Category Archives: truth

ለውግዘት የተሳሳቱ መልሶች

Publication15.jpgበህይወታችንና በአገልግሎታችን ውግዘትና ተቃውሞ ይብዛም ይነስም በየጊዜው የሚከሰቱ ነገሮች ናቸው፡፡

ሰዎች በትክክለኛውም መንገድ ይሁን በተሳሳተ መንገድ ሊቃወሙንና ሊያወግዙን ይችላሉ፡፡ ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል ተከትለው ትክክለኛውን እርምጃ ጠብቀው ሊያወግዙን ይችላሉ፡፡

ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። ማቴዎስ 18፡15-17

ሰዎች ለትክክለኛውም ሆነ ለተሳሳተ ምክኒያት ሊቃወሙንና ሊያወግዙን ይችላሉ፡፡ ሰዎች ከፍቅር ተነስተው እኛን ለማዳንና ከደከምንበት ለማቅናት የእኛን መመለስና እንደገና ጠቃሚ መሆን አልመው ሊያወግዙን ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ከቅናት ከጥላቻ መነሻ ሃሳብ /motive/ ስለ በለጥናቸው ፣ ስላደግንና ስለሰፋን ሊያወግዙንና ሊቃወሙን ይችላሉ፡፡

አንዳንዶቻችን እስከዛሬ ተወግዘን ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ከአሁን በኋላ ልንወገዝ እንችላለን፡፡ አንዳንዶቻችን በአደባባይ እንወገዛለን ሌሎቻችን ደግሞ በቤተሰባችን በትምህርታችንም ይሁን በአካሄዳችን ልንወገዝ እንችላለን፡፡ በምንም መልኩ ቢሆን የሚመጣን ተቃውሞና ወገዛ የምንቀበልበትና የምናስተናግድበት የተሳሳተና ትክክለኛ መንገድ አለው፡፡ ወገዛን በትክክለፃው መንገድ ካስተናገድነው ይጠቅመናል በተሳሳተ መልኩ ከመለስነው ደግሞ አይጠቅመንም፡፡

ለተቃውሞ የምንመልስበት አምስት የተሳሳቱ መንገዶች

ጥላቻ

ሰውን ሁሉ ከመውደድ በስተቀር ማንንም ሰው እንድንጠላ መብት የለንም፡፡ ሰው ጠላኝ ብለን ብንጠላ የምንጎዳው እኛው ነን፡፡ የተሳሳተ ሰውን እንኳን ለመጥላት መብት የለንም፡፡

እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ሮሜ 13፡8

መልሶ ማውገዝ

ያወገዘንን ሰው መልሶ ማውገዝ ተሳስቷል የምንለውን ነገር እኛው መድገም ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለት ስህተቶች አንድ ትክክል አያስገኙም፡፡ ትክክለኛ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መንገዱን ሳይጠብቅ ነው ያወገዘኝ ብለን የምንለውንም ሰው ትክክለኛ መንገዱን ሳንጠብቅ በስሜታዊነት ማውገዝ ስህተትን በስህተት ለማረም እንደ መሞከር ከንቱ ጥረት ነው፡፡

ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ ማቴዎስ 5፡38-39

እልኽ ውስጥ መግባት

እግዚአብሄር በህይወታችን የጠራን የተወሰነ ነገር እያለ ያንን ሃላፊነት ትተን የተቃውሞ መልስ ለመመለስ ጉልበታችንን ጊዜያችንን እውቀታችንምን ሁሉ ማባከን ስህተት ነው፡፡ ጥሪያችንን ትተን እልክ ውስጥ መግባት እግዚአብሄር የሰጠንን ተሰሚነት ፣ ፀጋና ፣ ጉልበትና ጊዜ አላስፈላጊ አታካራ ላይ ማዋል የህይወትና የአገልግሎት ብክነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠንን ሃላፊነት እርግፍ አድርገን ትተን ለተቃውሞ የመልስ እርምጃ መራመድ ብክነት ነው፡፡ የተሳተን ተቃውሞን የምናሸንፍበት አንዱ መንገድ ትክክለኛውንም ነገር በማድረግ በመቀጠል ባለማቋረጥ ነው፡፡

ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡2

መራገም

በተሳሳተም ይሁን በትክክለኛ መነሻ ሃሳብ እንዲሁም በትክክለኛው መፅሃፍ ቅዱሳዊው መንገድ ይሁን በሌላ መንገድ የተቃወመንን  ሰው ለመርገም አልተጠራንም፡፡ ሰውን ለመባረክ መልካምነቱን ለመፈለግ ለመልካምነቱ ለመስራት ብቻ ተጠርተናል፡፡ አጋጣሚውን ተጠቅመን የሚቃወመንን በእውነት በማመስገን በማክበር እድሉን ሌላውን ለማነፅ ልንጠቀምበት ይገባናል፡፡

ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡9

የተወገዝንበትን ነገር ይበልጥ ማጋነን

በተወገዝን ማግስት የተወገዝንበትን ነገር ይበልጥ ማፋፋም ማጋነን ትክክለኛው መንገድ አይደለም፡፡ ትምህርታችንና የህይወት መርሆዋችን ከሆነ ተቃውሞ ሲመጣ ካልለወጥነው እንኳን በዚያው ይቀጠላል እንጂ ይበልጥ ይበልጥ አይለጠጥም፡፡ ሌላው ፅንፍ የተሳሳተውን ሚዛናዊ አያደርገውም፡፡

በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ። ቲቶ 2:8

እራስን ከሰው ጋር አብሮ ማውገዝ

በተሳትነው ነገር ላይ ካልሆነ በስተቀር ስለተወገዝን በደፈናው ራስን ማውገዝ ሌላው ስህተት ነው፡፡ የተወገዝንበትን ነገር ራሱ መንፈስ ቅዱስ ሊመሰክርልን ይገባል እንጂ ሰዎች ስለፈረዱብን ብቻ ራሳችን ላይ መፍረድ ዋናው ስህተት ነው፡፡

ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ወይም በሌላ ሰው ዘንድ ብፈረድ ለእኔ ምንም አይደለም፤ እኔም በራሴ እንኳ አልፈርድም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡3

ተቃውሞን በአጠቃላይ እንደ ክፉ ማየት

ተቃውሞ በራሱ ክፉም መልካምም አይደለም፡፡ ለተቃዋሚው ክፉ የሚያደርገው በንፁህ የልብ መነሻ ሀሳብ ካላደረገው ወይም ትክክለኛውን መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርህ ሳይከተል በግብታዊነት ካደረገው ስህተት ይሆናል እንጂ ተቃውሞ በራሱ ስህተት አይደለም፡፡ ተወጋዡም ተቃውሞን እንከ እንቅፋትና እንደ ሰይጣን ስራ ካየው ከተቃውሞ ውስጥ ማውጣት ያለበትን ወሳኝ ጥቅም መጠቀም ያቅተዋል፡፡

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ኤፌሶን 5፡15-16

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28

ተቃውሞን ከሰው ጋር ማያያዝ

ተቃውሞ ሲደርስብን የተቃውሞውን ይዘት ከመመልከት ይልቅ አከሌ የተቃወመኝ እንደዚህ ስለሆነ ነው ብብሎ ምክኒያት መስጠትና ከሰው ጋረ ማያያዝ ከተቃውሞ የሚገባንን ጥቅም እንዳናገኝ ያደርገናል፡፡ ተቃውሞ ያጠራናል፡፡ ተቃውሞን በሚገባ ከያዝነው ትሁት ያደርገናል በዚያም የእግዚአብሄር ፀጋ እንዲበዛለን ያደርገናል፡፡

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5

እግዚአብሄር ቢፈቅድ በሚቀጥለው ፅሁፍ ትክክለኛው የውግዘትን መልሶች ሃሳብ ይዤላችሁ እቀርባለሁ፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አገልጋይ #ወገዛ #ስህተተ #ልብ #መሪ #ህሊና #ቀራጭ #ወገዛ #ትህትና #ፀጋ #ተቃውሞ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መነሻሃሳብ #ነቢይ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም

rock.jpgለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

በእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንኖረው በእግዚአብሄር ህግ በእግዚአብሄር ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር ህግ አንሰጠውም፡፡ እኛ በእርሱ ጥላ ስር እንገባለን እንጂ እርሱ በእኛ ጥላ ስር አይገባም፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡

በምድር ለይ ተቋቁመን ለመኖር የእግዚአብሄርን ሃሳብ ማግኘት አለብን፡፡ የምንከናወነው የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ስናገኝ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር እውነት ደግሞ ለራሱ ይቆማል፡፡ የእግዚአብሄርን እውነት ለማቆም የምንረዳው ምንም ነገር የለም፡፡

የመጨረሻው ማድረግ የምንችለው መልካምና የተሻለ ነገር በዚህ እውነት መተገን ነው፡፡ በዚህ እውነት የምንተገነው ለራሳችን ብለን ነው፡፡ ከእውነት ጋር የምንቆመው እውነትን ለመደገፍ ሳይሆን ለራሳችን ለመጠለል ብለን ነው፡፡

ከቃሉ እውነት ጋር የምንወግው እውነትን ደግፈን ለማቆም አይደለም፡፡ የቃሉ እውነት ደግፎ የሚያቆመው ማንንም ሰው አይፈልግም፡፡ በእውነት ላይ ተነስቶ የሚቋቋም ሰው የለም፡፡ በምድር ላይ ያለው ታላቁ ሰው እንኳን ለቃሉ እውነት እንጂ ከእውነት ተቃርኖ መዝለቅ አይችልም፡፡

የአዲስ ኪዳን አገልጋይ የነበረው ሃዋሪያው እንኳን በዚያ ሁሉ ክብሩ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ እንችልም ይላል፡፡ በእውነት ላይ ምንም ሊያደርግ የሚችል ሰው ከሰማይ በታች የለም፡፡

እጅግ ጠቢብ የሆነ ሰው ሊያደርግ የሚችለው ብልህ ነገር ለእውነት መቆም ነው፡፡ እጅግ የተሻለ ነገር የሚያደርገው ሰው ሊያደርግ የሚችለው በእውነት መጠለል ነው፡፡

ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እውነት #ቃል  #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት

የእውነት ጦር መሳሪያ

belt of truth.jpgሰይጣን ከመጀመሪያ ጀምሮ የሰው ልጆችን የሚያጠቃው በውሸት ነው፡፡ ሰይጣን ወደሄዋን መጥቶ ያታለላት እግዚአብሄር ከበላችሁ ትሞታላችሁ ያለውን አትሞቱም ብሎ በመዋሸት ነበር፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

የሰይጣን መስረቂያ ማረጃና ማጥፊያ መሳሪያው ውሸትን እንድንቀበልና ግራ እንድንጋባ ማድረግ ነው፡፡

ሰይጣን ህይወታችንን እንዳይበዘብዘው እውነትምን መፈለግ ፣ እውነትን ማሰብ ፣ እውነትን መናገርና እውነትን መኖር ይገባናል፡፡

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡32

ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ አሸንፎታል፡፡ ኢየሱስ ሰይጣንን ያሸነፈው ለእኛ ነው፡፡ እውነት በሰይጣን ላይ ያለንን ድል የምናፀናበት መንገድ ነው፡፡ በእውነት ወገባችንን መታጠቅ በሰይጣንን ላይ ያለንን ድል የምናስከብርበት መንገድ ነው፡፡ እውነት በሰይጣን ላይ ውጤታማ የጦር መሳሪያ ነው፡፡ እውነትን ስናስበው ስንናገረውና ስናርገው ሰይጣን በህይወታችንና በሚሰሙን ህይወት ስልጣኑን ያጣል፡፡

እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ ኤፌሶን 6፡14-15

እውነት የሌለው ሰው ራሱን መግዛት አይችልም፡፡ እውነት የሌለው ሰው ቆፍጠን ማለት አይችልም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት የሌለው ሰው በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል፡፡ ማቴዎስ 13፡21

እውነትን የሚያውቅ ሰው በህይወቱ ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም መብዛት ይሁን መጉደል አያግደውም፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡11-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እውነትን ተነጋገሩ

truth1.jpgእውነትን ላለመናገር ብዙ ጊዜ እንፈተናለን፡፡ በአለም ያለዑ ብዙ ነገሮች እውነቱን እንዳንናገር ያስፈራሩናል፡፡ ነገር ግን እውነትን መናገር የምንፈራበት ዋናውን ምክኒያት ብንረዳ እውነትን በመናገር ነፃ እንወጣለን፡፡

ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ኤፌሶን ሰዎች 4፡25

ሰው በውሸት ይታሰራል እንጂ ነፃ አይወጣም፡፡

የተሰራነውና ዲዛይን የተደረግነው ለእውነት ስለሆነ ውሸትን በተናገርን ቁጥር ህይወታችን እየተወሳሰበ ይሄዳል፡፡ ለውሸት ስላልተሰራንና ካለ ተፈጥሮአችን ስለምንዋሽ የተናገርነውን ውሸት ደግሞ ለመሸፈን በመጨነቅ ሌላ ውሸት መጨመር ግዴታ ነው፡፡

ውሸት ደግሞ በእኛ ውስጥ ስለሌለ ውሸቱን ለመሸፈን ቀላል አይደለም እጅግ ጭንቅ ነው፡፡ ውሸትን ባበዛን መጠን ደግሞ እስራታችን እየጠበቀ ይሄዳል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ፀጋ እውነትን ለመኖር ስለሆነ በዋሸን ቁጥር በራሳችን ወጭ ነው የምንዋሸው፡፡

ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡ ዮሃንስ 1፡14

ውሸትን በተናገርን ቁጥር በእኛ ዘንድ ያለው እውነተኛ መረጃ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በትክክል የመወሰን እድል እናጨልማለን፡፡ እውነትን ብብነግራቸው ይወስዱት የነበረወን እርምጃ እንዳይወስዱ እናሰናክላቸዋለን፡፡

ለምሳሌ ቀጠሮ ተቀጣጥረን ስንት ሰአት ላይ ትደርሳለህ ተብለን ስንጠየቅ አንድ ሰአት እንምደሚፈጅብን እያወቅን 30 ደቂቃ እንላለን፡፡ በእኛ ጋር ያለውን እውነተኛ መረጃ ባለ መናገራችን ያ ሰው ሰላሳ ደቂቃውን ለማሳለፍ እንዳይወስን እናደርገዋለን፡፡ ባልነው ጊዜ እንደማንመጣ እያወቅን እውነቱን ስላልነገርነው ብቻ እኛን በመጠበቅ ጊዜውን እንዲያባክነው እንፈርድበታለን፡፡

በፍቅር እንያዘው እንጂ እውነትን መናገር ለእኛም ለሚሰሙንም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤ ኤፌሶን 4፡15

ስለሚመስለንና በከንቱ ስለምንጓጓ እንጂ እውነት የማንናገርለት ነገር የእኛ አይደለም፡፡ ዋሽተን የምናገኘውን ነገር የእግዚአብሄር በረከት ብለን መጥራት እንችልም፡፡ ዋሽተን በምናገኘው ነገር ላይ ከእግዚአብሄር ዘንድ ድፍረት አይኖረንም፡፡

ውሸት ከሰይጣን ማስፈራሪያ ይመነጫል፡፡ የሚዋሽ ሰው ሰውን የሚፈራ ሰው ነው፡፡

ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል። ምሳሌ 29፡25

ውሸት የሰይጣን ባህሪ ነው፡፡ በመዋሸታችን ሰይጣን ይከብራል፡፡

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44

ስጋችንን በመጎሸም ከጥቂት ጀምረን እውነትን መናገር መማር አለብን፡፡ እውነትን ለመናገር ራሳችንን ማስለመድ አለብን፡፡

ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7

ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ኤፌሶን 4፡25

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: