Category Archives: Character

የእብዷ ተዋናይ ታሪክ

conscious.jpg

የእብዷ ተዋናይ ታሪክ

ግብዝነት ራስን አለመሆን ነው፡፡ ግብዝነት ያልሆኑትን መምሰል ነው፡፡ ግብዝነት ሌላውን ሰው ለመምሰል መሞከር ነው፡፡ ግብዝነት ራስን ያለመሆን አደገኛ እና አክሳሪ አካሄድ ነው፡፡

የሆኑትን መሆን እንጂ ማስመሰል ከባድ ነው፡፡ ተፈጥሮን መሆን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ተፈጥሮን መሆን ይቀላል፡፡ ያልሆኑትምን መሆን ግን ይከብዳል፡፡ የሆኑትን መሆን የመሰለ ነፃነት የለም፡፡

አንድ እብድ ድራማ የምትሰራ ሴት በቴሌቪዠን ቃለመጠይቅ ሲደረግላት ሰምቻለሁ፡፡ ድራማውን ስትሰራ እንደ እብድ ነው የምታስበው እንደ እንድ ነው የምትናገረው አኳኋኗ ሁሉ እንደ እብድ ነው፡፡ ታዲያ እንደእብድ ከምትሰራበትን ድራማ ስትጨርስ ወደ ጤነኝነት ሃሳብ ንግግርና አካሄድ ለመመለስ 2 ሰአት እንደ ሚፈጅባት በቃል መጠይቁ ላይ ስትናገር ሰምቻሉ፡፡

ይህች ሴት እንደ ጤነኛ ለመሆን ምንም ጥረት አይጠይቃትም፡፡ ጤነኛ ስለሆነች በቀላሉ እንደጤነኛ ታስባለች እንደጤነኛ ትናገራለች እንደጤነኛ ታደርጋለች፡፡ በቀላሉ ጤነኝነቱን ትኖረዋለች፡፡ ጤነኝነት ለእርስዋ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ጤነኝነት ለእርስዋ መኪናን እንደመንዳት ነው፡፡ እብደት ግን ለእርስዋ መኪናን እንደመግፋት ነው፡፡ እብደት ለእርስዋ ከተፈጥሮዋ ውጭ ስለሆነና በጤነኛ ሰው ስለሚሰራ ከባድ ነው፡፡

ጤነኛ ሳይሆኑ እንደጤነኛ መስራት ከባድ ነው፡፡ እብድ ሳይሆኑ እንደ እብድ ድራማ መስራት ከባድ ነገር ነው፡፡ ያልሆኑትን መሆን እጅግ ከባድ ነው፡፡

እንዲሁ ማስመሰልና ግብዝነት ከባድ ነገር ነው፡፡ ግብዝነት ህይወትን ያሳሰባል፡፡ ግብዝነት ጉልበትን በከንቱ ያባክናል፡፡

ግብዝነት የሆኑትን ካለመቀበል ይመጣል፡፡ ሰው ራሱን ካልተቀበለ እጅግ በጣም ችግር ነው፡፡ ሰው በራሱ ካልተማመነ ከባድ ነው፡፡ ሰው ባለከው ደረጃ ካልረካ ችግር ነው፡፡ ሰው ባለው ነገር ካፈረ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ሰው በደረሰበት ደረጃ ካልረካ ትልቅ ችግር ነው፡፡

ሰው ራሱን ካላደነቀ ሰው ራሱን ካልሆነ የችግሮች ሁሉ መንስኤ ይሆናል፡፡ ሰው ለራሱ አክብሮት ከሌለው እና ሌላውን መምስል ከፈለገ ውድቀት ነው፡፡

ሰው ለውስጥ ህይወቱ ቅድሚያ ካልሰጠና ለውጭ ህይወቱ እጅግ ከተጨነቀ ችግር ነው፡፡ ሰው ለችግሩ ምንጭ መፍትሄ ካልሰጠ ለሚታየው የችግሩ ውጤት ከተጨነቀ መፍትሄ ያለው ህይወት መኖር ያቅተዋል፡፡

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። የማቴዎስ ወንጌል 23፡25-27

ግብዝነት እግዚአብሄር የሚያየው ልብን ሳይሆን ፊትን ነው ብሎ መሳሳት ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፡7

ግብዝነት ከሰው የሚገኘውን ክብር እንጂ ከእግዚአብሄር የሚገኘውን ክብር አለመፈለግ ነው፡፡

ከሰው ክብርን አልቀበልም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በራሳችሁ እንደ ሌላችሁ አውቃችኋለሁ። እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የዮሐንስ ወንጌል 5፡4141-42፣44

ግብዝነት ውስጥን ላለማጥራት መስነፍ ነው፡፡ ግብዝነት ውስጥን በትጋት ያለማጥራት ስንፍናና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ራስን አለመስጠት ነው፡፡ ግብዝነት ራሰን ለማንፃት ከመትጋት ይልቅ በውጭው በመጣፍና በመሸፋፈን ሰውን ለመሸወድ መሞከር ነው፡፡

ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል፡፡ እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል። የሉቃስ ወንጌል 11፡39-41

ግብዝነት ለውስጥ ውበት ሳይሆን ለውጭ ውበት ይበልጥ ዋጋ መስጠት ነው፡፡ ግብዝነት ዋጋ ያለውን ነገር አለማወቅ ዋጋው ላነሰ ርካሽ ነገር ቅድሚያ መስጠት ነው፡፡

ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡3-4

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ ##ግብዝ #ውጭውን #ውስጡን #ልብ #ውበት #ዋጋ #ፊት #ባህሪ #ፍቅር #ልብ #ሃዘን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Advertisements

ባህሪ ይጠይቃል

come out of the cross2.jpgችሎታህ ወደ ላይ ላይ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ነገር ግን እዚያ ለመቆየት ባህሪ ይጠይቃል፡፡

ተሰጥኦው በርን ከፍቶ ያስገባሃል፡፡ ነገር ግን ባህሪ በክፍሉ ውስጥ ያቆይሃል፡፡

ስጦታህ ባህሪህ አንተን መጠበቅ የማይችልበት ቦታ ቢወስድህ ዋጋ የለውም፡፡

በህይወት ለመሳካት ስጦታ ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡

በህይወት ለመከናወን የተከፈተ እድል ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡

በህይወት ለመሳካት ተሰጥኦ ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡

በህይወት ለመከናወን ስጦታ የራሱ ድርሻ አለው ባህሪም የራሱ ድርሻ አለው፡፡

በህይወት ለመከናወን ስጦታ የሚሰራውን ባህሪ አይሰራውም ባህሪ የሚሰራውን ስጦታ አይሰራውም፡፡

በህይወት ለመከናወን ስጦታ ብቻ በቂ አይደለም፡፡

በህይወት ያነሰ ስጦታ ያላቸው ሰዎች ይበልጥ ሲከናወንላቸው ይታያል፡፡ በህይወት የበለጠ ክህሎት ያላቸው ሰዎች በባህሪ ማነስ ምክኒያት እንደሚገባው ሳይከናወልናቸው ይታያል፡፡

ስጦታን እኛ አንወስነውም፡፡ ተሰጥኦ ከእግዚአብሄር በስጦታ የሚሰጥ እንጂ ስጦታው እንዲሰጥ የሚደረግ ምንም አስተዋፅኦ የለም፡፡

ስጦታ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ስጦታ የሌለው ሰው የለም፡፡

ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ማቴዎስ 25፡15

ስጦታ አለን ማለት በህይወት ይከናወንልናል ማለት ግን አይደለም፡፡ በህይወት እንዲከናወንልን ስጦታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ እንዲሳካልን ከስጦታ ጋር ባህሪ ያስፈልገናል፡፡ እንዲያውም ስጦታውን የሚይዝ ባህሪ ከሌለን ስጦታው ከንቱ ነው፡፡ ስጦታውን ለመያዝ ባህሪን በትጋት ካላዳበርን ስጦታው ለማንም አይጠቅምም፡፡

ስጦታም ክህሎትም ተሰጥኦም የሚሰጠው ለሰው ጥቅም ነው፡፡ ከሰው ጋር እንዴት እንደምንኖር ካላወቅንና ባህሪው ከሌለን ስጦታው ለምንም አይጠቅመንም፡፡ ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ የትግስት ባህሪ ከሌለን ስጦታው ከንቱ ነው፡፡ የመከራን ጊዜ እንዴት እንድምናሳልፍ ትህትናን ካላዳበርን ምንም አይጠቅመንም፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። ምሳሌ 24፡10

ባህሪ የሌለው ስጦታ ማለት ዘይትን ቀዳዳ እቃ ውሰጥ እንደማስቀመጥ ያህል ብክነት ነው፡፡ ባህሪ ስጦታውን በሚገባ እንድንጠቀምበት ያስችለናል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ስጋ #ምኞት #ማሰብ #ህይወት #ሞት #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

ስልጣን ወይስ ባህሪ?

power or charcter.jpgእግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በባህሪው እንዲኖር ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረው ሰው የእግዚአብሄር ባህሪዎች ሁሉ ነበሩት፡፡

እግዚአብሄር የፈጠረው እግዚአብሄር አታድርግ የተባለውን ያንኑ ነገር በማድረጉ የተነሳ ከእግዚአብሄር ክብር ወደቀ፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ከመታዘዘ ይልቅ ተጨማሪ ሃይል ሲፈልግ የእግዚአብሄርን ባህሪ አጣው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ እነዚያን የእግዚአብሄር ባህሪያት እንዲሁም የፈለገውን ሃይል አጣው፡፡ ሰው እንደ እግዚአብሄር ለመሆን ባለው ጥማት የእግዚአብሄርን ባህሪ አጣው፡፡

ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ዘፍጥረት 3፡5

አሁንም የሰው ስጋዊ ባህሪ መልካሙን የእግዚአብሄርን ባህሪ አይፈልግም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሃይልን ነው፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ጊዜን መቆጣጠር እንጂ ትእግስትን አይደለም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሰውን መቆጣጠር እንጂ ለሌላው መገዛትን አይደለም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሁኔታን መቆጣጠር እንጂ ራስን መስጠት አይደለም፡፡

የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሃይሉን በትክክል የሚያስተዳድርበትን የእግዚአብሄርን ባህሪ ሳይሆን ሃይሉን ብቻ ነው፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ ለሃይል ይጓጓል፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ አንደኛ መሆንን እንጂ ማገልገልን አይፈልግም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ መጠቀምን እንጂ መጥቀምን አያስበውም፡፡ ስጋ ለሃይል እንጂ ለባህሪ ግድ የለውም፡፡

የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው፦ መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። እርሱም፦ ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት። ማርቆስ 10፡35-37

ስጋ በነገሮች መያዝ አይፈልግም፡፡ ስጋ መታገስ አይፈልግም፡፣ስጋ መጠበቅ አይፈልግም፡፡ ስጋ ሌላወን መውደድ አይፈልም፡፡ ስጋ ሌላውን መሸከም አይፈልግም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን ሁሉ መለወጥን እንጂ መታገስን አይደለም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን መተው እንጂ መውደድ አይደለም፡፡

ስጋ መናገርን እንጂ መስማትን አይፈልግም፡፡ ስጋ በንግግር ሁሉንም መቆጣጠርን እንጂ መስማትን አይፈልግም፡፡

ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። ያዕቆብ 3፡2

ስጋ የሚፈልገው ነገሮችን መቆጣጠር እንጂ ራሱን መስጠት አይደለም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን ሰው እንደርሱ ማድረግን እንጂ ሌላውን ሰው መምሰልን አይደለም፡፡ ስጋ ሌላውን ሁሉ ዝቅ አድርጎ መግዛት እንጂ ማንሳት ማስታጠቅ መልቀቅ አይፈልግም፡፡

ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። ማቴዎስ 10፡39

ስጋ ተጨማሪ ሃይልን እንጂ የባህሪ ለውጥን አይፈልግም፡፡ ስጋ ተጨማሪ ስልጣንን እንጂ መገዛትን አይፈልግም፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡1-3

ስለዚህ ነው ሃዋሪያው ጳውሎስ ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ የሚለው፡፡

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ስጋ #ምኞት #ማሰብ #ህይወት #ሞት #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

አስተዳዳሪው ከሚተዳደረው ይበልጣል

administrator.jpgእግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ለመባረክ ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን በሚባርከው በረከት ሰው ተጠቃሚ እንዲሆን እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡  ሰውን የሚባርከው በረከት እንዲባክን እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን በረከት በትክክል እንዲያስተዳድረው እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

ሰው የተሰጠውን በረከት በትክክል ካላስተዳደረ ያባክነዋል፡፡ ሰው የተሰጠውን በረከት የሚይዝበት ትክክለኛ አያያዝ ከሌለው በረከቱ ይባክናል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን ከመባረኩ በፊት የበረከቱን አስተዳዳሪውን ሰውን መስራቱን የሚያስቀድመው በዚህ ምክኒያት ነው፡፡ እግዚአብሄር ስለበረከቱ ሳይሆን ስለአስተዳሪው መሰራት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውና የሚያስቀድመው አስተዳዳሪው ሰው ከተሰራ በረከቱን በትክክል ማስተዳደር እንደሚችል እግዚአብሄር ስለሚያውቅ ነው፡፡ አስተዳደሪው በሚገባ ከተሰራ በረከቱን ለታሰበው አላማ ሊያውለው ይችላል፡፡

ስለዚህ ነው ሰውን ከመባረኩ በፊት እግዚአብሄር የሰውን ታማኝነት የሚመዝነው፡፡ አስተዳደሪው ታማኝ ከሆነ በረከቱ ለታለመለት አላማ ይውላል፡፡ አስተዳደሪው ታማኝ እስካልሆነ ደርስ ግን ሰው ምንም ቢባረክ በሚያፈስ እቃ ውስጥ እንደተቀመጠ ፈሳሽ በረከቱ ይባክናል፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20

አስተዳዳሪው ሳይሰራ በፊት የተገኘ በረከት ግን ከእግዚአብሄርም ሊሆን አይችልም እንዲሁም ደግሞ ንፁህ ሊሆን አይችልም፡፡ አስተዳዳሪው ቀስ በቀስ ሳይሰራ በፊት የተገኘ በረከት መሰረት እንደሌለው ቤት ነው፡፡ አስተዳደሪው ሰው በባህሪ ሳይሰራ አስቀድሞ የተገኘ ርስት ፍፃሜው ለመልካም አይሆንም፡፡

በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም። ምሳሌ 20፡21

ስለዚህ ነው ሰው ሃብቱን በትክክል ከማስተዳደሩ በፊት በባህሪ ማደግና ሃብቱን ለማስተዳደር የሚያስችለውን ብስለት ማግኘት እንዳለበት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ገላትያ 4፡1-2

ርስትን ለመቀበል ሰከንድ አይፈጅም፡፡ ነገር ግን ርስትን በትክክል ለማስተዳደር የሚያበቃ ብስለትን ለማግኘት ዘመናት ይጠይቃል፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህሪ #ፍቅር #ልብ #አስተዳደሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል

patience11.jpgትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16፡32

በምድር ላይ ሃያል የሆኑ ግን ለምድር በረከት ያልሆኑ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በምድር ላይ ባለጠጋ የሆኑ ነገር ግን ለምድር ስጋት የሆኑ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በምድር ላይ ጥበበኛ የሆኑ ነገር ግን የምድር አደጋ የሆኑ በጣም ብዙ ሰዎች ይገኛሉ፡፡

ሰው ሃይሉን ለክፋትም ይሁን ለበጎነት ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ሃይላችንን ለምን እንደምንጠቀምበት እስካልታወቀ ድረስ ሃይል አለን ማለት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሃይል በማን እጅ እንዳለ ካልታወቀ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ሃይልን ብቻ አይተህ ከተመኘኸው ሃይል ያለውን የጥፋት አቅም አልተረዳህም ማለት ነው፡፡

ሰው ባለጠጋ ነው ማለት ባለግነቱን ለክፋት እንደማይጠቀምበት ካልተረጋገጠ በስተቀር ባለጠግነቱን ብቻ የሚመኙት ነገር አይደለም፡፡ ሰው ባለጠግነቱን ለመልካም ነገር ብቻ ሳይሆን ሰውን ለመግደል ለማጎሳቆል ለመበዝበዝ ለማስለቀስ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

ሰው ጥቢብ ነው ማለት ጥበቡን ለክፋት አይጠቀምበትም ማለት አይደለም፡፡ ጥበብ አደጋ ሊሆን ይችላል፡፡ ጥበብ በረከት ሊሆን ይችላል፡፡ ጥበብ እንደሚይዘው ሰው ስጋት ሊሆን ይችላል፡፡

ሃያልነት ባለጠግነትና ጥበብ ከውጭ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ሃያልነት ባለጠግነትና ጥበብ የሚያስመኩ የእድገት መለኪያዎች አይደሉም፡፡ ሃያልነት ባለጠግነትና ጥበብ የሰውን ማደግ መለወጥና መልካምነት አያሳዩም፡፡

ለሰው ሃያልነትን የሚሰጠው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰውን ከባለጠግነት ጋር የሚያገናኘው የእግዚአብሄር አሰራር ነው፡፡ ለሰው የጥበብን አእምሮ የሚሰጠው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሃያልነት ባለጠግነትና ጥበብ ሃያሉን ባለጠጋውንና ጠቢቡን የሚያስመካው ምንም ነገር የለም፡፡

በመርህ መኖር ግን የሰውን የባህሪ እድገት ይጠይቃል፡፡ ትእግስት ግን የሰውን መለወጥ ይጠይቃል፡፡ ትእግስት ግን የተሻለ መረዳትን ይጠይቃል፡፡ ትእግስት ግን ራስን መግዛትን ይጠይቃል፡፡

ሰው ሃያልነቱ የሚለካው ራሱን ሲገዛ ብቻ ነው፡፡ ሰው ሃያልነቱ የሚለካው ማድረግ የሚፈልገውን ሲያደርግ ፣ ማድረግ የማይፈለገውን ሳያደርግ ነው፡፡ የሰው ሃያልነት የሚለካው ሰው በራሱ ላይ ሙሉ ስልጣን ሲኖረው ነው፡፡ የሰው ሃያልነቱ የሚለካው ራሱን ሲመራ ብቻ ነው፡፡

ሰው ባለጠግነቱ የሚለካው በውስጡ ባለጠጋ ሲሆን ነው፡፡ ሰው ባለጠግነቱ የሚለካው በሰላም ፣ በደስታ ፣ በእረፍትና በእርካታ ባለጠጋ ሲሆን ነው፡፡ ሰው ባለጠግነቱ የሚለካው በነፍሱ ባለጠጋ ሲሆን ነው፡፡

ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። 3ኛ ዮሐንስ 1፡2

ሰው ባለጠግነቱ የሚለካው በይቅርታና እና በምህረት ባለጠጋ ሲሆን ነው፡፡ የሰው ባለጠግነት የሚለካው ለራሱ ነገሮችን በራስ ወዳድነት በማግበስበስ ሳይሆን በመልካም ስራ ባለጠጋ ሲሆን ነው፡፡

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ  ጢሞቴዎስ 6፡18-19

ሰው ጠቢብነቱ የሚታወቀው እግዚአብሄርን በመፍራት ከእግዚአብሄርና ከሰው ጋር በትግስትና በትህትና ሲኖር ነው፡፡ ሰው ጠቢብነቱ የሚታወቀው በመጀመሪያ ከፈጠረው ጋር እንዴት በትህትና እንደሚኖር ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው ጠቢብነቱ የሚታወቀው በህይወቱ እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ለፈጠረው ለሰራው ለእግዚአብሄር እውቅና መስጠቱ ነው፡፡ ሰው ጠቢብነቱ የሚለካው ለእግዚአብሄር የመጀመሪያውን ስፍራ ሲሰጥ ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ምሳሌ 1፡7

ስለዚህ ነው ትእግስተኛ ሰው ከሃያል ስው ይሻላል የሚባለው፡፡

ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16፡32

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህሪ #ፍቅር #ልብ #የዋህ #ዝግተኛ #የመንፈስፍሬ #ውበት #የልብሰው #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል

form of godliness.jpgነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡1-5

የአምልኮ መልክ ኖሮዋቸው የእግዚአብሄርን ሃይል የካዱ ሰዎች በጣም የሚያሳዝኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ሃይሉን የካዱ ሰዎች በእግዚአብሄር ሃይል ስለማይታመኑ የራሳቸውን መንገድ ይሄዳሉ፡፡ በሃይሉ ስለማይታሙና የእግዚአብሄር ሃይሉ ይህን ያደርግልኛል ብለው ተስፋ ስለማያደጉ ማስመሰዩውን መንገድ ይሄዳሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ሃትል ስለካዱ የስጋን ሃይል ይጠቀማሉ፡፡ በፍቀር ስለማያምኑ ፍቅር የሌላቸው ሆነው ይመላለሳሉ፡፡ በእግዚአብሄር ሃየለ ስለማያምኑ በራሳቸው ቅልጥፍና ይታመናሉ፡፡ ራሰብን በመካድ ስለማያምኑ በ ስግብግብነት ይመላለሳሉ፡፡ በእግዚአብሄር ስለማያምኑ በረሳቸው ብልጠይት ይደገፋሉ፡፡

ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ

ሰዎች እግዚአብሄር እንደሚወዳቸው እርግጠኛ ስላይደሉ ደስተኞች አይደሉም፡፡ እግዚአብሄር እንደሚወደው የሚያውቅ ሰው ያርፋል ራስ ወዳድ አይሆንም፡፡ ሰዎች ራሳቸው ላይ ያተኩራሉ፡፡ ሌላውን መድረስ ፣ ሌላውን መጥቀም ፣ ማካፈል ፣ ለሌላው መኖር ፣ ሌላውን ማንሳት የሚባሉ ነገሮች ከራስ ወዳድንት ከፍ ያለ የከበረ ደረጃ እንደሆነ አያውቁም፡፡

ገንዘብን የሚወዱ፥

ሰዎች ገንዘብን በመውደዳቸው ጌታን ይንቃሉ፡፡ ሰዎች ገንዘብን በመውደዳቸው ሰውን አይወዱም፡፡ ሰዎች ገንዘብን በመውደዳቸው ይሰርቃሉ ፣ ይዋሻሉ ፣ ያጭበረብራሉ ፣ ይክዳሉ ፣ ሰዎችን ይጠላሉ፡፡ ገንዘብን መውደድ የክፋይ ሁሉ ስር እንደመሆኑ ገንዘብን የሚወድ ሰው እግዚአብሄርንም ሰውንም ስለማይወድ ምንም ክፋት ሊያደርግ ይችላል፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡10

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ማቴዎስ 6፡24

ትምክህተኞች፥

በገንዘብና በተለያዩ ጉሳቁሶች ይመካሉ፡፡ በራሳቸው ችሎታ ይመካሉ፡፡ ባላቸው ዝምድና በሚያውቁት ሰው በአራድነታቸው ይመካሉ፡፡

ትዕቢተኞች፥

ሰውን ሁሉ ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ፡፡ ባልጀራዬ ከእኔ ይሻላል አይሉም፡፡ ሰውን የሚፈልጉት ለጥቅማቸው ብቻ ነው፡፡ ካልጠቀማቸው ለሌላ ለምንም ነገር አይፈልጉትም፡፡ ከሁሉም የሚሻሉበትን መንገድ ባገኙት አጋጣሚ ያሳያሉ፡፡ ሁሉም እነርሱን ለመጥቀም የተሰራ እንጂ ልናገለግለው የሚገባ እንደሆነ አያውቁም፡፡

ተሳዳቢዎች፥

በታላቅ ቃል ይሳደባሉ፡፡ ሲሳደቡ ለነገ አይሉም፡፡ ለመሳደብ አይፈሩም፡፡ ሲናገሩ ደፋሮች ናቸው፡፡ በድፍረት ንግግር ሁሉንም ለመብለጥ የሚፈልጉ ይመስላሉ፡፡ በፊታቸው የተከበረ የማይሰደብ ሰው የለም፡፡ በግል ጥቅማቸው ፊት የቆመን ማንም ሰው ለማዋረድ ወደኋላ አይሉም፡፡ በግል ጥቅማቸው ፊት የቆመን ሰው ለማዋረድ ያለችውን ተሰሚነት ሁሉ ለክፋት ይጠቀሙበታል፡፡

ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥

ስልጣንን አያከብሩም፡፡ የሚሰሙት ምንም ስልጣን የለም፡፡ ለእነርሱ ሁሉም ሰው አልገባውም፡፡ እነርሱ ራሳቸውን ከፍ አድርገው ከመስቀላቸው አንፃር ማንም ሊሰሙት የተገባ አይደለም፡፡ ለማንም አይታዘዙም፡፡ ማንንም አይሰሙም፡፡ ለሁለም ሰው የሚያወጡት አቃቂር አለ፡፡ ሁሉም ሰው እነርሱም የሚሰማ እንጂ እነርሱ የሚሰሙት አንድም ሰው የለም፡፡

 

ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ። እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል። ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት። የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች። ማቴዎስ 11፡16-19

የማያመሰግኑ፥

ራሳቸውን ከመስቀላቸ አንፃር ይህ የሚኖሩበት ኑሮ የሚገባቸው እንደሆነ አያስቡም፡፡ ለአነርሱ የቱም ደረጃ አይመጥናቸውም፡፡ በየትኛውም ህይወት አይረኩም፡፡ በየትኛውም የህይወት ደረጃ ራሳቸውን ለማማጠን አይፈልጉም፡፡ ምንም ከፍ ያለ ደረጃ ለእነርሱ አይበቃል፡፡ እጅግ የተከበሩ ስለሆኑ ለክብራቸው የሚበቃ የህይወት ደረጃ የለም፡፡ ስለዚህ አያመሰግኑም፡፡ የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያደርጉት ከምስጋና ልብና በደስታ አይደለም፡፡

ቅድስና የሌላቸው፥

ህይወታቸው በመርህ አይመራም፡፡ ደስ ካላቸው የፈለጉትን ያደርጋሉ፡፡ ለእግዚአብሄር ነገሮችን መተው ፣ ከአለም እርኩሰት መለየት ፣ ራስን መካድ የሚሉት ቃላቶች በህይወታቸው የሉም፡፡ በቃሉ ሳይሆን በሁኔታው ነው የሚመሩት፡፡ የተሻለ ጥቅም ካስገኘላቸው ይዋሻሉ፡፡

ፍቅር የሌላቸው፥

እግዚአብሄርን አያውቁም፡፡ እግዚአብሄርን አይወዱም ሰውን አይወዱም፡፡ ፍቅር የላቸውም፡፡ ሌላውም መጥቀም ፣ ለሌላው ማካፈል ፣ አብሮ ማደግ የሚባሉት ሃሳቦች ለእነርሱ እንግዳና የሞኝነት ሃሳቦች ናቸው፡፡

ዕርቅን የማይሰሙ፥

የራሳቸውን ሃሳብ እንጂ የማንንም ሃሳብ ለመስማት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡እነርሱ ሃሳብ ብቻ ትክክል የሌላው ሃሳብ ሁሉ ስህተት ነው፡፡ ለሌላው ብለው ምንም ነገር ለመተው ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ እውቅና የሚሰጡት ለራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ብቻ ነው፡፡ የሚያርፉት የራሳቸውን ሃሳብ ሲያስፈፅሙ ብቻ ነው፡፡ ለጥቅማቸው እንጂ ለሰላም ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡

ሐሜተኞች፥

የሰውን ገመና ለመሸፈን የሚያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ማንንም ሰው እንደ ቤተሰብ አያዩም፡፡ ማንም ሰው በፊታቸው የከበረ አይደለም፡፡ ሰውን በሌላ ሰው ፊት ዝቅ ዝቅ ለማድረግ አይፈሩም፡፡ የአንዱን ገመና በሌላው ሰው ፊት ለመግለጥ አይፈሩም፡፡ የሌላውን ስም ለማጥፋት ጨካኞች ናቸው፡፡ ሌላውን ለማዋረድና ስሙን ለማጥፋት ፈጥረውም በውሸት ያወራሉ፡፡ ሌላውን ሰውን ማጣጣል እነርሱን ከፍ የሚያደርጋቸው ይመስላቸዋል፡፡

ራሳቸውን የማይገዙ፥

የፈሉትን ነገር በፈለጉት ጊዜ እንዲያገኙ ይፈልጋሉ፡፡ ትእግስት ፣ መጠበቅ ፣ መተው የሚሉትን መርሆች አያውቋቸውም፡፡ ከስጋቸው የሚሰሙት ድምፅ ሁሉ ትክክል ነው፡፡ ራስን መግዛት ፣ ስጋ መጎሸም ፣ ስጋን መከልከል የሚሉት ሃሳቦት በፍፁም አይገባቸውም፡፡

ጨካኞች፥

ምህረትና ርህራሄ የላቸውም፡፡ ለጥቅም ሲባል ምንም ነገር ለማድረግ ወደኋላ አይሉም፡፡ በጥቅም ላይ እነጂ በማንም ላይ ይጨክናሉ፡፡ ለእነርሱ ትክክል ጥቅም ማግኘት ነው፡፡ ጥቅም የሚያስገኝላቸው ማንኛውም ነገር በምንም ይምጣ በምንም ትክክል ነው፡፡

መልካም የሆነውን የማይወዱ፥

ትክክለኛው ህይወት  ከእነርሱ ስለሚለይ ይጠሉታል፡፡ ቀስ ብላ የምትከማቸውን ሃብት ያላዋቂ ያደርጉታል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ሲያዩ ያልገባው እውቀት ያነሰው ይመስላቸዋል፡፡ እንደ እነርሱ የማይሄድ ማንም ሰውን ይጠላሉ፡፡ መልካመ የሆነው ህይወት የእነርሱን ህይወት ስለሚያጋልጥ አይወዱትም፡፡

ከዳተኞች፥

በቃላቸው አይታመኑም፡፡ ለመካድ ቅርብ ናቸው፡፡ ታማኝነት ስለሌላቸው ከተመቻቸው ቅጥፍ አድርገው ይክዳሉ፡፡ የተሻለ ነገር ሲያገኙ ወዲያው ተገልብጠው ይገኛሉ፡፡ ቀድመው የገቡትን ቃል በቀላሉ ያፈርሳሉ፡፡ ስለቃሌ ልታገስ የሚል ነገር የላቸውም፡፡

ችኩሎች፥

ሁሉ ነገር በፍጥነት እንዲሆንላቸው ነው የሚፈልጉት፡፡ ነገር በፍጥነት ካልሆነላቸው ይሆናል ብለው አያምኑም፡፡ መጠበቅን ይፈሩታል፡፡ መታገስ አለማወቅ አለመረዳት ደካምነት ነው የሚመስላቸው፡፡

በትዕቢት የተነፉ፥

ማንም ሊያስተምራቸውና ሊመክራቸው አይችልም፡፡ ሁሉንም ያውቃሉ፡፡ አውቀውት ጨርሰዋል፡፡ ሌላው ሁሉ ሰው እንጂ እነርሱ መማር መለወጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ለመማር ለመለወጥ ዝግ ናቸው፡፡ በማንም ስልጣን ስር መግባት አይፈልሀጉም፡፡ ማንም እንዲያዛቸው አይፈልጉም፡፡ ማንንም መስማት አይፈልጉም፡፡

ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ

ደስታ መዝናናት የህይወታቸው ከፍተኛው አላማ ነው፡፡ የሚያስደስታቸውን ምንም ነገር ይቀበሉታል፡፡ የማያስደስታቸውን ምንም ነገር አይቀበሉትም፡፡ ህይወታቸውን በመሰረታዊ ፍላጎት ላይ ሳይሆን በቅንጦት ላይ ያባክኑታል፡፡ በህይወታቸው የሚመራቸው ደስታ ተድላ እንጂ ጌታ አይደለም፡፡

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል

የክርስትና ቋንቋው ሁሉ አላቸው፡፡ ንግግሩ ቃላቶቹ ሁሉ አላቸው፡፡ መልኩ ሁሉ አላቸው፡፡ ለውጭው መልካቸው በጣም ይጠነቀቃሉ፡፡ ሁሉንም ነገር ከላይ ከላይ ትክክል ለማድረግ እጅግ ይጠነቀቃሉ፡፡ የውጭውን ነገር ሁሉ በደንብ ይይዙታል ለልባቸው ግን ግድ የላቸውም፡፡ ዋናው የውጭው ይመስላቸዋል፡፡ ከሰው የሚመጣውን ክብር እንጂ ከእግዚአብሄር የሚመጣውን ክብር አይፈልጉም፡፡ ልባቸው ግን ክፋትና ቅሚያ ሞልቶባቸዋል፡፡

ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። ዮሃንስ 12፡43

ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡1-5

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ገንዘብን የሚወዱ #ትምክህተኞች #ትዕቢተኞች #ተሳዳቢዎች #ለወላጆቻቸውየማይታዘዙ #የማያመሰግኑ፥ #ቅድስና የሌላቸው #ፍቅርየሌላቸው #ዕርቅንየማይሰሙ #ሐሜተኞች #ራሳቸውን የማይገዙ #ጨካኞች #የማይወዱ #ከዳተኞች #ችኩሎች #በትዕቢትየተነፉ #ተድላን #እውቀት #ጥበብ #ማስተዋል #ቃል #መልካም #መታመን #መደገፍ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ኢየሱስም ከዚያ ፈቀቅ

qurrel.jpgፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት። ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። ማቴዎስ 11፡14-20

የኢየሱስ አገልግሎት በሁሉም ነገር ምሳሌ ሊሆንልን የሚችል አገልግሎት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲፈውስ ሰዎች ስለሃይማኖታቸው ምክኒያይ ተቃወሙት፡፡ ሲቃወሙት ግን የተቃወሙትን ሰዎች ለማሳመን ሲከራከርና ሲጣላ አይታይም፡፡ ኢየሱስ የተቃወሙትን ሰዎች በክርክር ለመርታትና አፋቸውን ለማስያዝ ጉልበቱን ሲጨርስ አትመለከቱም፡፡ ኢየሱስ የተቃወሙትን ሰዎች በንግግር ብዛት አፋቸውን ለማስያዝ በዚያም ሃያልነቱን ለማሳየት ሲከራከር አትመለከቱም፡፡

የኢየሱስ አገልግሎት ያለው ውስጡ ነው፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ከአንድ ከተወሰነ ቦታ ጋር የተያያዘ አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ከአንደ የተወሰነ ሁኔታ ጋር የተያያዘም አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ሲቃወሙት አብሮ የሚጠፋ አገልግሎት አልነበረም፡፡  የኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ጎሽ ሲሉት የሚጨምር ሲቃወሙት የሚከስም በውጭው የአየር ሁኔታ የሚወሰን አገልግሎት አልነበረም፡፡

የኢየሱስ አገልግሎት ለሌሎች ማሰናከያ የሚሰጥ አገልግሎት አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ደካሞች ሰዎች ሲቃወሙት በድካማቸው ላይ ድካም የሚጨምርና ይበልጥ የሚያሰናክላቸው አልነበረም፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት በተቃውሞ መካከል እንኳን ለሰዎች በጣም የሚጠነቀቅ ነበር፡፡

የኢየሱስ አገልገሎት ካልታወቅኩ ስሜ ካልገነነ ብሎ ለስሙ ታዋቂነት የሚከራከር ሰው አገልግሎት አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ሰዎች ዘጉብኝ አገልግሎቴ እንዳይወጣ አደረጉት ብሎ ነገሮችን ከሰዎች ጋር የሚያያይዝ አልነበረም፡፡

ኢየሱስ ስጋት አልነበረበትም፡፡ ኢየሱስ አገልግሎቱ ውስጡ እንዳለ ፣ ውስጡ ያለውን አገልገሎት ሊወስድ የሚችልና አገልግሎቱን ሊያስቆም የሚችል ማንም ሰው እንደሌለ ያውቃል፡፡

ኢየሱስ ትኩረቱ ሰዎችን በመጥቀም ፣ ሰዎች ነፃ በማውጣት ፣ ሰዎችን በመፈወስ ላይ እንጂ በስሙ በዝናውና በታዋቂነቱ ላይ አልነበረም፡፡

ኢየሱስ ጩኸቱ ሳይሰማ ሳይጨበጨብለት በላከው ተማምኖ ድምፁን አጥፍቶ ሰውን ፈውሶ ሰውን ነፃ አውጥቶ የሚያገለግል አገልጋይ ነበር፡፡

ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት። ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። ማቴዎስ 11፡14-20

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አገልግሎት #ሰላም #ክርክር #አይከራከርም #አይጮህምም #ፈቀቅ #ስኬት # #ስምረት #ፍርድ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት

አዘነላቸው ድውዮቻቸውንም ፈወሰ

moved by compassion.jpgብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። ማቴዎስ 9፡36

ኢየሱስ በምድር ላይ ያገለገለው ብዙዎችን ነፃ ያወጣው በአዘኔታና በርህራሄ ተመርቶ ነው፡፡ ርህራሄ ወደ ትክክለኛው አገልግሎት ይመራል፡፡ ርህራሄ ወደ እግዚአብሄር ሃሳብ ይመራል፡፡ ርህራሄ ወደፈውስ ወደነኛ ማውጣት ወደአገልግሎት ይመራል፡፡

እግዚአብሄር የሚሰራው በፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚንቀሳቀሰው በርህራሄ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲራራላችሁ ህይወታችሁን ይለውጣል፡፡ እግዚአብሄር ህይወታችሁን እንዲለወጥ ሲፈልግ ለሚያገለግላችሁ አገልጋይ ርህራሄውን ያካፍለዋል፡፡

እግዚአብሄር አገልጋዩን ለፈውስና ለነፃ ማውጣት ሊጠቀም ሲል ለአገልጋዩ ርህራሄ ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር እንዲጠቀምብህ ካስፈለገ ርህራሄ ያስፈልግሃል፡፡ ለምታገለግለው ህዝብ ርህራሄ ከሌለህ በከንቱ ትለፋለህ፡፡ የምታገለግለውን ህዝብ የምታገለገልው ካለፍቅርና ካለርህራሔ እንደስራ ከሆነ አገልግሎቱ ቢቀርብህ ይሻላል፡፡

በፍቅር የማይደረግ አገልግሎትም እንኳን ቢሆን አይጠቅምም፡፡ ካለ ምህረትና ርህራሄ የሚደረግ አገልግሎት ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ  ቆሮንቶስ 13፡1-3

የምታገለግላቸውንና የምትጠቅማቸውን ሰዎች ለማገልገል ፍቅር ያስፈልግሃል፡፡ ፍቅር ከሌለህ እግዚአብሄር አይጠቀምብህም፡፡ ፍቅርና ርህራሄ ካልመራህ እግዚአብሄር አልመራህም፡፡ ፍቅር ሃይልህ ካልሆነ እግዚአብሄር ሃይል አይሆንም፡፡ በፍቅርና በርህራሄ ካልሆነ እግዚአብሄር ካንተ ጋር አይሆንም፡፡

አለምን የምናሸንፍበት እምነት የሚሰራው በፍቅር ነው፡፡ እምነት እንዲሰራና በእምነት ሰዎችን ለመጥቀምና ለማገለግል ፍቅር ይጠይቃል፡፡ እምነት ከፍቅር ተለይቶ አይሰራም፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ገላትያ 5፡6

ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው ድውዮቻቸውንም ፈወሰ። ማቴዎስ 14፡14

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ምህረት #ርህራሄ #ፍቅር #መውደድ  #አዘነላቸው #ነፃማውጣት #አገልግሎት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ

ራስን መግዛት በሰይጣን ላይ በርን ይዘጋል

door.jpgሰይጣን የህይወት ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው እንጂ ስለሌላ አይመጣም፡፡ ሰይጣነ ስራው መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከዚህ ውጭ ስራ የለውም፡፡ ሰይጣን ተልእኮዬን ከግብ አደረስኩ የሚለው ሰዎች ሲሰረቁ ፣ ሲታረዱና ሲጠፉ ነው፡፡

ሰይጣን ደግሞ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ይሰራል፡፡

የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። ሉቃስ 8:12

ኢየሱስ የዚህ አለም ገዢ ይመጣል ከእኔ አንዳች የለውም ብሎዋል፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30

ኢየሱስ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ የተራበ የዚህ አለም ገዢ እየመጣ ከእኔ አንዳች የለውም ሊል እንዴት ቻለ?

እኛስ የዚህ አለም ገዢ እየመጣ በእኛ ላይ አንዳች እንዳይኖረው ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ሰይጣን በመስቀል ላይ በኢየሱስ ድል ስለተነሳ ተሸንፎዋል፡፡ ሰይጣን በግድ አስገድዶ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡

አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15

ነገር ግን ሰይጣን ሰውን የሚሰርቀው የሚያርደውና የሚያጠፋው በሰው ባህሪ ድክመት ተጠቅሞ ነው፡፡ ሰውጣን ሰውን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋቱ በፊት ደካማ ባህሪውን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን በሰው ውስጥ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነ ባህሪ ካላገኘ ሰውን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ አይቻለውም፡፡ ሰውን ለመስረቅ ሰይጣን በመጀመሪያ በሰው ውስጥ ጥላቻን ይፈልጋል፡፡ ሰውን ለማረድ ሰይጣን ቁጣን በሰው ውስጥ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ሰውን ለማጥፋት መጀመሪያ ትእቢትን በሰው ውስጥ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን እነዚህን ባሪያት በውስጣችን ካላገኘ ይመጣል ግን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ሰይጣን እነዚህን እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆኑ ባህሪያት ካገኘ ህይወታችን ለመስረቅ ለማረድና ለማጥፋት ይመቸዋል፡፡

በፍቅር በሚኖር ሰው ለመጠቀም ሰይጣን አይችልም፡፡ በምህረት የሚኖረውን ሰው ለማረድ ሰይጣን አይችልም፡፡ ትሁት የሆነን ሰው ህይወት ለማጥፋት ሰይጣን አይችልም፡፡

ስለዚህ ሰይጣንን በተዘዋዋሪ መንገድ ከህይወታችን ለመከላከልና ለሰይጣን በህይወታችን ውስጥ ስፍራ ለማሳጣት ባህሪያችንን መከታታል ይኖርብናል፡፡ በህይወታችን በሰይጣን ጥቃት ላይ በር ለመግዛት በእግዚአብሄር ቃል እግዚአብሄር መምሰል መልካም ባህሪያችንን መገንባት ይኖርብናል፡፡

ሰይጣን የሚወደውና የሚጠቀምበትን ባህሪ ከህይወታችን ካስወገድን የዚህ አለም ገዢ ይመጣል ከእኔ ግን አንዳች የለውም ማለት እንችላል፡፡

ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡26-27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

የስኬት መለኪያው

success.jpg

በህይወታችን ስኬት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ህይወታችን በስኬት ካልተለካ ብክነት ነው፡፡ ህይወቴ በስኬት ጎዳና ላይ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ በትክክል ካልተመለሰ ህይወታችን ካለፍሬና ውጤት አለመቅረቱ ምንም ማረጋገጫ አይኖረውም፡፡ ስኬት ደግሞ በአጋጣሚ የሚመጣ እድል አይደለም፡፡ ስለስኬት በሙሉ ስልጣን የሚነግረን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡

ስኬት ደግሞ የሚለካው የተፈጠርንበትን አላማ በመፈፀም ነው፡፡ ስኬት የሚለካው እግዚአብሄር እንደፈጠረን ንድፍ ወይም ዲዛይን መኖራችንን በመለካት ነው፡፡ ግን ጥያቄው ስኬት በምን ይለካል? ነው፡፡

ስኬት የሚለካው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን ለመፈፀም የሚያስችለን የክርስቶስ ባህሪ በእኛ ይታያል ወይ? የሚለውን ጥያቄ በታማኝነት በመመለስ ነው፡፡ በክርስትያና ስኬትን እንደኪሎና ርዝመት መለካት ቀላል ባይሆንም ነገር ግን ስኬት የሚለካባቸውን መመዘኛዎች ከእግዚአብሄር ቃል በመመልከት በስኬት ጎዳና ላይ መሆናችንና አለመሆናችንን መመዘን እንችላለን፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን ጥሪ ለመፈፀም የክርስቶስ ባህሪ ይጠይቃል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረውን አላማ ለመፈፀም የጠየቀው ባህሪ ነበር፡፡ አሁንም እኛ የእግዚአብሄር አላማ በህይወታችን ሙሉ ለሙሉ እንዲፈፀም የሚጠይቀን የክርስቶስ ባህሪ በእኛ ላይ መታየቱ ነው፡፡

ሰዎች የሚያከብሩዋቸውና የሚሰግዱላቸው ነውር የሚባሉ ነገሮችን መናቅ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን መሉ ለሙሉ እንድንፈፅም ይረዳናል፡፡ የሰው አስተያየት ሳይሆን የእግዚአብሄር ቃል የህይወታችን መመዘኛ ከሆነ በስኬት ጎዳና ላይ ነን፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2

ሩጥ ተቀደምክ ታለፍክ የሚለውን የአለም የፉክክር ድምፅ ችላ ብለንና በፈቃደኝነት ራሳችንን ከፉክክር አግለን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈፀም በትግስት ከሮጥን የተሳካልን ሰዎች እንደሆንን ሌላ ማርጋገጫ አያስፈልግም፡፡

ስኬታማ እንዳንሆን የሚያግደን የክርስቶስ ባህሪ በእኛ ውስጥ አለመታየቱ ነው፡፡ የክርስቶስ ባህሪ የማይታይበት ሰው ስኬታማ ነኝ ቢል ከንቱ ራሱን ያታልላል፡፡ የክርስቶስ ባህሪ የማይታየበት ሰው በሌላ በሁሉም ነገር ስኬታማ እንደሆነ ቢመስለው ስኬታማ አይደለም፡፡ የክርስቶስን ባህሪ በህይወቱ ለመገንባት ቅድሚያ የማይሰጥ ሰው ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡

እውነተኛ የስኬት መመዘኛ የክርስቶስ ባህሪ በእኛ ውስጥ መታየቱ ነው፡፡ የክርስቶስ ባህሪ በህይወቱ የተገነባ ሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ እየፈፀመ ነው፡፡ የክርስቶስን ባህሪ የተላበሰ ሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ላለመፈፀም የሚያግደው ምንም ሃይል አይኖርም፡፡ የክርስቶስን ባህሪ በሚኖር ሰው ላይ የሚሰራ ህግ የለም፡፡

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ገላትያ 5፡22-23

የክርስቶስ ባህሪ ያለው ሰው ህጉን ፈፅሞታል፡፡ የክርስቶስ ባህሪ ካለው ሰው ውጭ የእግዚአብሄርን አላማ በህይወቱ ፈፅሞ ለማለፍ ብቃቱ ያለው ሰው የለም፡፡

ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። ገላትያ 5፡14

በየደረጃው ላለው ለእግዚአብሄር አሰራር ራሱን ትሁት ከሚያደርግ ሰው በላይ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈፀም የሚያስችል ስልጣን ያለው ሰው የለም፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ 2፡5-8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ጌታ #ባህሪ #ፍቅር #ትህትና #ትእግስት #መከተል #ክርስቶስእስኪሳል #መምሰል #ክርስቶስንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: