Category Archives: Praise

ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።

conscious.jpgሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ። መዝሙር 105፡1-2

ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። መዝሙር 106፡1

ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርንም ስም አመስግኑ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን። መዝሙር 113፡1-3

ሃሌ ሉያ። አቤቱ፥ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ። መዝሙር 111፡1

ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት። አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፤ መዝሙር 33፡1-3

አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፤ እኛ ሕያዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔርን እንባርካለን፡፡ ሃሌ ሉያ። መዝሙር 115፡17-18

ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡4

እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት። ዕብራውያን 13፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

Advertisements

ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ

light-681199_960_720.jpgበመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-15

በምድር ላይ ያለነው ለአለም ብርሃን ለመሆን ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ስለእግዚአብሄርን በጎነት ለመመስከር ነው፡፡

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9

ሰዎች የምናስበውን የምንናገረውንና የምናደርገውን ነገር በቅርበት ይከታተላሉ፡፡ በምንናገረውና በምናደርግው ነገር ለእግዚአብሄር መንግስት ጥሩ ወይም መጥፎ ምስክር ልንሆን እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች ቤተክርስትያንን እንዲያምኑ ወይም እንዲጠራጠሩ ልናደርግ እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች አገልጋዮችንና መሪዎችን እንዲሰሙ ወይም እንዳይሰሙ ማድረግ እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንዲመጡ ወይም እንዳይመጡ ልናደርግ እንችላለን፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው ሰይጣን ስራ እንጂ ስለ እግዚአብሄር መልካምነት ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ጨለማ እንጂ ስለእግዚአብሄር ብርሃን ምስክር ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ሃይልነት እንጂ ስለእግዚአብሄር ሃያልነት አይናገርም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ተንኮል እንጂ ስለሚበልጠው ስለእግዚአብሄር ጥበብ ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሃጢያት ብርታት እንጂ ስለእግዚአብሄር ፀጋ ብርታት ሊመሰክር አይችልም፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው ጥያቄ ያለበት እንጂ ጥያቄው የተመለሰለት ሰው አይደለም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ኢየሱስ ጥያቄን ይመልሳል ብሎ የሚመሰከር ህይወትም አንደበትም የለውም፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው ሌላውን ሰው ወደ እግዚአብሄር መንግስት አያበረታታም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ሌላው ወደእግዚአብሄር መንግስት እንዳይመጣ እንቅፋት ይሆናል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ሌላው እግዚአብሄርን እንዲያገለግል አያበረታታም፡፡ የሚያንጎራር ሰው ሌላው ለእግዚአብሄር እንዳይሰጥ ያዳክማል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን በጎ ህሊና ያበላሻል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን እምነት ይሰርቃል፡፡ የሚያምጎራጉስር ሰው የሰዎችን ልብ ያወርዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን ተስፋ ያጨልማል፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው የተሸነፈ ሰው ነው፡፡ የተሸነፈን ሰው ለመከተል የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የአሸናፊነት መንገድ የጠፋበት ሰው ነው፡፡ የአሸናፊን መንግስት እንጂ ተሸናፊን መንግስት ውስጥ መግባት የሚፈልግ ሰው እንደሌለ ሁሉ የሚያንጎራጉር ሰው ለእግዚአብሄር መንግስት ምስክር መሆን አይችልም፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው ምህረትን እንድናደርግና ቻይ እንድንሆንና ቸር እንድንሆን የሚያስተምረውን የኢየሱስን ትምህርት ይቃወማል፡፡

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡39-41

የሚያንጎራጉር ሰው ስለራሱ ድካም እንጂ ስለሚሸንፈነው የእግዚአብሄር ፀጋ ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን ፀጋ በሚያበዛለት በድካሙ የማይመካ ሰው ነው፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9

በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-15

በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #አታንጎራጉሩ #አታጉረምርሙ #ብርሃን #ምስክር #ጠማማ #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ

kingdome.jpgከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10

የእስራኤል ህዝብ በእግዚአብሄር መሪነት ደስተኛ አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄር እንደዚህ አድርጎ ሊይዘን አይገባም ነበር የሚል ጥያቄ ነበራቸው፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄር ከዚህ በላይ ሊያደርግልን ይገባል የሚል ቅሬታ ነበራቸው፡፡ የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄ ጠላቶቻችንን እንደዚህ ነበር ማድረግ የነበረበት የሚል የተለየ ሃሳብ አላቸው፡፡ የእስራኤልክ ህዝብ እግዚአብሄር እንደሚገባን አልተንከባከበንም የሚል ጥያቄ ነበራቸው፡፡ ሰው የሚያንጎራጉረው በመሪው ላይ ጥያቄ ሲኖረው ነው፡፡

ሰው በሚስቴ በባሌ ደስተኛ እይደለሁም ሲል አልገረምም፡፡ ሰው በፍፁሙ በእግዚአብሄር መሪነት ላይ ጥያቄ ካለው ሚስት በባልዋ መሪነት ላይ ጥያቄ ባይኖራት ይገርማል እንጂ የማይገባት ነገር ስላለ አያስገርምም፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መሪነት ላይ አቃቂር የሚያወጣ ሰው በሰው መሪነት ላይ አቃቂር ቢያወጣ አያስገርምም፡፡ ሁላችንም በምናውቃቸው ሰዎች መሪነት ላይ አቃቂር ማውጣት እንችላለን፡፡

የሚያንጎራጉር ሰው በህይወቱ ለሰይጣን በር እየከፈተ ይሄዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን መንፈስ እያሳዘነ ይሄዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው እደከመ መቋቋም እያቃተው ይሄዳል፡፡ ስለዚህጅ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ አታንጎራጉሩ የሚለው፡፡

ማንጎራጎር ተስፋ መቁረጥ ነው

ማንጎራጎር ተስፋን አለማየት ነው፡፡ ማንጎራጎር ጨለማ ነው፡፡ ማንጎራጎር ተስፋ ቢስነት ነው፡፡

እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ። መዝሙር 71፡14

ማንጎራጎር እግዚአብሄር እውነተኛ ዳኛ መሆኑን መርሳት ነው

ማንጎራጎር እግዚአብሄር በወቅቱ እንደማየፈርድ መጠራጠር ነው፡፡ ማንጎራጎር አግዚአብሄር ለመፍረድ የሆነ ነገር እንደጎደለው ማሰብ ነው፡፡

ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? ያዕቆብ 4፡12

ማንጎራጎር እግዚአብሄርን አለማመስገን ነው

የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄር ምስጋና ያነሰበት ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን መልካምነት ያልተረዳ ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን አሰራር የማያውቅ ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን እርምጃ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡

በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡17-18

ማንጎራጎር በእግዚአብሄር ደስ አለመሰኘት ነው

በእግዚአብሄር ደስ የተሰኘ ሰው ጥያቄውን ዋጥ ያደርገዋል እንጂ ለማንጎራጎር አፉን ለመክፈት አይደፍርም፡፡

ማንጎራጎር በሰው ቁጣ የእግዚአብሄርን ፅድቅ የመስራት ከንቱ ሙከራ ነው፡፡

ማንጎራጎር በእግዚአብሄር መታመን አይደለም፡፡ ማንጎራጎር በራስ ችሎታ መታመን ነው፡፡ ማንጎራጎር የስጋ ክንፍ ነው፡፡

ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። ያእቆብ 1፡19-20

ማንጎራጎር የእግዚአብሄርን መሪነት ጥያቄ ውስጥ መክተት ነው

ምድርን እና ሞላዋን ለራሱ ክብር የፈጠረና እያስተዳደር ያለ ባለቤት እያለ የሚያንጎራጉር ሰው እግዚአብሄር መምራት በትክክል አልቻለም እያለ ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው መሪነቱን ከእግዚአብሄር ተቀብሎ በተሻለ ለማምራት እየተፈተነ ነው፡፡

ማንጎራጎር ባለን ነገር ላይ ሳይሆን በጎደለን ነገር ላይ ማተኮር ነው

እግዚአብሄር በህይወታችን ያደረጋቸው ከቁጥር የበዙ ታእምራቶች እያሉ አልሆነልኝም በምንለው ነገር ላይ ማተኮር ማጉረምረምን ያመጣል፡፡

የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል። ኢዮብ 9፡10

ማንጎራጎር እኔ አውቃለሁ ባይነት ነው

የሚያንጎራጉር ሰው ከእርግዚአብሄር በላይ እንደሚያውቅ የተሰማው ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው እግዚአብሄርን ሊመክርው የሚዳዳው ሰው ነው፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው በእግዚአብሄር ያልተረዳውነ አንድ ነገር ያገኘ የመሰለው ሰው ነው፡፡

ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡2

በፊቱ ሙግቴን አዘጋጅ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር። የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደ ሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር። ኢዮብ 23፡4-5

ማንጎራጎር ትእቢት ነው

ማንጎራጎር ሰው ከሚገባው በላይ በትእቢት ማሰብ ነው፡፡

ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡1

ማንጎራጎር እግዚአብሄርን አለመፍራት ነው፡፡

እግዚአብሄርን በትክክል የማያውቀው ሰው ይዳፈረዋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚዳፈር ሰው ለማንጎራጎር ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ላለማንጎራጎር የሚጠይቀውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው። ሰቆቃው ኤርምያስ  3፥29

ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።  ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥26

ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡27-28

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #አታንጎራጉሩ #አታጉረምርሙ #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

በሰማያት ላይ ለረድኤትህ እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም

cloudy_sky_over_mountains-t2 (1).jpgይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26

የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ የሚረዳን እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከመርዳት ውጭ ሌላ ስራ የለውም፡፡ የእግዚአብሄር ስራ እኛን መርዳት ነው፡፡

እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር በሰማይ ያለው በታላቅነት ነው፡፡ እግዚአብሄር በታላቅነት በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡

እግዚአብሄር ከፍ ያለ ቦታ ያለው ሁሉን ሊያይና ሊረዳን ነው፡፡

የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ። መዝሙር 53፡2

ስለዚህ ነው የእግዚአብሄርን እርዳታ ያየው መዝሙረኛው ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲህ እያለ የሚያመሰግነው፡፡

ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና። መዝሙር 63፡7

እግዚአብሄር አምላኩ የሆነለት ህዝብ ምስጉን ነው፡፡

የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤ መዝሙር 146፡5

ህዝቡን እንደሚረዳና እንደሚደግፍ እንደ እግዚአብሄር ያለ ማንም የለም፡፡ እንደ እኛ የታደለ ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ደስ ሊለው የሚገባው ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ሳያቋርጥ እግዚአብሄርን ማመስገን የሚገባው ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ሊረዳ ነው፡፡

ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #እርዳታ #ታላቅነት #ቃል #መልካም #መታመን #መደገፍ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ረድኤት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መዝሙር 136፡1-26

army.jpg1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

4 እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

5 ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

6 ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

7 ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

8 ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

9 ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

10 ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

12 በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

18 ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

22 ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

24 ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና

25 ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

መዝሙር 136፡1-26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

“No complaint” isn’t enough

cropped-concert_hands_in_the_air-wallpaper-2560x1440.jpgWhen people are asked about life they sometimes say “no complaint”. What they mean is that they don’t want to complain about God or thank Him either. Actually, they are tempted not to thank Him. They are tempted to complain.

All of us are tempted to complain. All of us are tempted not to thank Him either.

And it is clear that it is good not to complain. Complain is bad. Complain is criticizing Gods dealing in our lives. Complaint isn’t acceptable at all.

And do not grumble, as some of them did–and were killed by the destroying angel. 1 Corinthians 10:10

But not complaining isn’t enough. Being passive isn’t enough. It takes to praise God. Praising God is the will of God towards us.

give thanks in all circumstances; for this is God’s will for you in Christ Jesus. 1 Thessalonians 5:18

We have to humble ourselves not only to complain but also to thank God in everything.

Don’t just keep quite. Praise Him. Even if you are tempted not to praise him, defeat the Devil by praising him.

Not only we are commanded not to complain, we are also commanded to praise Him.

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#complain #praise #persecution #blessed #temptation #trial #tribulation #faith #church #perseverance #preaching #salvation #bible #countingthecost #test #facebook #abiywakuma #abiywakumadinsa

እግዚአብሄርን የሚያከብር ምስጋና

praise god.jpgምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡23

እግዚአብሄርን ማመስገን የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

የዋህነት የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

ብልጣብልጥ ሰው እግዚአብሄርን ሊያመሰግን አይችልም፡፡ ብልጣብልጥ ሰው ነገሮች የሚሆኑለት በብልጠቱ ይመስለዋል፡፡ በአራድነት መኖር የሚፈልግ ሰው የራሱን ቅልጥፍና እንጂ እግዚአብሄርን ሊያመሰግን አይችልም፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

ትህትና የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

ትእቢተኛ የሆነ ሰው ከእግዚአብሄር በላይ ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ሰው እግዚአብሄርን አያመሰግንም፡፡ ትሁት ሰው የማላውቅው ነገር አለ እግዚአብሄር ሁሉን ያውቃል ለሚል ሰው እግዚአብሄርን ለማመስገን ይቀለዋል፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?  ሚክያስ 6፡8

እምነት የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

በማየት የማይመላለስ ሰው ነገሩ ከመሆኑ በፊት እግዚአብሄርን ያመሰግናል፡፡ በዝቅታ ውስጥ እግዚአብሄርን ለማመስገን ከፍታን ማየት ይጠይቃል፡፡ በተቀራኒ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሄርን ለማመስገን የሚታየውን አለማየት የማይታየውን ማየት ይጠይቃል፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

እግዚአብሄርን ሃይልና ጥበብ ማወቅ የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

እግዚአብሄርን የሚያውቅ ሰው በእግዚአብሄር ላይ አያጉረመርምም፡፡ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ሰው እግዚአብሄርን ሁል ጊዜ ያመሰግነዋል፡፡

ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡27-28

የእግዚአብሄርን መልካምነት ማወቅ የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡

እግዚአብሄርን የሚያውቅ ሰው እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ እንጂ ሌላ እውቀት ስለሌለው ነበገር ሁሉ እግዚአብሄርን ያመሰግናል፡፡

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

ምስጋና አልባ መሥዋዕት

praise.jpgሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ። ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፤ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን? ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡7-14፣23

የእስራኤል ህዝብ መሥዋዕት የማቅረብ ትርጉሙን አልተረዳውም ነበር፡፡ የእስራኤል ህዝብ መሥዋዕት የሚሰዋው እንደ ልምድ ነበር፡፡ የእስራኤል ህዝብ መሥዋዕት የሚሰዋው ግዴታው ስለነበረ ይመስላል፡፡

ለእግዚአብሄር ግን መሥዋዕት የበግና የፍየል ጉዳይ አይደለም፡፡ መሥዋዕት ማድረግ ማለት የከብት ሃብታችሁን ለእግዚአብሄር ማካፈል ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሃብታችሁን አይካፈልም፡፡ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእግዚአብሄር ነው፡፡ ምድርና  ሞላዋ የእግዚአብሄር ናት፡፡

ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት: ዓለምም በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ መዝሙር 24፡4.

መስዋእት ማድረግ ማለት እግዚአብሄር ተርቦ ለእግዚአብሄር በግ አርዶ ማብላት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር መስዋእት እንዲያደርጉ ያዘዘው ርቦትና ጠምቶት አይደለም፡፡ ስጋ የምበላ ደም የምጠጣ ከሆነ ቢርበኝ ለአንተም አልነግርህም ይላል እግዚአብሄር፡፡

ታዲያ እግዚአብሄር ምን ፈልጎ ነው መስዋእት አድርጉ ያለው ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡

እግዚአብሄር የፈለገው ምስጋናን ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገው በበጉና በፍየሉ ላይ ተጭኖ የሚመጣውን ምስጋና ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገው በጉንና ፍየሉን የሚያመጣውን ሰው የልብ ምስጋናን ማየት ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገው የመስዋእት አድራጊውን የልብ ምስጋና ነው፡፡

በጉበና ፍየሉ ምስጋናውን የሚሸከም ተሸካሚ እንጂ ስጦታ አይደለም፡፡ በጉና ፍየሉ የልብን ምስጋና የሚያሳይ መጠቅያ እቃ እንጂ ራሱ ስጦታ አይደለም፡፡ በጉና ፍየሉ ምስጋናውን ማሳያ መንገድ እንጂ በራሱ ምስጋና አይደለም፡፡

የእስራኤል ህዝብ መስዋእት ሊያደርጉ ሲሄዱ በመጀመሪያ ደረጃ በእግዚአብሄር ፊት ሊታዩ ነው የሚሄዱት፡፡ እግዚአብሄር የሰውን የህይወት ጤንነት የሚያየው በምስጋናው ነው፡፡

በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በእስራኤል አምላክ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት በዓመት ሦስት ጊዜ ይታይ። ዘጸአት 34፡23

ሰው ወደእግዚአብሄር ሲገባ ፕሮቶኮሉ ወይም ስርአቱ በምስጋና መሆን አለበት፡፡

ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡4

እግዚአብሄር መስዋእትን ሲቀበል መጀመሪያ የሚያየው መስዋእት አድራጊውን ነው፡፡

አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ ዘፍጥረት 4፡4

አሁንም እግዚአብሄርን በምናገለግላቸው መንገዶች ሁሉ አገልግሎታችንን ከማየቱ ጌታ ልባችንን ያያል፡፡ በልባችን ምስጋና ከሌለ የምናገለግለው ከምስጋና ተነስተን ካልሆነ ባዶ ሃይማኖታዊ ወግ እየፈፀምን እንጂ ጌታን እያገለገልን አይደለም፡፡

ስናገለግል ፣ ስንሰጥ ፣ ህብረት ስናደርግና ስንመሰክር ከምስጋና ልብ ማገልገል አለብን፡፡

ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡14፣23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ምስጋና #መዳን #እምነት #መሥዋዕት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ

የግንኙነት መለኪያ – ምስጋና

termo.jpgምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 50፡23

ምስጋና እግዚአብሄር ስለደረገልን መልካምነት ምላሽ ከመስጠት ያልፋል፡፡ ምስጋና ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን የግንኙነት ደረጃ ያሳያል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኘነት ጤንነት ማወቅ ከፈለግን ምስጋናችንን መለካት ይጠይቃል፡፡

ምስጋና የሚሰዋ እርሱ ያከብረኛል ይላል፡፡ ምስጋና እግዚአብሄርን ማክበራችን ያሳያል ማለት ነው፡፡ ምስጋና ለእግዚአብሄር የመጀመሪያውን ስፍራ መሰጠታችንን ያሳያል፡፡ ምስጋና የተፈጠርንለትን አላማ እየፈፀምንም መሆናችንን ያሳያል፡፡

ምስጋና ስለ ትህትናችን ይናገራል

ምስጋና የልባችንን ትህትና ይገልጣል፡፡ ትሁት የሆነ ሰው እግዚአብሄር ላይ ለማጉረምረም ምክኒያት አያገኝም፡፡ ትሁት የሆነ ሰው እግዚአብሄር ከእኔ በላይ ያውቃል ይላል፡፡ ትሁት ሰው እኔ የማላውቀው ነገር አለ ይላል፡፡ ትሁት ሰው እግዚአብሄር የሚሰጠው አያንስበትም ይበቃዋል፡፡ ትሁት ሰው እግዚአብሄር የሚሰጠው ጥቂት ነገርን እንኳን እንደሚገባው አይቆጥረውም፡፡  ትሁት ሰው እያንዳንዱን መልካምነት አቅልሎ አያየውም፡፡

አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡7

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ያዕቆብ 1፡16-17

ምስጋና እግዚአብሄርን ስለመፍራታችን ይናገራል

ምስጋና እግዚአብሄርን እንደምንፈራው ያሳያል፡፡ ምስጋና ለእግዚአብሄር ያለንን ፍርሃትና አክብሮት ያሳያል፡፡ ለእግዚአብሄር የተለየ ክብር ያለው ሰው በእግዚአብሄር ፊት ምስጋናን እንጂ ማጉረምረም ሊያወጣ አይችልም፡፡

ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15

ምስጋና በእምነት መኖራችነንን ያሳያል፡፡ ምስጋና የምንመላለሰው በማየት ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ያሳያል፡፡ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ ካመንን እግዚአብሄርን ለማመስገን እንችላል፡፡

ምስጋናችን በእግዚአብሄር ደስታ መርካታችንንና አለምን መናቃችንን ያሳያል

ሰው ሃጢያት የሚሰራው የእግዚአብሄር ደስታ ወይም እቅርቦት አልበቃ ብሎት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ደስ የተሰኘ ሰው ግን ሃጢያትን ይንቃል፡፡ ከሃጢያት መራቃችን በእግዚአብሄር መርካታችንንና የሚያመሰግን ልብ እንዳለን ያሳያል፡፡

አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን። ዕብራውያን 13፡5-6

ምስጋና እግዚአብሄርን ማወቃችንን ያሳያል

ምስጋና የእግዚአብሄን አሰራር መረዳታችንን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር ያልተረዳ ሰው ሁል ጊዜ ጥያቄ አለው ሁል ጊዜ ያጉረመርማል፡፡ ምስጋና የሚሰጥ ሰው ግን የእግዚአብሄርን አሰራር የተረዳ ሰው ነው፡፡

በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡18

ምስጋና በእግዚአብሄር ላይ መደገፋችንን ይመሰክራል

ምስጋና በማናውቅው ነገር እንኳን በእግዚአብሄር ላይ መደገፋችንን ያሳያል፡፡ የጠበቅነው ነገር ሳይሆን ያልጠበቅነው ነገር ሲሆን በእውቀታችን ላይ ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ ተደግፈን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

የሁለቱ ቅርጫቶች ባለቤት ታሪክ

full empty 2.jpgአንድ የሰማሁትን ልብ የሚነካ ታሪክ ላካፍላችሁ፡፡ ታሪኩ በጣም ልቤን ስለነካኝና ስላስደነገጠኝ ምን ያህል ጊዜ ለሰዎች እንደተናገርኩት አላስታውሰውም፡፡

ታሪኩ እንደዚህ ነው፡፡ አንድ ክርስትያን ስለ አንዲት ክርስቲያን ሲፀልይ ራእይ ያያል፡፡ በራእዩም ውስጥ ሁለት ቅርጫቶችን ይመለከታል፡፡ አንደኛው ቅርጫት ሙሉ ነው ፡፡ አንደኛው ቅርጫት ግን ከሞላ ጎደል ባዶ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ክርስትያን ይህ ምንድነው ብሎ ጌታን ሲጠይቅ እግዚአብሄር ተናገረው፡፡

ይህ የምታየው የሞላው ቅርጫት የዚህች ሴት ልመናዋ ነው፡፡ ይህች ሴት መለመን ታውቅበታለች፡፡ ስለዚህ በትጋት ትለምነኛለች፡፡ ይህ የምታየው ከሞላ ጎደል ባዶው የዚህች ሴት የምስጋና ህይወትዋ ነው፡፡ ይህች ሴት እኔን እንዴት እንድምታመሰግን አታውቅም፡፡ እኔን ለማመስገን አትተጋም፡፡ እኔ ደግሞ ልመናዋን መመለስ እፈልጋለሁ፡፡

ለዚህች ሴት እንዲህ ብለህ ነገራት፡፡ እኔን ማመሰገን ጀምሪ፡፡ እኔን በነገር ሁሉ ማመስገን ተማሪ፡፡ እኔን የሚያመሰግን ህይወት ይኑርሽ፡፡ እኔን በትጋት ማመስገን ስትጀምሪ ይህ የፀሎት ልመናሽ ሁሉ እየተመለሰ ይሄዳል ብሎ ተናገረው፡፡

ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6

ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡4

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

%d bloggers like this: