Category Archives: Prayer

ለምንወደው የምንሰጠው የፍቅር ስጦታ

Publication15.jpgለምንወደው ሰው ምን አይነት የፍቅር ስጦታ ልስጠው ብላችሁ ብታስቡና እና የመረጃ መረብን ብትጠይቁ የፍቅር ስጦታ ሃሳቦች የሚል ብዙ አማራጭ ታገኛላችሁ፡፡ ለምትወደው ሰው እንደዚህ አይነት ስጦታ ብትሰጠው መልካም ነው የሚል ሃሳብ ይሰጣችኋል፡፡ ለዚህ በአል ይህንን ስጦታ ብትሰጠው ሰው ደስ ይለዋል የሚል ብዙ የስጦታ ሃሳቦችን ታገኛላችሁ፡፡ ለምትወዱት ሰው ስጦታ መስጠት ፈልጋችሁ ምን መስጠት እንዳለባችሁ ለየት ያለ የፈጠራ ሃሳብ እንዲሰጣችሁ የመረጃ መረቡን ትጠይቁ ይሆናል፡፡ ይህንን አይነት ቀለም ያለው አበባ ለዚህ አጋጣሚ ብትሰጥ አጋጣሚውን ልዩ ያደርገዋል በማለት የተለያየ ሃሳቦችን ይሰጣችኋል፡፡ አጠያይቃችሁ ሰዎች አማክራችሁ እንኳን ስጦታችሁ ላይሰምር ፣ ተቀባይነት ላያገኝ ፣ ላይወደድ ብሎም ላይጠቅም ይችላል፡፡

እኔ ደግሞ ሰው ለሚወደው ሰው ምን አይነደግሞ ሰውስጦታ ሊሰጥ እንደሚችል መፅሃፍ ቅዱስን አገላብጫለሁ፡፡ ሰው ለሚወደው ሰው የሚሰጠው ልዩ የሆነን የስጦታ ሃሳብ ስላገኘሁ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ይህ ስጦታ እንደ አበባ ስጦታ ፣ እንደ ልብስ ፣ እንደ ጌጣጌጥ ስጦታ በገንዘብ የሚገመት ስጦታ አይደለም፡፡ ይህ ስጦታ የሚቀበሉትን ሁሉ የሚባርክ እንደ እግዚአብሄር ቃል የሆነ ስጦታ ነው፡፡

ይህ ስጦታ የሰዎች ህይወት የሚለውጥ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ ሰዎችን የሚያበረታ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ ሰዎችን የሚያነሳ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ የሰዎችን ህይወት የሚለውጥ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ እራሳችንን ለፀሎት የምንሰጥበት የምልጃ ፀሎት ነው፡፡

ምልጃ በሌላ ሰው ቦታ ለሌላ ሰው በእግዚአብሄር ፊት የምንጠይቅበት ፀሎት ነው፡፡ ይህ የምልጃ ፀሎት የሌላውን መስማማት ወይም አለማስማመት አይጠይቅም፡፡ የሚማልድለት ሰው እንደሚማልድለት እንኳን ላያውቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን የምልጃው ውጤት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ይህ ፀሎት በሌላው ሰው ቦታ ሆነን ፣ የሌላው ሰው ስሜት እየተሰማን ፣ የሌላው ሰው ህመምን እየታመምንና የሌላውን ሸክም እንዳራሳችን ሸክም እየተሸከምን የምንፀልየው የፀሎት አይነት ነው፡፡

ምልጃ ሌላው ሰው መፀለይ በማይችልበት ጊዜ በእርሱ ፋንታ ሆኖ የሚፀለይ ፀሎት ነው፡፡ ምልጃ ሌላው ሰው በማይረዳበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ተረድቶ ስለሌላው ሰው የሚደረግ ልመና ነው፡፡

ጴጥሮስ የሚያደርገውን በማያውቅበት ጊዜ ይህንን የተመለከተው ኢየሱስ ስለ ጴጥሮስ ማለደ፡፡

ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃስ 22፡32

ለቅዱሳን መዳን ማሸነፍና መውጣት ልንማልድ ይገባናል፡፡

በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤ ኤፌሶን 6፡18

ስለሚወዱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለሚጠሉንም ሰዎች ልንሰጣቸው የምንችለው ድንቅ ስጦታ ስለ እነርሱ በእግዚአብሄር ፊት መማለድ ነው፡፡ ስለሰዎች በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ ልዩ ስጦታ ነው፡፡

ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ ማቴዎስ 5፡44

ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት። ሉቃስ 23፡34

ጌታን ሰለሚያውቁትም ስለማያውቁትም መማለድ ለሰዎች የምንሰጣው ልዩ ስጦታ ነው፡፡

. . . ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-2

ይህንን ምልጃ የምናደርገው በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና እርዳታ ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እብሮ ለመቃተት ግን ራሳችንን ማዘጋጀትና ጊዜን መስጠት የሚጠበቀው ከእኛ ነው ፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡26

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #ፀሎት #እግዚአብሄርንመፈለግ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #አላማ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መቃተት #መንበርከክ #መጠበቅ #ትግስት #መሪ

Advertisements

እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም

seek god11.jpgበቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።መዝሙር 105፡3-4

በምድር ላይ እንደተጠበቁት የማይገኙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ በጠበቅንባቸው ስላላገኘናቸው ብዙ ነገሮች ያሳዝኑናል ቅር ያሰኙናል፡፡ ሰዎች ብዙ ነገሮችን ጠብቀው በብዙ ነገሮች ይሰናከላሉ ያዝናሉ ይዝላሉ ተስፋም ይቆርጣሉ፡፡

ብዙ ነገሮች ካቅማቸው በላይ ተስፋ አድርገንባቸው ያሳዝኑናል፡፡

ነገር ግን እግዚአብሄርን መፈልግ ግን አስተማማኝ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄን መፈለግ መቼም አያከስርም፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ መቼም አይፅትም፡፡

እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው የማያሳዝንና የማያሰናክል አስተማማኝ ነገርን መርጧል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ግን ተስፋው አይጠፋም አይሰናከልም አያዝንም፡፡

እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ይፀናል ይበረታል ያሸንፋል፡፡ እግዚአብሄርን እንድመፈለግ አስተማማኝ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ አትራፊ ስራ የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ የሚያስመካ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ የሚያጓድድ ነገር የለም፡፡

እግዚአብሄርን እንደሚፈልግ ሰው ደስተኛ ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደሚፈልግ ሰው አትራፊ ሰው የለም፡፡  እግዚአብሄርን እንደሚፈልግ ሰው ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ባለጠጋውን እግዚአብሄርን እንደመፈለግ የመሰለ ባለጠግነት የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ አስደሳች ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈልግ ጥበብ የለም፡፡

ምክሩ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉት ነው፡፡

ሁሌ ለመሳካት ፣ ሁሌ ለመከናወን ፣ ሁሉ ለማሸነፍ ፣ ሁሉ ለመፅናት ሁልጊዜ ፊቱ መፈለግ፡፡

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።መዝሙር 105፡3-4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በዘፈንና በስካር አይሁን

Ethiopia_4.jpgክርስትና ከሚታወቅበት ልዩ ባህሪዎች አንዱ ሚዛናዊ የሆነንን ህይወት መምራት ነው፡፡ክርስትያን በደስታም የሚያከብረው እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን በደስታም ከልክ አያልፍም፡፡ ክርስትያን ደስታውና ዘና ማለቱ ሃጢያት እስኪያሰራው አያደርሰውም፡፡ ክርስትያን በነገሮች ያለመጠን አይፈነጥዝም ደስታውን ሁሉ በልክ ያደርጋል፡፡

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29-31

ክርስትያን በሃዘንም እግዚአብሔርን ነው የሚያየውም የሚያከብረውም እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን ሃዘኑም ለሞት የሚያደርስ ራስን የሚያስጥል ከመጠን ያለፈ አይደለም፡፡

የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10

ክርስትያን አገኘሁ ብሎ ብዙ አይበላም ራስን በመግዛት ራሱን ያዝ ያደርገዋል፡፡ ክርስትያን አገኘሁ አገኘሁ ብሎ ብዙ አይጠጣም፡፡ ክርስትያን ለመንቃት የሚያደክመውን ካለልክ እንዲዝናና የሚያደርገውን ኑሮ ይሸሻል፡፡ ክርስትያን ለመንቃትና ሳያቋርጥ ለመፀለይ ስለሚፈልግ እንቅልፍ እንቅልፍ የሚያስብለውን የሚያደክመውን ከመጠን ያለፈ ኑሮ አይኖርም፡፡

ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ሮሜ 13፡11-13

በመጠኑ መኖር በመንፈስ ለመንቃት ይጠቅማል፡፡ መንቃት ደግሞ ለመፀለይና ይጠቅማል፡፡ በመጠኑ መኖር ላለመዘናጋት ነቅቶ ለመፀለይ ይጠቅማል፡፡

በመጠኑ ኑሩ ንቁም፥ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያጋሳ አንበሳ ይዞራልና፤1ኛ ጴጥሮስ 5፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የአዲስ ዓመት ምኞት ወይስ ፀሎት?

large_what-if-i-don-t-want-to-pray-nryzc7wj (1).jpgበአዲስ አመት አብዛኛው ሰው ለሌላው መልካም ነገርን ይመኛል፡፡ በጎን ፈቃድ መግለፅና ለሌላው በጎውን መመኘት መልካም ነው፡፡ መልካም መመኘት ለሌላው ያለንን መልካም ፈቃድ ለማሳየት እጅግ ይጠቅማል፡፡

እንደ መንፈሳዊ ሰው ደግሞ መልካም እንደምንመኝላቸው ሁሉ ጊዜ ወስደን እንፀልይላቸዋለን ወይ?  የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ይገባናል፡፡

የምንወዳቸውን የምናከብራቸውን ወዳጆቻችንን መልካም ልንመኝላቸው ብቻ ሳይሆን ልንፀልይላቸው ይገባል፡፡

የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16

በአዲስ አመት ልንፀልይላቸው የሚገባ

  1. ለወንድሞችና ለእህቶች

ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16

  1. ለቤተክርስትያን መሪዎች

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ እኛ ጸልዩ። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡25

አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ የሚችል የለምና። 2ኛ ዜና መዋዕል 1፡10

  1. ጌታን ለማያውቁ ሰዎች

ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2-4

  1. ለወንጌል ሰራተኞችና ለሚሽነሪዎች

ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ ኤፌሶን 6፡19

በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ቆላስይስ 4፡3

  1. ለመንግስት ባለስልጣናት

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ተቃውሞ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ዋጋ እንዲሰጥ

32584-praying-hands-3-1200.1200w.tn.jpgወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ሰዎች አሰሪን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ስራን ሰርተውለት ጥሩ የሚከፍላቸውን አሰሪ ተግተው ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ዝነኛ ስም ያለው የተከበረ መስሪያ ቤት ሲሰሩ ይበልጥ ደስ ይላቸዋል፡፡

ሰራተኛንና አሰሪን የሚያገናኝ የሰው ሃይል አስተዳደር ኢንዱስትሪ ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ ትልልቅ ድርጅት ያላቸው ሰዎች ለድርጅታቸው በቋሚነት ሰራተኛ የሚመለምሉበትና የሚቀጥሩበት ትላልቅ መምሪያ አላቸው፡፡

ድርጅቶቹ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ የሚሰራላቸው ብቁ የሆነው ሰው ለመመልመል ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ሁሉም ግን የሚሰራላቸውን ሰው ነው የሚፈልጉት፡፡

ፈልጉኝና ዋጋን እሰጣችኋለሁ ያለ ሰው ሰምቼ አላውቅም፡፡ ስለፈለግነው ብቻ ዋጋን የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ዋጋን ይሰጣል፡፡

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ ሰው መሆን ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡26-28

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በእምነት መፈለግ ነው፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በፍፁም ልብ መፈለግ ነው፡፡

እግዚአብሔር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኩሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንም ባጣ ቆየኝ እንዲያደርገው አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔርን በሁለት ሃሳብ እንድንፈልገው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔርን ፈልገን እንደባለጠግነቱ መጠን ዋጋ እንዲሰጠን ካስፈለገ በፍፁም ልባችን ልንፈልገው ይገባል፡፡

እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርሚያስ 29፡13

ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ  1፡7-8

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህ አዲስ ዓመት እግዚአብሔርን በመፈለግ እንደባለጠግነቱ መጠን ከእግዚአብሔር ዋጋ የምንቀበልበት ዓመት ይሁን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #እግዚአብሔርንመፈለግ #መፀለይ #ፍፁምልብ #አዲስአመት #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሳያቋርጡ መፀለይ እንዴት ይቻላል?

cd4be7c6.jpgሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18

መፅሃፍ ቅዱስ ሳታቋርጡ ጸልዩ ብሎ ካዘዘ የምር ነው ማለት ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ካዘዘ ይቻላል ማለት ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ካለ መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው የምችለው የሚለውን ብቻ ነው፡፡

ሰው ሳያቋርጥ መፀለይ የሚችለው ፀሎት ምን እንደሆነ ሲረዳ ነው፡፡ ፀሎት ምን እንደሆነ  ያልተረዳ ሰው እንኳን ሳያቋርጥ ሊፀልይ ቀርቶ ምንም ሊፀልይም አይችልም፡፡

ተንበርክከን ወደ እግዚአብሄር የምንፀልይበት ጊዜ አለ፡፡ ቤታችንን ዘግተን የምንፀልይበት ጊዜ አለ፡፡ ድምፃችንን አውጠተን የምንፀልይበት ጊዜ አለ፡፡  ሁልጊዜ ግን በዚህ መንገድ መፀለይ አንችልም፡፡ በዚህ ሁሉ መንገድ መፀለይ የማንችልበት ጊዜ ይፈጠራል፡፡

ሳናቋርጥ ለመፀለይና በፀሎት ውስጥ ያለውን በረከት ተጠቃሚ ለመሆን በቀን ውስጥ ካለን የፀሎት ሰአት ውጭ መፀለይ መልመድ አለብን፡፡ ሳናቋርጥ በፀለይን መጠን ድላችን የማይቋረጥ ይሆናል፡፡

ሰው ድምፁን ሳያሰማ በዝምታ ከራሱ ጋር ይነጋገራል፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ሰው ድምፁን ሳያሰማ በልቡ ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ይችላል፡፡ ሌላው ሳይሰማ ሰው እግዚአብሄርን ሊጠይቅ ከእግዚአብሄር መልሱን ሊሰማ ይችላል፡፡ ሰው በስራው ላይ እያለ ከእግዚአብሄር ጋር በልቡ ሊነጋገር ይችላል፡፡

ፀሎት ልብን ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ማንሳት ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሄር የልብን ጩኸት ይሰማል የሚባለው፡፡ ሰው በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ልቡን ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ሊያነሳ ይችላል፡፡ ሰው በዝምታ የእግዚአብሄርን እርዳታ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሰው ሌላ የእለት ተእለት ስራውን እየሰራ የእግዚአብሄርን እርዳታ ሊፈልግ ይችላል፡፡

እውነት ነው ይህ ሁሉ ግን የሚጀመረው በርን ዘግቶ ከመፀለይ ነው፡፡ ሳያቋርጡ ፀሎትን የምንለማመደው ተንበርክከን ወደ ህልውናው ውስጥ መግባትን ከለመድን በኋላ ነው፡፡

አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ማቴዎስ 6፡6

በስራ ቦታህም ሆነ ባለህበት ቦታ የምትፀልየው ያለማቋረጥ ፀሎት እልፍኝህን ዘግተህ ለምትፀልየው ፀሎት ተጨማሪ ይሆናል እንጂ የእልፍኝህን ፀሎት ሙሉ ለሙሉ አይተካውም፡፡

ሳታቋርጡ ጸልዩ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ቃል #ፀሎት #ልመና #ሳታቋርጡ #እልፍኝ #እግዚአብሔር #መኖር #እምነት #መስማት #መታዘዝ #በቃሉመኖር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሔር ይፈለጋል!

seek god.jpgበቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። መዝሙር 105፡3

እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ባለጠጋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ ሰው ማንንም ባይፈልግ እግዚአብሔርን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው ሌላውን ነገር ለመፈለግ ጊዜ ባይሰጥ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ጊዜ መስጠት አለበት፡፡ ሌላ ነገር ሁሉ የሚፈልግ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሰው ከስሮዋል፡፡

ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥ የተቀደዱትንም ጕድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል። ኤርሚያስ 2፡13

እውነተኛ መረዳት ሲኖረን እግዚአብሔርን የማንፈልግበት የህይወት ክፍል እንደሌለ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔርን ባወቅነው መጠን ይበልጥ እንፈልገዋለን፡፡ እግዚአብሔርን በተረዳነው መጠን እግዚአብሔር ይበልጥ እንደሚያስፈልገን እንረዳለን፡፡ በእግዚአብሔር ነገር ማደጋችን የሚለካው እግዚአብሔርን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመፈለጋችን ነው፡፡ የህይወትን አሰራር በተረዳነው መጠን እግዚአብሔርን ይበልጥ እንፈልገዋለን፡፡

በእግዚአብሔር እውቀት ያለን ብስለት የሚለካው እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በመፈለጋችን ነው፡፡ አዋቂነታችን የሚለካው ከአዋቂዎች ሁሉ በላይ አዋቂ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ በመደገፋችን ነው፡፡

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28

እግዚአብሔር ሙሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያስመካል፡፡ እግዚአብሔር ያኮራል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ደስ ይበለው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው እድለኛ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው የተባረከ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ደስ ካላለው ማንም ደስ ሊለው አይችልም፡፡

እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰውን መልካምነት ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ይወዳል፡፡ እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ብቻ እርሱን በመፈለጋቸው ዋጋ ይከፍላል፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራዊያን 11፡4

እግዚአብሔርን ፈልጉት ትፀናላችሁ፡፡ እግዚአብሔርን ስትፈልጉት በእርሱ ታላቅ ሃይል ትገለጣላችሁ፡፡ እግዚአብሔርን በሚፈልጉት ሰዎች ድካም የራሱን ሃይል ይገልጣል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ሰዎች ድካም በብርታቱ ይሸፍናል፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። 2ኛ ዜና 16፡9

እግዚአብሄርን ስንፈልገው እንደባጣ ቆየኝ ሳይሆን በአክብሮት በሙሉ ልባችን እንድንፈልገው ይፈልጋል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነት ጨምርልን

faith_ann.jpgሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6

ለስጋችንና ለምስኪን እኔ አስተሳሰባችንን የሚመቹ ነገር ግን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የፀሎት ርእሶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል እምነትን ጨምርልን የሚለው አንዱ ነው፡፡

ሃዋሪያት ኢየሱስን እምነትን ጨርልን ሲሉት “እሺ ተቀበሉ እምነትን እየጨመርኩላችሁ ነው” አላላቸውም፡፡ ኢየሱስ ያለው ያላችሁን ትንሽ የምትመስለውን እምነት ተጠቀሙ ስራ ስሩባት ለውጥን ታመጣለች ነው፡፡ ኢየሱስ የሚለው ነገራችሁን ለመለወጥ የሚያስፈልጋችሁ ያላችሁ ትንሽ የምትመስለው እምነት ብቻ ነች፡፡ ኢየሱስ የሚለው የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል የሆነችውን እምነት መጠቀም አለባችሁ ለውጥ የሚመጣው በእርሱ ነው፡፡

የእምነት ትንሽ የለውም፡፡ እምነት ሁሉ ይሰራል፡፡ ያላችሁን እምነት ብትጠቀሙ ለውጥ ይመጣል፡፡ እምነት ጥቅም ላይ ሲውል ሁልጊዜ ታላቅን ስራን ይሰራል፡፡ የእምነት እርምጃን በመውሰድ ለውጥን ታያላችሁ፡፡

አንዳንድ ሰው የሚረካው በመለመን ብቻ ነው ፡፡ ባለው እምነት መጠቀም ፣ እርምጃ መውሰድ ፣ ስራ መስራትና ፍሬ ማፍራት አያውቅም፡፡ ስለዚህ በህይወቱ ለውጥን አያይም፡፡ ሰው የሚያስፈልገው አሁን ባለው እምነት መጠቀም ነው፡፡

ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ጥርጥር #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

አራቱ የማይመለሱ የፀሎት አይነቶች

not answerd prayer.jpgእግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጋር የሚደርስ ሰው ማድረግ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ማድረግ የማይገባቸው ነገሮች አሉ፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ሰው በእግዚአብሄር መንገድ ካልፀለየ አይመለስለትም፡፡

  1. ከፈቃዱ የሚቃረን ፀሎት

ከሰው አፍ የወጣውን ሁሉ እግዚአብሄር አይመልስም፡፡ በተለይ ከፈቃዱ የሚፃረንን ፀሎት እግዚአብሄር በፍፁም አይመልስም፡፡ ከባህሪው ጋር የሚቃረንን ልመና እግዚአብሄር አይመልስም፡፡

እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1ኛ ዮሐንስ 5፡14

  1. በቅንጦት የተፀለየ ፀሎት

ስንፀልይ የሚያስፈልገንን ነገር እንድንፀልይ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ የእኛን የምኞት ጥያቄ እንደሚመለስ በየትኛውም የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ቃል አልተገባልንም፡፡ ስለዚህ ከመፀለያችን በፊት እውነተኛ ፍላጎት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ስለዚህ ነው ለመፀለይ መቸኮል የሌለብን ፡፡ ለመፀለይ ምን እንደሚያስፈልገን ለማወቅ ጊዜ መሰጠት ያለብን፡፡ እንድ ጊዜ ፍላጎታችንን ካወቅን የሚመለስ ፀሎትን ለመፀለይ ቀላል ይሆንልናል፡፡

ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደምንፀልይ ያለማወቅ ድካማችንን የሚያግዘን፡፡ ሮሜ 8፡26

ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡3

  1. በጥርጥር የተፀለየ ፀሎት

እግዚአብሄር እምነትን ከእኛ ይጠብቃል፡፡ እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅርና እንክብካቤ በመረዳት እንድንፀልይ ይፈልጋል፡፡ ልባችንን ከጥርጥር እንድናነፃ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

  1. በማጉረምረም የሆነ ፀሎት

ወደእግዚአብሄር የመቅረብ ፕሮቶኮሉ ምስጋና ነውለእግዚአብሄርነቱና ለመልካምነቱ እውቅና መስጠት ግድ ይላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ምንም አድርጎልን እንደማያውቅ እግዚአብሄርን ለመውቀስ የምንወረውርው ቃል እግዚአብሄር አይመልሰውም፡፡

እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡3-4

ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ማጉረምረም #ምስጋና #ቅንጦት #ጥርጥር #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

የውጤታማ ፀሎት ቁልፍ

prayer fruitful21.jpgበፀሎት ውስጥ የተጠራቀመ አጅግ ታላቅ ሃይል አለ፡፡ ስለፀሎት ያለን መፅሃፍ ቅዱሳዊ መረዳት በፀሎት ህይወታችን ፍሬያማ እንድንሆን ያደርጋል፡፡ ፍሬያማ ፀሎትን ከማየታችን በፊት ፍሬያማ ያልሆነን ፀሎት እስኪ እንመልከት፡፡

የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16

ፍሬያማ ያልሆነ ፀሎት ንግግር ብቻ ነው፡፡

ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን መስማትና ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡ ሲጀመር እስኪጨረስ ለእግዚአብሄር መናገር ጸሎት አይደለም፡፡ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን ስለማናውቅ ሃሳባችንን ለእግዚአብሄር መናገር ብቻ ንግግር እንጂ ፀሎት አይደለም ፡፡

መክብብ 5፡2 ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።

ፍሬያማ ያልሆነ ፀሎት የፈሪ ዱላ ነው፡፡

ፀሎት የፈሪ ዱላ አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን ከእንቅልፉ የምንቀሰቅስበት መጥሪያ ጩኸት አይደለም፡፡ ፀሎት ስለህይወታችን ለእግዚአብሄር ካልነገርነው በስተቀር አያውቅም ብለን ለማሳወቅ የምንጥርበት ጥረት አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ስለማያውቅ የምናሳውቅበት ማስታወቂያ አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር የማያውቀውን ነገር በመንገር የምናስደንቅበት መንገድ አይደለም፡፡

ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡8

ፍሬያማ ያልሆነ ፀሎት እግዚአብሄርን ማስረጃ ነው፡፡

እግዚአብሄር ከእኛ ፀሎት መረጃን ሰብስቦና ተረድቶ የህይወት እቅዳችንን የሚሰራበት መንገድ አይደለም፡፡ የህይወት እቅዳችን ቀድሞውንም በእርሱ ዘንድ አለ፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

ፀሎት በእረፍት እግዚአብሄርን መስማትና ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡  ፀሎት ከአባታችን እግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ህብረት የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር ቁጭ የምንልበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ የምንጠይቅበት መንገድ ነው፡፡ ጸሎት ምን ላድርግልህ የምንልበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት ምኔን ልስጥህ ብለን የምንጠይቅበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን ለመስማት ፣ ለመታዘዝና ለማገልገል በፊቱ የምንቀመጥበት መንገድ ነው፡፡

ፀሎት እንደ አስተናጋጅ ሁለት እጃችንን ወደኋላ አጣምረን እግዚአብሄር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ የምንጠይቅበትና የምንሰማበት የአምልኮና የህብረት ጊዜ ነው፡፡

እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። ሐዋርያት 13፡2

የእግዚአብሄር መንፈስ ስለእኛ ወይም ስለሌላው እንዴት እንደምንፀልይ የሚመራን በፊቱ በእረፍት ስንሆን ነው፡፡ እንዴት መፀለይ እንደሚገባን መንፈስ ሲመራን ፀሎታችን አላማውን ይመታል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ቆይተን በምሪት የምንፀልየው ፀሎት ግቡን ይመታል፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ ተደግፈን የምንፀልየው ፀሎት ጊዜ ሳይወስድ ዝም ብሎ እንደማይተኩስ ጠብቆ አነጣጥሮ አላማውን እንደሚመታ ተኳሽ በፀሎት ህይወታችን ፍሬያማ ያደርገናል፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡26

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አጥብቆ #ፀሎት #ልመና #ኤልያስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሃይል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

%d bloggers like this: