለየ ሞተም፡፡

ሰውን ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር እንጂ ሰይጣን የፈጠረው ሰው የለም፡፡ ሰይጣን ሰውን አሳመፀ፡፡ ያመፀውም የሰው ልጅ እንኳን የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍጥረት መሆን ማለት ግን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ማለት አይደለም፡፡ በምድር ላይ የምታዩት ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጥረት ነው፡፡ በምድር ላይ የምታዩት ሰው ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ላይሆን ይችላል፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን መመዘኛ አለው፡፡ መመዘኛው ስራ አይደለም፡፡ መመዘኛው እምነት ብቻ ነው፡፡ መመዘኛው በእምነት የኢየሱስን የመስቀል ላይ እዳ መክፈል መቀበል ነው፡፡

ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሃጢያት ሁሉ በመስቀል ላይ ስለሞተ የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆነ ሰው ሁሉ መመዘኛውን ካሟላ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ይችላል፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ስለሞተ ብቻ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይሆብንም፡፡ ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ስለከፈለ ኢየሱስ የከፈለው ለእኔ ነው ብሎ የኢየሱስን አዳኝነት የተቀበለ ሁሉ እግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

የእግዚአብሔ ፍጥረት የሆነ ሰው ኢየሱስ ስለሃጢያቱ በመስቀል ላይ የከፈለለትን ለእኔ ነው ብሎ ባይቀበል ግን ለዘላለም ይጠፋል፡፡ ሰው ኢየሱስን ባይቀበል የዘላለም ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆኑ ሁሉ ኢየሱስን እንደ አዳኝና ጌታ አድርጎ በመቀበል ብቻ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤተሰቡ ሊቀበላቸው ይፈልጋል ኢየሱስን ተቀበሉ እንላለን፡፡

የእግዚአብሄር ልጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ይህን ፀሎት አብሮ ይፀልይ፡፡

እግዚአብሔር ሆይ ስለላክልኝ ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህን ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ ስለተሰቀለልኝና ስለሞተልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ከሙታን እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ እንደሁም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌተ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን ፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ዓመቱን አዲስ የሚያደርጉት አምስት ነገሮች

IMG_0871.jpgዓመት በራሱ አዲስ አይሆንም፡፡ ያው የተለመደው ሰኞ ማክሰኞ ሮብ ሃሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ ነው፡፡ በቀኖቹ የምናደርጋቸው ነገሮች ናቸው አመቱን በእውነት አዲስ የሚያደርጉት፡፡

አመቱ በእርግጥ አዲስ አመት እንዲሆን አዲስ ሰው ይጠይቃል፡፡ አዲስን ወይንጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ እንደማይጨምሩት አዲሱና አሮጌው እንደማይስማሙ ሁሉ ሰው በአዲስነት ካልተቀበለው አዲስ አመት አይጠቅመውም፡፡ ሰው ህይወቱን በመለወጥ የሚኖር ከሆነ ደግሞ ሁሉም ቀን አዲስ ቀን ሁሉም ወር አዲስ ወር ሁሉም አመት አዲስ አመት ይሆንለታል፡፡

በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ። ማቴዎስ 9፡16-17

አመቱን አዲስ የሚያደርጉ አምስት ዋና ዋና ነገሮች፡-

 1. ንስሃ

 

የቀደመውን የክፋት ሃሳብ መተው፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነውን አካሄድ መለወጥ፡፡ ከሃጢያት መንገድ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ መመለስ ህይወታችንን ያድሳል፡፡ በቀጣይነትም ከመፅሃፍ ቅዱስ ውጭ የምንኖረውን ኑሮ በንስሃ እና ሃሳብን በመለወጥ ስንለውጠው በንስሃ ህይወታችንን እናድሰዋለን፡፡

እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፣ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፡፡ ሐዋርያት 3፡19

 1. አዲስ ፍጥረት መሆን

 

ሰው ክርስቶስን በመቀበል አዲስ ፍጥረት ካልሆነ በስተቀር በየአመቱ አዲስ ይሆናል ብሎ ይጓጓል ጠብ የሚል አዲስ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ሳይቀበሉ በአዲስ አመት አዲስን ነገር ለማግኘት መጓጓት ከንቱ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ስተው ነገሬ አዲስ ይሆናል ማለት ዘበት ነው፡፡ እውነተኛው አዲስ ነገር በክርስቶስ የሚገኘው አዲስ ፍጥረትነት ነው፡፡ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረትነት እንጂ በአዲስ አመት አዲስን ነገር መመኘት አይደለም፡፡

 

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17

 

በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ገላትያ 6፡15

 

 1. አእምሮን በእግዚአብሔር ቃል ማደስ

 

ክርስቶስ ኢየሱስን እንደአዳኝ ከተቀበልን በሁዋላ አእምሮዋችንን በእግዚአብሄር ቃል እውቀት መለወጥ አለብን፡፡ የተለወጠ አእምሮ የተለወጠን ህይወት ያስገኛል፡፡ የአባታችንን ፈቃድ በምድር ላይ መፈፀም የምንችለው በቃሉ በተለወጠ አእምሮ ብቻ ነው፡፡

 

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

 

 1. አዲሱን ሰው መልበስ

 

በህይወታችንም በየጊዜው የሚፈትነንን የአሮጌውን ሰው ማንነት አውልቀን በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው መልበስ ይገባናል፡፡

 

በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ኤፌሶን 4፡23-24

 

የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፤ ቆላስይስ 3፡10

 

 1. የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ ማድረግ

 

የእስራኤል ህዝብ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው ያደረጉበትና በዚያም ነፃ የወጡበትን ቀን ነበር የወሩ የመጀመሪያው ቀን እንዲሁም የአመቱ የመጀመሪያው ወር ይሁንላችሁ የተባሉት፡፡

 

እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ዘጸአት 12፡1-2

 

እግዚአብሔር ለእስራኤል አዲስ አመትን የሰየመላቸው ነፃ የወጡበትን ቀን ነው፡፡ ነፃ የወጣችሁበት ቀን ሁሉ አዲስ ወራችሁ  ነው፡፡ ነፃ የወጣችሁበት ወር ሁሉ አዲስ አመታችሁ ነው፡፡ እስራኤል የእግዚአብሄርን የነፃነት መንገድ ተቀብለው የዳኑበትን ቀን ነው አዲስ አመት ይሁንላችሁ የተባለው፡፡

 

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡32

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት  #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #አቁማዳ #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ

የፃድቃን የማንነት ሚስጥር ሲገለጥ

orth.jpgፃድቃን ማናቸው የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ፅድቅ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ አስፈላጊ ነው፡፡

ፅድቅ ካለፍርሃትና ካለበታችነት ስሜት በእግዚአብሄር ፊት መቆም ነው፡፡

ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ተጣልቷል፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስ ነው ፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒትት ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይቷል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ነው፡፡ ፃዲቅ ማለት በክርስቶስ የመስቀል ሞትና ትንሳኤ ከእግዚአብሄር ጋር የታረቀና ካለሃፍረት ፣ካለበታችነት ስሜትና ካለፍርሃት በእግዚአብሄር ፊት በድፍረት የሚቆም ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ዕብራውያን 4፡16

ፅድቅ ማለት ተቀባይነት ማግኘት ማለት ነው፡፡

ፃድቃን ማለት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሃጢያት እዳቸውን እንደከፈለ ስላመኑ በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት የእግዚአብሄር ልጆች የሆኑ ማለት ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሐንስ 1፡12

ፅድቅ ማለት ተቀባይነት ያለው ፣ ንፁህና ትክክል ማለት ነው፡፡

ፃድቃን ማለት በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ምክኒያት ሃጢያታቸው ስለተደመሰሰላቸው ከዚህ በፊት ሃጢያት እንዳላደረጉ ተደርገው እንደንፁህ ሰው በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ ማለት ነው፡፡ ፃድቃን ኢየሱስ የእነርሱንም ሃጢያት ወስዶ የእርሱን ፅድቅ የሰጣቸው ናቸው፡፡

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21

ፅድቅ ማለት ፀደቀ ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ህይወትን መዝራት መለምለም ማለት ነው፡፡

በሃጢያት ምክኒያት ሁሉም ሰው በመንፈሱ ሙት ነው፡፡ በመንፈሱ ሙት የሆነው ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ በኩል ህይወትን ሲያገኝ ህይወትን ዘራ ለመለመ ፀደቀ ይባላል፡፡

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። ሮሜ ሰዎች 3፡23-24

ፅድቅ ማለት በእግዚአብሄር አሰራር ማመን ማለት ነው፡፡

ፃድቃን ማለት በእግዚአብሄር አሰራር የሚያምኑ አማኞች ማለት ነው፡፡ ፃድቃን ማለት ለመዳን ዘመናቸውን ሁሉ የሚሰሩ ማለት ሳይሆን ፃድቃን ማለት እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ የተቀበሉ ፣ ኢየሱስ በእነርሱ ምትክ በመስቀል ላይ እንደሞተና የሃጢያታቸውን እዳ ሁሉ እንደከፈለ የሚያምኑና የመዳንን ነፃ ስጦታ በእምነት የተቀበሉ ማለት ነው፡፡

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ኤፌሶን 2፡8

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፃዲቅ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ፃድቃን #መዳን #ፀጋ #ህይወት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ኢየሱስ በስጋ የመጣበት ዋናው ምክኒያት

nails jesu s.jpgኢየሱስ ወደምድር የመጣው በስጋ ነው፡፡ ኢየሱስ የመጣው ከሰው ልጅ ተወልዶ ሰው ሆኖ ነው፡፡

ኢየሱስ ሰው ሆኖ የመጣው በሰው የተሰራውን ሃጢያት በሰውነት ለመክፈል ነው፡፡

እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።  ሮሜ ሰዎች 5፡18-19

ኢየሱስ ከእኛ ስጋና ደም በመካፈል ወደ ምድር የመጣው ሰዎችን በፍርሃት ያሰረውን የሰይጣንን ሃይል በእኛ ምትክ እንደሰው በመሞት እንዲሽረው ነው፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብራውያን 2፡14-15

ኢየሱስ በስጋ የመጣው አንድ የእግዚአብሄር ልጅ በአባቱ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለውን ክብር ሊያሳየን ነው፡፡ ኢየሱስ እንደሰው በምድር መጥቶ ናሙናውን ባያሳየንና የእግዚአብሄር ልጅነትን ሞዴል ባይሆነን ኖሮ አንድ የሰው ልጅ ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን የአባትና የልጅ ግንኙነት ልንረዳው አንችልም ነበር፡፡

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14

ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር የተመላለሰው እኛ ኢየሱስን የምንከትል የእግዚአብሄር ልጆች የበኩር ወንድማችንን ኢየሱስን እንድንመስል ስለተጠራን ነው፡፡

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8፡29

ኢየሱስ እኛን ወንድሞቹን ሊመስለን የተገባው በተመሳሳይ መልኩ የምንፈተነውን ሊረዳን እንዲችል ነው፡፡

ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና። ዕብራውያን 2፡17-18

ኢየሱስ ሰው ሆኖ በነገር ሁሉ እንደእኛ የተፈተነው አሁንም በሰማይ በድካማችን ሊራራልን የሚችል ሊቀ ካህናችን እንዲሆን ነው፡፡

ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። ዕብራውያን 4፡15

ኢየሱስ በምድር ላይ አሸናፊ ሆኖ ተሳክቶለት የኖረው በሰውነቱ ነው፡፡ ኢየሱስ የአለምን መከራ ያሸነፈው እንደሰውነቱ ባይሆን ኖሮ አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ አይለንም ነበር፡፡

በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። ዮሃንስ 16፡33

ኢየሱስ በምድር ላይ ጌታን ያገለገለው እንደ ሰውነት ባይሆን ኖሮ አብ እንደላከኝ እኔም እልካችኋለሁ ማለት አይችልም ነበር፡፡

ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ዮሃንስ 20፡21

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በሰውነት #በስጋ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ወንድሞቹን #የበኩርልጅ #መውደድ #መስጠት #መልካምነት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የበይ ተመልካች

o-DAVID-CAMERON-facebook (1).jpgእናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። ኢሳይያስ 55፡1-2

እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር ለሁላችንም እኩል እድል ሰጥቶናል፡፡ እስኪ ግን እነዚህን ሁለት አይነት ሰዎች እንመልከት፡፡ እኛንስ ራሳችንን ከሁለቱ አይነት ሰዎች በየትኛው ነው የምንመድበው?

አንዱ በገና ኢየሱስ ተወለደ ፣ በስቅለት ኢየሱስ ሞተ ፣ በትንሳኤ ደግሞ ኢየሱስ ከሞት ተነሳ እያለ እንደ ታሪክ በአመት ሶስቴ እያስታወሰ ይኖራል፡፡ ሌላው ደግሞ ከዚህ ከኢየሱስ ከከፈለው የሃጢያት እዳ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ በመሆን በአመት 365 ቀን ከሃጢያት እስራት ነፃ ወጥቶ ይኖራል፡፡

አንዱ ለሁሉ ሰው በተገለጠው በዚህ የነፃ ስጦታ ተጠቃሚ በመሆን የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል፡፡ ሌላው ደግሞ ኢየሱስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ እያለ እንደታሪክ እያወራ ከዚህ ነፃ ስጦታ አንዳች ተጠቃሚ ሳይሆን የበይ ተመልካች ይሆናል፡፡

አንዱ በዚህ በሚያስችል የእግዚአብሄር ፀጋ ስጦታ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት በመካድ ከሃጢያት የበላይነትን ኑሮ ያጣጥማል፡፡ ሌላው ደግሞ ነፃነት በኢየሱስ ተዘጋጅቶ እያለ በሃጢያት እስራት ተተብትቦ የሃጢያት መጫወቻ ሆኖ ዘመኑን ይፈጃል፡፡

አንዱ በእግዚአብሄር ፀጋ ራስን የመግዛትን ፍሬ በህይወቱ ይጠግባል፡፡ ሌላው ደግሞ በእግዚአብሄር ፀጋ ራሱን እንዴት እንደሚገዛ ባለማወቅ የሰይጣን ጥቃት ሰለባ ሆኖ ይኖራል፡፡

አንዱ እግዚአብሄርን በመምሰል እግዚአብሄርን ደስ እያሰኘ በእግዚአብሄርም ደስ እየተሰኘ ይኖራል፡፡ ሌላው ደግሞ እግዚአብሄርን መምሰል እንደ ሰማይ ርቆበት ተስፋ ይቆርጣል፡፡

እግዚአብሄር ግን ለሁሉም ግብዣን አዘጋጅቷል፡፡ እግዚአብሄር ልዩ ልጅ የለውም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡11-14

ኢየሱስ ስለሃጢያትችን በመሞቱና የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ በመክፈሉ ሁላችንም በነፃነት መኖር እንችላለን፡፡ ሰዎችን ከባርነት ቀንበርት የሚያድን የእግዚአብሄር ፀጋ ለሁሉም ሰው ተዘጋጅቷል፡፡

አንዱ ኢየሱስ የሞተበትን ምክኒያት ሙሉ በሙሉ በመረዳት 365 ቀን የበረከቱ ተካፋይ ሲሆን ሌላው ግን እንደ ባህል በአመት አንዴ በማስታወስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞት ዋጋ የከፈለበት አላማ በህየወቱ ሳይፈፀም ይቀራል፡፡

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአመፃ ሁሉ እንዲቤዠን ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ አሁንም ከሃጢያት ካልዳንክ ኢየሱስ የሞተበት አላማ በህይወትህ ገና አልተፈፀመም፡፡

በአሉን ልታከብር ስትዘጋጅ እኔስ የኢየሱስ ሞት ተጠቃሚ ሆኛለሁ ወይስ እንደ ወግ በአመት አንዴ ነው የማስታውሰው ብለህ ራስህን ጠይቅ፡፡ ኢየሱስ የሞተበት አላማ በህይወትህ ካልተፈፀመ በአመት አንዴ በአሉን ማስታወስህ የበይ ተመልካች ወይም ቲፎዞ እንጂ ሌላ ምንም አያደርግህም፡፡

መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መቤትዠት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት

መዳናችንንና ወደ መንግስተ ሰማይ እንደምንሄድ በእርግጠኝነት እናውቃለን?

assuranec of salvation.jpgበህይወት ዘመናችን እንደዳንንና አሁን ብንሞት ወደ መንግስተ ሰማይ እንድምንሄድ ሁላችንም እርግጠኛ መሆን እንፈልጋለን፡፡ አንዳንድ ሰው አይ ይህ የሚታወቀው አሁን አይደለም ብሎ ያምናል፡፡ ሞተን መዳንና አለመዳናችን የምናውቀው የዚያን ጊዜ ነው ብሎ እድሉን የሚጠብቅ ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር ግን ይህን ታላቅ የመዳናችንን ነገር ለእድል አልተወውም፡፡ በጥርጥር በሁለት ሃሳብ እንዳንኖር ስለ ደህንታቸን ማወቅ የሚገባን ነገር ሁሉ በመፅሃፍ ቅዱስ ተጽፎዋል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስለመዳናችን በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ ይናገራል፡፡

እግዚአብሄር ስለመዳናችን ሁሉንም ነገር በቃሉ አስታውቆን እያለ አንድ ጊዜ ሞቼ በትክክለኛ መስመር ላይ እንደነበርኩ አረጋግጣለሁ ማለት ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ስንፍና ነው፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሄር ለመዳኛችን ያዘጋጀውን መንገድ ሳንከተል ቀርተን እግዚአብሄ ፊት ከቀረብን ሌላ እድል አይኖረንም፡፡ ዘመኔን ሁሉ የሄድኩት መንገድ የተሳሳተ ነው ብለን እንደገና እንደ አዲስ ልጀምር ማለት አንችልም፡፡

ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥ ዕብራውያን 9፡27

እውነት እግዚአብብሄር የሚፈርድብን መልካም ስራቸው ነው ክፉ ስራቸው የሚበልጠው ብሎ ነውወይስ እግዚአብሄ በኢየሱስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ በመቀበላችን ወይም ባለመቀበላችን ነው ?

መፅሃፍ ቅዱስ ስለመዳናችን ምን ይላል የሚለውን ማወቅ ከፀፀት ይጠብቀናል፡፡

ስለሃጢያቱ በመስቀል ላይ በሞተውና ሞትን ድል አድርጎ በተነሳው በኢየሱስ ያመነ ሰው የዘላለም ህይወት ህይወት አለው፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ። 1ኛ ዮሐንስ 5፡11-13

በኢየሱስ የሚያም ሰው ሁሉ የሃጢያት እዳው እንደተደመሰሰና ለሃጢያቱ ይቅር እንደሚያገኝ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ በትንቢታቸው መስክረዋል፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል። ሐዋርያት 10፡43

በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ከሃጢያት ኩነኔ ነጻ ናቸው፡፡ በኢየሱስ በማመናቸው ብቻ ሃጢያት እንዳልሰሩ እግዚአብሄር ይቀበላቸዋል፡፡

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ሮሜ 8፡1

በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ለዘላለም ከእግዚአብሄር ከተለዩበት ሞት ወደ ህይወት ይሸጋገራሉ፡፡ ነፃ ናቸው አይፈረድባቸውምም፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንሰ 5፡24

በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ በሰሩት መልካም ስራ ሳይሆን ኢየሱስ በሰራላቸው የመስቀል ስራ በማመን ፅድቅን አግኝተዋል፡፡

እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ ሮሜ 5፡1

ኢየሱስ የሞተው ስለሃጢያታችን ነው፡፡ ከሞት የተነሳው እኛን የምናምነውን ለማፅደቅ ነው፡፡ እርሱን በማመናችን የእርሱ ፅድቅ ለእኛ እንዲቆጠርልን ነው፡፡

ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።ሮሜ 4፡24-25

በኢየሱስ የሚያምኑ መዳናቸውና አለመዳናቸው እስኪሞቱና ስራቸው ተመዝኖ እስኪረጋገጥ የማይጠብቁት የዳኑት በፀጋ ወይም ነፃ ስጦታ ስለሆነ ነው፡፡ ሁሉ ሃጢያትን በመስራቱ ማንም በኢየሱስ በማመን እንጂ በስራ መፅደቅ ስለማይችል ነው፡፡

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9

በኢየሱስ የሚያምኑ መዳናቸውን አሁኑኑ ያረጋገጡት የእግዚአብሄር ልጅነት ስልጣን ስለተሰጣቸው ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

የመዳናቸው ማረጋገጫው እግዚአብሄር መንፈሱን ስለሰጣቸው ነው፡፡

አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። ሮሜ 8፡15

በኢየሱስ የመስቀል ስራ ያመነ ሰው የእግዚአብሄር መሆኑን ለማረጋገጥ የመንፈሱን ቀብድ ሰጥቶታል፡፡ የእግዚአብሄር ነው ተብሎ ታትሞበታል፡፡

ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡22

በኢየሱስ የሚያምን ሰው እንደዳነ  የሚያረጋግጠው በውስጡ ያለው የእግዚአብሄር መንፈስ ስለሚመሰክርለት ነው፡፡ የአለም ህዝብ ሁሉ ተሰብስቦ አልዳንክም ከሚለው ድምፅ ይልቅ በውስጡ የሚመሰክርለት የእግዚአብሄር መንፈስ ምስክርነት ድምፅ ይበልጣል፡፡

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ 8፡14-16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሄር #ጌታ #ኢየሱስ #ቃል #መዳን #መንፈስቅዱስ #ሞቱናትንሳኤ #መስቀል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መንግስተሰማያት #መፅሃፍቅዱስ #ፍርድ #የዘላለምህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የጥምቀት ትርጉም ሲገለጥ

baptism.jpgጥምቀት  ወሳኝ የክርስትና ህይወት ክፍል ነው፡፡

እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማርቆስ 16፡15-16

ኢየሱስን ለመከተል ማስተዋል ስንችልና በራሳችን ስንወስን እንጠመቃለን፡፡

ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው እኛን ከሃጢያት እስራት ሊያድን ነው፡፡ ኢየሱስ ሰውን ከሃጢያት የሚያድነው በሞቱና በትንሳአው ነው፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን ሲሰቀል ፣ ሲሞት ፣ ሲቀበርና ሞትን ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን ሲነሳ ያንን ሁሉ የሆነው ስለራሱ ሃጢያት አልነበረም፡፡

ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ስለእኛ ነበር፡፡ ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው እኛን ወክሎ በእኛ ፋንታ ነበር ፡፡

እኛም ኢየሱስን አምነን እንደ አዳኝና ጌታ ስንቀበለው እግዚአብሄር በመለኮታዊ አሰራሩ ከሀጢያት እስራት ነፃ ያወጣናል፡፡

እኛ ኢየሱስን ስንቀበል እንጠመቃለን፡፡ ጥምቀት ከኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ ጋር ራሳችንን የማስተባበሪያው መንገድ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ሲሰቀል እኛን ሃጢያት የሚያሰራንን የሃጢያትን ምኞት ስጋን ከክፉ መሻቱ ጋር በመስቀል ላይ እንደሰቀለው ከስቅለቱ ጋር የምንተባበርበት መንገድ ነው፡፡

ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። ሮሜ 6፡9-11

እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።

በውሃ ጥምቀት ለሃጢያትና ለአለም ክፉ ምኞት ሞቻለሁ ብለን እናውጃለን፡፡ ስንጠመቅ ከሞተውና ከተቀበረው ኢየሱስ ጋር ራሳችንን እያስተባበርን ነው፡፡ ኢየሱስ በመቃብር እንደተቀበረ እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር ለመተባበር በውሃ ስር እንቀበራለን፡፡ በውሃ በመጠመቅና በውሃ ውስጥ በመስመጥ ከመቀበሩ ጋር ራሳችንን እያስተባበርን ነው፡፡

ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ሮሜ 6፡2-3

ከውሃ ስንወጣ ደግሞ በአዲስ ህይወት ለመመላለስ ከአሁን በኋላ ለጽድቅ ህያው ለመሆን ከኢየሱስ ከሞት ከመነሳቱ ጋር ራሳችንን እናስተባብራለን፡፡

ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤ ሮሜ 6፡5

ጥምቀት ስናስብ ለስጋ ክፉ ምኞትና ለሃጢያትና ለአለም መሞታችንን ትርጉም ካልሰጠን ከንቱ ነው፡፡ ጥምቀትን ስናስብ ከሃጢያት የበላይ የሆነን አዲስ ህይወትን እንዳገኘን በትንሳኤ ለመመላለስ ትርጉም ካልሰጠን ጥቅም የለውም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥምቀት #ሞት #ትንሳኤ #መቀበር #አዲስህይወት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የጌታን መንገድ አዘጋጁ

highway.jpgየእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ። እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥ ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ። ማርቆስ 1: 1-4

ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት አስቀድሞ የመጣው መጥምቁ ዮሃንስ ነበር፡፡ ዮሃንስ የመጣው ለኢየሱስ መንገድን ለመጥረግ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር የተባለው አማኑኤል ከመምጣቱ በፊትና የእግዚአብሄርን ክብር ከማየቱ በፊት የሚቀድመው የሰው ልብ መዘጋጀት ነበር፡፡

እግዚአብሄር ስራን ሲሰራ ከሰው ጋር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ክብር በሰው ህይወት እንዲገለጥ ሰው ልቡን ማዘጋጀት አለበት፡፡ እግዚአብሄር ጨዋ ነው፡፡ በማይፈልገውና በማይጠብቀው ሰው ህይወት ውስጥ በግድ አይሰራም፡፡

በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ። ሉቃስ 3፡3-6

እግዚአብሄር ሲሰራ የሚቀበለውና አብሮት የሚሰራ ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በተዘጋጁ ሰዎች ታላላቅ ስራዎችን ይሰራል፡፡ እግዚአብሄር በሚፈልጉትና በሚጠብቁት ሰዎች በሃይል ይጠቀማል፡፡ እግዚአብሄር ልባቸውን እርሱን ለመቀበል የሚያዘጋጁትን ሰዎች ሊያድንና ክብሩን ሊያሳያቸው ይመጣል፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር በህይወታቸን መገለጥ የልባችን መንገድ መጠረግና መስተካካል አለበት፡፡

ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ

እኔ ለእግዚአብሄር ማዳን አልበቃም ለሚል ሰው የምስራች አለኝ፡፡ የእግዚአብሄር ማዳን ስጦታ እንጂ ደሞዝ አይደለም፡፡ የመዳኛና  የእግዚአብሄርን ክብር በህይወታችን የማያ መንገዱ የኢየሱስን የሃጢያት መስዋእትነት እንደ ስጦታ መቀበል እንጂ በመልካም ስራ ደህንነትን መግዛት አይደለም፡፡

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ማቴዎስ 11፡28

ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል

እኔ የእግዚአብሄር ማዳን አያስፈልገኝም፡፡ እኔ መልካም ሰው ነኝ ፡፡ የኢየሱስ መስዋእትነት አያስፈልገኝንም ፡፡ እኔ በራሴ ስራ እድናለሁ ለሚል በሚሰራው መልካም ስራ ለመዳን የሚወድ ቢኖር ትሁት እንዲሆንና የእግዚአብሄርን የማዳኛ መንገድ እንዲቀበል  ራሱን እንዲያዋርድ የቀረበ ጥሪ ነው፡፡

በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ገላቲያ 5፡4

ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9

ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን

የእግዚአብሄርን የማዳኛ መንገድ ለመቀበል በእምነት መሆን ይጠይቃል፡፡ በብልጠትና በሰው ጥበብ የእግዚአብሄርን መንገድ አንረዳም፡፡  በእምነትና በስብከት ሞኝነት የምንቀበለው እንጂ እንዴት እንደሆነ ተመራምረን በአእምሮዋችን ብጥር አድርገን የምንረዳው አይደለም፡፡

በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡21

ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን

የእግዚአብሄር ክብር እንዲገለጥ ልባችን መዘጋጀት አለበት፡፡ ሸካራው ልባችን ለእግዚአብሄር ማዳን መስተካከልና መዘጋጀት አለበት፡፡

ሰው ለእግዚአብሄር ማዳን ካዘጋጀ የእግዚአብሄር ክብር ይገለጣል፡፡ የእግዚአብሄር ክብር ስጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ይገለጣል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፡፡ ደህንነትና የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት የሚጠይቀው ልብን ለእግዚአብሄር ማዘጋጀት ብቻ ነው፡፡

ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #የእግዚአብሔርክብር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ዝግጅት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

አማኑኤል

virgin-mary-pics-1101.jpgእነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። ማቴዎስ 1:23

እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ፡፡ ከዘላለም የነበረው የእግዚአብሄር ቃል ስጋ ለበሰ፡፡ ኢየሱስ የሰውን ስጋ በመልበስ ከድንፍግል ማሪያም ተወለደ፡፡

እግዚአብሄር በሰው መካከል አደረ፡፡ ኢየሱስ በእኛ መካከል ተመላለሰ፡፡ ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ሙሉ ለሙሉ ከፈለ፡

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14

የአማኑኤል በሰው መካከል የመመላለስ ዋናው አላማ ሰዎችን ከሃጢያት ለማዳን ነው፡፡ ሰዎች ከሃጢያት የሚድኑት ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለላቸውን የሃጢያት መስዋእት ለእኔ ነው ብለው ሲቀበሉ ነው፡፡

ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ማቴዎስ 1:21

የገናን በአል ስናከብር ኢየሱስ የመጣበት ሰውን ከሃጢያት የማዳን አላማ በህይወቴ ተፈፅሟል ወይ ብለን መጠየቅ በአሉን ትርጉም ያለው በአል ያደርገዋል፡፡

ከሃጢያት ነፃ አልወጣሁም ምን ማድረግ ይገባኛል የሚል ማንም ሰው ካለ መፅሃፍ ቅዱስ ስለዛ ሰው እንዲህ ይላል፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10

ለመዳን የሚያስፈልገው ኢየሱስ ስለሃጢያትህ እንደሞተና በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ ማመንና ኢየሱስን የህይወት ጌታ አድርጎ መሾም ነው፡፡

ይህንን ፀሎት ከልብህ በመፀለይ የእግዚአብሄር ልጅ አድርጎ እግዚአብሄር እንዲቀበልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ሃጢያተኛ ነኝ፡፡ የሃጢያት ደሞዝ ደግሞ ለዘላለም ከአንተ መለየት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሃጢያት ለመዳኛ ያዘጋጀኸውን የሃጢያት መስዋእት ኢየሱስን እቀበላለሁ፡፡ እየሱስ ስለሃጢያቴ በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለና እንደሞተ ከሞትም እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ላይ ጌታ አድርጌ እሾመዋለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ዘመን ሁሉ እከተለዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የዘላለም ህይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መዳንህን እርግጠኛ ነህ?

salvation_724_496_80መዳናችንን በእርግጠኝነት የምናውቅው ከስጋ ተለይተን ስንሞት ወይም ኢየሱስ ዳግም ተመልሶ ሲመጣ ነው ወይስ አሁን መዳናችንን ርግጠኛ መሆን እንችላለን የሚሉት ሃሳቦች ሰዎችን ያከራክራሉ፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ግን ስለመዳናችን ምን እንደሚል ማወቅ አሁን ስለመዳናችን ምንም ጥርጥር እንዳይኖረንና እንደዳነ ሰው የእግዚአብሄር ልጅነትን ስራ በምድር ላይ ሰርተን እንድናከብረው ያስችለናል፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ በእኛ ምትክ ስለሞተና ስለተነሳ ኢየሱስ የሰራውን ስራ በእምነት ለእኔ ነው ብሎ ከመቀበል ወዲያ እኛ ለመዳናችን የምናደርገው ምንም ነገር የለም፡፡ የሚጠበቅንብን የደህንነትን ነፃ ስጦታ በእምነት መቀበል ነው፡፡
 • • ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለልንን የሃጢያት እዳ ለእኔ ነው ብለን ከተቀበልን የዘላለም ህይወት አለን፡፡

ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ። 1ኛ ዮሐንስ 5፡12-13

 • • ኢየሱስ ከዘላለም ፍርድ ሊያድነን እንደ ተላከ የሚያምን ሰው ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋግሯል ወደ ፍርድም አይመጣም፡፡
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሐንስ 5፡24
 • • ለእርሱ የሰጠነውን እንዳንሰናከል ማድረግ ይችላል፡፡ እንዲሁም ነውር የሌለን ሆነን በፊቱ እንድንቆም ማድረግ ይቻለዋል፡፡

ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው ይሁዳ 1፡24

 • • ለመዳን ወደ እርሱ ለመጣን ለሁላችን ሊማድልንና ፈፅሞ ሊያድነን ኢየሱስ በህይወት ይኖራል፡፡
ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ዕብራውያን 7፡25
 • • ኢየሱስን አዳኛችንና የህይወታችን ጌታ አድርገን ለተቀበልነው ሁሉ የዘላለም ህይወት ተሰጥቶናል፡፡ ከእግዚአብሄር እጅ ሊነጥቀን የሚችል ሃይል የለም፡፡
እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሐንስ 10፡28-29
 • • የአለም ህዝብ ተሰብስቦ አልዳንክም ቢለን እንኳን የእግዚአብሄር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ 8፡16
 • • የመዳኛውን መንገድ ውስብስብ አይደለም፡፡ የዘላለም ህይወት የማግኛው መንገድ በኢየሱስ ማመን ነው፡፡
እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። ዮሃንስ 6፡47
 • • ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፉ ከመሰከረ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልቡ ካመነ ሁሉ ይድናል፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ስለመዳንዎ አሁን እርግጠኛ መሆን ከፈለጉ ይህን ፀሎት ከልብዎ ይፀልዩ
እግዚአብሄር ሆይ ይህን የመዳኛ መንገድ በቃልህ ስለገለፅክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ የሃጢያቴም ደሞዝ ለዘላለም ከእግዚአብሄር መለያየት መሆኑን አውቄያለሁ፡፡ እኔ የዘላለምን ሞትን እንዳልሞት ኢየሱስ በእኔ ምትክ የሃጢያቴን እዳ ሁሉ በመስቀል ላይ እንደከፈለ አምናለሁ፡፡ እግዚአብሄርን ከሙታን እንዳስነሳው አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ በሞት ላይ ጌታ እንደሆነ እንዲሁም በህይወቴ ላይ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ ልጅ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሜን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ደህንነት #ዘላለም #መዳን #ፀጋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ኢየሱስ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አንድ መልስ የለውም – ሁሉም መልስ ነው

sad-man-seating-lonely-i-miss-you-wallpaperበአገራችን ስላለው የሰዎች መሞት ስናስብ ችግሩ አንድ መልስ እንደሌለው እናስተውላለን፡፡ ለጥያቄው አንድ መልስ ብቻ መመለስ አንችልም፡፡ አንዳንዱ ሰው መፀለይ ብቻ ነው መፍትሄው መናገር አያስፈልግም ይላል፡፡ ሌላው ደግሞ መቃወም ነው እንጂ መፀለይ ምን ያስፈልጋል ይላል፡፡ እንደ እኔ ግን አንድ መልስ የለውም እላለሁ፡፡ ይህን የመጣውን እንደ ክርስቲያን በተለያየ መልኩ መመለስ አለብን፡፡
እንደ ክርስቲያን የህዝብን እልቂት ስናይ በጣም እናዝናለን፡፡ ልባችን ይሰበራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስም ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ ስለሚል ስለሞቱት የሃዘንተኞችን ሃዘን እንካፈላለን፡፡ ወንድማቸውን እህታቸውን አባታቸውን እናታቸውን ልጃቸውን ካጡት ጋር እናዝናለን ልባችን ያለቅሳል፡፡
ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። ሮሜ 12፡15
ይህም ብቻ አይደለም ባገኘነው አጋጣሚ በልባችን ያለውን ሃሳብ እንናገራለን፡፡ የተሳሳተውን ትክክል አይደለም እንላለን፡፡ ስለዚህ ሕዝቡን በብዙ ሌላ ምክር እየመከራቸው ወንጌልን ይሰብክላቸው ነበር፤ የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ ገሠጸው፥ ሉቃስ 3፡18-19
እንዲሁም እንፀልያለን፡፡ እንፀልያለን የሚለው ቃል ለአንዳንዶች የማይሰራና (passive) ገቢር እንዳይደለ ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን የክርስቲያን ፀሎት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ክርስቲያንና ፀሎትን መለየት አይቻልም፡፡ ሰይጣን ስፍራን እንዳያገኝ አጥብቀን መፀለይ አለብን፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ የፃዲቅ ሰው ፀሎት በስራው እጅግ ሃይል ያደርጋል፡፡
የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። ያዕቆብ 5፡16-18
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-4
እግዚአብሄር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን እንዲያውቁ ይወዳል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳንል ወንጌልን እንሰብካለን፡፡ ባገኘነው አጋጣሚ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሃጢያት እንደሞተ የምስራቹን እንናገራለን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፖለቲካ #ፀሎት #ተቃውሞ #ሃዘን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ኢየሱስ ጌታ ነው

jesus-is-lordክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው የሶስት ቃላት አረፍተ ነገር ውስጥ እጅግ የተጠቀጠቁ ትርጉሞች ይገኙበታል፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ሲባል
1. ኢየሱስ በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሃያል ነው ማለት ነው፡፡
በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡9-11
2. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት በሞት ላይ ስልጣን ያለውን በሞቱ የሻረ ብቸኛ የነገስታት ንጉስ ነው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ እስኪመጣ ድርስ ሞት ሃያል ጌታ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ሞትን ያሸነፈ ማንም አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ሲመጣ ግን በሞት ላይ ስልጣን ያለውን ሰይጣንን በሞቱ መሻሩን ያሳያል፡፡
እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ ዕብራውያን 2፡14-15
3. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ሃይላትንና ስልጣናትን የገፈፈ የመጨረሻው ባለስልጣን ነው ማለት ነው ፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15
ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ኤፌሶን 1፡20-21
4. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ላይ መሪና ወሳኝ ነው ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በልባችን የመጀመሪያው ስፍራ የእርሱ ነው ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ከእርሱ ጋር የምናወዳድረው ምንም ነገር የለም ማለታችን ነው፡፡ በልባችን ዙፋን ላይ የተቀመጠው ኢየሱስ ነው ማለታችን ነው፡፡
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15 ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል እርሱን ከሁሉም በላይ እንወደዋለን ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል ከእርሱ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር የለም ማለታችን ነው፡፡ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። ሮሜ 8፡38-39
5. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል ከእጁ የሚነጥቀን ማንም ሃይል የለም በማለት እየተመካን ነው፡፡ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሐንስ 10፡29
6. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ላይ ጌታ ሊሆን የሚችለውን ነገር ሁሉ ላይ ጌታ ነው ማለታችን ነው፡፡
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 8፡38፣37
7. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት የዳነው በኢየሱስ ጌትነት ነው ማለታችን ነው፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
8. የምንሰብከው እንኳን ጌታ ክርስቶስ ነው፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
9. በቃልም ሆነ በስራ የምናደርገውን ሁሉ በጌታ ኢየሱስ ስም የምናደርገው ስለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ቆላስይስ 3፡17
10. በመጨረሻም የምንነግሰው የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር ነው፡፡
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ። ራእይ 7፡14 ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ንጉስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

አምስቱ የግንኙነት መመዘኛዎች

Father-and-Sonክርስቲያን ነኝ ያለ ሰው ሁሉ ክርስቲያን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ያለው ሰው ብቻ ነው፡፡
ሰው ሁሉ ሃጢያትን ሰርቶ ከእግዚአብሄር ክብር ስለወደቀ ንስሃ ገብቶ ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ አለበት፡፡ እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያቱ የሰራውን ስራ ለእኔ ነው ኢየሱስ የሞተው በእኔ ምትክ ነው ብሎ የሚቀበል ሰው እግዚአብሄር ይቀበለዋል በቤተሰቡ ውስጥ ልጅ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ይኖረዋል እግዚአብሄርን በግሉ ያውቀዋል፡፡
የኢየሱስ ከሃጢያት አዳኝነት የምስራች ሲበሰርላቸው ብዙ ሰዎች እኔ ክርስቲያን ነኝ ብለው ስለሚያስቡ ብቻ ኢየሱስን ለመቀበል ፈቃደኛ አይሆኑም፡፡ ነገር ግን ክርስትናን እንደማንኛውም ሃይማኖት ሃይማኖቴ ነው ብሎ የያዘ ሰው ሁሉ ድኗል ማለት አይቻልም፡፡ እየሱስ ወደምድር የመጣው አንድ ተጨማሪ ሃይማኖት ለመመስረት ሳይሆን ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁና የአባትና የልጅ ግንኙነት አንዲኖራቸው ነው፡፡
ክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጋር የግል ግንኙነት መመስረት ነው፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት እንዳለንና እንደሌለን 5 መመዘኛዎች
 • ህይወታችን በእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን የመጨረሻው ስልጣን ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄ ቃል አድርጉ የሚለንን እናደርጋለን አታድርጉ የሚለንን አናደርግም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ዕብራውያን 4፡12
 • እግዚአብሄርን በሰሚ ሰሚ ሳይሆን በግላችን እናውቀዋለን፡፡ እግዚአብሄርን በእለት ተእለት ህይወታችን እንፈልገዋለን በህይወታችን በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላችን ሲሰራ እናውቀዋለን፡፡
ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-2
 • ከእግዚአብሄር ጋር በየእለቱ እንነጋገራለን፡፡ እግዚአብሄርን የምናውቀው በታሪክ ወይም በሰዎች ልምምድ ሳይሆን የእግዚአብሄርን አባትነት በህይወታችን እንለማመዳለን፡፡ እንደ አባት እንጠራዋለን እንደ ልጅ ይሰማናል ይናገረናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
 • በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከማንም ከምንም አብልጠን ኢየሱስን እንከተላለን:: የኢየሱስን አስተምሮዎች ሁሉ እንታዘዛለን፡፡

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ማቴዎስ 28፡19-20

 • ኢየሱስ በልባችን ይኖራል፡፡ ክርስትና ሃይማኖታዊ ወግና ስርአት መፈፀም ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሄር መኖርና በእግዚአብሄር ሃይል ማገልገል ነው፡፡ ኢየሱስን የምናውቀው በልባችን ሲኖርና ከልባችን ሲመራንና በልባችን በመኖር ሃይል ሲሰጠን ነው እንዲያውም ኢየሱስ በእኛ ሲወጣና ሲገባ ስራውን ሲሰራ ነው፡፡
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ገላትያ 2፡20
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ

Vision is a Must!

visionBeing successful doesn’t come by accident. We have to follow some rules that ensure us to really be successful in life.

Following vision is important for successful living.  It is very important not only to get the vision but also to follow it strictly to reach at a certain goal and be fruitful in life. Without vision, we can go nowhere.

Where there is no vision, the people perish: but he that keepeth the law, happy is he. Proverbs 29፡18

A visionary person is the one who finds what God has for him and follow it. Having vision is seeing God’s agenda for our lives.

 • Vision isn’t ambition

We all have ambitions in life. We want to do this or that we wish to achieve that. We want to have the other. But vision isn’t motivated by our wish. Vision is God’s will for our lives. Vision doesn’t really depend on one’s human desire.

 • Vision isn’t career opportunity

We assess the need of the people around us and want to do something that will solve the problem around us. Vision isn’t looking for jobs or job opportunities in the areas we see lack in the country.

Vision doesn’t come by our statics evaluation. Vision doesn’t come by our research and conclusion as what must be done in a specific situation. That is not vision but earthly Knowledge at work.

 • Vision is to see

Vision is to see the God’s agendas. Being visionary is doing according to what is in God’s heart and mind. Being visionary is aligning self with the will of God for your life.

I will raise up for myself a faithful priest, who will do according to what is in my heart and mind. 1 Samuel 35: 2

Vision is doing what God is doing on earth. It is working with God in his Agendas.

They serve at a sanctuary that is a copy and shadow of what is in heaven. This is why Moses was warned when he was about to build the tabernacle: “See to it that you make everything according to the pattern shown you on the mountain.” Hebrews 8፡5

The visionary follows what he sees God does.

Jesus gave them this answer: Very truly I tell you, the Son can do nothing by himself; he can do only what he sees his Father doing, because whatever the Father does the Son also does. John 5:19

For More Articles

#Vision    #hiswill #hisleading #hisagenda #Jesus #Lord #Church #success # #inspired #sermon #church #leadership #steward #bible #theword #christ #purpose

Arise, shine

Free-woman-raising-arms-to-golden-sunset-summer-sky-like-praisingArise, shine, for your light has come, and the glory of the Lord rises upon you. See, darkness covers the earth and thick darkness is over the peoples, but the Lord rises upon you and his glory appears over you. Nations will come to your light, and kings to the brightness of your dawn. Isaiah 60: 1-3
Arise and shine says the Lord! This is your time to shine. This is your season. This is your time of visitation. This is your turn. This season is yours.
The reason: “For your light has come, and the glory of the Lord rises upon you”. It isn’t because of you. It is because of His strength. His light has come upon you. The glory of the Lord rises upon you.
Light is seen when it comes. When the light comes, it is known and recognized. When the light comes, the darkness gives place to the light.
Light signifies favor, development and beauty. When it says your light has come, it means your favor has come, your beauty has come, your attraction has come and your hope has come. No more waiting.
Don’t worry about the darkness around says the Lord. It doesn’t affect you. It is irrelevant to your progress and your favor. Don’t take it to heart. It doesn’t concern you. The darkness on earth doesn’t tell your fate. The darkness on earth is too small to predict your future.
On the contrary, the darkness of the people will glorify your light even further leave alone to affect it.
You are unique because Lord rise upon you. When the darkness covers the earth and thick darkness is over, the people, God will raise upon you to make you different from the rest. God will show himself in you. God will show his glory upon you. This is high time that God is using you to show His goodness and glory.
Nothing is exempt from being attracted by the glory of God. It attracts everyone.
The kings and the best on earth are helpless, but are attracted by you because of the glory of God upon you. All you need is to rise and shine.
To share this article
#glory #light #zion #church # Christianity #thetimeisnow #Godsglory #Jesus #ariseandshine #shine #arise #salvation #preaching #bible #Facebook #abiywakuma #abiydinsa #abiywakumadinsa

Free Indeed!

handcuffsSo if the Son sets you free, you will be free indeed. John 8:36
Mankind isn’t designed for any kinds of bondage. God created man free to serve the Lord in liberty. God created man with free-will. That is the reason that man isn’t comfortable with any kinds of bondage. No bondage goes with his design.
And there are many kinds of operations and slavery. And there are many kinds of freedoms. Any freedom is good. There are different degrees of bandages and different degrees of freedoms.
For instance, the Bible teaches us that borrower is slave to the lender.
The rich rule over the poor, and the borrower is slave to the lender. Proverbs 22:7
God created man to obey His will. When man disobeyed God, he had fallen from the glory of God. Man has fallen under the Devil’s operations. He became the slave of sin. And the slavery of sin is the worst kinds of all slavery of all time.
The only mission of the devil is to steal to kill and to destroy. In fact, he doesn’t come but to steal to kill and to destroy.
The thief comes only to steal and kill and destroy… John 10:10
And the Devil is the worst oppressor of all oppressors. The worst kind of oppression is by the Devil whose exclusive mission is to steal and kill and destroy. This is eternal slavery as it leads our separation from God eternally. Sin can separate us from God forever as the wage of sin is death. Romans 3:16
When you were slaves to sin, you were free from the control of righteousness. Romans 6:20
Don’t you know that when you offer yourselves to someone as obedient slaves, you are slaves of the one you obey—whether you are slaves to sin, which leads to death? Romans 6 16
The good news is that there is a way out of permanent oppression and slavery. Jesus came to set us free.
. . . I have come that they may have life, and have it to the full. John 10:10
There is no remedy found for slavery of sin under the earth. And what is the use of being free from all temporary operations and stay bound by the eternal slavery of sin? What benefits us, if we are the most liberated of all on earth and we are in bondage for eternity?
And what do you benefit if you gain the whole world but lose your own soul? Mark 8:36.
I came that they may have life. John 10 10
If a man accepts the way of salvation, he will be free indeed.
So if the Son sets you free, you will be free indeed. John 8:36
#freedom #liberty #sin #bondage #thedevil #grace #salvation #church #testimony #soulwinning #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? ይላል እግዚአብሄር

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረግ ፈልጎ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ህብረታቸው የተሳካ እንዲሆን ነው፡፡ ሰው በሃጢያት ከመውደቁ በፊት ከእግዚአብሄ ጋር የተሳካ ህብረትና ግንኙነት ነበረው፡፡ ሰው ግን እግዚአብሄር ላይ ሲያምፅና በሃጢያት ሲወድቅ ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ተቋረጠ፡፡
አሁንም ቢሆን ግን የእግዚአብሄር አላማ ከሰዎች ጋር ህብረትና ማድረግ ነው፡፡ ሰው በትህትና ከኖረ እግዚአብሄር ሁሌ ከሰው ጋር ህብረት መድረግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከምንሰራለት ምንም ቤት በላይ የትሁት ልብ ስጦታችን ወደ እኛ እንዲመለከት ያደርገዋል፡፡
ሰዎች ሊያስደስቱት ከሚያደርጉለት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ በላይ እግዚአብሄር ወደ ትሁት ሰው እንደሚመለከት ቃሉ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች እጅ በተሰራ ቤት ውስጥ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር ወደ ትሑትና መንፈሱም ወደ ተሰበረ ሰው ግን ይመለከታል፡፡ እግዚአብሄር በትሁት ሰው መኖር ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2
እኛም አገልጋዮች ለእግዚአብሄር ቤት መስራት ከፈለግን በወርቅ የተንቆጠቆጠ ቤት ከመስራት ይልቅ ትሑት፥ መንፈሱም የተሰበረ፥ በቃሉም የሚንቀጠቀጥን ሰው ለእግዚአብሄር መስራትና ማቅረብ ይበልጣል፡፡
እግዚአብሄር እኛን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን ከእርሱ ጋር ህብረት የሚያደርግ ፍጡር ፈልጎ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን እርሱን እንድንረዳውና ሙሉ ለሙሉ በምድር ላይ እንድንወክለው ነው፡፡ እግዚአብሄር ምንም ሳይሰስት በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን በእኛ ሊወጣና ሊገባ ፣ በእኛ አልፎ ሌሎችን ሊናገርና በእኛ ተጠቅሞ ሌሎችን ሊደርስ ስለፈለገ ነው፡፡
ስለሌሎች ነገሮች ሁሉ ሲናገር “እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር” የእርሱ ሊያደርገው የሚፈልገው አንድና ብቸኛ ነገር ሰውን ነው፡፡ ሊማርከውና የእርሱ ሊያደርገው የሚፈልገው የሰውን ልብ ነው፡፡ የእርሱ ሊያደርገው የሚፈልገው የሰውን ፈቃድ ነው፡፡ መጥቶ ሊኖርበት የሚፈልገው ትሁትን ልብ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው ለቃሉ በህይወቱ የመጀመሪያውን ስፍራ የሚሰጠውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚማርከው ቃሉን ለማድረግ በተጠንቀቅ የሚሰማውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያርፈውና የሚኖረው ለእግዚአብሄር ቃል የዋህና ትሁት በሆነ ሰው ውስጥ ነው፡፡
ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡2
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ትህትና #የእግዚአብሔርቤት #በቃሉመንቀጥቀጥ #ህብረት #እምነት #የተሰበረልብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No Big Deal

no big deal.jpgThere are some things we do in Christian’s life that are not big deals. We sometimes think that they are. But they are not. They are ordinary that don’t take God’s power to do them. They are weak for our testimony about the power of God that works in us.

Testifying about the power of God in us takes completely different lifestyle. It takes sacrifices. And it takes to believe in the power of grace that equips us to live higher standards.

If you love those who love you, It isn’t a big deal. Everybody can love those who love them. But you will be completely different if you love who hate you. If you pray for those who persecute you, you stand out from the crowd. That is a big deal. That takes something special.

If you love those who love you, what reward will you get? Are not even the tax collectors doing that? Mathew 5:46

Cursing who curses you is an ordinary lifestyle. It isn’t really a big deal if you curse those who curse you. Everybody are tempted to curse who curse them. But it takes higher life to bless who curse you.

bless those who curse you, pray for those who mistreat you. Luke 6:28

If you are strong in pleasant days, it isn’t a big deal. There is nothing special and extraordinary about it. But if you are steadfast in the days of calamity, you show that you have something different.

If you falter in a time of trouble, how small is your strength! Proverbs 24:10

If you hate who hate you, it isn’t a big deal. Any natural person is inclined to do that. And if you do good to those who are good to you, there is nothing unique about it. But if you love you enemies and do good to them, that takes the power of God to do it and earns you credit.

But to you who are listening I say: Love your enemies, do good to those who hate you, And if you do good to those who are good to you, what credit is that to you? Even sinners do that. Luke 6:27, 33

If we hope and believe what we have seen, it isn’t either hope or faith. It takes something supernatural to believe what you don’t see.

For in this hope we were saved. But hope that is seen is no hope at all. Who hopes for what they already have? Romans 8:24

When Thomas heard about the resurrection of Jesus after his death, He said I don’t believe unless I see. And he said he believes when he saw. But Jesus showed him a higher life.

Then Jesus told him, “Because you have seen me, you have believed; blessed are those who have not seen and yet have believed.” John 20:29

It is only by a sacrificial lifestyle that we can testify to the power of God that works in us. Nobody will see extraordinary in an ordinary lifestyle. Nobody sees the power of God in a natural lifestyle. But we can effectively testify about the salvation in Jesus by living out the life lives by the grace of God that enables us to live extraordinarily.

It is only by the higher lifestyle of grace that we testify about Jesus Christ and actually win souls for God.

For More Articles

ብርቅ ነው እንዴ?!

Work is love made visible

good is stronger than evil

Love Adventure

#excellnce #grace #salvation #church #testimony #soulwinning #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

አዋጅ !

Trumpet_3_Slider.jpgእግዚአብሄር ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለእርሱ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ዘር ሃይማኖት ፆታ ሳይለይ ለሁሉም የቀረበ ጥሪ ነው፡፡ የትኛውም ዘር የትኛውም ሃይማኖት የትኛውም ፆታ አየመለከተኝም የሚል የለም፡፡ ሁሉንም ይመለከታል፡፡ ከሁሉም አፋጣኝ ውሳኔ ይጠይቃል፡፡ ይህ ለራሱ ክብር የፈጠረን አምላክ ለሁላችንም እንዲህ ይላል፡፡ ለሁላችንም እንዲህ ይለናል፡፡
ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። ሉቃስ 9፡23-24
እኛን የፈጠረው አምላክ ከእኛ ሙሉ መታዘዘን ይጠይቃል፡፡ እርሱን እንዳንከተል ሊበቃ የሚችል ምንም ምክኒያት የለም፡፡ ጌታን እንዳንከተል የሚቀርብ ማንኛውም ምክኒያት ሰንካላ ምክኒያት ነው፡፡ ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡27
ጌታን የምንከተለው ለራሳችን ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው እንዳንጠፋ ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው ለዘላለም ከጌታ እንዳንለያይ ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ እንዳይኖር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደሆነ ኩሩ ነው፡፡
እግዚአብሄር ከፈጠረው ሰው ያነሰ ነገር አይቀበልም፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ሙሉ መሰጠትን ይጠይቃል፡፡ ለዚህ ነው ራሱን የማይክድ ሰው ለእኔ ሊሆን አይገባውም የሚለው፡፡
አንዱ አስቀድሜ አባቴን ልቅበር ባለው ጊዜ እየሱስ አይ ችግር የለም ጊዜ አለህ ቀስ ብለህ ትከተለኛለህ አላለውም፡፡ ጌታን የመከተያ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ።
ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው። ሉቃስ 9፡59-60
አንዱ እከተልሃለሁ ነገር ግን ቀድሜ ቤተሰቦቼን ልሰናበት ባለው ጊዜ የተከፋፈለ መሰጠትና ትኩረት ተቀባይነት እንደሌለው ነው እዚያው ያስረዳው፡፡
ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። ሉቃስ 9፡61-62
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ
#ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #ፌስቡክ #አዋጅ

መልካም ምግባር አይበቃም!

salvation illustration gggመልካምን መስራት መስራት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ለመዳን መልካም ስራ መስራት አይበቃል፡፡ ሰው ከአንዱ ሰርቆ ለሌላው ምፅዋት ቢሰጥ ያደረገው መልካም ስራ ያደረገውን ክፉ ስራ አይሽረውም፡፡ የሰው ችግር በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር መለየቱና መጣላቱ ነው፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23
የዚህ የእግዚአብሄር ክብር የጎደለው ሰው መጨረሻ ለዘላለም ከእግዚአብሄ መለያየት ነው፡፡
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ ሮሜ 6፡23
ይህንን ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለየት በሞት የሚያስፈርደውን ፍርድ ሊለውጥ የሚችል ማንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ግን በምህረቱ ሃጢያት ያልሰራውን አንድ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት በማድርግ የሃጢያታችንን ዋጋ ከፈለ፡፡
አሁን ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀውንም ይህንን የመዳኛ መንገድ እየሱስን ከተቀበለና እየሱስ ከሙታን እንደተነሳ በልቡ ካመነ እንዲሁም እየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፉ ከመሰከረ ይድናል፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ምንም በሰራው መልካም ስራ ሳይሆን እግዚአብሄር ለመዳኛ የሚሆነውን የሃጢያትን እዳ የከፈለውን እየሱስን የተቀበለውን እግዚአብሄር ልጅ አድርጎ ይቀበለዋል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ዮሃንስ 1፡12
በመልካም ስራው ሳይሆን እየሱስን በማመን ብቻ የዳነው ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀለትን መልካመ ስራ በመስራት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
%d bloggers like this: