Category Archives: joy

የማዳንህን ደስታ ስጠኝ

church leader.jpgየማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። መዝሙር 51፡12

እግዚአብሄር እኛን ለማዳን ሳይራራ አንድያ ልጁን ከፍሎዋል፡፡ ስለመዳናችን እጅግ ታላቅቅ ዋጋ ተከግፍሎዋል፡፡ መዳመናችንም ታላቅ ነው፡፡

ስለመዳናችን የምንሰማውን ነገር ልንጠነነቀቅ ይገባናል፡፡ መዳናችንን የሚያሳንስ ነገር የምንሰማ ከሆነ ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ነው፡፡ ከምንም ነገር በላይ መዳናችንን ቸል ለንለው አይገባንም፡፡ ስለመዳናችን እግዚአብሄርን በየጊዜው እንደ አዲስ ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል። በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ዕብራውያን 2፡2

የዳንነው ከሞት ነው፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንስ 5፡24

የዳንነው ለዘላላም ከእግዚአብሄር ጋር ከመለያየት ነው፡፡

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ማቴዎስ 25፡41

የዳንነው ከጨለማው ስልጣን ነው፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2

የዳንነው የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ ከመኖርና ህይወትን ካለማየት አሰቃቂ ህይወት ነው፡፡ የፈለስነው ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት  ነው፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

ይህንን መዳን የሚገባውን ስፍራ ካልሰጠነው ፣ ይህን መዳን ስናቃልልና ይህ መዳን ሲያንስብን በክርስትና ህይወታችን ሁሉ ነገራችን ይዛባል፡፡

ይህን ታላቅ መዳን በራሱ እንደሃብት ሳይሆን ግን እንደ መተላለፊያ ብቻ ስንቆጥረው ህይወታችን ይዛባል፡፡ ይህን መዳን በራሱ ታላቅ እድል እንደሆነ ስንረሳና እንደ ማትረፊያ መንገድ ብቻ ስናየው ህይወታችን በአደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡

በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡4-5

ይህን መዳን ስናከብረው በመዳናችን ደስ ስንሰኝ እግዚአብሄርን እንደሚገባው ማክበር እንችላለን፡፡ በዚህ መዳን ሳናቋርጥ ደስ ስንሰኝ ህይወታችን ሁሉ በምስጋና ይለመልማል፡፡ ይህን ታላቅ መዳን ስናከብረው በሁሉ ነገር እግዚአብሄርን በደስታ እንታዘዘዋለን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #ደስታ #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ

57972.pngጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፤ መዝሙር 32፡11

ራሳችንን እንመርምር ራሳችንን እንፈትን፡፡ ደስ እንዳይለን ያደረገው ነገር ምንድነው? ሰላማችንን የወሰደው ነገር ምንድነው? በእግዚአብሄር እንዳንመካ ያደረገን ነገር ምንድነው? እግዚአብሄርን እንዳናይ ያደረገን ነገር ምንድነው? ነገሮችን ጭልምልም እንዲልብን ያደረገን ነገር ምንድነው? ከእግዚአብሄር በላይ የገዘፈብን ነገር ምንድነው?

ምንም ይሁን ምንም በእግዚአብሄር ደስ እንዳንሰኝ የሚያደርገን ነገር መኖር የለበትም፡፡ እኛ ለክብሩ የሰራን የእግዚአብሄር ህዝቦች ነን፡፡

በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥ በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ። እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። መዝሙር 100፡2-3

ለክብሩ ተፈጥረናል፡፡ ኢየሱስን የምንከተል ሁላችሁ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡

በሌላ በሌላ ነገር ደስ ላይለን ይችላል፡፡ ዘመኑ የሚያስፈራ ሊሆን ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ግን ደስ ላለመሰኘት ምንም ምክኒያት የለንም፡፡

በብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ብናልፍም እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ በእኛ ላይ ያለው አላማ የፍቅር አላማ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ነገሮች ፈር የለቀቁ ቢመስልም እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ነው፡፡

ሰዎች ስለሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም በደስታ ዝለሉ ይለናል ጌታ ኢየሱስ፡፡

ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ሉቃስ 6፡22-23

ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ እግዚአብሄር አባታችን ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

መከራ በእኛ ውስጥ የሚሰራው እጅግ መልካም ነገር በመሆኑ በመከራ እንኳን ደስ እንዳንሰኝ ምክኒያት የለንም፡፡

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ያእቆብ 2፡2-3

እግዚአብሄርን ለሚወዱ ነገሮች ሁሉ በመጨረሻ ለእነርሱ በጎነት እንደሚሰረሩ ስለምናውቅ ደስ ይለናል፡፡

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28

ማንም ደስ ላለመሰኘት ምክኒያትን ቢያገኝ እኛ ግን በእግዚአብሄር ደስ ላለመሰኘት ምንም ምክኒያት አናገኝም፡፡

ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፤ መዝሙር 32፡11

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ሲጠሉአችሁ #ሲለዩአችሁም #ሲነቅፉአችሁም #ደስታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ሃሴት #ሰላም  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ሁልጊዜ በጌታ የመደሰት አስራ ሁለቱ ዋና ዋና ምክኒያቶች

rejoice.PNGሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4

እኛ በኢየሱስ አዳኝነት ላመንንና ክርስቶስን ለምንከተል ሁላችን ደስ መሰኘት የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ ደስ ላለመሰኘት ምክኒያት የለንም፡፡  ደስ ላለመሰኘት አንዳች ምክኒያት ልናገኝ አንችልም፡፡ ስለዚህ ነው ሁሉ ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ የሚለውን ትእዛዝ መተግበር ያለብን፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ የሚለውን ትእዛዝ ለመፈፀም ብዙ ምክኒያቶች አሉ፡፡ እንዲያውም በጌታ ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ የሚለውን ትእዛዝ ላለመፈፀም በቂ ምክኒያት ልናገኝ እንችልም፡፡

እውነት ነው ዙሪያችንን ስንመለከት ደስ የማይሉ ነገሮች ልናገኝ አንችላለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ሁሉ እያሉ ሁልጊዜ በጌታ ደስ እንዲለን ይጠበቅብናል፡፡

ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ሊለን የሚገባን ብዙ ምክኒያቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ፅሁፍ ያዘጋጀሁትን አስራ ሁለቱን ምክኒያቶች እነሆ፡፡

ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ሊለን የሚገባን 12ቱ ዋና ዋና ምክኒያቶች

 1. ካለምክኒያት በሚወደው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር ተወደናል፡፡

እግዚአብሄር የወደደን ሃጢያተኞችና ጠላቶች ሆነን ነው፡፡ አሁንም እግዚአብሄ የሚወደን ስለወደደን ነው፡፡ አንድ ነገር ስናደርግ የሚጠዓን ሌላ ነገር ስናደርግ የሚወደን እግዚአብሄር አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ፍፁም ፍቅር ነው፡፡ ከዚህ ከአግዚአብሄ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር የለም፡፡

እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ሮሜ 8፡33-35

 1. የሃጢያታችን እዳ ሙሉ ለሙሉ ተከፍሎዋል፡፡

በኢየሱስ የመስቀል ስራ ሙሉ ለሙሉ ከእግዚአብሄ ጋር ታርቀናል፡፡ እግዚአብሄር አሁን በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ ሃጢያታችንን ፈፅሞ አያስበውም፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች አድርጎናል፡፡ እንዲያውም ሌሎች ከእግዚአብሄር ጋር የሚታረቁበትን የማስታረቅ ቃል አኑሯል፡፡

እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19

 1. አዲስ ፍጥረት ሆነናል፡፡ የዘላለም ህይወት ተሰጥቶናል፡፡

ከዚህ ቀደም ሃጢያትን እንዳልሰራን ያህል እግዚአብሄር ተቀብሎናል፡፡ በቤተሰብ ውስጥ አሁን እንደተወለደ አዲስ ልጅ ተቀብሎናል፡፡ ስንሞት ደግሞ ወደየት እንደምንሄድ እናውቃለን፡፡

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ዮሃንስ 14፡1-3

 1. የእግዚአብሄር መንፈስ የሚኖርብን የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ ሆነናል፡፡

በምድር ላይ እንዲከናወንልን የሚያስፈልገውን ጥበብና ሃይል የሚሰጠንን መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል፡፡ ሁልጊዜ እንዲረዳን መንፈስ ቅዱስ በእኛ ይኖራል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ማደሪያ ቤተመቅደስ ሆነናል፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16

 1. እግዚአብሄር እረኛችን ነው የሚያሳጣንም ነገር የለም፡፡

እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡ እግዚአብሄር እየመራን አንደሆነ ከማወቅ በላይ የሚያስፈነጥዝ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ሆኖ የምናጣው ነገር የለም፡፡ እንዲያውም አሁን የሌለን ነገር ሁሉ ቢያንስ ቢያንስ ለአሁን የማያስፈልገን ስለሆነ ብቻ ነው፡፡

መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ዮሃንስ 10፡11

 1. እንድናሸንፍ ተወስኗል

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ስራ አሸናፊዎች ተደርገናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጠበቅ ውጤት የለም፡፡ ከአሸናፊ ቤተሰብ ከእግዚአብሄር በመወለዳችን አሸናፊ ተደርገናል፡፡ ሌሎችን የሚያሸንፉ አሸናፊዎች እኛ ግን አያሸንፉንም፡፡

በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 8፡37

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

 1. ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡

እግዚአብሄርን መስሎ ለመኖር የጎደለብን ነገር የለም፡፡ መንፈሳዊ ለመሆን የሚጠይቀው ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡ እንዲሁም በምድር ላይ ለመኖር የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

 1. ከሃጢያት የምንነፃበት መንገድ ተዘጋጅቶዋል፡፡

ሃጢያት ብንሰራ እንኳን በንስሃ ሃሳባችንና መንገዳችንን እንደለወጥን የኢየሱስ ደም ክርስቶስ ደም ከሃጢያታቸን ሁሉ ሊያነፃ የታመነ ነው፡፡

በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 1፡9

 1. እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡

እግዚአብሄርበሰማያት ከፍ ያለ ቦታ የሚኖረው ሊረዳን ነው፡፡

ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል። ዘዳግም 33፡26-27

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ሮሜ 8፡31

 1. የመለኮት ባህሪ ተካፋዮች ተደርገናል

የእግዚአብሄር መለኮታዊ ባህሪ ተካፋዮች ተደርገናል፡፡

ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡4

 1. ኢየሱስ ሊመራንና ሃይል ሊሆነን በውስጣችን ይኖራል

እግዚአብሄር ለጠራን ለማንኛውን ጥሪ ብቁ የሚያደርገን ኢየሱስ በልባችን ይኖራል፡፡

በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል። ቆላስይስ 2፡9-10

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5

 1. እግዚአብሄር ለእኛ ህይወት ሙሉ እቅድ አለው፡፡

እያንዳንዳችን  ስለ ህይወታችን የምናውቀው እውቀት ቢኖርም ማናችንም ሙሉ እውቀት የለንም፡፡ እግዚአብሄ የፈጠረን በአላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር ግን የህይወታችን እቅዱና ንድፉ በእጁ ነው ያለው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሄር ወደዚህ ምድር እንድንመጣ ያደረገው ያንን እቅድ እንድንፈፅም ነው፡፡ እኛ ባንረዳውም እግዚአብሄር ግን በህይወታችን ንድፍ ላይ በትጋት እየሰራ ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: