Category Archives: mind

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

seen by men.jpg

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

ክፉን በክፉ ላለመመለስ ህፃናተ ሁኑ እንጂ ስለህይወታችሁ እወቁ፡፡ ህይወታችሁን እንዳመጣላችሁ አትምሩት፡፡ ህይወታቸሁን ለመምራት አስቡ አቅዱ በእግዚአብሄር ቃል የታደሰ አእምሮዋችሁን ተጠቀሙ፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20

መውጫ መግቢያውን የምትቃኙ ንቁዎችና ብልሆች ሁኑ እንጂ ወደ ወሰዷችሁ የምትጎተቱ ሞኞች አትሁኑ፡፡

እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 10፡16

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

በእእምሮው ህፃን የሆነ ሰው የራሱ የህይወት መርህ የለውም የመጣው ነገር ሁሉ ይወስደዋል፡፡

ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡11

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

በአእምሮው የበሰለ ሰው የሰው የግል መጠቀሚያ አይሆንም፡፡ በአእምሮ የበሰለ ሰው ዘሎ ውሳኔን አይወስንም በአእመሮ ህፃን ያልሆነ ሰው አካሄድን ይመለከታል ይመዝናል፡፡

በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17

የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። መጽሐፈ ምሳሌ 14፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ህፃንነት #ብስለት #ጥበብ #ማስተዋል #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ

የቃሉ አካባቢን መጠበቅ

mind word atmosphere.jpgሰው አካባቢውን ከአየርና ከውሃ ብክለት ለመጠበቅ ታላቅ እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ ሰዎች የአለምን አረንጓዴነትና ለጤና ተስማሚነት ለመጠበቅ ማንኛውም ነገር ያደርጋሉ፡፡

ምድርን የሚበክልን ነገር ለምሳሌ የከታላላቅ ፋብሪካዎች የሚወጣውን የተበከለ ጭስ እንዲቀነስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ምክኒያቱም በቀጣይነት በቆሻሻ አካባቢ ውስጥ የሚኖር ሰው ከመታመምና ከመሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ ግን አለማችንን የሚበክለው እግዚአብሄርን ያለማመንና ጥርጣሬ ነው፡፡ ሰው አካባቢውን በእግዚአብሄር ቃል ካልሞላ እምነት የሚፈጥረውን የእግዚአብሄርበ ቃል ብቻ ካልሰማ እግዚአብሄርን ካላመነ በስተቀር እግዚአብሄርን ደስ ሊያሰኝ ከእግዚአብሄር የሆነውንም ነገር ሊቀበል አይችልም፡፡ ከባቢው ተበላሽቶ እግዚአብሄርን ማመን ካቃተው ሰው የበልጥ ምስኪን ሰው የለም፡፡

ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን የአስተሳሰብ አካባቢያችንን በመበከል መንፈሳዊ ጤንነታችንን የሚጎዱ ነገሮችን ሊያስፋፋ ይመጣል፡፡

የሰይጣን የመስረቂያ የማረጃና የማጥፊያ አካባቢዎች አለማመን ፍርሃትና ጥርጣሬ ናቸው፡፡ ሰይጣን ካለማመንና ፍርሃትና ጥርጣሬ ውጭ ሌላ ሃይል የለውም፡፡

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አካባቢያችንን በእግዚአብሄር ቃል እንድንሞላና ንፅህናውን ከአለማመን እንድንጠብቅ የሚያስተምረን፡፡ አካባቢያችን በእግዚአብሄር ቃል ስንሞላና የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ ንፁህ መንፈሳዊ አየርን መተንፈስ እንችላለን፡፡

የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ በፍጹምም ነፍስ በፍጹምም ኃይል ለመውደድ አካባቢያቸውን በእግዚአብሄር ቃል እንዲሞሉና ከብክለት እንዲጠብቁና እንዲያፀዱ ተመክረዋል፡፡

አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9

የእግዚአብሄር ህዝብ መሪ የነበረው ኢያሱ የእግዚአብሄርን ቃል ለመፈፀም እንዲያስችለው ቃሉን በቀንና በሌሊት እንዲያሰላስልና በቃሉ አካባቢ ውስጥ እንዲኖር ታዟል፡፡

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። እያሱ 1፡8

እግዚአብሄር እንደልቤ ያለው መዝሙረኛው ዳዊት መዝሙሩን የጀመረው አካባቢውን ከክፋት ሃሳብ ብክለት ስለሚጠብቅና በእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ ስለሚኖረው ሰው ምስጉንነትና የዘወትር ክንውን በመናገር ነው፡፡

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡1-3 ሃዋሪያው ሰው አለምን የማይመስልበትን ብቸኛው መንገድ የሃሳብን አካባቢ በእግዚአብሄር ቃል በማፅዳትና በመጠበቅ እንደሆነ ያስተምራል፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

መንፈሳዊ ህይወታችንን ከብክለት ለመጠበቅ በአስተሳሰብ አካባቢያችን የሚፈቀድላቸውና የማይፈቀድላቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደሚገቡ መፅሃፍ ቅዱስ በአፅንኦት ያስተምራል፡፡

በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊሊጲስዮስ 4፡8 ስለዚህ ነው ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ምን እንደምትሰሙ ተጠበቁ ያላቸው፡፡

አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። ማርቆስ 4፡24

ስለዚህ ነው የእግዚአብሄር ቃል በቤታችን በስልኮቻችን በመኪናችን ልንሰማና ልናነብ የሚገባን፡፡ ለዚህ ነው ባገኘነው አጋጣሚ የእግዚአብሄርን ቃል ከባቢ መፍጠር ያለብን፡፡ ለዚህ ነው የእግዚአብሄርን ቃል ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መጫወት ያለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ለመረዳትና ለመጠበቅ የእግዚአብሄርን ቃል አካባቢ መፍጠርና በከባቢው ውስጥ መኖር አለብን፡፡  ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ አካባቢህን ጠብቅ ያለው፡፡

ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 4፡20 ፣ 22-23

አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9

ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ቃል #ምስጉን #ሃሳብ #ማሰላሰል #ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #ፌስቡክ #አዋጅ

እነዚህን አስቡ

thinking.jpgበቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8
ለተሳካ ምድራዊ ህይወት የህይወትን ህግ ጠብቀን መራመድ እንዳለብን ሁሉ ለተሳካ የክርስትና ህይወት ለመኖር እንደ መፅሃፍ ቅዱስ ስርአት አእምሮዋችንን መግራት ይገባናል፡፡ ሃሳብ በእግዚአብሄር ቃል መፈተን አለበት፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድን ሃሳብ ፈትነን ማወቅ አለብን፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
ለማንኛውም ነገር የሚሰራና የማይሰራ ህግ እንዳለው ሁሉ ለአስተሳሰብ ህይወታችንም የሚሰራና የማይሰራ መንገድና ህግ አለ፡፡ ለማንኛውም ውጤትና ፍሬያማነት ህግን ጠብቀን መራመድ እንዳለብን ሁሉ ለክርስትና ህይወታችን ፍሬያማነት የአስተሳሰብን ህግን መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡
ሰው በልቡ እንደሚያስበው እንዲሁ ነው፡፡ እንደሚያስብው እንዲሁ ነውና፡፡ ሰላምን የሚያስብ ሰላማዊ ይሆናል፡፡ ክፋትን የሚያስብ ሰው ክፉ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ምሳሌ 23፡7
ለብዙ ነገር ህግ እንዳለ ሁሉ ለአስተሳሰብ ህይወታችንም ህግ አለው፡፡ እያንዳንዱ ነገር በትክክል የሚሰራበትና የማይሰራበት መንገድ እንዳለው ሁሉ አእምሮዋችን በትክክል የሚሰራበትና የማይሰራበት መንገድ አለው፡፡
በማንኛውም ነገር የማይደረግና ህግ የሚከለክለው ነገር እንዳለ ሁሉ በአስተሳሰባችንም ማሰብ ያለብንና ማሰብ የሌለብን ነገሮች አሉ፡፡ በማንኛውም ነገር ጠቃሚ ነገር እንዳለ ሁሉ በአስተሳሰባችንም የሚፈቀድና ጠቃሚ አስተሳቦች አሉ፡፡
የመፅሃፍ ቅዱስ የአስተሳሰብ ህግ ከተከተልን ህይወታችን ይባረካል፡፡ የመፅሃፍ ቅዱስ የአስተሳሰብ ህግ ካልተከተልን ግን ህይወታችን ካለ ፍሬ ይቀራል፡፡
የሰው አስተሳሰብ ወሳኝ የህይወት ክፍል ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ወደ አእምሮዋችን የሚመጣውን ነገር ሁሉ እንዳናስብ ያስጠነቅቀናል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ለአስተሳሰብ ህይወታችን ህግ እንዲኖረን ያስተምራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ለማሰብ የምንፈቅድለትና የማንፈቅድለት ነገር እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ፍሬያማ የሚያደርገን ሃሳቦች እንዳሉና ህይወታችንን የሚያበላሹ አደገኛ ሃሳቦች እንዳሉ ያስተምረናል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ አስተሳሰባችን በእነዚህ መመዘኛዎች ተመዝነው ያለፉ ብቻ እንዲሆኑ መፅሃፍ ቅዱስ ያዛል፡፡ እነዚህን መመዘኛዎች ያላሟላ ነገር ማሰብ እንደሌለብን መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8
እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ሰይጣን የውሸት አባት ነው፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ይመጣል፡፡ /ዮሃንስ 10፡10/ ሰይጣን የሰውን ህይወት የሚያጠፋው ውሸትን እንዲያምኑ በማድረግ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ሄዋን እንድትወድቅ ያደረገው ውሸትን እንድታምን በማድረግ ነበር፡፡ እውነተኛ የሆነውን ነገር ብቻ ማሰብ ህይወታችንን ከጠላት ይጠብቃል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት ነው፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል የሆነ ነገር ሁሉ እውነት ነው፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነን ነገር ማሰብ ህይወትን ለጥፋት አደጋ ያጋልጣል፡፡
ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥
ጭምትነት ማለት ጨዋነት ፣ ረጋ ማለት ፣ ንፁህ ላልሆነ ጥቅም አለመስገብገብና ኩሩ መሆን ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችን ረጋ ያለ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የሰይጣንና የእግዚአብሄር ድምፅ የሚለይበት መንገድ ሰይጣን ይስቸኩላል እግዚአብሄር ግን በእረፍት ውሃ ዘንድ ይመራል፡፡ ሰይጣን ያዋክባል እግዚአብሄር ግን በዝምታ ያሳምናል፡፡ ሰይጣን አሁን ካላደረህክ ያመልጥሃል ይላል፡፡ እግዚአብሄር ግን ተናግሮ እስክትረዳው ይጠብቃል፡፡
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። ራእይ 3፡20
ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ፅድቅ እውነት እና ትክክለኛውን ነገር ውስጣችን ያውቀዋል፡፡ እውነተኝነትንም ማሰብ ከእግዚአብሄር ጋር እንድንወግን ያደርገናል፡፡ ትክክለኛውን ነገር አለማድረግ ደግሞ ከእግዚአብሄር ተቃራኒ እንድንሆን ያደርገናል፡፡
ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ሰው በተፈጥሮው ንፁህን ምግብ ካልበላ እንደሚታመም ሁሉ ሰው ንፁህን ነገር ብቻ ካላሰበ መንፈሳዊ ህይወቱ ይቆሽሻል፡፡ ሰው ሊያቆሽሸው የሚመጣውን ሃሳብ እንቢ ካላለ በስተቀር ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ያበላሽበታል፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሚለው፡፡
በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2-3
ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥
ጥላቻ ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡ የጥላቻ ሃሳብ ከሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን ሰውን ሊጠቀምበት ሲፈልግ ጥላቻን ይከትበታል፡፡ ጥላቻ የገባበት ሰው ለሰይጣን ዘር ለም መሬት ነው፡፡ ስለዚህ የምናስበው ነገር እግዚአብሄርን ይሁን ሰውን እንድንጠላ ሳይሆን እንድንወድ የሚያደርገን ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ምግብ ስንበላ መርጠን እንደምንበላ ሁሉ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ ብቻ እንድናስብ ጥላቻ ያለበትን ነገር ሁሉ በፍጥነት ከአስተሳሰብ ህይወታችን እንድናስወግድ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥
እግዚአብሄር መልካም ነው፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እግዚአብሄር ተስፋችን ነው፡፡ ወድቀን እንኳን እግዚአብሄር የሚያስበውና የሚናገረው ስለመነሳታችን ነው፡፡ ተስፋን የሚያጨልም ሃሳብ የእግዚአብሄርን መልካምነት እንድንጠራጠር የሚያደርግ ሃሳብን ከአእመሮዋችን በፍጥነት አሽቀንጥረን መጣል ይኖርብናል፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ያዕቆብ 4፥11
በጎነት ቢሆን
እግዚአብሄር መልካም አምላከ ነው፡፡ እኛም ለጆቹ ማሰብ ያለብን በጎነትን ነው፡፡ ለሰዎች መልካም ማሰብ መልካም መናገር መልካምን ማድረግ የእግዚአብሄር ልጅነት ባሀሪ ነው፡፡ ስንፈጠር ለክፋት ስላልተፈጠረን ከበጎነት ውጭ ማሰብ ህይወታችንን ይጎዳል፡፡
ምስጋናም ቢሆን፥
ባለን መርካት ፣ ራሳችንን ማጠን ፣ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ እግዚአብሄርን ማመስገን ከእኛ ይጠበቅብናል፡፡ ማጉረምረም ያለበትን ነገር በማሰብ ትክክለኛውን ነገር ማደረግ እንችልም፡፡ ምስጋናን በማሰብ ደግሞ ልንሳሳት አንችልም፡፡ ምስጋና ከእግዚአብሄር ጋር ላለን ግንኙነት ወሳኝ ነው፡፡
አእምሮዋችን ያመጣልንን ሃሳብ የምናስብ ከሆነ እንደምናስበው እንሆናለን፡፡ አእምሮዋችንን ከጠበቅን ህይወታችንን እንጠብቃለን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እግዚአብሔር #ጌታ #አእምሮ #ማደስ #መለወጥ #መከተል #መከተል #መምሰል #እግዚአብሔርንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከሞተ ስራ ንስሃ

change-744x330.jpgበመፅሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ካሉት ለሰመረ የክርስትና ህይወት መሰረት ከሆኑት መሰረታዊ ትምህርቶች መካከል ንስሃ አንደኛው ነው፡፡፡

ንስሃ ሃሳብን መለወጥ ሲሆን ሰው በፊት ከሚኖርነት የኑሮ አስተሳሰብ እእምሮው ተለውጦ በአዲስ አስተሳሰብ መኖር ሲጀምር ንስሃ ገባ ይቨባላል፡፡

ንስሃ መግባት ማለት የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶችን ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ንስሃ ከምንሄድበት መንገድ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ መመለስ ነው፡፡ ሃሳባችንን ለውጠን ካልተመለስን በስተቀር የምናደርጋቸው ማንኛውም ሃይማኖታዊ ስርአቶች ሃይማኖተኛ እንደሆንን እንዲደሰማን ያደርጉ ይሆናል እንጂ ለእውነተኛ መንፈሳዊነት አይጠቅሙም፡፡ እግዚአብሄር መመለስን ይባርካል፡፡

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። ሐዋርያት 3፥19-20

በአለማችን ላይ በአስተምሮት ትምህርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ያስነሳቸው የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪው ዴሪክ ፕሪንስ ሲናገሩ በክርስትና ህይወት ላለማደግና ላለመለወጥ ትልቁ ፈተና ንስሃ አለመግባት ነው ይላሉ፡፡ እንዲሁም በቤተክርስትያን ውስጥ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥሩ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች ናቸው ይላሉ፡፡

ሰው በአለም አስተሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሊሰራ ሲሞክር ሁሉ ነገር ይዛባበታል፡፡ የአለም ሃሳቡን ለመተው ያልተዘጋጀ ሰው አብረው በፍፁም የማይሄዱ ሁለት ነገሮችን አብሮ ሊያስኬድ በመሞከር ህይወቱን ያጠፋል፡፡ የማንስሃ ንስሃ ያልገባው ሰው የሚፈልገውን ነገር ቢያገኝ እንኳን የእግዚአብሄርን አብሮነት በህይወቱ ያጣዋል፡፡

ጌታን የተቀበልነው ይህ አስተሳሰቤና ኑሮዬ አያዋጣኝም ብለን ነው፡፡ ነገር ግን ጌታን የተቀበለው ለሃይማኖት ለውጥ ከሆነ ምንም ውጤት ሳናገኝ ህይወችንን አናባክናለን፡፡

ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ኤፌሶን 4፥22-23

አንድ ጊዜ እንደዚህ ሆነ፡፡ አንድ እህት ስለአንድ አገልጋይ እየነገረችኝ ነበር፡፡ ይህ አገልጋይ በጌታ ባይሆን ኖሮ ስንት ሴቶችን ያማርጥ እንደነበረ የነገራትን ስትነግረኝ በጣም ደነገጥኩ፡፡ አልነገርኳትም እንጂ በልቤ ይህ ሰው ንስሃ አልገባም ህይወቱ አደጋ ላይ ነው አልኩ፡፡

ይህ በቤተክርስትያን ውስጥ በጣም ሲያገለግል የነበረው እግዚአብሄር ያስነሳው አገልጋይ ከአመታተ በኋላ ወደኋላ ተመለሰና ያ ሲመካበት የነበረውን ሃጢያት ማድረግ ጀመረ፡፡ ወደ ቤተክርስትያን መጥቶ ነበር እንጂ የሃጢያት ጣእም በአፉ ውስጥ ነበር፡፡ ሃጢያትን አልተፀየፈውም አላፈረበትም ነበር፡፡

እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና። ሮሜ 6፥21

ያለውን ማንኛውም አስተሳሰብ ለእግዚአብሄርን ቃል ለመለወጥ የወሰነ የተሰበረ ሰው በቤተክርስትያን ሲያድግና ሲለወጥ ታያላችሁ፡፡

በአስተሳሰባችን አለምን መስለን እግዚአብሄር ይባረከናል ብሎ መገመት ራስን መታለል ነው፡፡ ስለዚህ ነው በአለም አስተሰሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ስለማይሳካልን መፅሃፍ ቅዱስ አስተሳሰባችሁንና አካሄዳችሁን ለውጡ ንስሃ ግቡ የሚለን፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፥2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ሃሳብ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ንስሃ #መንገድንመቀየር #አስተሳሰብንመቀየር #መለወጥ #በረከት #መታደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አእምሮ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም

snake.jpgመጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ኤፌሶን 6፡12

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡3-5

ከምናስበው በላይ ብዙ ነገሮች መንፈሳዊ ናቸው፡፡ የሰይጣን መንፈሳዊ አለም በክፋት ይሰራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ጠላት ዲያቢሎስ አያርፍም ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ዙሪያችንን ይዞራል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን እኛን ለማጥቃት ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ ጴጥሮስን ተጠቅሞ በሰው ሃሳብ ሊያጠቃው የመጣውን ዲያቢሎስ ኢየሱስ ለይቶ አወቀው፡፡ ኢየሱስ በጊዜው ጠላት ከተጠቀመበት ከጴጥሮስ ላይ አይኑን እንስቶ የዚህ የክፉ ሃሳብ ምንጩን ዲያቢሎስ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን፡፡

ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። ማቴዎስ 16፡22-23

ብዙ ጊዜ ግን አይናችንን ከጠላታችን ዲቢሎስ ላይ አንስተን እርሱ ለጥፋት በሚጠቀምባቸው ሰዎች ላይ ለማድረግ እንፈተናለን፡፡

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8-9

እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የሰው ጠላት የለንም፡፡ ጠላታችን አንዱ ዲያቢሎስ ነው፡፡ እውነት ነው ሰይጣን የሰዎችን አእምሮ ተጠቅሞ እነርሱንም እኛንም ለመስረቅ ለማረድና ለማጥፋት ይመጣል፡፡

ስለዚህ የእኛ መጋደል ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም፡፡ ከደምና ከስጋ ጋር የምንጋደል ከሆንን በተሳሳተ ገድል ህይወታችንን እያባከንን ነው፡፡ መጋደላችን ከሰው ጋር በፍፁም አይደለም፡፡

መጋደላችን ከክፉ መንፈሳዊ አለም መናፍስት ጋር ነው፡፡ ሰው በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ ክፉን ሃሳብ በሰው ውስጥ ልከው ሰው ክፉ እንዲያደርግ የሚያደርጉት የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ናቸው፡፡

የሰዎችን ቅንነት የሚያበላሸውን ሰዎች ውስጥ ክፋት የሚጨምረውን ክፋትን የሚያባብሰውን ክፉን በጌታ በኢየሱስ ስም ልንቃወም ይገባናል፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

ሰዎች አንድ ነገር ሲደርስባቸው እከሌ ነው ብለው ይደመድማሉ ከዚያም መጋደላቸው ከእከሌ ጋር ይሆናል፡፡ ሰዎች ስጋ ለባሽን እንጂ ከዚያ አልፈው ስጋ ለባሽን ለክፋት የሚያነሳሳውን ካላዩ እውነተኛ ጠላታቸውን አያውቁም፡፡ ሰዎች ከሰው አልፈው የክፋቱን ምንጭ ክፉ መንፈሳዊ አለምን ካላዩ ኢላማቸውን ይስታሉ፡፡ ሰዎች ግን የክፋትን ምንጭ መንፈሳዊ አለምን ከለዩና ትኩረታቸውን ከስጋ ለባሽ ላይ እንስተው ወደ መንፈሳዊ አለም ካዞሩ ችግሩን ከስሩ በማድረቅ ውጤታማ ይሆናሉ፡፡

አይናችንን ከሰዎች ላይ አንስተን የሚታለሉትን ሰዎች የሚጠቀመውንና ፈቃዱን የሚያስደርጋቸውን ከተቃወምን በሰዎችም ህይወትና በእኛም ህይወት የጠላትን ስራ ማፍረስ እንችላለን፡፡

በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #የጦርመሳሪያ #ምሽግ #አእምሮ #ሃሳብ #ማታለል #ብርቱ #ተቃወሙት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእግዚአብሔር ፈቃድ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ

mind renewal.jpgየእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን እንዲያመልክና እንዲያገለግል ነፃ ወጥቷል፡፡ ስኬት የተፈጠሩለትን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡ ስኬት ለተፈጠሩነት አላማ መኖር ነው፡፡ ስኬት የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ደግሞ በህይወታችን ፈቃዱን መለየት አለብን፡፡ በምድር ላይ ብዙ ድምፆች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእነዚያ ብዙ አይነት ድምፆች መካከል መለየት ለእግዚአብሄርን ፈቃድ ኖረን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመለየት አእምሮዋችን በእግዚአብሄር ቃል መታደስ አለበት፡፡ በአለም አስተሳሰብ በተበላሸ አእምሮ የእግዚአብሄን ፈቃድ መለየት በፍፁም አይቻልም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሚገባ መለየት የሚችል እእምሮ በእግዚአብሄርን ቃል የታደሰ አእምሮ ብቻ ነው፡፡

መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አእምሮዋችን ከተሳሳተ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ካልሆነ አለማዊ አስተሳሰብ በእግዚአብሄር ካልታደሰና ካልተለወጠ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መለየት ይሳነናል፡፡

አእምሮዋችንን ከሌሎች አስተሳሰቦች ሊያፀዳና እንደ እግዚአብሄር ቃል ሊለውጥና ሊያድስ የሚችለው የእግዚአብሄርን ቃል ማንበብና ማሰላለስ ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ጌታ #አእምሮ #ማደስ #መለወጥ #መከተል #መከተል #መምሰል #እግዚአብሔርንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም

soul without knowledge.jpgነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ ምሳሌ 19፡2

ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራልንን የደህነት ስራ በማመን ኢየሱስን ከተቀበልን በኋላ በክርስቶስ እንዴት እንደምንኖር ማወቅ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ ሰው በቃሉ እውቀት ነፍሱን ካላደሰ ጌታን ተቀብሎ እንዳልተቀበለ ሰው በአሮጌ ማንነቱ ሊኖር ይችላል፡፡

ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ኤፌሶን 4፡22-24

ሰው በሃጢያት ምክኒያት አስተሳሰቡ ተበላሽቶዋል፡፡ ሰው ኢየሱስን ተቀብሎ በእግዚአብሄር ቃል እውቀት ነፍሱን ካላዳናት በስተቀር የሰይጣን እስረኛ ሆና ልትቆይ ትችላለች፡፡ ሰው ኢየሱስን ተቀብሎ በእግዚአብሄር ቃል እውቀት ካልታጠቀ የእግዚአብሄርን አላማ በህይወቱ ሊፈፅም አይችልም፡፡ ሰው ከልጅነቱ በተለያየ መንገድ የሰማው እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነ የአለም አሰራር በነፍሱ ውስጥ አለ፡፡ ሰው ዳግመኛ ከእግዚአብሄር ቃል ተወልዶ ወደ እግዚአብሄ ምንግስት ሲገባ በእግዚአብሄር ቃል ነፍሱን ማደስ አለበት፡፡ ነፍሱን በእግዚአብሄር ቃል የሚያድስ ሰው ብቻ ነው ነፍሱን ከአለማዊ ክፉ አስተሳሰብና ከሰይጣን ጥቃት የሚያድናት፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21

ሰው በክርስቶስ  ከእግዚአብሄር ጋር ታርቆ እንደባይተዋር ሊኖር ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ እውቀት ከሌላው በሽንፈት ሊኖር ይችላል፡፡ ሰው በክርስቶስ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ተቀላቅሎ ሳለ የእግዚአብሄር ቃል እውቀት ከሌለው  የእግዚአብሄርን አላማ በህይወቱ ሳይፈጽም እንደ ማንኛውም ተራ ሰው ኖሮ ሊያልፍ ይችላል፡፡

ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝሙር 49፡12

ኢየሱስን ለተቀበለ ሰው በክርስቶስ ታላቅ አርነት ተዘጋጅቶለት እያለ የቃሉ እውቀት ከሌለው በእስራት ሊኖር ይችላል፡፡ የኢየሱስን አዳኝነት መቀበል ለመዳን የመጀመሪያው ደረጃ ቢሆንም ሰው እውነትን አውቆ ካልኖረበት ነፃ መውጣት በፍፁም አይችልም፡፡

ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡21-32

እግዚአብሄር በክርስቶስ ሁሉን ስላዘጋጀልን ከእኛ የሚጠበቀው እግዚአብሄርንና ክርስቶስን በማወቅ ፀጋና ሰላም እንዲበዛል ነው፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እውቀት #ጥበብ #ነፍስ #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #መልካም #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #አእምሮ #ሰላም #ማስተዋል #ልጅ

“መልካም” ወይስ የእግዚአብሄር ሃሳብ

good or god.jpgከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። ዘፍጥረት 3፡5-6

የክርስትና ህይወት የውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ በክርስትና ያሉት ምርጫዎች ደግሞ መልካሙን እና ክፉውን የመምረጥ ምርጫዎች አይደሉም፡፡ ብዙ መልካም የሆኑ የእግዚአብሄር ፈቃድ ግን ያልሆኑ ነገሮች በህይወታችን ይመጣሉ፡፡

ሰይጣን አታላይ ነው፡፡ ሰይጣን ወደሄዋን የመጣው እኔ ሰይጣን ነኝ ብሎ አይደለም፡፡ ሰይጣን ወደ ሄዋን የመጣው መልካም በሚመስል ነገር ነው፡፡ ሰይጣን ለሄዋን ያሳያት መልካም አሳቢ በመምሰል ነው፡፡

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ዘፍጥረት 3፡6

እግዚአብሄር መልካም ካላለው ምንም መልካም ነገር የለም፡፡ አብላጫው ድምፅ መልካም ቢለውም እግዚአብሄር መልካም ካላለው መልካም አይደለም፡፡ ያማረ ቢሆንም እግዚአብሄር መልካም ካላለው ህይወት የለበትም፡፡ ለአይን ቢያስጎመጅም እግዚአብሄር የእግዚአብሄር ፈቃድ ከሌለበት አሳሳች ነው፡፡ ለጥበብም መልካም እንደሆነ ብናይም እግዚአብሄር መልካም ካላለው መልካም አይደለም፡፡

እግዚአብሄር በነቢዩ በራሳቸው ማስተዋል ብቻ በጭፍንነት ስለሚመሩ ሰዎች ያስጠነቅቃል እንዲህ ሲል፡-

ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው! በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው! ኢሳይያስ 5፡20-21

አለም በክፉ ተይዟል፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከህዝብ አብላጫ ድምፅ አናገኘውም፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ የሚገኘው መልካም በሚመስል ነገር ውስጥ ሳይሆን በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ አገልግለን ለማለፍ ሰዎች መልካም የሚሉትንና እኛ መልካም የመሰለንን መከተል ሳይሆን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእግዚአብሄር ቃልና ከመንፈሱ ማግኘትና መከተል ይኖርብናል፡፡

የእግዚአብሄርን ቃል እንደ መናገር የከበረ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን በህይወታችን ውስን ስለሆንን መንፈስ ቅዱስ በእስያ እና በሚስያም እንዳንናገር ይልቁንም በመቄዶንያ እንድንናገር የሚፈልግበት ጊዜ አለ፡፡ እዚህ ቃሉን መናገር መልካም ነው ግን የእግዚአብሄር ሃሳብ አይደለም፡፡

በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤ በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤ ሐዋርያት 16፡6-7

ኢየሰስ ለአይሁድ ተላልፎ እንደሚሰጥ ለደቀመዛሙርቱ ሲነግራቸው ጴጥሮስ መልካም ሃሳብ አምጥቶ አየሱስን ከመሞት ሊከለክለው  ሞከረ፡፡ የኢየሱስ መሞት በሰው እይታ መልካም አይደለም ግን የእግዚአብሄር ፈቃድ ነበር፡፡ ሰይጣን የሰውን መልካም ሃሳብ ተጠቅሞ ኢየሱስን ከመሞት ሊያስቆመው ነበር፡፡

ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። ማቴዎስ 16፡22-23

ስለዚህ ነው በራስህ ማስተዋል ጠቢብ አትሁን የሚለው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ ምሳሌ 3፡5-7

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #መልካም #መታመን #መደገፍ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ገዳም አይቀድስም ከተማ አያረክስም

monestry.jpgለእግዚአብሄር ክብር ስለተፈጠረን ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር ከመፈለጋችን የተነሳ ከከተማ ወጥተን የሆነ ቦታ ሄደን ብቻችንን ብንሆን እንመኛለን፡፡ በአካባቢያችን ያለውን የሰውን የአለማዊነት ምኞት በመፀየፍ ነፍሳችን ትጨነቃለች፡፡

ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና፡፡ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡7-8

ችግሩ ግን ሃጢያት ያለው በከተማ ውስጥ አይደለም፡፡ ቅድስም ያለው በገዳም ውስጥ አይደለም፡፡ ሃጢያት ያለው በሰው ልብ ውስጥ ነው፡፡

ለውጭው ነገራቸው እጅግ የሚጨነቁትንና ውጫዊ ነገር ያረክሰናል ብለው ለሚያስቡት ፈሪሳዊያን ኢየሱስ የውጭ ነገር ሰውን እንደማያረክስ ሰውን የሚያረክሰው የሰው የልብ ሃሳብ እንደሆነ ያስተምራቸዋል፡፡ ክፉ ሃሳብ የሚመጣው ከትልቅ ከተማ ውስጥ አይደለም፡፡ ክፉ ሃሳብ የሚወጣው ከሰው ልብ ውስጥ ነው፡፡

ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ማቴዎስ 15፡18-19

ስለዚህ ኢየሱስ በልባቸው እንዲቀደሱ ቅድስና በቦታ ለውጥ ሳይሆን ቅድስና በልብ ለውጥ እንደሚመጣ ሲያስተምራቸው እንመለከታለን፡፡፡ ሰው ልቡን ከክፉ ሃሳብ ካጠራ አለሙን ከተማም ይሁን ገጠር ያጠራዋል፡፡ ሰው የልቡ ሃሳብ ከክፋት ካልጠራ ግን ከተማም ይኑር ገዳምም ይግባ ዋጋ ከአለም እርኩሰት መለየት አይችልም፡፡

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። ማቴዎስ 23፡25-26

ስለዚህ ነው ሰው አለምን ከመምሰል የሚድነው ገዳም በመኖር ወይም ከተማ ባለመኖር ሳይሆን ሰው አለምን የማይመስለው በአስተሳሰብ እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

ሰው በእግዚአብሄር ቃል አስተሳሰብ በልቡ መታደስ ካለተለወጠ የትም የትም ቢኖር አለማዊ አስተሳሰብ ይኖረዋል፡፡ ሰው ደግሞ በእግዚአብሄር ቃል አስተሳሰቡ ከተለወጠ ቅልጥ ያለው መሃል ከተማ እየኖረ አለምን ሳይመስል በቅድስና እግዚአብሄርን አስከብሮ ይኖራል፡፡

ኢየሱስ በቃሉ አማካኝነት እዚሁ በአለም እያለን እንድንቀደስ እንጂ ከአለም እንዲያወጣን አልፀለየም ፡፡

ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም። በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። ዮሃንስ 17፡15-17

አለምም የሚባለው የሃጢያተኝነት ምኞት እንጂ ከተማ አይደለም፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #አእምሮ #ልብ #ገዳም #አለም #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የአስተሳሰብ ንፅህና

mind descipiline.jpgሰይጣን የሰው ልጅ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድ እና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ተልእኮ የለውም፡፡

ሰይጣን በማይታዘዙት ልጆች ላይ የጥፋት አላማውን ይሰራል፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2

እኛ ግን ከጨለማው ስልጣን ስለዳንንና ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት ስለፈለስን በእኛ ላይ ስልጣን የለውም፡፡

እኛን የሚዋጋን በሃሳብ ነው፡፡ ሰይጣን ክፉ ሃሳብን ወደ አእምሮዋችን ይልካል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነውን ሃሳቡን ከተቀበልነው አላማውን ያስፈፅምብናል፡፡ ካልተቀበልነው ግን ሃሳቡና አላማው በውስጣችን ይሞታል፡፡

ሰው ሃሳቡ ከተበላሸ ህይወቱ ይበላሻል፡፡ ሰው በሃሳቡ የሃጢያትን ሃሳብ ካስተናገደ ሰው በህይወቱ የሃጢያትን ህይወት ያደርገዋል፡፡ ሰው ሃሳቡን ከሃጢያት ከጠበቀ ህይወቱን በንፅህና ይጨብቃል፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

ሰው በአስተሳሰብ ህይወቱ እግዚአብሄርን ከፈራ ከሃጢያት የነፃ ህይወት ይኖረዋል፡፡ ሰው አያየኝም ብሎ የሃጢያትን ሃሳብ የሚያስተናግድ ሰው ሃጢያትን ሲያደርገው ይገኛል፡፡

ሰው አስተሳሰቡ ቅጥ ያጣ መሆን የለበትም፡፡ ሰው አስተሳሰቡ ስርአት ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ህይወታችንን በንፅህና ለመጠበቅ ማሰብ የሚገባን ነገሮች አሉ ማሰብ የማይገባን ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡ ወደ አእምሮዋችን የመጣውን ሃሳብ ሁሉ አናስብም፡፡ በአእምሮዋችን ውስጥ እንዲቆይ የምንፈቅድለት ሃሳብ አለ፡፡ ከአእምሮዋችን በፍጥነት አሽቀንጥረን የምንጥለው ሃሳብ አለ፡፡

በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8

አእምሮዋችንን ከክፉ ሃሳብ ወረራ ከጠበቅን ህይወታችንን ከሰይጣን ጥቃት እንጠብቃለን፡፡

የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡5

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #ንፅህና #ምኞት #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የንስሃ ህይወት

publication2በአዳም ምክኒያት የሰው ልጅ ሁሉ በሃጢያት እስራት ውስጥ ወድቆዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር ንስሃ መግባት አለበት፡፡
የአለም የአሰራር ስርአትና የእግዚአብሄር መንግስት አሰራር ፍፁም የተለያዩ ናቸው፡፡
የአለም አሰራር በፍፁም በራስ ወዳድነትና በስጋ ምኞት ላይ የተመሰረተ አሰራር ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት አሰራር ደግሞ በፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16
ሰው በአለም ሲኖር ራሱ በራሱ ላይ ጌታ ሆኖ ነው የሚኖረው፡፡ ያመረውን ያደርጋል ያላመረውን አያደርግም፡፡ እግዚአብሄርን ያስደስታል ወይ? እግዚአብሄርን ያስቆጣል ወይ? ብሎ አያስብም፡፡ ምክኒያቱም በአለም የሚኖር ሰው እግዚአብሄር ጌታው አይደለም፡፡ በህይወቱ የእግዚአብሄርን ጌትነት ጥሎታል፡፡
የእግዚአብሄር መንግስት አሰራር ደግሞ በፍቅርና በፍቅር ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው፡፡ የአለም አስተሳሰብና የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብ ፍፁም የተለያዩ ናቸው፡፡
አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ማርቆስ 12፡30-31
በእግዚአብሄርት መንግስት ውስጥ የሚኖር ሰው በራሱ ላይ ጌታው እርሱ ራሱ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ ያመረውን ሳይሆን ጌታ የወደደውን ነው የሚያደርገው፡፡ ጌታ አድርግ የሚለውን ያደርጋል፡፡ ጌታ ተው የሚለውን ይተዋል፡፡
የአለም አሰራርና ክርስትና አብረው የማይሄዱ በጣም የተለያየ አሰራር ስላላቸው ጌታን የሚቀበል ሰው ንስሃ መግባት አለበት፡፡ ጌታን የሚቀበል ሰው የአስተሳሰብ ለውጥ ካላመጣ በአለም በሚኖርበት አስተሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ልኑር ካለ የማይሆን ነገር እየሞከረ ነው፡፡ ሰው ጌታን ሲቀበል የእግዚአብሄርን ቃል በመቀበል ከአለማዊ አስተሳሰብ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ ወደ ኋላ ካልዞረ እግዚአብሄር ያዘጋጀለት በረከት ውስጥ መግባት ያቅተዋል፡፡
ንስሃ ማለት ባዶ ሃይማኖታዊ ስርአት መፈፀም ሳይሆን አለማዊ አስተሳሰብ መለውጥ መንገድን መለወጥ ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ እንደ አለማዊነት አሰራር በመኖር ሊሳካለት አይችል፡፡
ሰው ወደጌታ ሲመጣ መጀመሪያ መረዳት ያለበት ሁለቱ መንግስታት ፍፁም የተለያዩ እንደሆኑና በአለማዊ አሰራር በእግዚአብሄረ መንግስት መቀጠል እንደማይቻል አስተሳሰቡን መለወጥ እንዳለበት ነው፡፡
እውነተኛ ንስሃ ያልገባና የአለምን አሰራር ጥሎ በእግዚአብሄር መንግስት አሰራር በቃሉ ለመኖር ልቡን ያላዘጋጀ ሰው በክርስትናው ሊዘልቅ አይችልም፡፡
ንስሃ ጌታን ስንቀበል የምናደርገው የአንድ ጊዜ ድርጊት ሳይሆን የህይወት ዘይቤ ነው፡፡ ንስሃ ጌታን ሲቀበል ብቻ የሚገባው ነገር ሳይሆን አለማዊ ሃሳቡን በእግዚአብሄር ቃለ ለመለወጥ ልብን ሁል ጊዜ ማዘጋጀት ነው፡፡ የንስሃ ህይወት አለማዊ አስተሳሰብን ጥሎ የእግዚአብሄርን ቃል ለመቀበል ትሁት መሆን ማለት ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስን ተቀብሎ ለዳነ ሰው ወደበረከት መግቢያው ብቸኛው መንገድ የንስሃ ህይወት ነው፡፡ ሰው በማንኛውን ጊዜ እንደቃሉ ያልሆነውን ሃሳቡን ትቶ ለእግዚአብሄር ቃል የሚገዛ ልብ ከሌለው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሊባረክ አይችል፡፡
ሰው በማንኛውም ጊዜ የሚያውቀውን እውቀት ለእግዚአብሄር መንግስት እውቀት ለመተው የንስሃ ህይወት ያስፈልገዋል፡፡ ሰው በአለም ከኖረበት አስተሳሰብ ወደ እግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብ ለመለወጥ ሁሌ በትህትና ሊኖር ይገባዋል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ሃጢያት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የህይወትፍሬ #መናገር #ቅባት #ትግስት #መሪ

የአእምሮ ብስለት ይጠይቃል

daisys-1024x393አንዳንድ ጊዜ ከምናስበው በላይ በአእምሮ ያለመብሰል በህይወታችን ሲንፀባረቅ ይታያል፡፡ ችግሩ ደግሞ አብዛኛው ሰው በሳል የሆነ ይመስለዋል፡፡ በሳል የሆነ የመሰለው ሰው ከእግዚአበሄር ቃል የብስለቱን መጠን መለካትና በእግዚአብሄር ቃል ወደከፍ ያለ የብስለት ደረጃ ለማደግ መትጋት ይገባዋል፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ቆሮንቶስ 14:20
ብስለታችንን የምንለካባቸው መንገዶችና በሳል ሰው ያለው አመለካከት ተዘርዝረዋል፡፡
· በሳል ሰው ለልዩነት አክብሮት ያለው ነው ያልበሰለ ሰው ከእርሱ የተለየ ማንኛውም ነገር ስህተት ይመስለዋል፡፡ ሰውን ሁሉ ተመሳሳይና አንድ አይነት ለማድረግ ይሞክራል፡፡ ሰው ግን ክቡር ነው እያንዳንዱ ሰው እንደ የሁኔታው ሊያዝ ይገባዋል፡፡ ስለዚህ ያልበሰለ ሰው ከእርሱ ለተለየው ሰው ምንም ቦታ የለውም፡፡
· በሳል ሰው ለትንንሽ ሰዎች ባለው አክብሮት ይታወቃል በሳል ሰው ራሱን በሚገባ ስሚያውቅ ሌሎችን ለመድረስ ሰዎችን አይመርጥም፡፡ በሳል ሰው ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሌላ በምንም ነገር አይመዝንም፡፡ በሳል ሰው ሰውን የሚያውቀው በክርስቶስ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ሮሜ ሰዎች 12፡16
· በሳል ሰው የራሱን ሃሳብ ብቻ አይፈልግም በሳል ሰው የሌሎችም ሃሳብ ቢደረግ እንደሚሳካ ያምናል፡፡ በሳል ሰው በሌሎችም እግዚአብሄር እንደሚጠቀም ያምናል፡፡ በሳል ሰው ለአንድነት ራሱን ትሁት ያደርጋል፡፡
በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ፊልጵስዩስ 2፡1-2
· በሳል ሰው በደረሰበት ቦታ ሁሉ ላለው ስልጣን እውቅና ይሰጣል፡፡
በሳል ሰው የስልጣንን ጥቅምና አላማ ስለሚረዳ ለስልጣን አክብሮት አለው፡፡ በሳል ሰው ስልጣንንየሚያከብረው ለታይታ ሳይሆን ሁልጊዜ ነው፡፡
እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው። ማቴዎስ 8፡9
· በሳል ሰው ለቁሳቁስ ዝቅተኛ አመለካከት ያለው ሰው ነው፡፡ ቁሳቁስን የሚያከብር ሰው በሳል ሰው አይደለም፡፡ በሳል ሰው ቁሳቁስ ካላቸውን ደረጃ በላይ አጋኖ አያያቸውም፡፡ በሳል ሰው ከቁስና ከውጭ እይታ በላይ ለልብ እውቅና ይሰጣል፡፡
ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡7-8
እርስዎም ስድስተኛውን ይጨምሩበት ?
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ቁሳቁስ #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ
%d bloggers like this: