Category Archives: 2nd coming

ጌታን ያዘገየው

preach111.jpgእግዚአብሄር ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንዲሰቀልና የሰው ልጆችን የሃጢያት እዳ ሁሉ እንዲከፍል የላከው ሰዎች እንዳይጠፉና ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንዳይለያይ ነው፡፡

መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14

እግዚአብሄር የሰዎችን ጥፋት አይወድም፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ኢየሱስን ከመቀበላችን በፊት ኢየሱስ ተመልሶ ያለመጣው እኛ እንድድን ነው፡፡ ሁሉ ንስሃ እንዲገቡ ወዶ ይታገሳል፡፡

ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9

በአለም ላይ ያለነው ኢየሱስ በዘገየበት ጊዜ የመንግስቱን ወንጌል እንድንሰበክ ነው፡፡ ይህ ወንጌል ከተሰበከ በኋላ የአለም መጨረሻ ይሆናል፡፡

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9

ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። ማቴዎስ 24፡14

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመናገር #ኢየሱስይመጣል #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ኢየሱስ መምጫው እንደቀረበ እስካሁን ያወቅናቸው ወሳኝ ነገሮች

jesus coming.jpgኢየሱስ በቶሎ ተመልሶ እንደሚመጣ

እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእይ 22፡12

ኢየሱስ ተመልሶ የመጣው በድካም እንዳይደለ ፣ ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣው ስለሰው ልጆች ሊሞት እንዳይደለ ፣ ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣው በመስቀል ላይ ስለሰራልንን ስራ ምን እንዳደረግንና እንዴት እንደተቀበለንው ለማየት እና ለመፍረድ እንደሆነ

ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። ራእይ 1፡18

ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣው ሰዎች የእለት ተእለት ኑሮዋቸውን እየኖሩ ባለተጠበቀ ጊዜ እንደሆነ

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡37-39

ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣው ሊከፍለን እንደሆነ

እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእይ 22፡12

ኢየሰስ ተመልሶ የሚመጣው እንደሌባ በድንገት እንደሆነ

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡1-2

ኢየሱስ እስካሁን ተመልሶ ያልመጣው ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ እንደሆነ

ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9

ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣው ሁሉም ሰዎች በሚያዪት ሁኔታ አንደሆነ

እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። ራእይ 1፡7

ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። ሐዋርያት 1፡11

ኢየሱስ ተመልሶ መምጣቱ ለማያምኑት እጀግ አስፈሪ እንደሆነ

በዚያን ጊዜ ተራራዎችን፦ በላያችን ውደቁ፥ ኮረብቶችንም፦ ሰውሩን ይሉ ዘንድ ይጀምራሉ፤ ሉቃስ 23፡30

ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣባትን ቀን ማንም እንደማያውቅ

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። ማቴዎስ 24፡36

ኢየሱስ ተመልሶ ስለመምጣቱ ማድረግ የምንችለው ብቸኛ ነገር በየእለቱ መዘጋጀት እንደሆነ

ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፡11-14

ኢየሱስ ተመልሶ ያልመጣው ወንጌልን እንድንሰብክ እንደሆነ

ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡9

ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። ማቴዎስ 24፡14

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ኢየሱስይመጣል #እንደሌባ #በድንገት #ዋጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: