Category Archives: Holy Spirit

የጌታ መንፈስ አብሮን እንዲሆንና በሃይል እንዲሰራ የሚያደርጉ 5 ነገሮች

church leader.jpgየእግዚአብሄር መንፈስ መገኘት ለማንኛውም ጥያቄያችን መልስ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሲገኝ በህይወታችን ሙሉ ነፃነትን እንለማመዳለን፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሲገኝ በህይወታችን የማይቻል ነገር አይኖርም፡፡

ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡17

እኛ የምናደርጋቸው የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚያሳዝኑት ነገሮች አሉ፡፡ እኛ የምናደርጋቸው የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚያስደስቱት ነገሮች አሉ፡፡

ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡30

የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚስቡ ባህሪዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ የሚገፉ ባህሪዎችም አሉ፡፡

የልብ ንፅህና

የእግዚአብሄር መንፈስ በሃይል እንዲገኝና ከእኛ ጋር አብሮ እንዲሰራ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ የልባችን ንፅህና ነው፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስና ንፁህ ስለሆነ ንፁህ ነገር ይስበዋል፡፡

ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡8

ትህትና

እግዚእብሄር ትእቢተኛን ይቃወማል ለትሁታንም ፀጋን ይሰጣል፡፡ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡5

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? ትንቢተ ኢሳይያስ 66፡1-2

እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።

እግዚአብሄርን መፍራት

ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል። መዝሙረ ዳዊት 24፡3-5

ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡10-12

ምስጋና

በሆነው ባልሆነው የማያጉረመርም ሰው የእግዚአብሄርን መንፈስ አብሮይት ሊሀና ሊሰራ አይችልም፡፡ እግዚአብሄን በነገር ሁሉ የሚያመሰግን ሰው ግን የእግዚአብሄር መንፈስ አብሮት ይሰራል በሚያልፍበት ነገር ሁሉ ውስጥ አብሮት ይሆናል ያሳልፈዋል፡፡

አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። ትንቢተ ኢሳይያስ 43፡2-3

ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙረ ዳዊት 50፡23

መፈለግ

ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው። እግዚአብሔርም፦ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው። እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡12-15

እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ትንቢተ ኤርምያስ 29፡13-14

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #መገኘት #ህልውና #ቃል #ህልዎት #የጌታመንፈስ #አብሮነት #ክብር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት #አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነፃነት #ሞገስ #እረፍት #እርካታ #አርነት #ንፅህና #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የጌታም መንፈስ ባለበት

church leader.jpg

ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡17

የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ መታወክ የለም፡፡ የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ ደስታ አለ፡፡ የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ ተስፋ አለ፡፡ የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አቅጣጫን የሚያሳይ ብርሃን አለ፡፡

ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። መዝሙረ ዳዊት 16፡8 ፣ 9 ፣ 11

የጌታ መንፈስ ባለበት እርካታ አለ፡፡

እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙረ ዳዊት 17፡15

የጌታ መንፈስ ባለበት እረፍት አለ፡፡

ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው። እግዚአብሔርም፦ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው። እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡12-15

የእግዚአብሄር መንፈስ ባለበት ሁለንተናዊ ነፃነት አለ፡፡

ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። ማቴዎስ 18፡19-20

ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡17

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #መገኘት #ህልውና #ቃል #ህልዎት #የጌታመንፈስ #አብሮነት #ክብር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት #አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ነፃነት #ሞገስ #እርፍት #እርካታ #አርነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ

pride.jpgከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስይስ 2፡20-21

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚል ትእዛዝ ለእኛ በክርስቶስ አምነን ለዳንን አይገባንም፡፡ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚል ትእዛዝ ለእኛ የማይመጥንበትን ምክነቢያቶች እንመልከት

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ አለማዊ ስርአት ነው

በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጣቸው አይኖርም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄርን ፍቅር አልተረዱም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር ፍቅር አይመራቸውም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች መንፈሳቸው ሙት ነው፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች በእግዚአብሄር መንፈስ ህያው አልሆኑም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄር ቃል በውስጣቸው የለም፡፡ ስለዚህ  አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ ኤፌሶ 2፡1

በአለም ያሉ ሰዎች የሚመሩት አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ  ስርአት ብቻ ነው፡፡ ሌላ የሚያሸንፍ መንፈስ በውስጣቸው ስለሌለ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ ብቻ ነው በአለም ያሉትን ሰዎች የሚያሸንፋቸው፡፡ ለእኛ ግን መንፈሳችን ህያው ስለሆነ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ትእዛዝ አያስፈልገንም፡፡ እኛ በኢየሱስ ስለምንኖር ቃሎቹም በውስጣችን ስለሚኖር እግዚአብሄር በመንፈሱ አማካኝነት ይመራናል፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የመጀመሪያ ትምህርት ነው

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የመጀመሪያ ትምህርት ነው፡፡ ልጅ መጀመሪያ የነገሮችን ጉዳትና ጥቅም በራሱ ስለማይረዳ ትእዛዘ ይሰጠዋል፡፡ ልጅ በራሱ አነሳሽነት ነገሮችን ለማድርግ ብቃቱን ስላዳበረ ትእዛዝ በትእዛዝ ይሰጠዋል፡፡ ልጅ እራሱ አውቆ ነገሮችን ስለማይሰራ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ተብሎ ይታዘዛል፡፡

ጎልማሳ ሰው ግን ይህ አያስፈልገውም፡፡ የነገሮችን ጥቅምና ጉዳት ስለሚያመዛዘን በራሱ ይወስናል፡፡ በተመሳይ መልኩ በክርስትና የምንመራው በህጉ መንፈስ እንጂ በህጉ ፊደል አይደለም፡፡ ህጉን ተረድተን በገባነ መንገድ እንተረጉመዋለን እንጂ ሰዎች ይህን አድርጉ ይህን አታድርጉ እያሉ እንደህፃን ልጅ እንዲመሩን እንጠብቅም፡፡  ቃሉን ሰምተን የታዘዘው ትእዛዝ ለምን እንደታዘዘ ተረድተን እናደርገዋለን እንጂ በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ይህን አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚለን ሌላ ሰው እንጠብቅም፡፡

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሰው ስርአት ነው

አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሰው ስርአት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት አንድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስርአት እግዚአብሄርን እና ባልንጀራህን ውደድ ነው፡፡ ትእዛዛት ሁሉ በሁለቱ ትእዛዛት ይጠቃለላሉ፡፡

እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። ሮሜ 12፡8-10

የትእዛዛት ሁሉ አላማ እኛ በፍቅር እንድንኖር መርዳት ነው፡፡

የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡5

ከፍቅር ህግ በላይ የሚጨምር ግን ህጉን ይሽረዋል፡፡

ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። ማርቆስ 7፡13

ለእኛ ግን የእግዚአብሄር ምንፈስ በእናንት ውስጥ ይኖራል እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ነው የምንባለው፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20-27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አትያዝ #አትቅመስ #አትንካ #አለማዊ #ስርአት #መጀመሪያ #ፅድቅ ሰላም #መንፈስቅዱስ #ደስታ #መብል #መጠጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ድምፅ #ቅባት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መሪ

የፀሎት መሰረት

prayer foundation.jpgበፀሎት ውስጥ እጅግ ታላቅ ሃይል አለ፡፡ ለእግዚአብሄር የኖሩና እግዚአብሄርን ያገለገሉ ሰዎች ሁሉ በፀሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ የፀሎት ሰዎች የሃይል ሰዎች ናቸው፡፡ የፀሎት ሰዎች የእምነት ሰዎች ናቸው፡፡ የፀሎት ሰዎች ፍሬያማ ሰዎች ናቸው፡፡ ካለ ፀሎት የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሚገባ መፈፀም የማይታሰብ ነገር ነው፡፡

ፀሎት ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ የምናደርግው ነገር ነው፡፡ ፀሎት የምናስበውን ሃሳብ ተናግረን የምንሄድበት ነገር አይደለም፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን መስማት ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡

የፀሎት ዋናው ክፍል እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ የፀሎት መሰረቱ እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ ፀሎት የሚጀመረው ለእግዚአብሄር ከመናገር አይደለም፡፡ ፀሎት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከመስማት ነው፡፡

ፀሎትይ ወደአእምሮዋችን የሚመጣውን ነገር ተናግሮ መነሳት አይደለም፡፡ ፀሎት የሚጀመረው በእግዚአብሄር ፊት ከመቆየት ነው፡፡ ጸሎት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከመጠበቅ ነው፡፡

ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። መዝሙር 40፡31

የፀሎት ዋናው ጉዳይ ለእግዚአብሄር ንግግር ቅድሚያ መስጠት ነው፡፡ የፀሎት ዋናው ክፍል ለማናገር ሳይሆን ለመስማት መቅረብ ነው፡፡

ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን። መክብብ 5፡1-2

በፀሎታችን ፍሬያማ የምንሆነው በእግዚአብሄር ላይ በተደገፍን መጠን ብቻ ነው፡፡

በፀሎት ለመናገር የሚያስቸኩለን ነገር የለም፡፡ የሚያስፈልጋችሁን እርሱ ያውቃል ብሎናል፡፡

አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡7-8

ፀሎት በእረፍት መሆን አለበት፡፡ ፀሎት በፀጥታና በመታመን መሆን አለበት፡፡

የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ ኢሳያስ 30፡15

የፀሎት ዋናው ክፍል በእግዚአብሄር ፊት ማረፍ ነው፡፡ የፀሎት ዋናው ክፍል እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ የፀሎት መሰረት እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡

ከእግዚአብሄር መንፈስ ውጭ በራሳችን እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅም፡፡ በፀሎታችን መንፈሱን መጠበቅና መስማት ያስፈልገናል፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ሮሜ 8፡26-27

በፀሎታችን የእግዚአብሄርን መንፈስ ሰምተን የምንፀልየው ፀሎት መሬት አይወድቅም፡፡ የፀሎት ዋናው እና በጣም አስፈላጊው ክፍል የእግዚአብሄርን መንፈስ መጠበቅና መስማት ነው፡፡ መንፈሱን ሰምተን የምንፀልየው ነገር ሁሉ አንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ስለሆነ ሁሉም ይመለሳል፡፡ መጠበቅ መታገስ የሚጠይቀው መንፈሱን መስማት እና መከተል እንጂ ለእግዚአብሄር መናገር አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ የመንፈስን ሃሳብ ካወቅን የሚመለስ ፀሎትን መፀለይ ይቀላል፡፡

መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-12

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ይማልዳል #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅም

prayer help.jpgእንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ሮሜ 8፡26-27

ፀሎት ወሳኝ የህይወታችን ክፍል ነው፡፡ ፀሎት እንደ እስትንፋስ ይቆጠራል፡፡ ሰው ሳይተነፍስ መኖር እንደማይችል ሁሉ ሰው ሳይፀልይ በእግዚአብሄር መኖር አይችልም፡፡

ክርስትና ወግና ስርአትን ብቻ የመጠበቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ክርስትና ህይወት ነው፡፡ በክርስትና ህይወታችን በሁሉም ነገር በእግዚአብሄር መንፈስ ላይ መደገፍ እንዳለብን ሁሉ በፀሎትም በእግዚአብሄር መደገፍ ይገባናል፡፡

ነገር ግን የተሳካን የፀሎት ህይወት በራሳችን አናመጣውም፡፡ የቱም እውቀታችን የተሳካ የፀሎት ህይወት ሊያመጣልንም አይችልም፡፡ የቱም የክርስትና ልምዳችን በራሱ የተሳካን የፀሎት ህይወት ሊያመጣልን አይችልም፡፡

እንዲያውም እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅም፡፡

በምድር ያለነው የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም እንጂ የምንፈልገውን ነገር ለማድረግ አይደለም፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን በመቀበል የዳነው አስቀድሞ በክርስቶስ ኢየሱስ የተዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለመፈፀም ነው፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

የምንፀልየው የራሳችንን ጉዳይ ለማስፈፀም አይደለም፡፡ የምንፀልየው የእግዚአብሄርን አላማ ለማወቅና ለመከተል ነው፡፡ አሁን ስለምን መፀለይ እንዳለብን የእግዚአብሄርን ሃሳብ የሚያውቀው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ካለብን መንፈስ ቅዱስ ሊገልጥልን ይገባል፡፡ ካለመንፈስ ቅዱስ ምሪት የእግዚአብሄርን ሃሳብ ምን አሁን ምን መፀለይ እንዳለብን አናውቅም፡፡ በአእምሯችን የመጣውን ብቻ መናገር ወደ ውጤት አያደርስም፡፡

መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-12

በራሳችን የእግዚአብሄርን ፈቃድ አናውቅም፡፡ በራሳችን የእግዚአብሄርን አላማ አንረዳም፡፡ በራሳችን ምን መፀለይ እንደሚገባን አናውቅም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ምን መፀለይ እንዳለብን ያለማወቅ ድካማችንን ሊያግዘን ያስፈልጋል፡፡

ለእግዚአብሄር ከመናገራችን በፊት መንፈሱን ልንሰማ ይገባል፡፡ መንፈሱን ሰምተን የምንናገረው ነገር ሁሉ ውጤት አለው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር የሚያየውና የሚያውቀው መንፈስ ያለማወቅ ድካማችንን ያግዛል፡፡

ፍሬያማ የፀሎት ህይወት የሚሰጠንና ፀሎታችንን ወደ ውጤት የሚያደርሰው እንደው መፀለይ ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት መፀለይ ነው፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ሮሜ 8፡26-27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ይማልዳል #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

የአፅናኙ መንፈስ ቅዱስ አምስት እጥፍ በረከቶች

holy spirit 5.jpgአብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ (አፅናኝ ፣ ተሟጋች ፣ የሚማልድ ፣ አማካሪ ፣ አብሮ የሚቆም ) እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ  14:26

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ እንደአባት ነበር፡፡ እንደአባት ይመራቸዋል ያስተምራቸዋል ይመክራቸዋል፡፡ ኢየሱስ በምድር በነበረ ጊዜ ስጋ ለብ ስለመጣ ውስን በመሆኑ ይህንን ሊያደርግ የቻለው ለደቀመዛሙርቱ ብቻ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከምድር ላይ ሲወሰድ ደቀመዛሙርቱን አባት እንደሌላቸው ልጆች እንደማይተዋቸውና አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣና እንደሚመራቸው ይነግራቸው ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ እና በአማኙ ውስጥ ሲኖር የሚያደርጋቸውን አምስት ነገሮችን እንመልከት፡፡

  1. አፅናኝ

ኢየሱስን ስንቀበል እና መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሲኖር የሚያደርገው ነገር እኛን ማፅናናተ ነው፡፡ ማፅናናተ ማለት ደግሞ ህይወታቸንነ ማመቻቸት የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር የሚቆረቁረንን ነገር ማወገድ እንቅፋትን ከፊታችን ማስወገድ ማጽፅናናት ደስ ማሰኘትና በደስታ እና በስኬት ጌታን እንድንከተል ማስቻል የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው፡፡

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ዮሃንስ 14፡15-16

  1. ተሟጋች

መንፈስ ቅዱስ ጠበቃችን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ወገን ሆኖ ነገሮችን እና ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ ይቆምልናል፡፡ እኛ መናገር ባልቻልን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አፋችንን ተጠቀሞ ይናገርልናል፡፡ በህይወት ሁኔተ ውስጥጭ በተግዳሮት ውስጥ የእኛ ወገን ሆኖ ምን ማድረግ እንዳለብን እንደጠበቃ ያማክረናል ይመራናል፡፡

አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ማቴዎስ 10፡19-20

  1. የሚማልድ

መንፈስ ቅዱስ ምን መፀለይ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ እንኳን ያለማወቅ ድካችንን ያግዛል፡፡ ፀሎታችን ከንቱ አንዳይሆን ይረዳል፡፡ ፀሎታችን የእግዚአብሄርን ልብ ያማከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ጸሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡26

  1. አማካሪ

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ድንቅ መካር ነበር፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ድንቅ መካር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚመክረው ምክር መሬት ጠብ የማይል ምክር ነው፡፡

እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡27

  1. አብሮ የሚቆም

መንፈስ ቅዱስ ሁሌ አብሮን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን ለዘላለም ከእኛ ጋር አብሮ እንዲኖር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አልነበረም ብለምን የምናመካኝበት ጊዜ የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በየጊዜው አይጎበኘንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል፡፡

ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። ሐዋሪያት 6፡10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #የሚማልድ #አማካሪ #ተሟጋች #ጠበቃ #እውነት #በውስጣችሁ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች

Holy-Spirit.jpgብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሃንስ 14፡15-18

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ያስተምራቸውና ይመራቸው ነበር፡፡ ጥያቄ ሲኖርባቸው ጥያቄያውን በትክክል ይመልስላቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን እንደአባት ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸው ነበር፡፡

ኢየሱስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ በሚወሰድበት ጊዜ ግን ደቀመዛሙርቱ የኢየሱስን የአባትነት መሪነት ያጡታል፡፡ ኢየሱስ ወደሰማይ ሲወሰድ በግል እያንዳንዳቸውን አግኝቶ ሊመክራቸ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራቸው አይችልም ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስ ከምድር ከመሄዱ በፊት አባት እንደሌላቸው ልጆች ካለ ምሪትና ካለ ማፅናናት እንደማይተዋቸው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተመልሶ እንደሚመጣ ለደቀመዛሙርቱ የሚነግራቸው፡፡

አሁን መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ አለ፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በሚከተሉ ሰዎች ውስጥ ያድራል፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ያደርገው የነበረውን ማፅናትና ምሪት ሁሉ ይሰጣል፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ሊያፅናና ፣ ሊመክር ፣ ሊያስተምርና ወደ እውነት ሁሉ ሊመራ የሚችለው ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምደር ሲኖር በስጋ የተወሰነ ስለነበር የምድር ህዝብን ሁሉ በግል ሊያፅናናና ሊመራ አይችልም ነበር፡፡

አሁን መንፈስ ቅዱስ ግን በስጋ ስለማይኖርና በስጋ ስለማይወሰን ኢየሱስን የተቀበሉት ሰዎች ሁሉ ውስጥ ይኖራል፡፡ ኢየሱስን በሚከተሉት ሰዎች ሁሉ ውስጥ በመኖር ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸዋል፡፡

እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሃንስ 14፡15-18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #እውነት #በውስጣችሁ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ

secrat.jpgለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። ቆላስይስ 1፡27

እግዚአብሄር ልጆቹ ሁሉ አንዲያሸንፉ ስለፈለገ በነገር ሁሉ ያሸነፈው ኢየሱስ በሚያምኑት ሁሉ ውስጥ እንዲኖርና እነርሱ እንዲያሸንፉ አደረገ፡፡

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

. . . ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ . . . ኤፌሶን 3፡16-17

ክርስቶስ የክብር ተስፋ አለው፡፡ የክብር ተስፋ የለው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡

አንድ እቃ መግዛት ከፈለጋችሁ ቀብድ ታስይዛላችሁ፡፡ ቅበድ አስያዛችሁ ማለት እቃው ለእናንተ ይቀመጥላችኋል እንጂ የሌላ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡ ሌላ ገዢ ከመጣ ቀብድ ተከፍሎበታል አይሸጥም ይባላል፡፡

እንዲሁም እግዚአብሔር በክርስቶስ የደም ዋጋን በመክፈል የእርሱ አድርጎናል፡፡ የእርሱ መሆናችንን ማረጋገጫ የሚሆንብን የመንፈሱን መያዣ ሰጥቶናል፡፡ እኛ የእርሱ ነን፡፡ ተስፋችን ሙሉ ነው፡፡

ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።2ኛ ቆሮንቶስ 5:5

በምድር ላይም አሸናፊ ሆነን የምንኖረው የክብር ተስፋ በእኛ ውስጥ ስላለ ነው፡፡ የምድር አሸናፊነታችንም ተስፋ በሰማይና ምድር ሁሉ ስልጣን የተሰጠው ክርስቶስ በእኛ ውስጥ መሆኑ ነው፡፡

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5

ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። ቆላስይስ 1፡27

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በልባችን #የእግዚአብሄርቤተመቅደስ #ክርስቶስ #ክርስቶስበእኛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ክርስቶስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በመንፈሱ #የእግዚአብሄርቤተመቅደስ #እምነት

መንፈስ ቅዱስ በእኛ

GodMuscleinYouBlogHeader.jpgክርስትና ስርአትንና ወግን የምንፈፅምበት ባዶ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና በምድር እግዚአብሔርን መስሎ የመኖር ህይወት ነው፡፡ ክርስትና ሁለንተናን ለእግዚአብሔር መንግስት መስጠት ነው፡፡ ክርስትና በሁለንተና ጌታ ክርስቶስን መከተል ነው፡፡ ክርስትና ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ በመፈፀም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ ክርስትና እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጠርንበትን አላማ ማሳካት ነው፡፡

ይህ ከፍ ያለ የክርስትና የህይወት ደረጃ ወግና ስርአትን በመፈፀም ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ይህ ከፍ ያለ የክርስትና የኑሮ ደረጃ የእግዚአብሔርን ሃይል ይጠይቃል፡፡ ካለ እግዚአብሔር ሃይል ይህ ደረጃ የማይታሰብ ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ነው፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ የተቀበልብን ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ይኖራል፡፡ ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች ልዩ የሚያደርገው ክርስቶስ በተከታዮቹ ውስጥ መኖሩ ነው፡፡ ጌተራ ኢየሱስን አዳኛችን ያደረግን ሁላችን የእግዚአብሔር ልጅነት ስልጣንን አግኝተናል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅነትን ደረጃ ለመኖር የሚያስፈልገን ሃይል ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

በክርስትና የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን እንድኖር ብቁ የሚያደርገን የእግዚአብሔር መንፈስ በውሰጣችን ስለሚኖር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ስራ የምንሰራው በራሳችን ይል አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን መስለን የምንኖረው በሰው ጉልበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅነትን የህይወት ደረጃ የምናሟላው በውስጣችን በሚኖረው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5

መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን በውስጣችን ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንኖር ሊያግዘን በልባችን ይኖራል፡፡

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ዮሃንስ 14፡15-17

የእግዚአብሔርን ልጅነትን የህይወት ደረጃ የምናሟላው በእግዚአብሔርን መንፈስ ረዳትነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር በልቡና በነፍሱ እንዳለ የምንኖረው በውስጣችን ባደረው በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት ነው፡፡

እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የመኖሪያ ፈቃድ

anointing.gifእግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲግባባ ነው፡፡ ሰው በምድር ላይ የእግዚአብሄርን አላማ እንዲያስፈፅም በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ተፈጥሮአል፡፡

ሰው ሃጢያት በሰራና በእግዚአብሄር ላይ ባመፀ ጊዜ ከእግዚአብሄ ጋር የነበረው የአባትና ልጅ ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መግባባት አቃተው፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ እውነትን አጣው፡፡

ኢየሱስ ወደምድር የመጣውና የሃጢያት እዳችንን ሁሉ የከፈለው የእግዚአብሄር ልጆች እንድንሆንና የእግዚአብሄር መንፈስ እንዲያድርብንና ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራን ነው፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20፣27

የእግዚአብሄር መንፈስ ለጥቂት ሰዎች ብቻ አይደለም፡፡ በጌታ ኢየሱስ ያመነ ሰው ሁሉ ከቅዱሱ ቅባት ተቀብሎዋል፡፡ በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላችን የእግዚአብሄር ምሪት ስለሚያስፈልገን ይህ የተቀበልነው ቅባት በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16

ይህ በእኛ ውስጥ ለዘላለም የሚኖረው ቅባት የእግዚአብሄርን መንገድ ያስተምረናል፡፡

ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ዮሃንስ 16፡13

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ዮሐንስ 14፡15-17

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።ዮሐንስ 14፡26

እከሌ ካላስተማረኝ ዋጋ የለኝም እስከማንል ድረስ ወይም ግዴታ ሌላ አስተማሪ ሊያስተምረን እስከማያስፈልገን ድረስ ቅባቱ በህይወታችን ማወቅ ያለብንን ነገር ሁሉ ያስተምረናል፡፡

በውስጣችን የሚኖረው ቅባት የሚያስተምረን አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳይሆን ዘወትር ያስተምረናል፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ከየት አገኘዋለሁ እሰከማንል ድረስ የእግዚአብሄር እውነት በቅባቱ በልባችን ቀርቦዋል፡፡

ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ሮሜ 10፡6-7

ይህ በውስጣችን ያለው ቅባት የሚያስተምረን ስለሁሉ ነው፡፡ በህይወታችን ያለውን ሃላፊነት የምንወጣበትን እውቀት ሁሉ ይሰጠናል፡፡ ይህ ትንሽ ነው ብሎ የሚንቀውና የማያስተምረን ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ከምናስበው በላይ ስለህይወት ዝርዝር ነገራችን እንደሚገደው ሁሉ  በውስጣችን ያለው ቅባት ስለዝርዝር ነገራችን ሁሉ ያስተምረናል፡፡ ማቴዎስ 10፡30

ይህ ቅባት የሚያስተምረው ነገር ሁሉ አስተማማኝ እውነት ነው፡፡ በሌላ በማንም ባትተማመኑ በውስጣችሁ ቅባት መተማመን አለባችሁ፡፡ ማንም ቢዋሽ ይህ ቅባት እውነተኛውን ነገር ይናገራል፡፡

እንዳስተማረን በእርሱ ልንኖር ይገባናል፡፡ በሌላ በምንም ለመኖር ብንፈራ ቅባቱ ባስተማረን ለመኖርት መፍራት የለብን፡፡ ሌላ ምንም ያስተናል ብንል ብንጠራጠር ቅባቱ ግን አያስተንም፡፡ በሌላ በምንም እውቀት ለመኖር ነፃነቱ ባይኖረን ቅባቱ እንዳስተማረን ለመኖር ግን ነፃነቱ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ በቅባቱ ምሪት ነፃ ካልሆንን በምንም ነፃ አንሆንም፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡20፣27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #እውነት #ምሪት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት  #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የሚመራ መንፈስ

How-to-Establish-Yourself-as-a-Thought-Leader-in-Your-Field1.jpgአብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 14፡26

በሃጢያት ምክኒያት እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተቅበዝብዘን ነበር፡፡ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር የሚረዳ አልነበረም፡፡ በእግዚአብሄር መንገድ የሚሄድ ሰው አልነበረም፡፡

ባለመታዘዝ ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የተለያየውን የሰው ልጅን የሃጢያት እዳ ለመክፈል ኢየሱስ ወደ ምድር መጣ፡፡ በኢየሱስ ሞት የሃጢያት እዳው ሁሉ በመስቀል ላይ ስለተከፈለ ሰው በንስሃ ወደ እግዚአብሄር ሲመለስ እግዚአብሄር የራሱን መንፈስ ይሰጠዋል፡፡ ኢየሱስን አንደ አዳኝና ጌታ ስንቀበለው የሚሰጠን መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄርን የመጀመሪያውን ሃሳብ ያሳየናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሰው የሃጢያት ሃሳብ ወዳልተቀላቀለው ንፁህ የእግዚአብሄር ሃሳብ ያሳየናል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራላል፡፡

እኛ እግዚአብሄር እንዲመራን ከምንፈልገው በላይ እርሱ እኛን ሁልጊዜ ሊመራን ይፈልጋል፡፡ ለሁል ጊዜ መሪያችን ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል፡፡

መንፈስ ቅዱስን ለምሪታችን ፈልገነው የሚጎልብን ምንም እውነት የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ መርቶን የማንረዳውና የምንስተው ምንም ነገር የለም፡፡ ለምሪታችን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ተደግፈን የምናጣው ብርሃን የለም፡፡

በምናደርገው በማንኛውም ውሳኔ ፈቃዱን መጠየቅ እንድንችል መንፈስ ቅዱስ መኖሪያውን በእኛ ውስጥ  አድርጓል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው

SPIRIT BORN.jpgከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዮሐንስ 3፡3-6

ኢየሱስ ኒቆዲሞስ ለተባለው የህግ መምህር ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም አለው፡፡

ሰው ወደዚህ ምድር ለመግባት ከእናትና ከአባቱ መወለድ አለበት፡፡ ይህ መወለድ የመጀመሪያው መወለድ ነው፡፡ ስለዚህ መወለድ መፅሃፍ ቅዱስ በዮሃንስ 1፡13 ሲናገረው ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ በማለት ወደምድር መግቢያውን መንገድ ይናገራል፡፡

ወደዚህ ምድር ለመግባት በስጋ ከእናትና ከአባታችን እንደተወልድን ሁሉ መንፈስ ወደ ሆነው በአይን ወደማይታየው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ደግሞ እንዲሁ መወለድ አለብን፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በመንፈስ እንጂ በስጋ አይን ስለማትታይ በመካከላችን ብትሆንም ዳግመኛ ካልተወለድን ልናያት አንችልም፡፡

ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡20-21

ከእናትና ከአባታችን ባንወለድ ኖሮ ወደ ምድር መንግስት መግባት እንደማንችል ሁሉ መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ካልተወለድን በስተቀር ወደ እግዚአብሄር /መንፈስ/ መንግስት መግባት አንችልም፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ ዮሃንስ 4፡24

መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር የተወለደው መንፈስ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ከእናትና ከአባቱ ካልተወለደ የምድርን መንግስት ማየት እንደማይችል ሁሉ ሰው ደግሞ መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ካልተወለደ የመንፈስን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡

መጀመሪያ ከእናትና ከአባቱ የተወለደ ሰው ሁለተኛ መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3

ከእናትና ከአባታችን የተወለድነውን የመጀመሪያውን መወለድ የስጋ መወለድ ይለዋል፡፡ ወይም ስጋችን ከስጋ እንደተወለደ ይናገራል፡፡ ከእናታችንና ከአባታችን የተወለደው ስጋችን ነው፡፡ መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር የሚወለደው ደግሞ መንፈሳችን ነው፡፡

ሰው ከእናትና ከአባት ካልተወለደ በስተቀር ወደቤተሰብ መግባት እንደማይችል ሁሉ ሰው መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ካልተወለደ በስተቀር ወደእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ መግባት አይችልም፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ዮሃንስ 1፡12-13

ስለዚህ ነው ከስጋ የተወለደ ስጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር የተወለደው መንፈስ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር የተወለደ መንፈስ እንጂ ሌላ ምንም ነገር ሊሆን አይችልም፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መንፈስ #የእግዚአብሄርልጅ #ስጋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን

አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሄር የሚመራበት ትንሽ የዝምታ ድምፅ

tickling-ears-healthy-heartእግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው እግዚአብሄርን እንዲሰማውና እንዲረዳው አድርጎ በመልኩና በአምሳሉ ነው የፈጠረው፡፡ ሰዎች ሁሌ እንዲረዱት እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ እኛ እግዚአብሄርን ለመስማትና ፈቃዱን ለማወቅ ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር እኛ ፈቃዱን እንድናውቅ ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ደግሞ አንዳንዴ ሳይሆን ሁል ጊዜ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር በስራ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እየተናገረ ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት እግዚአብሄርን እንዲናገረን ማድረግ ሳይሆን እግዚአብሄርን መስማት ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንዴት እንደምንረዳ ማወቅ ነው፡፡

ብዙ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሄርን የማይሰሙት እግዚአብሄር ስላልተናገረ ወይም እግዚአብሄር ፈቃድ ፈቃዱን ሰውሮት ሳይሆን እግዚአብሄር እንዲናገራቸው የሚጠብቁት በጣም አስደናቂና ድራማዊ መንገድ ስለሆነ ነው፡፡

ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሄር የሚናገር የሚመስላቸው በነጎድጉዋድ ድምፅ ከሰማይ በከፍተኛ ድምፅ ነው፡፡ እውነት ነው እግዚአብሄር እንደዚያም ይናገራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እጅግ ለተለየ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር በዚያ መልክ አይናገርም፡፡

ኤልያስ እግዚአብሄርን በነፋስ ፣ በምድር መናወጥ እንዲሁም በእሳት ውስጥ ቢጠብቀውም እግዚአብሄር ግን ሰዎች በሚጠብቁዋቸው በነጎድጉዋድ ውስጥ አልነበረም፡፡

እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። 1ኛ ነገሥት 19፡11-12

መንፈሳችን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያውቃል፡፡ ከእግዚአብሄር ዳግም በተወለደው በመንፈሳችን ውስጥ የእግዚአብሄር ፈቃድ አለ፡፡ የእኛ ሃላፊነት ያንን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመረዳት ጊዜ ወስደም ልባችንን መስማት ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ጊዜ ወስደን የመንፈስን ምስክርነት በልባችን ውስጥ መፈለግና መስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄን ፈቃድ ለመስማት ራሳችንን ስንሰጥ ትንሽዋን የለሆሳስ ድምፅ በልባችን መስማት እንችላለን፡፡

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ሮሜ 8፡14፣16

የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንድናውቅ ተሰጥቶናል፡፡ ይህንን የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናውቀው በመንፈሳችን አማካኝነት ነው፡፡ ኢየሱስን ስንቀበል ከእግዚአብሄር የተወለደው መንፈሳችን የእግዚአብሄን ፈቃድ ያውቃል፡፡ ይህ በስንት ጊዜ አንድ ጊዜ የሚሆ ሳይሆን መንፈሳችን በሰማን ቁጥር የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንሰማበት መንገድ ነው፡፡

በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡11-12

ስለ አንድ ነገር የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ስንፈልግ ልባችንን መስማት ያስፈልገናል፡፡ በልባችን የእግዚአብሄን አዎንታ ወይም አሉታ ምልክት እንፈልጋለን፡፡ በልባችን የእግዚአብሄርን የፈገግታ ወይም የተኮሳተረ ፊት እንፈልጋለን፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ስንፈልግ በልባችን መንፈሳዊውን የማስጠንቀቂያ ቀይ መብራት ወይም የይለፍ አረንጋዴ መብራት ለመለየት ጊዜ መውሰድ ያስፈልገናል፡፡

DUNK360-Featured-Image-kanye.pngየእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ስንፈልግ በልባችን መንፈሳዊውን የማስጠንቀቂያ ቀይ መብራት ወይም የይለፍ አረንጋዴ መብራት ለመለየት ለመለየት ጊዜ መውሰድ ያስፈልገናል፡፡

traffic_light_hearts__eps_vector_sjpg2297.jpg

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማወቅ ስለምንፈልግበት ነገር ስናስብ እና በፀሎት ልባችንን ለመስማት ጊዜ ስንወስድ ልባችን ወይ በሰላም ይሞላል ወይም ልባችን ይረበሻል፡፡ ለእግዚአብሄ ፈቃድ ልባችንን ስናዳምጥ ወይ ልባችን በደስታ ይሞላል ወይም ይኮሰኩሰናል፡፡ ስለዚህ ነው ለልባችን ሰላም ቅድሚያ መስጠትና በልባችን ሰላም ካልተሰማን የእግዚአብሄር ፈቃድ ስላይደለ ማድረግ የሌለብን፡፡ በልባችን ደሰታ ከፈሰሰና ሰላም ከተሰማን ደግሞ የእግዚአብሄር  ፈቃድ መሆኑን አውቀን ማድረግ ያለብን፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ ቆላስይስ 3፡15

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የሰመጠው ጓደኛ ታሪክ

sinking.jpgዎች ማን ኒ የተባሉ ቻይናዊ አገልጋይ The Normal Christian Life በአማርኛ (ክርስትና እንዲህ ነው) ተብሎ በተተረጎመው መፅሃፋቸው ላይ እኛ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንዴት መደገፍ አንዳለብን ሲያስተምሩ ይህንን ታሪክ ፅፈዋል፡፡

በድሮ ዘመን  የምንታጠብበት የተዘጋጀ ቦታ ስላልነበረን ሰውነታችንን የምንታጠበው ወንዝ ወርደን ነበር፡፡ እንደተለመደው አንድ ጊዜ ወንዝ ወርደን እየታጠብን እያለ አንዱ ዋና የማይችል ጓደኛችን ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ዋና ባለመቻሉ ለመዳን ባለው መፍጨርጨር ምክኒያት ብቅ ጥልቅ ይል ጀመር፡፡ አንድ በመካከላችን ዋና የሚችል ጓደኛችን ነበርና ገብተህ አውጣው ብለን መጮኽ ጀመርን ፡፡ ነገር ግን ጥያቄያችን ዋና የሚችለውን ጓደኛችንን ብዙም ሊያንቀሳቅሰው አልቻለም፡፡ በዚህም ምክኒያት ቶሎ ወደ ውሃው በመግባት ሊያወጣው አልሞከረም ነበር፡፡ ጓደኛችን ቆየት ብሎ ግን ውሃ ውስጥ ገብቶ ጓደኛችንን አወጣው፡፡

በጣም ተገርመን ለምንድነው ግን መጀመሪያ ወደውሃ ውስጥ ገብተህ ለመርዳት ያልሞከርከው ለሚለው ጥያቄያችን መልሱ ይህ ነበር፡፡ ልክ ውሃ ውስጥ አንደወደቀ እኔም ወደውሃው ብገባ ኖሮ እሱ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም እንሰጥም ነበር፡፡ ምክኒያቱም እርሱ በሙሉ ሃይሉ ነበር የነበረው፡፡ ለመዳን በሚያደርገው መፍጨርጨር አንገቴ ላይ ተጠምጥሞ ይደፍቀኝና ይገድለኝ ነበር፡፡

ስለዚህ ነው ትንሽ መጠበቅ የፈለግኩት፡፡   ከትንሽ ጊዜ በኋላ በራሱ ሞክሮ ሲያቅተውና እየደከመ ሲመጣ በትንሽ ሃይል ገፍቼ አወጣዋለሁ ብዬ ነው፡፡ እርሱም ጉልበቱን በመፍጨርጨርና በመሞከር ስለቀነሰ እኔንም ሊገድለኝ የማይችለብት ድካም ላይ ነበር የነበረው ብሎ አስረዳን፡፡

እንዲሁም በህይወታችን የሚያስፈልገን ነገር በራሳችን ጉልበት መፍጨርጨር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ላይት ማረፍና መደገፍ ነው፡፡ እኛ በራሳችን ጉልበት ለማድረግ ስንሞክርና ስንፍጨረጨር እግዚአብሄር ያርፋል፡፡ እኛ በእርሱ ላይ ስናርፍ ፣ ለእርሱ እሺ ስንልና ራሳችንን በእርሱ ላይ ስንተው እርሱ በእኛ ይሰራል፡፡

በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ገላትያ 5፡25

በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ሮሜ ሰዎች 8፡1-2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መሰጠት #መገዛት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የህይወት ዛፍ ፍሬ

publication2እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ መልካምና ክፉን እንዲያውቅ አድርጎ አልነበረም የፈጠረው፡፡ ሰው ሲፈጠር እግዚአብሄርን እየሰማ እየታዘዘ እንዲኖር ነው፡ ሰው ሲፈጠር በየዋህነት እግዞአብሄርን እየተከተለ እንዲኖር ነው የተፈጠረው፡፡
ሰው የተፈጠረው በህይወት ዛፍ ፍሬ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው አንድ ምሪት ብቻ በየዋህነት እንዲከተል ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡16-17
ሰው በሃጢያት ሲወድቅ መልካምና ክፉውን በራሱ እየመረጠ እንዲኖር ተገደደ፡፡ ሰው በራሱ ሆነ፡፡ ሰው በግምት ለመኖር ተገደደ፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር አንድ ምሪት በየዋህነት የመመራትን እድሉን ሊያገኘው አልቻለም፡፡
ሰው ክፉና መልካምን በራሱ ለመለየት ስለመረጠ ከእግዚአብሄር ክብር ወደቀ፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ብቻ የመመራት እድሉን አጣው፡፡ ሰው በአንዱ የህይወት ዛፍ ፍሬ የመኖር ነፃነቱን ተነፈገ፡፡ የሰው ህይወቱ ተከፋፈለ፡፡ የሰው ህይወቱ ተሰነጠቀ፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን አላማ ሳተ፡፡
ሰው መልካም ነው ብሎ የሚያስበው ሁሉ መልካም አይደለም፡፡ ሰው ክፉ ነው ብሎ የሚያስበው ሁሉ ደግሞ ክፉ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሰው በራሱ ምርጫ ባሪያ ሆነ፡፡
አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። ኢሳይያስ 55፡8-9
ኢየሱስ የሃጢያታችንን እዳ ከከፈለ በኋላ ግን እግዚአብሄር ወደ ቀድሞ አንዱ ምሪት ሊመልሰን የሚያስፈልገውን የሃጢያት እዳ ሁሉ በልጁ በኢየሱስ በኩል ከፈለ፡፡ አሁንም ኢየሱስን ስንቀበለው በልባችን መኖር ይጀምራል፡፡
የእግዚአብሄር ህይወት በልባችን ሲኖር በአእምሮዋችን “ይህ ክፉ ነው” “ይህ መልካም ነው” በሚል ብቻ በራሳችን ከመኖር እንወጣለን፡፡ በውስጣችን ያለውን የእግዚአብሄርን ህይወትን በየዋህነት ከተከተልን የእግዚአብሄር ወዳዘጋጀልን የክብር ደረጃ እንደርሳለን፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ሮሜ 8፡2
“ይህ ክፉ ነው” “ይህ መልካም ነው” ብለን መምረጥ ሳያስፈልገን በውስጣችን ያለውን መንፈስ በመከተል ብቻ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሙላት በመፈፀም እግዚአብሄርን እናስደስተዋለን፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #የእውቀትዛፍፍሬ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የህይወትፍሬ #መናገር #ቅባት #ትግስት #መሪ

አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ

Holy-Spirit-Best-Relationship.jpg

ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ያስተምራቸው ይመራቸው ነበር ፡፡ ኢየሱስ የመሄጃው ጊዜ ሲደርስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፡፡ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፡፡

ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐንስ 14፡15-16

ኢየሱስ ሲመራቸውና ሲያፅናናቸው ለነበሩት ደቀመዛሙርት እኔ አብን እለምናለሁ ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አፅናኝ ይሰጣችኋል አላቸው፡፡

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ዮሐንስ 14፡15

የተሰጠን መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ በእኛ ላይ የሚያርፍ ሳይሆን በእኛ ውስጥ በመኖር የሚመራንና የሚያፅናናን የሚረዳን የሚመራን የሚደግፈን የሚያስተምረን ጠበቃ የሚቆምልን መንፈስ ነው፡፡

እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።ዮሐንስ 14፡17

ይህን መንፈስ አለም ስለማያየው አይቀበለውም እኛ ግን በውስጣችን ስለሞኖርና ስለሚመራን ስለሚናገረን ስለሚያስተምረን እናውቀዋለን፡፡

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 14፡16

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: