Category Archives: Test Temptation trial

ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል

sky_hd-t2.jpgየኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡10-12

ወደጌታ የመጣነው ጌታን የሚከተሉ ሰዎች በእሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ስላገለገሉን ነው፡፡ በጌታ የበረታነው ለእግዚአብሄር መንግስት ዋጋ የሚከፍሉ ሰዎች በመከራ ውስጥ እያለፉ ጌታን ስላሳዩን ነው፡፡

እነርሱ በተለያየ መልኩ ሲሰደዱና በመከራ ሲያልፉ የክርስቶስ ሞት በእነርሱ ይሰራ ነበር፡፡ ክርስቶስ እንደሞተ ያገለገሉን አገልጋዮች በሞት ውስጥ ያልፉ ነበር፡፡

የኢየሱስ ህይወት በአገልግሎታቸው ይገለጥ ዘንድ በስጋቸው መከራን ይቀበሉ ነበር፡፡ የኢየሱስን ህይወት እንዲያካፍሉን በመከራ ውስጥ ያልፉ ነበር፡፡

ስለዚህ ሞቱ እኛን ባገለገሉን ላይ ይሰራ ነበር ህይወቱ በእኛ ይሰራ ነበር፡፡ እነርሱ ሞቱን ሲካፈሉ እኛ ህይወቱን ተካፈልን፡፡

አሁን ደግሞ እኛ የምናገለግላቸው ሰዎች የክርስቶስን ህይወትን ይካፈሉ ዘንድ የክርስቶስ ሞት በእኛ ይሰራል፡፡ እኛ ከክርስቶስ ሞት ጋር ስንካፈልና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የሚሰሙን ሰዎች የክርስቶስን ህይወት ይካፈላሉ፡፡

እኛ በተለያየ መልኩ ስንሰደድና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የሚሰሙን ሰዎች የክርስቶስን ህይወት ይካፈላሉ፡፡ እኛ ስንጨፈለቅ እነርሱ ጭማቂን ይጠጣሉ፡፡ እኛ አገልጋዮቹ ስንሰደድና በመከራ ውስጥ ስናልፍ የክርስቶስ ሞት በእኛ ይሰራል የክርስቶስ ህይወት ደግሞ በምናገለግላቸው ላይ ይሰራል፡፡ ክርስቶስ እንደሞተ በሞት ውስጥ እናልፋለን፡፡ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ የምናገለግላቸው አገልግሎታችን ህይወቱን ይካፈላሉ፡፡

ስለዚህ አሁን ሞቱ በእኛ ይሰራል ህይወቱ እኛ በምናገለግላቸው ላይ ይሰራል፡፡

የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡10-12

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #መከራ #ፈተና #ሞት #ህይወት #ስጋ #መፅናት #መታገስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ስለፈተና የቃሉ የጥበብ አንኳሮች

test.jpgፈተና ፈተናነው፡፡ ፈተና ቀላል አይደለም፡፡ ፈተና ሲገቡበት የሚወጡበት አይመስልም፡፡ ፈተና ሳይመጣ ደግሞ የሚመጣ አይመስል፡፡ ፈተና አስጨናቂ ነገር ነው፡፡ ስለፈተና የእግዚአብሄር ቃል የሙሉውን ከተረዳን በፈተና እንዴት መቋቋም እንደምንችል እናውቃለን፡፡ ስለፈተና ከተረዳን ፈተና ማስፈራቱን ባያቆምም ይቀንሰዋል፡፡ ምክኒያቱም ፈተና ይመጣል፡፡ ፈተና ቢመጣ አይደለም የሚባለው ፈተና ሲመጣ ነው የሚባለው ምክኒያቱም ዝናብ ጎርፍ ነፋስ ይመጣል፡፡

ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ማቴዎስ 7፡25

  1. ለፈተና እንግዳ አትሁን

በአንድም በሌላ መልኩ ያለኸው በፈተና ውስጥ ነው፡፡ እንዲሁም በአንድም በሌላም መልኩ ሌላ ፈተና እየመጣ ነው፡፡ ፈተና ሊነካህ የማይች ሰው አድርገህ ራስህን አትቁጠር፡፡ ፈተና ቢመጣም ገፈተናውን ልታልፍ እንደምትችል በትህትና አስብ፡፡

በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። ዮሃንስ 16፡33

  1. የፈተናን አላማና ውጤት ተረዳ

የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል በህይወታችን የምንወርሰው በትግስት ነው፡፡ ፈተና ትእግስትን በህይወታችን ይሰራል፡፡

ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ሮሜ 8፡3-4

  1. በፈተናው ላይ አታተኩር

አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ፡፡ አንተ በምድር ላይ የእግዚአብሄርን አላማ እንድታስፈፅም የተላክ የእግዚአብሄር መልክተኛ ነህ፡፡ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስብህ በፈተና ግብ ላይ እንጂ በፈተናው ላይ ብቻ አታተኩር፡፡

እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራዊያን 12፡1-2

  1. እግዚአብሄር በክፉ እንደማይፈትን ተረዳ

ፈተና ሲመጣ እግዚአብሄር ሊጥልህ እንዳማይፈትንህ ተረዳ፡፡ ለክፉ የመጣውን ፈተና እግዚአብሄ ለመካለም ለውጦ አንተን ያጠራሃል፡፡ እግዚአብሄር ግን ሊጥል እንደማይፈትንህ አትርሳ፡፡ እግዚአብሄር በክፉ እንደማይፈትንህ ስትረዳ ከፈተናው በአሸናፊነት እንደምትወጣ ጉልበት ታገኛለህ፡፡

ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። ያዕቆብ 1፡13

  1. ከፈተና ግብ ለማምለጥ አትሞክር

ከፈተና ለማምለጥ ካልሞከርክና ከታገስከው ትግስት ሙሉ ሰው ያደርግሃል፡፡ ትግስት ከአንተ ላይ የማያስፈልገውን ነገር ያራግፋል፡፡ ትግስት የሚያገኘው እግዚአብሄር የማይወደውን ስጋዊ ባህሪ እንጂ አንተን አይደለም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርን የሚያሳዝነውን ስጋዊ ምኞት እንዲገድል ተባበር፡፡ ከፈተና ይዘህ የምትወጣውን በሌላ በምንም መንገድ የማይገኘውን ሙላት  አስብ፡፡ በፈተናው ላይ ሳይሆን ከፈተና ውስጥ በምታገኘው ነገር ላይ አተኩር፡፡ ፈተናው በህይወትህ በሚሰራው ወሳኝ ስራ ላይ ካተኮርክ በፈተናው ለመፅናት ጉልበትን ታገኛለህ፡፡

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ያዕቆብ 1፡2-4

  1. በፈተና ወቅት በጥንቃቄ ኑር

በፈተናው ውስጥ ስታልፍ ሰይጣን በፈተናው ውስጥ ያዘጋጀውን ወጥመድ ውስጥ አለመውደቅህን እርግጠኛ ሁን፡፡ በፈተናው ውስጥ በእግዚአብሄር ህግ መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡ በፈተናው ውስጥ ቸኩለህ የተሳሳተ ውሳኔ ላለመወሰን ታገስ፡፡ የሰይጣን አላማ ሊያረክስህ ነውና በፈተናው ጊዜ በንፅህና መመላለስህን እርግጠኛ ሁን፡፡ በፈተናው ጊዜ በህጉ መጫወትህን እርግጠኛ ሁን፡፡

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ኤፌሶን 5፡15

  1. በፈተናው ውስጥ በጌታ ደስ ይበልህ

የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን። ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ያዕቆብ 1፡2-3

  1. ከፈተናው የተሻለ ነገር ማውጣትህን እርግጠኛ ሁን

አንተን ለመጣል የመጣውን ፈተናውን መልሰህ ለራስህ ጥቅም አውለው፡፡ በፈተናው አትሸነፍ በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ፡፡ ክፉውን ቀኖች ዋጅተህ ለራስህ ጥቅም አውላቸው፡፡

ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ቆላስይስ 4፡5

  1. ጥበብን ጠይቅ

ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፡፡ ማንኛውም ጥያቄ መልስ አለው፡፡ ለጊዜው ቢመስልም መልስ የሌለው ጥያቄ መፍትሄ የሌለው ችግር የለም፡፡ የፈተና ከባድነት መውጫውን አለማየት ነው፡፡ መውጫውን ማየት እንድትችል ጥበብን ከእግዚአብሄር ለምን፡፡

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡2-5

  1. ከፈተናው ውስጥ ምስጋናን ይዘህ ውጣ

በፈተናው ወቅት አመስግን፡፡ ምሰጋና ሲመቸን የምናቀርበው ብቻ ሳይሆን ሳይመቸን የምንሰዋው ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄርን እጅግ የሚጣፍጠው ምስጋና በአስቸጋሪ ነገር ውስጥ ሆነህ የምትሰዋው ምስጋና ነው፡፡ ከፈተናው ውሰጥ ምስጋናን ብቻ ይዘህ ውጣ፡፡ ከፈተናው ውስጥ እከሌ እንዲህ አደረገኝ አከሊትይ እንዲህ አደረገችኝ አትበል፡፡ ከፈተናው ውስጥ ይዘህ መውጣት ያለብህ ብቸኛ ትምህርት እግዚአብሄር መልካም ነው የሚል መሆን አለበት፡፡ ብዙ ቅዱሳን በተለያየ ከፍታና ዝቅታ አልፈዋል፡፡ ሁሉም ግን ሲወጡ እግዚአብሄር መልካመ ነው የሚል መረዳት ይዘው ነው የወጡት፡፡

እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። ናሆም 1፡7

ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝመር 50፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #አምላክ #ፈተና #መከራ #ትግስት #ምሉአን #ፍፁማን #ደስታ #ምስጋና #ፅናት #ጥበብ #እምነት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: