Category Archives: heaven

ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን

victorian-poor-children-clothes.jpg

በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። 1 ቆሮንጦስ 15፡19

እኛ በአለም እንኖራለን እንጂ ከአለም አይደለንም፡፡ እኛ ከአለም አይደለንም፡፡

እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም። የዮሐንስ ወንጌል 17፡16

ይህ ምድር ጊዜያዊ መኖሪያችን ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ ሰው በምድር በምድር የተቀመጠው እንዲያስተዳድርና እንዲገዛ ብቻ እንጂ ሰው ከምድር ስለሆነ አይደለም፡፡ ሰው የወጣው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ከምድር አይደለም፡፡

በምድር ያለነው ወደ አለም ተልከን ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው የስራ ድርሻና ተልእኮ ስለለን ነው፡፡

ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 17፡18

በምድር የሚያቆየን የተላክንበት አላማ እንጂ ሌላ አላማ አይደለም፡፡ ዓለም የተገባችን አይደለችም፡፡

ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። ወደ ዕብራውያን 11፡38

ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዘላለም ህይወት ነው፡፡ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለእግዚአብሄር ልጅነት ህይወት ነው፡፡ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለአጭር የምድር ኑሮ ብቻ አይደለም፡፡ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው በምድር ለመኖር ከሆነ ከሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡ በክርስቶስ ያመንነው በምድር ደልቶን ለመኖር ከሆነ ከሁሉ በላይ የሚታዘንልን ምስኪኖች ነን፡፡

ክርስቶስን የተከተልነው ትልቅ ቤት ውስጥ ለመኖርና የተሻለ መኪና ለመንዳት ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡

ክርስቶስን የተከተልነው ዝነኛ ለመሆን ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን፡፡

የእምነት አባቶች በምድሪቱ እንግዶችና መጻተኞች ክፉ ውድድር ውስጥ ሳይገቡ በእምነት ኖሩ፡፡

እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ወደ ዕብራውያን 11፡13-14

የእምነት አባቶች በምድሪቱ እንግዶችና መጻተኞች ሆነው ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሳቸውን ሳያጠላልፉ በእምነት ኖሩ፡፡

የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡4

ምክኒያቱም የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቁ ነበርና፡፡

አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡16

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ትዳር #ንግድ #ወታደር #ዘማች #መዋረድ #መከራ #ፈተና #መፅናት #መታገስ #እንግዶች #መጻተኞች #ምስኪኖች #ተስፋ #አለም #የተገባ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

የመንግስቱ አስተሳሰብ

42b43-stairway-to-heaven-widescreen-wallpaper-free-download.jpgበምድር ላይ ህዝብን የሚያስተዳድርና የሚገዛ መንግስት እንዳለ ሁሉ በመካከላችን የእግዚአብሄር መንግስት አለ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በአይን የማይታይ በስፍራ የማይወሰን መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ንጉስ ያለው ህዝብና የራሱ የአሰራር ህግ ያለው መንግስት ነው፡፡

ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡20-21

በተቃራኒው አለም ማለት ሰይጣን የሚገዛበት የአሰራር ስርአት ነው፡፡ አለም ማለት ከተማ ማለት ሳይሆን ሰው ባራሱ ላይ ጌታ የሆነበት ከእግዚአብሄር መንግስት ተቃራኒ የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡

ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16

የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብና የአለም አስተሳሰብ እጅግ የተለያዩ ናቸው፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡17

አለም ማለት ከእግዚአብሄር ቃል የተቃረነ የአስተሳሰብ ዘይቤና ዋጋ አመለካከት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብ ከአለም አስተሳሰብ የሚለይበት አስር መንገዶች

  • የፍቅርና ራስ ወዳድነት አስተሳሰብ

የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳብ እግዚአብሄርንና ሰውን ሁሉ የመውደድ አስተሳሰብ ነው፡፡ ከእግዚአብሄርና ከሰው ጋር በአክብሮት የምንኖርበት ስርአት ነው፡፡ የአለም መንግስት ግን ራስ ተኮር የሆነ እያንዳንዱን ነገር ከግል ጥቅም አንፃር ብቻ የሚመዘንበት ስርአት ነው፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ቆላስይስ 1፡13-14

  • የብርሃንና የጨለማ መንግስት

የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ምሪት የተሞላ ነው፡፡ የአለም መንግስት ግን የእግዚአብሄር ምሪት የሌለበት ሰዎች መቼ እንደሚደናቀፉ የማያውቁበት የጨለማ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የግልፅነት መንግስት ሲሆን የአለም መንግስት ድብቅ መንግስት ነው፡፡

ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል። ዮሃንስ 3፡19-21

  • የእውነትና የሃሰት አስተሳሰብ

የእግዚአብሄር መንግስት የእውነት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ከእግዚአብሄርን ቃል የመጀመሪያውን የእግዚአብሄርን ሃሳብ የሚከተል መንግስት ነው፡፡ የአለም አሰራር ግን ላይ ላዩን ብቻ ማስተካል የሚፈልግ ውስጡን ግን የማያጠራ የሃሰት ማስመሰያ አስተሳሰብ ነው፡፡ የአለም አስተሳሰብ ውጭውን ብቻ በማሳመር የሚያታልል ሲሆን የእግዚአብሄር መንግስት ትኩረቱ የውስጥ የልብ ንፅህና ነው፡፡

ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15

  • ማገልገልና የመገልገል መንገድ

በእግዚአብሄር መንግስት ባለን ነገር ሁሉ ለማገልገልና ሌሎችን ለመጥቀም የምንኖረው ኑሮ ሲሆን የአለም አስተሳሰብ በስልጣናችን ተጠቅመን ለመጠቀምና ሰዎች እንዲያገለግሉንና እንዲጠቅሙን የምንሄድበት አስተሳሰብ ነው፡፡

  • የመዝራትና የማከማቸት አስተሳሰብ

የእግዚአብሄር መንግስት የመዝራትና የመስጠት አስተሳሰብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሌሎችን በመባረክና በማንሳት የሚረካ አስተሳሰብ ነው፡፡ በአለም ግን ሰው ደህንነት የሚሰማው ሲያከማች ሲሰበስብ ነው፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ ማቴዎስ 6፡19-20

  • የይቅርታና የበቀል አካሄድ

የእግዚአብሄር መንግስት የምህረትና የይቅርታ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእጅጉ ይቅር የተባሉ ሰዎች በተራቸው ሌላውን ይቅር ለማለት የተዘጋጁ ሰዎች መንግስት ነው፡፡ የአለም መንግስት ግን የበቀልና የተንኮል አስተሳሰብ የገነነበት ሲሆን አንዱ በሌላው ላይ ተረማምዶ ወደላይ ከፍ የሚልበት ክፉ አሰራር ነው፡፡ በአለም አስተሰታሳብ በፊትህ የሚቆመውን አስወግደህ ማለፍ አዋቂነት ነው፡፡

  • የመተባበርና የፉክክር አስተሳሰብ

በእግዚአብሄር መንግስት ለሌላው መነሳትና ማሸነፍ በደስታ የሚሰራበት ሲሆን በአለም አሰራር ግን ሌላውን በመጣል ከሌላው በላይ ከፍ ብሎ ለመታየት በትእቢት የሚኬድበት የአሰራር ዘይቤ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የሌላውን ጉድለት ለመሙላት የመሄድ አስተሳሰብ ሲሆን የአለም አስተሳሰብ ሌላው ሁሉ ለእርሱ እንዲሰራለት ራስን ብቸኛ እንደተመረቀ መቁጠር ነው፡፡

  • ዘላለማዊና ጊዜያዊ አስተሳሰብ

የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብ የሚመዘነው በዘላለማዊ እይታው ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚኖር የእግዚአብሄር ልጅ ጊዜያዊውን ደስታ ንቆ የሚኖረበት ህይወት ነው፡፡ የአለም አስተሳሰብ ግን ለጊዜያዊው ነገር ህይወትን የማባከን ህይወት ነው፡፡

  • የትህትናና የትእቢት አስተሳሰብ

የእግዚአብሄር መንግስት መዋረድና የዝቅታን አስተሳሰብን ሲያስተምር የአለም አስተሳሰን ግን የትእቢት የከፍታ የንቀትና  አስተሳሰብን ያራምዳል፡፡ በአለም አሰራር ትህትና ሽንፈትና ደካማነት ነው፡፡

  • የየዋህነትና የብልጠት አካሄድ

የእግዚአብሄር መንግስት አስተሳሰብ ሃይልን ለክፉ ነገር ያለመጠቀም ውሳኔ ሲሆን በአለም ግን ብልጠትና አቋራጭ ተጠቅሞ ወደላይ ከፍ ማለትን የሚያበረታታ አሰራር ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሰው ስለ ደህንነቱ በእግዚአብሄር ላይ የሚደገፍበት ሲሆን የአለም አሰራር ግን ባለህ ሃይል እና ተሰሚነት ሁሉ ተጠቅመህ ሌላውን በመጣልና በማዋረድ ከፍ የማለት አስተሳሰብ ነው፡፡ በአለም አንተ ከፍ እንድትል ሌሎች መዋረድ አለባቸው፡፡

ስለዚህ ነው ኢየሱስ የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ እያለ ይሰብክ የነበረው፡፡ በአለም አስተሳሰብ በእግዚአብሄር መንግስት ሊሳካልን አይችልም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ንስሃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ሃጢያት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የህይወትፍሬ #መናገር #ቅባት #ትግስት #መሪ

ሰማይ በጨረፍታ

heaven 2.jpg10-11 በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤

12 ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ፥ የአሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።

13 በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥ በሰሜንም ሦስት ደጆች፥ በደቡብም ሦስት ደጆች፥ በምዕራብም ሦስት ደጆች ነበሩ።

14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።

15 የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።

16 ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፥ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት አሥራ ሁለትም ሺህ ምዕራፍ ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።

17 ቅጥርዋንም ለካ፥ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ፥ እርሱም በመልአክ ልክ።

18 ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፥ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።

19 የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥

20 አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፥ አሥረኛው ክርስጵራስስ፥ አሥራ አንደኛው ያክንት፥ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።

21 አሥራ ሁለቱም ደጆች አሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እየአንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።

22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።

23 ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።

24 አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤

25 በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥

26 የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ።

27 ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።

ራእይ 21፡10-27

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #ሰማይ #ወርቅ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ተስፋ #እንቁ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መዝገብህ ባለበት ልብህ

ልብህ የሚሄደው መዝገብህ ባለበት ቦታ ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው ሃብቱና ልቡ ተነጣጠለው አይኖሩም፡፡ መዝገብህ ባለበት ልብህ በዚያ ይሆናል፡፡ መዝገብህ በሌለበት ቦታ ልብህ በዚያ አይኖርም፡፡ ትኩረትህ ሁሉ የሚኖረው የኔ የምትለው የምትጠነቀቅለት ነገር ባለበት ቦታ ነው፡፡ ስለዚህ አለ ኢየሱስ ልባችሁ በሰማይ እንዲያ…

Source: መዝገብህ ባለበት ልብህ

መዝገብህ ባለበት ልብህ

publication1ልብህ የሚሄደው መዝገብህ ባለበት ቦታ ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው ሃብቱና ልቡ ተነጣጠለው አይኖሩም፡፡ መዝገብህ ባለበት ልብህ በዚያ ይሆናል፡፡
መዝገብህ በሌለበት ቦታ ልብህ በዚያ አይኖርም፡፡ ትኩረትህ ሁሉ የሚኖረው የኔ የምትለው የምትጠነቀቅለት ነገር ባለበት ቦታ ነው፡፡ ስለዚህ አለ ኢየሱስ ልባችሁ በሰማይ እንዲያተኩር ወሳኙ መንገድ ፣ ልባችሁ በሰማይ እንዲቀር የሚረዳው ነገር ፣ ልባችሁ በሰማይ ትኩረት እንዲያዝ ከፈለጋችሁ መዝገባችሁን በሰማይ አስቀምጡ እያለን ነው፡፡
በምድር ላይ የምንደገፍበት ነገር ሲጠፋ ልባችን ወደ ሰማይ መዝገብ ያዘነብላል፡፡ ነገር ግን የምድር ሃብታችን ሲበዛና በዚያም ለመታመን ስንፈተን ልባችንም በምድር ላይ ይቀራል፡፡ ልባችንን የምንጥልበት ሃብታችን በምድር ላይ እየበዛ በሄደ መጠን ልባችን ከሰማይ ላይ እየተነሳ ይሄዳል፡፡ መዝገባችን በምድር ሲሆን ልባችንም በምድር ይሆናል፡፡ መዝገባችን በሰማይ ሲሆን በቅፅበት ልባችንም በሰማይ ይሆናል፡፡
ብዙ ጊዜ ልባችን ከሰማይ በመነሳት እንፈተናልን፡፡ በዚህ ፈተና ያለመውደቅ መንገዱን ኢየሱስ ያስተምራል፡፡ መዝገብን በምድር የመሰብሰብ ጉዳቱ ልባችንን ከሰማይ ላይ እንዲነሳ ሰማይ ትኩረታችን እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ መዝገብን በሰማይ የመሰብሰብ ጥቅሙ ልባችንን በሰማይ ይሰበስብልናል፡፡
ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ማቴዎስ 6፡19-21
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መዝገብ #ሃብት #ሰማይ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የዘላለምን ሕይወት ያዝ

lay-22መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12
የዘላለም ህይወት የእግዚአብሄር ታላቅ ስጦታ ነው፡፡ ይህን ታላቅ ስጦታ እንደመቀበላችን መጠን ህይወታችን ሁሉ በዚያ ስጦታ መቃኘት አለበት፡፡
ምንም ነገር ስናስብ ከዘላለማዊ ህይወት እይታ እንፃር ማሰብ አለብን ፣ ምንም ነገር ስንወስን ከዘላለም ህይወት አንፃር ልንወስን ይገባል ፣ ምንም ነገር ስናደርግ ዘላለም እንደሚኖር ሰው ማድረግ አለብን፡፡
በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ። ያዕቆብ 2፡12
ሰው ዘላለማዊ ህይወትን ካልያዘና የሚያደርገውን ሁሉ ከዘላለማዊ ህይወት አንፃር ካልመዘነውና ካላደረገው እይታው የቅርብና የአሁኑን ብቻ ያያል፡፡
እነሆም፥ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፤ እናንተ፦ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል። ኢሳይያስ 22፡13
ሰው ትክክለኛ እይታ አለው የሚባለው ነገሮችን ሁሉ በዘላለም እይታ ማየት ሲችል ብቻ ነው፡፡ እይታው ዘላለምን ካላሳየው የቅርቡን ብቻ የሚያይ እውር ሰው ነው፡፡
እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡9
ከምድር ምንም አይነት ስኬትና ክንውን ጋር ሲነፃፀር የዘላለምን ህይወት የሚያክለው የለም፡፡ በእይታችን የዘላለም ህይወት ከሌለና እግዚአብሄርን ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ለምድራዊ ህይወት ብቻ ከሆነ ምስኪኖች ነን፡፡
በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡19
እያንዳንዱ እርምጃችን ዘላለም ለሚኖር ሰው የሚገባ መሆን አለበት፡፡ ከምንም ነገር በላይ የዘላለምን ህይወት በትጋት መጠባበቅ አለብን፡፡ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ፊልጵስዩስ 3፡20
በምድር ላይ የምናደርገው ማንኛውም ነገር በነፃነት ህግ እንደሚፈረድባቸው በጌታ ዙፋን ፊት እንደሚቀርቡ ሰዎች መሆን ይኖርበታል፡፡
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤ ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። ቆላስይስ 3፡1-4
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#የዘላለምህይወት #ሰማይ #ዘላለም #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
%d bloggers like this: