Category Archives: Prosperity

እግዚአብሔር የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን

pride.jpg

የገቢ ምንጫችሁ የሆነ ሰው ወደዳችሁም ጠላችሁም የወደፊት እድላችሁን ይወስናል፡፡ የገቢ ምንጫችሁን የሚያመጣ ሰው የሚለውን ላለመስማት ከባድ ብቻ ሳይሆን የማይቻልም ነው፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም  የገቢ ምንጫችሁን የሚያመጣ ሰውን ራእይ በህይወታችሁ ታስፈፅማላችሁ፡፡

በገንዘብ ስለተገዙት ባሮች መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ይህንኑ ነው፡፡ ስለባሮች መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እናንተ ክርስትያን ስለሆናችሁ የምታገለግሉትና የምትታዘዙት ጌታን ክርስቶስን ነው እንዲሁም የርስትን ብድራት የምትቀበሉት ከእርሱ ነው እያለ እግዚአብሄር ምንጫቸው መሆን እንዳለበት ያስተምራል፡፡ እግዚአብሄር ቀጣሪያቸውና ከፋያቸው ሲሆን በነፃነት ሰውን በማገልገል እግዚአብሄርን እንደሚያገለግሉ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡6-8

ጌታ የገቢ ምንጫችሁ እግዚአብሄር ሲሆን ሰዎች እንዲያዩዋችሁ ለታይታ መኖርን ታቆማላችሁ፡፡

ሰዎች የገቢ ምንጫችሁ ሲሆኑ ከሰው እንጂ ከእግዚአብሄር የሚገኘውን ክብር ማግኘት አትፈልጉም፡፡ ሰዎች የገቢ ምንጫችሁ ሲሆኑ ከልባችሁ ሳይሆን ሰዎችን እያያችሁ ለታይታ ብቻ ትኖራላችሁ፡፡ ሰዎች የገቢ ምንጫችሁ ሲሆኑ ሰውን እንጂ እግዚአብሄርን ለማስደሰት አትፈልጉም፡፡

እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የዮሐንስ ወንጌል 5፡44

ጌታ የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን ለጌታ ብቻ ለመኖር ነጻነትን ታገኛላችሁ፡፡

አገልጋይ ለኑሮ ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ቤተክርስትያን በምድር ላይ ተልእኮዋን ለመወጣት ገንዘብ ያስፈልጋታል፡፡ ለራእይ ማሳካት ገንዘብን እንዲሰጡ እግዚአብሄር ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ ነገር ግን ሰዎች እግዚአብሄርን በመታዘዝ በገንዘባቸው ያገለግሉናል እንጂ የገቢ ምንጫችን በመሆን የሚፈልጉትን ነገር የሚያስደርጉን መሆን የለባቸውም፡፡ የገቢ ምንጫችን ሲሆን ብቻ ነውእግዚአብሄር የሰጠንን ነገር በገንዘቡ ሊገዛ የሚፈልግ ሰው ካለ እምቢ እንድንል አቅም የሚኖረን፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን እንደ ሀዋርያቱ  የእግዚአብሄርን ስጦታ በገንዘቡ ሊገዛ የሚመጣውን ሰው ከገንዘብህ ጋር ጥፋ ማለት እንችላለን፡፡

ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና። እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። የሐዋርያት ሥራ 8፡18-20

ጌታ የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን ማንም ሰው አያስፈራራችሁም

ጌታ የገቢ ምንጫችሁ ሲሆን ማንም ሰው የእኔን ፍላጎት ካላሟላህ ገንዘብ መስጠትን አቆማለሁ ብሎ አያስፈራራችሁም፡፡ ሰው እናንተን በማገልገል እግዚአብሄርን እንደሚያገለግል ካልተሰማው ለእርሱም ለእናንተም አይጠቅምም፡፡ በገንዘቡ የሚያስፈራራችሁን ሰው በሰላም እንዲሄድ ትፈቅዱለታላችሁ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ሲጠቀም እግዚአብሄር በልባችን ያስቀመጠውን ራእይ እንድናደርግ እንጂ ገንዘብ የሚሰጡንን ሰዎች ራእይ እንድናደርግ አይደለም፡፡ በእነርሱ ውስጥ ያለውን ራእይ ማድረግ ከፈለጉ እኛ እናስፈልጋቸውም፡፡ እኛ  ከእግዚአብሄር የተቀበልነው በቂ ራእይ አለን፡፡ እግዚአብሄር የገቢ ምንጫችን ሲሆን ማንም ሰው እኔ የምፈልገውን ነግው የምታደርገው ካለበለዚያ ዋ ብሎ አያስፈራራንም፡፡

ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡12

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን ማንም ሰው ክብራችሁን እንዲነካ አትፈቅዱለትም፡፡

ጌታ ምንጫችህ ሲሆን ማንም ሰው እኔ ባልሰጠው ይሞታል ብሎ ክብራችንን እንዲያዋርድ አንፈቅድለትም፡፡ ጌታ ምንጫችህ ሲሆን ማንም ሰው እኔ ባልደርስለት ዋጋ የለውም ነበር እንዲል አንፈቅድም፡፡ ለጌታ ልንሰጥና ልናገለግለውም ራሳችንን ሰጥተን የጌታን ስራ ለመስራት ሰውን አንለምንም፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን የወንጌል ማህበርተኛ ለመሆን ሰዎችን በራሳችን ወጭ እናገለግላለን፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን በነፃ ወንጌልን የማገልገል ትምክታችንን ማንም ከንቱ እንዲያድርግብን አንፈቅድም፡፡

እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡15

እንግዲህ ደመወዜ ምንድር ነው? ወንጌልን እየሰበክሁ በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ እንዳልጠቀም ወንጌልን ያለ ዋጋ ብናገር ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡18

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን በእኛ ማግኘት ጌታ ብቻውን ይመሰገናል፡፡

ጌታ ምንጫችን ሲሆን የጌታን ክብር ለማንም ስጋ ለባሽ እንሰጠም፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን ማንንም ሰው እንደ አዳኛችን አናይም፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን ለእኛ የሚሰጡ ሰዎች ለጌታ በመስጠታቸው እግዚአብሄርን ያመሰግናሉ እንጂ ራሳቸውን አያመሰግኑም፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን ለእግዚአብሄር የሚሰጡ ሰዎች ለጌታ በመስጠታቸው ራሳቸውን እንደ እድለኛ ይቆጥራሉ፡፡ ጌታ ምንጫችን ሲሆን በህይወታችን የጌታና የሰው ክብር ከሚቀላቀል ሰዎች የሚያደረጉልን ጥቅም ቢቀርብን ይሻለናል፡፡

አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ኦሪት ዘፍጥረት 14፡22-24

ጌታ ምንጫችን ሲሆን በእናንት ማግኘት ማንም እንዲጠራ አትፈቅዱም

ጌታ ምንጫችን ሲሆን ለእኛ የሚሰጥ ሰው ለእግዚአብሄር እንደሰጠ መቁጠር አለበት፡፡ እንደው ለእኛ አዝኖ ብቻ የሚያድርግልንን አንቀበለም፡፡ እኛ ብዙዎችን ባለጠጋ የምናደርግ ሁሉ የእኛ የሆነ የእግዚአብሄር አገልጋዮች እንጂ የሚታዘንልን ምስኪን ሰዎች አይደለንም፡፡

ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡10

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን በሙሉ ልቡ ያልሆነ በስስት የሚሰጠውን ሰው አልቀበለም ማለት ትችላላችሁ

ጌታ ምንጫችን ሲሆን ብቻ ነው በደስታ ከሚሰጠው ሰው ብቻ የምንቀበለው፡፡ ደስ ሳይለው በልቡ እየሰሰተ የሚሰጥን ሰው ላለመቀበል ድፍረቱ የሚኖረን ጌታ ምንጫችን ሲሆን ብቻ ነው፡፡

የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፤ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። መጽሐፈ ምሳሌ 23፡6-7

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን ለሰዎች ስለሚበዛው ስሌት እንጂ ስጦታቸውን ፈላጊ አትሆኑም

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን ህይወታችሁን ይለውጣል ብለላችሁ ተስፋ የምታደርጉት አንድም ሰው ከሰማይ በታች አይኖርም፡፡ ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን ሰዎች ለእግዚአብሄር ስራ ስለመስጠታቸው ለሰዎች ስለሚበዛው ስሌት እንጂ ስጦታቸውን ፈላጊ አትሆኑም፡፡

በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡17

ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን የእግዚአብሄርን ቃል በነፃነት ለመኖርና ለመስበክ ድፍረት ይኖተራችሁዋል፡፡ ጌታ ምንጫችሁ ሲሆን ለሰው ብላችሁ የእግዚአብሄርን ቃል እውነት አታመቻምቹም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ምንጭ #አቅራቢ #ሰጭ #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው

your will.jpg

በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡12-13

የሆድ ነገር ብዙ ሰዎችን የማይፈልጉትን እንዲያደርጉ ያስደርጋቸዋል፡፡ የሚጠፋው የሆድ ነገር ብዙ ሰዎችን ያዋርዳል ከአላማም ያደናቅፋል፡፡ ብዙ ለጌታ ሲሮጡ የነበሩትን ሰዎችን የሆድ ነገር አሳስሮ ሽባ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ ብዙ ሰዎች ስለሆድ ብለው ራእያቸውን ጥለው እጅግ ያለቅሳሉ፡፡

ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ወደ ዕብራውያን 12፡16

ጌታ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም እንዳለ የሆድ ነገር የሰለጠናበቸው ሰዎች ጌታ እንደሚገባ ሊሰለጥንባቸው አይችልም፡፡ የሆድ ነገር የሚገዛቸው ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ለጌታ ሊገዙ አይችሉም፡፡

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። የማቴዎስ ወንጌል 6፡24

ሰው እያደገ ሲሄድ ፍላጎቱ በዚያው መጠን ስለሚጨምር የሆድ ፈተና የሌለበት ሰው የለም፡፡ ሁሉም ሰው ነገ ስለሚበላው ነገር በሆዱ ይፈተናል፡፡ ሁሉም ሰው የያዘውን እውነት እንዲያመቻምችና ሆዱን እንዲሞላ ተከታታይ ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ ሁሉ ሰው ስለሆድ ምክኒያት ህሊናው የማይፈቅድውን ነገር እንዲያደርግ ይፈተናል፡፡

ትራባለህ ታጣለህ የሚል ማስፈራራትን ከሰማን የያዝንውን የእግዚአብሄር ቃል እውነት እንጥላለን፡፡ ነገር ግን ብራብም ባጣም አላዬን አልሸጥም ካልን ብንራብም ብናጣም ምንም አንሆንም ነገር ግን አላችን እናስፈጽማለን፡፡ ሃዋሪያው መጥገብንም መዋረድንም አውቀዋለሁ ሲል የማያውቅህን ሄደህ አስፈራራ የሚል ይመስላል፡፡ ሃዋሪያው ማግኘትንም ማጣትንም ልካቸውን ስላወቀ አንዳቸውም ከአላማው አያስፈራሩትም አያስቆሙትም፡፡ ማጣትና መዋረድ የሚያስፈራውና የሚያስቆመው የማያውቀውን ሰው ነው፡፡ መጉደልን የሚያውቅ ሰው ሁሉን የሚያስችለው እግዚአብሄር እንጂ መራብ በህይወቱ ላይ ምንም ስለማይቀንስ መብዛት በህይወቱ ላይ ምንም ስለማይጨምር ማጣት አያስፈራራውም፡፡

እኛ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ስንፈልግ ለሆድ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ይሰጠናል ብለን የእግዚአብሄርን ቃል ካመንን  የእግዚአብሄርን ፈቃድ በዘመናችን አገልግለን ማለፍ እንችላለን፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡12-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ድሆች ስንሆን

1-techcompanie.jpg

በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡7-9

ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ለጻድቃን አይደለም፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ለበሽተኞች ነው፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ለሃያላን አይደለም ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ለደካሞችነው፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ምንም አያስፈልገንም ለሚሉ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ለድሆች ነው፡፡

የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። የሉቃስ ወንጌል 4፡17-19

የአገልጋይ ክብሩ ደሃን ባለጠጋ ማድረግ ነው፡፡ እውነተኛ አገልጋይ የሚፈልገው ደሃን ነው፡፡ እውነመተኛ አገልጋይ ድሃን ባለጠጋ ያደርጋል፡፡

ዳዊትን የተከተሉት ሰዎች እጅግ የተጣሉ የተጨነቁና የተከፉትን ሰዎች ነበር፡፡

የተጨነቀውም ሁሉ፥ ብድርም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተከማቸ፤ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 22፡2

ዳዊትን የተከተለውን የተጨነቀውም ሁሉ፥ ብድርም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ የምድሪቱ ሃያላን አደረገው፡፡

ሦስቱም ኃያላን የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፥ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 23፡16

የአገልጋይ ክብር ምንም ያልሆነውንና ምንም የሌለውን ሰው አጥቦና አሸላልሞ ባለጠጋ ማድረግ ነው፡፡

ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡9

የአገልጋይ ክብር ድሆችን በነገር ሁሉ ባለጠጋ ማድረግ ነው፡፡

ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡5-6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ abiy Wakuma dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ያልታወቁ #የታወቅን #የምንሞት #ሕያዋን #የተቀጣን #አንገደልም  #ኀዘንተኞች #ደስ #ድሆች #ባለጠጎች #የሌለን  #ሁሉየእኛነው #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል

success11.jpgነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡2-3

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እርሱን እንዲያመልከውና እንዲታዘዘው ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ቃሉን እንዲሰማና እንዲያደርግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በቃሉ አንዲኖር ነው፡፡

እግዚአብሄር በሌላ ነገር ሳይሆን በቃሉ ደስ የሚሰኝን ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሌላን ነገር ሳይሆን ቃሉን የሚሰማን ሰው ይፈልጋል፡፡

አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9

እግዚአብሄር ሌላ ነገርን ሳይሆን ቃሉን የሚያስብን ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን በቀንና በሌሊት የሚያሰብን ሰው ይፈልጋል፡፡

በረከትና ስኬት ያለው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናሰላስል እና ስናደርገው ህይወታችን ፈፅሞ ይለወጣል፡፡

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8

የእግዚአብሄርን ቃል የሚያሰላስልና የሚያደርግ ሰው እግዚአብሄር ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ የተሳካ እንደሆነ ሁሉ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስብና የሚያደርግ ስው በሚሰራው ሁሉ ይከናወናል፡፡

ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ቃል #ምስጉን #ሃሳብ #ማሰላሰል #ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #አቢይ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስኬት #ክንውን ###ፌስቡክ #አዋጅ

We Are Meant to Thrive, Not Just Survive

Untitled-1.jpgWe are created by God for a specific purpose. We are created in His glory. We are not here by accident. We are created on purpose. We are here to have dominion.

We are not just surviving; we are not here just to keep ourselves from perishing. We are not here to continue to live or exist. We are not here just to continue living in spite of danger or hardship.

It is one thing to get by and completely another thing to flourish in life. It is one thing to get along with life and another thing to prosper in life.

How pity we are if we are just surviving, what pity is that if we are just existing.

If only for this life we have hope in Christ, we are of all people most to be pitied. 1 Corinthians 15:19

Yes, off-course we are meant to survive life situations. We are meant to survive life circumstances and situations. We are meant to service life trails and temptations.

But it isn’t that. It isn’t only surviving. It isn’t only to survive temptation. It isn’t only self-protection. It isn’t only self-defense.

We are not here for eating and drinking. We have a higher vision of seeking the Kingdome of God and his righteousness. We are on a mission.

So do not worry, saying, ‘What shall we eat?’ or ‘What shall we drink?’ or ‘What shall we wear?’ But seek first his kingdom and his righteousness, and all these things will be given to you as well. Matthew 6:31, 33

We have a purpose to fulfill. We have a kingdom to advance its interest. We are here to enforce the will of God on earth as it is in heaven.

We are not here just to protect ourselves from the devil. We are here to destroy the work of the devil.

The one who does what is sinful is of the devil, because the devil has been sinning from the beginning. The reason the Son of God appeared was to destroy the devil’s work. 1 John 3:8

We are equipped in such a way that the gates of hell shall not prevail against us. We go and plunder the kingdom of darkness. We go and preach the gospel. We snatch others as from fire.

save others by snatching them from the fire; to others show mercy, mixed with fear—hating even the clothing stained by corrupted flesh. Jude 23

We are meant to prosper. We are meant to be offensive. We are meant to attack the kingdom of the enemy. We are active doing the work of God.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#persecution #blessed #temptation #survive #thrive #trial #tribulation #faith #church #perseverance #preaching #salvation #bible #countingthecost #test #facebook #abiywakuma #abiywakumadinsa

የእውነተኛ ባለጠጋ አስራ ሶስት ምልክቶች

wealth.jpgብዙ ባለጠጋ ያልሆነ ሰው ባለጠጋ እንደሆነ ለመምሰል ይጥራል፡፡ እውነተኛን ባለጠጋ የምንለየው በአስተሳሰቡ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በአስተሳሰቡ የበለጠገ ነው፡፡

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ማንም ባለጠጋ መሆን እንደሚችል ያምናል፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ እርሱ ባለጠጋ የሆነው እርሱ ብቻውን ሱፐር ስታር ስለሆነ እንደሆነ አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠጋ የሆነው እርሱ ብቻውን የተመረቀ ስለሆነ አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ማንም እግዚአብሄር ጊዜውን ያመጣለት ሰው ባለጠጋ ሊሆን እንደሚችል ያምናል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ሲያድግ አብረውት ማደግ ያለባቸው ሰዎች እንዳሉ ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ እድገቱን በራሱ ላይ ብቻ አያውለውም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ አብሮ በማደግ ሌሎችን በማንሳት ያምናል፡፡

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን አይፈራም፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን ያውቀዋል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የድህነትን ውስንነት ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትን አይፈራም ባለጠግነትን አያከብርም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነት እንዳይመጣባቸው ማናቸውንም የተሳሳተ ነገር እንደሚያደርጉት ሰዎች ድህነትን አይሰግድለትም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የድህነትንም የብልጥግናንም ልካቸውን ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ድህነትም ሃብት ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚያኖር ያውቃል፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12-13

 1. ባለጠጋ የሆነ ሰው ባለጠጋ ለመምሰልና ባለጠግነቱን ለማሳየት አይጥርም፡፡

ባለጠጋ የሆነ ሰው አላማውን ይኖራል፡፡ ባለጠጋ የሆነ ሰው ከማንም ጋር አይፎካከርም፡፡ ባለጠጋ የሆነ ሰው ማንንም ለመብለጥ አይጥርም፡፡ ባለጠጋ ጎረቤቱን ተንጠራርቶ ሳያይ በቤቱ የሚያስፈልገውን ብቻ ያደርጋል፡፡

ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤

እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና። ገላትያ 6፡4-5

 1. ባለጠጋ የሆነ ሰው ማንም ሰው ባለጠጋ ሊሆን እንደሚችል ያምናል

እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት የውስጥ እንደሆነ ያምናል፡፡ እውነተዓ ባለጠጋ ባለጠግነቱ ብርጭቆ ከእጅ ወድቆ እንደሚሰበር አጣለሁ ብሎ አይፈራም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በድንገት ባለጠግነቱን እንደሚያጣው አያስብም፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት በገንዘብ ውስጥ በእውቀት ውስጥና በሃይል ውስጥ ሳይሆን እውነተኛ ባለጠግነት በሰው ውስጥ እንዳለ ያምናል፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት መንፈሳዊ ስሌት እንደሆነ ያስባል፡፡ እውነተኛ ባለጠግነት ከምድራዊ አካውንት ጋር የማይጨምርና የማይቀንስ ልዩ መንፈሳዊ አካውንት እንደሆነ ያውቃል፡፡

በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ፊልጵስዩስ 4፡17

 1. እውነተኛ ባለጠጋ በመልካም ስራ ባለጠግነቱ ይታወቃል፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ መታወቅ የሚፈልገው ባለው ገንዘብ ሳይሆን ባለው ገንዘብ ተጠቅሞ በሰራው መልካም ስራ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት በመልካም ስራ እንጂ በገንዘብ እንዳይደለ ያውቃል፡፡

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19

 1. እውነተኛ ባለጠጋ በምህረትም በይቅርታም የበለጠገ ነው፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነቱ ግንጥል ጌጥ ያለሆነ በሁሉም የህይወት ዘርፉ ያደገ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በነፍሱ የበለጠገ ነው፡፡

ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። 3ኛ ዮሐንስ 1፡2

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ኤፌሶን 2፡4

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ልቡ ሰፊ ነው

እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘብ እንደሚመጣና እንደሚሄድ የሚረዳ ከምንም በላይ ለሰው ልጅ አክብሮት ያለው ልቡ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ቋጣሪ አይደለም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ የእሱ በረከት ከሰው ጋር እንደማይገናኝና የገንዘቡን ንጥቂያ በፀጋ የሚቀበል ነው፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እብራዊያን 10፡34

 1. እውነተኛ ባለጠጋ በቅንጦት ላይ ገንዘቡን ላለማጥፋት ይጠነቀቃል፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ያለው ገንዘብ መሰረታዊ ፍላጎት ማሟያ እንደሆነ የቀረው ግን የሚያካፍለውና የሚሰጠው እንደሆነ ያውቃል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ በቅንጦት ላይ ገንዘቡን ላለማባከን የለመደ በልክ የሚኖር ሰው ነው፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:6-8

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘቡን እጅግ አስተማማኝ ቦታ ላይ የሚያከማችና እጅግ አትራፊ ነፍስን የሚያድንበት ቦታ ላይ የሚዘራ ነው፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ማቴዎስ 6፡19-21

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9

 1. እውነተኛ ባለጠጋ በህይወት እጅግ አስፈላጊ ነገሮች ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችሉ በነፃ የሚሰጡ ስጦታዎች እንደሆኑ ያስባል፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ገንዘብ እጅግ ውስን እንደሆነና ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው እጅግ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ያውቃል፡፡

እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡4

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ኑሮውን እየኖረ እየተደሰተ እንጂ ባለጠጋ ለመሆን ህይወትን አያቆምም ደስታውንም ለወደፊት አያስተላልፍም፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት የህይወትን ስጦታ አያጎሳቁልም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ወዳጁም አያጣም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ደስታውን አያጣም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት ሰላሙን የሚያሳጣ ነገር አያደርግም፡፡ እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት የሰውን በጎ ፈቃድ የሚያሳጣውን ነገር አያደርግም፡፡

እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡18-19

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ለባለጠግነት አይቸኩልም፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ባለጠግነት በጊዜ ውስጥ በሚፈታን ታማኝነት የሚገኝ እንጂ በአንዴ የማይገኝ እንደሆነ ያውቃል፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11

 1. እውነተኛ ባለጠጋ ስለሃብቱ አይመካም፡፡

እውነተኛ ባለጠጋ ስለሃብቱ እግዚአብሄርን ብቻ ያመሰግናል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 9፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህ – ከውስጥ ወደ ውጭ የሆነ ክንውን

How+to+stop+the+fighting+in+your+family+(4).pngወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። 3ኛ ዮሐንስ 1፡2

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በለመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለክንውን ነው፡፡ እግዚአብሄር ለውድቀት የፈጠረው ሰው አልነበረም፡፡

ሰው በሃጢያት ምክንያት ክንውንን ከህይወቱ አጣው፡፡

ኢየሱስ ወደምድር የመጣው የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ለመክፈልና የእግዚአብሄር ልጅነትን ክንውን በህይወታችን ሊመልስ ነው፡፡

እውነተኛ ክንውን ደግሞ የሚጀምረው ከውስጥ ነው፡፡ ሰው ሲከናወንለት መጀመሪያ በነፍሲ ይከናወንለታል፡፡ በውጭው የሚከናወንለት ሰው ተከናወነለት አይባል፡፡ ነፍሱ ያልተከናወነችና በነፍሱ የተቀብዘበዘ ክንውኑ የውሸት ክንውን ነው፡፡ እግዚአብሄር ውጫችን እንዲከናወን የሚፈልገው የውጭውን ክንውን የሚሸከመው ውስጣችን በተከናወነ መጠን ነው፡፡ የውጭውን ክንውን የሚያስተዳደረው የውስጣችን ባህሪያን በተሰራና ባደገ መጠን ውጫችን እንዲከናወን እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

ታላቁና ክንውን የነፍስ ክንውን ነው፡፡ ታላቁ ክንውን የነፍስ ነፃ መውጣት ነው፡፡ ትልቁ ክንውን የነፍስ ከጥላቻ ከመራርነት ከመቅበዝበዝ ነፃ መውጣት ነው፡፡

የነፍስ ክንውን መገለጫዎች

ፍቅር

በፍቅር የሚመላለስ ሰው እውነተኛ የተከናወነለት ሰው ነው፡፡ በጥላቻ የሚኖር ሰው በእስራት ይኖራል፡፡ በጥላቻ የሚኖር ሰው በጨለማ ይኖራል፡፡ በጥላቻ የሚኖር ሰው በስቃይና በጉስቁልና ይኖታል፡፡

እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 4፡16

ሰላም

ሰው ሰላም ካለው ሃብታም ነው፡፡ ሰላም የሌላው ሰው ምንም ቢኖረው ጎስቋላ ነው፡፡ ሰው ሰላም ከሌለው ደካማ ነው አቅምም የለውም፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

እርካታ

ሰው ባለው ነገር ካልረካ በጉድለት ይኖራል፡፡ ሰው ባለው ነገርና በደረሰበት ደረጃ ራሱን ካማጠነና ከረካ በነፃነት ይኖራል፡፡

ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡4

ደስታ

የልብ ደስታ የሌለውና የሚያዝን ሰው ደካማ ይሆናል፡፡ የልብ ደስታ ሃይላችን ነው፡፡ ሰው በጌታ ያለው ደስታ ከምንም ሃዘን በላይ ከሆነ እንዳይጎዳ ይጠብቀዋል፡፡ ሰው በምድራዊ ማግኘትና ማጣት ደስታው ከፍና ዝቅ የማይል ሰው የተከናወነለት ሰው ነው፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4

ምሪት

ምሪት ያለው ሰው የት እንዳለ ወደየት እንደሚሄድ የሚያውቅ ሰው ብርሃን አለው፡፡ ሰው ግን የሚሄድበትን ካላወቀ ሲደርስም አያውቅም፡፡ ሰው የሚሄድበትን ካላወቀ መቼ እንደሚሰናከል አያውቅም፡፡

ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል። ምሳሌ 19፡2

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡17-19

የልብ ንፅህና

ሰው መሃሪና ይቅር ባይ ካልሆነ አልተከናወነለትም፡፡ ልቡ ንፁህ ላልሆነ ሰው እውነተኛ ክንውን የማይታሰብ ነው፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21

እምነት

ሰው እግዚአብሄርን ካመነ የተከናወነለት ሰው ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። እብራዊያን 11፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ደስታ #እርካታ #ሰላም #ምሪት #ፍቅር #እምነት #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

የፍላጎትና የቅንጦት መለያ መንገድ

tumblr_static_lamborghini-gallardo-luxury-car.jpg

ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረው ሰው የተፈጠረው ለተወሰነ አላማና ግብ ነው፡፡ ሰው ሁሉንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ ሰው በምድር ላይ ማድረግ የሚችለው የተወሰነውን የእግዚአብሄርን ልዩ አላማ ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሄርን ስንከተል እርሱ የሚያስፈልገንን ሁሉ ያሟላል፡፡ እግዚአብሄር የሚያቀርብልን የሚያስፈልገንን ነገር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር የምንፈልገውን ነገር ሁሉ አያቀርብልንም፡፡ ሰውም የሚያገኘው አቅርቦት በተጠራበት በተለየ አላማ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሰው የሚያቀርበው ለፈጠረው አላማ ብቻ ነው፡፡  የፈጠረው ሰው የሚያስፈልገው ነገር እንዳይጎድልበት እግዚአብሄር በትጋት ይሰራል፡፡ ለመሰረታዊ ፍላጎታችን ሁሉ እግዚአብሄር ሙሉ ሃላፊነትን ይወስዳል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ለቅንጦት ፍላጎታችን ሃላፊነት አይወስድም፡፡

የሰው ስኬት የሚወሰነው በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት በመቻሉ ላይ ነው፡፡ የሰው ተግባራዊ ጥበብ የሚለካው በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት በመረዳቱ ነው፡፡ በቅንጦትና በመሰረታዊ ፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ አንዳንዴ ቀላል ባይሆንም ስለሁለቱ ልዩነት ከእግዚአብሄር ቃል መማር እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃልን ከተመለከትንና ከተረዳን ህይወታችንን በመሰረታዊ ፍላጎት ላይ ብቻ በማተኮር እግዚአብሄር የሚሰጠንን አቅርቦት ለታለመለት አላማ በሚገባ መጠቀም እንችላለን፡፡

ሁለት ተመሳሳይ ሰዎችን የሚለየው ይህ መርህ ነው፡፡ አንዱ ያገኘውን ነገር ሁሉ ራሱን በመግዛት በሚያስፈልገው በመሰረታዊ ፍላጎት ላይ ብቻ ያጠፋዋል፡፡ ሌላው ደግሞ በሚፈልገው ነገር ላይ ሁሉ ማጥፋት ሲጀምር የሚያስፈልገው ዋናው ነገር ይጎድለዋል፡፡

ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል። ምሳሌ 12፡9

የሚበላው ሳይኖረው ከሚኵራራ ይልቅ፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ ሠራተኛ የሚያሳድር ይሻላል። ምሳሌ 12፡9 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ብዙን ጊዜ ችግራችን የእግዚአብሄር አቅርቦት ማግኘት እጥረት አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ችግራችን መሰረታዊ ፍላጎትንና ቅንጦትን መለየት  አለመቻላችንና ለመሰረታዊ ፍላጎት የተሰጠንን አቅርቦት በቅንጦት ላይ ስለምናውለው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ከራሳችንና ከሰዎች ጋር ሰላም የምናጣው ከመሰረታዊ ፍላጎት አልፈን ለቅንጦት ስንሮጥ ነው፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡1፣3

በክርስትና ስኬታማ ለመሆን የመሰረታዊ ፍላጎት መርህ ሊገባን ይገባል፡፡ በህይወት ለመሳካት መሰረታዊ ፍላጎትን ከቅንጦት መለየት አስፈላጊ ስለሆነ ሁለቱን እንዴት እንደምንለይ ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡፡

መሰረታዊ ፍላጎትን መለያው መንገዶች

 1. መሰረታዊ ፍላጎት ግዴታ የሆነ ነገር ነው፡፡

መሰረታዊ ፍላጎት በጣም ግዴታ ከመሆኑ የተነሳ ፍላጎታችን ካልተሟላ የህይወት አላማችንን መፈፀም አንችልም፡፡ መሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄር በምድር ላይ ያስቀመጠንን ልዩ አላማ ለመፈፀም ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡8

አንዳንዴ ግን አጥተነው እስካላየን ድረስ ብዙ ነገሮች የሚያስፈክልጉን ይመስለናል፡፡ አጥተነው ግን ምንም ሳንሆን በተግባር እስካላየን ድረስ የማንረዳው ብዙ የሚያስፈልጉ የሚመስሉን ነገር ግን የማያስፈልጉ ነገሮች አሉ፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡12-13

ለምሳሌ የምግብ አላማ ብርታት መስጠት ፣ ሰውነታችንን መገንባትና ከበሽታ መከላለከል ነው፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርግልን ምግብ መብላት መሰረታዊ ፍላጎት ሲሆን ስለምግቡ ጣእም ፣ ስለምግቡ ትኩስነትና ቅዝቃዜ ከተነጋገርን ግን ስለመሰረታዊ ፍላጎት ሳይሆን ስለምቾት ወይም ቅንጦት እየተነጋገርን ነው፡፡ ቅንጦት ቢገኝ ጥሪ ነው ነገር ግን ግዴታ አይደለም፡፡

ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ። ሐጌ 1፡6

 1. መሰረታዊ ፍላጎት ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው፡፡

በሁለቱ መካከል መምረጥ ግዴታ ከሆነብን የምንመርጠው ነገር መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ መሰረታዊ ፍላጎት የምናስቀድመው ነገር ነው፡፡ ቅንጦት ቢቆይ ችግር የለውም እንዲውም ባይገኝ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም የምንለው ነገር ቅንጦት እንጂ መሰረታዊ ፍላጎት አይደለም፡፡

ለዚህ ምሳሌ የሚሆንን የእስራኤል ህዝብ ነው፡፡ የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ሲወጡ በህይወታቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነፃነታቸው እንጂ በመንገድ ላይ የሚበሉት የምቾት ወይም የቅንጦት ምግብ አልነበረም፡፡ በምድር በዳ ሲጓዙ እግዚአብሄር ሁሉንም ፍላጎት የሚያሟላ ጉልበት የሚሰጥ ፣ ሰውነትን የሚገነባና ከበሽታ የሚከላከል ንጥረ ነገርን ሁሉ ያካተተመናን መናን ሰጣቸው፡፡ የእስራኤ ህዝብ ግን እንደለመዱት አይነት ሆድን ያዝ የሚያደርግ ከበድ ያለ ምግብ ስላልነበረ ስለመና በእግዚአብሄር ላይ አጉረመረሙ፡፡ የእስራኤል ህዝብ ጥያቁ የመሰረታዊ ፍላጎት ጥያቄ ሳይሆን የምቾትና የቅንጦት ጥያቄ ነበር፡፡

ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ፦ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ የለም፤ ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ። ዘኍልቍ 21፡5

በሁሉም የህይወታችን አቅጣጫ በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት ተረድረተን ለመሰረታዊ ፍላጎት ቅድሚያ ከሰጠን በህይወታችን ከእኛ አልፈን ብዙዎችን ማገልገል እንችላለን፡፡

ያም ሆነ ይህ የክርስትና የመጨረሻ ደረጃ የመጨረሻው የስኬት ጣራ ስለ መሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ታምኖ ጌታን መከተል ነው፡፡

ፀሎት፡ እግዚአብሄር አምላክ ሆይ ይህንን ቃል እንድሰማ ስለረዳኝ አመሰግናለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በተማርኩት መሰረት ለመሰረታዊ ፋልጎት ቅድሚያ መሰጠት እችል ዘንድ ልዩነቱን ስለምታስተምረኝ አመሰግናለሁ፡፡ በእያንዳንዱም የህይወት ክፍሌ በሁለቱ መካከል መለየት አችል ዘንድ ጥበብን ስለምትሰጠኝና ስለምትረዳኝ አከብርሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ልጅ ስለሆንክ ብቻ

primary-education-in-ethiopia.jpgእግዚአብሄር የሚንከባከበን ስለሰራንና ወይም ስላልሰራን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚንከባከበን ልጅ ስለሆንን ብቻ ነው፡፡ የትኛው ወላጅ ነው በቤቱ የተወለደ ልጁ ስራ ሲሰራ የሚመግበው ካልሰራ ደግሞ ምግብን የሚከለክለው? ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቱ የሚሟላው ልጅ ስለሆነና በቤተሰቡ ውስጥ ስለተወለደ ብቻ ነው፡፡

ታዲያ የምንሰራው ለምድነው?

የምንሰራው የልጅነት መብታችንን ከእግዚአብሄር ለመቀበል አይደለም፡፡ የምንሰራው እግዚአብሄር ልጄን ምን አበላዋለሁ ብሎ ስለተጨነቀ እግዚአብሄርን ለመርዳት አይደለም፡፡ የምንሰራው ስራና በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን የልጅነት መብት  ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ወፎችን የሚመግበው መስሪያ ቤት ሄደው ስለሰሩ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄ ፍጥረት ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡

ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? ማቴዎስ 6፡26

የምንሰራው የክህንነት ሃላፊነታችንን ለመወጣት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን በኋላ እኛን ካህናት አድርጎናል፡፡ ስለእግዚአብሄር ለሰዎች እንመሰከራለን፡፡ በድርጊትም በቃልም ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናለን፡፡ የእግዚአብሄር የምስራች ወንጌል መልክተኞች ነን፡፡

የምንሰራው ለክርስቶስ ምስክርነታችን ሃይል እንዲሰጠን ነው፡፡ ክርስትያን ሰነፍ እንዳልሆነ እንዲያውም ጠንካራ ሰራተኛ እንደሆነና በእግዚአብሄር ፀጋ ተጨማሪ ምእራፍ የሚሄድ እንደሆንን በማሳየት በውስጣችን ስከለሚሰራወ የእግዚአብሄር ፀጋ ምስክር ለመሆን ነው፡፡

እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡10-12

ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡41

የምንሰራው በስራ ቦታችን ላሉት ሰዎች ብርሃን ለመሆን ነው፡፡ የምንንሰራው ከፍ ያለ የእግዚአብሄር ህይወት እንዳለ ለማሳየት ነው፡፡ የምንሰራው የእግዚአብሄር ቃል ሊፈፅሙት የሚቻልና የሚገባ ክቡር ቃል እንደሆነ በህይወታችን ምሳሌ ለመሆን ነው፡፡ የምንሰራው በአካባቢያችን ላሉ ሰዎች የእግዚአብሄር መንግስትን መረዳት ለማካፈል ነው፡፡

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። ማቴዎስ 5፡14-15

የምንሰራው በስራ ለምንገናኛቸው ሰዎች የምድር ጨው ለመሆን ነው፡፡

የምንሰራው በስራ ለሚገናኙን ሰዎች በህይወታችን የእግዚአብሄር መልካምነትን ጣእም ለማቅመስ ነው፡፡

ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን። ቆላስይስ 4፡6

ስራም ስንሰራ የመጀመሪያው ስራችን ለሰዎች የእግዚአብሄር መልካምነት ምስክር መሆን ነው፡፡ እንደ ክርስትያን የመጀመሪያ ጥሪያችን በህይወታችን ስለክርስትና መመስከር እንደመሆኑ መጠን ቀጣሪያችን የምድር ጌታችን ሳይሆን ቀጣሪያችን ጌታ ክርስቶስ ነው፡፡

እንደ ክርስትያን የመጀመሪያ ጥሪያችን ክርስቶስን በመምሰል ለሌሎች መመስከር እንደመሆኑ መጠን ቀጣሪያችንም ከፋያችንንም ጌታ ክርስቶስ ነው፡፡

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላስይስ 4፡23-24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #ልጅነት #ብርሃን #ጨው #ምስክርነት #ጌታክርስቶስ #ርስት #ብድራት #ስራ #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለጠግነትምቾት #አቅርቦት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ህይወትን ፍፁም የሚያደርጉ አምስቱ የእግዚአብሄር አቅርቦቶች

wheat.pngበህይወት ለማግኘት የምንፈልገውና እንዲሆንልን የምንጥራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ህይወት በራሱ ፍፁም አይደለም ጉድለት አለው፡፡ ህይወት በራሱ ፍፁም አይደለም፡፡ ህይወትን ምንም ሳይጎድለው ፍፁም የሚያደርገው የእግዚአብሄር አሰራር ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። 2ኛ ዜና 16፡9

ህይወትን ፍፁም የሚያደርገው አምስቱ የእግዚአብሄር አሰራሮችን እንመልከት

 1. ስንደክም የሚያበረታን የእግዚአብሄር ሃይል

ሰው በሃይሉ አይበረታም፡፡ ሰው ይደክማል፡፡ ሰው በራሱ መሄድ የሚችለው ትንሽ ነው፡፡ ሰው በራሱ ሃይል ብቻ ከታመነ እግዚአብሄር በህይወቱ ያቀደውን ከፍ ያለ ሃሳብ መፈፀም ይሳነዋል፡፡ ሰው  በእግዘአብሄር ሃይል ላይ ከተደገፈ ግን የእግዚአብሄርን ሃሳብ በህይወቱ አገልግሎ ማለፍ ይችላል፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9

 1. ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርግ የእግዚአብሄር ሞገስ

ሰው በተፈጥሮው ሰውን ለመውደድ ብዙ መመዘኛዎች አሉት፡፡ ሰው ግን ካለምክኒያት እንዲወደን የሚያደርግ የእግዚአብሄር አሰራር ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያየው ቦታ እንድንደርስ ሞገስን ይሰጠናል፡፡ ሰዎች ፊታችንን ሲቀበሉና ሃሳባችንን ሲሰሙና ሲቀበሉ ስናይ የእግዚአብሄርን ድንቅ አሰራር እንመለከትበታለን፡፡

እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ። ኢሳይያስ 55፡5

በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤ ሮሜ 1፡5

ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡12

 1. አስተዋይ የሚያደርግ የእግዚአብሄር ጥበብ

የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን ፈፅመን እግዚአብሄርን በምድር ላይ እንድናከብረው እግዚአብሄር ብርሃንን ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሄር ከአስተማሪዎቻችን ይልቅ ጥበበኛ ያደርገናል፡፡ የምናልፈው ከማይመስለን ከባድ ፈተና ሊታደገን እግዚአብሄር መረዳትን በመስጠት መውጫውን ያዘጋጃልናል፡፡ አስበን የማናውቅውን ጥልቀ ነገር መረዳትን ይሰጠናል፡፡ በጥናትና በአእምሮ እውቀት የማይመጣ መገለጥ በህይወታችን ሲመጣ እግዚአብሄር በህይወታችን ሊሰራ ላለው ተልእኮ አስፈላጊ ስለሆነ በቀላሉ ለመረዳት የማይቻለውን የመንፈስን ነገር መረዳትን እናገኛለን፡፡

እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። የሰሎሞንም ጥበብ በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብጽ ጥበብ ሁሉ በለጠ። 1ኛ ነገሥት 4፡29-30

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5

 1. የእግዚአብሄር አቅርቦት

 

እግዚአብሄር ወደጠራን ጥሪ መግባት እንድንችል ይኖረናለ ብለን የማንገምተውን የገንዘብ አቅርቦት እግዚአብሄር ወደእኛ ሲያመጣ የእግዚአብሄርን አሰራር እናይበታለን፡፡

በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡8-9

 1. ከሃዘን በላይ የሚያደርገን ሰላምና ደስታ

 

በምድር ላይ የሚያሳዝኑ ብዙ ነገሮች ይገጥሙናል፡፡ ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር እያለ ከሃዘን በላይ እንድንኖር የሚደርገን የእግዚአብሄር ስጦታ ደስታ ነው፡፡ ሊሰብረን የመጣው ሃዘን እንደፈሳሽ ውሃ ያልፋል፡፡ ሊያስቆመን የመጣው ሃዘን በልባችን ባለው ደስታ ይዋጣል፡፡ ልባችን ሊሰብር የመጣው ሃዘን አቅም ያጣል፡፡

እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም። ዮሃንስ 16፡22

በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል  #በረከት #ስኬት #ጥበብ #ማስተዋል #ሞገስ #አቅርቦት #ሃይል #ፀጋ #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን

3dd2ec58bd3d62ca64f1dc59c8688fca.jpgያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10

በአብ ቀኝ በክርስቶስ መቀመጣችን ሁሉንም የህይወት ጥያቄያችንን ይመልሳል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ባለን የክብር ብዛት ውርደትን እንታገሳለን፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ባለን ስፍራ ሰዎች የሚጋደሉለትን የምድርን ነገር ሃብት ፣ ዝና እና ስልጣን እንንቃለን፡፡

በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ኤፌሶን 2፡6-7

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2

 1. ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፡፡

በምድር ላይ ታዋቂ ላንሆን አንችላለን፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ግን ታዋቂዎች ነን፡፡ እግዚአብሄር ልኮናል ፣ እግዚአብሄር ያውቀናል ፣ እግዚአብሄር ተደስቶብናል፡፡ ሰው እንደሚያይ የማያየው እግዚአብሄር ያውቀናል፡፡ ሰው የናቀውን የሚያከብር እግዚአብሄር ዋጋ ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዬ ልንለው የሚገባው የእግዚአብሄርን እይታ ብቻ ነው፡፡ በሰው ዘንድ ለመታወቅ ጉልበታችን አንጨርስም፡፡ ለጠራን ለመሮጥ እንጂ ለታዋቂነት ለመፍጨርጨር ትርፍ ጊዜ የለንም፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን እንድንፈፅመው የጠራንን ጥሪ በዝምታ እንፈፅማለን፡፡  ሰው እንደ እግዚአብሄር አያውቀንም የሰው ማክበርን ማዋረድም አያስደንቀንም፡፡ በሰው ዘንድ ያልታወቅን ስንባል የታወቅን ነን፡፡ ሰውንም ለማስደሰት በምድር ላይ የለንም፡፡

ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ዮሃንስ 12፡43

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ገላትያ 1፡10

 1. የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፡፡

የምንሰራው ምድራዊ እና ስጋዊ ነገር አይደለም፡፡ የምንኖረው ፣ የምንወጣውና የምንገባው በራሳችን ጉልበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር እርዳታ በሃይል ከእኛ ጋር አለ፡፡ እንድንኖርለትና እንድናገለግለው የጠራን በሃይል ከእኛ ጋር ይሰራል፡፡ ምንም በጎ ነገር ቢገኝብን ከእርሱ ነው፡፡ በራሳችን ስንደክም እንኳን የእርሱ ሃይል ተሸክሞ ያሻግረናል፡፡ ስንደክም የእግዚአብሄ ፀጋ ይበዛልናል፡፡ ስንዋረድ እግዚአብሄር ያከብረናል፡፡ ስንደክም ያን ጊዜ ሃይለኛ ነን፡፡ የውጭ ሰውነታችን ሲጠፋ የውስጡ ሰውነታችን እለት እለት ይታደሳል፡፡ የምንሞት ስንመስል ህያዋን እየሆንን ነው፡፡

ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16

በተዋረድን ቁጥር እየጠለቅን ስር እየሰደድንና መሰረታችን እየሰፋ ነው፡፡ እምነታችን ሲፈተን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተንና ይበልጥ እንደሚጠራ እምነታችን እየጠራና እየከበረ ነው፡፡

በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡6-7

 1. የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፡፡

ሰዎች የተለያየ ነገር ቢያደርጉን አያስቆሙንም፡፡ ምናችንንም ቢወስዱብን ራእያችችንን ፣ እምነታችንንና አገልግሎታችንን ሊወስዱብን አይችሉም፡፡ ሰዎች ሊያጠፉን ቢፈልጉ የእግዚአብሄር እጅ ከእኛ ጋር ስላል በከንቱ ይደክማሉ፡፡ በእግዚአብሄር ምህረት ስለምንኖር የሰዎችም ይሁን የሰይጣን ቁጣ በህይወታችን ላይ የሚያመጣው ልዩነት የለም፡፡

አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ። ሐዋርያት 5፡38-39

ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 9፡36-37

 1. ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፡፡

በአለም በሚሆነው ነገር እናዝናለን፡፡ ሰዎች ለአለማዊነት ህይወታቸውን ሲሰጡና ለአለም ነገር ሲሮጡ ስናይ ፃድቅ ነፍሳችን ትጨነቃለች፡፡ በጌታ ግን ደስ ይለናል፡፡ በነገሮች ልናዝን እንችላለን በጌታ ግን ሁልጊዜ ደስ ይለናል፡፡ ሰላማችንና ደስታችን አለም እንደሚሰጠው በሁኔታውች የሚለዋወጥ አይደለም፡፡ በመከራ ብናልፍም በጌታ ግን ደስ ይለናል፡፡ በአለም ያለውን መከራ የምንፈጋፈጠው በደስታ ነው፡፡ በአለም ያለው የሚያሳዝን ነገር ሁሉ ተሰብስቦ በልባችን ያለውን ደስታ ሊያጠፋው አቅም የለውም፡፡ በልባችን ያለው ደስታ ከአለም ሃዘን ሁሉ ይበልጣል፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4

 1. ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፡፡

ራእያችን ሰዎችን ማገልገል እንጂ ለራሳችን መጠቀም አይደለም፡፡ ራእያችን ሰዎችን ማንሳት እንጂ ራሳችን መነሳት አይደለም፡፡ ራእያችን ሰዎችን ማገልገል እንጂ በሰዎች መገልገል አይደለም፡፡ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት እጅግ ከመባረካችን የተነሳ ለምንበላውና ለምንጠጣው አንጨነቅም፡፡ የሚያሳስበን የሰዎች መባረክ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቀኝ ከመቀመጣችን የተነሳ የዘወትር ሸክማችን ሰዎችን ባለጠጋ ማድረግ ነው፡፡

የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡28

የሚያረካን ሰዎች ሲለወጡ ማየት ነው፡፡ የምንረካው ሰዎች ካሉበት ነገር ሲወጡ ነው፡፡ የምንረካው ሰዎች ከከበባቸው ነገር አልፈው ሲሻገሩ ነው፡፡ የገንዘብ ሃብት ባይኖረንም የሰው ሃብታሞች ነን፡፡ ተቀማጭ ገንዘብ ባይኖረንም በገንዘባችን ያፈራናቸው በሰማይ የሚቀበሉን ሰዎች አሉ፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9

የሰው መንፈሳዊነት እና ስኬት ባገኘው ገንዘብ የሚሰራው ስራ እንጂ ባጠራቀመው በምድራዊ ሃብቱ አይለካም፡፡ በምድር ቤተመንግስት ላናስገነባ አንችላለን በህይወታችን ዘመን ሁሉ የእግዚአብሄርን ቤተክርስትያን በገንዘባችን እንደግፋለን፡፡ የብዙ ገንዘብ ባለቤቶች ባንሆንም ባለን ገንዘብ የመልካም ነገር ባለጠጎች ነን፡፡

ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19

የስራችን የምስክር ደብዳቤ በብእርና ቀለም የተፃፈ ሳይሆን በእኛ አማካኝነት የእግዚአብሄር ቃል በልባቸው የተፃፈ ሰዎች ናቸው፡፡

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 3፡1-2

 1. አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው፡፡

በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተባርከናል፡፡ ያለን ትልቁ ሃብት የእግዚአብሄር አቅርቦት ነው፡፡ ያለን ትልቁ ሃብት በእኛ ስም የተከፈተልን መንፈሳዊ ሂሳብ ወይም አካውንት ነው፡፡ እጃችን ባዶ ቢሆንም ከባለጠጋው አባታችን በእምነት እንዴት እንደምንቀብል የምናውቅ የእምነት ባለጠጎች ነን፡፡ ኪሳችን ባዶ ቢሆንም የሚያስፈልገንን ነገር በሚያስፈልገን ጊዜ የማያሳጣን እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡ የሚታይ ሃብት ባይኖረንም የሚያስፈልገንን ሁሉ የምናገኝበት የማይታይ ሃብት አለን፡፡ ምድራዊ ሃብት ባይኖረንም እግዚአብሄርን የምናስደስትበትና ፈቃዱን በምድር ላይ የምንፈፅምበር እምነት አለን፡፡

በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ፊልጵስዩስ 4፡17

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ክርስቶስን የሰጠን እግዚአብሄር አብሮ ሁሉንም ሰጥቶናል፡፡ የሚጎድለን እንዳይኖር አድርጎ በሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ባርኮናል፡፡

ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡21-23

ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡9-10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ያልታወቁ #የታወቅን #የምንሞት #ሕያዋን #የተቀጣን #አንገደልም  #ኀዘንተኞች #ደስ #ድሆች #ባለጠጎች #የሌለን  #ሁሉየእኛነው #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የመንግስቱ ኢኮኖሚ – ኢንቨስትመንት

money-growth-investment-seed-ss-1920-770x300.jpgኢንቨስትመንት ማለት በአንድ አትራፊ ነገር ላይ መዋእለ ኑዋይን ማፍሰስ ማለት ነው፡፡

በተለይ ገንዘባችንን ለእግዚአብሄር ቤት ሰጥተን ፣ መሰረታዊ ፍላጎታችንን አሟልተን የሚተርፈውን ገንዘብ መልሰን ኢንቨስት ብናደርገው ተጨማሪ ውጤት ይሰጠናል፡፡

ገንዘብን ጥሩ ወለድ በሚሰጥበት ባንክ በማስቀመጥ ጥሩ የወለድ ትርፍ ማግኘት ያቻላል፡፡

ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ማቴዎስ 25፡27

እኛን በግል የማይፈልገን እንደ አክሲዮን በመግዛት ገቢያችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ እንዲሁም ንብረት በመግዛትና በማከራየት በመሳሰሉት ላይ ኢንቨስት ብናደርገው ስራው እኛን በግል ሳይፈልገንና ተቀጣሪ ሳያደርገን ገቢያችንን ያሳድጋል፡፡ እንዲሁም እኛን በግል የማይፈልግ ኢንቨስትመንት ስራ መስራት ባልቻልንበት ጊዜ እንኳን ገንዘባችን ለእኛ ስለሚሰራ ገቢያችን አይቋረጥም፡፡

ኢንቨስትመንት ተቀጥረን ከምንሰራበት ከምናገኘው ገንዘብ በተጨማሪ እኛን በግል የማይፈልገን ኢንቨስትመንትና ትርፍ ይኖረናል ማለት ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የግል ስራችንን ብንሰራ እንኳን ከስራችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የገቢያችንን አይነትና መጠን ማብዛት እንችላለን፡፡

ለምሳሌ ጋራዥ ያለው ሰው ተጨማሪ ገንዘቡን የተበላሸ መኪና ገዝቶ በመጠገን መኪና በማሻሻጥ በመሳሰኩት ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ኢንቨስት ቢያደርግ ተጨማሪ ትርፍ ያገኛል ለእግዚአብሄርም መንግስት የሚሰጠው ገንዘብ ይበዛል፡፡

የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ። ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል። ምሳሌ 27፡13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ኢንቨስትመንት #ገቢ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የመንግስቱ ኢኮኖሚ – ገንዘብን ማስቀመጥ

save.jpgበምድር ስንኖር በጥበብ መኖር እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ከገንዘብና ከሃብት በላይ እንዴት እንደምናስተዳደረው ማወቅ ገንዘቡን ለሚገባው አላማ እንድናውለው ይረዳል፡፡ ጥበብ ከብዙ ውጣ ውረዶች ይጠብቀናል፡፡

በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። ምሳሌ 3፡14

ገንዘብን ማጠራቀም ወይም መጠባበቂያ ገንዘብን ማስቀመጥ በጣም ጠቃሚ በመሆኑ ካላስፈላጊ ውጣ ውረዶች ያድነናል፡፡ አንዳንድ ወር ወጭው ይበዛል፡፡ ሌላው ወር ደግሞ ወጭው ያንሳል፡፡ በዚህ መሰረታዊ ፍላጎታችንን ካሟላን በኋላ የግዴታ የቀረውን ገንዘብ ሁሉ በቅንጦት ላይ ማዋልና መጨረስ የለብንም፡፡ ከመሰረታዊ ፍላጎት ተረፍ ያለ ገንዘብ በሚመጣ ጊዜ ወደፊት ፍላጎት እንዳለ አውቀን  የተረፈውን ገንዘብ አጥፍቶ አለመጨረስና መያዝ ያስፈልጋል፡፡

ያለንን ገንዘብ ሁሉ አጥፍቶ አለመጨረስ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ጥበብ ነው፡፡

የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20

ገቢዎች ይለዋወጣሉ፡፡ ገቢ ሲለዋወጥ ኑሮዋችንም አብሮ ከፍና ዝቅ እንዳይል ገንዘብ ተረፍ ብሎ በሚለመጣበት ጊዜ ለወደፊት ማስቀመጥ ይጠቅማል፡፡

በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል። ምሳሌ 10፡5

ከመሰረታዊ ፍላጎት የተረፈውን ስናስቀምጠው ነው በተሻለ ነገር ላይ ማፍሰስ የምንችለው፡፡ ስናጠራቅም ብቻ ነው ገቢያችንን ለማስፋት በተለያዩ ነገሮች ላይ ኢንቨስት የምናደርገው፡፡

የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ። ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል። ምሳሌ 27፡13

ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ ገንዘብ የሚጠራቀምበት ኮሮጆ ነበረው፡፡

ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦ ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥ ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና። ዮሃንስ 13፡29

ይብዛም ይነስም እንጂ ሊቆጥብ ሊያጠራቅም ሊያስቀምጥ የማይችል ሰው የለም፡፡

የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የመንግስቱ ኢኮኖሚ – መስጠት

12741-wallet-cash-money.800w.tn.jpgእኛ የተፈጠርነው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ የተፈጠርነው ሌሎችን ለማገልገል ነው፡፡ ገንዘብን መስጠት ገንዘብን እንደመስራት በጣም ወሳኝ የሆነ ልምምድ ነው፡፡

እግዚአብሄር የሚሰጠን ገንዘብ የምንበላውና የምንዘራው ነው፡፡

ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡10

እግዚአብሄር የሚሰጠን ገንዘብ ነፍሳችንንና ሌሎችን የምናገለግልበት ገንዘብ ነው፡፡ በእጃችን ያለው ገንዘብ የእኛ ብቻ አይደለም፡፡

በእጃቸን ያለው ገንዘብ ባለቤቶች ሳንሆን አስተዳዳሪዎች ነን፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር እንደመፈጠራችን መጠን በእጃችን ያለው ገንዘብ እግዚአብሄር እንደወደደ እንደእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝ የምናስረዳድር ደጋግ መጋቢዎች ነን፡፡

ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤

እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ . . .የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር። ሮሜ 12፡6፣8

በእጃችን ያለው ሁሉ የምንበላው አይደለም የምንሰጠውም እንጂ፡፡

እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት፤ ጐተራህም እህልን ይሞላል፥ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች። ምሳሌ 3፡9-10

ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፤ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም። ምሳሌ 11፡24

ሰው ደግሞ ብሰጥ ይጎድልብኛል ብሎ እንዳያስብ ስጥ ስለሰጠህ አይጎድልብህም ይሰጥሃል ተባለ፡፡

ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። ሉቃስ 6፡38

ስለዚህ ነው ከሚቀበል ይበልጥ የሚሰጥ የተባረከ ነው የሚለው፡፡

እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ። ሐዋርያት 20፡35

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ

ethiopian-birr-922x614.jpgእኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9

በእግዚአብሄር እይታ ለወንጌል ስራ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም የማይውል ማንኛውም ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

በእግዚአብሄር እይታ ለእግዚአብሄር መንግስት ዋነኛ አላማ ለሆነው ሰዎችን የማዳን ስራ የማይውል ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ለዘላላማዊ ህይወት አላማ የማይጠቅም ማንኛውም ሃብት የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡ ሰዎችን ለማዳን የማንጠቀምበት ለሰዎች ብርሃን ለመሆን የማንጠቀምበትና የምድር ጨው ለመሆን የማይጠቅመን ማንኛውም ሃብት የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ለሰዎች መልካምን አድርጋላቸው በህይወታችን መስክረን የእግዚአብሄን መልካምነት አሳይተናቸው ለጌታ ለመማረክ የማይጠቅመን  ማንኛውም ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ራቁታችንን ወደምድር መጥተናል ራቁታችንንም እንመለሳለን፡፡ በምድር ላይ የምናገኘው ለእግዚአብሄር መንግስት ስራ የማይጠቅም ገንዘብ ሁሉ ከዘላለማዊ ህይወት አንፃር ከንቱ ገንዘብ ነው፡፡

በምድር ያከማቸነው በመልካም ስራ ወደ መንግስተ ሰማያት የማንልከው ገንዘብ ጥለነው የምንሄደው ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19

በመልካም ስራ ያልመነዘርነው ገንዘብ በመልካም ስራ ባለጠጋ ያላደረገን ገንዘብ በብር ተከምሮ ያለ ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ ማቴዎስ 6፡19-20

ልባችንን ወደ ሰማይ የማይስበን ገንዘብን ፣ ልባችንን ወደ ምድር የሚስበን ገንዘብና ልባችንን ወደ ሰማይ እንዳናተኩር የማያደርገን ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ማቴዎስ 6፡20-21

ሰዎችን ለዘላለም ህይወት የማንማርክበት ፣ ምድር ላይ ጥለነው የምንሄደው ፣ በመሬት ስበት ምክኒያት ወደሰማይ ይዘነው የማንሄደው ፣ በምድር ላይ ብቻ በዘላለማዊ ሃብት የምንመነዝረውና በምድር ላይ ብቻ ዋጋ ያለው ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ንፁህ ባለጠግነት

hastly gained.jpgበችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11

በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም። ምሳሌ  20፡21

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20

በስርቆት የተከማቸች ሃብት የፅድቅ መሰረት ስለሌላት ትፈርሳለች፡፡

በስራና በድካም የተከማቸች ሃብት ሰፊ መሰረት ስላላት ትበዛለች፡፡

በማጭበርበርና በውሸት የተሰበሰበች ሃብት የተሳሳተ ዘር ስለሆነች መብዛት ያቅታታል፡፡

በንፅህናና በመጠበቅ የተገኘች ሃብት መልካም ዘር ስለሆነች ትበዛለች፡፡

በጭቆና የተከማቸች ሃብት ፍፃሜዋ አያምርም፡፡

በንፅህና የተከማቸች ሃብት ፍፃሜዋ አስተማማኝ ነው፡፡

በአቋራጭ የተገኘ ሃብት በንፅህና አይገኝም፡፡

በእግዚአብሄር መንገድ ያልተገኘ ሃብት ባለሃብቱ ንፁህ ሊሆን አይችልም፡፡

ጥቂት በጥቂት የተከማቸ ሃብት ይበዛል፡፡

በአቋራጭ የተገኘ ሃብት የሚገኘው ገንዘብን በመውደደ ሰውንና እግዚአብሄርን ባለመውደድ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን መንገድ ጠብቆ በጊዜ መካከል የተገኘ ሃብት ምንም ሊሆን አይችልም አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡

በእግዚአብሄር መንገድ ያልሆነ ገንዘብ በሙስና ፣ በስርቆትና በማጭበርበር ይመጣል፡፡

በታማኝነት ከእኛ ጋር አብሮ ያደገ ሃብት ከእግዚአብሄር ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ችኮላ #ሃብት #በረከት #ጥቂትበጥቂት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #የታመነ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

 

ህይወታችንን የምናባክንባቸው 8 መንገዶች

waste.jpg

 1. ከእግዚአብሄር ውጭ ህይወትን መፈለግ

ሰው የተፈጠረው እና ዲዛይን የተደረገው በእግዚአብሄር እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡ ሰው የሚያየውና የሚከተለው የሚታየውን ቁሳቁስ ብቻ ከሆነ ህይወቱን እያባከነ ነው፡፡

እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡4

 1. እግዚአብሄር ያልመራንን ለመስራት መሞከር

እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠው ነገር ሁሉ የተቀመጠው እግዚአብሄር በህይወታችን ላለው አላማ ነው፡፡ የምናባክነው ትርፍ ነገር የለም፡፡ ሰው በህይወቱ ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ መፈለግና መከተል ትቶ እግዚአብሄር ያላለውን ነገር ሲያደርግ ህይወቱን ያባክናል፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

 1. ከጎረቤታችን ጋር መፎካከር

እግዚአብሄር ልዪ ለሆነ የህይወት አላማ እያንዳንዳችንን ጠርቶናል፡፡ የጎረቤታችንና የእኛ የህይወት አላማ ይለያያል፡፡ እኛ ግን ከጎረቤታችን ጋር ከተፎካከረን የማይገናኝና የማይሆን ነገር እያፎካከርን ነው፡፡ እኛ መወዳደር ያለብን እግዚአብሄር በህይወታችን ካስቀመጠው የህይወት ግብ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን ግብ ከመታን ስኬታማ ነን፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ግብ ካልመታን ደግሞ ከማንም የበለጥን ቢመስለን ህይወታችንን እባክነናል፡፡

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡12

 1. ባለፈው ህይወት ውስጥ መኖር

ሰው ያለፈውን ካልረሳ ደጋግሞ ይኖረዋል፡፡ ሰው ያለፈውን ካልረሳ ከወደፊቴ ይልቅ ያለፈው ይሻላል እያለ ነው፡፡ ሰው ያለፈውን ካልረሳ በወደፊቱ ተስፋ ቆርጧል ማለት ነው፡፡ ሰው ባለፈው ከኖረ በልቡ አርጅቷል ማለት ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ ፊልጵስዩስ 3፡13

 1. ስለኑሮ መጨነቅ

ሰው ድርሻውን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ትቶ ስለኑሮ ከተጨነቀ ህይወቱን ያባክናል፡፡ ሰው በአንድ ጊዜ የእግዚአብሄርን መንግስት መፈለግ እንዲሁም ስለኑሮ መጨነቅ አይችልም፡፡ ሰው ለሁለት ጌቶች መገዛት አይችልም፡፡ ለገንዘብ የሚገዛ ሰው ለእግዚአብሄር መገዛት አይችልም፡፡ ለኑሮ የሚጨነቅ ሰው ለእግዚአብሄር መንግስት የሚጠቅመውን ውድ ህይወቱን ያባክናል፡፡

ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ሉቃስ 12፡25

 1. በሚታይ መኖር

ሰው በሚታየው ብቻ የሚኖር ከሆነ የማይታየውን የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ካልቻለ ህይወቱን ያባክናል፡፡ ሰው በምድር ላይ ብቻ ስላለው ኑሮ ካሰብ ለዘላለም ስለሚኖርበት ህይወት ካላሰበና የዘላለም ህይወትን ካልያዘ ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

 1. ነፍስን ማጉደል

ሰው ስለስጋው ብቻ ከሮጠ ነፍሱን ግን ከበደለ ብክነት ነው፡፡ ሰው ስጋውን ጎድቶ ነፍሱን ቢያለማ ይሻለው ነበር፡፡ ሰው ግን በምድር ላይ ሁሉንም አግኝቶ ዘላለማዊ ነፍሱን ግን ከጎዳ ምንም አይጠቅመቅውም፡፡

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16፡26

 1. በፍቅር አለመኖር

ሰው ሁሉንም ነገር ትክክል አድርጎ ነገር ግን በፍቅር ካላደረገው ብክነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ሰው ምንም ነገር የሚያደርገው ከፍቅር መሆን አለበት፡፡ ሰው ግን ሁሉን ነገር አድርጎ በፍቅር ግን ካላደረገው ከንቱ ነው፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡2-3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #ጭንቀት #ፉክክር #ምስጋና #ሁልጊዜ #ልብ #ለበጎስራሁሉ #ፀጋንሁሉ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእውነተኛ ብልፅግና ገፅታዎች

prosperity 8.jpgብልፅግና ክንውም ነው፡፡ ሰው ብልቡ ያለውን ነገር ለመፈፀም መቻል ብልፅግና ነው፡፡ ሰው ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ጀምሮ ወደፍፃሜ ማምጣት ብልፅግና ነው፡፡

አንዳንድ ሰው ገንዘብ ብቻ ካገኘ ብልፅግና ይመስለዋል፡፡ ክንውን ከገንዘብ በላይ ነው፡፡ ክንውን የሚጠይቃቸው ገንዘብ ሊያደርገው የማይችል ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

ክንውን የሚያስፈልገንን ገንዘብ በሚያስፈልገን ጊዜ ማግኘትን ያጠቃልላል፡፡ ብልፅግና የሚገለጥባቸው ሰባት መንገዶች

 1. ብልፅግና ነገሮችን የማስተዳደር ችሎታ ማግኘት ነው፡፡

ሰው ሁሉም ነገር ኖሮት እንዴት እንደሚያስተዳድረው ጥበቡ ከሌለው ክንውን ይጎድለዋል፡፡ ሰው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ወይም ቁሳቁስ ነገር አግኝቶ ያገኘውን ነገር ለታሰበለት አላማ ማዋል ካልቻለ ክንውን የለም፡፡

 

 1. ብልፅግና ብክነትን መቀነስ ነው፡፡

ክንውን ብክነትን መቀነስ ነው፡፡ ሰው ያገኘውን ነገር የተወሰነውን እጅ ቢያባክንና የቀረውን እጁን ቢጠቀምበት ልዩነት ያመጣው የብክነቱ መብዛትና ማነሱ እንጂ ያገኘው ገንዘብ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ብክንውን ሲባርክ የብክነትን ቀዳዳውን እንድትረዳና እንድትቀንስ ያደርግሃል፡፡ እግዚአብሄር ሲባርክ ክብደት መስጠት ላለብህ ነገር ቅድሚያ እንድትሰጥ መረዳት በመስጠት ክንውንን ይሰጥሃል፡፡

ጥበብን የወደደ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ጋለሞቶችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል። ምሳሌ 29፡3

የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20

 1. ብልፅግና ከትክክለኛ ሰው ጋር መገናኘት ነው፡፡

በልብህ ላለው ስራ የሚያስፈክግህን ሰው ማግኘት ክንውን ነው፡፡ ሁሉም ነገር ኖሮህ እንደራሱ አድርጎ የሚሰራልህ ትክክለኛውን ሰው ካላገኘህ ልትከናወን አትችልም፡፡ በአለም ላይ ይልቁ ሃብት ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር በታማኝ ሰው ይባርካል፡፡ እግዚአብሄር ሲባርክህ የሚያስፈልግህ ችሎታ ካለው ቁልፍ ሰው ጋር ያገናኝሃል፡፡

እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤ ፊልጵስዩስ 2፡20

 1. ብልፅግና የምትበላውና የምትዘራውን መለየት ነው፡፡

የምትዘራውን ከበላህ ክንውን የለም፡፡ ክንውን የምትበላውን ብቻ እንድትበላና ሌላውን ደግሞ እንድትዘራውና ብዙ እንድታጭድ ያስተምርሃል፡፡ ብልፅግና ለወደፊት ማፍሰስ ያለብህን መዋእለ ንዋይ ወይም ኢንቨስት ማድረግ ያለብህን መረዳቱን ይሰጥሃል፡፡

ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል፥ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡10

የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20

 1. ብልፅግና መሰረታዊ ፍላጎትና ቅንጦት የመለየት ችሎታ ነው፡፡

የክርስትያን የመጨረሻ ክንውን መሰረታዊ ፍላጎቱን አማልቶ ጌታን መከተል ነው፡፡ እግዚአብሄር መሰረታዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ቃል ገብቷል፡፡ እግዚአብሄር የምንፈልገውን ሁሉ አያሟላም፡፡ ስለዚህ እግፍዚአብሄር የሰጠንን ሃብት በመሰረታዊ ፍላጎት ላይ ብቻ የማዋል ጥበብ ብልፅግና ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን ሃብት በቅንጦት ላይ አባክኖት ሊከናወን አይችልም፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

 1. ብልፅግና እግዚአብሄር የሰጠህን ሰው በሚገባ የመያዝ ችሎታ ነው፡፡

እግዚአብሄር ለሰው የሚሰጠው ታላቁ ሃብት ሰው ነው፡፡ ሰው ብቻውን ያን ያህል ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ለሰው ሰው ያስፈልገዋል፡፡ ብልፅግና እግዚአብሄር ያመጣልንን እድል የመጠቀም ችሎታ ነው፡፡ ሰውን እንደአቅሙ እንደ ደረጃው እንዴት ማክበርና መያዝ እንዳለበት ካላወቀ ክንውን ከየትም አይመጣም፡፡

ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ማቴዎስ 25፡15

 1. ብልፅግና በህይወት መደሰት መቻል ነው፡፡

ህይወትን ሃላፊነት ብቻ አይደለም፡፡ ህይወት እንድንደሰትበት የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ ሰው ባለበት ደረጃ በደረሰበት ደረጃ ደስ መሰኘት ከቻለ ያ ክንውን ብልፅግና ነው፡፡ ሰው ደስ የመሰኘት ቀጠሮውን “ይህን ሳገኝ እንዲህ ስሆን” እያለ የሚያስተላልፈው ከሆነ ክንውን አይደለም፡፡ ሰው ዛሬ ባለበት ደረጃ ባለበት ሁኔታ በህይወቱ ደስ መሰኘት ካልቻለ የተከናወነ ሰው አይደለም፡፡

እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡18-19

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

በአስሩ የድህነት አስተሳሰብ ምልክቶች ዛሬ ህይወትዎን ይመዝኑ

mindብልፅግና የሚመነጨው ከእግዚአብሄር ሲሆን ድህነት የሚመነጨው ከሰይጣን ነው፡፡ ድህነትም ብልፅግናም የሚያልፈው በሰው አእምሮ ነው፡፡ ሰው የሚበለፅገው አእምሮው ነው፡፡ አእምሮው የበለፀገ ሰው ደሃ መሆን አይችልም፡፡ አእምሮው ደሃ የሆነ ሰው ሊበለፅግ አይችልም፡፡

የድህነት አስተሳሰብ ያለው ሰው ደሃ ነው፡፡ የብልፅግና አስተሳሰብ ያለው ሰው ባለጠጋ ነው፡፡

በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ምሳሌ 23፡7

 • ምስኪን እኔ – የድህነት አስተሳሰብ

ሰው ራሱን እግዚአብሄር በክርስቶስ እንደሚያየው ካላየና ሰው በሚታይ ነገር ብቻ ራሱን ከመዘነ ድሃ ሰው ነው፡፡ ድሃ ለመሆን ገንዘብ ማጣት አያስፈልግም፡፡ ገንዘብ ኖሮት የእግዚአብሄር አቅርቦት የማይታየውና የእግዚአብሄር የሚያስችል ሃይል መረዳት የሌለው ሰው አስተሳሰቡ ያልበለፀገ ሰው ደሃ ሰው ነው፡፡

 • እንድበለፅግ ሰው ያስፈልገኛል የሚል የድህነት አስተሳሰብ

እኔን ለማንሳት ሃብታም ሰው ይጠይቃል የሚል ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ እኔን ለማንሳት የሚያስፈልገው እግዚአብሄር ብቻ ነው የሚል ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ለመበልፀግ ሰው አያስፈልግህም፡፡ ለመበልፀግ የሚያስፈልግህ ባለጠጋውን እግዚአብሄን ማወቅና ከእርሱ ጋር እንዴት መኖር እንዳለብህ መረዳት ነው፡፡ ሰው ግን ለብልፅግናውና ስለ እድገቱ አይኑን ከእግዚአብሄር ላይ ካነሳ ደሃ ሰው ነው፡፡ ደሃ ለመሆን ገንዘብ ማጣት የለበትም፡፡

ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል። መዝሙር 75፡6-7

 • ያለማመስገን – የድህነት አስተሳሰብ

የማያመሰግን ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄርን ላለማመስገን ምክኒያት የሚያገኝ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ ምንም ቢደረግለት የማይበቃው ሰው ደሃ ሰው ነው፡፡ ለአንዳንድ ሰው ምንም ነገር የሚበቃ አይደለም፡፡ ድሃ ሰው ሁል ጊዜ ጎረቤቱን ያያል ፡፡ የድህነት አስተሳሰብ ያለበት ሰው ከጎረቤቱ የሚመኘው ነገር አያጣም፡፡ አንዳንድ ሰው እግዚአብሔር በቤቱ የሚሰራውን ድንቅ ስለማያይ አይኑ ወደጎረቤቱ ይቀላውጣል፡፡ ለመኖር እጅግ ብዙ ነው የሚያስፈልገው ደሃ ሰው ነው፡፡ ድሃ ሰው ይህ ይህ ይህ ከሌለኝ ዋጋ የለኝም የሚል አስተሳሰብ ያለው ሰው ነው፡፡  ድሃ ሰው ምንም ቢሆንለት ምኞት ቱን መቆጣጠር ስለማያውቅ ይሰቃያል፡፡

ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፤ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም። ምሳሌ 21፡26

ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡10

 • ድህነትን መፍራት – የድህነት አስተሳሰብ

አንዳንድ ሰው ድህነትን በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ድሃ ላለመሆን ምንም ነገር ያደርገሃል፡፡ ድህነት የሚያስፈራራህ ከሆንክ ከድህነት ፍርሃት ነጻ መውጣት አለብህ፡፡ ድህነትን የሚፈራ ሰው እግዚአብሔን አይፈራም፡፡ የድህነት ፍርሃት የሚመራው ሰው እግዚአብሄር ሊመራው አይችልም፡፡ ማጣትን አይቶ ምንም እንደማያመጣ የተረዳ ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ድህነትን አልፎበት ልኩን ያየና የናቀው ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ሰው የሚኖረው በእግዚአብሄር ፀጋ እንደሆነ እንጂ በማግኘት እንዳልሆነ የተረዳ ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡11-12

 • ማግኘትን ማክበር – የድህነት አስተሳሰብ

ሰው ሃብታምም ባይሆን ሃብትን በተሳሳተ መልኩ የሚረዳ ሰው በድህነት እስራት ውስጥ ይኖተራል፡፡ ሃብታም ቢሆን ደስታ እንደሚያስገኝ ማሰብ የድህነት ምልክት ነው፡፡ ሃብት ቢያገኝ እንደሚሳካለት ማሰብ ድህነት ነው፡፡ ሃብት ማድረግ የማይችለው ብዙ ነገር እያለ ሃብት መስራት የማይችለውን ነገር ይሰራል የሚል የተሳተ ግምት ድህነት ነው፡፡ ለሃብት የተሳሳተ ግምት መኖር ድህነት ነው፡፡ እግዚአብር ብቻ የሚሰራውን ነገር ሃብት ይሰራል ብሎ መጠበቅ የድህነት አስተሳሰብ ነው፡፡

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

 • ቅንጦት – የድህነት አስተሳሳብ

ደሃ ሰው ራሱን መግዛት ስለማይችል ያለውን ነገር በማያስፈልግ ነገር ላይ ያባክናል፡፡ የድህነት አስተሳሰብ ያለው ሰው ያለውን ጥሪት በሚያስፈልገው ነገር ላይ ሳይሆን በምኞቱ ላይ በማዋል ሃብቱን ያባክናል፡፡ ድሃ ሰው ያለውን ነገር በማያስፈልግ በቅንጦት ነገር ላይ ያባክናል፡፡ የድህነት አስተሳሰብ ያለው ሰው ያለውን ነገር በአላስፈላጊ ነገር ላይ ስለሚያጠፋው በሚያስፈልገው ነገር ይቸገራል፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6

 • አልችልም – የድህነት አስተሳሰብ

ድሃ ሰው እችላለሁ የማይል ሰው ነው፡፡ ሁሌ አልችልም የሚል ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠኝን ስራ ሁሉ ሰርቼ ማለፍ እችላለሁ የሚል ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ሲደክም እንኳን የእግዚአብሄር ፀጋ ድካሜን ይሸፍናል የማይል ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ በመከራ ውስጥ ሲያልፍ እጅ የሚሰጥ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ በድካሜ የእግዚአብሄር ፀጋ ድካሜን ይፈፅመዋል የማይል ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ ከራሱ አልፎ የሚያስችልን የእግዚአብሄርን ሃይል የማያይ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣4-5

 • ይቅር አለማለት – የድህነት አስተሳሰብ

ሰው የበደሉትን ይቅር ካላለ ፣ ካልቀቀና የሙጥኝ ካለ ደሃ ሰው ነው፡፡ መበደል የለብኝም ብሎ ካሰበ እና ለመበደል ምንም ቦታ የማይሰጥ ሰው ቋጣሪ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር በብዙ ይቅር ብሎት ሌላውን ይቅር ማለት የማይችል ደሃ ሰው ነው፡፡ የእግዚአብሄን ይቅርታ ውጦ ሌላን ይቅር የማይል ሰው ስስታም ሰው ነው፡፡

ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ማቴዎስ 18፡32-33

 • አለመስጠት – የድህነት አስተሳሰብ

ሰው የተፈጠረው ለመስጠትና ለመባረከ ነው፡፡ ሃብቱን ራሱ ላይ ብቻ የሚያፈስ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ መሰብሰብ እንጂ መስጠትና መባረክ የማያውቅ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ ራስ ወዳድ የሆነ ስለሌላው ግድ የማይለው ሰው ምንም ያህል ሃብት ቢኖረው ድሃ ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰጠው ገንዘብ የዘላለምን ወንጌልን የማይሰራ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ ሰው ባለጠግነቱ የሚለካው በሚያከማቸው ሳይሆን ባከማቸው ባለጠግነት በሚሰራው መልካም ስራ ነው፡፡

ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው። ሉቃስ 12፡21

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9

በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው። እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡17-19

 • አለመተው – የድህነት አስተሳሰብ

የድህነት አስተሳሰብ ያለው ሰው በህይወቱ ለቀቅ ያለ አይደለም፡፡ የእርሱ ነገር ወደሌላ ሰው እንዲያልፍ አይፈልግም፡፡ ለሳንቲምም ቢሆን ይጨቃጨቃል፡፡ መብቱን በፍፁም አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ንጥቂያን በቀላሉ አያየውም፡፡ ይሁን አይልም አይተውም፡፡ እኔን ድሃ ሊያደርገኝ የሚችል ሰው የለም አይልም፡፡ እያንዳንዷን ስንጣሪ አንቆ ነው የሚቀበለው፡፡ ይህ ሰው ድሃ ሰው ነው፡፡ ለቀቅ ያለ አስተሳሰብ የለውም፡፡ በውስጡ ባለው በእግዚአብሄር ፀጋ አይመካም፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ዕብራውያን 10፡34

እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡40-41

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል  #በረከት #ስኬት #የድህነትአስተሳሰብ #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ስለ 14ቱ የብልፅግና መገለጫዎች ሰምተዋልን?

prosperity.jpgብልፅግና ከገንዘብ ያለፈ ነው ፡፡ ብልፅግና የሚያስፈልገንን ገንዘብ ማግኘት ነው፡፡ ብልፅግና የሚያስፈልገንን አለማጣት ነው፡፡ የብልፅግና መገለጫዎች አንዱ ገንዘብ ቢሆንም የብልፅግና መገለጫዎች ግን በገንዘብ ብቻ አይወሰኑም፡፡

ገንዘብ የማይገዛቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እንዲያውመ ውድ ነገሮች ገንዘብ ሊገዛቸው የሚችላቸው አይደሉም፡፡ በህይወታችን ውድ ነገሮች በነፃ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡

ብልጥግና የሚገለጠባቸው አስራ አራቱ መንገዶች፡-

 • ብልፅግና ሃሳብን ማግኘት ነው፡፡

እግዚአብሄር መፈለግን በልባችን ያስቀምጣል፡፡ መፈለግና የልብ መነሳሳት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ኖሮን ስለአንድ ነገር መፈለግን የልብ መነሳሳትን ካላገኘን ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ አቅጣጫን ማግኘት ብልፅግና ነው፡፡

 • ብልጥግና ሰላም ማግኘት ነው፡፡

ሰው ሁሉንም ነገር አግኝቶ ሰላም ከሌለው ከዚያ ሰው ይበልጥ ደሃ ሰው የለም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም የሆነ ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም የሆነ ሰው ደግ ከሰው ጋር ሰላም ይኖረዋል፡፡

የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል። ምሳሌ 16፡7

 • ብልፅግና ሰውን መውደድ ነው፡፡

የሰው ታላቅ ሃብት ሰው ነው፡፡ ምንም ያህል ገንዘብ ኖሮት ሰውን መውደድ የማይችል ሰው ባለጠጋ ሊባል አይችልም፡፡

የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡17

 • ብልፅግና እግዚአብሄርን መፍራት ነው፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንደምንኖር ከማወቅ በላይ ብልፅግና የለም፡፡ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ክብር ከመስጠት በላይ ብልፅግና የለንም፡፡

የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት። መዝሙር 34፡9

 • ብልፅግና እረፍት ማግኘት ነው

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ማቴዎስ 11፡28-29

 • ብልፅግና ደስታ ነው

ሰው ሁሉ ነገር ኖሮት በህይወቱ ደስተኛ ካልሆነ ምን ይጠቅመዋል፡፡ እግዚአብሄር ደስታን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር ቀለል አድርገን ማየት ያለብንን ቀለል አድርገን እንድናይ ያስችለናል፡፡ አንዳንድ ሰው ማግኘት መሰብሰብ እንጂ ያገኘውን ማጣጣም አያውቅም፡፡

እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡19

 • ብልፅግና እግዚአብሄርን መፈለግ ነው

ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም። መዝሙር 34፡ 10

 • ብልፅግና ሰውን ማመን ነው፡፡

ሰውን ማመን የማይችል ሰው ባለጠጋ አይደለም፡፡ ካለሰው ምንም ማድረግ ስለማንችል ሰው ክዶትም ሆነ አታሎትም ሰውን እንደገና የሚያምን ሰው ባለጠጋ ነው፡፡

 • ብልፅግና መርካት ነው፡፡

ምንም ነገር ቢኖረው የማይረካ ሰው ባለጠጋ ሰው አይደለም፡፡ ባለው ምንም ነገር የሚረካ ሰው ደግሞ ደሃ ሊሆን አይችልም፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6

 • ብልፅግና ካለምንም ብክነት ነገሮችን መጠቀም ነው

ብልፅጽግና ነገሮችን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ነገሮች ሳይባክኑ ለታሰበላቸው አላማ መዋላቸው ብልፅግና ነው፡፡ ብዙ ነገር ኖሮት የሚያስተዳድርበት ጥበብ የሌለው ሰው ደሃ ሰው ነው፡፡

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ኤፌሶን 5፡18

 • ብልፅግና ሞገስ ማግኘት ነው

ምንም ያህል ገንዘብ ቢኖረን በእግዚአብሄር ዘንድ ግን ተቀባይነት ካጣን ከዚህ በላይ ድህነት የለም፡፡ ምንም ያህል ገንዘብ ቢኖረን በሰው ፊት ሞገስ ተቀባይነት መወደድን ካላገኘን ምንም ማድረግ እንችልም፡፡ ምንም ሃብት ቢኖረን እንደራሱ አድርጎ በታማኝነትና በትጋት የሚሰራልን ሰው ከሌለን እንቀጭጫለን፡፡

የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ። ነህምያ 2፡18

 • ብልፅግና የልብ ስፋት ነው

ሰውን ይቅር የሚል የሚተው ምህረት የሚያደርግ ሰው ባለጠጋ ሰው ነው፡፡ ነገሮች ኖረውት ልቡ ቻይ ያልሆነ ሰው ግን ባለጠጋ ሰው አይደለም፡፡

እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። 1ኛ ነገሥት 4፡29

 • ብልፅግና የምንሰራው ነገር ወደፍፃሜ መድረስ ነው

እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤  ነህምያ 2፡20

 • ብልፅግና የእግዚአብሄር አብሮነት ነው

አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፤ ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ። እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡14-15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #የእግዚአብሄርአብሮነት #እረፍት

ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ

60926761.jpgባለጠግነት ማለት በሚያስፈልገን ጊዜ የሚያስፈልገንን ነገር ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠንን ስራ ሰርተን ለማለፍ የሚያስፈልግንን አቅርቦት ሁሉ ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ለእግዚአብሄር በሙላት ለመታዘዝ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ አለማጣት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ጌታን በነገር ሁሉ መከተል እንድንችል አቅም ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ከባለጠጋ አምላከ ጋር ያለ መልካም ግንኙነት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ለጥሪያችን የሚያስፈልገንን ነገር አለማጣት ማለት ነው፡፡

ባለጠግነት ማለት በእግዚአብሄር ዙፋን ቀርቦ ጉዳይን ማስፈፀም ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ዕብራውያን 4፡16

ባለጠግነት ማለት የሚያስፈልገንን ሁሉ የሚጨምርልን የእግዚአብሄር ልጅ መሆን ማለት ነው ፡፡

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33

ባለጠግነት ሁሉን ቻይ የሆነውን መታመንና መጥራት ነው፡፡

በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12

ባለጠግነት ታላቅና ሃይለኛን ነገር ወደሚያደርገው መጮኽ ነው፡፡

ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ኤርምያስ 33፡3

ባለጠግነት ማለት ባለጠጋው የእግዚአብሄር ከእኛ ጋር መኖር ማለት ነው፡፡

እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡19-20

ባለጠግነት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ወዳለው መለመን ነው፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #መለመን #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን

Hawaii-Beach-Wallpaper-HD.jpgአምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19

እንዳላችሁ ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን ፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ይሞላባችኋል አላለም ቃሉ፡፡ የሚሞላብን እንደባለጠግነቱ መጠን ነው፡፡

ለምኑ ፈልጉ አንኳኩ፡፡ ለምኑ ሲል ለምኑ ነው፡፡ ለመለመን ግን ኪሳችንን እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የባንክ ሂሳባችሁን እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የቤተሰባችሁን ሃብት እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የደሞዛችሁን ልክ እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የምናየው የባለጠግነቱን መጠን ብቻ ነው፡፡

እንዳላችሁ ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን ፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ለምኑ አላለም፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11

ለሚጠሩት ደሞዝተኛ ሰራተኞች ፣ ለሚጠሩት ባለሃብቶች ፣ ለሚጠሩት ነጋዴዎች ፣ ለሚጠሩት ባለጠጎች ወይም ለሚጠሩት የባንክ ሂሳብ ባለቤቶች አላለም፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡ ባለጠግነቱ ከእርሱ ከሚጠራው እንጂ ከእነርሱ ከሚጠሩት አይደለም፡፡ ለምነው ሲቀበሉ ጠርተውት ሲያባለፅጋቸው ብቻ ነው የሚበለፅጉት፡፡

በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #መለመን #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን

Hawaii-Beach-Wallpaper-HD.jpgአምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19

እንዳላችሁ ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን ፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ይሞላባችኋል አላለም ቃሉ፡፡ የሚሞላብን እንደባለጠግነቱ መጠን ነው፡፡

ለምኑ ፈልጉ አንኳኩ፡፡ ለምኑ ሲል ለምኑ ነው፡፡ ለመለመን ግን ኪሳችንን እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የባንክ ሂሳባችሁን እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የቤተሰባችሁን ሃብት እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የደሞዛችሁን ልክ እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የምናየው የባለጠግነቱን መጠን ብቻ ነው፡፡

እንዳላችሁ ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን ፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ለምኑ አላለም፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11

ለሚጠሩት ደሞዝተኛ ሰራተኞች ፣ ለሚጠሩት ባለሃብቶች ፣ ለሚጠሩት ነጋዴዎች ፣ ለሚጠሩት ባለጠጎች ወይም ለሚጠሩት የባንክ ሂሳብ ባለቤቶች አላለም፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡ ባለጠግነቱ ከእርሱ ከሚጠራው እንጂ ከእነርሱ ከሚጠሩት አይደለም፡፡ ለምነው ሲቀበሉ ጠርተውት ሲያባለፅጋቸው ብቻ ነው የሚበለፅጉት፡፡

በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #መለመን #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

አስራ ሁለቱ የብልፅግና ገፅታዎች

17626120_618456725018450_2216219705830181252_n.jpgእግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ የእግዚአብሄርም ቤተሰብ ባለጠጋ ቤተሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ከእግዚአብሄር ቤተሰብ በላይ ባለጠጋ ሊሆን የሚችል ቤተሰብ የለም፡፡

ይህ ባለጠግነት አንድ አይነት ባለጠግነት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ባለጠግነት ዘርፈ ብዙ ባለጠግነት ነው፡፡ ይህ ባለጠግነት በሁሉ ነገር የተትረፈረፈ ባለጠግነት ነው፡፡

ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፤ ኤፌሶን 3፡8-9

 • በፍቅር ባለጠጎች ተደርገናል

ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ። ኤፌሶን 3፡18-19

 • በብዙ ልዩ ልዩ አይነት ጥበብ ባለጠጎች ተደርገናል

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ኤፌሶን 3፡10

ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። ኤፌሶን 1፡8

 • ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ባለጠጋ ተደርገናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

 • በታላቅ ሃይል ባለጠጋ ተደርገናል፡፡

እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥ ኤፌሶን 3፡20

 • በእምነት ባለጠጎች ተደርገናል፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? ያዕቆብ 2፡5

 • በትንሳኤው ሃይል ባለጠጎች ተደርገናል፡፡

ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። ሮሜ 8፡11

ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡19

 • በበጎ ስራ ባለጠጎች ተደርገናል፡፡

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19

 • በአስተማማኝ የሰማይ ባንክ የምናስቀምጥ ባለጠጎች ተደርገናል፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ ማቴዎስ 6፡19-20

 • በምድራዊ ገንዘብ የዘላለም ወዳጆች በማፍራት ባለጠጎች ተደርገናል፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9

 • በእግዚአብሄር የሚያስችል ሃይል ባለጠጋ ተደርገናል፡፡

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14

በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል። ቆላስይስ 2፡9-10

 • በሚያስፈልገን ገንዘብ ሁሉ ሙላትን ተሰጥቶናል፡፡

አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19

 • ገንዘብ ሊገዛው የማይችለውን እግዚአብሄርን መምሰል አትርፈናል፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል  #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የብልፅግና ወንጌል

የብልፅግና ወንጌል.jpgሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር አምሳል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሙላት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄር የቤተሰብ አባል እንዲሆን ነው፡፡

ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄ ክብር ወደቀ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ እንድንሆን በክርስቶስ የሃጢያታችን እዳ ሁሉ በክርስቶስ ተከፈለ፡፡

ወንጌል የምስራች ቃል ነው፡፡ ወንጌል ስለ መዳን መንገድ አብሳሪ ነው፡፡ ወንጌል የሙላት መልእክት ነው፡፡ ወንጌል የእግዚአብሄር የማዳን ሃይል ለሰው የተገለጠበት መልእክት ነው፡፡ ወንጌል የብልፅግና መልእክት ነው፡፡

ወንጌል በክርስቶስ ስለተዘጋጀልን የሙላት ህይወት ይናገራል፡፡

እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ወንጌል ስለነፃ ስጦታ ይናገራል፡፡

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14

ወንጌል ስለ አዳነን የእግዚአብሄር ፀጋ ባለ ጠግነት ይናገራል፡፡

በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። ኤፌሶን ሰዎች 1፡6-8

ወንጌል ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ስለ ሆነው ስለ እግዚአብሄር ይናገራል፡፡

መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡11-12

ወንጌል በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነው ስለአባታችን ስለ እግዚአብሄር ይናገራል፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን ሰዎች 2፡4-5

ወንጌል ስንደክም እንኳን በሃይሉ ድካማችንን ስለሚሞላው ስለ ጌታ ይናገራል፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡10

ወንጌል ሃጢያት ሲበዛ ከመጠን ይልቅ ስለሚበልጥ ፀጋ ያውጃል

እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ። ሮሜ 5፡20-21

ወንጌል ሃይል በክርስቶስ ሁሉን ስለሚያስችል እግዚአብሄር ይናገራል

ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡13

ወንጌል እንደ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልገንን ሁሉ ስለሚሞላብን እግዚአብሄር ይናገራል

አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19

ወንጌል እረኛችን ስለሆነና የሚያሳጣን ስለሌለ ጌታ ይናገራል

በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል። ዮሃንስ 10፡9

ወንጌል በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ስለባረከን ጌታ ይናገራል

በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ኤፌሶን 1፡3

ወንጌል የሚያስፈልገንን ሁሉ ሊሞላብን ስለሚችለው ስለእግዚአብሄር ይናገራል

እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ኛ  ቆሮንቶስ 9፡8-9

ወንጌል ሁሉ የእናንተ ነው ስላለው ጌታችን ይናገራል

ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡21-23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል  #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእግዚአብሄር መንግስት እንጂ ባለጠግነት ጉልበትህና ድካምህ አይገባውም

follow money3.jpgለእግዚአብሄር ልጅ የገባውና የሚመጥነው ለእግዚአብሄር መንግስት መስራት ነው፡፡ የባለጠግነት ሩጫ ለእግዚአብሄር ልጅ አይገባም፡፡ ባለጠጋ ለመሆን መድከም ለእግዚአብሄር ልጅ የማይመጥነው ተራ ነገር ነው፡፡ ባለጠግነት ጉልበታችንና ድካማችን የማይገባው ተራ ነገር ነው፡፡

ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል፤ ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና። ምሳሌ 23፡3-5

ኢየሱስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ  ለመብል ብለው የተከተሉትን ሰዎች ለእግዚአብሄር እንዲሰሩ አንጂ ለሚጠፋ መብል እንዳይሰሩ ያስተምራቸዋል፡፡

ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። ዮሃንስ 6፡27

እጅግ ሃያል የሆነው የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን እንዳይሰራና ፍሬያማ እንዳንሆን የሚያደርገው የባለጠግነት ማታለል ነው፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።ሉቃስ 4፡19

ስለዚህ ነው ኢየሱስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም ያለው፡፡ ለባለጠግነት መድከም ጌታን የማያውቁ የመንግስቱ አላማ የሌላቸው በኑሮ ከመካት የተሻለ አላማ በህይወታቸው የሌላቸው የተራ ሰዎች አካሄድ ነው፡፡

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በልጅነታችን

sonship222.jpgእግዚአብሄር ልጅ ስለሆንን ብቻ ለኑሮ የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናል፡፡ በክርስትና ህይወታቸን ስኬታማ ለመሆን ለዚህ እውነት እግዚአብሄር አይናችንን ሊከፍት ይገባል፡፡ ይህን ካልተረዳን የእስራኤል ህዝብ የሴይርን ተራራ እንደዞረ እኛም ካለውጤት ህይወታችንን እንፈጃለን፡፡

አንድ ልጅ አባቱ የሚንከባከበው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ የሚያሟላለት ስራ ስለሰራ ፣ ምርታማ ስለሆነና ገንዘብ ስለሚያመጣ አይደለም፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ስለተወለደ ልጅ ስለሆነ ብቻ ከተወለደ ቀን ጀምሮ አባት ልጁን የመንከባከብ ግዴታ አለበት፡፡

አባት ልጅን የሚንከባከበው በቤተሰቡ ውስጥ ስለተወለደ ብቻ ነው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የተወለደን ልጅ መንከባከብ የአባት ግዴታ ነው፡፡ የአባት አቅርቦት የልጅነት መብት ነው፡፡ ዛሬ ስራ ይህን ያህል ሰአት ሰርቷል ብሎ አይደለም አባት ሃላፊነቱን የሚወጣው፡፡ ልጅም በማለዳ ወደ ስራ ሄዶ አይደለም ከአባቱ ምሳ የሚጠይቀው፡፡

እንዲሁም እግዚአብሄር የሚንከባከበን የሚያስፈልገንን ነገር የሚያሟላልን ልጅ ስለሆንን ብቻ እንጂ ስራ ስለሰራን ስላልሰራን አይደለም፡፡

እግዚአብሄር እንድንሰራ የሚፈልገው ስራ የምድር ጨው የመሆንና የአለም ብርሃን የመሆን ጥሪ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ለመብላትና ለመጠጣት ለመልበስ አይደለም፡፡ በምድር ላይ ያለነው ከመብላትና ከመልበስ በላይ ለከበረ ስራ ነው፡፡ በጨለማ ላሉት ብርሃን መንገዱን እነዲያዩ ብርሃን አነሆናቸዋለን፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ማቴዎስ 5፡13-14

የእኛ ስራ ክህንነት ነው፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18

የመጀመሪያው ጥሪያችን መልክተኝነት ነው፡፡ የክርስቶስ አምባሳደሮች ነን፡፡ በምድር ያለነው እግዚአብሄርን እና መንግስቱን ለመወከል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን መልካም ለሰዎች እናሳያለን፡፡ የእግዚአብሄርን መልካምነትና መሃሪነት በድርጊታችንና በቃላችን እናንፀባርቃለን፡፡

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡16

እግዚአብሄርን በመፍራት ሰዎች እግዚአብሄርን እንዲፈሩ እናበረታቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር የሚታረቁበትን የመዳን እውቀት ቃል እንሰጣቸዋለን፡፡ እኛ ከሃጢያት የዳንን ሰው ከሃጢያት መዳን እንደሚችል ሞዴል እንሆናቸዋለን፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20

ዋናው ስራችንና ቅጥራችን ክህንነት ነው፡፡ የሙሉ ጊዜ ካህናት ነን፡፡ በገንዘብ የተገዙትን ክርስቲያን ባሪያዎች እንኳን ጌታን የሚያገለግሉ እንደሆኑና ብድራትን የሚከፍላው የቀጠራቸው እግዚአብሄር እንደሆነ ጥሪያቸውም ክህንነት እንደሆነ ሐዋሪያው ጳውሎስ የሚያስረዳቸው፡፡

ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላስይስ 3፡24

የክህነነት ስራችንን እየሰራን ግን ሌሎች የሙያ ስራዎችን በመስራት ገንዘብን እናገኛለን፡፡ እግረመንገዳችንን በምንሰራው ስራ ጌታ በምድር ላይ የሚያስፈልገንን ነገር እንድናሟላ ይረዳናል፡፡ እግዚአብሄር ስራ እንድንሰራ የሚፈልገው ስራ ካልሰጠሁት ምን ይውጠዋል ብሎ አይደለም፡፡ ስራ ካልሰራ እኔ ከየት አምጥቼ እንከባከበዋለሁ ብሎም አይደለም፡፡ ይህ የምድራዊ ስራ ቢኖርም ባይኖርም ጌታ እኛን ይንከባከበናል ያኖረናል፡፡ እግዚአብሄር የሚንከባከበን ሌላ ስራ ስለሰራን ስላልሰራን ሳይሆን ልጅ ስለሆንን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሰዎች ስለሚበሉት ፣ ስለሚጠጡትና ስለሚለብሱት አንዳይጨነቁ ጌታ ኢየሱስ ያስተማረው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

በእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ ስራ መቀጠር መብላት መጠጣት መልበስ ጥያቄ ሆኖ አያውቅም፡፡ በክርስትና የመጀመሪያው ጥሪያችን ክህንነት ነው፡፡ ሌላው ስራ ከሙሉ ጊዜ የክህንነት አገልግሎታችን ጎን ለጎን የምናደርገው ነው፡፡ በክርስትና ካለሌላ ሙያ መኖር እንችላለን ካለ ክህንነት ግን መኖር አንችልም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #አቅርቦት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ጥሪ #ክህንነት #ስራ #መልክተኛ #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የቃልኪዳን ስምረት

A_Broken_Covenant (1).jpgቃልኪዳን በአለም ላይ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ሃሳቦች አንዱ ነው፡፡ ብዙ ወሳኝ ነገሮች የሚደረጉት በቃልኪዳን ነው፡፡ ቃልኪዳንን አለመረዳት በአለም ላይ ያለን ሃብትና እምቅ ጉልበት አለመረዳት ነው፡፡ ቃልኪዳንን አለመረዳት አላማን መሳት ነው፡፡ ቃልኪዳንን አለመረዳት ፍሬቢስ መሆን ነው፡፡

ቃልኪዳን በሁለት ወገኖች መካካል የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ አንዱ ወገን ለሌላው ወገን የሚያደርግለት ነገር ሌላኛውም እንዲሁ ለሌላው የሚያድርገለት ነገር አለ፡፡

እኛ በብዙ ነገሮች የተወሰንን ስለሆንን ሁሉንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡ ለወሳኝ ነገሮች  የቃልኪዳን አጋር ያስፈልገናል፡፡ ቃልኪዳን ደግሞ በራስ ድርሻ ላይ ብቻ ማተኮርን ይጠይቃል፡፡

በአለም ላይ ያለው ችግር በራስ ሃላፊነት ላይ ያለማተኮር ችግር ነው፡፡ በአለም ላይ ያለው ግራ መጋባት የመጣው የስራ ክፍፍልን ካለመረዳትና የራስን ድርሻ ብቻ ፈፅሞ ካለማረፍ የሚመነጭ ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ህብረትን ፈልጎ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት እያደረገ ምድርን የሚያስተዳድርለትን የሚረዳውና የሚግባባው ፍጥረት ፈልጎ ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ ዘፍጥረት 1

ሰው በሃጢያትም ከወደቀ በኋላ እግዚአብሄር የሰው ልጆችን ለመድረስና አላማውን በምድር ላይ ለማስፈፀም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ እግዚአብሄር በዘመናት መካከል ከአብርሃም ፣ ከኖህ ፣ ከእስራኤል ህዝብ ጋር ቃልኪዳን ሲያደርግ ነበር፡፡

አሁንም በዚህ ዘመን እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ላይ መስዋእትነት ከእኛ ጋር ኪዳን ገብቷል፡፡ እግዚአብሄር መንግስቱን የሚሰራለትና የሚያስፋፋለት ሰው ፈልጎ ከእኛ ጋር ቃልኪዳን ገብቷል፡፡

ነገር ግን አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ሰዎችን ግራ የሚያጋባቸው የቃል ኪዳን የስራ ድርሻ ነው፡፡ አሁንም በዘመናችን ሰዎች እግዚአብሄር ወዳየላቸው የህይወት ከፍታ እንዳይገቡ የሚያግዳቸው የቃልኪዳንን ድርሻን አለመረዳት ነው፡፡

ለምሳሌ ሰዎች የሚበላና የሚጠጣ የሚለበስ በመፈለግ ህይወታቸውን የሚያባክኑት የእግዚአብሄርን አቅርቦት የቃልኪዳን ድርሻ ባለመረዳት ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

በዚህ የቃል ኪዳን ስምምነት መሰረት የሰው ድርሻ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ በእግዚአብሄ ፊት ትክክለኛ ነገር ማድረጉን ማረጋገጥ ነው፡፡ የሰው ድርሻ እግዚአብሄን በምድር መወከል ነው፡፡ የሰው ድርሻ ለእግዚአብሄር መንግስት ደህንነት ማሰብ ነው፡፡ የሰው ድርሻ ለእግዚአብሄር መንግስት ማሸነፍና መስፋፋት መስራት ነው፡፡  የሰው ድርሻ የእግዚአብሄን ቤተክርስትያን በጎነት መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ የመንግስቱን አባላት መንከባከብና ማስነሳት ነው፡፡

እግዚአብሄር መንፈስ ስለሆነና በስጋ ውስጥ ስለማይኖር በምድር ላይ ይህንን እንድናደርግለት የጠራን እኛን ነው፡፡ እኛ ይህንን ማድረግ እንችላል፡፡ በዚህ ማድረግ በምንችለው ድርሻ ላይ ብቻ ብናተኩር ውጤታማ እንሆናለን እግዚአብሄርንም በሙላት አገልግለን እናልፋለን፡፡

የእግዚአብሄ ድርሻ ደግሞ ለሰው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ነገር ማሟላት ነው፡፡ ይህንን እንዲህ አድርገው ብሎ የሚመክረው የለም፡፡ ይህን ደግሞ እርሱ ያደርገዋል፡፡

አሁን ሰው የተሰጠውን ይህንን በቂ ሃላፊነት ጥሎ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚንካከበው ቁጭ ብሎ ቢጨነቅ ከንቱ ነው፡፡ ሰው በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ማድረግ አይችልምና እግዚአብሄር የሰጠውን መንግቱንና ፅድቁን የመፈለግ ሃላፊነቱን እየጣለ ነው፡፡ እግዚአብሄር እኔን በትክክል ይይዘኝ ይሆን ብሎ ሲፈራ ድርሻውን መወጣት ያቅተዋል፡፡ እግዚአብሄር አያያዙን ያውቅበት ይሆን ብሎ ሰው ቢያወጣና ቢያወርድ ህይወቱን እያባከነ ነው፡፡

ሰው በህይወቱ ይህን የቃል ኪዳን ሃላፊነት ካልተረዳና በራሱ ሃላፊነት ብቻ ላይ ካላተኮረ የእስራኤል ህዝብ የሴይርን ተራራ እንደዞሩት ይዞራል እንጂ እግዚአብሄር ወዳሰበለት ግብ አይደርስም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄር #አትጨነቁ #ቃልኪዳን #መታመን #መደገፍ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእውነተኛ ስኬት ምንጭ

can-stock-photo_csp14928105.jpgምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡1-3

በእግዚአብሄር ህግ ደስ የሚለው ሰው ምስጉን ነው

የእግዚአብሄር ቃል ተስፋችን ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስኬታችን ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ህይወታችን ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ደስ የሚለው ሰው እንደሚሳካለት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል እክብሮት ያለው ሰው ሊወድቅ አይችልም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሚወድ ሰው እንደሚወጣና እንደሚወርስ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ብርሃን እንደሆነና የትኛውም ጨለማ ሊያሸንፈው እንደማይችል እንዲሁ የእግዚአብሄርን ቃል የያዘ ሰው ሊቋቋመው የሚችል  ከሰማይ በታች ምንም ሃይል የለም፡፡

ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም። ዮሐንስ 1፡5

የእውነተኛ ስኬት ምንጩን ያገኘ ሰው የተመሰገነ ነው

የእውነተኛ ስኬት ምንጩ የእግዚአብሄር ቃል ስለሆነ ሰው ለስኬት የሚያስፈልገው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መልክ ስለተፈጠረ ካለ እግዚአብሄር ቃል ሙሉ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ስለተፈጠረ ካለ እግዚአብሄር ቃል ማሰብና ማሰላሰል እውነተኛ ስኬት ውስጥ መግባት አይችልም፡፡

እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡4

ዘላቂ ስኬት ያለው ሰው የተመሰገነ ነው

ብዙ ስኬት የሚመስሉ ወቅታዊ ነገሮች አሉ፡፡ ስኬቶች ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስኬት ግን ምንም የማይለውጠው ስኬት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስኬት ዘመን የማይሽረው ስኬት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስኬት በሌሎች በምንም ነገሮች የማይቀያየር ስኬት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስኬት ሰይጣንም ሆነ ምንም ሁኔታ የማይወሰን አስተማማኝ ስኬት ነው፡፡

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡1-3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ስኬት #ክንውን #ቃል #ማሰላሰል #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የገንዘብ ሚስጥር

Talking from the heart Blog

Ethiopian-Birr.jpg
የገንዘብን ልክ አለማወቅ በህይወት እንድንሳሳት የሚያደርግና ህይወታችንን በሙላት እንዳንደሰትበት የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ የሰውን ብስለት የሚለካው ሰው ለገንዘብ ያለውን ስፍራ በማየት ነው፡፡ ሰው ለገንዘብ ያለውን ግምት ከተበላሸ ሌሎች ነገሮች ያለው ሁሉ ግምት ይበላሻል፡፡
ሰው ገንዘብ ማድረግ የሚችለውንና ገንዘብ ማድረግ የማይችለውን ጠንቅቆ ካልተረዳ ከገንዘብ ጋር ያለው ግንኙነት ይበላሻል፡፡ ሰው ከልክ በላይ ለገንዘብ ክብር ከሰጠና ገንዘብን በህይወቱ መጀመሪያ ካደረገ ገንዘብን ይወዳል ይባላል፡፡
ገንዘብን መውደድ ወይም ከገንዘብ ጋር ያለ የተሳሳተ ግንኙነት ወይም ለገንዘብ ያለ የተሳሳተ ግምት ከሌሎች ነገሮች ጋር ያለ ግንኙነትን ሁሉ ያዛባል፡፡ ሰው ከገንዘብ ጋር ያለው ግንኙነት ከተሳሳተ ሌላ የማይሳሳት ምንም ግንኙነት አይኖረውም፡፡
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።1ኛ ጢሞቴዎስ 6:10
ገንዘብን የሚወድ ክቡሩን ሰውን አይወድም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው እግዚአብሄርን ይጠላል፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው ገንዘብን ከሰው ያስበልጣል፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰውን መናቅ አይከብደውም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው እግዚአብሄርን ለመውደድ አቅም ያጣል፡፡ ለገንዘብ የሚገዛ ለእግዚአብሄር መገዛት አይችልም፡፡
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም…

View original post 101 more words

አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን

Publication1.jpgእንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

በሃጢያት ምክኒያት የሰው ቅድሚያ አሰጣጥ ተዛብቷል፡፡ ይህ ቅደም ተከተል ካልገባው የሰው ህይወት ከንቱ ሩጫ ነው፡፡ ሰው ይህን ቅደም ተከተል ካላስተካከለ በህይወቱ የሚስተካከል ምንም ነገር አይኖርም፡፡

ኢየሱስም አለ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት አትጨነቁ፡፡ መብላትና መልበስ የህይወት አላማችሁ አይሁን፡፡ መጠጣትና መልበስን እንደ ራእይ አትያዙት፡፡ መብላትና መጠጣትን መከተል አይመጥናችሁም፡፡ መብላትና መልበስን መፈለግ የእግዚአብሄር ቤተሰብ አባልነት ክብራችሁ አይመጥነውም፡፡ ከመብላትና መጠጣት ያለፈ ክብር ያላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡ ከመጠጣትና ከመልበስ እጅግ የላቅ ጥሪ አላችሁ፡፡ የሚበላና የሚጠጣ ከመፈለግ የተሻለ ክብር አላችሁ፡፡

መብላትና መጠጣትን መፈለግ ክብር አይደለም፡፡ የሚበላውና የሚለበሰውን መፈለግ ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ መብላትና መልበስን ማንም ሰው ፣ ማንም መንገደኛ ፣ ማንም ተራ ሰው ይፈልገዋል፡፡

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ማቴዎስ 6፡32

እግዚአብሄር አያስፈልጋችሁም እያለ አይደለም፡፡ ይህ ለኑሮ እንደሚያስፈልግ አባታችሁ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄርን አታስረዱትም፡፡ ስለ ባተሌነታችሁ ለእግዚአብሄር የሚበላና የሚጠጣ ለመፈለግ ነው ብላችሁ ለእግዚአብሄር ምክኒያትን አትሰጡትም፡፡

ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።

እግዚአብሄር እያለ ያለው የሚበላ የሚጠጣ የሚለበስ መፈለግ ድርሻችሁ አይደለም፡፡ አስቀድማችሁ ድርሻችሁን አድርጉ፡፡ አስቀድማችሁ የሚመጥናችሁን አድርጉ፡፡ አስቀድማችሁ የተጠራችሁትን አድርጉ፡፡ አስቀድማችሁ የቤተሰቡን ክብር ጠብቁ፡፡ አስቀድማችሁ መንግስቱን ተንከባከቡ፡፡ አስቀድማችሁ መንግስቱን ፈልጉ፡፡

ይህ ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡ ይህ ሁሉ ተጨማሪ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ምርቃት ነው፡፡ ይህን ሁሉ እስከማትፈልጉ ድረስ እግዚአብሄር የድርሻውን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር ያቀርባል፡፡ ይጨመርላችኋል፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሁሉ የእናንተ ነው

wonderful-sleeping-relax-cute-baby-boy-wallpapers-hd-1024x768px.jpg1 ቆሮንቶስ 3:21 ሁሉ የእናንተ ነው፡፡

 • የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ

እግዚአብሄር ለኢየሱስ የሰጠውን ክብር ኢየሱስ ለእኛ ሰጥቶናል፡፡ ይህንንም ክብር የሰጠን ኢየሱስ እና አብ አንድ እንደሆኑ እኛም በኢየሱስ አንድ እንድንሆን ነው፡፡

እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ ዮሐንስ 17፡22

 • መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና

አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ። ሉቃስ 12፡32

 • ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን

በህይወት ጌታን ለመከተልና እግዚአብሄር በህይወታችን ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ጨርሰን እንድናከብረው የሚያስፈልገው ወጭ ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

 • እግዚአብሄር እረኛችን ነው

መልካም ነገር የሚባል ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡ መልካም ከሚባል ነገር አንጎድልም፡፡

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 1፡23

. . . እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም። መዝሙር 34፡10

 • መግባት የእኛ ነው፡፡

እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ ዕብራውያን 10፡19-20

 • ንግስና የእኛ ነው

በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። ሮሜ 5፡17

 • በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው

እግዚአብሄር አብ ኢየሱስን በሚወደው መጠን ይወደናል፡፡

እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። ዮሐንስ 17፡23

ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡21-23

ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ለሁሉም ሰው አይደለም፡፡ ሁሉ የእናንተ ነው የተባሉት ኢየሱስን የህይወታቸው አዳኝና ጌታ አርገው  የተቀበሉትን ብቻ ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ሁሉየእናንተነውና #መንግስት #ፍቅር #እረኛእግዚአብሄር #ክርስቶስ #የሚያስፈልገውን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

የገንዘብ ሚስጥር

Ethiopian-Birr.jpg
የገንዘብን ልክ አለማወቅ በህይወት እንድንሳሳት የሚያደርግና ህይወታችንን በሙላት እንዳንደሰትበት የሚያደርግ ነገር ነው፡፡ የሰውን ብስለት የሚለካው ሰው ለገንዘብ ያለውን ስፍራ በማየት ነው፡፡ ሰው ለገንዘብ ያለውን ግምት ከተበላሸ ሌሎች ነገሮች ያለው ሁሉ ግምት ይበላሻል፡፡
ሰው ገንዘብ ማድረግ የሚችለውንና ገንዘብ ማድረግ የማይችለውን ጠንቅቆ ካልተረዳ ከገንዘብ ጋር ያለው ግንኙነት ይበላሻል፡፡ ሰው ከልክ በላይ ለገንዘብ ክብር ከሰጠና ገንዘብን በህይወቱ መጀመሪያ ካደረገ ገንዘብን ይወዳል ይባላል፡፡
ገንዘብን መውደድ ወይም ከገንዘብ ጋር ያለ የተሳሳተ ግንኙነት ወይም ለገንዘብ ያለ የተሳሳተ ግምት ከሌሎች ነገሮች ጋር ያለ ግንኙነትን ሁሉ ያዛባል፡፡ ሰው ከገንዘብ ጋር ያለው ግንኙነት ከተሳሳተ ሌላ የማይሳሳት ምንም ግንኙነት አይኖረውም፡፡
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።1ኛ ጢሞቴዎስ 6:10
ገንዘብን የሚወድ ክቡሩን ሰውን አይወድም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው እግዚአብሄርን ይጠላል፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው ገንዘብን ከሰው ያስበልጣል፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰውን መናቅ አይከብደውም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው እግዚአብሄርን ለመውደድ አቅም ያጣል፡፡ ለገንዘብ የሚገዛ ለእግዚአብሄር መገዛት አይችልም፡፡
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ማቴዎስ 6፡24
ገንዘብን የሚወድ ገንዘብን ስለማይጠግብ በህይወቱ የሚያጠግበውና የሚያረካው ምንም ነገር አይቀርለትም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው ሰው ሊያረካው አይችልም፡፡ የሰው የህይወቱ አላማና ግብ እግዚአብሄርን መውደድና እግዚአብሄርን መፈለግ ነው፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው ግን የህይወቱ ብቸኛ ራእይና ግብ ገንዘብ ስለሚሆን ለእግዚአብሄር ጊዜ አይኖረውም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው በገንዘብ ፣ በሰውም ሆነ በእግዚአብሄር የመርካት እድሉን ጨርሷል፡፡
ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። መክብብ 5፡10

ለተጨማሪ ፅሁፎች

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ብር #ብልፅግና #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የጻድቃን መንገድ

airplane-take-off-at-sunset-hd-wallpaper-768x480የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4፡18
ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበላችንና በህይወታችን ላይ በመሾማችን እግዚአብሄር ልጆች አድርጎ ተቀብሎናል፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ስለሆንንና እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ስለሚሰራ ነገሮች ሁሉ ይከናወንልናል፡፡
በጌታ ኢየሱስ የመስቀል ስራ አምነው የዳኑትን ጻድቃንን መንገዳቸው ከንጋት ብርሃን ጋር ይመሳሰላል፡፡ የንጋት ብርሃን ጠቃሚና ወሳኝ ብርሃን ነው፡፡ የንጋት ብርሃን ጨለማው ማለፉንና ብሩህ ቀን መምጣቱን የሚያበስር እርግጠኛ ምልክት ነው፡፡ የንጋት ብርሃን የሙሉ ተስፋ ብርሃን ነው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስከሚሆን እየጨመረ እንደሚሄድ ያስተምራል፡፡ የጻድቃን መጨመር ፣ ማበብ መውጣት ፣ ማሸነፍ እርግጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ተገናኝቶ የሚወርድ ፣ የሚጠፋ ፣ የሚከስም ሰው የለም፡፡ ጻድቃን እየወጡና ከፍ እያሉ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
የጻድቃን መንገድ ግን እንደዱብዳ አይደለም፡፡ የጻድቃን ማበብ ድንገተኛ አይደለም፡፡ የጻድቃን መንገድ ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ነገር ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ በጊዜያት ውስጥ የታመነና ፀንቶ የቀጠለ ሰው እጅግ እስከሚባረክ ድረስ እንደሚባረክ ያስተምራል፡፡
የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20
የንጋት ብርሃን ከጭላልጭልነት ጀምሮ እንደሚበረታና የቀትር ፀሃይ እስከሚሆን ቀስ በቀስ እየጨመረ እንደሚሄድ ሁሉ የጻድቃን መንገድም እንዲሁ ጥቂት በጥቂት ይጨምራል፡፡
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11
የንጋት ብርሃን ሙሉ ቀን እስከሚሆን መጨመሩን እነደማያቆም እንዲሁ የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስከሚሆን እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡ የጻድቃን መንገድ ሙሉ በረከት በህይወታቸው እስከሚገለጥ ድረስ መጨመሩን አያቆምም፡፡ የጻድቃን በረከት ከመጨመር አይቆምም፡፡
የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4፡18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ጻድቃን #የታመነ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #በረከት #ትግስት #መሪ

አሁንም ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ

submitአሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። ኢዮብ 22:21
እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር አቅዶ የሰራን ከእርሱ ጋር እንድንስማማ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን በዋነኝነት እርሱን እንድንታዘዘው ነው፡፡
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳይያስ 43፡7
ሰው ግን ከእርሱ ጋር ካልተስማማና ለእግዚአብሄር ካልተገዛ በህይወቱ ምንም ነገር ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ካልተስማማ ሁሉ ነገር ስለሚዘበራረቅና ምንም የሚሳካ ነገር ስለሌለ ሰላሙን ያጣል፡፡
ስለዚህ ምክሩ አሁንም ከእግዚአብሄር ጋር ተስማማ ነው፡፡ መጀመሪያ ሰላም ታገኛለህ፡፡ እግዚአብሄር ፀጋውን ያበዛልሃል፡፡ ከዚያም በመታዘዝህ የእግዚአብሄርን በረከት ታገኛለህ ህይወትህም ይለመልማል፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ተሰቃየ፡፡ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ ፈቃድ ይሁን በማለት ከእግዚአብሄር ጋር ተስማማ፡፡ ጨክኖም ለእግዚአብሄር ታዘዘ፡፡
ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።ማቴዎስ 26፡39
አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። ኢዮብ 22:21
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መታዘዝ #ተስማማ #ሰላም #ስኬት ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ወደር የለሽ ብልፅግና

Road to successበክርስትና ህይወታችን አድገን አድገን የመጨረሻው የስኬትና የብልፅግና ደረጃ ምን እንደሆነ ማወቅ ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስንደርስ እንድናውቀውና እንድንረካ “ይሄ ነው” እንድንል ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡
ስለዚህ ደረጃ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ አስተያየት አላቸው፡፡ ይህንን ሁሉ አስተያየት ብንሰማ እንስታለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሚለውን ከሰማን ግን እናርፋለን፡፡
የክርስትና ህይወት ግቡ ምንድነው? የክርስትና ህይወት የስኬት ጣራው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ሊመልስልን ሙሉ ስልጣን ያለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ደግሞ እውነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ኦሪጂናል የእግዚአብሄር ሃሳብና ፈቃድ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ሰው ደረሰበት የሚባለው ምን ሲኖረው ነው? የጌታ ሰው እንደው ህይወቱ ሲያስቀና የሚያስብለው ምንና ምን ሲኖረው ነው? የሚለውን ጥያቄ መፅሃፍ ቅዱስ በሚገባ ይመልሰዋል፡፡
ክርስቲያን በለፀገ የሚባለው ሚሊየነር ሲሆን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ተሳካለት ደረሰበት የሚባለው ዝነኛ ሲሆን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ደረሰበት ይህ የተሳካለት ሰው ነው የሚባለው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን ሲከተል ነው፡፡ ክርስቲያን ደረሰበት የሚባለው እግዚአብሄር በህይወቱ ላስቀመጠው ሃላፊነት የሚያስፈልገው ነገር ካልጎደለበት ነው፡፡ ክርስቲያን ተሳካለት የሚባለው ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ፍላጎት ካሟላ ነው፡፡
ጌታ ከመከተል የተሻለ የስኬት ደረጃ የለም፡፡ ጌታን ከመውደድ ያለፈ የብልፅግና ደረጃ የለም፡፡ ጌታን ከማምለክና እግዚአብሄርን ከመምሰል የላቀ የስምረት ደረጃ የለም፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ክብራችን አይፈቅድም !

bada-kaun-hindi-story-1ልጅነታችን ክብር አለው ልጅነታችን የእግዚአብሄር የቤተሰብነት አባል ታላቅ ክብር አለው፡፡ እንደ ልጅነታችን ክብር የማይስማማ ምንም ነገር ለማድረግ እንፈልግም፡፡ ከልጅነት ክብራችን ጋር የማይሄድ ማንኛውም ጥቅም እንንቀዋለን፡፡ ክብራችን ተነክቶ የምናገኘውን ጥቅም ከምናገኝ ሞት ይሻለናል፡፡
እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡15
አንዳንድ ሰዎች ሃዋሪያው ጳውሎስ ጌታን የሚያገለግለው ስለሚጠቀም ነው ጥቅሙ ቢቀርነት አገልግሎቱን ያቆማል የሚል አመለካከት ለነበራቸው ሰዎች ለማሳየት ሰዎች የሚሰጡትን ስጦታ አልተቀበለም፡፡ ምክኒያም ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡3-4
 • ለመዋሸት ክብራችን እይፈቅድም
ውሸት ከፍርሃት ይመነጫል፡፡ እኛ ደግሞ በፍቅር የምንኖር ስለሆንንና ፍፁም ፍቅርም ፍርሃትን አውጥቶ ስለሚጥል አንዋሽም፡፡ ከምንዋሽ በውሸት የሚመጣው ጥቅምን ቢቀርብን ይሻለናል፡፡ የልጅነትን ክብራችንን እንዲነካ ለምንም ነገር አንፈቅድም፡፡ እውነትን የማንናገርለት ነገር የእኛ እንዳልሆነ እናምናለን፡፡
እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም። ኢሳይያስ 52፥12
 • ለመለማመጥ ክብራችን አይፈቅድም በመሃላ በመለማመጥ በብዙ ቃልና በብዙ ጭንቅ ሰዎችን ልናሳምን አንጥርም፡፡ በእግዚአብሄር እንታመናለን፡፡ እግዚአብሄር ያላደረግልንን ነገር አንወስድም፡፡ የራሳችንን ሃይል ጨምረን የምናመጣው ነገር በእውነት የእኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ያላደረገልንን ነገር ሁሉ የእኛ እንዳልሆነ ነው የምንቆጥረው፡፡
በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። ማቴዎስ 5፡36-37
 • ክብራችን ነውረኛን ረብ አይፈቅድም የቤተሰቡ ደረጃ ክብር የሌለበትን ጥቅም ያስንቃል፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ ነው የምናምነው፡፡ በነውር በወስላታነት በታማኝነት ያልሆነ ጥቅምን እንንቃለን፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ እናምናለን፡፡
ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡9
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
 • ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም ፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ መስራት ሲችል እራሱ እየሰራ የሚያስፈልገውን ያሟላ ነበር፡፡
ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም። 2ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡8
 • ከስስታም ሰው ለመቀበል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
ሰው የሚያደርግልንና የሚሰጠን ደስ ብሎት ከልቡ ካልሆነ እየሰሰተ ከሚሰጠን ሰው ለመቀበል ክብራችን እይፈቅድም፡፡ ሰው በልቡ ባይበላ እያለ ከሚሰጠን መራብ ይሻለናል፡፡
የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፤ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ። ምሳሌ 23፡6-8
 • ወንጌልን ዝቅ አድርጎ ለሚያይ ሰው ጋር መከራከር ክብራችን እይፈቅድም፡፡ የወንጌልን ክብር ከማይረዳ እንዲያውም ልንጎዳው እንደመጣን ከሚያስብ ሰው ጋር በክርክር ጊዜያችንንና ጉልበታችንን መጨረስ ክብራችን አይፈቅደውም፡፡
በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ። ማቴዎስ 7፡6
 • ከሰነፍ ጋር ለመመላስ ክብራችን አይፈቅድም፡፡ እውነትን ለማወቅ ፈልጎ ከሆነ እንረዳዋለን፡፡ እኛን ለማዋረድ ፈልጎ ከሆነ ለክርክር ጊዜ የለንም፡፡ አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት። ምሳሌ 26፡4
በክርክርና በጭቅጭቅ የሚገኘውን ጥቅም ለማግኘት ክብራችን አይፈቅድም፡፡ ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። ምሳሌ 20፡3
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ . . . የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡3
 • መስራት እየቻልን የሌላን ሰው እርዳታ አንጠብቅም፡፡
ለለበጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡11-12
 • ቃልኪዳናችን ከእግዚአብሄር ጋር ስለሆነ ስለመባረካችን ስለማደጋችንና ስለመለወጣችን ማንም ስጋ የለበሰ ክብሩን አንዲወስድ አንፈቅድም፡፡ ስለስኬታችን ክብሩን ከጌታ ጋር የሚሻማ ከሆነ ጥቅሙን እንተዋለን፡፡ ሰው እኔ አነሳሁት ከሚለን የሚያደርግልን ይቅርብን፡፡
አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ዘፍጥረት 14፡22-24
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#እግዚአብሔር #አምላክ #ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የስኬት ቁልፍ

%e1%89%80%e1%89%81%e1%88%8d%e1%8d%8dህይወትን ይኖሩታል እንጂ በአንድና በሁለት አረፍተ ነገር ወይም በብዙ ፅሁፎች ሊገልፁት አይችሉም፡፡ ህይወት ሁሉ ነገር ፍንትው ብሎ የሚታይበት ነገር ሳይሆን ሚስጢራዊነት ያለው አሰራሩን መረዳት የሚጠይቅ ነገር ነው፡፡ የህይወት ቁልፍ ሚስጢር ነው፡፡ ሰው እንዴት እንደሚሳካለትና እንደሚከናወንለት ለማወቅ ብዙ ሰዎች ካለማቋረጥ ይመራመራሉ፡፡ የተለያዩ የስኬት መንገዶች ናቸው የሚሏቸውን ሲያስቀምጡ ይታያል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ስኬት እንዴት እንደሚመጣ የክንውንን ቁልፍ ለማወቅ እጅግ የደከመውን ጠቢቡን ሰለሞን እንመለከታለን፡፡ ንጉስ ሰለሞን እነዚህን የሚላቸውን ሃያልነት ባለጠግነትና ጥበበኝነት በተግባር ደርሶባቸው እንደሚሰሩና እንደማይሰሩ በህይወቱ የፈተናቸው ነገሮች ናቸው፡፡
ጠቢቡና ሰለሞን ተመራምሮ ተመራምሮ የደረሰበትን ሚስጢር ይነግረናል፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን የስኬት ቁልፍ አብዛኛው ሰው ከሚያስበው የተለየ መሆኑን እሱም ሃሳቡን እንደለወጠ እኔም ተመለስኩ ብሎ ምን እንደተረዳ ያስረዳናል፡፡
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11
ተመልከቱ እግዚአብሄር አይሆንም ካለ የሩጫ ድል ለፈጣን አይሆንም፡፡ስንቱ ፈጣን ሯጭ የሂሳብ ባለሞያ ሆኗል፡፡ ፈጣኑ ሯጭ ስንት ጊዜ ተስፋ ቆርጦ እግዚአብሄር በሰው ተጠቅሞ አበረታቶታል ከወደቀበት እንደገና አንስቶታል፡፡
ስንቱ ሃያል እዚህ ግባ በማይባል ደካማ ሰው ተሸንፏል፡፡ ስንቱ ደካማ ሃያሉን ሰው አዋርዶታል፡፡ ዳዊትን ሃያሉን ጎሊያድን ሲያሸንፍ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደል ያውቅ ዘንድ ነው። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እናንተንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።1ኛ ሳሙኤል 17፡47
እግዚአብሄር ካልሰጠ ባለጠግነት በቅልጥፍና አይመጣም፡፡ ስንቱ በትንሽ ነገር ምክኒያት ሊይዘው ካለው የባለጠግነት ደረጃ ወድቆዋል ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ባለጠግነት ወድቆበታል፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡8
እግዚአብሄር ይሁን ካላለ ሰው አዋቂነቱ ብቻ ሞገስን አይሰጠውም፡፡ የስንት አስተዋዮች ማስተዋል ተጥሏል፡፡ ብዙ የማይጠበቅበት ሰው ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
በዚያም ወራት የመከራት የአኪጦፌል ምክር የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ነበረች፤ የአኪጦፌልም ምክር ሁሉ ከዳዊትና ከአቤሴሎም ጋር እንዲህ ነበረች። 2ኛ ሳሙኤል 16፡23
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ። የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይሻላል አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።2ኛ ሳሙኤል 17፡14
ሁሉን የሚያሰካካውና የሚያገናኘው የጊዜና የእድል ባለቤቱ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡እነዚህን ፈላጊና ተፈላጊ የሚያገናኘው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
የስኬት ቁልፉ ያለው ባለጠግነትም ሃያልነትም ጠቢብነትም ጋር ሳይሆን የክንውን ቁልፉ ያለው እግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አይኖቻችን ወደአንተ ናቸው፡፡ በሃይላችን በጥበባችን በሃብታችን አንታመንም፡፡ በአንተ ብቻ እንታመናለን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ስኬት #ባለጠጋ #ጠቢባን #ሃያላን #ሞገስ #ክንውን #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ቃል ቃል ቃል

%e1%89%83%e1%88%8d-5ቃል ታላቅ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ የሰውን የልቡን ሃሳብ የምንረዳው በቃል ብቻ ነው፡፡
ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል። ምሳሌ 20፡5
ሰዎች ለሁልጊዜ አብረው በጋብቻ ለመኖር የሚሰጣጡት አንድ ነገር ቃል ነው፡፡
ቃል በጣም ሃያል መሳሪያ እንደመሆኑ መጠን በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግ በውስጡ ሊያጠፋም ህይወት ሊሰጥም የሚችል እምቅ ጉልበት ያለው ነገር ነው፡፡
እንዲያውም ቃላችን የህይወታችንን ሁኔታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የህይወት ደረጃችን ነፀብራቅ ነው፡፡
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። ያዕቆብ 3፡2
ስለቃል አጠቃቀም መፅሃፍ ቅዱሳዊ ምክሮች
 • ቃልህ ጥቂት ይሁን
ቃላትን ከመናገራችን በፊት እራሳችን መቅመስ አለብን፡፡ ሰው በአንድ ጊዜ ጥቂት ቃላትን ብቻ ነው ቀምሶ መናገር የሚችለው፡፡ ብዙ ቃላትን ከተናገረ አጣጥሞ ቀምሶ ፈትሾ የመናገር ችሎታው እየቀነሰ ስለሚሄድ ይስታል፡፡
በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። ምሳሌ 10፡19
 • ቃሎችህ ቀላል ይሁኑ
የቃል አላማ ሃሳብን መለዋወጫ በመሆኑ ቃልህ ሁለትና ሶስት ትርጉም አይኑረው፡፡ ግልፅ ሁን፡፡ ቃሎችህ አንድ ትርጉንም ብቻ ይኑራቸው፡፡ በቃሎችህ ደግሞ ለማሳመን በጣም አትጣር፡፡ ቃሎችህ ራሳቸው ያሳምኑ፡፡ እንዲሁም በቃሎች ተማመንባቸው፡፡ ቃሎችህን ለመግባቢያ እንጂ በመሃላና በቃል ብዛት ሰዎችን አላግባብ ለመቆጣጠር አትጠቀምባቸው፡፡
ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። ማቴዎስ 5፡37
 • በወሳኝ ጊዜ ቃልን የሚሰጥህና እግዚአብሄር ነው
አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ ማቴዎስ 10፡19
 • ቃል ከመናገርህ በፊት ስማ
ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል። ምሳሌ 18፡13
በቃሉ የሚቸኵለውን ሰው ብታይ፥ ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው። ምሳሌ 29፡20
 • ቃልህ ፀጋን የሚመግብ እንደሆነ አውቀህ ሌላ አፍራሽ ነገር እንዳይሸከም ተጠንቀቅ
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
ኤፌሶን 4፡29
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለሚጠሩትም ባለ ጠጋ ነው

View of smiling man raising his hands standing in the fieldበአለም ላይ የሃብት ችግር የለም፡፡ በአለም ላይ ለሁሉም ሰው የሚበቃ ምንጭ አለ፡፡ እግዚአብሄር የአቅርቦች ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ በአለም ላይ ያለው ችግር እግዚአብሄርን ያለመፈለግና እግዚአብሄርን ያለመጥራት ችግር ነው፡፡ በምድር ላይ ያለው ችግር ወደ እግዚአብሄር ያለመፀለይ ችግር ነው፡፡
እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ባለጠግነት የሚጠቀሙበት የሚጠሩት ናቸው፡፡ የሚጠሩት የእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡ የሚጠሩት በእግዚአብሄር ባለጠግነት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ከባለጠግነቱ ተካፋዮች የሚሆኑት ሃብታሞች ብቻ አይደሉም ፡፡ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚጠቀሙት የሚሆኑት ሃያላን ብቻ አይደሉም፡፡ ወይም ደግሞ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚካፈሉት ጠቢባብን ብቻ አይደሉም፡፡ የሚጠሩት ሁሉ ከባለጠግነቱ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ፤ ሮሜ 10፡12
እግዚአብሄርን ያየው አንድስ እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው የተባለለት እየሱስ ስለእግዚአብሄር ልብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ማቴዎስ 7፡7
ለምኑ እንጂ ያለው በንግዳችሁ ልክ ለምኑ አላለም፡፡ ፈልጉ እንጂ ያለው በደሞዛችሁ ልክ ፍለጋችሁን ወስኑት አላለም፡፡ አንኳኩ እንጂ ባላችሁ ካፒታል ልክ አንኳኩ አአላለም፡፡
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡8
የእግዚአብሄር ባለጠግነት ከሃብቱ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ነው፡፡ ልመናችሁን በገቢያችሁ አትወስኑት ፡፡ ፀሎታችሁን በሃብታችሁ አትወስኑት፡፡ እግዚአብሄርን በኑሮዋችሁ ደረጃ አትወስኑት፡፡
እግዚአብሄርን ካልጠራነው ግን የባለጠግነቱ ተካፋይ ልንሆን አንችልም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ለምኑ #ባለጠግነት #አንኳኩ #ሃብት #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Incredible Opportunity to Prosper

shake.jpgIf you remain in me and my words remain in you, ask whatever you wish, and it will be done for you. John 15:7
We can’t fully describe the prosperity of God in our words. He is simply prosperous. In fact, He is the only and perfect reference to prosperity.
Through believing on the Lord Jesus Christ who came to pay our sin penalties on the cross, God adopted us God adopted us to be His sons and daughters through Jesus Christ. We are his children if we accept Jesus as our savior and Lord.
Our opportunity with Him is unspeakable. He just wants to give Himself to us His children.
He who did not spare his own Son, but gave him up for us all–how will he not also, along with him, graciously give us all things? Romans 8:32
We are constantly amazed and surprised to know how much freedom we have in Christ and the immeasurable riches in Him. God designed us to partake the riches of God.
He gladly and constantly invites us to make the most out of His riches. And Jesus who “is in closest relationship with the Father, has made him known.” John 1:18
If you remain in me and my words remain in you, ask whatever you wish, and it will be done for you. John 15:7
And in His words of invitation Jesus explains that it is the word of God by which we realize the prosperity of God in our lives. It takes the word to tap into the unsearchable riches of the Christ.
It takes to abide by the word. It takes to abide in the word. We have to obey and do the word to tap into the riches of God. And it takes the word to abides in us.
The riches of God are invested in the word of God. The word is designed to transfer the riches of God to us. We actually walk in the riches of God as much as we walk in the word of God.
As long as my God’s word has a place in your life , Your words will have a place in God’s.
As much as you are meek towards His word, He will be meek towards yours.
God is saying As long as you give yourself to my word, He will give Himself to you.
God is saying as much as you obey and do His word, He will do yours.
He is actually saying that When you treasure His word, He will treasure yours.
If you remain in me and my words remain in you, ask whatever you wish, and it will be done for you. John 15:7
#abide #prosperity #riches #God #Jesuschrist #church #salvation #abiywakumadinsa #abiydinsa #facebook

Motives are weighed by the LORD

Gold-Heart-ScaleIt isn’t only what we do in life that matters it is also why we do the things we do. Even our good activities should be checked as in what motive we do the things we do.

Even the respected good spiritual activities like prayer can be done in wrong motives.

Then Jesus said to his host, “When you give a luncheon or dinner, do not invite your friends, your brothers or sisters, your relatives, or your rich neighbors; if you do, they may invite you back and so you will be repaid. Luke 14:12

We are already paid for the spiritualIt isn’t only what we do in life that matters it is also why we do the things we do. Even our good activities should be checked as in what motive we do the things we do. Even the respected good spiritual activities like prayer can be done in wrong motives. Then Jesus said to his host, “When you give a luncheon or dinner, do not invite your friends, your brothers or sisters, your relatives, or your rich neighbors; if you do, they may invite you back and so you will be repaid. Luke 14:12 We are already paid for the spiritual activities we expect reward from God if we do it in a wrong motive. “And when you pray, do not be like the hypocrites, for they love to pray standing in the synagogues and on the street corners to be seen by others. Truly I tell you, they have received their reward in full. Matthew 6:5

Men see the appearance but God sees the heart and evaluates the motive behind our action. All a man’s ways seem right to him, but the LORD evaluates the motives. Proverbs 21:2 Now if any man builds on the foundation with gold, silver, precious stones, wood, hay, straw, each man’s work will become evident; for the day will show it because it is to be revealed with fire, and the fire itself will test the quality of each man’s work. 1 Corinthians 3:12-13 All a person’s ways seem pure to them, but motives are weighed by the LORD. Proverbs 16:2 activities we expect reward from God if we do it in a wrong motive.

“And when you pray, do not be like the hypocrites, for they love to pray standing in the synagogues and on the street corners to be seen by others. Truly I tell you, they have received their reward in full. Matthew 6:5

Men see the appearance but God sees the heart and evaluates the motive behind our action. All a man’s ways seem right to him, but the LORD evaluates the motives. Proverbs 21:2

Now if any man builds on the foundation with gold, silver, precious stones, wood, hay, straw, each man’s work will become evident; for the day will show it because it is to be revealed with fire, and the fire itself will test the quality of each man’s work. 1 Corinthians 3:12-13

All a person’s ways seem pure to them, but motives are weighed by the LORD. Proverbs 16:2

https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

%d bloggers like this: