Category Archives: Repentance

ከሞተ ስራ ንስሃ

change-744x330.jpgበመፅሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ካሉት ለሰመረ የክርስትና ህይወት መሰረት ከሆኑት መሰረታዊ ትምህርቶች መካከል ንስሃ አንደኛው ነው፡፡፡

ንስሃ ሃሳብን መለወጥ ሲሆን ሰው በፊት ከሚኖርነት የኑሮ አስተሳሰብ እእምሮው ተለውጦ በአዲስ አስተሳሰብ መኖር ሲጀምር ንስሃ ገባ ይቨባላል፡፡

ንስሃ መግባት ማለት የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶችን ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ንስሃ ከምንሄድበት መንገድ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ መመለስ ነው፡፡ ሃሳባችንን ለውጠን ካልተመለስን በስተቀር የምናደርጋቸው ማንኛውም ሃይማኖታዊ ስርአቶች ሃይማኖተኛ እንደሆንን እንዲደሰማን ያደርጉ ይሆናል እንጂ ለእውነተኛ መንፈሳዊነት አይጠቅሙም፡፡ እግዚአብሄር መመለስን ይባርካል፡፡

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። ሐዋርያት 3፥19-20

በአለማችን ላይ በአስተምሮት ትምህርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ያስነሳቸው የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪው ዴሪክ ፕሪንስ ሲናገሩ በክርስትና ህይወት ላለማደግና ላለመለወጥ ትልቁ ፈተና ንስሃ አለመግባት ነው ይላሉ፡፡ እንዲሁም በቤተክርስትያን ውስጥ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥሩ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች ናቸው ይላሉ፡፡

ሰው በአለም አስተሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሊሰራ ሲሞክር ሁሉ ነገር ይዛባበታል፡፡ የአለም ሃሳቡን ለመተው ያልተዘጋጀ ሰው አብረው በፍፁም የማይሄዱ ሁለት ነገሮችን አብሮ ሊያስኬድ በመሞከር ህይወቱን ያጠፋል፡፡ የማንስሃ ንስሃ ያልገባው ሰው የሚፈልገውን ነገር ቢያገኝ እንኳን የእግዚአብሄርን አብሮነት በህይወቱ ያጣዋል፡፡

ጌታን የተቀበልነው ይህ አስተሳሰቤና ኑሮዬ አያዋጣኝም ብለን ነው፡፡ ነገር ግን ጌታን የተቀበለው ለሃይማኖት ለውጥ ከሆነ ምንም ውጤት ሳናገኝ ህይወችንን አናባክናለን፡፡

ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ኤፌሶን 4፥22-23

አንድ ጊዜ እንደዚህ ሆነ፡፡ አንድ እህት ስለአንድ አገልጋይ እየነገረችኝ ነበር፡፡ ይህ አገልጋይ በጌታ ባይሆን ኖሮ ስንት ሴቶችን ያማርጥ እንደነበረ የነገራትን ስትነግረኝ በጣም ደነገጥኩ፡፡ አልነገርኳትም እንጂ በልቤ ይህ ሰው ንስሃ አልገባም ህይወቱ አደጋ ላይ ነው አልኩ፡፡

ይህ በቤተክርስትያን ውስጥ በጣም ሲያገለግል የነበረው እግዚአብሄር ያስነሳው አገልጋይ ከአመታተ በኋላ ወደኋላ ተመለሰና ያ ሲመካበት የነበረውን ሃጢያት ማድረግ ጀመረ፡፡ ወደ ቤተክርስትያን መጥቶ ነበር እንጂ የሃጢያት ጣእም በአፉ ውስጥ ነበር፡፡ ሃጢያትን አልተፀየፈውም አላፈረበትም ነበር፡፡

እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና። ሮሜ 6፥21

ያለውን ማንኛውም አስተሳሰብ ለእግዚአብሄርን ቃል ለመለወጥ የወሰነ የተሰበረ ሰው በቤተክርስትያን ሲያድግና ሲለወጥ ታያላችሁ፡፡

በአስተሳሰባችን አለምን መስለን እግዚአብሄር ይባረከናል ብሎ መገመት ራስን መታለል ነው፡፡ ስለዚህ ነው በአለም አስተሰሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ስለማይሳካልን መፅሃፍ ቅዱስ አስተሳሰባችሁንና አካሄዳችሁን ለውጡ ንስሃ ግቡ የሚለን፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፥2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ሃሳብ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ንስሃ #መንገድንመቀየር #አስተሳሰብንመቀየር #መለወጥ #በረከት #መታደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አእምሮ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የህይወት ለውጥ ቁልፍ

repent 2.jpgንስሃ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ንስሃ እግዚአብሄርን እና ሰውን የሚያስማማ ብቸኛው ነገር ነው፡፡ ንስሃ ህይወታችንን ይለውጣል፡፡ ህይወታችን የሚለወጠው ንስሃ በገባንበት መጠን ብቻ ነው፡፡

ንስሃ ማለት ደግሞ የአስተሳሰብ ለውጥ ማለት ነው፡፡ ንስሃ ማልቀስ አይደለም ፡፡ ንስሃ መፀፀት አይደለም፡፡ ንስሃ መንገድን መለወጥ ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው ፍፁም አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ ነገር ግን ሰው አትብላ የተባለውን በመብላት በእግዚአብሄር ላይ አመፀ፡፡ ከአመፀኛው አዳም የተወለድን ሁላችን በአመፅ ተወለድን፡፡

እግዚአብሄር ደግሞ ቅዱስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስለ አብዛኛው ሰው ብሎ መንገዱን አይለውጥም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር መለወጥ ያለብን እኛ ነን፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንኖረው በእግዚአብሄር መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚቀበለን የእርሱን መንገድ ከተቀበልን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስለማንም ሰው ቃሉን አይለውጥም፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር የወደቅንበትን የቀድሞ ሃሳብ መተው አለብን፡፡ በወደቅንበት አስተሳሰብ ከእግዚአብሄር ጋር መቀጠል አንችልም፡፡ ከሰይጣም መንግስት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ለመምጣት የአስተሳሰብ ለውጥ (ንስሃ) ያስፈልጋል፡፡ ካለ እውነተኛ  ንስሃና ካለ አስተሳሰብ ለውጥ ከአለም ወደ እግዚአብሄር መንግስት መምጣት  አይቻልም፡፡

የአለም አሰራርና የእግዚአብሄር መንግስት አሰራር በፍቅርና በጥላቻ መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ የአለምና የእግዚአብሄር ቤተሰብ አሰራር በፍቅርና በራስ ወዳድነት መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ በአለም አሰራር በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ  ሊሳካልን አይችልም፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ በአለም መርህ ልንከናወን አንችልም፡፡  ሁለቱ መንግስቶች አምላካቸው ፍላጎታቸው አሰራራቸው እጅግ ተቃራኒዎች ናቸው፡፡

በአለም የኖርንበት መርህ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ስኬታማ አያደርገንም፡፡ ሰዎች በአለም የኖሩበትን አሰራር በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሊኖሩበት ሲሞክሩ ህይወታቸው በከንቱ ይባክናል፡፡ በእግዚአብሄር ምንግስት እንዲሳካልን ከአለምን አሰራር ነፃ መውጣት አለብን፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ያዕቆብ መልእክት 1፡21

ከአለም ስንመጣ ባለን እውቀት አይደለም የምንቀጥለው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት ከአዲስ ነው የምንጀምረው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት በጀመርነው እርምጃ አይደለም የምንቀጥለው በእግዚአብሄር መንግስት ወደሃላ ዞረን ነው የምንመለሰው፡፡

በእግዚአብሄር መንግስት ለመማር የቀድሞ ሃሳባችንን ለመለወጥ ትሁት መሆን አለብን፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት የእግዚአብሄርን ቃል አሰራር ለመማርና ለመለወጥ ካልተዘጋጀን ህይወታችን የትም አይደርስም፡፡ የህይወት ለውጥና ፍሬያማነት የሚገኘው የቀድሞውን አስተሳሰባችንን ጥለን በአዲሱ አሰራር ለመኖር የዋህ ስንሆን ብቻ ነው፡፡

ጌታን እንደተቀበልን ብቻ ሳይሆን በየእለቱ የራሳችንን ሃሳብ ጥለን የእግዚአብሄርን ቃል መርህ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት የሚሳካልን ሃሳባችንን ለመለወጥ በፈቀድን መጠን ብቻ ነው፡፡ ካለ በለዚያ የእስራኤል ህዝብ ወደተስፋይቱ ምድር መግባት አቅቶት የሴይርን ተራራ አርባ አመት እንደዞረ እኛም ካለውጤት እንዲሁ እንባክናለን፡፡

ስለዚህ ነው በእግዚአብሄር ፈቃድ ሃሳባችንንና መንገዳችንን እንድንለውጥና የመጣንበትን አለም አንዳንመስል መፅሃፍ ቅዱስ የሚያዘን፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

ከሃጢያት አለመመለስ እንጂ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሄር ሊያቆራርጠው አይችልም

Repent-TurnAround.jpgሃጢያት በእግዚአብሄር ዘንድ አፀያፊ ነገር ነው፡፡ ሃጢያት ቀልድ አይደለም፡፡ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሄር የለያየ ከባድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ከባድ የሆነ አመፅ እንኳን ሰውን ከእግዚአብሄር እንዲለየው እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡

እግዚአብሄር በሰው ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡ ሰው በሃጢያቱ እንዲሞት እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ የእግዚአብሄር ፍላጎት ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸው ህብረት እንዲታደስ ነው፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ለሰው ካለው ፍቅር የተነሳ ሃጢያት ከሰው ጋር ያለውን ህብረትን አበላሽቶት እንዳይቀር እግዚአብሄር እቅድን አዘጋጅቷል፡፡ ሰው ንስሃ ከገባ ሃሳቡንና መንገዱን ከቀየረ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሄር ሊያቆራርጠው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር ሃጢያት በመስራታችን ሳይሆን በመመለሳችን ደስ ይሰኛል፡፡ በሃጢያታችን ስናዝንና ስንመለስ እግዚአብሄር ይረካል፡፡

በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 1፡9

እግዚአብሄር የኢየሱስ ደም እንዲፈስና ያደረገው በሃጢያት ምክኒያት ነው፡፡ ስለዚህ ነው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሃጢያት ሁሉ የሚያነፃው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው በማንኛውም ሃጢያት ውስጥ ቢገኝና ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ህብረት ቢበላሽ በኢየሱስ ደም በኩል ተመልሶ ወደ ህብረቱ መግባት የሚችለው፡፡

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1ኛ ዮሐንስ 1፡7

ሰው ንስሃ አለመግባቱ ፣ አለመመለሱና በሃጢያት መቀጠሉ እንጂ ሃጢያት መስራቱ ብቻ ሰውን ከእግዚአብሄር ለዘላለም ሊያቆራርጠው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ አለመቀበሉና መጣሉ እንጂ ሃጢያቱ ከእግዚአብሄር ለዘላለም አይለየውም፡፡

ሃጢያት ሰውን ለዘላለም ከእግዚአብሄር የሚለይ ቢሆን ኖሮ ሁላችን ለዘላለም ከእግዚአብሄር በተለየን ነበር፡፡ እኛ ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንዳንለያይ እግዚአብሄር በንስሃና መንገድን በመለወጥ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲታደስ አስቻለን፡፡ አሁንም ማንም የዘላለም ፍርድ ቢያገኘው ከሃጢያቱ ስላልተመለሰ ብቻ ነው፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ንስሃ #መመለስ #ሃጢያት #ይቅርታ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #መናዘዝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: