Category Archives: peace

የሰው የጥላቻ ችግር የእግዚአብሔር ችግር ነው

conscious1.jpg

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ፍፁም ተደርጎ ነው፡፡ ሰው እንደተፈጠረበት አላማ እግዚአብሄርን እየታዘዘ እግዚአብሄርን እየሰማ ይኖር ነበር፡፡ ሰው በህይወቱ ምንም ችግር አልነበረበትም፡፡

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡27

በሰው ህይወት ውስጥ ችግር የተጀመረው ሰው እግዚአብሄር አትብላ ያለውን ያንኑ ፍሬ በመብላት ከእግዚአብሄር ጋር ችግር ውስጥ በወደቀበት ጊዜ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ችግር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ምንም ችግር በህይወቱ አልነበረም፡፡

ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ። ኦሪት ዘፍጥረት 3፡6-7

ሰው የተፈጠረው በየዋህነት እግዚአብሄርን በፍፁም እያመነ እየተደገፈው በመታዘዝ እንዲኖር ነበር፡፡ ሰው ግን የሰይጣንን ምክር በመስማት እግዚአብሄር ላይ ያለውን እምነት አጣው፡፡ ሰው ሃሳቡ ተበላሸ ለእግዚአብሄር ያለው ቅንነት ተመታ፡፡ ሰው በእግዚአብሄ ላይ በማመፁ ለከእግዚአብሄ ጋር ተጣላ፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

በሰው ህይወት ውስጥ ጦርና ጠብ የተጀመረው ሰው በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ ነው፡፡ የሰው የጦርና የጠብ ችግር የመነጨው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላሙን ሲያጣ ሰው ከራሱ ጋር ሰላም አጣ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሲጣላ ከሰው ጋር ተጣላ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላሙን ሲያጣው ከሌሎች  ነገሮች ሁሉ ጋር ሰላምን አጣ፡፡

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ሰላም የነበረ ጊዜ ሰው ከራሱ ጋር ያለው ግንኙነትና ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ሰላም ነበረ፡፡ አሁንም ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ሰላም ሲሆን ሰው ከራሱ ጋር ያለው ግንኙነትና ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ሰላም ይሆናል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ካልሆነ ከራሱ ጋር እንዲሁም ከሌላ ሰው ጋር ሰላም አይሆንም፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በሰው ዘንድ ጦርና ጠብ የሚመጡበትን ምንጭ ሲናገር ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት መበላሸት ጦርና ጠብና  እንደሚያመጣ ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም የሌለው ሰው ለማንም ሰላም ሊሰጥ አይችልም፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። የያዕቆብ መልእክት 4፡1-3

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያስተካክል በህይወቱ ያሉት ሌሎች ግንኙነቶች ሁሉ ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ሲዛባ ሌሎች ግንኙነቶች ሁሉ ይዛባሉ፡፡

ሰው የጥላቻ ችግር የተጀመረው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የጥላቻ ችግሩ የሚፈታው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ሲስተካከል ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚወድና ከእግዚአብሄር ጋር ያልተጣላ ሰው ሰውን ይወዳል ከሰውም ጋር አይጣላም፡፡ ሰው ሰውን የሚወደውና ከሰው ጋር የማይጣላው እግዚአብሄርን እንደሚገባ ሲወድ ነው፡፡

ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡20

ከሰው ጋር የሚጣላ ሰው በሆነ መልኩ መጀመሪያ ከእግዚአብሄር ጋር በሆነ ነገር አልተግባባም፡፡ ሰው ቢጣላችሁ በእናንተ አልጀመረም፡፡ እናንተን እንዲጣላችሁ ያደረገው ያ ጥል የመነጨው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላምን በማጣትና ከእግዚአብሄር ጋር በመጣላት ነው፡፡

ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። የዮሐንስ ወንጌል 15፡18

የሰው የጦርና የጠብ ችግር ከስር መሰረቱ የሚፈታው ከእግዚአብሄር ጋር እንጂ ከሰው ጋር አይደለም፡፡ ከሰው ጋር ያለው ጦርና ጠብ ፍሬው እንጂ ስሩ አይደለም፡፡

ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ። የማቴዎስ ወንጌል 12፡33

ሰው ከሰው ጋር ያለውን ችግር በቴክኒክና በታክቲክ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ቢያስተካከል ሌሎች ሁሉ ግንኙነቶች ይስተካከላሉ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰላም #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ምንጭ #ክፉ #ጦር #ጠብ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ

kingdome.jpgየእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ሮሜ 14፡17

የእግዚአብሄር መንግስት የቁሳቁስ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የሚበላና የሚጠጣ ጉዳይ አይደለም፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ከፍ ያለ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የመንፈስ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የእግዚአብሄርና የልጆቹ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የነገስታት ቤተሰብ መንግስት ነው፡፡

ለእግዚአብሄር መንግስት በሚበላና በሚጠጣ መጋጨት አይመጥነውም፡፡

የእግዚአብሄር መንግስ አትቅመስ አትንካ በሚል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚተዳር መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ስርአት በስርአት የሆነበት መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በስርአት ብዛት ሰዎችን የሚቆጣጠሩበት መንግስት አይደለም፡፡

ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስይስ 2፡20-21

የእግዚአብሄር መንግስት ልጆቹ በመንፈሱ የሚመሩበት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሰው ከውጭ በስርአትና በህግ ሰውን የሚቆጣጠርበት መንግስት ሳይሆን የእግዚአብሄር መንፈስ እያንዳንዱን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራበት መንግስት ነው፡፡

እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27

የእግዚአብሄር መንግስት ሰው በፍቅር በፈቃዱ ለእግዚአብሄር የሚገዛበት የፍቅር መንግስት ነው፡፡

የእግዚአብሄ መንግስት ፅድቅ ነው

የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክል መሆን መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛ አቋም መያዝ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄ መንግስት ኢየሱስን ፈፅሞ መከተል ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት የሰላም መንግስት ነው

የእግዚአብሄር መንግስት የእረፍት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ላይ የመደገፍ መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የፉክክርና የረብሻ መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ረጋ ብለን እግዚአብሄርን እየሰማን የምንኖርበበት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄ መንገስት በረብሻ ጊዜ እንኳን አእምሮን የሚያልፍ ሰላም የምንለማመድበት መንግስት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የደስታ መንግስት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት የቁሳቁስ ደስታ መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የእርስ በእርስ ፉክክር መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በገንዘብ የመመካት መንግስት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በኑሮ የመመካት መንግስት አይደለም፡፡

ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሃንስ 2፡15-16

የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ደስ የመሰኘት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ብቻ የመመካት መንግስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ሁልጊዜ በጌታ ደስ የምንሰኝበት የደስታ መንግስት ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፅድቅ #ሰላም #መንፈስቅዱስ #ደስታ #መብል #መጠጥ ##ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አለም #ሃጢያት #ድምፅ #ቅባት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የህይወትፍሬ #መናገር #ቅባት #ትግስት #መሪ

የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ

peace of god.jpgበአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

በምድር ብዙ ድምፅና ማስፈራራት አለ፡፡ አለም አይሆንም አትችልም አይሳካልህም በሚሉ ድምፆች የተሞላች ነች፡፡

አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም ጎሽ ቀጥሉ የእግዚአብሄርን ስራ እየሰራችሁ ነው፡፡ በትክክለኛ መንገድ ላይ ናችሁ ሰላም ነው እንድትለን መጠበቅ የለብንም፡፡ አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም በእኛ ላየ ነው የሚሰራው አንጂ ለእኛ አይደለም የሚሰራው፡፡ ከአለም እንደዚህ አይነትን ማረጋገጫ መጠበቅ ሃዘን ውስጥ ይከታል፡፡

ትክክልኛውንና እውነተኛውን ነገር የምንረዳው ከመንፈሳዊው አለም ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር የምናውቀው በመንፈሳዊው አለም ብቻ ነው፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27

የእግዚአብሄርን ነገር የምንሰማው በልፀባችን ነው፡፡ ከግርግሩ ወጣ ብለን ወደልባችን መልስ ብለንብ ልባችንን የምንሰማበት ጊዜ ሊኖረን ይገባል፡፡ በዚህ መድር ላይ ትክክለኛውን ማረጋገጫ ሎሰጠን የሚችል ብቸኛው ነገር ልባቸነ ነው፡፡

አካባቢያችን በታላቅ ረብሻ ቢሞላም እንኳን ልባችን ሰላም ነው ካለ ሰላም ነው፡፡ አእምሮዋችን በጭንቀት ሃሳብ ቢወጠር እንኳን ልባችን ሰላም ከሆነ ሰላም ነው፡፡

ልባችን ሰላም ከሆነ ሁሉ ሰላም ስለሆነ እርፍ ልንል ይገባናል፡፡ የሚመራን የአለም ጩኸትና ማስፈራራት ሳይሆን ሂዱ ቁሙ እያል የሚመራን የክርስቶስ ሰላም ይሁን፡፡

ስለዚህ ነው ዘማሪ ተከስተ ጌትነት

ውስጤ ስሰማው ሳደምጠው

ሁሉ ሰላም ሰላም ነው

ውጭውን አይቶ ልቤ እንዳይሰጋ

እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ

በማለት የዘመረው፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አእምሮ #መንፈስ #ሰላም #ልብ #አይታወክ #አይፍራ #ጭንቀት #ቅባት #ይግዛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ልባችሁ አይታወክ አይፍራም

green-light.jpgሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። ዮሐንስ 14፡27

በልባችን ሰላም ካለን ሁሉ ነገር መልካም ነው፡፡ ውጭው ተረብሾ የውስጥ ሰላም ካለን  ነገር ሁሉ ትክክል ነው፡፡ በአእምሮዋችን ግራ መጋባት ኖሮ በልባችን ሰላም ካለን ሁሉ ሰላም ነው ማለት ነው፡፡ ልባችሁ ብቻ አይታወክ እንጂ ሌው ችግር የለም ብሎናል፡፡

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐንስ 14፡1

ከውጭ ያለው ነገር እንደማይታወክ መተማመኛ የለንም፡፡ ልባችንን በሰላም እንደሚጠብቀው ግን ቃል ግብቶልናል፡፡

ምንም ምንም መከተል ባትችሉ የልባቸሁን ሰላመ ተከተሉ፡፡ በውጭው ምንም ነገር ባትተማመኑ በልባችሁ ሰላም ተማመኑ፡፡ ምንም የውጭ ነገር እንዲመራችሁ ባትፈቅዱ የልባችሁ ሰላመ ይምራችሁ፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

እንዲያውም በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ብሎዋል፡፡ ነገር ግን አይዞዋችእሁ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ፡፡ እናንትም እያሸነፋችሁት ነው፡፡ ስለዚህ ሰላማችሁን አትጡ፡፡ ሰላማችሁ አይወሰድ፡፡ ሰላም ነው እያለን ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መታዘዝ #ተስማማ #ሰላም #ልብ #አይታወክ #አይፍራ #ስኬት ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: