Category Archives: purpose

ከዛሬ ተግዳሮት ባሻገር

your will.jpg

ይብዛም ይነስም ችግሮች ወደህይወታችን በየጊዜው ይመጣሉ፡፡ ችግሮቹ ሲከሰቱ ችግሮችን መፍታት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ችግሮች ሲከሰቱ ችግሮችን ካልፈታናቸው ችግሮቹ የእግዚአብሄርን አላማ ከማድረግ ሊያደናቅፉን ይችላሉ፡፡

ችግሮች ሲመጡ መፍታት መልካም ሆኖ ሆኖ ሳለ ችግሮችን ከመፍታት የተሻለ መንገድ ደግሞ አለ፡፡

በህይወታችን አላማ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ እንድንሰራ ያዘጋጀውን ስራ በትክክል ማወቅ አለብን፡፡ እግዚአብሄ በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ በትጋት መከተል አለብን፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠው አላማ ላይ በትጋት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ለመፈፀም ስንንቀሳቀስ ከጉዞዋችን ሊያግደን የሚመጣ ችግርን እና ፈተናን ማለፍ ሃላፊታችን ነው፡፡

በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡9-10

ካልሆነ ግን ችግሮች ይመጣሉ እንፈታዋለን፡፡ የህይወት አላማ ከሌለን ለተወሰነ ጊዜ ደግሞ ተዝናንተን እንኖርና ደግሞ ሌሎች ችግሮች ይመጣሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ችግሮችን እየፈታን ችግሮቹ የሚጠብቁብንን ነገሮች እያደረግን ህይወታችንን እንገፋለን እንጂ እግዚአብሄር በህይወታችን ባለው አላማ እንደሚገባን ወደፊት መሄድ አንችልም፡፡ በየጊዜው የሚመጡትን ችግሮች በመፍታታችን ብቻ ከረካን እግዚአብሄር በህይወታችን ያቀደውን አላማ ከግብ ለማድረስ ይሳነናል፡፡

በየጊዜው መልካቸውን እየለዋወጡ የሚመጡትን ችግሮችን ብቻ እየፈታን የምንኖር ከሆንን ትልቁን የእግዚአብሄርን አላማ ምስል ማየት ያቅተናል፡፡ በየጊዜው የሚመጡትን ችግሮች ብቻ በመፍታት ላይ ከተሰማራን ዋናውን የእግዚአብሄርን አላማ ማየት ይሳነናል፡፡ በየጊዜው የሚመጡትን ችግሮች እየፈታን ከኖርን ሰይጣን የተለያየ የቤት ስራ እየሰጠን ባተሌ ያደርገናል፡፡ በየጊዜው የሚመጡት ችግሮች ላይ ብቻ ካተኮርን ስለነገ ማሰብ ያቅተናል፡፡ በየጊዜው የሚመጡት ችግሮች ላይ ባቻ ካተኮርን እግዚአብሄር በህይወታችን ስላለው ዋናው አላማ ማሰብና ማቀድ ያቅተናል፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

በህይወታችን የእግዚአብሄር አላማ ያስፈልገናል፡፡ በህይወታችን ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ በትጋት መከተል ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ለመከተል ስንሄድ የሚቋቋመን ነገር ብቻ ነው ችግር ሊሆንብን የሚገባው፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ከመከተል የሚቋቋመን ችግር መፍታት የአላማችን መፈፀም አካል ሰለሆነ እግዚአብሄር በዚህ ይከብራል፡፡

ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 29፡18

የሰይጣን አላማ ህይወታችንን በጥቃቅን ነገር ባተሌ ማድረግና ከአግዚአብሄር አላማ ማደናቀፍ ነው፡፡ በህይወታችን የእግዚአብሄር አላማ በትክክል መረዳት ከሌለንና እግዚአብሄር ለምን የተለየ አላማ እንደፈጠረን ካልተረዳን ሰይጣን የቤት ስራ እየሰጠን ህይወታችንን ከንቱ ያደርጋል፡፡ ወደዚህ ምድር ለምን የተለየ አላማ እንደመጣን ካልተረዳን ችግሮችን በመፍታታችን ብቻ ደስ እያለን ዋናውን የእግዚአብሄርን አላማ ሳናከናውን ጊዜያችን ያልፋል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

ስለዚሀ በተነሳሽነት መንፈስ የእግዚአብሄርን ልዩ አላማ መፈለግ አለብን፡፡ በተነሳኽሽነት መንፈስ ያንን አላማ ለመፈፀም እቀድ ማውጣት አለብን፡፡ በተነሳሽነት መንፈስ ያንን አላማ ለማስፈፀም የህይወት እቅዳችንን በትጋት መከተል አለብን፡፡

የእግዚአብሄርን አላማ በትጋት ስንከተል ችግሮች የሚሆኑት አታልፍም ብለው በፊታችን የሚቆሙ ከአለማችን ሊያደናቅፉ የሚመጡ እንቅፋቶች ብቻ ይሆናሉ፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ በመፈፀም ላይ ከተጋን ሰይጣን ሊመራንና በየጊዜው በሚሰጠን የቤት ስራ ላይ ባተሌ ሆነን ዋናውን የህይወታችን አላማ አንዘነጋም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #ችግር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው

your will.jpg

በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡12-13

የሆድ ነገር ብዙ ሰዎችን የማይፈልጉትን እንዲያደርጉ ያስደርጋቸዋል፡፡ የሚጠፋው የሆድ ነገር ብዙ ሰዎችን ያዋርዳል ከአላማም ያደናቅፋል፡፡ ብዙ ለጌታ ሲሮጡ የነበሩትን ሰዎችን የሆድ ነገር አሳስሮ ሽባ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ ብዙ ሰዎች ስለሆድ ብለው ራእያቸውን ጥለው እጅግ ያለቅሳሉ፡፡

ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ወደ ዕብራውያን 12፡16

ጌታ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም እንዳለ የሆድ ነገር የሰለጠናበቸው ሰዎች ጌታ እንደሚገባ ሊሰለጥንባቸው አይችልም፡፡ የሆድ ነገር የሚገዛቸው ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ለጌታ ሊገዙ አይችሉም፡፡

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። የማቴዎስ ወንጌል 6፡24

ሰው እያደገ ሲሄድ ፍላጎቱ በዚያው መጠን ስለሚጨምር የሆድ ፈተና የሌለበት ሰው የለም፡፡ ሁሉም ሰው ነገ ስለሚበላው ነገር በሆዱ ይፈተናል፡፡ ሁሉም ሰው የያዘውን እውነት እንዲያመቻምችና ሆዱን እንዲሞላ ተከታታይ ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡ ሁሉ ሰው ስለሆድ ምክኒያት ህሊናው የማይፈቅድውን ነገር እንዲያደርግ ይፈተናል፡፡

ትራባለህ ታጣለህ የሚል ማስፈራራትን ከሰማን የያዝንውን የእግዚአብሄር ቃል እውነት እንጥላለን፡፡ ነገር ግን ብራብም ባጣም አላዬን አልሸጥም ካልን ብንራብም ብናጣም ምንም አንሆንም ነገር ግን አላችን እናስፈጽማለን፡፡ ሃዋሪያው መጥገብንም መዋረድንም አውቀዋለሁ ሲል የማያውቅህን ሄደህ አስፈራራ የሚል ይመስላል፡፡ ሃዋሪያው ማግኘትንም ማጣትንም ልካቸውን ስላወቀ አንዳቸውም ከአላማው አያስፈራሩትም አያስቆሙትም፡፡ ማጣትና መዋረድ የሚያስፈራውና የሚያስቆመው የማያውቀውን ሰው ነው፡፡ መጉደልን የሚያውቅ ሰው ሁሉን የሚያስችለው እግዚአብሄር እንጂ መራብ በህይወቱ ላይ ምንም ስለማይቀንስ መብዛት በህይወቱ ላይ ምንም ስለማይጨምር ማጣት አያስፈራራውም፡፡

እኛ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ስንፈልግ ለሆድ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ይሰጠናል ብለን የእግዚአብሄርን ቃል ካመንን  የእግዚአብሄርን ፈቃድ በዘመናችን አገልግለን ማለፍ እንችላለን፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡12-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በህይወቴ የምጠላው

pride.jpg

በህይወቴ የምፈራው ሞትን አይደለም፡፡ ሞት የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሞት የሚያስፈራው የጌታ ኢየሱስን አዳኝነት ላልተቀበለ ሰው ለዘላለም ከእግዚአብሄር መለያያ መንገድ ስለሆነ ያስፈራል፡፡ ሞት የሚያስፈራው ከሞት ፍርሃት ነፃ ላልወጣ ላልዳነ ሰው ነው፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ወደ ዕብራውያን 2፡14-15

የስጋ ሞት ከምድራዊ ህይወት ወደ መንፈሳዊ ህይወት የምንሸጋገርበት መተላለፊያ በር ነው፡፡ በእውነት ካሰብነው እግዚአብሄር በሰማይ ያዘጋጀልንን ክብር ካየነው መሞት ያስደስታል እንጂ አያስፈራም፡፡ መሞት እንዲያውም እረፍትና ጥቅም ነው፡፡ በምድር የምንኖረው የእግዚአብሄርን መንግስት ለመስራት እንጂ ለእግዚአብሄር ስራ ባይሆን ኖሮ መሞት እረፍት ነው፡፡

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21-23

በህይወቴ የምፈራው ማጣትን አይደለም፡፡

ማጣት እንደማይገድል አይቸዋለሁ፡፡ ማጣት ሊፈራ የሚገባ እንዳይደለ አይቼዋለሁ፡፡ ማጣት ማንንም መንከስ እንደማይችል እንደታሰረ ውሻ ባዶ ጩኸት መሆኑን በህይወቴ አይቼዋለሁ፡፡ ማጣት የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈፀም እንደማያግድ አይቼቸዋለሁ፡፡ ዋናው ነገር ማጣት ወይም ማግኘትን ሳይሆን ሁሉንም የሚያስችለን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ መሆኑ ነው፡፡ ክርስቶስ ካለ ተጨማሪ ነገር አያስፈልገንም፡፡ ክርስቶስ ካለ ማጣት አያቆመንም፡፡ የሚያስችለን ማግኘት ሳይሆን ክርስቶስ ነው፡፡ በክርስቶስ ሁሉን እንችላለን፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13

በህይወቴ የምፈራው ድካምን አይደለም፡፡

ስንደክም ስንዋረድ በድካምና በመዋረድ ውስጥ ክብር አለ፡፡ በራሳችን ስንደክም ያን ጊዜ በክርስቶስ ሃይል ሃይለኛ ነኝ፡፡ የእግዚአብሄር ጉልበት በድካሜ ስለሚታይበት በድካሜ ደስ ይለኛል፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡9-10

በህይወቴ የምፈራው ሃዘንን አይደለም

ሃዘንተኛን በማፅናናት የተካነ የመፅናናት አምላክ እግዚአብሄር አባቴ ነው፡፡ አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም የሚሰጥ እገዚአብሄ አብሮን ነው፡፡

የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡3

በህይወቴ የምፈራው መከራን አይደለም

ፈተና እኛን አሻሽሎን አበርትቶን ከፊት ይልቅ አሳድጎን ነው የሚያልፈው፡፡ ከምንችለው በላይ እንድንፈትን የማይፈቅድ ታማኝ እግዚአብሄር ስላለ መከራን አያስፈራንም፡፡ መከራ የሚያገኘው በእኛ ላይ ያለን የማያስፈልግ ስጋዊነትነ ብቻ ነው፡፡ መከራ የሚያራግፈው ክርስቶስን የማይመስለውን የስጋ ምኞታችንን ብቻ ነው፡፡ ስጋዊነትን በሰዎች ህይወት ስናይ እንደሚቀፈን ሁሉ ለእግዚአብሄር የማይመቸው በመከራ የሚራገፈውን ስጋዊነትን ስናይ እግዚአብሄር ይመስገን ልንል ይገባል፡፡

ሰላም ለእናንተ ይሁን። ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። የያዕቆብ መልእክት 1፡2-4

መውጫውን ያዘጋጀው እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ስላለ ፈተና አያስፈራም፡፡

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13

የሚያስፈራው የእግዚአብሄርን ሃሳብ መጣስ ነው፡፡ የሚያስፈራው የምድር ህይወታችንን ለጊዜያዊ ለግል ጥቅማችን ማሳለፍ ነው፡፡ የሚያስፈራው ዋጋቸውን በምድር ተቀብለዋል መባል ነው፡፡ የሚያስፈራው በህይወታችን ዘመን ሁሉ እግዚአብሄር ያላለንን ነገር ሲያደርጉ በመኖር ህይወትን ማባከን ነው፡፡ የሚያስፈራው እግዚአብሄር ያዘዘንን ትተን እግዚአብሄር ያላዘዘንን ነገር ማድረግ ነው፡፡ የሚያስፈራው እግዚአብሄር ያልጠራንን ነገር በማድረግ አንዱን ህይወታችንን ማባከን ነው፡፡ የሞያስፈራው እግዚአብሄር ሳያዘን አንድ እርምጃን መራመድ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #መዳን #እምነት #ማስተዋል #አላማ #ግብ #የምፈራው #የምጠላው #ማጣት #ሃዘን #ፈተና #ሞት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ማሰብ #መሪ

ሲሆን ህልም ተራ

conscious

ሲሆን ህልም ተራ

አንዳንድ ሰው ሲናገር ስትሰሙት ህልሙ ተራ እንደሆነ በግልፅ ያስታውቃል፡፡ አንዳንድ ሰው ሲናገር ስትሰሙት እይታው ቅርብ እንደሆነ ቃላቶቹና በህይወቱ ዋጋ የሚሰጣቸው ነገሮች ያሳብቁበታል፡፡

ኢየሱስ ወደምድር ሲመጣ በጨለማ የነበርነውን እኛን ማየት የማንችለው የነበርነውን እኛን ብርሃን ሰጠን፡፡ ኢየሱስ ህይወታችንን ለመለወጥ በምድር ላይ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ እይታችን ከምድር አንስቶ ሰማይ ላይ እንዲሆን ማድረግ ነበር፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ የማቴዎስ ወንጌል 6፡19-20

ሰው የኢየሱስን ትመህርት ሰምቶ ምኞቱ ፣ ፍላጎቱና ህልሙ ካልተቀየረ የኢየሱስ ትምህርት አልገባውም ማለት ነው፡፡ ሰው ኢየሱስን አይቶ እይታው ካልተስተካከለ እምነትን አልተረዳም ማለት ነው፡፡

እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡9

መፅሃፍ ቅዱስ እይታችንን ከማስተካከል አንፃር ያስተማረውን ጥቂት ነገሮች እንመልከት፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ እንብላ እንጠጣ ነገ እንሞታለን ከሚል አጭር እይታ እንድንድን ያስተምራል፡፡

ክርስቶስን ሳንረዳ ተስፋ አልበነረንም፡፡ ተስፋችን ዛሬን መደሰት አለማችንን መቅጨት ነበር፡፡ በአለም ያለ ሰው የሚያየው ዛሬን ብቻ  ነው፡፡ በአለም ያለ ሰው ነገሮችን የሚመዝነው በዛሬ ጥቅሙ ነው፡፡ በአለም ያለ ሰው ነገሮችን የሚያየው ለዛሬ በሚያገኘው ጥቅም ብቻ ነው፡፡

በአለም ያለ ሰው ምድርን እንደ ጊዜያዊ ስፍራ ማየት አይችልም፡፡ በአለም ያለ ሰው ምድርን እንደመተላለፊያ ማየት አይችልም፡፡ በአለም ያለ ሰው ምድርን እንደጊዜያዊ ድንኳን ማየት አይችልም፡፡ አለማዊ ሰው ያለው ይህ ህይወት ብቻ ነው፡፡ አለማዊ ሰው እኔ የሚጠይቀው ከዚህ ነገር ምን አገኛለሁ የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ አለማዊ ሰው ከራሱ በስቲያ የሚያየው ጌታ ስለሌለ ያለውን ህይወት እንደፈለገ ያደርገዋል፡፡ አለማዊ ሰው ጌታ ኢየሱስ ጌታው ስላይደለ የራሱ ጌታ ራሱ ነው፡፡

በአለም ያለ ሰው በዘላለም ህይወት አእምሮ መኖር አይችልም፡፡  በአለም ያለ ሰው ነገሮችን በዘላለም ህይወት ሚዛን መመዘን አይችልም፡፡ በአለም ያለ ሰው ነገሮችን በዘላለም ህይወት እይታ ማየት አይችልም፡፡ በአለም ያለ ሰው አንድ ቀን በእግዚአብሄር ፊት እንደሚጠየቅ ሰው በሃላፊነት ስሜት ሊኖር አይችልም፡፡

አእምሮው ያልታደሰም ሰው እንዲሁ ዳግም ይወለድ እንጂ ነገሮችን የሚያየው አለማዊ ነገሮችን እንደሚያየው ነው፡፡ አእምሮው ያልታደሰ ሰው ምድርን እንደጊዜያዊ መተላፊያ መንገድ ሊያይ አይችልም፡፡ አእምሮው በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ ሰው በዘላማዊ ህይወት እይታ ነገሮችን ሊመዝን አችልም፡፡ አእምሮው ያልታደሰ ሰው ከሞት ተነስቶ በእግዚአብሄር ፊት እንደሚጠየቅ በሃላፊነት ስሜት እግዚአብሄርን በመፍራት ሊኖር አይችልም፡፡

እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡32

አእምሮው ያልታደሰ ሰው የሚያስበውና የሚያልመው ከማንኛውም ነገር ውስጥ ምን ጥቅም እንደሚያገኝ ነው፡፡ አእምሮው ያልታደሰ ሰው የሚያስበው በእግዚአብሄር መንግስር ላይ ምን እንደሚዘራ ምን ኢንቨስት አንደሚያደርግ አያስብም፡፡ አእምሮው ያልተለወጠ ሰው የሚያስበው እርሱ ስለሚበዛለት ጥቅማጥቅም እንጂ የእግዚአብሄር ህዝብ ስለሚያገኘው በረከት መለወጥና መሻገር አይደለም፡፡ አእምሮው በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ ሰው ካለው የምስኪንነት አስተሳሰብ የተነሳ ከምንም ነገር ውስጥ ምን እንደሚያገኝ ነው፡፡ አእምሮው በእግዚአብሄር ቃል ያልታደሰ ሰው ምን እንደሚሰጥ ፣ ምን እንደሚባርክና ምንን እንደሚጠቅም አያስበውም፡፡ አእምሮው ላልታደሰ ሰው አምላክ ሆድ እንጂ እግዚአብሄር አይደለም፡፡ አእምሮው በእግዚአብሄር ቃል ያልተለወጠ ሰው አሳቡ ምድራዊ ነው፡፡

መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡19-20

አእምሮው ያልታደሰ ሰው የእግዚአብሄርን መንግስትር እና የእግዚአብሄርን ቤተክርስትያን የሚያየው እንደ ቤተሰብ ሳይሆን እንደመጠቀሚያ መንገድ ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በላይ ያለውን እንጂ በምድር ያለውን እንዳንፈልግ ያስተምረናል፡፡

እይታችን ከሙታን እንደተነሱ ሰዎች በምድር ላይ ከቀረ በክርስትና ህይወታችን ውጤታማ አንሆንም፡፡ እይታችን በሰማያዊ ስፍራ እንደተቀመጡ ሰዎች ካልሆነ ህይወታችን ከማያምኑት የማይሻል ይሆናል፡፡ እይታችን በሰማያዊው ስፍራ በመንፈሳዊው በረከት ሁሉ እንደተባረከ ሰው ካልሆነ እግዚአብሄር በልቡና በነፍሱ እንዳለ ፈቃዱን በምድር ፈጽፅመን ማለፍ እንችልም፡፡

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡1-2

መፅሃፍ ቅዱስ እንደ አህዛብ የሚበላና የሚጠጣ በመፈልግ ህይወታችንን እንዳናባክን ያስተምረናል፡፡

እኛ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ እኛ በራሳችን አይደለንም፡፡ እኛ አምላክ አለን፡፡ እኛ የሚያስፈልገንን ነገር የሚያቀርብልን አባት አለን፡፡ የእኛ አላማ አባታችን ከእኛ የሚፈልገውን ነገር በማድረግ እርሱን ማስደሰት እንጂ ይጨመርላችኋል ያለውን የሚበላና የሚጠጣ በመፈለግ አይደለም፡፡ እይታችን ከአህዛብ ካልበለጠ ለእግዚአብሄር ጠቃሚ ልንሆን አንችልም፡፡ እይታችን የሚበላና ከሚጠጣ መፈለግ አልፎ የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቁን በመፈለግ ላይ ካልሆነ በክርስትና ህይወታችን እንከስራለን፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡31-33

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እይታ #ተስፋ #መፀለይ #መንፈስ #በረከት #መዝገብ #ሰማይ #እንግዶች #ዘላለም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እይታ #ምድራዊ #ሰማያዊት #ማየት #ቅርብ

ራእይ ባይኖር

vision_in_a_bottle.jpgራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። ምሳሌ 29፡18

በአጠቃላይ አነጋገር ራእይ ማለት ማየት መረዳት ማለት ነው፡፡

እንደ መፅሃፍ ቅዱስ ደግሞ ራእይ አለን ማለት ማለት እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ሃሳብ ማወቅ መረዳት ችለናል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛ እንድንሰራ የሚፈልገውን ነገር ማወቅ ማለት ነው፡፡ በህይወታችን እንድንሰራው በውስጣችን ያለ ሸክም ራእይ ይባላል፡፡ ካልሰራነው እረፍትን የማይሰጠን ሸክም ራእይ ይባላል፡፡ የህይወት ትኩረታችን ራእይ ይባላል፡፡ የህይወተ አላማችን ራእይ ይባላል፡፡ በምድር ላይ የምንኖርበት ምክኒያት ራእይ ይባላል፡፡

በምድር ላይ የተፈጠርነው ለምክኒያት ነው፡፡ በምድር ላይ የተፈጠርነው እንደ ድንገት በእድል አይደለም፡፡ በምድር ላይ ያለነው በአጋጣሚ አይደለም፡፡

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ኤርሚያስ 1፡4-5

በምድር ላይ የተፈጠርነው እግዚአብሄር ያዘጋጀውን ስራ ለመስራት ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ያገኘነውን ስራ ሁሉ ለመስራት አይደለም፡፡ በምድር ላይ ያለነው የሚያዋጣውን ስራ ሁሉ ለመስራት አይደለም፡፡ በምድር ላይ ያለነው ለእኛ የተዘጋጀውን ስራ ለመስራት ነው፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

እግዚአብሄር ሲፈጥረን ከስራ ጋር ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር ሲፈጥረን የመደበልን ስራ አለ፡፡ እግዚአብሄር ሲፈጥረን ለመደበልን ስራ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ በመስጠት ነው፡፡ የተፈጠርነው እግዚአብሄር ለመደበልን ስራ የሚያስፈልገው ስጦታና ክህሎት ሁሉ በውስጣችን ተቀምጦ ነው፡፡ የተፈጠርነው በምድር ላይ ለተመደበልን ስራ ከሚያስፈልገው ክህሎት ሁሉ ጋር ነው፡፡

እግዚአብሄር ለምን እንደጠራን ማወቅ የሚያስፈልገው ስለዚህ ነው፡፡ በህይወት ራእይ እንዲኖረን የሚያስፈልገው ስለዚህ ነው፡፡

ራእይ የምናገኘው ሁኔታዎች አይደለም፡ሸ ራእይት የምናገኘው ከወላጆቻቸነ አይደለም፡ የልጅነት ምኚታችንን አይደለም እንደራእይ የምንከተለው፡፡ሸ ራእይትን የመናገኘው በምድር ላይ ያለውን ክፍተት በማየት አይደለም፡፡

ራእይን የሚሰጠው ለራሱ ስራ አላማ የፈጠረን እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ለክብሩ ከፈጠረን ከእግዚአብሄር ብቻ ራእያችንን እናውቃለን፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ የሚያስባትን ሃሳብ ማወቅ ራእይን መቀበል ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

እግዚአብሄር ለእኛ የሚያስበውን ሃሳብ ያውቃል፡፡ ከመወለዳችን በፊት የተወለድንበት ምክኒያት ነበር፡፡ ከመወለዳችን በፊት ስንወለድ የምንሰራው ስራ ነበር፡፡ የተወለድንበት ምክኒያት ልንሰራው ያለ የተመደበልን ስራ ስለነበረ ብቻ ነው፡፡

የእኛ ስራ በፀሎት ከእግዚአብሄር ራእያችንን መቀበል ነው፡፡ እግዚአብሄ ሆይ ምን እንድሰራ ነው በምድር ላይ ያለሁት ብሎ መጠየቅ የእኛ ሃላፊነት ነው፡፡ በምድር ላይ ያለሁት ለምንድነው ብሎ መጠየቅ ሃላፊነታችን ነው፡፡ የእኛ ስራ የተቀበልነው ራእይ በምድር ላይ በትጋት መፈፀም ነው፡፡

የህይወቱን ራእይ ከእግዚአብሄ ፈልጎ ያላገኘ ሰው መረን ነው፡፡ ራእይ የሌለው ሰው የት እንደሚሄድ የማያውቅ ስርአት የሌለው ሰው ነው፡፡ ራእይ የሌለው ሰው መነሻም መድረሻም ስለሌለው አያርፍም፡፡ ራእይ የሌለው ሰው የሚሄድበትን ስለማያውቅና ሲደርስ ስለማያውቅ በህይወቱ እረፍት የለውም፡፡ ራእይ የሌለው ሰው ሌላው የሚሰራውን ሊሰራ ሲሞክር ለዚያ ስላልተካነ ይወድቃል፡፡ ራእይ የሌለው ሰው ግብ ስለሌለው ፍሬያማ አይሆንም፡፡ ራእይ የሌለው ሰው አንድ ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ ለአንድ ስራ እንደ ፈጠርከኝ አውቃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ለምን እንደ ፈጠርከኝ እረዳ ዘንድ አይኖቼክ ክፈት፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አስቀድሞ የተመደበለኝን ስራ ብቻ ለመስራት እችል ዘንድ መንፈስህ ስለሚመራኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ የተለያዩ ነገሮችን አይቼ ከራእዬ እንዳልወጣ በመንፈስህ ጠብቀኝ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ራእዬን መከተል እችል ዘንድ ፀጋን ስለምታበዛልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡  በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ፡፡ አሜን

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አማርኛ #ስብከት #መረን #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን

your will.jpgጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ። ማቴዎስ 26፡39

ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃስ 22፡42

አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ። ማርቆስ 14፡36

እኛ ለእግዚአብሄር ክብር ለመኖር የተጠራን ሁላችን ለእግዚአብሄር መኖር እንፈልጋላን፡፡ ኢየሱስን ስንከተል ለክብሩ ለመኖር ወስነን ነው፡፡ ኢየሱስን የተከተልነው ለሞተልንና ለተነሳው ለኢየሱስ እንጂ ወደፊት ለራሳችን ላለመኖር ነው፡፡

በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።  2ኛ ቆሮንቶስ 5፡15

በተለያየ ጊዜያት በህይወታችን የተለያዩ ምርጫዎች ይቀርቡልናል፡፡ በተለይ ኢየሱስን በሁለንተናችን ለመከተል የወሰንንእኛ ክርስትያኖች በየጊዜው የእኛ ፍላጎትና የእግዚአብሄር ፍላጎት ሲለያይ እንመለከታለን፡፡ በህይወት ጉዞዋችን እኛ የምንፈቅደውና እግዚአብሄር የሚፈቅደው በፊታችን እንደምርጫ ሲቀርብልን እናገኛለን፡፡፡ እኛ በህይወታችን እንዲሆን የምንወደው ነገር እግዚአብሄር የማይወደው ነገር ይሆንና እጅግ እንጨነቃለን፡፡ ወይም እኛ የማንወደው ነገርን እግዚአብሄር ይህንን እወዳለሁ ሲለን የእግዚአብሄርን ወይም የእኛን ለመምረጥ በውሳኔ መካከል ራሳችንን እናገኛለን፡፡

የራሳችንን ፈቃድ መከተል ለጊዜው ደስ ይል ይሆናል እንጂ ዘለቄታዊነት የለውም፡፡ የራሳችንን ፍላጎት መከተል እኛን ከእግዚአብሄር ፈቃድ በረከቶች ውጭ ያደርገናል፡፡ የራሳችን ፈቃድ መከተል በምድር ላይ ያለንን አንድ የህይወት እድል እንድናባክነው ያደርገናል፡፡  የራሳችንን ፍላጎት መከተል የእግዚአብሄር አብሮነት ያሳጣናል፡፡ የራሳችን ፍላጎት መከተል ክስረት ያመጣብናል፡፡ የራሳችንን ፍላጎት መከተል በእግዚአብሄር ፊት ያለንን ድፍረት ያሳጣናል፡፡

የእኛ ምርጫ ችግር አለበት፡፡ የእኛ ምርጫ ሁሉን የማያውቅ ሰው ምርጫ ነው፡፡ የእኛ ምርጫ እውቀት የጎደለው ሰው ምርጫ ነው፡፡ የእኛ መርጫ እንከን አያጣውም፡፡ በአለም ላይ የእጅግ ጥበበኛው ሰው ምርጫ ፍፁም አይደለም ጉድለት አለበት፡፡

የእግዚአብሄር ምርጫ ሁሉ የሚችል አምላክ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ የቅዱስ አምላክ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ የፍቅር አምላክ ምርጫ ነው፡፡

ስለዚህ ነው በራሳችን ፈቃድና በእግዚአብሄር ፈቃድ መካካል የምንጨነቀው፡፡ የእኛ ምርጫ ምን ያህን እንከን እንዳበት ስለምናውቅ በራሳችን መንገድ ላመሄድ ከራሳችን ጋር እንከራከራለን፡፡ በራሳችን ማስተዋል መደገፍ ስለማንፈልግ ነው ሁልጊዜ የእግዚአብሄርን ምርጫ መከተል የምንፈልገው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ምሳሌ 3፡5

የእግዚአብሄር ምርጫ የተሳሳተና የማይመስል ብዙዎች የማይደግፉት ቢሆን እንኳን የእርሱ ምርጫ ከየትኛውም መርጫችን የተሻለ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ ሞኝነት ቢመስል እንኳን የእግዚአብሄር ሞኝነት ከሰው ጥበብ ይጠበባል፡፡

ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡25

ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃስ 22፡42

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ ስለተናገርከኝ ስለዚህ ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በሁለንተናዬ ለአንተ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ የአንተን ፈቃድ ብቻ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ፈቃድህን ስለምትገልጥልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ፈቃድህን እንድከተል ሃይል ስለምትሆነኝ ፀጋህን ስለምታበዛልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተን በሁለንተናዬ እስከመጨረሻው ተከትዬህ ስለማልፍ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለ ሁሉም ተመስገን ፡፡ በኢየሱስ ስም ፡፡ አሜን

Simply the best

simple.jpg

There are more and more temptation to make our lives complicated and bound us by some external factors. But it is always the simpler the better. Let’s see the reasons why simple is always better.

 • Simple is Clear

We are designed to be simple. But men are deceived into complicating their lives. People despise simple things. They only boast on complicated things which they are not created for.

This only have I found: God created mankind upright, but they have gone in search of many schemes.” Ecclesiastes 7:29

We are created to manage simple things. We are limited. We can only manage simple things. We are not good at managing complicated things.  That is the reason the Bible warns us against a multitude of words.

In the multitude of words sin is not lacking, But he who restrains his lips is wise.  Proverbs 10:19

That is the very reason that the Bible equates simplicity with purity and complication with impurity.

All you need to say is simply ‘Yes’ or ‘No’; anything beyond this comes from the evil one. Matthew 5:37

 • Simple is focused

Without focus, we can’t succeed in life. To be focused we must have to have limited responsibilities. We have to put the priority in order to simplify our responsibility and tackle a problem at a time. We live in the world of limited resources. We don’t have all the time and energy we want. We have to decide to give the due priority to the things that we can’t live without.  To utilize our resources effectively, we have to simplify responsibility and thereby our lives.

 • Simple is independent.

When you make your life simple, you will minimize the ways you depend on others. You will be more in control of your life. Simplicity eliminates the things we just want but don’t actually need them. We have to decisively cut the things that we can live without doing them. That makes us to be free to focus on the things we have to.

The want doesn’t deserve our priority. The want can only be done at the expense of the need.

Actually, you can judge a person’s real productivity by the way he simplifies things or complicates them.

Make your life simplified.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#God #Jesus #life #simplicity #complex #complicated #clear #focus #independence #rejoice #trustgod #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው

god is ;ove.jpgበእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ  2፡4

እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡

እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4፡8

እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው እርሱን የሚመስል ሊያናግረውና ሊረዳው የሚችል ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በፍቅር ነው፡፡

እግዚአብሄር ለሰው ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሰው ያለው እቅድ የሰላም እቅድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሄር ለሰው ያለው አላማ ፍፃሜና ተስፋ ያለው እቅድ ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

እግዚአብሄር የሚያየን በፍቅር አይን ነው፡፡

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፤ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና። ዘካርያስ 2፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው

purpose.jpgእግዚአብሄር ጠቢብ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን አዋቂ ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን በድንገት አልፈጠረውም፡፡ እግዚአብሄር እየፈጠረ እያለ እንደ ድንገት ሰው የሚባል ፍጥረት አልፈጠረም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ሰው እንዴት እንደሚሆን ፣ ምን እንደሚኖረውና ምን ምን እንደሚያደርግ ያውቅ ነበር፡፡

እንዲያውም እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረበት ምክኒያት ሰው በምድር ላይ የሚያደርገው ስለነበረ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረበት ምክኒያት ለአላማው ሰውን አይነት ፍጥረት ስለፈለገ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረበት ምክኒያት የሰው አይነት ፍጥረት ብቻ ሊሰራው የሚችለው አላማ ስለነበረው ነው፡፡

እግዚአብሄር መጨረሻውን ከመጀመሪያ ያያል፡፡ እግዚአብሄር ድንገት የሚመጣለትን ሃሳበ የሚያደርግ አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው እንዲሁም እግዚአብሄር ለአላማው ጨካኝ ነው፡፡

በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ኢሳያስ 46፡10

እያንዳንዳችን ወደምድር የመጣነው በስማችን የተለየ አላማ ስለነበረ ነበር፡፡ አብሮን የተፈጠረው ክህሎትና ስጦታ ለዚያ አላማ ማስፈፀሚያ የሚውል ነው፡፡ እያንዳንዳችን ወደምድር የመጣነው እኛ ብቻ ልንሰራው የሚገባ የተለየ አላማ ስላለ ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር አላውን በምድር ላይ በትጋት እየሰራው ነው፡፡ እግዚአብሄር ለአላማው ጨካኝ ነው፡፡

ኢየሱስ የእግዚአብሄርን አላማ ለማስፈፀም ተጨነቀ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈፀም ነፍሱ እስከሞት አዘነች፡፡ ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይሁን የእኔ ፈቃድ አይሁን በማለት ለእግዚአብሄር ዘላለማዊ አላማ ራሱን ሰጠ፡፡

እግዚአብሄርም የሰው ልጆች መዳን በኢየሱስ መስዋእትነት መፈፀም ስለነበረበት ኢየሱስ ለምን ተውከኝ እስከሚል ድረስ እግዚአብሄር ጨከነ፡፡

በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር

hope2.jpgለፍጻሜሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ። ኤርምያስ 31፥17

ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ታስቦና ታቅዶ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ተፈጥሮአል፡፡

እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍጥረት 1፡26፣28

ሰው ከመፈጠሩ በፊት ለምን እንደሚፈጠር እግዚአብሄር ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡ ሰው ድንገት አልተፈጠረም፡፡ ወይም ሰው አላማ የተፈለገለት ከተፈጠረ በኋላ አይደለም ፡፡ ሰው ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረለት በቂ አላማ ነበረው፡፡ ሰው የመፈጠሩ ምክኒያት ያንን የተፈጠረለትን አላማ እንዲፈፅም ነው፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10

ስለዚህ ሰው ወደ ምድር የመጣው የሚደርስበት ቦታ እና ግቡ ታውቆ ነው፡፡ እግዚአብሄር የመጨረሻውን ከመጀመሪያ ያያል፡፡

በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ኢሳያስ 46፡10

ድንገት ወደምድር የመጣ አንድም ሰው የለም፡፡ በምድር ላይ የምናየው ማንኛውም ሰው ይረዳውም አይረዳውም ወይም ይከተለውም አይከተለውም የእግዚአብሄርን የተለየ አላማ ለማስፈፀም ተወልዶዋል፡፡

እግዚአብሄር የህይወት ፍፃሜያችንን የሚሰራው በየጊዜው የፀሎት ርእሳችንን እየሰበሰበና እያሰበበት አይደለም፡፡ እኛ ወደምድር ከመምጣታችን በፊት ወደምድር የመጣንለት እኛ ብቻ የምንፈፅመው ልዩ አላማ አለ፡፡ ወደ ምድር የመምጣታችን ምልክቱ በስማችን የተዘጋጀ የህይወት አላማ መኖሩ ነው፡፡

እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ዮሐንስ 18፡37

ተስፋ ያለን የፍፃሜ ሰዎች ነን፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በሲንጋፖር ውስጥ የትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ፈተናው ከመድረሱ በፊት ለወላጆቹ ይህን ደብዳቤ ላከ

23804395_10212502836579309_85256023_n.jpgውድ ወላጆች

የልጆችዎ ፈተናዎች በቅርቡ ይጀመራል፡፡ ለልጅዎ ደህና ውጤት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ፡፡

ነገር ግን እባክዎን ይህንን አይርሱ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል ሂሳብን መረዳት የማይፈልግ አርቲስቶች አሉ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል  ስለ ታሪክ ወይም የእንግሊዘኛ ሥነ-ጽሑፍ ግድ የማይሰጠው ሥራ ፈጣሪዎች ወይም ነጋዴዎች አሉ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል የኬሚስትሪ ውጤታቸው ምንም የማያመጣላቸው ሙዚቀኞች አሉ፡፡ ከፊዚክስ ፈተና ውጤታቸው የበለጠ አካላዊ ብቃታቸው አስፈላጊ የሆነ አትሌቶች አሉ፡፡

ልጅዎ ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ውጤት ካላመጡ እባክዎን በራስ የመተማመን ስሜታቸውንና ክብራቸውን መንካት የለብዎትም፡፡ መልካም ይሁን በሉዋቸው፡፡ ይህ ፈተና ብቻ ነው! በህይወት ውስጥ በጣም ወሳኝ በሆኑ በርካታ ክህሎቶች ተክነዋል፡፡ ምንም ውጤት ቢያመጡ ይወደዱዋቸው አይፍረዱባቸው፡፡

እባክዎ ይህን ያድርጉ፡፡ ልጆችዎ በምንም ሁኔታ ውስጥ ካበረታቷቸው ዓለምን ሲያሸንፉ ይመለከታሉ፡፡ አንድ ፈተና ወይም ዝቅተኛ ውጤት ህልማቸውን እና ችሎታዎቻቸውን አያጠፋውም፡፡ እባክዎ በአለም ውስጥ ብቸኛ ደስተኛ ሰዎች  ዶክተሮች እና ኢንጂነሮች ብቻ ናቸው ብለው አያስቡ፡፡

በታላቅ አክብሮት

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ክህሎት #ስጦታ #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #ጥሪ #እንደተፃፈ #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ

ethiopian-birr-922x614.jpgእኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9

በእግዚአብሄር እይታ ለወንጌል ስራ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም የማይውል ማንኛውም ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

በእግዚአብሄር እይታ ለእግዚአብሄር መንግስት ዋነኛ አላማ ለሆነው ሰዎችን የማዳን ስራ የማይውል ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ለዘላላማዊ ህይወት አላማ የማይጠቅም ማንኛውም ሃብት የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡ ሰዎችን ለማዳን የማንጠቀምበት ለሰዎች ብርሃን ለመሆን የማንጠቀምበትና የምድር ጨው ለመሆን የማይጠቅመን ማንኛውም ሃብት የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ለሰዎች መልካምን አድርጋላቸው በህይወታችን መስክረን የእግዚአብሄን መልካምነት አሳይተናቸው ለጌታ ለመማረክ የማይጠቅመን  ማንኛውም ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ራቁታችንን ወደምድር መጥተናል ራቁታችንንም እንመለሳለን፡፡ በምድር ላይ የምናገኘው ለእግዚአብሄር መንግስት ስራ የማይጠቅም ገንዘብ ሁሉ ከዘላለማዊ ህይወት አንፃር ከንቱ ገንዘብ ነው፡፡

በምድር ያከማቸነው በመልካም ስራ ወደ መንግስተ ሰማያት የማንልከው ገንዘብ ጥለነው የምንሄደው ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡18-19

በመልካም ስራ ያልመነዘርነው ገንዘብ በመልካም ስራ ባለጠጋ ያላደረገን ገንዘብ በብር ተከምሮ ያለ ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ ማቴዎስ 6፡19-20

ልባችንን ወደ ሰማይ የማይስበን ገንዘብን ፣ ልባችንን ወደ ምድር የሚስበን ገንዘብና ልባችንን ወደ ሰማይ እንዳናተኩር የማያደርገን ገንዘብ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። ማቴዎስ 6፡20-21

ሰዎችን ለዘላለም ህይወት የማንማርክበት ፣ ምድር ላይ ጥለነው የምንሄደው ፣ በመሬት ስበት ምክኒያት ወደሰማይ ይዘነው የማንሄደው ፣ በምድር ላይ ብቻ በዘላለማዊ ሃብት የምንመነዝረውና በምድር ላይ ብቻ ዋጋ ያለው ገንዘብ ሁሉ የአመፃ ገንዘብ ነው፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእግዚአብሄር መንግስት እንጂ ባለጠግነት ጉልበትህና ድካምህ አይገባውም

follow money3.jpgለእግዚአብሄር ልጅ የገባውና የሚመጥነው ለእግዚአብሄር መንግስት መስራት ነው፡፡ የባለጠግነት ሩጫ ለእግዚአብሄር ልጅ አይገባም፡፡ ባለጠጋ ለመሆን መድከም ለእግዚአብሄር ልጅ የማይመጥነው ተራ ነገር ነው፡፡ ባለጠግነት ጉልበታችንና ድካማችን የማይገባው ተራ ነገር ነው፡፡

ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል፤ ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና። ምሳሌ 23፡3-5

ኢየሱስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ  ለመብል ብለው የተከተሉትን ሰዎች ለእግዚአብሄር እንዲሰሩ አንጂ ለሚጠፋ መብል እንዳይሰሩ ያስተምራቸዋል፡፡

ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። ዮሃንስ 6፡27

እጅግ ሃያል የሆነው የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን እንዳይሰራና ፍሬያማ እንዳንሆን የሚያደርገው የባለጠግነት ማታለል ነው፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።ሉቃስ 4፡19

ስለዚህ ነው ኢየሱስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም ያለው፡፡ ለባለጠግነት መድከም ጌታን የማያውቁ የመንግስቱ አላማ የሌላቸው በኑሮ ከመካት የተሻለ አላማ በህይወታቸው የሌላቸው የተራ ሰዎች አካሄድ ነው፡፡

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ራእይን መቀበል

vision.jpgሰው በእግዚአብሄር አምሳል ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሯል፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ አግኝቶ ካልፈፀመው ህይወቱን ያባክናል፡፡ ሰው እግዚአብሄር ለእርሱ ያለውን አላማ አግኝቶ ከፈፀመው ግን በህይወት ይሳካል፡፡ ሰው እግዚአብሄር በህይወቱ ሊሰራ ያለውን አይቶ ከተባበረ ከእግዚአብሄር ጋር በመስራቱ ውጤታማ ይሆናል፡፡

ስለዚህ ነው ሰው ራእይ ያስፈልገዋል የምንለው፡፡ ሰው ራእይ ከሌለውና የእግዚአብሄርን አላማ በህይወቱ ካላገኘ በከንቱ ይተጋል፡፡

ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ምሳሌ 29፡18

እግዚአብሄር ካልመራን በስተቀር ለእግዚአብሄር ብለን የምናደርጋቸው ሁሉ እግዚአበሄር አይቀበላቸው፡፡ እግዚአብሄር የሃሳብ እጥረት የለበትም፡፡ እግዚአብሄን በራእይ አንረዳውም፡፡ እግዚአብሄር ህይወታችን በምን መንገድ መሄድ እንዳለበት እቅዱ አለው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።  ኤርምያስ 29፡11

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም። ዮሃንስ 1፡1-5

በመጀመሪያው ቃል ወይም ራእይ ነበረ

ምንም ባልነበረ ጊዜ ቃል ነበረ፡፡ ሁሉን የሚያመጣው ራእይ ስለሆነ ምንም ሳይኖር የሚቀድመው ራእይ ነው ፡፡ በራሳችን አነሳሽነት የሆነ ቦታ እየሄድን እግዚአብሄርን እግረመንገዳችንን ከመንገድ ላይ የምንጭነው ነገር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ተጠቅሞ መሄድ የሚፈልግበት የራሱ እቅድ አለው፡፡ ምንም ነገር ከማድረጋችን በፊት የሚቀድመው የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግ ነው ወይም ራእይን መቀበል ነው፡፡ ምንም ነገር ለማድረግ ከመፈለጋችን በፊት ራእይን መፈለግ አለብን፡፡ ምክኒያቱም ነገሮች በእግዚአብሄር የሚሆኑት በራእይ ነው፡፡

ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ

ራእይ አውጥተን አውርደን የምንቀርፀው ሳይሆን ከእግዚአብሄር የምንቀበለው ነው፡፡ የእኛ የህይወት ንድፋችን ያለው በእግዚአብሄር ዘንድ ነው፡፡ ራእይ ከእግዚአብሄር ይገኛል እንጂ ከሁኔታዎች አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር ለምን እንደፈጠረንና ለምን እንደሰራን ስለሚያውቅ ራእይን ሊሰጠን የሚችው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚደግፈው ራእይ ከሰዎች ፣ ከሁኔታዎች ፣ ከሃሳባችንና ከምኞታችን አይገኝም፡፡

ቃልም እግዚአብሔር ነበረ

ራእይ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ቃልን ያዝነው ማለት እግዚአብሄርን ያዝነው እንደማለት ነው፡፡ እንዲሁም ራእይ አለን ማለት የእግዚአብሄር ሙሉ እርዳታ ከእኛ ጋር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ራእይን ወይም የእግዚአብሄርን ፈቃድ በተከተልንበት የህይወታችን ክፍል በእግዚአብሄር ሙሉ የውክልና ስልጣን የምንመላላስ እንሆናለን፡፡ እግዚአብሄር ሃላፊነትን በሰጠን አካባቢ ሙሉ ስልጣን አለን፡፡ ራእይ በተቀበልንበት የእግዚአብሄርን አላማ ባወቅንበት የህይወታችን ክፍል ሁሉ ሰይጣንም ፣ ሁኔታዎችም ፣ ሰዎችም ፣ ሊያቆሙን አይችሉም፡፡

በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። ኢያሱ 1፡5

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን የእግዚአብሄር ሙሉ የውክልና ስልጣን ስለሚያስፈፅሙ አማልክት የሚላቸው፡፡

ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ ዮሐንስ 10፡34-35

ሁሉ በእርሱ ሆነ

እግዚአብሄር ፈቃዱን በሙሉ ስለሚደግፍ ራእይ ሁሉንም ያመጣል፡፡ ራእያችን ምግባችን ነው ፣ ራእያችን ልብሳችን ነው ፣ ራእያችን እርካታችን ነው ፣ ራእያችን ውበታችን ነው ፣ ራእያችን ዝናችን ነው ፣ ራእያችን ሙላታችን ነው ፣ ራእያችን ደስታችን ነው ፣ ራእያችን ሞገሳችን ነው፡፡ ራእያችንን ተከትለን የሚጎድልብን መልካም ነገር አይኖርም፡፡

በእርሱ ሕይወት ነበረች

የእግዚአብሄር ህይወት የሚፈሰው በራእያችን ውስጥ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ህይወት ማስተላለፍ ከፈለግን ከእግዚአብሄር ስለህይወታችን ያለውን አላማ መግኘትና የእግዚአብሄርን እቅድ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ በራእያችን ስንሄድ ህይወትን እንሸከማለን፡፡ በራእያችል ስንኖር ህይወትን እናካፍላለን፡፡ በራእይ ስንኖር ህይወት ይሆንልናል ህይወትም ይበዛልናል ህይወትንም እናካፍላለን፡፡ እኛም ሆነ የምናገለግላቸው ሰዎች እውነተኛውን ህይወት ማጣጣም የሚችሉት በራእይ ስንኖር ነው፡፡

ከሆነውን አንዳች ያለእርሱ አልሆነም

ትርጉም ያለው ነገር ማድረግ ካለብን በራእይ ነው፡፡ ካለ ራእይ ምንም ነገር አይሆንም፡፡ ካለ ራእይ ዘላለማዊ ነገር ሊደረግ አይችልም፡፡ ካለ ራእይ እውነት ነገር ማድረግ አይቻልም፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር ማድረግ ካለብን በራእይ ብቻ ነው፡፡

ህይወትም የሰው ብርሃን ነበረች

ሁላችንም እግዚአብሄር እንዲጠቀምብን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ተጠቀምብን የሚለው የልባችን የዘወትር ጩኸት ነው፡፡ ለሰዎች ብርሃንን የምናካፍለው የእግዚአብሄን ህይወት በማካፈል ነው፡፡ ህይወት ያለው ፣ የሚሰራ ፣ የሚያድግና የሚበዛ አገልግሎት ለማገልገል ራእይ ወሳኝ ነው፡፡ ራአይ ካለን ህይወት ይኖረናል፡፡ ራእይ ካለን እንደዘር የሚሰራ ፣ የሚበዛና ፣ የሚያሸንፍ ነገር ይኖረናል፡፡

ብርሃንም በጠለማ ይበራል

ጨለማ ያለበትን የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ብርሃንን ሲሰጠንና ፈቃዱን ሲገልጥልን ብቻ ነው በጨለማ ላይ ብርሃንን ማብራት የምንችለው፡፡ የእግዚአብሄርን የፈቃዱን እውቀት ራእይን ስናገኝ ብርሃንን ለሰዎች እናስተላልፋለን፡፡ ሰዎችን ላስጨነቃቸው ጨለማ ላይ ብርሃን ፣ ለድካማቸው ብርታት ፣ ለበሽታቸው መድሃኒት ፣ ለውድቀታቸው መነሳትና ለሞታቸው ህይወት እናካፍላለን፡፡

ጨለማም አላሸነፈውም

ጨለማን ለማሸነፍ መታገል አይጠይቅም ፡፡ ለጨለማ ብርሃንን ማብራት ብቻ በቂ ነው፡፡ ብርሃንን ሊቋቋም የቻለ ጨለማ እንደሌለ ሁሉ ራእይን ሊቋቋም የሚችል አንድም ሃይል ከሰማይ በታች የለም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መሳጭ ታሪክ

black-women-beautiful-eyes-1-614x800.jpgይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤

አንድ የሰማሁትን ልቤን የነካኝን ታሪክ ላካፍላችሁ፡፡

በክርስትያን ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ልጅ ወደ ታላቅ እህቱ ይሄድና እግዚአብሄርን ማየት እፈልጋለሁ ይላታል፡፡ እህቱም አይደለም እኮ እግዚአብሄር አይታይም ብላ ትመልስለታለች፡፡

በመልሱ ያልረካው ልጅ ወደ እናቱ ጋር ይሄድና እማዬ  እንዴት ነው እግዚአብሄርን ላየው የምችለው ይላታል፡፡ እሱዋም እግዚአብሄር የሚታየው በቃሉ ነው ብላ ትመልስለታለች፡፡

በእህቱም በእናቱም መልስ ያልረካው ልጅ በእርጅና ምክኒያት አይናቸው ወደፈዘዘ ወደአያቱ ይቀርብና አያቴ እግዚአብሄርን ማየት እፈልጋለሁ ብዬ እህቴን ብጠይቃት እግዚአብሄር አይታይም አለችኝ እናቴ ደግሞ እግዚአብሄር በቃሉ ነው እንጂ አይታይም አለችኝ፡፡ ፊታቸው በደስታ የበራው አያቱ ልጄ አሁን አሁንማ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ምንም ነገርም አልታይም ብሎኛል አሉት ይባላል፡፡

በእነዚህ መካከል የነበረው ልዩነት የእይታ ልዩነት ነው፡፡ ለአያትየው መንፈሳዊው አለም ፍንትው ብሎ ከመታየቱ የተነሳ የምድራዊው ነገር ጨልሞባቸዋል፡፡

ኢየሱስ ጌታና ንጉሷ የሆነባት የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን አለች፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቱ እንደሞተለት አምኖ ዳግመኛ ያልተወለደ ማንም ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።ዮሐንስ 3፡3
ዳግመኛ እንደተወለድን እንደ እኛ ባለጠጋ ሰው የለም፡፡ ግን ማየት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን አይናችን ተከፍቶ ካላየን ባለጠጋ ለመሆን በከንቱ በመድከም ጊዜያችንን እናባክናለን፡፡

ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19

የሰው ጤንነት አይን ነው፡፡ አይኑ የታመመና በትክክል የማያይ ሁለንተናው ይጨልማል፡፡

መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ! ማቴዎስ 6፡21-23

መንፈሳዊውን አለም ማየት የተሳናትን የቤተክርስትያን መሪ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ ይላል ጌታ፡፡ ሰው ካላየ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ ነኝ ብሎ ይመካል ራቁቱን ሆኖ የዘነጠ ይመስለዋል፡፡

ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ። ራእይ 3፡18

ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እይታ #አይን #ቃል #የጠራ #ኩል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው

publication2-jpg1እግዚአብሄር ለአላማ ፈጥሮናል፡፡ የመፈጠራችን አላማ ደግሞ ከመኖር ያለፈ አላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰራን ለራሱ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ የሚያኖረን የእርሱን ክብሩንና በጎነቱን እንድናሳይለት ነው፡፡
ወደ ምድር የመጣነው ድንገት አይደለም፡፡ ወደ ምድር የመጣነው እግዚአብሄር ስለፈለገን ነው፡፡ እግዚአብሄር ክብሩን ሊገልጥብን እንድናገለግለው ለፈቃዱ እንድንኖር ወደ ምድር አምጥቶናል፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ለመኖር የሚያስፈልገንን የማሟላት ሃላፊነት ያለበት እግዚአብሄር ሲሆን ለእግዚአብሄር ክብር የመኖር ሃላፊነት ያለብን ደግሞ እኛ ነን፡፡ የእኛ ሃላፊነት የእግዚአብሄን መንግስት ጥቅምና በጎነት መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ሃላፊነት የሚያስገልገንን ሁሉ ማሟላት ነው፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33
ስለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ለህይወት የሚያስፈልገንን ሁሉ እግዚአብሄር በክብር እንደሚሞላብን የሚያስተምረው፡፡ አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
ስለዚህ ነው መዝሙረኛው እረኛው እግዚአብሄር ስለሆነ ከሚያስገልገው ነገር አንዱንም እንደማያሳጣው የዘመረው፡፡ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
አንድ የማከንብራቸው የእግዚአብሄር ሰው “የሌለኝ ነገር ሁሉ የሌለኝ ስለማያስፈልገኝ ነው” አሉ፡፡
እውነት ነው እግዚአብሄር እረኛችን ሆኖ የሌለን ነገር ካለ ቢያንስ ቢያንስ ለአሁን አያስፈልገንም ማለት ነው፡፡ ወደፊት የሚያስፈልገን ከሆነ እግዚአብሄር በጊዜው ውብ አድርጎ ሰርቶታል፡፡ ለአሁን ግን የሌለኝ ሁሉ የማያስፈልገኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ መልካም የሚያደርግ ሆኖ መልካም ለማደርግ ሙሉ ችሎታ ኖሮት ሳለ የሌለን ነገር የማያስፈልገን ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እረኛ #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ኤጭ ደግሞ ለኑሮ

publication1111111እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡31-32
ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን ለኑሮ እንዳንጨነቅ ኢየሱስ ደጋግሞ ደጋግሞ ያስተምረናል፡፡ ስለኑሮ መጨነቅ የእናንተ አይደለም እያለን ነው፡፡ ለኑሮ መጨነቅ አይመጥናችሁም እያለን ነው፡፡ ስለኑሮ መጨነቅ ክብራችሁ አይፈቅደውም እያለንም ነው፡፡
ስለኑሮ መጨነቅንና ለመኖር መኖርን እንደትልቅ ነገር አይተውት የሚኖሩለትና የሚሞቱለት ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለመኖር ነው የሚኖሩትና የሚሰሩት፡፡ እነዚህ ሰዎች ለመኖር የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ከመኖር ውጭ የሚኖሩለት ምንም ነገር የላቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች መኖር የሙሉ ጊዜ ሃላፊነት ነው፡፡
ህይወታቸውን ሁሉ የሰጡት ለመኖር የሚያስፈልገውን በማሟላት ነው፡፡ የሚኖሩለት የእግዚአብሄር ጥሪ በህይወታቸው ላይ የለም፡፡ እግዚአብሄር ለህይወታቸው ያስቀመጠውን የተለየ አላማ አላገኙትም፡፡ ስለሚበላና ስለሚለበስ ከመጨነቅ የተሻለ ስራ የላቸውም፡፡
ስለኑሮ መጨነቅ እግዚአብሄርን የማያውቁ የተሻለ የህይወት አላማ የሌላቸው ሰዎች የህይወት ዘይቤ እንደሆነ ኢየሱስ ያስተምራል፡፡ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ማቴዎስ 6፡32
ለመኖር የሚጨነቁት ሌላ ምንም ሃላፊነት የሌለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ለመኖር የሚጨነቁት ሌላ የተሻለ የሚኖሩለት የህይወት ራእይ ስለሌላቸው ነው፡፡ ለመኖር የሚጨነቁት በህይወታቸው የሚከተሉት የእግዚአብሄር አላማ በህይወታቸው የሌላቸው ናቸው፡፡ እነዚያ ለመኖር የሚጨነቁት መንገዱ የጠፋባቸውና እግዚአብሄር ለከበረ የህይወት አላማ እግዚአብሄርን ለማምለክና ለማገልገል እንደጠራቸው የማያውቁ ናቸው፡፡ ስለኑሮ የሚጨነቁት የሚፈልጉት የእግዚአብሄር መንግስት ስሌላቸው ነው፡፡ እነዚህ ስለሚበላና ስለሚጠጣ የሚጨነቁት የሚፈልጉት የእግዚአብሄር ፅድቅ ስለሌላቸው ነው፡፡
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33
ኑሮን ዋና የህይወት አላማ ያደረጉት ናቸው ስለመኖር ብለው የሚኖሩት፡፡ እነዚህ ሰዎች ህይወታቸውን ሁሉ የሚጨርሱት ለመኖር በመጨነቅ ለመኖር በመሞከር ብቻ ነው፡፡ እንደው ከመኖር የተሻለ ምንም የሚከተሉት የህይወት አላማ የላቸውም፡፡ የመጨረሻውና ታላቁ ግባቸው መኖር ነው፡፡
በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡19
ለእነርሱ መኖር ብቻውን ትልቅ ነገር ነው፡፡ ለእነርሱ እግዚአብሄር ሊሰሩት ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ መስራት ሳይሆን ኖሮ ኖሮ መሞት ትልቅ ገድል ነው፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ኢየሱስ ስለኑሮ አትኑሩ ለመንግስቴ ኑሩ እያለን ነው፡፡ ፅድቅን ለማሳየት ስትኖሩ ይህ ሁሉ ነገር ምርቃት ነው እያለን ነው፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡31-32
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #ህልም #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መጤ አይደለንም

11111ክርስትያን በተለያየ ምክኒያት ከትውልድ ሃገሩ ወጥቶ በሌላ ሃገር ይኖራል፡፡እግዚአብሄር ከአንድ ቦታ ይልቅ በሌላ ቦታ እንድናገለግለው እርሱን እያሳየን አንድንኖር ሲፈልግ በሮችን ይከፍታል፡፡
ራሳችንን ለጌታ ከሰጠንበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሄር እየመራን ነው፡፡ እግዚአብሄር ተመለስ ብሎ እስካልተናገረን ድረስ በእግዚአብሄር ሃሳብ ውስጥ እንዳለን እናውቃለን፡፡ አንዳንዱ በትምህርት ምክኒያት ፣ ሌላው ለስራ ፣ ሌላው ከቀሩት የቤተሰቡ አባላት ጋር ለመኖር ፣ ሌላው ከጓደኛው ጋር ለመገናኘት የመሳሰሉት ወደ ተለያዩ አገሮች በመሄድ ይኖራል፡፡
ሰው የተለያየ ምክኒያት ይስጠው እንጂ እግዚአብሄር ፍቃዱ ካልሆነና በስተቀር የሚሰራው የእግዚአብሄር ስራ ከሌለ በስተቀር የውጭ አገር በሮች አይከፈቱም ልቡንም አያነሳሳም፡፡
ከሀገር ለመውጣት ቢፈልጉም ቢመኙም ቢፀልዩም ያልቻሉ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን፡፡ በተቃራኒው ብዙም ሳያስቡበትና ሳይጓጉ አጋጣሚ በሚመስል መንገድና ባልተገመተ ሁኔታ አገር የለወጡ ብዙ ሰዎች ደግሞ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሄር የሚዘጋውን የሚከፍት እንደሌለ የሚከፍተውን ደግሞ የሚዘጋ እንደሌለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል። ራእይ 3፡7
እግዚአብሄር በውጭ አገር የፈለገውን የሚከለክል ማንም የለም፡፡ እግዚአብሄር ምድርን ሁሉ የፈጠረው ሰው እንዲኖርበትና እንዲገዛ ነው፡፡ እግዚአብሄ ፈቅዶ ልባችንን ካነሳሳና በሮችን ከፍቶ ወደሌላ አገር ከወሰደን የምንሰራው የእግዚአብሄር ስራ አለማለት ነው፡፡ ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሄር ናት፡፡
እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ማርቆስ 16፡15
የኢየሱስ ተከታዮች በመሆናችን በትውልድ አገራችንም ይሁን ከትውልድ አገራችን ውጭ እኛ ቀድሞውንም እንግዶችና መፃተኞች ነው፡፡ እኛ ክርስቲያኖች እንግዶችና መጻተኞች የሆነው የስጋ ኑኖዋችን ጊዜያዊ አንደሆነና ከስጋ ተለይተን ከጌታ ጋር ለዘላለም እንደምንኖር ስለምናውቅ ነው፡፡ ይህች ምድር የኛ ዘላለማዊ ቤት እንዳይደለች ስላወቅንና በምድር እንደ ጊዜያዊ ተላላፊዎች ለጊዜያዊ አላማ በእንግድነት ስለምንኖር ነው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ኢየሱስን ስለሚከተሉት ክርስቲያኖች የምድር ቆይታ ሲናገር ቀድሞውንም እንደ እንግዶችና እንደ መጻተኞች እንደሆነ ያስተምራል፡፡
ቀድሞም እንግዶች እንግዶች ስለሆንን ነው በአለማዊ ከንቱ ውድድር ውስጥ ገብተን የተጠራንለትን ኢየሱስን የመከተል አላማ የማንተወው፡፡ በመጨረሻ ለእርሱ እንዴት እንደኖርንለት የሚጠይቀን ጌታ እንዳለ በማወቅ ነው በምድር ላይ እንደ እንግዳና ተላላፊ የምንኖረው፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡11
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ዕብራውያን 11፡13-16
እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ፊልጵስዩስ 3፡20
እኛ ቀድመን በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች ነን፡፡ ቀድመን አንዴ በምድር ስንኖር እንግዶችና መጻተኞች ሆነናል፡፡ እግዚአብሄር በምድር ሁሉ ስለሚልከን ግን ከተወለድንበት ምድር ወደሌላ ምድር ስንሄድ እንግዳ አይደለንም፡፡ ሁለተኛ እንግዶችና መጻተኞች ልንሆን አንችልም፡፡
የምድር ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡ ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሄር ናት፡፡ ምድር ሁሉ የእግዚአብሄር ናት፡፡
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት: ዓለምም በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ፡፡ መዝሙር 24፡4
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ መናገር #አትፍራ #ታመን #እንግዶች #መጻተኞች

እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ

fear-eyeእግዚአብሔርም በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ፥ በዚህም ሕዝብ መንገድ አንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፥ እንዲህም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ፦ ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፦ ዱለት ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። ኢሳይያስ 8፡11-12
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15
መቼም ቢሆን ደግሞ ሁኔታን እንድንፈራ እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ አይናችን ከእግዚአብሄር ላይ ተነስቶ ሁኔታ ላይ ሲሆን ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት ይዛባል ፍሬያማነታችን ይቀንሳል፡፡
እኛ በክርስቶስ አምነን ከእግዚአብሄር ጋር የታረቅን ሁሉን የሚያውቅ አባት ነው ያለን፡፡ እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉን ቻይ የሆነ አምላከ ነው ያለን፡፡ ከእኛ በላይ ሊረጋጋ የሚገባው ከእኛ በላይ ከፍርሃት በላይ ሆኖ ሊኖር የሚገባው ከእኛ በላይ ከሁኔታዎች በላይ ሆኖ ሊወጣና ሊገባ የሚገባው ሰው የለም፡፡ እንዲያውም የጌታችንን ብርሃን የምናሳየውና የምናንፀባርቀው ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ሲሸፍን ነው፡፡ ኢሳያስ 60፡1
ለእኛ ግን ጨለማ አይሆንም፡፡ ለእኛ ግን መጥፊያ አይደለም፡፡ ለእኛ ግን በእድል የተሞላ ዘመን ነው፡፡ ለእኛ ግን ጌታን የምናሳይበት ትልቅ እድል ነው፡፡ ለእኛ ግን ዘመን ስለማይሽረው ስለአምላካችን ሃያልነት በግልፅ የምንናገርበት ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ ለእኛ ግን በአምላካችን ላይ የምንጓደድበት ዘመናችን ነው፡፡
ይህ ዘመን ለጨነቃቸው መፍትሄ አለ መንገዱ ይህ ነው ብለን የምናሳይበት ታላቅ መድረክ ነው፡፡ ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ህዝቡን ሲያስጠነቅቅ ይህ ሕዝብ፦ ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፦ ዱለት ነው አትበሉ፤ ንግግራችሁ አይደባለቅ ንግግራችሁ ይለይ፡፡ ሌሎች የሚቀድሱት የሌላቸው እንደሚሉት አትበሉ፡፡ ሌሎች አምላክ የሌላችውን ቋንቋ አትጠቀሙ፡፡ ሌሎች የሚፈሩትንም አትፍሩ ፍርሃት ለእናንተ አይደለም ይላል እግዚአብሄር፡፡ መፈራት የማይገባውን እየፈራችሁ አግዚአብሄርን አታስቀኑት፡፡
መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት።1ኛ ጴጥሮስ 3፡15
እናንተ የምታመልኩት አምላክ የተለየ መሆኑን በድርጊታችሁ አሳዩ፡፡ የእናንተ ድርሻ ጌታን ብቻ መፍራትና ለእርሱ ብቻ የተለየ ስፍራ መስጠት ነው፡፡ ሌሎችን አማልክት ከሚያመልኩ ጋር ተቀላቅላችሁ እንደ እነርሱ የሽንፈት ወሬ እያወራችሁ እርሱን ከሌሎች አማልክት ጋር አትቀላቅሉት፡፡ እግዚአብሄር በልባችሁ ብቸኛውን ስፍራ ይፈልጋል፡፡
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ኢየሱስ #ጌታ #ቀድሱት #መዳን #እምነት #አትፍሩ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ

ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ

considerህይወት ጥንቃቄን የሚጠይቅ የስራ ሃላፊነት ነው፡፡ ይህን ሃላፊነት በሚገባ ልንወጣው እንችላለን ወይም ደግሞ ይህን ሃላፊነት በሚገባ ላንወጣው እንችላለን፡፡ ማቴዎስ 25፡14-23
ልቡን በመንገዱ ላይ ሳያደርግ ሳያስብ ፣ ሳያስተውል በዘፈቀደ የሚኖር ሰው አለ፡፡ ይህ የህይወት እውነታ ነው፡፡ አንዳንዱ እግዚአብሄርን ሲያስደስት ይኖራል አንዳንዱ ሲያሳዝነው ዘመኑ ያልፋል፡፡ እግዚአብሄር አባቱን የሚታዘዝ ልጅ አለ፡፡ እንዲሁም አባቱን የማይታዘዝ ልጅ ደግሞ አለ፡፡
ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። ሚልክያ 3፡17
ህይወታችንን በየጊዜው ካልመረመርንና ካልፈተሽን ግን ካላስተዋልን ማመፃችንን የምናውቀው ከእለታት አንድ ቀን ከረፈደ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ አስተውሉ የሚለው ጥሪ መስማት ወይም ልባችሁን በመንገዳችሁ አድርጉ የሚለው ትእዛዝ መታዘዝ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ኢየሱስ ስለዘሪው ምሳሌ ሲያስረዳ ቃሉ ሲዘራበት ሙሉ ፍሬ የሚያፈራው አይነት ልብን ሲናገር የሚያስተውል ብሎ ይገልፀዋል፡፡ ማስተዋል ማለት ደግሞ በቀጣይነት ማስታወስ አለመርሳት ሁሌ ማሰብ ከአእምሮ አለመጥፋት በምንወስነው ውሳኔ ሁሉ ማገናዘብ ከግምት ውስጥ መክተት ማለት ነው፡፡
በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል። ማቴዎስ 13፡23
ስለዚህ ነው በየጊዜው ከምንሰራው ከማንኛውም ነገር አለፍ ብለን ራሳችንን ማየት ያለብን፡፡ በተለይ በዚህ በፈጣንና ለማሰብ ጊዜ በማይሰጥ ዘመን ጊዜያችንን መስዋእት በማድረግ ጊዜ ወስደን የምናስብበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባናል፡፡
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
በየጊዜው የማይፈተን ህይወት በትክክለኛ መንገድ ላይ እንዳለ ምንም ማረጋገጫ የሌለው የብክነት ህይወት ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #መዳን #እምነት #ማስተዋል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ማሰብ #መሪ

ወደር የለሽ ብልፅግና

Road to successበክርስትና ህይወታችን አድገን አድገን የመጨረሻው የስኬትና የብልፅግና ደረጃ ምን እንደሆነ ማወቅ ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስንደርስ እንድናውቀውና እንድንረካ “ይሄ ነው” እንድንል ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡
ስለዚህ ደረጃ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ አስተያየት አላቸው፡፡ ይህንን ሁሉ አስተያየት ብንሰማ እንስታለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሚለውን ከሰማን ግን እናርፋለን፡፡
የክርስትና ህይወት ግቡ ምንድነው? የክርስትና ህይወት የስኬት ጣራው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ በሚገባ ሊመልስልን ሙሉ ስልጣን ያለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ደግሞ እውነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ኦሪጂናል የእግዚአብሄር ሃሳብና ፈቃድ ነው፡፡
የእግዚአብሄር ሰው ደረሰበት የሚባለው ምን ሲኖረው ነው? የጌታ ሰው እንደው ህይወቱ ሲያስቀና የሚያስብለው ምንና ምን ሲኖረው ነው? የሚለውን ጥያቄ መፅሃፍ ቅዱስ በሚገባ ይመልሰዋል፡፡
ክርስቲያን በለፀገ የሚባለው ሚሊየነር ሲሆን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ተሳካለት ደረሰበት የሚባለው ዝነኛ ሲሆን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ደረሰበት ይህ የተሳካለት ሰው ነው የሚባለው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን ሲከተል ነው፡፡ ክርስቲያን ደረሰበት የሚባለው እግዚአብሄር በህይወቱ ላስቀመጠው ሃላፊነት የሚያስፈልገው ነገር ካልጎደለበት ነው፡፡ ክርስቲያን ተሳካለት የሚባለው ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ፍላጎት ካሟላ ነው፡፡
ጌታ ከመከተል የተሻለ የስኬት ደረጃ የለም፡፡ ጌታን ከመውደድ ያለፈ የብልፅግና ደረጃ የለም፡፡ ጌታን ከማምለክና እግዚአብሄርን ከመምሰል የላቀ የስምረት ደረጃ የለም፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ክብራችን አይፈቅድም !

bada-kaun-hindi-story-1ልጅነታችን ክብር አለው ልጅነታችን የእግዚአብሄር የቤተሰብነት አባል ታላቅ ክብር አለው፡፡ እንደ ልጅነታችን ክብር የማይስማማ ምንም ነገር ለማድረግ እንፈልግም፡፡ ከልጅነት ክብራችን ጋር የማይሄድ ማንኛውም ጥቅም እንንቀዋለን፡፡ ክብራችን ተነክቶ የምናገኘውን ጥቅም ከምናገኝ ሞት ይሻለናል፡፡
እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡15
አንዳንድ ሰዎች ሃዋሪያው ጳውሎስ ጌታን የሚያገለግለው ስለሚጠቀም ነው ጥቅሙ ቢቀርነት አገልግሎቱን ያቆማል የሚል አመለካከት ለነበራቸው ሰዎች ለማሳየት ሰዎች የሚሰጡትን ስጦታ አልተቀበለም፡፡ ምክኒያም ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡3-4
 • ለመዋሸት ክብራችን እይፈቅድም
ውሸት ከፍርሃት ይመነጫል፡፡ እኛ ደግሞ በፍቅር የምንኖር ስለሆንንና ፍፁም ፍቅርም ፍርሃትን አውጥቶ ስለሚጥል አንዋሽም፡፡ ከምንዋሽ በውሸት የሚመጣው ጥቅምን ቢቀርብን ይሻለናል፡፡ የልጅነትን ክብራችንን እንዲነካ ለምንም ነገር አንፈቅድም፡፡ እውነትን የማንናገርለት ነገር የእኛ እንዳልሆነ እናምናለን፡፡
እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም። ኢሳይያስ 52፥12
 • ለመለማመጥ ክብራችን አይፈቅድም በመሃላ በመለማመጥ በብዙ ቃልና በብዙ ጭንቅ ሰዎችን ልናሳምን አንጥርም፡፡ በእግዚአብሄር እንታመናለን፡፡ እግዚአብሄር ያላደረግልንን ነገር አንወስድም፡፡ የራሳችንን ሃይል ጨምረን የምናመጣው ነገር በእውነት የእኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ያላደረገልንን ነገር ሁሉ የእኛ እንዳልሆነ ነው የምንቆጥረው፡፡
በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። ማቴዎስ 5፡36-37
 • ክብራችን ነውረኛን ረብ አይፈቅድም የቤተሰቡ ደረጃ ክብር የሌለበትን ጥቅም ያስንቃል፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ ነው የምናምነው፡፡ በነውር በወስላታነት በታማኝነት ያልሆነ ጥቅምን እንንቃለን፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ እናምናለን፡፡
ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡9
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
 • ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም ፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ መስራት ሲችል እራሱ እየሰራ የሚያስፈልገውን ያሟላ ነበር፡፡
ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም። 2ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡8
 • ከስስታም ሰው ለመቀበል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
ሰው የሚያደርግልንና የሚሰጠን ደስ ብሎት ከልቡ ካልሆነ እየሰሰተ ከሚሰጠን ሰው ለመቀበል ክብራችን እይፈቅድም፡፡ ሰው በልቡ ባይበላ እያለ ከሚሰጠን መራብ ይሻለናል፡፡
የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፤ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ። ምሳሌ 23፡6-8
 • ወንጌልን ዝቅ አድርጎ ለሚያይ ሰው ጋር መከራከር ክብራችን እይፈቅድም፡፡ የወንጌልን ክብር ከማይረዳ እንዲያውም ልንጎዳው እንደመጣን ከሚያስብ ሰው ጋር በክርክር ጊዜያችንንና ጉልበታችንን መጨረስ ክብራችን አይፈቅደውም፡፡
በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ። ማቴዎስ 7፡6
 • ከሰነፍ ጋር ለመመላስ ክብራችን አይፈቅድም፡፡ እውነትን ለማወቅ ፈልጎ ከሆነ እንረዳዋለን፡፡ እኛን ለማዋረድ ፈልጎ ከሆነ ለክርክር ጊዜ የለንም፡፡ አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት። ምሳሌ 26፡4
በክርክርና በጭቅጭቅ የሚገኘውን ጥቅም ለማግኘት ክብራችን አይፈቅድም፡፡ ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። ምሳሌ 20፡3
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ . . . የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡3
 • መስራት እየቻልን የሌላን ሰው እርዳታ አንጠብቅም፡፡
ለለበጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡11-12
 • ቃልኪዳናችን ከእግዚአብሄር ጋር ስለሆነ ስለመባረካችን ስለማደጋችንና ስለመለወጣችን ማንም ስጋ የለበሰ ክብሩን አንዲወስድ አንፈቅድም፡፡ ስለስኬታችን ክብሩን ከጌታ ጋር የሚሻማ ከሆነ ጥቅሙን እንተዋለን፡፡ ሰው እኔ አነሳሁት ከሚለን የሚያደርግልን ይቅርብን፡፡
አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ዘፍጥረት 14፡22-24
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#እግዚአብሔር #አምላክ #ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በፈቃዱ ውስጥ እንዳለው በምን አውቃለው?

leading-questions-800x400በእየሱስ የመስቀል ስራ ከእግዚአብሄ ጋር ከታረቅን በኋላ የመጀመሪያው በህይወታችን የምንፈልገው ነገር የእግዚአብሄርን ፈቃድ ነው፡፡ በህይወታችን የምንጠላውና የማንፈልገው ነገር ደግሞ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ መገኘትን ነው፡፡
አብዛኛው ክርስትያን በህይወቱ የሚፈልገው ዋና ነገር ምን እንደሆነ ቢጠየቅ የሚመልሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግና እግዚአብሄርን በህይወቱ ማክበር ነው፡፡
ግን አንዴት ነው የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስጥ መሆኔንና አለመሆኔን የማውቀው የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስጥ መሆናችንን ለማወቅ የሚረዱ ሰባት ነጥቦች፡፡
1.የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ከምንጠማው በላይ እግዚአብሄር ፈቃዱን እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ እንዲያውም ሲጀመር የፈጠረን ፈቃዱን እንድናደርግ ለክብሩ ነው ፡፡ ፈቃዱን አንድንረዳና እንድናደርግ ሙሉ ለሙሉ አብሮን ይሰራል፡፡
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳይያስ 43፡7
2. የእግዚአብሄርን ፈቃድ መረዳት ለሁላችን የተሰጠ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድን መረዳት ለጥቂት ሰዎች የተሰጠ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አማኝ የተሰጠ ዕድል ነው፡፡ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ዮሃንስ 10፡4-5
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ዮሃንስ 10፡14
3. የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስብስብና ለመረዳት የሚያስቸግር አይደለም፡፡ ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3
4. የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንረዳው ከተናጋሪው ችሎታ እንጂ ከሰሚው ችሎታ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፈቃዱን የሚያሳውቀን በመስማት ደረጃችን ወርዶ በሚገባን መንገድ ነው፡፡ ፈቃዱን ለማወቅ እስከፈለግን ድረስ እስኪገባን ድረስ ይናገረናል፡፡
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል። ዮሃንስ 7፡17
5. በጣም አስደናቂ በሆነ በደመናና በታላቅ ድምፅ አልተናገረንም ማለት እየመራን አይደለም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር አብዛኛውን ጊዜ በልባችን በለሆሳስ ነው የሚናገረን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሄርን ምሪት እንዲሁ እንረዳዋለን እንጂ ማስረዳት ከባድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር ግን እናውቀዋለን፡፡
እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። 1ኛ ነገስት 19፡11-12
6. በአጠቃላይ እግዚአብሄር በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ ደስተኛ ካልሆነ ይናገረናል፡፡ እግዚአብሄር ተበሳጭቶብን ኖሮ ኖሮ ድንገት ሲደሰትብን አይደለም የሚናገረን፡፡ እግዚአብሄር በእኛ በደረስንበት ደረጃ ባለንበት ሁኔታ ደስተኛ ነው፡፡ ያልተደሰተበት ነገር ካለ ያሳየናል፡፡ እኛ ራሳችንን ከምንረዳው በላይ እርሱ እኛን ይረዳናል፡፡
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ሮሜ 8:1
7. ፈቃዱን ለማድርግ መፈለግንና መነሳሳትን በምህረቱ የሚሰጠን አግዚአብሄር ነው፡፡ ስለ መልካምነቱ እንዲሁ ማድረግን የሚሰራው እርሱ ራሱ ነው፡፡
ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ፊልጵስዩስ 2፡10

We can Live Beyond our Generation

 
600_top_baby_namesWe are a part of generations. We build a foundation for the next generation and we actually shape it in what we say and do. We contribute to the success or failure of the next generation of believers. We can set a practical example for the Christian generation to come.
We desire that the generation coming obey the king of Glory we happily submit to. Our concern is how we influence the next generation while we are living in ours. We want to know how we effectively influence the next generation to facilitate for their lives of following Jesus. We want to be a role model for the people around us now and to leave foot-prints for the next generation.
We don’t just live for ourselves only. We also have the responsibility of the next generation to come. Our daily godly lives give a fuel to the next generation to be on fire for God. How we behave in this will encourage or discourage next. The way we worship God and serve him will be used as a measuring tool for the generation to come.
What we say and do in our generation actually influence the next one. We have the great opportunity of being a role model in what we say and do. But you have carefully followed my doctrine, manner of life, purpose, faith, longsuffering, love, and perseverance 2 Timothy 3:10
We can be real models of following Jesus wholeheartedly for the next generation to look up to. We can be good examples in the high regard we give to the word of God in our daily lives for the next generation.
We can be examples of faith-living. We can facilitate for their rising. We sacrifice for their comfort. We encourage the next to sacrifice more by what we sacrifice now.
A generation that will see us as fathers and mothers of faith is coming. We are here to contribute for the advancement of the Kingdome and presence of God in our generation and the generation to come.
We want as many as of our children, grandchildren and great grandchildren will follow Jesus if he tarries. We want as many of them minister the gospel. We want them to follow the pure teaching of Jesus without compromise.
It is only by living for God and for him only that we can give the next generation a practical example how to follow Jesus.
I am reminded of your sincere faith, which first lived in your grandmother Lois and in your mother Eunice and, I am persuaded, now lives in you also. 2 Timothy 1:5
#generation #model #example #church #legacy #Christian #Jesus #God #Abiywakuma #Abiywakumadinsa #salvation #abiydinsa #Facebook

The Way to Glory

sun-shining-through-clouds-1920x1200-wallpaper280202We want God to use us mightily. We ask God “use me and I will do whatever it takes”. When the time to pay the price that isn’t expected comes, we think of going back to our comfort zones. We feel to drop everything thinking it is too much.
Hold on, these are what the Bible teaches about temptation.
 • You are not the only person When you understand that everyone is tempted it gives you the energy to bear it.
No temptation has overtaken you except what is common to mankind. 1 Corinthians 10:13
 • There will never be too much price to pay compared to the glory coming
I consider that our present sufferings are not worth comparing with the glory that will be revealed in us. Romans 8:18
 • God will always provide a way out also. We trust our father God to have the answer for the test. It is on Him.
But when you are tempted, he will also provide a way out so that you can endure it. 1 Corinthians 10:13
 • God’s faithfulness doesn’t allow Him to let us be tempted beyond what we can bear.
And God is faithful; he will not let you be tempted beyond what you can bear. 1 Corinthians 10:13
 • The wisdom that comes from God works for us in this situation. One of the meanings of wisdom is to know what to do when we don’t know what to do.
Whenever you face trials of many kinds, If any of you lacks wisdom, you should ask God, who gives generously to all without finding fault, and it will be given to you. James 1:2, 5
 • We are benefited from persevering in the test of life. It makes us matured lacking nothing. Because you know that the testing of your faith produces perseverance.
Let perseverance finish its work so that you may be mature and complete, not lacking anything. James 1:3-4
 • Our response should be rejoicing as God is in control and things are actually working together for our good.
Consider it pure joy, my brothers and sisters, whenever you face trials of many kinds, James 1:2

ስልጣኑ በእጃችን ነው !

aid970661-728px-Explore-Layers-in-the-Mind-and-Live-Beyond-Them-Step-1-Version-2 (1)ሰው ሲፈጠር ፈቃድ ያለው ተደርጎ ስለተፈጠረ አንድን ነገር ከማድረጉ በፊት ያስባል ምን ማድረግ እንዳለበትም ይወስናል፡፡ አስቦ የወሰነ ሰው የሚያደርገው እንዳሰበው እንደዚያው ነው፡፡
በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ . . . ምሳሌ 23፡7
ስለዚህ ነው ሁልጊዜ ስለመስረቅ የሚያስብ ሰው ሌባ ነው፡፡ ስለ ጥላቻ የሚያስብ ሰው የመውደድ አቅም ሊኖረው አይችልም፡፡
ሰው እርምጃውን ማስተካካል የሚችለው በሃሳብ ደረጃ ነው፡፡ ሰው በሃሳብ ደረጃ ብቻ ነው ምን ማድረግ እንዳለበት ሊወስን የሚችለው፡፡ ሰው ግን ሃሳቡን ሳይቆጣጠር ወደ አእምሮው የሚመጣውን ክፉ ሃሳብ ሁሉ እያሰበ መልካም ሰው እሆናለሁ ብሎ መጠበቀ እንክርዳድ ዘርቶ ስንዴን ለማጨድ እንደ መጠበቅ ነው፡፡ ሰይጣን ሰውን እጁን ጠምዝዞ በግድ ሃጢያትን ማሰራት አይችልም፡፡
ሰይጣን ሰውን ሃጢያት ሊያሰራ ሲመጣ የሚልከው ሃሳብን ነው፡፡ ሰው ሃሳቡን ከተቀበለውና ካስተናገደው ለመፈፀም የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡
ሃሳቡን ግን በፍጥነት ከተቃወምነውና ከጣልነው ክፋት ላለመስራት አቅም ይኖረናል፡፡ ሃሳባችንን ካልተጠቀመ በስተቀር ሰይጣን ሃጢያት ሊያሰራን በፍፁም አይችልም፡፡
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3
ምን ማሰብ እንዳለብንና እንደሌለብን የምንወስነው እኛ ነን፡፡ በማንኛውም ጊዜ ሃሳብ ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሃሳቡን ለማስተናገድም ሆነ ለመጣል ስልጣኑ በእኛ እጅ ነው፡፡ ሃሳቡን ካላስተናገድነው በእኛ ላይ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ህይወታችንን በንፅህና ለመጠበቅና ለእግዚአብሄር የምንጠቅም ለመሆን የእግዚአብሄርን ቃል በተለይም እነዚህን አስቡ ተብሎ የተነገረውን ብቻ ማሰብ ያለብን፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8 ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum…

ራዕይ ግዴታ ነው!

vision1ሰው በህይወት እንዲከናወንለት የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ አለበት እንጂ ሰው በድንገት እንደ እድል አይከናወንለትም፡፡

በህይወይት ለመከናወን ራዕይ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ራዕይ የሌለው ሰው የትም አይደርስም፡፡ ሰው ህይወቱን በሚገባ ተጠቅሞ ፍሬያማ እንዲሆን ራዕይን መከተል ወሳኝ ነው፡፡

ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። ምሳሌ 29፡18
ሰው ራዕይ አለው ወይም ባለራዕይ ነው የሚባለው ለህይወቱ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ወይም አጀንዳ ሲያውቅና ሲከተል ነው፡፡
 • ራዕይ ምኞት አይደለም፡፡
በህይወታችን የምንመኛቸው ውይ ይህ ቢሆንልኝ የምንላቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ መልካም ናቸው አንዳንዶቹ ግን መልካም ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ራዕይ ግን የሰው ምኞች በራሱ ሊደርስበት የሚፈልገው ነገር አይደለም፡፡ራዕይ የሰው ምርጫና ፍላጎት አይደለም፡፡
 • ራዕይ እድል አይደለም፡፡
ራዕይ በሃገሪቱ ላይ ያለውን የስራ እድል ወይም በአካባቢው ያለውን ክፍተት በመመልከት የሚመርጡት የስራ እድል አይደለም፡፡ ራዕይ በመመልከት የምንከተለው ነገር አይደለም፡፡ ራዕይ ምድራዊ እውቀታችንን አሰባስበን የምንገነባው የፕሮጀክት እቅድ አይደለም፡፡ ይህ ራዕይ ሳይሆን ይህ ምድራዊ እውቀት ነው፡፡
 • ራዕይ ማየት ነው
ራዕይ የእግዚአብሄርን የተለየ አጀንዳ ማየት ነው፡፡ ራዕይ እግዚአብሄር በልቡና በነፍሱ እንዳለ ማድረግ ነው፡፡
የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል። 1ኛ ሳሙኤል 2፡35
እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና። ዕብራዊያን 8፡5
ራዕይ እግዚአብሄር ስለህይወታችን ያየውን አይቶ መከተል ነው፡፡ በራዕይ ስንመራ እግዚአብሄር አብሮን ይቆማል፡፡ የጉዞዋችን ሁሉ ወጪው በእርሱ ነው፡፡ ስራውን ለመፈፀም የሚያስፈልገውን አቅራቦት ሁሉ ይሰጠናል ያበረታናል እንዲሁም በየጊዜው ይመራናል ፡፡
በዚህም እግዚአብሄር በምድር ላይ ያዘጋጀልንን ስራ ሰርተን በምድር እናከብረዋለን፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum…

የአገልጋይነት ስሪታችን

wash_feet.jpgእግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር በምድር ላይ ያለውን ችግር እንዲፈታ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የሚፈጠረው ለሰዎች ከሚያስፈልገው ልዩ ችሎታና /talent/ ተሰጥኦ ጋር ነው ፡፡
በምድር ላይ የተፈጠርነው ከእኛ ለተሻለ ነገር ነው፡፡ የእኛ በምድር ላይ የመወለድ አላማ ከእኛ ለሚበልጥ አላማ ነው፡፡ እኛ በምድር ያለነው በዋነኝነት ለሌላው ሰው ነው፡፡ በምድር ያለነው ሌላውን ለማገልገልና ለመጥቀም ነው፡፡ ሰውን እውነተኛ እርካታን የሚያገኘው ሌላውን የማገልገል ሃላፊነቱን ሲወጣ ብቻ ነው፡፡
ሰው ሌላውን ማገልገል ቸል ሲል ሁሉ ነገሩ ይዘበራረቃል፡፡ ሰው ሌላውን ከማገልገል ይልቅ ራስ ወዳድ ሲሆን ምንም የተሟላ ነገር ቢኖረውም እንኳን ህይወቱ ሰላም የሌለው ጎስቋላ ይሆናል፡፡
ለራሱ ብቻ ለመኖር እንደተፈጠረ በተሳሳተ መልኩ የሚያስብ ሰው ምንም ነገር ቢኖረው ባለው ነገር አይረካም፡፡ ራስ ወዳድ ሰው የእኔነት ጥማቱንና ረሃቡን አርክቶ አይዘልቀውም ስለዚህ ሰው ባለው ነገር አይረካም፡፡
ነገር ሁሉ ያደክማል፤ ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፤ ዓይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም። መክብብ 1፡8
ሰው ግን የተፈጠረው ለሌላው ሰው እንደሆነ ሲረዳና ሌሎችን ማገልገል ላይ ሲያተኩር በህይወቱ ይረካል የሚያጣውም ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ሰው የተፈጠረበትን ሰዎችን የማገለገል አላማ ሲያሳካ የራሱ ኑሮ ጥያቄ አይሆንበትም፡፡
ሰው ሌላውን ለማገልገል ለሌላው ጥቅም ስለተሰራ የምትፈልገውንም ነገር ሁሉ እንሰጥሃለን ስራ ግን አትስራ ቢባል ስራን ካልሰራ እንደተገደለ ይቆጥረዋል፡፡
ሰው የተፈጠረበትን ሰውን የማገልገል ክብር ሲረዳ ለሰዎች በመኖር ሰዎችን በማንሳት ሰዎችን በመጥቀም ይረካል፡፡ ሰው ሊያገለግል የሚችል በመልካምነት የተሞላ ሰውን ሊያነሳ የሚችል በሰው ህይወት ላይ ዋጋን መጨመር የሚችል ሰውን ማስደሰትና መጥቀም የሚችል እንደሆነ መተማመን ሲኖረው በህይወቱ ዘመን ሁኩ ሌሎች ላይ ዋጋ በመጨመር ላይ ያተኩራል፡፡
ምስኪን እኔ አስተሳሰብ ያለበት ሰው ግን ነጥቆ ሰብስቦ አከማችቶ ለራሱ ብቻ ኖሮ ምንም መልካም አሻራ ሳይተው ያልፋል፡፡ ስለዚህ ነው ለራሱ ብቻ የሚኖር ታሪኩ በመቃብር ያልቃል ለሌሎች የሚኖር ግን በጠቀማው ባነሳቸውና ባገለገላቸው ሰዎች አማካኝነት አሻራው ለዘመናት ይቆያል የሚባለው፡፡ እኔ ህይወትም መንገድም እውነትም ነኝ ያለው እየሱስ እንዲህ ይላል፡፡
እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም። ማቴዎስ 20፡28
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር ያድርጉ ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum…

 

Designed to Serve

wash_feetGod created man to solve problems. Every man is created with built-in talent to contribute to the advancement of others. We are born on earth for a purpose greater than us. We are not just born to eat, drink and die. We are born for others. we are born to serve others and add value in their lives.
Man is designed and created to serve others. Man is only satisfied in adding value in others. If man follows selfishness, he will be miserable as his design doesn’t allow that. Even if man gets everything under the sun, he will never be satisfied unless. He is only satisfied and a life well-lived when he serves others and live for them.
All things are wearisome, more than one can say. The eye never has enough of seeing, nor the ear its fill of hearing. Ecclesiastes 1:8
If a man is promised to be provided with everything and is prevented from working and serving others, it will be like killing the person. Only provision can’t satisfy the person, unless he works and contribute to the wellbeing of others. That is the design of man. For the person who serve others, provision isn’t a question at all.
If a person has a poor-me mentality he will never have the confidence to serve others. He will die in trying to be satisfied by gathering things thinking that satisfaction is found in accumulating material things.
But those who understand the glory of serving and benefiting others will live to serve others. They are confidence in what they can do in the lives of others beyond themselves.
It is said that the legacy of the person who lives for himself will end at his funeral but the legacy of the person who live for others will echo long after the burial through the persons served by him. Jesus answered I am the way and the truth and the life.(John 14:6) encourages us to serve other following his examples.
just as the Son of Man did not come to be served, but to serve, and to give his life as a ransom for many. Matthew 20:28
Click to share this article with others
#serve #design #service #addvalue #benefitothers #church #legacy #Christian #Jesus #God #Abiywakuma #Abiywakumadinsa #salvation #abiydinsa #Facebook

ጊዜው አሁን ነው!

clock-running-out-time-vector-illustration-character-31770782ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ ፣ እድሜያችንን መቍጠር አስተምረን፡፡ መዝሙር 90፡12
በምድር ያለን ጊዜ ምን ያህል አጭር እንደሆነ በተረዳን መጠን ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም እንተጋለን፡፡ የምድር ኑሮዋችን አጭር መሆኑን እስካላስታወስን ግን በተለያዩ ምክኒያቶች የምናባክነው ይበዛል፡፡
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። መዝሙር 39፡4
በምድር ላይ ያለን ጊዜ የተሰጠንን ስራ ለመጨረስ የሚበቃ እንጂ ምንም የሚባክን ትርፍ ጊዜ የለንም፡፡ በጊዜ አስተዳደራችን እጅግ የተሳካልን ብንሆን ጊዜያችንን ሙሉ ለሙሉ ብንጠቀምበት ነው፡፡ የልባችንም ጩኸት በምድር ላይ ምን ያህል እንደምንኖር ማወቅ ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ በምድር ለይ የምንኖረው ለአጭር ጊዜ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፤ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል። መዝሙር 144፡4
ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። ያዕቆብ 4፡14
እርግጥ ነው እግዚአብሄር በምድር ያለን ጊዜ አጭር እንደሆነ ይነግረናል እንጂ የሚቀረንን ቀን ምን ያህል እንደሆነ ቁጥሩን አይነግረም፡፡
እኛም የሚያስፈፈልገን ነገር ዛሬ ብቻ የእኛ እንደሆነና ዛሬን በሚገባ መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው፡፡ ዛሬን በሚገባ እስከተጠቀምንበት ድረስ ህይወታችንን ሁሉ በሚገባ እንጠቀምበታለን፡፡
በዛሬ ስኬታማ ከሆንን በህይወት ዘመናችን ሁሉ ስኬታማ እንሆናለን፡፡ አንዳንዴ ነገ ለጌታ ለመኖር ልዩና የተሻለ እድል ይዞልን እንደሚመጣ እናስባለን፡፡እንደዚያ በማሰብ በዛሬ ላይ ካለአግባብ እንዝናናለን፡፡ ነገ ግን ምን እንደሚያመጣ አናውቅም፡፡ ነገ ካሰብነው በላይ ተግዳሮቶችን ይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ ዛሬንም ነገንም በሚረዳን በእግዚአብሄር እንጂ በነገ መመካት የለብንም፡፡
. . . ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ያዕቆብ 4፡13
ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ። ምሳሌ 27፡1
መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ የምድር ጊዜያችን አጭር እንደሆነ ደጋግሞ ይነግረናል፡፡ በከንቱ የምንዝናናበትና የምናባክነው ትርፍ ጊዜ ጊዜ የለንም፡፡ ተርፎን የምናባክነው ምንም ጊዜ የለም፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገን ወደዛሬ አምጥተንም መኖር እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሄር ቀኑን ጊዜውን እንደከፋፈለው ሁሉ በህይወት ያሉትን ስራዎቻችንን በጊዜ ከፋፍሎዋቸዋል፡፡ ነገን ዛሬ ላይ አምጥተን ለመኖር መሞከር ጥበብ አይደለም፡፡ የነገን ተግዳሮት ዛሬ ለመፍታት መሞከር ህይወትን ካለአግባብ ለመቆጣጠር መሞከር ነው፡፡ ጠቢብ ለነገ ዛሬ ያቅዳል ነገር ግን የነገን ለነገ ትቶ የዛሬን ዛሬ ይሰራዋል፡፡ ዛሬን ለመኖር ያለን ዛሬ ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ . . . ዘመኑን ዋጁ። ኤፌሶን 5፡15-16
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ

God’s Purpose Prevails!

zen-kid-rock-water-blue-34572368 (2).jpgMany are the plans in a person’s heart, but it is the LORD’s purpose that prevails. Proverbs 19:21
God is a god of purpose. God created everything on purpose. God create us on purpose. He doesn’t do anything without planning.
God doesn’t rule the earth purposeless. God has a plan for everything happening on earth. God is an active leader of the earth, he isn’t just a spectator.God is an initiator.
God has interests in everything done on earth. When Job failed to control the fate of his life, He finally understood that God has a purpose. He finally acknowledged that nobody will stand against Him.
Then Job replied to the LORD: I know that you can do all things; no purpose of yours can be thwarted. Job 42: 1-2
The best thing we do is to search for the purpose of God for our lives instead of picking the most appealing idea on earth. Our wisdom is evaluated by our following after purpose of God and not coming up with a popular idea as how things are done.
The best thing man can do is to follow God’s purpose instead of trying to do what the majority’s best idea.
Even Apostle Paul, one of the most influential leaders of Christianity testified about following after the purpose of God instead of coming against it.
For we cannot do anything against the truth, but only for the truth. 2 Corinthians 13:8
Truth doesn’t need our support. It can survive by itself. Instead, we need the truth to survive. We shield ourselves with the truth for our own sake.
The wisest man on earth doesn’t want to come against the truth but for it. Anyone who wants establishment and survival in life will go for the truth. Going for the truth saves man from ineffective trial to change the purpose of God on earth.
How much you feel mighty, don’t ever try to change the purpose of God on earth. No one survived coming against His purposes. The wisest will drop his plans quick, search for God’s purpose and will following it.
Many are the plans in a person’s heart, but it is the LORD’s purpose that prevails. Proverbs 19:21
#godspurpose #wisdom #theplanofthelord #survival #powerofgod #grace #salvation #church #testimony #soulwinning #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

የእግዚአብሔር ምክር ይፀናል!

zen-kid-rock-water-blue-34572368 (2).jpgበሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረውን ነገር ሁሉ የፈጠረው በአላማ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራውን ነገር ሁሉ የሚሰራው በእቅድ ነው፡፡
እግዚአብሄር እንዳመጣለት የሚኖር አምላክ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ ለሚሆነው ለእያንዳንዱ ነገር ሁሉ እቅድ አለው፡፡ እግዚአብሄር እጁን አጣጥፎ የሚሆነውን እያየ አይደለም፡፡
ሰዎች ውስን ስለሆንንና ሁሉንም ነገር ማድረግ ስለማንችል ብለን ብለን ሲያቅተንና ከአቅማችን በላይ ሲሆን ዳግመኛ መሞከር ከንቱ ሲሆንብን ለቀን እንነዳለን፡፡ የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም እንላለን፡፡
የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን። ሐዋሪያት 21፡14
እግዚአብሄር ጀማሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ ስለሚሆነው ነገር የመጀመሪያው መሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ እንዲሆንለት የሚፈልገውም ነገር ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ነው ኢዮብ ሞከረ ሞከረና ከእግዚአብሄር ሃሳብ ጋር መጋፋት እንደማይችል ሲረዳ ለእግዚአብሄር እንዲህ አለ፡፡ ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡1-2
ስለዚህ ሰው በልቡ ያለውን ምርጥ ሃሳብ ለማድረግ ከመሞከር ይልቅ የእግዚአብሄር ሃሳብ አግኝቶ ማድረጉ ይመረጣል፡፡ ከሰው ልጆች እጅግ የተሻለ አሳብ ይልቅ የእግዚአብሄር አሳብ ይበልጣል፡፡ እጅግ ታላቅ ከተባለው የሰው አሳብ ይበልጥ የእግዚአብሄር ምክር ትበረታለች በምድር ላይ ትሆናለች፡፡
ሰው ጠቢብ የሚሆነው የሰውን የተሻለ አሳብ በማግኘት ሳይሆን የእግዚአበሄርን ምክር በመፈለግ ነው፡፡ ለሰው ብልህነቱ የሰውን አስገራሚ አሳብ መፈለጉ ሳይሆን ታዋቂና ዝነኛ ያልሆነችውን የእግዚአብሄን ፈቃድ መከተሉ ነው፡፡
ለሰው አስተማማኙና ተመራጩ ነገር ሰዎች ሁሉ በአንድ ድምፅ የተስማሙበትን ምርጥ አሳብ ለማድረግ መፍጨርጨሩ ሳይሆን የእግዚአብሄርን አሳብ መከተሉ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚያ ሁሉ ክብሩ ስለእውነት ሃያልነት እንዲህ እያለ ይመክረናል፡፡
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም 2ኛ ቆሮንጦስ 13፡8
እውነት በራስዋ ሃያል ነች፡፡ እውነት ምንም ደጋፊ አትፈልግም፡፡ ከእውነት ጋር የምንወግነው ለራሳችን ብለን ነው፡፡ ሰው የተሻለ ጠቢብ ከሆነ እውነትን ፈልጎ በእውነት ይተገናል እንጂ እውነትን ለመለወጥ አንድ እርምጃ አይራመድም፡፡ ሰው ብልህ ከሆነ እውነትን ፈልጎ ማድረጉ ከብዙ ትግልና መላላጥ ያድነዋል፡፡ የትኛውንም ያህል ሃያልነት ቢሰማን የእግዚአብሄር ምክር ላይ አንበረታም፡፡
ምንም ብንበረታ የእግዚአብሄርን ምክር ለመለወጥ መሞከራችን ጠቢብ አያደርገንም፡፡ ሰው መፅናት ከፈለገ ከምትፀናው ከእግዚአብሄር ምክር ጋር መወገኑ ወደር የሌለው ብልህ ያደርገዋል፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #ህብረት #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Love Adventure

Adventure_in_love.jpgThe life of love is adventure. whoever likes something unique and strong can take this life. Love isn’t for the everyone. 

 

We learn love diligently. It isn’t bestowed accidentally. We don’t find ourselves in love by chance. We don’t fall in true love. Love isn’t ordinary. True lovers who understand its value practice it and give themselves wholly to it. 

 

Love takes to identifying oneself to the loved one in understanding. And understanding others takes to give yourself to know them in humility. 

 

Love isn’t cheap and it isn’t for everyone. The life of love is the life of determination and perseverance not just accidental. The lazy don’t survive in the life of love as its standards are high. Love isn’t for the lazy as it takes to make an effort to diligently understand those who are different from us. The life of love isn’t for the wimpy and the weak. Love tests our endurance thoroughly . Love takes to stand on the vow we give in the difficult situations. Love is so powerful that the only reason that makes us continue is the word of promise that we give to the other. 

 

Love is so valuable that it is the only way we stand the true test of patience in it. Love is so unique and constant that we care for others not only in the good days but also in the days that are not so pleasant.

Love isn’t a straight line. It takes to stand the ups and the downs of life in patience and without giving up. Love isn’t emotion as it takes to stand in the midst of the change of our emotion. 

 

Love isn’t for the proud as it takes to value others above yourself. Love isn’t for the selfish as it so high life that it diligently works to add value in the life of others. And love is so satisfied din its progress that it always rejoices in the success of others. 

 

Do nothing out of selfish ambition or vain conceit. Rather, in humility value others above yourselves, Philippians 2:3 

 

Love isn’t for the poor-me mentality as it takes to see yourself rich who always have something to give to others. 

 

Love isn’t for the discontented as they constantly focus their lack in life. Love is for the contented and for those ready to give and share what they have. 

 

Love is so understanding and confident that it believes in someone when nobody believes in them. 

 

Love isn’t an easy task , it takes to make a room for your enemies in your heart. Love is a disciplined life style in which we don’t use our power to do evil to others when we are able to do it. Love is nothing less than an adventure. 

 

#Love #godislove #giving #compassion #church #Jesus #heart #AbiyWakumaDinsa #AbiyDinsa #facebook

ሁላችንም ሯጮች ነን

almaz ayana.jpgበእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡ 24-26
ሁላችንም እንሮጣለን ፡፡ ሁሉም ሩጫ ወደውጤት አያመጣም፡፡ ውጤታማ ሩጫ አለ ከንቱ ሩጫ አለ፡፡ የሁላችንም ሩጫ ለኦሎምፒክ ላይሆን ይችላል፡፡ ሁላችንም የኦሎምፒክን ሚኒማ ላናሟላ እንችላለን፡፡
ግን ሁላችንም በህይወት ለመሮጥ በሩጫው ባለቤት እግዚአብሄር በእየሱስ አዳኝነት ካመንን ብቁ ልንሆንና ሚኒማውን አሟልተናል መሮጥም እንችላለን፡፡ እንደ ማንኛውም ሩጫ ይህም የዘላለም ሩጫ ህግ አለው፡፡ ስለዚህ የዘላለም ውጤት ስለሚያስገኘው ሩጫ ህግ መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
 • ውጤት ለሁሉም አይደለም፡፡ የክርስትናውን ሩጫ ከሌላ የሚለየውና ደግነቱ ከአንድ እስከ ሶስት የወጣ ብቻ የሚሸለምበት እንደ አካል ብልት ሁላችንም ለተለያየ ተግባር ስለተጠራን በዚህ ሩጫ በሚገባ የሮጠ ሁሉ ይሸለማል፡፡
 • ለመዳን እየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ስላ ማመን ብቻ ሲጠይቅ ለመሸለም ግን ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ በክርስትና ህይወት የሚሸለመው በድንገት አይደለም፡፡ ለአክሊል በትጋት በውሳኔና በእውቀት የሰራ ይሸለማል፡፡ ለዚህ ነው መፅሃፍ ታገኙ ዘንድ ሩጡ የሚለው።
 • ሩጫ ትግስትንና ጥበብን ይጠይቃል፡፡ ሩጫ ሰውነትን መግዛትና ዲሲፒሊን ይጠይቃል፡፡ ውጤት ቁጥብነትን ስለሚጠይቅ ሯጭ የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሯጭ የሚበላውና የማይበላው አለ፡፡ ሯጭ በሩጫው ውጤት ለማምጣት ሰውነቱን በነገር ሁሉ ይገዛል፡፡
 • የህይወት ሩጫ ሽልማት ከማንኛውም የኦሎምፒክ ሽልማት ይበልጣል፡፡ የምድር ሽልማት የሚጠፋ ሽልማት ነው፡፡ ይህ ሽልማት ስንሞት አብሮን የሚሄድ ሽልማት አይደለም፡፡ ይህ ሽልማት የመሬት ስበት ይዞ የሚያስቀረው ከነፍስና ከመንፈሳችን ጋር አብሮን ወደሰማይ የሚሄድ አይደለም፡፡ የህይወት ሽልማት የዘላለም ነው፡፡
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። ዮሃንስ 6፡27 5.
 • ይህ የዘላለም ሽልማት ሩጫ በትኩረትና በአላማ የሚሮጥ ነው፡፡ በዚህ ሩጫ ላይ ስናተኩር በፊታችን ከሩጫችን የሚያስተጓጉሉንን እንቅፋቶች እናልፋለን፡፡ መንፈሳዊ ህይወታችን በቃሉ ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ ትኩረታችንን ሊከፋፍል የሚመጣውን የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል እንቃወማለን፡፡
በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። ማቴዎስ 13፡22 6.
 • ሩጫ ትግስት ፡ ጥበብና እርጋታን ይጠይቃል፡፡ የህይወት ሩጫ ማራቶን እንመሆኑ መጠን ጉልበት አለኝ ተብሎ የሚበረርበት አይደለም፡፡ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ዕብራውያን 12፡1
 • የሩጫ ወደር የሌለው ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው፡፡ እርሱን ተመልክተን እንደሱ ከሮጥን የማናሸንፍበት ምክኒያት የለም፡፡ እየሱስ በፊቱ ስላለው ዘላለማዊ ደስታ ብዙ ነገሮችን ንቋል፡፡
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
#ሩጫ #ትግስት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከእግዚአብሄር የመቀበያ ጥበብ

the-fastest-way-to-receive.jpgብዙዎቻችን እግዚአብሄር ፀሎታችንን እንደሚሰማ እናምናለን እንፀያለንም፡፡ እውነትም እግዚአብሄርም ፀሎትን የሚመልስ ህያው አምላክ ነው፡፡

ግን ስንቶቻችን ነን የፀሎት መልሳችንን እንዴት ከእግዚአብሄር እንደምንቀበል የምናውቅ? መፀለያችን ብቻ ሳይሆን እንዴት የፀሎታችንን መልስ ከእግዚአብሄር እንደምንቀበል ካላወቅን በስተቀር እግዚአብሄር ፀሎትን የማይመልስ ሁሉ ሊመስለን ይችላል፡፡

ወይም ደግሞ እግዚአብሄር እንደሚባርክ አምነን ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን እንሰጣለን፡፡ ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን በመስጠታችን ምንም እንደማይጎድልብን እናምናለን፡፡ እውነትም ነው ለእግዚአብሄር ሰጥቶ የጎደለበት ሰው የለም፡፡

ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን ስንሰጥ እግዚአብሄር ገንዘብን ሊሰጠን ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን ስንሰጥ እግዚአብሄር የሚሰጠን ገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡

በህይወታችን ከእግዚአብሄር የምንፈልገው ነገር ገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሄር የምንፈልገው ብዙ አይነት ነገር አለ፡፡ ገንዘብ ውስን ስለሆነ ገንዘብ ሊመልሳቸው የማይችላቸው ብዙ ጥያቄዎች በህይወታችን አሉ፡፡

እግዚአብሄርም መሃሪ ስለሆና የህይወታችንን የጊዜውን ጥያቄ በሚገባ መመለስ ስለሚፈልግ ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን ስንሰጥ የሚሰጠን ወይም መልሶ የሚባርከን በገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡ ከገንዘብ በላይ እጅግ አስፈላጊና ውድ ነገሮች በህይወታችን አሉ፡፡

እግዚአብሄር ገንዘብን ይሰጣል ገንዘብ ብቻ አይደለም እግዚአብሄር ሰላምን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር እርካታን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር ሞገስን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር እረፍትን ይሰጣል፡፡ የምንበላውን እህልና ውሃ እንኳን የሚባርከው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር በሽታን ከመካከላችን ያርቃል ፡፡ ዘጸአት 23፡25

እግዚአብሄር ሲባርክ አንድን ጥሩ ነገር እንድናደርግ በምሪት ይባርከናል፡፡ ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ እግዚአብሄር በልብ መነሳሳት ይባርከናል፡፡ የማይቻለውን ነገር እንድናደርግ ያልተለመደ ድፍረትን ይሰጠናል፡፡ እርሻን አርሰን እንድንበላ ጉልበትን የሚሰጠን እንኳን እግዚአብሄር ነው፡፡

በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል። ዘዳግም 8፡17

ነግደን እንድናተርፍ እግዚእብሄር ጥበብን ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሄር እንዲከናወንልን በሮችን ይከፍትልናል፡፡ ካለንበት ሁኔታ ውስጥ እንድንወጣ ቃልን በጊዜው የሚሰጠው እግዚአብሄር ነው፡፡ እነዚህን ፈላጊና ተፈላጊ የሚያገናኘው እግዚአብሄር ነው፡፡

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11

እግዚአብሄርን በህይወታችን የማንፈልግበት ሁኔታ የለም፡፡ እግዚአብሄርንም የሚባርከን በሁሉም መንገዶች ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ብልፅግና ማለት ብዙ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የምንፈልገውን ነገር በምንፈልግበት ጊዜ ማግኘት ነው፡፡

እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥ ኤፌሶን 3፡20

ከእግዚአብሄር መቀበላችን የተረጋገጠ ነውና ወደእግዚአብሄር መፀለያችንንና ለእግዚአብሄር መስጠታችንን እናብዛ፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

የሚያስፈልገው አንድ ነገር

one-finger.jpgበህይወት እግዚአብሄር እንዳለልን በልቡና በነፍሱ እንዳለ መኖር የከበረ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ይህ ነው ብለን በግምት በመኖር ህይወታችንን ከምናባክን እግዚአብሄር የሚፈልገውን አግኝተንና አድርገን ማለፍ ወደር የማይገኝለት መታደል ነው፡፡

እግዚአብሄር ምን እንደሚፈልግ እንድንገምትለትና እንድናደርገው አልጠየቀንም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገውን ግልፅ አድርጓል፡፡ የሚያስፈልገው ብዙ ነገር አይደለም፡፡

ሰዎች እግዚአብሄርን ለማስደሰትና ለማስደነቅ በራሳቸው የሚሄዱት ብዙ መንገዶች እግዚአብሄርን አያስደንቁትም፡፡ ሰዎች የሚያስፈልገውን ነገር ሳያደርጉ በአገልግሎት ስም ጭምር እግዚአብሄርን ለማስደሰት የሚያደርጉት ነገሮች እግዚአብሄር ጎሽ አይላቸውም፡፡

እግዚአብሄር የሚፈልገውን ያውቃል የሚፈልገውም እንዲደረግለት ይፈልጋል ይጠብቃል፡፡

እየሱስ እነማርያም ቤት ሲሄድ አላማው ቤተሰቡ የእግዚአብሄርን ቃል እንዲሰሙና ፈቃዱን እንዲረዱ ነው፡፡ ማርታ ግን በቤት ስራ ልታገለግለው ጉድ ጉድ በማለትዋ እየሱስ ወደቤተሰቡ የሄደበትን አላማ ፈፅሞ ሳተችው፡፡ እየሱስና ማርታ ተላለፉ፡፡

በዚያ ሰአት የማርታ ከምንም አስቀድሞ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ወደር የማይገኝለት የህይወት ምርጫ ነበር፡፡ እርስዋ ግን እየሱስ ይፈልጋል ብላ ያሰበችውን እንጂ እየሱስ የፈለገውን አላደረገችም፡፡

እርስዋ ለእየሱስ መልካም ነው ብላ የገመተችውን በማድረግ ልታገለግለው ደፋ ቀና ትል ነበር፡፡ ያ እየሱስን አላስደሰተውም፡፡ ብዙ ነገር በማድረጉዋ እያገለገለች እያስደሰተችው መሰላት፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችን ቅድሚያ እንድንሰጠው የሚፈልገው ነገር ቃሉን መስማት ነው፡፡ ከኑሮ ከስራ ከአገልግሎትም ከሩጫም በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚያስፈልገው ቃሉን መስማት ነው፡፡

እንዲያውም እየሱስ የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው አለ፡፡ የሚያስፈልገው በአለም ሩጫና ባተሌነት ሳይወሰዱ ረጋ ብሎ እግዚአብሄር ከኔ ምን ይፈልጋል ብሎ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማግኘት ጊዜን መስጠትና ያንን ማድረግ ነው፡፡

ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው። ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች። ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው። ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። ሉቃስ 10፡38-42

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

የአይን መከፈት

ምን ይጠቅማል ?

ምን ይጠቅማል ?

 

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

 

ሕይወታችሁ ምንድር ነው?

tea.jpgበአለም ላይ ያለው ነገር ሁሉ አላፊ ጠፊም ነው፡፡ የሚታየው ነገር ሁሉ ያልፋል፡፡ ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ ምክኒያቱም የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው ነው የመጣው፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

አሁን በአይን የሚታየው ነገር ሁሉ ሃላፊ ነው ፡፡ መንፈሳዊው አለም በአይን የማይታየው አለም ብቻ ነው ቋሚና የማያልፈው፡፡

የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡18

የሰውን ህይወት እንኳን ስንመለከት ከዘላለም ጋር ሲነፃፀር ህይወቱ ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ነው፡፡

ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። ያዕቆብ 4፡14

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በላይ ያለውን እሹ የሚለው፡፡ በላይ ያለው መንፈሳዊው አለም ዘላቂውና ቋሚው አለም ብቻ ነው አስተማማኝ ፡፡ እርሱ ብቻ ነው የማያልፈው፡፡

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2

ለዘላለም የሚኖረው ሰማዩንና ምድሩን የፈጠረው የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እንዲሁም የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደርግ ሰው ለዘላለም ይኖራል፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡17

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

በላይ ያለውን እሹ

ምን ይጠቅማል ?

የክህደት ጥሪ

ልጅነቴ

 

#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እንፍዋለት #ሕይወታችሁ #ዘላለም #የእግዚአብሄርቃል #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከፊታችን ያሉ መልካም ቀኖች

tongueእግዚአብሄር መልካም ነው፡፡ ለእኛ ለልጆቹ ሁል ጊዜ የተሻለ ነገር አለው፡፡ ከፊታችን እስከዛሬ ካየናቸው የተሻሉና መልካም ቀኖች እየመጡ ነው፡፡
 
እነዚህን መልካም ቀኖች ማየት የሚፈልግ ማድረግ ያለበት ነገሮች አሉ፡፡ መልካም ቀኖች ይመጣሉ ግን እነዚህን ቀኖች ማየትና አለማየት የእኛ ፋንታ ነው፡፡ በአንደበታችን የምናደርገው ነገር መልካሞቹን ቀኖች እንድናይ ወይም እንዳናይ ያደርጉናል፡፡
 
ህይወትን የሚወድና መልካሙንም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው በንግግሩ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሰው እንደፈለገ እነደልቡ እየተናገረ መልካሞችን ቀኖች አያለው ማለት ዘበት ነው፡፡
 
 
ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡10
 
ምክኒያቱም አንደበት እሳት ነው ፡፡ ካላግባብ ከተጠቀምንበት የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፡፡
 
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ ያዕቆብ 3፡6
 
 
አንደበታችንን የማንገታ ከሆንን ሊረዳን ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን የተሰጠንን ቅዱሱን የእግዚአብሄርን መንፈስ እናሳዝናለን፡፡
 
ሰው ራሱን ከመልካም ቀኖች ውድቅ ላለማድረግ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ሊከለክል ግዴታ ነው፡፡
 
 
ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ኤፌሶን 4፡29-30
 
ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡10
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
 
 
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አንደበት #ምላስ #መልካምቀኖች #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እንደ ንጽሕት ድንግል

10virgins.JPGበእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2-3

ሃሳብ በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ ሃሳብ ይነፃል ሃሳብ ይበላሻል፡፡ ሃሳብ ሲበላሽ ቅንነትና ንፅህና ይለወጣል፡፡ ቅን እና ንፁህ የነበረው ሰው ጠማማ እና የተጣመመ ሃሳብ ያለው ሰው ይሆናል፡፡

ሰው ሃሳቡ ሲበላሽና ቅንነቱ ሲለወጥ በእግዚአብሄር ማመኑን ያቆማል፡፡ ይህ በእግዚአብሄር ላይ ያለው እምነቱ መቀነሱ የሚታወቀው በአፉ ተናግሮት አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ማመን የከበደው ሰው በድርጊቱ ይታወቃል፡፡

ሰው ቅንነቱ ሲለወጥ ለመንፈሳዊ መሪዎች ያለው አክብሮት ይቀንሳል፡፡ ሰው ሃሳቡ ሲበላሽ ለቤተክርስቲያን ያለው መሰጠት ይቀንሳል፡፡ ለቤተክርስቲያን ገንዘቡን ሰጥቶ የማይጠግበው ሰው ቅንነቱ ሲበላሽ መጠራጠር ይጀምራል፡፡ ሰው ቅንነቱ ሲበላሽ የእግዚአብሄርን ህዝብ ማገልገል መፍራት ይጀምራል፡፡ የእግዚአብሄርን ህዝብ በትጋት በማገልገል የሚታወቀው ሰው ሃሳቡ ሲበላሽ ጊዜውንና ጉልበቱን መሰሰት ይጀምራል፡፡ ሰው ቅንነቱ ሲበላሽ ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር ህብረት ላለማድረግ ሰንካላ ምክኒያቶች ይበቁታል፡፡ ሰው ቅንነቱ ሲበላሽ ለሰዎች ስለጌታ ከሃጢያት አዳኝነት መናገር ይቀንሳል፡፡ ሰው ቅንነቱ ሲበላሽ ከፀሎት ይልቅ ሌሎች ነገሮች ያምሩታል፡፡

ጌታ እንዲነግዱና እንዲያተርፉ ንጉስ መክሊትን ስለሰጣቸው ምሳሌ ሲናገር አንድ መክሊት የተሰጠው ለንጉሱ ያለው ሃሳብ ስለተበላሸና ቅንነቱ ስለተለወጠ መክሊቱን ወስዶ ቀበረው፡፡

አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ማቴዎስ 25፡18, 24-25

እንዲነግድ እንዲያተርፍና እንዲያድግ እንዲሾም የተሰጠውን መክሊት የቀበረው ምክኒያቱ የንጉሱን አላማ ስለተጠራጠረና ለንጉሱ ያለው ሃሳብ ሰለተበላሸ በዚያም ቅንነቱ ስለተለወጠ ነው፡፡

እግዚአብሄርን ማገልገል ታላቅ ጥቅም እና ታላቅ እድል ነው፡፡ ራሳችሁን ተመልከቱ ተመለሱም፡፡ ሃሳባችሁ እንዳይበላሽና ቅንነታችሁ እንዳይለወጥ ትጉ፡፡ ሃሳባችሁ እንዲለወጥ የሚመጣውን ማንኛውንም ሃሳብ አትቀበሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ እመኑ፡፡

በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2-3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ብፁሃን የዋሆች

የአእምሮ ገዳም

ሰነፍ በልቡ

የትኛው ጥበብ ?

#አተረፈ #ንፅህና #ቅንነት  #ንጉስ #መክሊት #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት

ተቃወሙ!

resist.jpegየዲያቢሎስ አላማ አንድና አንድ ነው፡፡ ዲያቢሎስ ከመጣ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ለሌላ ነገር አይመጣም፡፡

ዲያቢሎስንብ የመጋዣው መንገድ ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ ማመፅ ወደ እግዚአብሄር አለመጠጋትና ከሃጢያት ጋር መጫወት ነው፡፡

ዋነኛው ታዲያ ዲያቢሎስን የመቃወሚያው መንገድ ለእግዚአብሄር መገዛት ነው፡፡ ዲያቢሎስን የመቃወም ውጤታማው መንገድ ወደ እግዚአብሄር መቅረብ ነው፡፡

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ያዕቆብ 4፡7-8

ልጆች ሆነን ሸንኮራ ስንመጥ የምንጥለው ምጣጭ ዝንብን ይስባል፡፡ ዝንብን መከላከያው ውጤታማው መንገድ የዝንብ ማባረሪያና መግደያ አይደለም፡፡ ምክኒያቱም ዝንብን የሚስበው ቆሻሻ ስለሆነ ቆሻሻው እስካለ ድረስ ሁሌ ዝንብ ይሳባል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን ማሳደድ ተፈጥሮው ስለሆነ ቆሻሻን አስቀምጠን ዝንብ አይምጣ ማለት አንችልም፡፡

ነገር ግን ዝንብን የማባረሪያው መንገድ አካባቢን ማፅዳት ነው፡፡ አካባቢውን ከፀዳ ዝንብ ቢመጣ እንኳን የሚፈልገውን ስለማያገኝና እዚያ አካባቢ መቆየት ስራ መፍታትና ጊዜ ማባከን ስለሚሆንበት ዝንብ አይቆይም፡፡

እንዲሁ ሰይጣንን በህይወታችን እንዳይሰርቅ እንዳያርድና እንዳያጠፋ የምናደርግበት ዋነኛው መንገድ ሀጥያትን መፀየፍ ከክፉ የወጣትነት ምኞት መሸሽ ነው፡፡

ሰው ፍምን በብብቱ ታቅፎ አያቃጥለኝ ማለት እንደማይችል ሁሉ ሃጢያትን እየሰራ ሰይጣን አይስረቀኝ ማለት አይችልም፡፡ ሰው ለሰይጣን ተስማሚ ለም መሬት የሆነውን ጥላቻን በልቡ ይዞ ሰይጣን በህይወቴ አያጥፋ አይግደል የማለት አቅሙ አይኖረውም፡፡

ለሰይጣን ፍቱምን መድሃኒቱ እርሱን የሚስቡትን ነገሮች ሃጢያትንና ጥላቻን ከህይወት ማራቅ ነው፡፡ ሰይጣንን የመቃወሚያው መንገድ ለእግዚአብሄር እንደቃሉ መገዛትና ወደ እግዚአብሄር መቅረብ ነው፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

የክህደት ጥሪ

ዘመኑን ግዙ

ገንዘብ የክፋት ስር አይደለም

የራስ ጥፋት

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

 

ሳታቋርጡ ፀልዩ

cryሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18

በህይወት ማሸነፍ እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ ሰው በህይወቱ ሁል ጊዜ ካለማቋረጥ ማሸነፍ ይችላል፡፡

እኛ የእግዚአብሄር የክብሩ መገለጫ እቃዎች ነን፡፡ በራሳችን ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ እግዚአብሄር ላይ በታመንን መጠን ሁሉ ግን ሁሌ እናሸንፋለን የሚሳነንም ነገር አይኖርም፡፡

ሳታቋርጡ ድል እንድታደርጉ ሳታቋርጡ ጸልዩ፡፡

መፀለይና ማሸነፍ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሁሌ ማሸነፍ ይቻላል? አንዳንድ ሰዎች ይህ ሊደረስበት የማይቻል ነገር እንደሆነ ያስቡታል፡፡

መልሱ  ግን አዎን ሳያቋርጡ በመፀለይ ሁሌ ማሸነፍ ይቻላል ነው፡፡ ማረጋገጫው ምንድነው ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ሁሉ መልሱ እግዚአብሄር የማይቻል ነገር አያዝዝም ፡፡ እግዚአብሄር ካዘዘ ይቻላል ማለት ነው ፡፡

ሳያቋርጡ መፀለይ ማለት ሁሌ ተንበርክኮ መፀለይ ማለት ግን አይደለም፡፡ መፀለይ መንበርከክን ወይም በርን መዝጋትን ቢያጠቃልልም በእነዚህ ብቻ አይወሰንም፡፡

ሳያቋርጡ መፀለይ ማለት ካለማቋረጥ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ፣ ካለማቋረጥ ልብን ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ማንሳት እና ሌላም ስራ እየሰሩም ቢሆን ካለማቋረጥ በውስጥ ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ማለት ነው፡፡ ፀሎት በውስጥ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር መጮኽ ነው፡፡

እግዚአብሄር የልብን ጩኸት ይሰማል፡፡

እግዚአብሄር አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁሌ እንዲሳካልን ስለሚፈልግ ሳታቋርጡ ጸልዩ እያለ እየጋበዘን ነው፡፡

ሳናቋርጥ በመፀለይ ሳናቋርጥ እንከናወን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

#ኢየሱስ #ጌታ  #ፀሎት #የእግዚአብሄርእርዳታ #የልብጩኸት #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

 

በምድር ተቀመጥ

face_eyes_lion_fur_mane_85403_3840x2400.jpgበምድር ስንኖር የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር እንዳንፈፅም ሊያስፈሩን የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

አንዳንድ ሰው ወጥቶ ህይወትን መጋፈጥ ሲፈራ ተኝቶ መዋል ያምረዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ቶሎ ወደ ሰማይ እንዲሄድ ይመኛል፡፡ የሆነ ቦታ ብቻ መሄድ ከምድር መውጣት ይፈልጋል፡፡

በጌታ በእየሱስ ያመነ ሰው ወደሰማይ የሚሄድበት ጊዜ አለው፡፡ ላሁን ግን የሚሰራ ስራ ስላለ በዚሁ በምድር ይቆያል፡፡

አንዳንዴ የሰዎችን ክፋት ስናይ ዘመኑ ያስፈራራናል፡፡ የፍርሃቱን ስሜት ከሰማነው ሽምድምድ አድርጎ ሊያስቀምጠን ነው የሚመጣው፡፡

የኑሮውን ውድነት ስታስብ እንዴት ነው የሚኖረው ትል ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር አምላካዊ መልስ ግን ይህ ሁሉ ችግሮች ባሉባት በዚችሁ ምድር ተቀመጥ ታምነህ ተሰማራ ነው፡፡

እግዚአብሄር ግን የሚፈልገው በዚህ በእንግድነት አገራችን በምድር ላይ ታምነን እንድኖር ነው፡፡

እዚሁ ጠላት ባለበት ምድር ላይ ኖረህ እንድታሸነፍ ነው እንጂ  ጌታ ከአለም እንድትወጣ አይደለም የሚፈልገው፡፡

እግዚአብሄርን ከማመናችን በፊት ምድር እየተሻሻለች መሄድ የለባትም፡፡ ከማሸነፋችን በፊት የሰዎች ባህሪ መሻሻል የለበት፡፡ እንዲሳካልን ሰዎች ሁሉ በእግዚአበሄር ማመን የለባቸውም፡፡

አለም ግን ወዴት እየሄደች ነው ብለን በሞራል መላሸቅ መገረማችንን እያለ እንዲያውም እየበዛ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ . . . በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ ነው የሚለው፡፡

 • እዚሁ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማ አህዛብን በሚሸፍንበት ነው ብርሃንህን ሊያወጣ የሚፈልገው፡፡

ብርሃን መቷልና የእግዚአብሄርም ክብር መቷልና ተነሽ አብሪ። እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማ አህዛብን ይሸፍናሉ ነገር ግን በአንች ላይ እግዚአብሄር ይወጣል ክብሩም በአንች ላይ ይታያል፡፡ መዝሙር 60፡1-2

 • በሞት ጥላ መካከል ነው አብሮህ መሆን የሚፈልገው፡፡

በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። መዝሙር 23፡4

 • በጠላቶችህ ፊት ለፊት ነው ራስህን በዘይት መቀባት የሚፈልገው፡፡

በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። መዝሙር 23፡5

 • እዚሁ ደረቁ ምድር ላይ መቶ እጥፍ እንድታፈራ የሚፈልገው፡፡

ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው። ዘፍጥረት 26፡12

እግዚአብሄር ግን ታምነን እንድኖር ነው የሚፈልገው፡፡ ለዚህ ነው በምድር ተቀመጥ ታምነህ ተሰማራ የሚለው፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። መዝሙር 37፡3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ተጓደዱ

ጣሉት

የማይታይ እጅ

#ድፍረት #መተማመን  #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

ብፁሃን የዋሆች

 

dove2የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ማቴዎስ 5፡5

የዋህ በአማርኛ መዝገበ ቃላት ” ገር ፣ ቅን ፣ መሠሪነት የክፋት ብልጠት የሌለው ” በማለት ተተርጉሟል፡፡

የዋህ ማለት በሰው ላይ ክፉ ለማድረግና ለግሉ አላግባብ ለመጠቀም አቅሙና ችሎታው እያለው ሰውን ላለመጉዳት የሚጠነቀቅ ሃይሉን ለክፋት የማይጠቀምና ከክፋት የሚከለከል ሰው ማለት ነው፡፡

የዋህነት ደካማነት አይደለም፡፡ የዋህነት እንዲያውም ብርታት ነው ፡፡ ጀግና የሚባለው ራሱን የማይገዛ ሰው ሳይሆን ክፋት ለማድረግ ሲፈተን ራሱን የሚገዛ ለክፋት እጅ የማይሰጥ ብርቱ ሰው ነው፡፡

የዋህነት ሞኝነት አይደለም፡፡ እንዲያውም የዋህነት ሁኔታውን ጥበበኛው እግዚአብሄር እንዲይዘው ለጌታ የመተው ብልጠት ነው፡፡ የዋህነት ራስ የመበቀልን ፈተና በማለፍ ብድራቱን ለሚመልሰው ለእግዚአብሄር እድሉን መስጠት ነው፡፡

ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ሮሜ 12:19

የዋህነት የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ፅድቅን እንደማይሰራ በመረዳት ለእግዚአብሄር ገዢነት እውቅና መስጠት ነው፡፡ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። ያዕቆብ 1፡20

የዋህነት “ብትበደሉ አይሻልምን?” የሚለውን የእግዚአብሄርን ቃል አምኖ ሌላውን ከመበደል ይልቅ ራስ በመበደል ከእግዚአብሄር ሽልማት መቀበል ነው፡፡

እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡7

የዋህነት ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና መስጠት ነው፡፡ የዋህነት እግዚአብሄርን ምንጭ ማድረግ ነው፡፡ የዋህነት አላግባብ ከሰው አለመጠበቅ ነው፡፡ የዋህነት የስኬት ቁልፍ ያለው በምድር እንዳይደለ ማወቅ ነው፡፡ የዋህነት በጥበብ በሃይል በባለጠግነት አለመመካት ነው፡፡ ይልቁንም የዋህነት ፅድቅና ፍርድን ምህረትን የሚያደርግ እግዚአብሄር መሆኑን በማወቅ መመካት ነው፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፦ ኤርምያስ 9፡23-24

የዋህነት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ በየዋህነት እግዚአብሄርን ካስደሰትነው ምድርን እንወርሳለን፡፡ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ማቴዎስ 5፡5

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ዘመኑን ግዙ

eagleእንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16 

ብዙ ሰዎች የሚሳሳቱትና ከስኬት የሚወድቁት ቀኖቹ ለእነርሱ እንደሚሰራላቸው ባለማስተዋል በማሰብ ነው፡፡ ሰዎች ዘመኑ መልካም እንደሆነ ነገር ዘና ሲሉና በማስተዋል ካልነቁ እግዚአብሄር ወዳየላቸው የክብር ደረጃ መድረስ ያቅታቸዋል፡፡ 

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው፡፡ በጥንቃቄ ሳንኖር ቀኖቹ በራሳቸው ዝም ብለው ለእኛ ይሰራሉ ብለን ከጠበቅን አንሳሳታለን፡፡ ቀኖቹ በራሳቸው ለእኛ በጎነት አይሰሩም፡፡ መልካሙ የምስራች ግን እነዚህን ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ማድረግ መቻላችን ነው፡፡ እነዚህን ክፉ ቀኖች መግዛት የሚቻልበትና ለእኛ ስኬት እንዲሰሩ የሚደረግበት መላ አለ፡፡ 

ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ብሎም እግዚአብሄር ወዳየልን የህይወት አላማ መድረስ የምንችለው በጥበብ ጥንቃቄ ስንመላለስ ነው፡፡ 

የእግዚአብሄር ቃል በሚሰጠን ጥበብ ከተመላለስን እነዚህን ክፉ ቀኖች ገልብጠን ለእኛ በጎነት እንዲሰሩ ማድረግ እንችላለን፡፡ በሚበልጥ በእግዚአብሄር ጥበብ ከኖርን ክፋታቸው በእኛ ላይ እንዳይሰራ አድርገን ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ መኖር እንችላለን፡፡ 

ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15 

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢነት #ጥበብ #አቢይዋቁማ

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ

Africans-5.pngየእግዚአብሄርን ፈቃድ መረዳት የመሰለ ነገር የለም፡፡የህይወታችን ጥማት ጌታን መከተልና እግዚአብሄርን ማስደሰት በመሆኑ የእግዚአብሄር ፈቃድን ስናገኝ እንደሰታለን፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነ ነው፡፡ ሮሜ 12፡2
ሁል ጊዜ ደስ ይበላችሁ የሚለው የእግዚአብሄ ፈቃድ በመፅሃፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ ግልፅ ተደርጎ ተፅፎዋል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
እውነት ነው ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ የሚለው ትእዛዝ ሁል ጊዜ ቀላል አይደለም፡፡ ቤጌታ ግን ሁል ጊዜ ደስ መሰኘት ይቻላል፡፡ ግን እንዴትና በምን ምክኒያት ነው ሁል ጊዜ በጌታ ደስ መሰኘት የሚቻለው?
ሁልጊዜ ደስ መሰኘት የሚቻለው እግዚአብሄር በታላቅ ዋጋ የገዛን የህይወታችን ባለቤት መሆኑን በማመን ነው፡፡ እግዚአብሄር ባለቤት ስለሆነ ደግሞ እኛ እንኳን ግድ ባይለን ስለ እያንዳንዱ የህይወታችን አቅጣጫ ዝርዝር ጉዳይ ግድ ይለዋል፡፡
በዋጋ ተገዝታችኋልና . . . ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20
ሁልጊዜ መደሰት የሚቻለው እግዚአብሄር በአላማ እንደወለደን ስንረዳና ኢየሱስን ለሃጢያታችን እስኪሰዋ ድረስ ለእግዚአብሄር በጣም አስፈላጊ ሰዎች እንደ ሆንን ስናስታወስ ነው፡፡ ፍቅር የሆነው እግዚአብሄር ወዶናል፡፡
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ 1ኛ ዮሐንስ 3፡16
ሁልጊዜ በእግዚአብሄር የምንደሰተው እርሱ እረኛችን ስለሆነና በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብናልፍ እርሱ ከእኛ ጋር ስለሚሆን ነው፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥. . . በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፡፡ መዝሙር 23፡1፣4
ሁል ጊዜ በጌታ ደስ የሚለን ለእኛ የሚያስባትን ሃሳብ እርሱ ስለሚያውቀው ነው፡፡ የህይወት እቅዳችን እርሱ ጋር ስላለና በጥንቃቄም እየፈፀመው ስለሆነ ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11
ሁልጊዜ ደስ የሚለን ለእኛ የሚያስብልን የተባለ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ አባት በሰማይ ስላለን ነው፡፡
እርሱ ስለእናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 5:7
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ

ታላቅ ነው !

GREATER ISልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4:4

በክርስትና ህይወታችን የትም አትሄድም ፣ በላሁህ ፣ ጣልኩህ ፣ አሁንስ አታመልጥም ብለው የሚያስፈራሩ ብዙ ነገሮች ይነሳሉ፡፡

በአካባቢያችን ያሉትን ሁኔታዎች በማሳየት እግዚአብሄር የተናገረን ነገር እንደማይሆንና ሊፈፀም እንደማይችል ሊያስረዱንና ሊያሳምኑን ይጥራሉ፡፡

ክርስትናን በሚገባ ለመኖር አቅም እንደሌለን የአለም ሃይል እንደሚያሸንፈን በብዙ ሊያሳምኑን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

ነገር ግን . . .

እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ሊቋቋም የሚችል ምንም ሃይል አልነበረም የለም ወደፊትም አይኖርም፡፡

እየሱስ በምድር ሲኖር አሸንፎ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በሙላት እንደፈፀመ እኛንም ሊያሸንፈን የሚችል በፊታችን የሚቆም ምንም ሃይል የለም፡፡

በምድር ያለው ተግዳሮት እንደማናሸንፍ ማረጋገጫ ሊሆን በፍፁም አይችልም፡፡ እንዲያውም የተግዳሮት መኖር ወደአሸናፊነት እየገሰገስን እንደሆንንና ልናሸንፍ እንደምንችል ማረጋገጫው ነው፡፡

ከእኛ የተነሳ ሳይሆን በውስጣችን ካለው የተነሳ እንደምናሸንፍ ሳይታለም የተፈታ ነገር ነው፡፡

በእኛ ያለው በአለም ካለው ማንኛውም ተግዳሮትና ሃይል ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነው፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

የአእምሮ ገዳም

1024px-Tatev_Monastery_from_a_distanceየእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2

ሰዎች እግዚአብሄርን በመፈለጋቸውና ከዚህ አለም ነፃ ለመውጣት በመፈለጋቸው ከአለም መሸሽና ገዳም መግባት ይፈልጋሉ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ገዳም ቢገቡም ጠልተውት የመጡት ክፉ የሃጢያት ሃሳብ ተከትሎዋቸው ይመጣል፡፡ በዚህም ምክኒያት ምንም ከከተማ ወጥተው ገዳም ቢገቡም የአለማዊነት አስተሳሰብ በአእምሮአቸው እስካለ ድረስ ከአለም መለየት ያቅታቸዋል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ አለምን ስለማንመስልበት ገዳም ይናገራል፡፡ ይህን አለም አለመምሰል የምንችለው ብቸኛው መንገድ አእምሮዋችን በእግዚአብሄር ቃል ሲታደስና የአለም ክፉ አስተሳሰብ በልባችን ቦታ ሳያገኝ ሲቀር ብቻ ነው ፡፡

አለማዊ የሚያደርገን ከተማ መኖራችን ወይም ከሰው ተለይተን አለመኖራችን ሳይሆን አእምሮዋችን በእግዚአብሄር ቃል አለመታደሱና ከሃጢያት ሃሳብ ጋር መኖራችን ነው፡፡ አእምሮዋችን በእግዚአብሄር ቃል ሲቃኝና ሲለወጥ በህይወታችን ለአለማዊነት ምንም ስፍራ አይኖርም፡፡

አለማዊ ከሚያደርገን ከሃጢያት ሃሳብ ጋር እስካለን ድረስ ከከተማ ወጥተን ከሰው ተለይተን ገዳምም ብንገባ ከሃጢያት ባርነት አናመልጥም፡፡ ምክኒያቱም አለማዊ ከሚያደርገን የሃጢያት ክፉ ሃሳብ አእምሮዋችን እስካልታደሰ ድረስ አለምን አለመምሰል አንችልም፡፡

ነገር ግን ባለንበት በስራችን በምንኖርበት ቦታ ሁሉ በእግዚአብሄር ቃል አእምሮአችንን ካደስነው ይህን አለም ሳንመስል እግዚአብሄርን እያስደሰትን መኖርና ማገልገል እንችላለን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ማኅፀን ገብቶ ይወለድ?

የህይወት ጥያቄ

ይቻላል – እግዚአብሄርን ማስደሰት

 

 

 

በላይ ያለውን እሹ

col3-1-3-set-your-mind-on-things-above.jpgከክርስቶስ ጋር በትንሳኤ በመነሳታችንና በሰማያዊ ስፍራ ከክርስቶስ ጋር በመቀመጣችን እንዲሁም በሰማያዊው በረከት ሁሉ ከመባረካችን የተነሳ ሰዎች የሚጋደሉለት የምድር ነገር አያጓጓንም ፡፡
ለጊዜያዊ ደስታ ብለን አባታችንን እግዚአብሄርን ማሳዘን አንፈልግም፡፡ ለምድራዊ ተራ ነገር እግዚአብሄን መፍራታችንን አንተውም፡፡
ለምድራዊ ክብር ለማግኘት ሰዎችን አንጠላም አንበድልም ፡፡ ለከንቱ የምድር ውድድር የተሰጠንን የክርስትና ወንጌል ተልዕኮ ቸል አንልም፡፡
ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡32 እንደሚሉ ሰዎች ምድራዊ የሚያልፍ ገንዘብ ለማግኘት ሰዎችን አንቀማም፡፡
ይህ የእግዚአብሄር ቤተሰብነት የልጅነት ክብራችን አይፈቅድልንም፡፡ ክርስቶስን ለማወቅና ለእርሱና ለእርሱ ብቻ ለመኖር ሁሉን እንደ ጉድፍ እንቆጥራለን፡፡
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

እንደ ሌባ

like a thief.jpgእየሱስ የሰው ልጆች ሰለ ደህንታቸው ምን እንዳደረጉ ሊጠይቅና በምድር ላይ ሊፈርድ ተመልሶ የሚመጣው እንደሌባ ድንገት ነው፡፡ ሰዎች የእለት ተእለት ኑሯቸውን እየኖሩ እየበሉ እየጠጡ እያገቡና እየተጋቡ ማንም ሳያውቅ ኢየሱስ በድንገት ይመጣል፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡1-2

እየሱስ በቶሎ እንደሚመጣ እንጂ በምን ቀንና ሰአት እንደሚመጣ አናውቅም፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለ ነገር ተዘጋጅቶ መጠበቅ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር ሰው ማርቲን ሉተር ክርስቶስ ትናንትና እንደሞተ ፡ ዛሬ ጠዋት እንደተነሳ ፡ ነገ ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ በዝግጅት ኑሩ በማለት ይመክራሉ፡፡

ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። ማቴዎስ 24፡36-39

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ኢየሱስን ተመልክተን

እየሱስ ይመጣል

የሚበልጥ ምርጫ

የክህደት ጥሪ

እየሱስ ይመጣል

jesus comesየሰው ልጆች ሁሉ በሃጢያት ሃይል ስር ወድቀው ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ በሃጢያት ምክኒያት ለዘላለም ከእግዚአብሄር በተለያዩ ጊዜ የሃጢያታቸውን እዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ለመሞት እየሱስ ወደ ምድር ላይ መጥቶ ነበር፡፡

እየሱስ የሞትን ሃይል አሸንፎ ከሞት ተነስቶአል፡፡ በክብርም አርጎ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦዋል፡፡

አሁን ዓመተ ምህረት ወይም የምህረት አመት ነው፡፡ ማንም ሰው ሃጢያተኝነቱን ተረድቶ ሀጢያቱ ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንደሚለየው አውቆ ንስሃ ለመግባት መልካመ አጋጣሚ ነው፡፡ የሰው ልጆች ንስሃ እንዲገቡና እንዲመለሱ በመታገስ እየሱስ በሰማይ ቆይቶዋል፡፡

እየሱስ ዋጋ የከፈለው ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለሰው ልጆች ሁሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡4

እየሱስ በቅርብ ተመልሶ ይመጣል፡፡

እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእይ 22፡12

የሚገርመው ነገር ግን ተመልሶ የሚመጣው የሃጢያት እዳ ሊከፍል የሰው ልጆችን ሊያድን በድካም አይደለም፡፡ በቅርቡ ተመልሶ ሲመጣ በሃይልና በስልጣን ለእያንዳንዱም እንደ ስራው ሊከፍል በመላዕክት ታጅቦ ነው የሚመጣው፡፡

በቶሎ እመጣለሁ የሚለው ቃል እየሱስን ለሚከተል ሰው የሚያስፈነድቅ የምስራች ሲሆን እየሱስን ላልተቀበለ የሚያርበደብድ አስፈሪ መልዕክት ነው፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ምን ይጠቅማል ?

የክህደት ጥሪ

ልጅነቴ

 

 

 

ማኅፀን ገብቶ ይወለድ?

new born.jpgአንዳንድ ሰው የትም እንደማያመልጣቸው ሲናገሩና ሌላውን ሲያስፈራሩ የእናትህ ሆድ ተመልሰህ እንደምትገባ አይሃለሁ! ይላሉ፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስም ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? የሚል ጥያቄ ያቀረበ ኒቆዲሞስ የሚባል ሃይማኖተኛ የአይሁድ አስተማተሪ ነበረ፡፡
 
ኒቆዲሞስ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው እየሱስ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም ስላለው ነበር፡፡
 
ምንም የኢትዮጲያን ብናውቅ ኢትዮጲያን ብንወድ ስለ ኢትዮጲያ ታሪክ አስተማሪ ብንሆን ነገር ግን ከኢትዮጲያዊ ካልተወለድን በስተቀር ወደዚህ ወደ ኢትዮጲያ ምድር መግባትና ኢትዮጲያዊ መሆን በፍፁም አንችልም፡፡
 
እንደዚሁ የእግዚአብሄርን መንግስት ብንፈልግ ስለ እግዚአብሄር መንግስት ታሪክ ብናውቅ ስለመንግስቱ ብናስተምር እንኳን የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን ብትኖርም እንኳን ዳግመኛ ካልተወለድን በስተቀር ልናያትም ሆነ ልንገባባት እንችልም፡፡
 
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ዮሐንስ 3፡3-5
 
ሰው ወደ ምድር ለመግባት ከእናቱና ከአባቱ መወለድ ግዴታው እንደሆነ ሁሉ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ከውሃና ከመንፈስ መወለድ አለበት፡፡ እየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለው የሃጢያት እዳ ለእኔ ነው ብሎ የተቀበለና እየሱስን የህይወቱ አዳኝና ጌታ እድርጎት የሾመ ሰው ሁሉ ዳግመኛ ከእግዚአብሄር ይወለዳል፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም ይኖራል፡፡
 
ነገር ግን ሰው ከእናቱ እስከሚወለድ ድረስ ምድርን እንደማያያትና እንደማይገባባት ሁሉ እንዲሁ ሰው ምንም ሃይማኖተኛና መልካም ሰው ቢሆንም ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሄርን መንግስትና ቤተሰብ ሊያያትም ሊገባባትም አይችል፡፡
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር ያድርጉ
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

የአይን መከፈት

eyes.jpgጌታ እየሱስን ተቀብለን የዚህ የእግዚአብሄር መንግስትን ጥቅሞች ተጠቃሚ እንዳንሆን የሚያደርገው አንዱ ምክኒያት መንፈሳዊ እውርነት ወይም የአይን አለመከፈት ነው፡፡ አይናቸው የተከፈተላቸው በቀላሉ የሚያዩትን በረከት እኛ ማየት ባለመቻላችን ብቻ ህይወታችን ውስን ከመሆኑም በላይ በክርስትና ህይወታችን መደሰት ያቅተናል፡፡
እውር ሰው አጠገቡ ያለውን መልካም ነገር ማየት እንደማይችል የልቦናችን አይኖቻችን ካልተከፈቱ በስተቀር እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀልንን በጎነትና ክብር ማየት ይሳነናል፡፡
እግዚአብሄር በክርስቶስ እየሱስ ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ካዘጋጀልን በኋላ ባርከኝ የሚለው ጥያቄያችን አንዳንዴ ተገቢ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእኛ ችግር የበረከት እጥረት ሳይሆን በረከቱን የማየት የእይታ እጥረት ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ነው የመንፈስ አይናችን እየተከፈተ ሲሄድ ባርከኝ የሚለው ጥያቄያችን እየቀነሰ ለበረከት በሁሉ እጅግ ባለጠጎች መደረጋችንን ስላምናውቅ ፀሎታችብን ለበረከት አድርገኝ በሚለው የፀሎት ርእስ የሚሞላው፡፡ ስለዚህ ነው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ያለውን ተዝቆ የማያልቅ ሃብት ለማየት የልብ አይን መከፈት ወሳኝ ነው የሚባለው፡፡
ይህንን በክርስቶስ ያለውን አርነት ስናይ ብቻ ነው ክርስትናችንን በሚገባ የምናጣጥመው፡፡
ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ሰነፍ በልቡ

13438801_10154181473475903_8905141808802260981_nሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። መዝሙር 14፡1

ሰነፍ ወይም ሞኝ እግዚአብሄር የለም የሚለው በቃሉ አይደለም ፡፡ በቃሉ አውጥቶ ሲናገር ላይሰማ ይችላል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ ጮክ ብሎ እግዚአብሄር የለም ይላል፡፡

ሰው በልቡ እግዚአብሄር የለም ማለቱን ስንፍናውን የሚያሳዩ ድርጊቶች አሉ፡፡

ሰው እግዚአብሄን መፈለግ ትቶ የእርሱ የህይወት ቁልፍ በምድር ላይ እንዳለ የሚያስብ ከሆነ በአኳሃኑ እግዚአብሄር የለም እያለ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ፈጥሮት እርሱን የማይፈልግና የሚገባውን ክብር የማይሰጥ ሰው ሞኝና ሰነፍ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ አድርጎ ለእግዚአብሄር ትኩረት የማይሰጥ ሰው ሞኝ ነው፡፡ በህይወቱ ለእግዚአብሄር ስፍራ የሌለው ሰው የማያስተውል ሰው ነው፡፡

ሰው ብልጠቱና አስተዋይነቱ የሚታወቀው የፈጠረውን እግዚአብሄርን ሲፈልግ ነው፡፡ የፈጠረውን እግዚአብሄርን ቸል ከማለት በላይ ሞኝነትና ስንፍና የለም፡፡

ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ። መዝሙር 53፡1-2

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

የትኛው ጥበብ ?

አሕዛብ ይፈልጋሉ

እርሱን እወቅ

የንጉስ ብልጫ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

እምነት ይመጣል

Embrace_Words.jpgካለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ እንዲያው ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን ይገባዋል፡፡ ዕብራውያን 11፡6
 
በአጭሩ ከእግዚአብሄር ለመቀበል እመነት ወሳኝ ነው፡፡
 
ካለእምነት የእገዚአብሄር ሃይልና በረከት ተጠቃሚ መሆን አይቻልም፡፡
መልካሙ የምስራች ግን እምነት እመነት ይመጣል፡፡ እምነትን ማምጣት ይቻላል፡፡ እምነት ሊኖረን ይችዐላል፡፡ እምነት ልናገኝ እንችላለን፡፡
እምነት ሊመጣ መቻሉ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው ?
ግን እምነት የምናገኘው እንዴት ነው ? እምነት እንዴት የመጣል ?
መፅሃፍ ቅዱስ እምነት እንዲኖረን መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እምነት እንዴት እንደሚመጣም ያስተምረናል፡፡
 
እምነት ከመስማት ነው መስማትምን በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ሮሜ 10፡17
 
እምነት የሚመጣበት አንዱና ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄር ቃል በመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣበት ሌላ መንገድ የለውም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ከእግዚአብሄር ለመቀበል የሚያስችለን እምነት የሚመጣበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡
 
በህይወታችን እምነት እንዲበዛና ከእግዚአብሄር አብልጠን ዋጋን እንድንቀበል የእግዚአብሄር ቃል በትጋት እናንብብ እንስማ፡፡
 
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
 
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ምን ይጠቅማል ?

city vs soulሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16:26

ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ማለት በአለም ላይ ያለው ሀብት ሁሉ የእርሱ ቢሆን ፡ በአለም አንደኛ ዝነኛ ቢሆን ፡ በአለም ላይ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ የሚችል ሃያል ሰው ቢሆን ማለት ነው፡፡ ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?

መልሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡

ከነፍስ  ዋጋ ጋር ሲተያዩ እነዚህ ነገሮች ከንቱ የከንቱም ከንቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተደምረውና ከአንድ ነፍስ ጋር በፍፁም አይወዳደሩም፡፡

ሰው እነዚህን ሃብት ፡ ዝናና ፡ ሃይል ሁሉ ደምሮ ለነፍሱ ቤዛና ዋጋ ሊከፍልላት የማይበቁ እጅግ በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው፡፡

በምድር ላይ እነዚህን ነገሮች ብናጣ በአለም ላይ ማንም ባያውቀን ፡ የመጨረሻ ደካማ ሰዎች ብንሆን ፡ ከምንበላውና ከምንለብሰው ውጭ ምንም የሌለን ብንሆን እንኳን ነፍሳችንን ካላጣን አንጎድልም አንከስርም፡፡ ነፍሳችንን ላለማጉደል እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንኳን ብንተው ተጠቃሚ ነን አትራፊም ነን፡፡

ነፍሳችንን ላለማጉደል የምንወስደው ማንኛውም እርምጃ ሁሉ ትክክለኛ የጠቢብ ውሳኔ ነው፡፡

ስለዚህ ነው ከመርፈዱ በፊት ጌታ እየሱስን ለመከተል መወሰን ያለብን፡፡

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። 26 ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16: 24-26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ተጓደዱ

ፈጣን ባለጠግነት

የማይታይ እጅ

የህይወት ትርጉም

የንጉስ ብልጫ

sheba.jpgእየሱስን እንደ አዳኝና ጌታችን አድርገን በመቀበላችን ንጉሱ እግዚአብሄር ልጆቹ አድርጎናል፡፡ የነገስታት ቤተሰብ አባላት ነን፡፡ የንጉሱ ወንድና ሴት ልጆቹ ሆነናል እንደንጉስ በመመላለስ ሌሎች ምስክር መሆን እንችላለን፡፡
ግን ስንቶቻችን ነን እንደ ንጉስ ለቀቅ ያለና ሰፋ ያለ ኑሮ የምንኖረው?
እንደንጉስ ልጅ ማለቴ እንደ ምድራዊ ንጉስ በቤተመንግስት ውስጥ የሚኖር ማለት አይደለም፡፡ ንጉስ ማለት በ2017 ሞዴል ማርቼዲስ መኪና የሚሄድ ማለት አይደለም፡፡ ንጉስ ማለት በወርቅ የተሰራ የሚያብለጨልጭ ልብስ የሚለብስ ማለት አይደለም፡፡ ይህንማ ተራም ንጉስ ያደርገዋል፡፡
 
ምንም ሃብት ቢኖረው ተበድያለሁ አሳየዋለሁ የሚል ይቅር ለማለት የሚከብደው ሰው ንጉስ አይደለም፡፡ ንጉስ እቃዬን ወሰደብኝ ብሎ ለጥቂት ነገር የሚጣላ ቋጣሪ አይደለም፡፡ ንጉስ ካልነኩኝ አልነካም ከነኩኝ ግን እዘርራቸዋለሁ የሚል አይደለም፡፡
 
ይልቁንም ንጉስ ማለት ህይወቱ ለቀቅ ያለ ሰው ማለት ነው፡፡ ንጉስ ማለት ልብሱ ሳይሆን አእምሮው የበለፀገ ማለት ነው፡፡ ንጉስ ማለት ቤቱ ሳይሆን ልቡ የሰፋ ማለት ነው፡፡ ንጉስ ማለት በወርቅ ልብስ ሳይሆን በየዋህነት የጠሽቆጠቆጠ ልብ ያለው ማለት ነው፡፡ ንጉስ ምህረት የማያልቅበት ትግስቱ የበዛ ከእርሱ ለተለዩ ሰዎች ልቡ የሰፋ ለቀቅ ያለ ሰው ነው፡፡
እየሱስ ስለዚህ የህይወት ንግስና ሲናገር እንዲህ አለ፡፡
 
39 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ 40 እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ 41 ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። 42 ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል። 43 ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 44-45 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። 46 የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? 47 ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? 48 እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። ማቴዎስ 5፡39-48
የንግስናችን ብልጫ በህይወት ጥራት ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ በምህረት ብዛት ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ በይቅርታችን ብዛት ነው፡፡የንግስናችን ብልጫ ጠላቶቻችንን በመውደድ ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ ሌላውን በመሸከም ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ በልብ ስፋት ነው፡፡
 
የእኛ ባለጠግነት በእግዚአብሄር ስለሆነና የእኛን ንብረት ወስዶ ደሃ ሊያደርገን የሚችል ማንም ሰው እንደሌላ ተረድተን በብዙ በመተው የንግስናችንን ብዛት እናሳያለን፡፡ ንግስናችን ማንም ሊኖረው የሚችለው የቁሳቁስ ብልጫ ሳይሆን የህይወት ጥራት ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ የእግዚአብሄር ባህሪ ማንፀባረቃችን ነው፡፡ የንግስናችን ብልጫ የተቀበልነውን ታላቅ ፀጋ /የሚያስችል ሃይል/ ማሳየት ነው፡፡
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ማቴዎስ 5፡46-47
 
በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። ሮሜ 5፡17
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
 

የትኛው ጥበብ ?

Wilfred-Otten-image.jpgበህይወት ለመከናወን ጥበብ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በህይወት ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ በሚገባን ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን የሚያሳየን ጥበብ ነው፡፡
 
ጥበብ ሁሉ ግን መልካም ጥበብ አይደለም፡፡ የሚገነባ ጥበብ አለ የሚያፈርስ ደግሞ ጥበብ ደግሞ አለ፡፡ ሰው ጥበብ አለው ማለት ከላይ ከእግዚአብሄር የተቀበለው ነው ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዴ እነዚህን ከእግዚአብሄር የሆነውንና ከሰይጣን የሆነውን የጥበብ አይነቶች ለመለየት እንቸገራለን፡፡
 
መፅሃፍ ቅዱስ የእነዚህ እጅግ የተያዪ የጥበብ አይነቶች ባህሪያቸውና የሚለዩበትን ምልከቶች ያስተምረናል፡፡ ጥበብ ብለን እየኖርን ያለንበትን እንድንፈርትሽና ከላይ ያልሆነውን ጥበብ በፍጥነት እንድንጥል የላይኛይቱን ጥበብ በየዋህነት በኑሮዋችን እንድናሳይ ይመክራል፡፡
 
ከላይ ከእግዚአብሄር የምንቀበለውና የምድር የስጋና የአጋንንት ጥበብ ባህሪያቸውንና ምልክታቸውን መፅሃፍ ይዘረዝራል፡፡
 
ላይኛይቱ የእግዚአብሄር ጥበብ
 
ንፅህት- ከልብ ንፅህና ከክፉ ሃሳብ የሌለባት
ታራቂ- ርሁርጉ ሰላምን የምትፈልግ ለአንድነት የምትተጋ
እሺ ባይ – ትሁት ታዛዥ አገልጋይ
ምህረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፡ ምህረትን የምትወድ
ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት- የምትታመን፡ የማታስመስል
 
የምድር የስጋ የአጋንንት ጥበብ
 
መራርነት – ይቅር የማትል ፡ የማትተው
ቅንአት- የሌላው መልካምነት እረፍት የሚነሳት
አድመኝነት – ለራስ ጥቅም ሰዎችን ለክፋት የሚያነሳሳ
ሁከትና ክፉ ስራ – ረብሻን የሚወድ
ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡13-17
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
 

የህይወት ጥያቄ

simple oromo.jpgበታሪክ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ ተጠቃሚዎቹ ስለነዳጅ ፍጆታቸው በደንብ ማሰብ ጀመሩ፡፡ ከዚያም የነዳጅ ፍጀጆታቸውን ካልቀነሱ እየጨመረ ያለውን የነዳጅ ዋጋ መቋቋም እንደማይችሉ በተገነዘቡ ጊዜ እርምጃዎችን ወሰዱ፡፡ ከወሰዱዋቸው እርምጃዎች መካከል አንድ መኪና በምን ያህል ፍጥነት ሲጓዝ ዝቅተኛ ነዳጅ እንደሚበላ ማጥናትና መተግበር አንዱ ነበር፡
ሁለተኛ በመርከቦችና በመኪናዎች ላይ ያሉ ከባድ ግን አላስፈላጊ የሆኑ ሸክሞችን አስወገዱ፡፡ በዚህ ሁኔታ የነዳጅ አጠቃቀማቸውን በመቀነሳቸው በነዳጅ ላይ ያላቸውን መደገፍ መቀነስና ህይወታቸውን ቀለል ማድረግ ችለው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ የነዳጅ ሻጮቹ የነዳጁን ዋጋ እንዲቀንሱ ማስገደድ ችለው ነበር፡፡ እስከያ ጊዜ ግን ባነሰ ነዳጅ መኖር እንደሚቻል አይረዱም ነበር፡፡
በህይወት ዘመናችን የምንፈልገውንና የሚያስፈልገንን መለየት አንድ ሲደመር አንድ ስንት ይሆናል እንደሚለው ቀላል አይደለም፡፡
በህይወታችን የሚያስፈልገን ነው ብለን በሙሉ ልባችን የምናምነው ነገር ሁሉ ላያስፈልገን ይችላል፡፡ በእውነት የማያስፈልገን መሆኑን የምንረዳው አጥተነው ካለ እርሱ በስኬት መኖር ስንችል ነው፡፡
አሁንም የምንፈልገው ነገር ላይ ሳይሆን የሚያስፈልገን ነገር ላይ ብቻ ካላተኮርን ለእግዚአብሄር የመኖራችን ውጤታማነት ይቀንሳል፡፡ የኑሮ ጥያቄ አያልቅም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል ባልንበት መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የምንችለው፡፡
አሁንም እኛ መለወጥ እንችላለን፡፡ ከምናስበው በላይ ካለብዙ ነገሮች መኖር ማሸነፍ መከናወን እንችላለን፡፡ ካልሆነ ግን ራስን ሳያማጥኑ ለእግዚአብሄር መኖርም ሆነ እግዚአብሄርን ማገልገል ዘበት ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ኢየሱስን ተመልክተን

man-looking-upሰዎች ሁል ጊዜ የተሳካለትንና ለስኬታቸው ምሳሌ የሚሆናቸውን ሞዴል ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ነው የተሳካላቸውን የፊልም ተዋናኞችና ታዋቂ ሰዎች ልብሳቸውንና የፀጉር ስታይላቸውን ሳይቀር የሚኮርጁትና እነርሱን ለመምሰል የሚሞክሩት፡፡
 
በክርስትናም እንዲሁ ሞዴል የሚሆኑ የክርስትና ህይወታቸውን ፍሬ እያየን የምንከተላቸው የቀደሙ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡
 
የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።ዕብራውያን 13፡7
 
እንደ እየሱስ በክርስትናችን እንዲሳካልንና በነገር ሁሉ አሸንፈን እግዚአብሄርን ደስ ለማሰኘት የእየሱስን ህይወት መመልከት አለብን፡፡ እየሱስን በመምሰላቸው የምንመስላቸው ሰዎች ቢኖሩም ፍፁም ምሳሌያችን ግን እየሱስ ነው፡፡
 
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
 
ኢየሱስን የሚመስሉትንና እየሱስን የምንመለከተውና የምንመስለው
 
• ሩጫን በትግስት መሮጥ
 
ክርስትና እንደ መቶ ሜትር ሩጫ ውድድር አይደለም፡፡ ክርስትና እንደማራቶን ውድድር ነው፡፡ ክርስትና እንደ መቶ ሜትሩ የሩጫ ውድድር ጉልበት አለኝ ተብሎ የሚገሰገስበትና በሰከንዶች የሚጨረስ ሩጫ አይደለም፡፡ ማራቶን ጉልበት ቢኖረንም ጉልበታችን ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅመን ሳንቸኩል ፡ ሳንሰለች ፡ በንቃት ፡ በድካም ሳናቋርጥ ፡ ለሰዓታት በትግስት የምንሮጠው ሩጫ ነው፡፡
 
• ነውርን መናቅ
 
ሌላው እየሱስን የምንመስለው በሰዎች ዘንድ ነውር የሚባለውንና ሰዎች የሚያንቋሽሹትን እንደ ሞኝነት የሚቆጥሩትን የእግዚአብሄርን ቃል በየዋህነትና በሞኝነት ተቀብሎ ማድረግ ነው፡፡ በሰው ዘንድ እንዳንናቅ እና እንዳንጠላ ፈርተን የማንታዘዘው የእግዚአበሄር ቃል የለም፡፡ ቃሉን እንጂ ነውርን አናከብርም፡፡ ነውረኛ እንዳንባል በመፍራት ቃሉን ከመታዘዘ ወደኋላ አንልም፡፡ በሚንቁና በሚያጥላሉ መካከል እየሱስ ጌታ እንደሆነ እንናገራለን እንመሰክራለን፡፡ በድፍረትም ቃሉን እንኖራለን፡፡
 
• የወደፊት ሽልማት ላይ እንጂ መከራው ላይ አለማተኮር
 
በፊታችን ስላለ ሽልማት በመከራ በመታገስ እርሱን ልንመስለው ይገባል፡፡ ምክኒያቱም ሁል ጊዜ “ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ” እንቆጥራለን፡፡ ሮሜ 8፡18
 
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን “መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ” ተብለን ሽልማታችንን ከእግዚአብሄር ለመቀበል እንትጋ ፡፡ ማቴዎስ 25፡23
 
ይህን ኝሁፍ ለሌሎች ሼር ያድርጉ
 

ይቻላል – እግዚአብሄርን ማስደሰት

Girl-Smile-Closeup 2.jpgበምድር ላይ ሰዎችን የሚያስደስቱና የሚያስደንቁ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ሰዎች መልካመ ሲለብሱ ደስ ይላቸዋል፡፡ ሰዎች መልካም ሲበሉ ከፍ ይላሉ፡፡ ሰዎች ትልቅ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ደስ ይላቸዋል ይደነቃሉ፡፡
እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ ቁርጥ እርሱን አስመስሎ ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄርም እንደ እኛ ስሜት አለው፡፡ እኛን የሚያስደንቁና የማያስደንቁ ነገሮች እንዳሉ እንዲሁ እግዚአብሄርን የሚያስደንቁትና የማያስደንቁት ነገሮች አሉ፡፡
እኛን የሚያስደስቱን ነገሮች ሁሉ ግን እግዚአብሄርን አያስደስቱትም ወይም አያስደንቁትም፡፡ እዚህ ጋር ግን እግዚአብሄርን የሚያስደስተው ምን እንደሆነ በግልፅና በማያሻማ ቋንቋ ተገልጾ እናገኘዋለን፡፡ ደግሞም በእምነት ባልተደረገ ማንኛውም ነገር እግዚአብሄርን ማስደሰት ዘበት እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
 • በዚህ ምድር ስንኖር በምድራዊ በአይናችን ከሚታየው ነገር ባሻገር የእግዚአብሄርን መንግስት ስናይና እግዚአብሄርን በውሳኔያችን ስናስቀድም ለእርሱ እውቅና ስንሰጥ እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ ሮሜ 8፡14 እና ምሳሌ 3፡5-6
 • በዙሪያችን ከከበበን ነገሮች በላይ የእግዚአብሄርን ቃል ስናምን እግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡ ሮሜ 4:18
 • በምድር ኑሮዋችን በአይን የማይታየውን የሰማያዊውን መንግስት ያውም መንግስተ ሰማያት በመጠበቅ ስንኖር እግዚአብሄርን እናስደስተዋለን፡፡ ፊሊጲስዩስ 3፡20
 • በእለት ኑሮዋችን በተፈጥሮ አይን የማይታየውን በውስጣችን የሚኖረውን ጌታ እየሰማንና እየታዘዝን ስንኖር እግዚአብሄር ይደሰታል፡፡ ገላቲያ 2፡20
 • በእምነት በሰማይ ቤት እንዳለን የምድር ኑሮዋችን ጊዜያዊ መተላለፊያ ብቻ እንደሆነ አድርገን እንደ እንግዳና መፃተኛ ስንኖር እግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡11 እና 2ኛ ቆሮንጦስ 5፡7-8
 • በስጋዊ አይናችን የማይታየውን እግዚአብሄርን በኑሮዋችን ሁሉ እየፈራን ስንኖር እግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡ ማቴዎስ 10፡28
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ቤተ እግዚአብሄር

images man house 2በአሁኑ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሄር የሚኖርበት ነው ብለው የሚያስቡትን ቤት ዋጋው እጅግ ውድ በሆነ በወርቅና በከበረ ድንጋይ ያሳምሩታል ያስጌጡታል፡፡ እግዚአብሄርም ቤቱ ውስጥ መጥቶ እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡
 
እግዚአብሄር ግን እጅ በሰራው በማንኛውም ቤት ውስጥ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር የሚኖረው ራሱ በፈጠረው በሰው ልጅ ውስጥ ነው፡፡
 
ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤ ሃዋሪያት 17፡24
 
እየሱስ ስለ ሃጢያቱ እንደ ሞተለትና ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ ወደሚያምንና ወደሚመሰክር ሰው የእግዚአብሄር መንፈስ ይመጣል በእርሱም ውስጥ ማደር ይጀምራል፡፡
 
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን . . . የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17
 
ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20
 
እኛን ክርስቲያኖች ከሌሎች ሰዎች የሚለየን እግዚአብሄር በውስጣችን መኖሩ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር በእኛ ውስጥ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ውስጥ ለሰዎች መልካም ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ውስጥ ለሰዎች ፍቅሩን ይገልጣል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ውስጥ ሰዎችን ያስጠነቅቃል፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄር ከክፉ ስራቸውም እንዲመለሱ ይገስፃል፡፡
 
እግዚአብሄር በአፋችን ተጠቅሞ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር በእግራችን ተጠቅሞ ይሄዳል ለሰዎች ይደርሳል፡፡ እግዚአብሄር በእጃችን ተጠቅሞ ለሰዎች መልካም ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር በልባችንና ተጠቅሞ ሰዎችን ይወዳል፡፡ በስሜታችን ተጠቅሞ እግዚአብሄር ለሰዎች ይራራል፡፡
 
እግዚአብሄርን ያየው አንድስ እንኳን የለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናየው ውስጣቸው እግዚአብሄር በሚኖር የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ በሆኑ ክርስቲያኖች ነው፡፡ እኛ የእግዚአብሄር መኖሪያ ቤቱ ነን፡፡
 
ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡16
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

የክህደት ጥሪ

many-times-did-jesus-fall-carrying-cross_f50b52727618a9cfክርስቲያን መሆን ወይም የእየሱስ ተከታይ መሆን የሃይማኖት ለውጥ ማድረግ አይደለም፡፡ የእየሱስ ደቀመዝሙርነት ጥሪ የሃይማኖት ለውጥ ጥሪ አይደለም፡፡ ክርስትና ራስን የመካድ ጥሪ ነው፡፡
 
ሌሎች ሃይማኖቶች የተለያየ ደንብና ስርአት ይቀበላሉ፡፡ ክርስትና ግን ራስን ከመካድ ያነሰ ነገር አይቀበልም፡፡ ሰው ምንም ያህል መልካም ምግባር ለማድረግ ቢሞክር ራሱን ክዶ እየሱስን ካልተከተለ ደቀመዝሙር ሊሆን በፍፁም አይችልም፡፡
 
ለሁሉም እንዲህ አላቸው። በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ። ሉቃስ 9፡23
 
እየሱስ ስለ ሃጢያታችን እንደሞተ እኛ ደግሞ የነፍሳችንን የሃጢያት ምኞት ክደን ለእርሱ ልንኖርለት ይገባል፡፡ እለት በእለት በቃሉ የመኖር ሃላፊነታችንን እየተወጣን ለእርሱ እና ለእርሱ ብቻ እንድንኖርለት ይፈልጋል፡፡
 
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡27
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

እንተያይ

1414-hands loveለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ዕብራውያን 10፡24-25

ሁላችንም በፍቅር መኖር እንፈልጋለን፡፡ ከእኛ ይበልጥ በፍቅር የሚኖር ሰው ስናይ እንደእርሱ ለመሆን እንቀናለን፡፡ ፍቅር ለሰነፎች አይደለም፡፡ ፍቅር ትጋትን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ርካሽ አይደለም፡፡ ፍቅር በትጋትና በንቃት ሊጠበቅ ፡ ሊነቃቃና ሊታደስ ይገባዋል፡፡

ከሰል በደንብ እንዲቀጣጠልና በመቀጣጠል እንዲቆይ መራገብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ፍቅርም እንዲበረታና እንዲቆይና መነቃቃት ይገባዋል፡፡ ፍቅርን የሚያነቃቃው ደግሞ በትጋት መገናኘትና መተያየት ነው፡፡

መልካም ስራም እንዲሁ ትጋትንና ፅናትን ይጠይቃል፡፡ መልካም ስራ ጉልበትን ይጠይቃል፡፡ መልካም ስራ ፅናትንና ብርታትን ይጠይቃል፡፡ መልካም ስራ በትጋት ካልተቀጣጠለ እየሟሸሸ ይሄዳል ቀስ በቀስም ይጠፋል፡፡

በትጋት እርስ በእርስ መተያየት መልካምን ስራ ያነቃቃዋል፡፡ አንዳችን በአንዳችን እምነት እንበረታታለን ፡፡ እንዳችን እንዳችንን እንቀርፃለን፡፡ አንዳችን አንዳችንን እንሞርዳለን እንስላለን፡፡ በመሰብሰብና በመተያየት እንታደሳለን፡፡

ለፍቅርና ለመልካም ስራ እንድንነቃቃ የእግዚአብሄርን ቃል ከሚያምኑ ፡ ከሚኖሩትና  ከሚናገሩ ሰዎች ጋር በትጋት እንሰብሰብ ፡፡ እንዴት ለጌታ እንደሚገባ እንደምንኖር እርስ በእርሳችን እንመካከር፡፡

አንዳንዴ መልካም የሰራን እየመሰለን እንስታለን፡፡ ሰው ከተሰበሰብንና እርስ በእርሳችን ከተያየን ሌላው ችግራችንን ይነግረናል፡፡ የሌላውንም ችግር አይተን ለጌታ እንዲኖር በፍቅር ማበረታታት ቤተሰባዊ ሃላፊነታችን ነው፡፡ አንዳችን የሌላው ጠባቂዎች ነን፡፡ ይህንንም የመሰብሰብ መልካም ልማድ አብልጠን እንድናደርግ መፅሃፍ ይመክረናል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ታመን

በሃይማኖት ብትኖሩ

ፀጋን በከንቱ

የማይታይ እጅ

ልጅነቴ

c7b4bd45aa0f127aa70888bac834f2e1ትዝ ይለኛል ልጆች ሆነን በወላጆቻችን ወደ ሱቅ ወይም ወደ ማደያ እንላክ ነበር ፡፡ ከመካከላችን ለፈጣንና አስተማማኝ መልክት የሚላክ ታማኝ ልጅ አለ ለዚያ የማይላክ የማይታመንበት ልጅ ደግሞ ነበር፡፡

የወላጆችን የልብ የሚያደርስ መልክተኛ የሚባለው በመንገድ ያለው ወሬ የማይወስደው ፡ አላፊውንና አግዳሚውን ሰውና መኪና ሲያይ የማይቆም ፡ የሆነ ግር ግር ሲያይ ለወሬ የማይጓጓ ሲሆን ልብ የሚያደርስ መልክተኛ ተብሎ በወላጅ ይላካል፡፡ ይህ መልክተኛ የወላጅን ሸክም ተሸክሞ እስከሚፈፅመው የማያርፍ ተወዳጅ መልክተኛ ነው፡፡
የማይላከው ልጅ ደግሞ ፈጠን ፈጠን ብሎ የማይራመድ ፡ ጉልበቱን የሚሰስት ፡ ወሬ ወይም በመንገድ ላይ የሚያየው ጫወታ የሚያታልለው ፡ እንደተላከ የሚረሳው ፡ አንዳንዴ የተላከውን ረስቶ ሌላ ነገር ገዝቶ የሚመጣ ወይም ደግሞ ከተላከ እጅግ ዘግይቶ የሚደርስ ልጅ ነው፡፡
አሁንም እኛ በምድር ላይ ያለነው በእግዚአብሄር ተልከን ነው ፡፡ (2ኛ ቆሮንጦስ 5፡20) ይህ ቤታችን አይደለም፡፡ /(ፊልጵስዩስ 3፡20) በምድር ያለነው መብላትና መጠጣት ትልቅ ነገር ሆኖ ሳይሆን ለስራና ለተልኮ ነው ፡፡ (ዮሃንስ 20፡21)
ስለዚህ በልጅነታችን የልብን እንደሚያደርሰው ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤(ማቴዎስ 25፡21) የሚለው ልጅ እንሁን
የአለም ብርሃንና የምድር ጨው የመሆን መልክታችንን ለአፍታ ረስተን በዚያ ፋንታ ሌላ ነገር ስናደርግ አንገኝ (ማቴዎስ 5፡14)
በምድር ያለው ክፉ ውድድር ሳያጓጓን “የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል” የተላክንበትንም የወንጌል አላማ ፈፅመን የላከንን ጌታ እናስደስት (ማቴዎስ 13፡22)
በሃጢያት ሃሳብና በነፍስ ተግዳሮት መልክተኞች መሆናችንን በሰማይ የሚጠብቀንና የሚጠይቀን የላከን እንዳለ አንርሳ (1ኛ ጴጥሮስ 2፡11)
እንደ ሰነፉ ልጅ ለጌታ ስራ ጉልበታችንን ጊዜያችንን ገንዘባችንን ሳንሰስት ለጌታ ኖረን እንለፍ (ሉቃስ 6፡38)

ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ

worship.jpgእግዚአብሄርን ማምለክ ከሰማይ በታች እጅግ ልዩ ልምምድ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማየት እጅግ ያስደስታል፡፡ በእግዚአብሄር ክብርና መልካምነት መዋጥ መረስረስ መወሰድ የመጨረሻው ልምምድ ነው፡፡ ይህ ልምምድ በምድር ላይ ካሉ የሚያስደስቱ ልምምዶች እጅግ ይለያል፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ከምንም ጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡

ጌታን እየሱስን የሚወዱ ክርስቲያኖች ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ አንተ ነህ፡፡ አንተንና አንተን ብቻ እናመልካለን ይሉታል፡፡ ራእይ 1፡8

ስለዚህ ነው መዝሙረኛው ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ የሚለው እግዚአብሄርን በክብሩ ማየት ስለወደደ ነው፡፡ መዝሙር 122፡1

በእግዚአብሄር መገኘት የዘላለም ደስታና ፍስሃ አለ፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ያድሳል ያለመልማል፡፡

የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። መዝሙር 16፡11

እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 16፡15

እግዚአብሄርን ስናለምልክ የራሳችንን ድካም እንረሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልክ በእግዚአብሄር ሃይል እንታደሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመለክ በጨለማ ውስጥ ብርሃንን እናያለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመለክ በእግዚአብሄር መልካምነት እንወሰዳለን እንማካለን እንረሰርሳለን፡፡

እግዚአብሄርን በውበቱ ስናየው ማስተዋሉ በማይመረመር በእግዚአብሄር እውቀት እርፍ እንላለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልክ ተስፋችን ይለመልማል፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልክ ራሳችንንና የከበቡንን ነገሮች እንረሳለን፡፡

ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል። ኢሳይያስ 33፡17

አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። ዘጸአት 23፡25

አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ። ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ። መዝሙር 63፡1-2

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ተጓደዱ

የማይታይ እጅ

የክርስትናችን ማተብ

መንግስትን ሊሰጣችሁ

%d bloggers like this: