Category Archives: evangelism

በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም ይሰደባል

your will.jpg

በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ። ወደ ሮሜ ሰዎች 2፡24

የምንኖረው ለራሳችን አይደለም፡፡ የምንኖረው ለጌታ ነው፡፡

ከእኛ አንድ ስንኳ ለራሱ የሚኖር የለምና፥ ለራሱም የሚሞት የለም፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡7

እኛ በሃጢያታችን ምክንያት ሟች ነበርን፡፡ አሁን የምንኖረው ስለእኛ ለሞተልን ለጌታ የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡

በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15

በክርስቶስ ስም ተጠርተናል፡፡ የክርስቶስንም ስም ተሸክመን እንኖራለን፡፡

ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ የሐዋርያት ሥራ 9፡15

የምናደርገው ነገር ሁሉ ክርስቶስን ያከብራል ወይ ክርስቶስን ያሰድበዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንኖርና መልካም ነገር ስናደርግ ሰዎች የተሸከምነውን የክርስቶስን ስም ነው እንጂ እኛን አያዩም፡፡ ክፉም ነገር ስናደርግ የተሸከምነውን የኢየሱስን ስም እንጂ እኛን አያዩም፡፡

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡16

የእግዚአብሄርን መንግስት ስም እንደተሸከመ ሰው በሃላፊነት እንኑር፡፡ የእግዚአብሄርን ልጅ የክርስቶስን ስም እንደተሸከመ ሰው በጥንቃቄ አንመላለስ፡፡ የእግዚአብሄርን ስም እንደተሸከመ ለመንግስቱ ሃላፊነት እንደሚሰማው ሰው እናስብ እንናገር እናድርግ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ስም #ይመሰገናል #ይሰደባል #ይከብራል #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

የብርሃን ሸክም

church leader.jpgእናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡14-16

ለእይታ ብርሃን በጣም እስፈላጊ ነገር ነው፡፡  ሰው አይን ስላለው ብቻ አያይም፡፡ አይን ያለው ሰው ለማየት ብርሃን ያስፈልገዋል፡፡ ሰው ካለብርሃን ምንም ነገር ማየት አይችልም፡፡ ሰው ቀለምን እንዲለይ ብርሃን ያስፈልገዋል፡፡ ሰው እንዲያይ ብርሃን ያስፈልገዋል፡፡

ካለብርሃን ሰው ማየት ስለማይችል የብርሃንነት ሃላፊነት በጣም ወሳኝ ሃላፊነት ነው፡፡

ኢየሱስ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ሲል በቃላችንና በኑሮዋችን ሰው እንዲያይ ማድረግ እንደምንችል እየነገረን ነው፡፡ ኢየሱስ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ሲል ብርሃን ያለበትን ወሳኝ ሃላፊነት እያስታወሰን ነው፡፡

እኛ ካላሳየነው በጨለማ የሚሄደው ሰው ነገሮችን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በጨለማ ያለ ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን እግዚአብሄርን ካላሳየነው በጨለማ ያለው ህዝብ እግዚአብሄርን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በጨለማ ያለ ህዝብ የዘላለምን ህይወት ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በመታለል የሚኖረው ህዝብ እውነትን ማየት አይችልም፡፡ እኛ ብርሃን ሆነን ካላሳየነው በሰይጣን ግዛት ውስጥ በጭቆና የሚኖረው ህዝብ የእግዚአብሄርን ፍቅርና ይቅርታ ማየት አይችልም፡፡

ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው። የዮሐንስ ወንጌል 8፡12

ኢየሱስ የአለም ብርሃን ሆኖ በምድር ላይ ተመላልሷል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ እግዚአብሄርን አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የዘላለም ህይወትን አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የነበርንበትን የውድቀት ህይወት አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የእግዚአብሄርን የመዳኛ መንገድ አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ ዋጋ የሚሰጠውንና የማይሰጠውን ነገር ለይቶ አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ የእግዚአብሄርን መንግስት አሳይቶናል፡፡ ኢየሱስ ብርሃን ሆኖ ፍጸፃሜያችንን አሳይቶናል፡፡

በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። የማቴዎስ ወንጌል 4፡14-16

አሁንም እኛ ብርሃን ሆነን እግዚአብሄርን መፍራትን ለሌሎች እናሳያለን፡፡ እግዚአብሄርን በመፍራት ሌሎች እግዚአብሄርን እንዲፈሩ በኑሮዋችን እናስፈራራለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የሚኖሩትን የሃጢያት ህይወት እንገልጣለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ክርስትና እንደሚቻል ለሰዎች መገለጥን እንሰጣለን፡፡

ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ዮሃንስ 3፡19-20

እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች እግዚአብሄርን የሚያገኙበትን መንገድ እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን በሃጢያት ምክኒያት ሰዎች ያሉበትን ውድቀት እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የተዋረደውን ከከበረው እንዲለዩ እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የዘላለም ህይወትን እንዲያዩ እናደርጋሃል፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር እንዲለዩ እናደርጋለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን ሰዎች የእግዚአብሄርን ፍቅር እንዲያዩት እናደርጋለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን የእግዚአብሄርን ሃይል ብርታት እናሳያለን፡፡ እኛ ብርሃን በመሆን የሚያድነውን የእግዚአብሄርን ፀጋ እናሳያለን፡፡

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ወደ ቲቶ 2፡11

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡14-16

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ጨለማ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ምስክርነት #አማርኛ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ጥሪ #ክህንነት #ስራ #መልክተኛ #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #ፌስቡክ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሚሰክረው ልጅ እናት ታሪክ

church leader.jpgኬኔት ሃገን የተባሉ የእግዚአብሄር ሰው በአንዱ ስብከታቸው ላይ ስለ አንድ ሴት ታሪክ ያናገራሉ፡፡

በየቤተክትርስትያን እየተጋበዝኩ በማገለግልበት ጊዜ ከስብከት በኋላ አንድ ሴት መጥታ ለልጄ ፀልይለት ብላ ጠየቀችኝ፡፡ ልጅዋ ስላለበት ሁኔታም ስረታስረዳኝ ህይወቱ በጣም የተበላሸ ነው ፣ በጣም ይሰክራል ፣ ከምሽቱ 8 ሰአት ነው ወደቤት የሚመጣው ብላ ነገረችኝ፡፡

እኔም ታሪክዋን ከሰማሁ በኋላ ለልጅዋ እንደማልፀልይለት ነገርኳት፡፡ ያንን ያልኩት ስላላዘንኩ ሳይሆን የእርስዋን ትኩረት ለማግኘት ስለፈለኩ ነበር ይላሉ የእግዚአብሄር ሰው ኬኔት ሃገን፡፡

እንዴት ስትለኝ አልፀልይለትም ነገር ግን አንቺ ሂጂና ለልጅሽ ፍቅርን አሳዪው ብዬ መክርኳት፡፡

ከቆየ በኋላ አንድ ቀን ያቺ ሴት ወደእኔ መጥታ ታሳውሰኛለህ ወይ ብላ ጠየቀቺኝ፡፡ አይ አላስታውስሽም እልኳት፡፡ በጣም ለሚሰክረው ልጄ እንዲለወጥ እንድትፀልይልኝን የጠየቅኩህ ሴት ነኝ ብላ አስታወሰቺኝ፡፡

ፍቅርን አሳዩው ባልከኝ መሰረት አትስከር ብዬ መጨቃጨቄን ትቼ የእናትነት ሃላፊነቴን ብቻ መወጣት ጀመርኩ፡፡ እናት ለልጅ የምታደርግለትን ነገር ሁሉ አደርግለት ጀመር፡፡ እንደ ቤተሰቡ ካህን እንዲህ አድርግ እንዲህ አታድርግ የሚለውን ጭቅጭቅ ትቼ በራሴ ሃላፊነት ላይ ማተኮር ጀምረኩ፡፡

አንድ ሌሊት እንዲሁ ሰክሮ መጥቶ በነጋታው እሁድ ነበርና ቤተክትርስትያን ውሰጂኝ አለ፡፡ እኔም አይ ትላንትና አምሽተህ ነው የገባኸው ደክሞሃል እረፍ ብለው ሊቀበልኝ አልቻለም፡፡ እኔ ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ ብሎ ጌታን ተቀበለ በማለት የፍቅር ህይወት የተበላሸ ህይወት የነበረውን ልጅዋን እንዴት እንደለወጠ መሰከረችልኝ በማለት ይመሰክራሉ፡፡

የሰው የፍቅር ህይወት ከምንም ንግግር በላይ ሃይል አለው፡፡ ፍቅርን ስናሳየው ሰው ይማረካል፡፡ ፍቅር የማይገባው ፍቅር የማይማርከው ሰው የለም፡፡

ምንም አያውቅም የምንለው ምንም አይረዳም የምንለው ሰው ፍቅርን ያውቀዋል፡፡ በክፉ የተያዘው አለም ፍቅርን ይለያል፡፡

እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡35

ይህ ቃል ከዚህ የእግዚአብሄር ቃል ጋር ይስማማል፡፡

እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡1-2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ምስክርነት #ኑሮ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው

veiled.jpgወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው። ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4

ወንጌል ግልፅ ነው፡፡ ወንጌል ኢየሱስ ስለሰው ልጆች ሃጢያት እንደሞተ እንደተቀረ በሶስተኛው ቀን ሞትን ደል አድርጎ ስለመነሳቱ ነው፡፡

ይህንን ለመረዳት የማያስቸግር ቀላል እውነት የማይረዱ ሰዎች አሉ፡፡ ይህንን ቀላል እውነት ተረድተው ከመዳን ይልቅ በመቃወም ሳያውቁት ለጥፋት የተዘጋጁ ሰዎች አሉ፡፡

ሰይጣን የሰው ልጆች ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ እንጂ ሌላ አላማ የለውም፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰዎች ህይወት እንዲሆንልንና እንዲበዛልን የመጣውን ኢየሱስን እንዳይረዱና እንዳይድኑ ሰይጣን የልባቸውን አይኖች በተለያየ የስህተት ሃሳብ ያጨልማል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተቀብለው እንዳይድኑ ከወንጌል ሌላ የተሳሳተ አማራጭ ሃሳብ ይሰጣቸዋል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን አምነት ከዘላለም ፍርድ እንዳያመልጡ የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ ያቃልልባቸዋል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተረድተው እንዳይከተሉ ክርስትና ሞኝነት በማስመሰል አእምሮዋቸውን ያጨልማል፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ተረድተው እንዳይድኑ በተለያየ ነገር ባተሌ ያደርጋቸዋል፡፡

ብዙ ነገሮችን የሚረዱ ሰዎች ይህንን ቀላል እውነት መረዳት ሳይችሉ ሲቀሩ በጣም እንገረማለን፡፡ ብዙ ነገሮችን የተመራመሩና ያገኙ ሰዎች ይህንን ውስብስብ ያልሆነ ለመረዳት የማያዳግት እውነት ማየት ሲሳናቸው ያስገርማል፡፡

ሰይጣን የሰው ልጆች ጠላት ነው፡፡ ሰዎች ተነግሮዋቸው ተመስክሮላቸው ይህንን እውነት የማያዩበት ምክኒያቱ የማያምኑትን ሃሳብ ያጨለመው ሰይጣን ስለአለ ብቻ ነው፡፡

ሰይጣን የማያምኑትን ሃሳብ ባሳወረ ቁጥር የሚያዩበትን የተገለጠልንን ብርሃን እናካፍላቸዋለን፡፡ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰዎች ብርሃንን ከማካፈል ቸል አንልም፡፡ አንድ ቀን ጨለማውን የሚገፍ ብርሃን ይታያቸዋል፡፡

ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ሐዋርያት ሥራ 26፡22-23

በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ጨለማ #አሳወረ #ብርሃን #ወንጌል #መመስከር #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በምድር ላይ ያለንበት ዋነኛው አላማ

evangelism8.jpgኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20

ብዙ ጊዜ የሚባል አባባል አለ፡፡ በምድር ላይ የምንፈፅመው የወንጌል አላማ ባይኖረው ልክ በክርስቶስ እንደዳንን እግዚአብሄር ወደ ራሱ ይሰበስበን ነበር፡፡ እውነት ነው ከምንም ነገር በላይ በምድር ላይ የወንጌል አደራ አለብን፡፡ በምድር ያለነው እግዚአብሄርን በሚመስል ኑሯችን ለአለም የመዳንን መንገድ ለማሳየት ነው፡፡

እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ሐዋርያት ሥራ 16፡17

በምድር ያለንው ብርሃን ልንሆን ነው፡፡ በምድር ያለነው የምድር ጨው ለመሆን ነው፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ማቴዎስ 5፡13-14

በምድር ያለነው በስራችን የእግዚአብሄርን መልካምነት ለማንፀባረቅ ነው፡፡ በምድር ያለነው የእግዚአብሄርን መንግስት ለመግለጥ ነው፡፡

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡16

በየእለት ነፍሳችንን የምንክደው በኑሮና በቃል ወንጌልን ለመሰበክ ነው፡፡

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን፥ እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌልን መመስከር በሃሴት እፈጽም ዘንድ፥ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፡፡ ሐዋሪያት ሥራ 20:24

በምድር ያለነው ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ ነው፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-19

በምድር ያለነው የክርስቶስ አምባሳደሮች በመሆን ነው፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20

በምድር ላይ ሌሎች ሌሎች የምናደርጋቸው አላማዎች ቢኖሩንም ወንጌልን ስንኖርና ስንሰብክ እግረ መንገዳችን የምናደርጋቸው ነገሮች እንጂ ዋና ነገሮች አይደሉም፡፡ በምድር ላይ ያለንበት ዋናው ምክኒያት ወንጌልን መስበክ ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ወንጌልን ስበኩ አስፈላጊ ከሆነ ቃልን ተጠቀሙ

evangelism7.jpgይህ የአሲሲ ቅዱስ ፍራንሲስ ንግግር ነው፡፡ ወንጌልን ለመስበክ መሰረት የሆነንን የወንጌልን ህይወት ለማሳየት የተነገረ ንግግር ነው፡፡ የወንጌል ቃል ካለወንጌል ህይወት ሙሉ አይሆንም ለማለት ነው፡፡ ይህ ማለት የወንጌል ስብከት መሰረቱ የወንጌል ህይወት ነው ማለት ነው፡፡ የወንጌል ስብከት የንግግር ቃል ብቻ ሳይሆን ሙሉ የህይወት መሰጠት እንደሚጠይቅ ለማሳየት ነው፡፡

ወንጌልን ለሰዎች ስንናገር ሰዎች የምንነግራቸውን ነገር ከማመናቸው በፊት ስለንንግራችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ስለምንሰብካቸው ቃል ትክክለኝነት የሚያረጋገጡት ደግሞ ህይወታችንን አይተው ነው፡፡

የምንኖረው ኑሮ ከምንሰብከው ስብከት ጋር አብሮ ካልሄደ ሰዎች ይህንን ወንጌል አይቀበሉም፡፡ የምንነግራቸው ቃል ከሚያውቋቸው ክርስትያኖች ህይወት ጋር አብሮ ከሄደ ብቻ ሰዎች ጌታን ለመቀበል ይወስናሉ፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ማቴዎስ 5፡13-14

ሁላችንም ወደጌታ የመጣነው ተሰብኮልን ብቻ ሳይሆን የክርስትያኖችን የህይወት ንፅህና አይተንና የሚሰበከው ቃል ከህይወታቸው ጋር አንድ መሆኑን ነው፡፡ እኛም የምንሰብካቸው ሰዎች ጌታን ለመከተል የሚወስኑት ጌታን የሚከተሉትን ሰዎች ህይወት አይተው ነው፡፡

ጌታን የሚከተል ሰው ህይወት ካላጓጓቸው የምንነግራችው ቃል አያጓጓቸውም፡፡ የህይወት ጥራታችን ካጓጓቸው ግን የምንነግራችው ነገር ሁሉ ያጓጓቸዋል እንደእኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ካለንግግር በህይወት ብቻ ለወንጌል ሊማረክ ይችላል ካለወንጌል ህይወት ግን በንግግር ብቻ ለወንጌል ሊማረክ አይችልም፡፡

እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው። 1ኛ የጴጥሮስ 3፡1-2

የክርስትናን ህይወት ስንኖር የኢየሱስ ስም ተሸክመን እንኖራለን፡፡ የተጠራነው ኢየሱስን በምድር ላይ ለመወከል ነው፡፡ የተመረጥነው የኢየሱስን ስም እንድንሸከም ነው፡፡ የተጠራነው የኢየሱስን ስም በመልካም እንድናስጠራ ነው፡፡

ጌታም፦ ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤  ሐዋርያት ሥራ 9፡15

የምናደርገው መልካም ነገር በሙሉ ሰዎች እግዚአብሄርን እንዲያመሰግኑ ወይም እንዳያመሰግኑ ያደርጋል፡፡

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡16

ራሳችንን እየካድን በፍቅር የምንኖር ከሆነ ለሰዎች ስለ ኢየሱስ የማያከራክር ፍፁም ምስክሮች እንሆናለን፡፡

እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ። እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። ዮሃንስ 13፡34-35

የምንኖረው ኑሮ ለክርስትና ምስከርነት ድጋፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ህይወታችንን በጥንቃቄ የምንኖር ከሆነ ሰዎች ጌታን እንዲከተሉ ጉልበትን እንሰጣቸዋለን፡፡ የምንኖረው ኑሮ እግዚአብሄርን በመፍራት ከሆነ ሌሎች ሰዎች እግዚአብሄርን እንዲፈሩ እናደርጋቸዋለን፡፡ እግዚአብሄርን የመፍራት ህይወታችን ሌሎች እኔስ ለምንድነው እግዚአብሄርን የማልፈራው እንዲሉ ያስገድዳቸዋል፡፡

ያለ ነቀፋ መሆናችን ፣ የዋሆች መሆናችን ፣ ነውርም የሌለብን መሆናችን ፣ ሳናንጐራጉርና ክፉም ሳናስብ ሁሉን ማድረጋችን ብቻ በጨለማው አለም እንደብርሃን እንድንታይ ያደርገናል፡፡

በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-16

እያንዳንዱ ህይወታችን በሰዎች ይታያል፡፡ አንድ ነገር ሲደርስብን የምንሰጠው መልስ በሰዎች ትኩረት ውስጥ አለ፡፡ የምንኖረው ኑሮ ለክርስትና እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡ ለወንጌል ምስክርነታችን ዋናው መሰረት ጌታን የሚከተል ሰው በየእለት ኑሮው የሚኖረው ኑሮ ምስክርነት እንጂ የሚናገረው ሃይማኖታዊ ቃልና የሚያደርገው ሃይማኖታዊ ስርአት አይደለም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ

evangelism 11.jpg

እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማርቆስ 16፡15-16

እኛ ሁላችን በጨለማ በነበርነበት ጊዜ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ወንጌልን ሊሰብክና በጨለማ ያሉትን ከእስራት ሊያወጣ ነው፡፡

ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር። ማቴዎስ 4፡17

አሰብ እኔን እንደላከኝ እንደሂ እልካችሃለሁ ይላ ኢየሰስ ፡፡

ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ ዮሃንስ 17፡18

እግዚአብሄ መንፈሱን የሰጠን በህይወትና ምሳሌነትና በቃል ወንጌልን እንድንሰብክ ነው፡፡

ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። ዮሃንስ 20፡21-22

ኢየሱስ ያለውን ስልጣን ሁሉ ትቶልን የሄደው ወንጌልን እንድንሰብክና ሰዎችን ከጨለማ እንድንታደግ ነው፡፡

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ

slide-connected.jpgበወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23

ይህን ሁሉ የማደርገው፣ ከወንጌል በረከት እካፈል ዘንድ፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው።(አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23

በአለም ላይ ሰዎች ከትልቅ ድርጅት ስለገዙት አክሲዮን ይናገራሉ፡፡ ሰዎች በአለም ላይ ስለገዙትና ስላላቸው ቦንድ በኩራት ይናገራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ለምድር ይጠቅማል፡፡

ሰው ግን የታወቁ የምድር ማህበሮች ማህበርተኛ ሆኖ ነገር ግን በወንጌል ማህበርተኛ ካልሆነ ምስኪን ሰው ነው፡፡

የምድር ጉዟቸውን መልስ ብለው ሲያዩ ፎቅ አልሰራሁም ታዋቂ አልሆንኩም ውድ መኪና አልነዳሁም ነገር ግን በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተክርስትያንን ደግፌያለሁ የሚሉ የተባረኩ ሰዎች አሉ፡፡

የምድር ጉዟቸውን መለስ ብለው ሲያዩ ተምሬ ዶክተር አልሆንኩም ነገር ግን ወንጌልን ለመስበክ ህይወቴን ሙሉ ሰጥቼያለሁ በማለት በህይወታቸው የሚረኩ ሰዎች አሉ፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9

አላገባሁም አልወለድኩም ነገር ግን በህይወቴ ሁሉ የእግዚአብሄርን ቤተክርስትያን የወንጌል ስራ ስደግፍ ኖሬያለሁ የሚሉ በሚገባ የተኖረ ህይወት የሚኖራቸው ሰዎች አሉ፡፡

በምድር ላይ የምንም ማህበር አባል ያልሆኑ የወንጌል ግን ማህበርተኛ ለመሆን ህይወታቸውን የሚያፈሱ ጉልበታቸውን ገንዘባቸውን እውቀታቸውን ጊዜያቸውን ለወንጌል ስራ የሚሰጡ የተባረኩ ሰዎች አሉ፡፡

አሁንም በ2018 ዓም ያዳነንን ወንጌል ማህበርተኛ ለመሆን የማይጠፋ የዘላለም ሽልማት ስለሚያስገኘው ስለወንጌል ሁሉንም ለማድረግ እንወስን ፡፡

በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ማኅበረተኛ #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በበረት የተወለደው ኢየሱስ በልባችን ካልተወለደ አይጠቅመንም

jesus born.jpgእግዚአብሄር ሰውን ሁሉ ፈጥሮታል፡፡ ሰው ሁሉ በሃጢያት ወድቋል፡፡ ሁሉም ሰው የእግዚአብሄር ፍጥረት ነው፡፡ ሁሉም ሰው ግን የእግዚአብሄር ልጅ አይደለም፡፡ ወይም ኢየሱስ ስለሰዎች ሁሉ በመስቀል ላይ ሊሞት በምድር ላይ ስለተወለደ ብቻ ሰው ሁሉ ከመቀፅበት የእግዚአብሄር ልጅ አይሆንም፡፡ የብቻ ሰውር ልጅ ለመሆን መመዘኛ አለው፡፡ ለእግዚአብሄር ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሄር ልጅ ለመሆን ብቸኛው መመዘኛ ኢየሱስን መቀበል ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

በበረት የተወለደው ኢየሱስ በልባችን ካልተወለደ አይጠቅመንም፡፡ ሃይማኖተኛ ልንሆን እንችላለን፡፡ ብዙ ነገሮችን ለእግዚአብሄር ብለን ልናደርግ እንችላለን፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራልንን ለእኔ ነው ብለን ኢየሱስን በመቀበል ዳግመኛ ካልተወለድን ግን የኢየሱስ በምድር ላይ መወለድ አይጠቅመንም፡፡ ኢየሱስን ያደንቀው ለነበረ ኒቆዲሞስ ለተባለ የህግ መምህር ኢየሱስ ያለው ይህንን ነው፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ዮሃንስ 3፡3፣5

በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ገናን በፍቅር ልናከብረው እንችላለን፡፡ ኢየሱስን ከልባችን ልናደንቀው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ በልባችን ካልኖረ ወደ ምድር የመጣበትንና ከድንግል ማርያም የተወለደበትን አላማ ስተነዋል፡፡

ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ዮሃንስ 1፡21

ኢየሱስ በምድር ላይ ስለተወለደ ብቻ ከመቀፅበት አንድንም፡፡ ኢየሱስ ስለተወለደ ብቻ ሰዎች ከመቀፅበት የሚድኑ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ ለፍጥረት ሁሉ ወንጌልን ስበኩ ብሎ ባላዘዘን ነበር፡፡ የምስራቹን ቃል ሰምተው የሚያምኑ ብቻ ናቸው የሚድኑት፡፡

እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማርቆስ 16፡15-16

የሚድኑት ኢየሱስን እንደ አዳኝ የተቀበሉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ የምንም ሃይማኖት ተከታዮች ስለሆንን ብቻ አንድንም፡፡ ከሃጢያት የሚያድነን ኢየሱስን እንደ አዳኝና ጌታ አድርገን መቀበላችን ብቻ ነው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16

ሰዎች በየእለቱና በየደቂቃው ኢየሱስን እየተቀበሉና እየዳኑ ነው፡፡ እኛ ግን ኢየሱስን ወደ ልባችን ሳናስባውና በልባችን ሳይወለድ ኢየሱስ በምድር ላይ ስለተወለደ ብቻ ድነናል ብለን ካሰብን ተታለናል፡፡ የኢየሱስ መወለድ እንዲጠቅመን ወንጌልን ማመን ይጠበቅብናል፡፡ የሚያድነን የእግዚአብሄር ሃይል የኢየሱስ ስለሃጢያታችን መሞቱን የምስራች ማመን ነው፡፡

በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ሮሜ 1፡16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ገና #ልብ #ዳግመኛመወለድ #የማዳንሃይል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች

gie5qj78T.jpgመልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ። ሉቃስ 2፡10-14

ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን

ኢየሱስ የተወለደው ለህዝብ ሁሉ ነው፡፡ ኢየሰስ የተወለደው ለፍጥረት ሁሉ ነው፡፡ ኢየሱስ የመጣው ከሴት ለተወለደ ሰው ሁሉ ነው፡፡

ታላቅ ደስታ የምሥራች

የኢየሱስ መወለድ የምስራች ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ መልካም ዜና ነው፡፡

መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? ሮሜ 10፡15

አትፍሩ

የኢየሱስ መወለድ የሰውና የእግዚአብሄር መታረቅ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ የኢየሱስ መወለድ ድስ ይምንሰኝበት ዘና የምንልበት እንጂ የምንፈራበት አይደለም፡፡ ፍርሃት ነግሶ ከነበረ ፍርሃት ከዚህ በኋላ አይኖርም፡፡

በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። ሉቃስ 1፡74-75

ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና

የተቀባ አዳኝ ጌታ የሆነ ኢየሱስ ተወልዶልናል፡፡

ክብር ለእግዚአብሔር

ሰው በእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሯል፡፡ ሰዊች ኢየሱስን በመቀበል የእግዚአብሄ ልጆች ይሆናለሁ ወደ ልጅነት ክብራቸው ይመለሳሉ፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ሲቀበሉ እግዚአብሄርን ማከበር ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ክብር መስጠት የሚችለው ሰው ኢየሱስን በመጀመሪያ በመቀበሉ ነው፡፡

ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡23

ሰላምም በምድር

ሰው እውነተኛ ሰላምን የሚለማመደው በኢየሱስ ነው፡፡ በኢየሱስ ያለውን ሰላም ያላየ ሰው እውነተኛውን ሰላም ገና አላየም፡፡ ኢየሱስ የሚሰጠውቅ ሰላም አለም እንደሚሰጠው አይደለም፡፡

ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። ዮሃነስ 14፡27

ለሰውም በጎ ፈቃድ

እግዚአብሄር ለሰዎች ያለውን በጎ ፈቃድ ያሳየው በኢየሱስ ነው፡፡ ሰው ሁሉ እረኛ እንደሌለው በግ ተቅበዝብዞ ጠፍቶ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሄር ኢየሱስን ላከልን፡፡ የእግዚአብሄር በጎ ፈቃድ የተገለጠው በኢየሱስ መወለድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሰዎች ያለውን ርህራሄና ልብ ያየነው በኢየሱስ መወለድ ነው፡፡

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መወለድ #ገና #ክሪስማስ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #አላማ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አትፍሩ #የምስራች #ደስታ #ክብር #ሰላም #በጎፈቃድ

%d bloggers like this: