Category Archives: BLOOD

የትንሳኤ በዓል በዓመት 365 ቀናት እንደሚከበር ያውቁ ኖሯል?

easter.jpgየትንሳኤ በአል በአመት አንዴ ከ365 ቀናት ውስጥ አንድ ቀን የሚከበር ከሆነ ከንቱ ነው፡፡ የትንሳኤ በአል መከበር ያለበት በህይወታችን ዘመን ሁሉ ነው፡፡ ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ በሁሉም የአመቱ ቀኖች መኖትር ይኖርብናል፡፡ ኢየሱስ የሞተበትንና የተነሳበትን አላማ በሁሉም የአመቱ ቀኖች ተጠቃሚ መሆን ይኖርብናል፡፡

ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ሞቷል፡፡ እኛ ደግሞ 365 ቀናት ለሃጢያት ልንሞት ይገባናል፡፡

ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ሮሜ 6፡6

ኢየሱስ በመሰቀል ላይ ተሰቅሎዋል እኛ ደግሞ 365 ቀናት ለአለምና ለምኞቱ መሞት ይገባናል፡፡

ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። ገላትያ 6፡14

ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን በድል ከሞት ተነስቷል፡፡ እኛም ለፅድቅ ህያው መሆን አለብን፡፡ ኢየሱስ በታላቅ ሃይል ከሙታን እንደተነሳ እኛም በመለኮራዊ ሃይል 365 ቀኖችን ለእግዚአብሄር መኖር ይገባናል፡፡

እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ። ሮሜ 6፡11

ካልሆነ ግን በአመት አንድ ቀን ትንሳኤን ማክበት ከንቱ ነው፡፡ በአመት አንድ ቀን ብቻ ትንሳኤን ማክበር ኢየሱስ የሞተበትን አላማ መሳት ነው፡፡

መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14

መልካም የትንሳኤ ህይወት!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ትንሳኤ #ሃይል #ስልጣን #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መልካም የትንሳኤ ህይወት

ressurection power1.jpgየትንሳኤን በዓል ማክበር አለ፡፡ የትንሳኤን ህይወት መኖር አለ፡፡

ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ለራሱ አይደለም፡፡ ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ለእኛ ነው፡፡ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው በእኛ ምትክ ነው፡፡ ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ስለእኛ ነው፡፡

ኢየሱስ ሲሞትና ሲነሳ እኛም አብረነው ተነስተናል፡፡ ከኢየሱስ ጋር አብረን የተነሳን ሁላችን የትንሳኤውን ሃይል በህይወታችን እንድንለማመደው ተሰጥቶናል፡፡ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳይ ያው ሃይል በእኛ ውስጥ ይሰራል፡፡ ሰው በጉልበቱ ክርስትናን ሊኖር አይችልም፡፡ ክርስትና የትንሳኤውን ሃይል ይጠይቃል፡፡

ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። ኤፌሶን ሰዎች 1፡18-22

የትንሳኤን ህይወት የሚኖረው ሰው የሚታወቅባቸው ሰባት መንገዶች

 1. በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው ከሃጢያት በላይ የሆነን ኑሮ ይኖራል፡፡

ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ሮሜ 6፡6

 1. በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሰይጣን ላይ ስልጣን አለው፡፡

እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሉቃስ 10፡19

 1. በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሃጢያተኛ ስጋ ላይ ስልጣን አለው፡፡

እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤ ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። ሮሜ 8፡12፣14

 1. በትንሳኤ ሃይል የሚኖር ሰው እግዚአብሄር በምድር ላይ በሰጠው ራእይ ላይ ሙሉ ስልጣን አለው፡፡

ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14

 1. በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሁኔታዎች ላይ ስልጣን አለው፡፡

በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ሮሜ 8፡37-38

 1. በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በመንፈሳዊ ሞት ላይ ስልጣን አለው፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብራውያን 2፡14-15

 1. በትንሳኤ ሃይል የሚኖር ሰው ስጋዊ አካሉ በመንፈሱ ሃይልን ያገኛል፡፡

ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። ሮሜ 8፡11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ትንሳኤ #ሃይል #ስልጣን #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሞት – የተሸነፈ ጠላት

gate.jpgሰው ሃጢያትን በሰራ ጊዜ ሞትን ሞተ ከእግዚአብሄር ተለያየ፡፡ ለሰው ከእግዚአብሄር ከመለየት በላየ የሞት ሞት የለም፡፡ ኢየሱስ ወደምድ የመጣው እኛን ወደ እግዚአብሄር ሊመልሰን ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ ለእኔ ነው ብሎ የሚቀበል ሁሉ የዘላለም ህይወት ያገኛል፡፡ ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር ይኖራል፡፡ ሰው ህይወት ከሆነው ከእግዚአብሄር ጋር ከተገናኘ ከለዚህ በኋላ የሚያስፈራው መንፈሱ ከስጋ የመለየት ነገር የለም፡፡

እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብራውያን 2፡14-15

ሞት ለዘመናት ሰዎችን በባርነት ቀንበር ይዞ ቆይቷል፡፡ ሰዎች ከሞት የሚያድናቸው አጥተው ተጨንቀዋል፡፡ ሰዎች ከሞት የሚያስጥላቸው ማንም አልነበረም፡፡

በኢየሱስ ትንሳኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞት ተሸነፈ፡፡ ሞት አቅሙን አጣው፡፡ ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን ድል ነሳው፡፡ ሞት ድል የተነሳው ለኢየሱስ ብቻ እለነበረም፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ሞት እንዳይገዛቸው ነፃ ወጡ፡፡ አሁን ኢየሱስን የሚከተል ሞት ስጋቱ አይደለም፡፡

ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ? 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡55

አሁን ሞት አያስፈራም፡፡ አሁን ሞት ሃይል የለውም፡፡ ሞት ተሸንፎዋል፡፡ ሞት በህይወት ተውጧል፡፡

አሁን የዘላለም ህይወት ስላለን ሞት የምድር አገልግሎትን ጨርሰን የምንመረቅበት መንገድ ነው፡፡

በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡6

ሞት በስጋ ውስጥ ከመኖር የምናርፍበት መንገድ ነው፡፡

በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡2

ሞት ከድንኳን ወደ እጅ ወዳልተሰራ ቤት የምንገባበት በር ነው፡፡

ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡1

ሞት በጊዜና በቦታ ከተወሰነው አለም ወዳልተወሰነውና ወደተሻለ አለም የምንገባበት መንገድ ነው፡፡

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ዮሐንስ 14፡1-2

ሞት ጌታችንን የምናይበት ከጌታም ጋር ለዘላለም የምንኖርበት መንገድ ነው፡፡

በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ፊልጵስዩስ 1፡23

በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡2

ሞት የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን የሚለብስበት መንገድ ነው፡፡

የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን። ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡49፣54

 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ተነሥቷል

happy-easter-jesus-resurrection-risen-hd-wallpaper-background (1).jpgአዝ፦ ተነሥቷል (2x) ፡ የመቃብር ፡ ደጃፍ ፡ ተከፍቷል

ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል

ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ ፡ የታል?

በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል (2x)

 

ኢየሱስ ፡ ማሸነፉን ፡ ይስማ ፡ ኢየሩሳሌም

ይውጣ ፡ ምሥራቹ ፡ ከዓለም ፡ እስከዓለም

ይስማኝ ፡ ጠላትም ፡ መርዶውን ፡ አልቅሶ

ጌታ ፡ እንደው ፡ ተነስቷል ፡ አይሞት ፡ ተመልሶ

 

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) ፡ የመቃብር ፡ ደጃፍ ፡ ተከፍቷል

ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል

ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ ፡ የታል?

በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል

 

ይወገድ ፡ ድንጋዩ ፡ ጠባቂውም ፡ ይምጣ

ኢየሱስን ፡ ካቃተው ፡ ጌታ ፡ መውጫ ፡ ካጣ

የትኛው ፡ ጠባቂ ፡ ነው ፡ የከለከለው

ጌታ ፡ መቃብሩን ፡ ሲፈነቃቅለው

 

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) ፡ የመቃብር ፡ ደጃፍ ፡ ተከፍቷል

ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል

ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ ፡ የታል?

በዕውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥስቷል

 

ይነገር ፡ ለዓለም ፡ ምስራች ፡ ይሰማ

ሞትን ፡ አሸንፏል ፡ ጀግናው ፡ ኢየሱስማ

ይህ ፡ ሐሰት ፡ አይደለም ፡ ዘለዓለም ፡ እውነት ፡ ነው

ይታይ ፡ የጌታችን ፡ መቃብር ፡ ባዶ ፡ ነው

 

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) ፡ የመቃብር ፡ ደጃፍ ፡ ተከፍቷል

ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል

ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ ፡ የታል?

በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል

 

ይሄ ፡ ነው ፡ እንግዲህ ፡ የጐልጐታው ፡ ሚስጥር

ወንጌላችን ፡ ኢየሱስ ፡ ከሙታንም ፡ በኩር

ሙትን ፡ አናመልክም ፡ መቃብር ፡ የዋጠ

ያሸነፈን ፡ እንጂ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳ

 

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) ፡ የመቃብር ፡ ደጃፍ ፡ ተከፍቷል

ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል

ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ ፡ የታል?

በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል

 

መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

መስቀል የለሽ “ወንጌል”

cross less.jpg

የክርስትና ልቡ ያለው መስቀል ላይ ነው፡፡ መስቀል የሌለበት ወንጌል ልብ እንደሌለው አካል ነው፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እንደሞተ የማያስተምር እና በትምህርቶች ሁሉ ሞቱና መነሳቱ የወጡ ከሆነ ከርስትና አይደለም፡፡

የሰባኪዎች ፈተና ክርስቶስ እንደተሰቀለ መስበክ ትተው ወንጌሉን በጥበብ ብልጫ መከሸን ነው፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን አንደተሰቀለ እኛም መስቀላችንን ይዘን እንድንከተለው ካልሰበከ ተሳስቷል፡፡ ሃዋሪያው ግን ስብከቴ በክርስቶስና እርሱም በተሰቀለበት መስቀል ዙሪያ ብቻ እንዲሆን ወስኛለሁ ይላል፡፡

እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡1-2

ማነንም ሰው የመለወጥ አቅም ስለሌለው መስቀል የለሽ ስብከቶችን ሰይጣን አይፈራም፡፡ ሰይጣን ስለመስቀል እስካልተናገራችሁ ድረስ የፈለጋችሁትን ሀይማኖት ያድላችኋል፡፡

የክርስትና ሃይሉ የመስቀሉ ቃል ላይ ነው፡፡

የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል እኛም አብረን ተሰቅለናል፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ሲሞት እኛ ሃጢያታችን ይቅርታ አገኘን፡፡ እኛ እብረነው በተሰቀልን ጊዜ ከሃጢያተኛ ስጋችን ተሰቀለ፡፡

ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ሮሜ 6፡6

የሰው እውነተኛ ፈተና መስቀሉን በሞኝነት መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ ነው፡፡

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡23

የክርስትና የመጨረሻ አላማው የትንሳኤውን ሃይል መረዳት ነው

እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡10-11

ሰዎች ሲስቱ የሚነሱት በመስቀል ላይ ነው፡፡

ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። ፊልጵስዩስ 3፡18-19

ለትውልድ የምናስተላልፈው የወንጌል ቃል ይህ ነው፡፡

እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3-4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ሞት #ኢየሱስ #ክርስቶስ #መስቀል #ጠቦት #በግ #ደም #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የክርስቶስ ደም አስፈላጊነት

 

blood_2-1.jpg

 

1. ከከንቱ ኑሮአችንም የተገዛነው እና የተዋጀነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡

ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡18-19

 1. ከሞተ ስራ ህሊናችንን ያነፃው የክርስቶስ ደም ነው፡፡

ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? ዕብራውያን 9፡14

ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤ ዕብራውያን 10፡22

 1. የተቀደስነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። ዕብራውያን 13፡12

እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ሮሜ 3፡25

 1. የተቤዠነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡ ካለደም ስርየት የለም፡፡

በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ኤፌሶን 1፡7

እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም። ዕብራውያን 9፡22

 1. የሃጢያት ልብሳችን የታጠበው በክርስቶስ ደም ነው፡፡

እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ። ራእይ 7፡14

ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ ራእይ 1፡5

 1. በእምነት በፀጋ ብቻ የምንፀድቅበት አዲስ ኪዳን የተሰጠን በክርስቶስ ደም በኩል ነው፡፡

እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡25

 1. የፀደቅነው በደሙ ነው፡፡

ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ሮሜ 5፡9

 1. ወደእግዚአብሄር የቀረብነው በክርስቶስ ደም ነው

አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። ኤፌሶን 2፡13

 1. የክርስቶስን ስጋ ያልበላ የክርስቶስን ደም ያልጠጣ በራሱ ህይወት የለውም፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ዮሐንስ ወንጌል 6፡53

 1. የክርስቶስን ደም የናቀ ሌላ ምንም የመዳን እድል የለውም

የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? ዕብራውያን 10፡29

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጠቦት #በግ #ደም #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በኢየሱስ ሞት የተፈፀሙ ሶስት ነገሮችና ትርጉማቸው

cross jesus2.jpgኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተበት ጊዜ ሶስት ታላላቅ ትርጉም ያላችው ሁኔታዎች ተፈፅመዋል፡፡

 1. የቤተመቅ ደስ መጋረጃ ተቀደደ

ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ ማቴዎስ 27፡50-51

እግዚአብሄር ቅዱስ ነው፡፡ በሃጢያት ምክኒያት ሰው ወደ እግዚአብሄር መግባት አይችልም ነበር፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እዳ ሙሉ ለሙሉ ስለከፈለ እግዚአብሄርና ሰው መለያየት ቀረ፡፡ ሰው በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሄር መግባት ተሰጠው፡፡

እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ ዕብራውያን 10፡19-20

 1. ቅዱሳን ከሞት ተነሱ

መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ። ማቴዎስ 27፡52-53

ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እዳ በመስቀል ላይ ስለሞተ በኢየሱስ ያመንም ሁላችን አሁን በትንሳኤ ህያው እንደሆንን ያሳያል፡፡

ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡5

 1. የኢየሱስንም የእግዚአብሄር ልጅነት የማያምኑ መሰከሩ

ስድስት ሰዓትም ያህል ነበረ፥ ጨለማም እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ሆነ፥ ፀሐይም ጨለመ፥ ሉቃስ 23፡44

የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ። ማቴዎስ 27፡54

የምድር መናወጥና በቀን ጨለማ ሆነ፡፡ ተፈጥሮ እንኳን ስለኢየሱስ ሞት መልስን ሰጠች፡፡ የኢየሱስ መሞት ዋናው አላማ ሰዎች በስሙ አምነው ከሃጢያታቸው እንዲድኑ ነው፡፡

እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። ሉቃስ 24፡46-48

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መስቀል #ስቅለት #ጠቦት #መጋረጃ #ደም #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተፈፀመ #ቤተመቅደስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ተፈፀመ!

paid.jpgኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። ዮሐንስ 19፡30

ኢየሱስ የሰው ልጆችን የሃጢያት እዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ይህን ጊዜ ነው ተፈፀመ ያለው፡፡ ግን ተፈፀመ ያለው ምን እንደነበር እንመልከት፡፡

ተፈፀመ-በእግዚአብሄር እና በሰው መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ አበቃለት

የሰውና የእግዚአብሄ ጠላትነት አበቃለት፡፡ አሁን ማንም ሰው ሃጢያተኛ እንደሆነ አምኖ በንስሃ ወደ እግዚአብሄር ከመጣ እግዚአብሄር በይቅርታ ይቀበለዋል፡፡

እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ኤፌሶን 2፡14-15

ተፈፀመ-እግዚአብሄርንና ሰውን የማስታረቅ ስራ ተጠናቀቀ

እግዚአብሄርና ሰው የተጣሉበት የሃጢያት እዳ ፈፅሞ በመከፈሉ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ይችላል፡፡ ሰው ካሁን በሁዋላ ከአግዚአብሄ ጋር ጠላት ሆኖ ቢኖር ስላልፈለገ እንጂ የሃጢያቱ እዳ ስላልተከፈለለት አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19

ተፈፀመ-አሮጌው ኪዳን

ሰዎች በስራ ከእግዚአብሄር ተቀባይነት የሚያገኙበት አሮጌው ኪዳን ተፈፀመ፡፡ አሁን ሰው የኢየሱስን የመስቀል ስራ ለእኔ ነው ብሎ በመቀበል ብቻ ይፀድቃል የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናል፡፡

ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና። ሮሜ 3፡28-29

ተፈፀመ-የሃጢያት እዳ ሁሉ ተከፈለ

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት እዳ በእምነት መቀበል እንጂ ማንም ስለሃጢያት እዳው ለመክፈል መሞከር የለበትም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መስቀል #ስቅለት #ጠቦት #በግ #ደም  #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተፈፀመ #መስቀል #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የፋሲካ ሚስጥር

BLOOD.jpgየእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ። በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት። ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቅቡት። ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም። ዘጸአት 12፡5-7፣11-13

እስራኤላዊያን ከግብፅ ሲወጡ ያደረጉት ስርአት የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ነበር፡፡ እስራኤላዊያን ያረዱት ጠቦት ለእኛ ሃጢያት የሞተው የኢየሱስ ምሳሌ ነበር፡፡

እስራኤላዊያን እንዲያርዱት የታዘዙት ነውር የሌለበት ጠቦት ነበር፡፡ ዘጸአት 12፡5

በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። ዮሃንስ 1፡29

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21

የእስራኤል ህዝብ ከሞት መቅሰፍት እንዲድኑ ደሙን በመቃናቸው ላይ እንዲረጩት ታዘዋል፡፡ ዘጸአት 12፡6

ንስሃ በመግባት በኢየሱስ ደም የታጠበ ሰው ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋግሯል አንጂ ሞትን አያይም፡፡

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንስ 5፡24

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

ደሙን ባየ ጊዜ መቅሰፍት ወደቤታቸው አይገባም ነበር ያልፋቸው ነበር፡፡  ዘጸአት 12፡13

ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን የደሙ ምልክት በእኛ ላይ ይኖራል፡፡ ማንኛውም አይነት  ከህይወት የተለየ ነገር (ሞት) በእኛ ላይ ስልጣን የለውም፡፡

እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም። ራእይ 12፡11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጠቦት #በግ #ደም #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: