ከመሪው ነው

እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር ለእርሱና ለእርሱ ብቻ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ ግን የእግዚአብሄርን ሃሳብመና ፈቃዱን እንዴት ልናውቅ እንችላለን የሚለው ጥያቄ እግዚአብሄርን በህይወቱ ደስ ማሰኘት ከሚፈልግ ሰው የሚወጣ ጥያቄ ነው፡፡

እኛ በእግዚአብሄር መመራት ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር እኛን ሊመራን ይፈልጋል፡፡ ግን እንዴት ይመራናል፡፡

እግዚአብሄር እንዴት እንደሚመራን ለማወቅ

  1. እንድንረዳውና እንድንከተለው ስለሚፈልግ እግዚአብሄር እኛን በመልኩና በአምሳሉ እንደፈጠረን ልናውቅ ይገባል፡፡ ዘፍጥረት 1፡27
  1. እግዚአብሄር ፈቃዱን ለመፈፀም ወደ እርሱ የመጡትን ሁሉ በደስታ ይመራል፡፡

እግዚአብሄር የሚናገረው በእኛ ቋንቋ መሆኑን መረዳት አለንብን፡፡ እግዚአብሄር እንደ መስማት ደረጃችን እንደ የአቅማችን የአንድ ቀንን ልጅ የሚናገርበትና የሁለት አመትን ልጅ የሚመራበት የራሱ የተለያየ መንገድ አለው፡፡ የጌታን ምሪት ከልባችን ፈልገን ድምፁን አንስተውም፡፡

መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ዮሐንስ 10፡14-15

  1. እግዚአብሄር በማይታወቅ ቋንቋ ተናግሮ እንድንታዘዘው አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር እንድንረዳ አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡ እርግጥ ነው እግዚአብሄር ያለውን አለማድረግ እንችላለን፡፡ ፈቃዱን ለማድረግ ከልባችን ፈልገን ከእግዚአብሄር የምናጣው ምሪት ግን የለም፡፡

ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል።  ዮሐንስ 7፡1

  1. እግዚአብሄር እኛን የሚያሳስበን ነገር ሁሉ ግድ ይለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከምናስበው በላይ እግዚአብሄር ስለ ጥቃቅንና ዝርዝር ጉዳያችን ግድ ይለዋል ሁሌም ይመራናል፡፡
  1. እግዚአብሄርን የምንሰማው እርሱ መልካም እረኛ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናውቀው ከተመሪው የመስማት ችሎታ ሳይሆን ከመሪው የመናገር ችሎታ የተነሳ ነው፡፡ ከተመሪዎቹ የሚጠበቀው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማግኘት እግዚአብሄርን በፀሎት መፈለግ ነው፡፡

መልካም እረኛ እኔ ነኝ።  በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ ዮሐንስ 10፡11 ፣ 3

  1. የእግዚአብሄርን ምሪት ፈልገን ያልተረዳነው ነገር ካለ እግዚአብሄር አልመራንም ማለት ነው፡፡ በሁኔታው እርምጃ ሳንወስድ እግዚአብሄር እስከሚመራን ፊቱን በመፈለግ መጠበቅ ይገባናል፡፡
  1. የእግዚአብሄርን ምሪት በተረዳን ቁጥር ሁሉ ስንታዘዝ የእግዚአብሄር ምሪት በህይወታችን እየበዛ እንደሚሄድ ማወቅ አለብን፡፡

መልካም እረኛ እኔ ነኝ። . . . እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሐንስ 10፡11 ፣ 10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

በኃይልና በብርታት አይደለም!

The Heart Matters, God is a respecter of hearts

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 11, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 3 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: