Category Archives: satan

ራስን መግዛት በሰይጣን ላይ በርን ይዘጋል

door.jpgሰይጣን የህይወት ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው እንጂ ስለሌላ አይመጣም፡፡ ሰይጣነ ስራው መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰይጣን ከዚህ ውጭ ስራ የለውም፡፡ ሰይጣን ተልእኮዬን ከግብ አደረስኩ የሚለው ሰዎች ሲሰረቁ ፣ ሲታረዱና ሲጠፉ ነው፡፡

ሰይጣን ደግሞ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ይሰራል፡፡

የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። ሉቃስ 8:12

ኢየሱስ የዚህ አለም ገዢ ይመጣል ከእኔ አንዳች የለውም ብሎዋል፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤ ዮሃንስ 14፡30

ኢየሱስ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ የተራበ የዚህ አለም ገዢ እየመጣ ከእኔ አንዳች የለውም ሊል እንዴት ቻለ?

እኛስ የዚህ አለም ገዢ እየመጣ በእኛ ላይ አንዳች እንዳይኖረው ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ሰይጣን በመስቀል ላይ በኢየሱስ ድል ስለተነሳ ተሸንፎዋል፡፡ ሰይጣን በግድ አስገድዶ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡

አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15

ነገር ግን ሰይጣን ሰውን የሚሰርቀው የሚያርደውና የሚያጠፋው በሰው ባህሪ ድክመት ተጠቅሞ ነው፡፡ ሰውጣን ሰውን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋቱ በፊት ደካማ ባህሪውን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን በሰው ውስጥ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነ ባህሪ ካላገኘ ሰውን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ አይቻለውም፡፡ ሰውን ለመስረቅ ሰይጣን በመጀመሪያ በሰው ውስጥ ጥላቻን ይፈልጋል፡፡ ሰውን ለማረድ ሰይጣን ቁጣን በሰው ውስጥ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ሰውን ለማጥፋት መጀመሪያ ትእቢትን በሰው ውስጥ ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን እነዚህን ባሪያት በውስጣችን ካላገኘ ይመጣል ግን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ሰይጣን እነዚህን እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆኑ ባህሪያት ካገኘ ህይወታችን ለመስረቅ ለማረድና ለማጥፋት ይመቸዋል፡፡

በፍቅር በሚኖር ሰው ለመጠቀም ሰይጣን አይችልም፡፡ በምህረት የሚኖረውን ሰው ለማረድ ሰይጣን አይችልም፡፡ ትሁት የሆነን ሰው ህይወት ለማጥፋት ሰይጣን አይችልም፡፡

ስለዚህ ሰይጣንን በተዘዋዋሪ መንገድ ከህይወታችን ለመከላከልና ለሰይጣን በህይወታችን ውስጥ ስፍራ ለማሳጣት ባህሪያችንን መከታታል ይኖርብናል፡፡ በህይወታችን በሰይጣን ጥቃት ላይ በር ለመግዛት በእግዚአብሄር ቃል እግዚአብሄር መምሰል መልካም ባህሪያችንን መገንባት ይኖርብናል፡፡

ሰይጣን የሚወደውና የሚጠቀምበትን ባህሪ ከህይወታችን ካስወገድን የዚህ አለም ገዢ ይመጣል ከእኔ ግን አንዳች የለውም ማለት እንችላል፡፡

ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡26-27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

ከእናንተም ይሸሻል

flee.jpgዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7

መፅሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ እንደሌለ አድርጋችሁ ኑሩ ብሎ አይመክረንም፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ በራሱ እንዲሄድ ተስፋ አድርጉ አይለንም፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ስሙን አታነሱት እርሱም ይተዋችኋል አላለንም፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ስለ ዲያቢሎስ ወደ እግዚአብሄር ፀልዩ አላለንም፡፡

ስለዲያቢሎስ ወደእግዚአብሄር መፀለይ ሙሴ ባህሪን መክፈያውን በትር በእጁ ይዞ ወደ እግዚአብሄር እንደጮኽው አይነት የተሳሳት ጩኸት ነው፡፡

ሰው በእግዚአብሄ ክብር ተፈጥሮዋል፡፡ ሰው በስልጣን እንዲገዛ ተፈጥሮዋል፡፡

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍጥረት 2፡27-28

ሰው አታድርግ የተባለውን ያንኑ ነገር በማድረጉና እግዚአብሄር ላይ በማመፁ የተነሳ የነበረውን መንፈሳዊ ስልጣን ለሰይጣን አስረክቦ ነበር፡፡

ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ከሰው ስልጣኑን በመውሰድ የዚህ አለም ገዢ የነበረውን ሰይጣንን ስልጣን ለመሻር ነው፡፡

እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ ዕብራውያን 2፡14-15

ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የሰይጣንን ስልጣንን ገፎታል፡፡

አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15

እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሉቃስ 10፡19

ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ተልእኮ በፍፁም የለው፡፡ ሰይጣን የሰውን ህይወት ሊሰርቅ ሊታርድ ሊያጠፋ ይመጣል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን የማይቃወመው ሰው ካገኘ ህይወቱን ይሰርቃል ያርዳል ያጠፋል፡፡ ሰይጣን ሲመጣ ስልጣኑን የሚያውቅ የሚነግረው ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ስልጣኑን ተረድቶ የሚቃወመው ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ከህይወታችን እና የእኛ ከሆኑት ነገሮች ለመሸሽ ትእዛዛችንን ይጠብቃል፡፡

ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #እባቡ #ጊንጥ #ሥልጣን #ተቃወሙ #ይሸሻል #ገፎ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም

snake.jpgመጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ኤፌሶን 6፡12

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡3-5

ከምናስበው በላይ ብዙ ነገሮች መንፈሳዊ ናቸው፡፡ የሰይጣን መንፈሳዊ አለም በክፋት ይሰራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ጠላት ዲያቢሎስ አያርፍም ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ዙሪያችንን ይዞራል፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

ሰይጣን እኛን ለማጥቃት ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ ጴጥሮስን ተጠቅሞ በሰው ሃሳብ ሊያጠቃው የመጣውን ዲያቢሎስ ኢየሱስ ለይቶ አወቀው፡፡ ኢየሱስ በጊዜው ጠላት ከተጠቀመበት ከጴጥሮስ ላይ አይኑን እንስቶ የዚህ የክፉ ሃሳብ ምንጩን ዲያቢሎስ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን፡፡

ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። ማቴዎስ 16፡22-23

ብዙ ጊዜ ግን አይናችንን ከጠላታችን ዲቢሎስ ላይ አንስተን እርሱ ለጥፋት በሚጠቀምባቸው ሰዎች ላይ ለማድረግ እንፈተናለን፡፡

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8-9

እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የሰው ጠላት የለንም፡፡ ጠላታችን አንዱ ዲያቢሎስ ነው፡፡ እውነት ነው ሰይጣን የሰዎችን አእምሮ ተጠቅሞ እነርሱንም እኛንም ለመስረቅ ለማረድና ለማጥፋት ይመጣል፡፡

ስለዚህ የእኛ መጋደል ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም፡፡ ከደምና ከስጋ ጋር የምንጋደል ከሆንን በተሳሳተ ገድል ህይወታችንን እያባከንን ነው፡፡ መጋደላችን ከሰው ጋር በፍፁም አይደለም፡፡

መጋደላችን ከክፉ መንፈሳዊ አለም መናፍስት ጋር ነው፡፡ ሰው በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ ክፉን ሃሳብ በሰው ውስጥ ልከው ሰው ክፉ እንዲያደርግ የሚያደርጉት የክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ናቸው፡፡

የሰዎችን ቅንነት የሚያበላሸውን ሰዎች ውስጥ ክፋት የሚጨምረውን ክፋትን የሚያባብሰውን ክፉን በጌታ በኢየሱስ ስም ልንቃወም ይገባናል፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

ሰዎች አንድ ነገር ሲደርስባቸው እከሌ ነው ብለው ይደመድማሉ ከዚያም መጋደላቸው ከእከሌ ጋር ይሆናል፡፡ ሰዎች ስጋ ለባሽን እንጂ ከዚያ አልፈው ስጋ ለባሽን ለክፋት የሚያነሳሳውን ካላዩ እውነተኛ ጠላታቸውን አያውቁም፡፡ ሰዎች ከሰው አልፈው የክፋቱን ምንጭ ክፉ መንፈሳዊ አለምን ካላዩ ኢላማቸውን ይስታሉ፡፡ ሰዎች ግን የክፋትን ምንጭ መንፈሳዊ አለምን ከለዩና ትኩረታቸውን ከስጋ ለባሽ ላይ እንስተው ወደ መንፈሳዊ አለም ካዞሩ ችግሩን ከስሩ በማድረቅ ውጤታማ ይሆናሉ፡፡

አይናችንን ከሰዎች ላይ አንስተን የሚታለሉትን ሰዎች የሚጠቀመውንና ፈቃዱን የሚያስደርጋቸውን ከተቃወምን በሰዎችም ህይወትና በእኛም ህይወት የጠላትን ስራ ማፍረስ እንችላለን፡፡

በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #የጦርመሳሪያ #ምሽግ #አእምሮ #ሃሳብ #ማታለል #ብርቱ #ተቃወሙት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የአስተሳሰብ ንፅህና

mind descipiline.jpgሰይጣን የሰው ልጅ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ከማረድ እና ከማጥፋት ውጭ ሌላ ተልእኮ የለውም፡፡

ሰይጣን በማይታዘዙት ልጆች ላይ የጥፋት አላማውን ይሰራል፡፡

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡1-2

እኛ ግን ከጨለማው ስልጣን ስለዳንንና ወደፍቅሩ ልጅ መንግስት ስለፈለስን በእኛ ላይ ስልጣን የለውም፡፡

እኛን የሚዋጋን በሃሳብ ነው፡፡ ሰይጣን ክፉ ሃሳብን ወደ አእምሮዋችን ይልካል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነውን ሃሳቡን ከተቀበልነው አላማውን ያስፈፅምብናል፡፡ ካልተቀበልነው ግን ሃሳቡና አላማው በውስጣችን ይሞታል፡፡

ሰው ሃሳቡ ከተበላሸ ህይወቱ ይበላሻል፡፡ ሰው በሃሳቡ የሃጢያትን ሃሳብ ካስተናገደ ሰው በህይወቱ የሃጢያትን ህይወት ያደርገዋል፡፡ ሰው ሃሳቡን ከሃጢያት ከጠበቀ ህይወቱን በንፅህና ይጨብቃል፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

ሰው በአስተሳሰብ ህይወቱ እግዚአብሄርን ከፈራ ከሃጢያት የነፃ ህይወት ይኖረዋል፡፡ ሰው አያየኝም ብሎ የሃጢያትን ሃሳብ የሚያስተናግድ ሰው ሃጢያትን ሲያደርገው ይገኛል፡፡

ሰው አስተሳሰቡ ቅጥ ያጣ መሆን የለበትም፡፡ ሰው አስተሳሰቡ ስርአት ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ህይወታችንን በንፅህና ለመጠበቅ ማሰብ የሚገባን ነገሮች አሉ ማሰብ የማይገባን ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡ ወደ አእምሮዋችን የመጣውን ሃሳብ ሁሉ አናስብም፡፡ በአእምሮዋችን ውስጥ እንዲቆይ የምንፈቅድለት ሃሳብ አለ፡፡ ከአእምሮዋችን በፍጥነት አሽቀንጥረን የምንጥለው ሃሳብ አለ፡፡

በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8

አእምሮዋችንን ከክፉ ሃሳብ ወረራ ከጠበቅን ህይወታችንን ከሰይጣን ጥቃት እንጠብቃለን፡፡

የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡5

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #ንፅህና #ምኞት #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አንደኛው የሰይጣን የጥቃት ደረጃ

brazil-brasil-rainforest-627903-h (1).jpgየሰይጣን አላማ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ከመጣ ከእነዚህ አላማዎች ውጭ ስለሌለ ስለምንም አላማ አይመጣም፡፡  ሰይጣን ሃሳቡን የሚያስፈፅምለት ሰው ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን ይህንን የሚያደርገው ደረጃ በደረጃ ነው፡፡

ሰይጣን አላማውን በሰዎች ተጠቅሞ ያስፈፅማል፡፡ ሰይጣን ሰዎችን በዋነኝነት የሚያጠቃውና የመስረቅ የማረድና የማጥፋት አላማውን በእነርሱም ይሁን በሌላ ሰው ህይወት ላይ የሚያሳካው በሃሳብ ነው፡፡ ሰይጣን የሰዎችን ህይወት ለመስረቅ በስፋት የሚጠቀመው ሃሳብን በመላክ ነው፡፡ ሰይጣን ወደ አእምሮዋችን እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነን ሃሳብ በመላክ ህይወታችንን ሊሰርቅ ይችላል፡፡ ሰይጣን ክፉና ሃሳብን ወደሰዎች አእምሮ በመላክ ብቻ የአላማው ማስፈፀሚያ ያደርጋቸዋል፡፡

ሰይጣን በክርስቶስ የመስቀል ስራ ሙሉ ለሙሉ የተሸነፈ ስለሆነ በተለይ እኛ ኢየሱስን የምንከተል የሚዋጋበት ዋነኛው መንገድ ክፉ ሃሳብን ወደ አእምሮዋችን በመላክ ነው፡፡

ሰይጣን ሃሳብን ልኮ አእምሮዋችንን ካበላሸ መንገዳችንን ያበላሻል፡፡ ህይወታችን የምንጠብቀው ሃሳባችንን በመጠበቅ ነው፡፡ ሃሳቡን መጠበቅ የቻለ ሰው ህይወቱን ጠብቋል፡፡

በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡2-3

ሰውን የሚያረክሰው ከመንገዱ የሚያሰናክለው ክፉ ሃሳብ ነው፡፡ ሰው በልቡ የሰይጣንን ሃሳብ ካስተናገደ ክፋት ሁሉ የሚወጣው ከልብ ሃሳብ ነው፡፡ ሰይጣን በልባችን ላይ ክፉ ሃሳብ ማስቀመጥ ካልቻለ ክፋትን ሊያሰራን አይችልም፡፡

ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ማቴዎስ 15፡18-19

አእምሮዋችን ከዳነ እኛ እንድናለን፡፡ አእምሮዋችን ካልዳነ ሰይጣን በህይወታችን እድል ፈንታን ያገኛል፡፡ አእምሮዋችን የሚድነውና ከሰይጣን ጥቃት የሚጠበቀው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። ያዕቆብ 1፡21

ልባችንን ከጠበቅን ህወታችንን እንጠብቃለን፡፡ ልባችን ለሰይጣን ጥቃት ከተጋለጠ ህይወታቸን ለሰይጣን ጥቃት ይጋለጣል በዚያም ሰይጣን አለላማውን መስረቅ ማረድና ማጥፋት በህይወታችን እንዲፈፅም እንፈቅድለታለን፡፡  ልባችንን በትጋት በእግዚአብሄ ቃል ካልጠበቅን ህይወታችን ለአደጋ ይጋለጣል፡፡

አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 4፡23

በእግዚአብሄር ቃል ላይ መደገፍ የሚያስፈልገን ሰይጣን ህይወታችንን እንዳያጠፋ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ላይ እምነት የሚያስፈልገን በህይወታችን ላይ የሚላኩትን የሚንበለበሉትን የጠላት ጥቃቶች ለመቋቋም ነው፡፡

በሰው ህይወት ላይ ሰይጣን መግባትን የሚያገኘው በሃሳቡ ከተታለለ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን ያላታለለው ሰው ህይወት ውስጥ የመግባትና የማጥፋት መንገድ አያገኝም፡፡

የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ ኤፌሶን 6፡11፣16

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#አተረፈ #ንፅህና #ሃሳብ #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ስብከት #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሰይጣን ብቸኛው መሳሪያ

Masking-Pain.jpgየዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌሶን 6፡11

የጠላት የዲያብሎስ አላማ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ዲያቢሎስ የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ ድል ነስቷል፡፡

አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15

ሰይጣን የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን ማንንም በግድ ጎትቶ ሃጢያት ሊያሰራ አይችልም፡፡ ሰይጣን እንደታሰረ ውሻ ነው፡፡ የታሰረ ውሻ እንደሚጮህና እንደሚረብሽ ሁሉ ሰይጣንም መሳሪያው ጩኸት ፣ ማስፈራራትና ማታለል ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን የጥርጥርን ሃሳብ ወደ አእምሮዋችን ልኮ ከተቀበልነው ከእምነት መንገድ እንስታለን፡፡

ሰይጣን ሃሳብን ወደ አእምሮው ልኮ በሰይጣን ሽንገላ የተሸነፈ ሰው የሰይጣንን ማስፈራሪያ ፈርቶ ከመንገዱ ይመለሳል፡፡ በሰይጣን ሽንገላ የተታለለ ሰው በኑሮ ፍርሃት እግዚአብሄርን ከማገልገል ይመለሳል፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19

በሰይጣን የሃጢያት ሽንገላ የተታለለ ሰው ለእግዚአብሄር በቅድስና መኖር አይቻልም ብሎ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በሰይጣን ሽንገላ የተሸነፈ ሰው አለምን ማሸነፍ አይቻልም ብሎ ለአለም አሰራር እጅ ይሰጣል፡፡

ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16

ሰይጣን ስልጣኑ ስለተገፈፈ ብቸኛው መሳሪያው ማታለል ነው፡፡ ሰይጣን ካታለለን ክፋት ያሰራናል፡፡ ሽንገላውን ከተቃወምን እግዘኢአብሄርን አገልግለን እናልፋለን፡፡

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ከማታለሉ እንድንጠበቅ የሚመክረን፡፡ ከማታለሉ የምንጠበቀው የእግዚአብሄርን ቃል ስንረዳ ብቻ ነው፡፡ ከሰይጣን ማታለል የምንጠበቀው በእግዚአብሄር ጥበብ ብቻ ነው፡፡

የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ኤፌሶን 6፡11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: