Category Archives: worship

ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል

ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው። ዘፍጥረት 32፡3Gods-Beauty-god-the-creator-27196695-410-312.gif

እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። መዝሙር 27፡4

ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል። ኢሳያስ 33፡17

እግዚአብሄርን እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን ለማምለክ ስለተሰራን እግዚአብሄርን እንደማየት የሚያረካ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደማምለክ የሚያሳርፍ ነገር የለም፡፡

እግዚአብሄርን ስናመልከው አካባቢያችንን እንረሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው ከሁኔታችን እንወጣለን፡፡ እግዚአብሄርን በውበቱ ስናየው እናርፋለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው በጎነቱን እናስታውሳለን፡፡ እግዚአብሄርን እንዳለ ስናየው በሃይሉ እንበረታለን፡፡

እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። ኢሳይያስ 40፡15

እግዚአብሄርን እንዳለ ስናየው በጥበቡ እንማረካለን፡፡ በእግዚአብሄርን ስናመልከው በፍቅሩ እንወሰዳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው በመልካምነቱ እንረሰርሳለን፡፡ እግዚአብሄርን ስናመልከው ልባችን ከፍ ይላል፡፡ እግዚአብሄርን ስናየው ካለንበት የምድር ስበት ከፍ እንላለን፡፡

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። 1ኛ ዜና 16፡10

የዘላለሙን እግዚአብሄርን ስናመልከው የምድር ኑሮዋችን ያጥርብናል፡፡ የዘላለሙን እግዚአብሄርን ስናመልከው ሰማይን እናያለን፡፡ መጀመሪያና መጨረሻ የሆነውን እግዚአብሄርን ስናመልከው ዘላለምን እንመለከታለን፡፡

ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።ራእይ 1፡8

እግዚአብሄርን ስናመልከው መጀመሪያና መጨረሻ በሆነው በእግዚአብሄር እንወሰዳለን፡፡ ታላቁን እግዚአብሄርን ስናመልከው ያለንበት ፈታኝ ሁኔታ ያንስብናል፡፡ መኖሪያችን እግዚአብሄርን ታላቅነት ስናይ የኑሮ ፍርሃት ከህይወታችን ይሞታል፡፡

መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ዘዳግም 33:27

ማስተዋሉ የማይመረመረውን እግዚአብሄርን ስናመልከው የህይወት ጥያቄያችንን ፈልገን እናጣዋለን፡፡ ባለጠጋውን እግዚአብሄርን ስናመልከው በባለጠግነቱ እንመካለን፡፡

የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። መዝሙር 50፡10

ሃያሉን እግዚአብሄርን ስበናመልከው የራሳችንን ድካም እንረዳለን፡፡ ማስተዋሉ የማይመረመረውን እግዚአብሄርን ስናምለከው ያለንን ውስንነት እንረሳለን፡፡ ሁሉን ማድርግ የሚችለውን እግዚአብሄርን በውበቱ ስናየው መንገዳችን ይቀልልናል፡፡

ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡2

የምድር መሰረቶች የእርሱ የሆኑትን እግዚአብሄርን በክብሩ ስናየው በአባታችን ደስ እንሰኛለን፡፡

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አምልኮ #መገዛት #ቃል #ደስታ #እርካታ #እህል #መመልከት #ማየት #ተመልክተን #መቃጠል #መቀጣጠል #ክብር #አገልግሎት #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በሰማያት ላይ ለረድኤትህ እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም

cloudy_sky_over_mountains-t2 (1).jpgይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26

የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ የሚረዳን እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከመርዳት ውጭ ሌላ ስራ የለውም፡፡ የእግዚአብሄር ስራ እኛን መርዳት ነው፡፡

እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር በሰማይ ያለው በታላቅነት ነው፡፡ እግዚአብሄር በታላቅነት በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡

እግዚአብሄር ከፍ ያለ ቦታ ያለው ሁሉን ሊያይና ሊረዳን ነው፡፡

የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ። መዝሙር 53፡2

ስለዚህ ነው የእግዚአብሄርን እርዳታ ያየው መዝሙረኛው ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲህ እያለ የሚያመሰግነው፡፡

ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና። መዝሙር 63፡7

እግዚአብሄር አምላኩ የሆነለት ህዝብ ምስጉን ነው፡፡

የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤ መዝሙር 146፡5

ህዝቡን እንደሚረዳና እንደሚደግፍ እንደ እግዚአብሄር ያለ ማንም የለም፡፡ እንደ እኛ የታደለ ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ደስ ሊለው የሚገባው ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ሳያቋርጥ እግዚአብሄርን ማመስገን የሚገባው ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ሊረዳ ነው፡፡

ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #እርዳታ #ታላቅነት #ቃል #መልካም #መታመን #መደገፍ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ረድኤት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል

tripartite-01.pngአባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐንስ 4፡20-24

ኢየሱስ ከሳምራዊትዋ ሴት ጋር ሲነጋገር ለሁላችን ትልቅ መረዳትን የሚሰጥን ነገር ተናግሮዋል፡፡ ሳምራዊትዋ ሴት ሳምራዊያን በዚያ ተራራ ላይ ለእግዚአብሄር እንደሚሰገድ እንደሚያምኑ አይሁዳዊያን ደግሞ የሚሰገደው በኢየሪሳሌም ነው እንደሚሉና ተናገረች፡፡

ኢየሱ የመለሰላት መልስ ግን ከሁለቱም ለየት ያለ ነበር፡፡ ኢየሱስ በአዲሱ ኪዳን ሰው በዚያ ተራራም ይሁን በኢየሩሳሌም እግዚአብሄር እንደማይሰገድለት አስተማራል፡፡

እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በተራራ ላይ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡

ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም። ሃዋሪያት 7፡48-50

እግዚአብሄር ሰው በሰራው ቤተመቅደስ ውስጥ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄርን  በሆነ ቤት ውስጥ ብንፈልገው አናገኘውም፡፡

ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡20

ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤ ሃዋሪያት 17፡24

እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በስጋ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄ በአንድ አገር ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ ከተማ ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ ቤት ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ ስፍራ አይገኝም፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? ኢሳያስ 66፡1

ለእግዚአብሄር የሚሰግዱለት ሰዎች በመንፈስ ሊያገኙት ይገባል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያገኙት ሰዎች በመንፈስ ብቻ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የሚሰግዱለት ሰዎች በመንፈስ ብቻ ሊሰግዱለት ይችላሉ፡፡

እግዚአብሄር የሚፈልገው በስጋ የሚሰግዱለትን ሰዎች አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በመንፈስ የሚሰግዱለትን ሰዎች ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በእውነትና በመንፈስ የሚሰግዱለትን ሰዎች ነው፡፡ ለእግዚአብሄር በልባቸው የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳያስ 66፡2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #እግዚአብሄር #አምልኮ #ስግደት #እውነት #መንፈስ #ኢየሩሳሌም #ቅዱሳን #ጌታ #ሰማእታት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እምነት #ክብር #ፍቅር #ምስል #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ኦርቶዶክስ #ማርያም #አንድ #ብቻ #ሰይጣን

የስግደት አደጋው

worship11.jpgበእነዚህ ቀናት ከእግዚአብሄር ውጭ ለሰው ለመላእክት ለቅዱሳን ለሰማእታት ስግደት ይገባል አይገባም ስግደት ከተገባስ እስከምን ድረስ ነው ስግደት የሚገባው የሚለው ጥያቄ ሲያከራክር ቆይቶዋል፡፡

የዚህ ፅሁፍ አላማ የስግደትን አይነቶችና መጠን ለመተንተን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ውጭ ያለ ስግደት ያለውን አደጋና ለምን ስግደት አደገኛ እንደሆነ ጥቂት ለማለት ነው፡፡

ስግደት ማለት እገዛልሃለሁ እታዘዝሃለሁ አንተ ጌታዬ ነህ ባንተ እታመናለሁ ማለት ነው፡፡ ስግደት ማለት አንተ ፈጣሪዬ ነህ እኔ ያንተ ነኝ ባንተ ተስፋ አደርጋለሁ ማለት ነው፡፡ ስግደት ማለት ለምንሰግድለት ነገር ራሳችንን አሳልፈን መስጠት ማለት ነው፡፡

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስግደትን በተመለከተ ለእግዚአብሄር መስገድ እንደሚገባ በብዙ ቦታዎች ተጠቅሶዋል፡፡

ትኩረታችንን የሚፈልጉ እንድንሰግድላቸው በየጊዜው የሚፈትኑ የሚማርኩን ካልሰገድክልኝ ብለው የሚያስፈራሩ ብዙ ነገሮች በአለም ላይ አሉ፡፡ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ ያለበት ግን ለእግዚአብሄር ነው፡፡

እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና። ሮሜ 14፡11

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሄር ህዝብ ለእግዚአብሄር እንዲሰግዱ በብዙ ቦታዎች ታዞዋል፡፡ እግዚአብሄር ስለፈጠረን ስግደት እንደሚገባው መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡

ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ፤ መዝሙር 95፡6

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሄር ህዝብ ለእግዚአብሄር ብቻ እንጂ ለመልአክት እንዳይሰግዱ ታዞዋል፡፡

ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ። ራእይ 19፡10

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሄር ህዝብ ለእግዚአብሄር ብቻ እንጂ እግዚአብሄርን ለሚመስል ነገር ስእል ወይም ምስል እንኳን እንዳይሰግዱ ታዞዋል፡፡

በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ ዘፀአት 20፡4-5

ስግደት ለእግዚአብሄር ለአምላክነቱ ክብር የምናሳይበት መንገድ ነው፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ሊከበር እንደሚገባ በብዙ ቦታዎች ተጠቅሶዋል፡፡

ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፥ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ። ኢሳያስ 42፡12

አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለዘላለምም ስምህን አከብራለሁ፤ መዝሙር 86፡12

በመፅሃፍ ቅዱስ ከእግዚአብሄር በላይ ይሁን ከእግዚአብሄር እኩል ማንም እንዳይከበር በብዙ ቦታዎች ታዞዋል፡፡ እግዚአብሔር ከምንም ሰው ጋር ፣ ከማንም መላክእት ጋር ፣ ከየትኛውም ቅዱሳን ጋር አንደ አንዱ እንዲቆጠር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ ነው፡፡

እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ታላቅ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ። መዝሙር 34፡3

በመፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ክብሩን ለማንም እንደማይሰጥ ተመልክቶዋል፡፡

እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። ኢሳያስ 42፡8

በመፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ክብሩን ለማንም ለስጋ ለባሽ እንደማይሰጥ ተመልክቶዋል፡፡

ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። ሐዋሪያት 12፡23

በመፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ክብሩን ለማንም መልአክ እንደማይሰጥ ተመልክቶዋል፡፡

እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ። ራእይ 22፡9

ሰይጣን የወደቀው እንደእግዚአብሄር መመለክ ስለፈለገ ነው፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው መመለክንና እንዲሰገድለት ነው፡፡

ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ማቴዎስ 4፡9

እግዚአብሄርን የሚያመልክና ለእርሱ የሚሰግድ ሰው ለሰይጣን አይሰግድም፡፡ ለእግዚአብሄር የማናመጣውን ማንኛውንም ስግደት የሚቀበለው ሰይጣን ነው፡፡ ለሰው ብንሰግድ ፣ ለመላእክት ብንሰግድ ፣ ለምስል ብንሰግድ ፣ ለዛፍም ብንሰግድ ፣ ለወንዝም ብንሰግድ ስግደቱን በተዘዋዋሪ የሚቀበለው ሰይጣን ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር እንዲሰግድ ሰይጣን አይፈልግም፡፡

ሰው ለእግዚአብሄር አይስገድ እንጂ ለምንም ነገር ቢሰግድ ሰይጣን ደስ ይለዋል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ካልሰገደ በተዘዋዋሪ ለእርሱ እንደሚሰግድ ሰይጣን ያውቃል፡፡

ዲያብሎስም፦ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው። ሉቃስ 4፡6-7

ትኩረታችሁ በእግዚአብሄር ላይ አይሁን እንጂ በምንም ነገር ላይ ቢሆን ሰይጣን ደስተኛ ነው፡፡ ትኩረታችሁ ከእግዚአብሄር ላይ ይነሳ እንጂ ትኩረታችንሁ ምንም ነገር ላይ ቢሆን ሰይጣን ተጠቃሚ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር አትስገዱ እንጂ ለምንም ነገር ብትሰግዱ ሰይጣን ይጠቀማል፡፡ እግዚአብሄርን ብቻውን አትስገዱለት እንጂ ከምንም ነገር ጋር አብራችሁ ብትሰግዱለት ሰይጣን ግቡን ይመታል፡፡

የሰይጣን ግብ እግዚአብሄር ብቻውን እንዳይመልክ ነው፡፡ የሰይጣን ግብ እግዚአብሄር ከሌሎች ሰዎች ፣ ከሌሎች ቅዱሳን ፣ ከሌሎች መላእክት ጋር አብሮ እንደ አንዱ እንዲመለክ ነው፡፡ የሰይጣን ግንብ የእግዚአብሄርን ክብር በሰዎች ፣ በቅዱሳን ፣ በመላእክት ፣ በምስል መሸፈን ነው፡፡

እግዚአብሄር ደግሞ የሁሉም ፈጣሪ እና አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደ አንዱ እንዲመለክ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ብቻውን መመለክ ነው የሚፈልገው፡፡ እግዚአብሄር ከምንም ከምንም ጋር እንዲቆጠር አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ብቻውን ካላመለካችሁት ከማንም ጋር አብራችሁ እንድታመልኩት አይፈልግም፡፡

እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። ኢሳያስ 42፡8

ስለዚህ ነው በአዲስ ኪዳን ለእግዚአብሄር የሚሰግዱ ሰዎች በተወሰነ ቦታ ሳይገደቡ በእውነትና በመንፈስ ባሉበት ቦታ ለእግዚአብሄር እንደሚሰግዱለት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሃንስ 4፡23-24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #እግዚአብሄር #አምልኮ #ስግደት #ጣኦት #መላእክት #መመካት #ቅዱሳን #ጌታ #ሰማእታት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እምነት #ክብር #ፍቅር #ምስል #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ኦርቶዶክስ #ማርያም #አንድ #ብቻ #ሰይጣን

እግዚአብሔርን አመልካለሁ

worship.jpgየዚያን ጊዜም፦ ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን፤ ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት። እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ አላቸው። ዮናስ 1፡8-9

ነቢዩ ዮናስን ስራህ ምንድነው ብለው በጠየቁት ጊዜ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ ብሎ ነበር የመለሰው፡፡

እግዚአብሄርን ማምለክ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ቤተክርስትያን አዳራሽ መሄድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ መዘመር አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ሁለንተናችነን የሚጠይቅ መሰጠት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ 24 ሰአትና 7 ቀን የሚጠይቅ የህይወት ዘይቤ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ከንግግር ያለፈ ሙሉ አስተሳሰብንና ሙሉ ድርጊትን የሚጠይቅ መሰጠት ነው፡፡

እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሃያል አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረንና ህይወታችንን በእጁ የያዘ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከእግዚአብሄር ጋር በጥንቃቄ መኖር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን አለመናቅ ማክበር ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና። ዘጸአት 20፡7

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን እንደ በላይ አምላክ ማየት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በምናደርገው በማንኛውም ነገር የእርሱን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርብን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄርን ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት ማለት ነው፡፡

ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ሮሜ 1፡20-21

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር መገዛት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእግዚአብሄር እሺ ማለት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን መስማትና መታዘዝ ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ያዕቆብ 4፡7

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት የእግዚአብሄር ባሪያ መሆን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት የራስን ፈቃድ ለእግዚአብሄር አሳልፎ መስጠት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ለእኛ ደስታ ሳይሆን ለእሱ ደስታ መኖት ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን። ያዕቆብ 1፡1

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መልካምነት መሳብ መደነቅ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር ባህሪ መማረክ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምልክ ማለት በእግዚአብሄር አሰራራ መዋጥ ማለት ነው፡፡

በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ራእይ 1፡16-17

በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ። እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝሙር 66፡2-3

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ማፍቀር ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሄርን መውደድ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም በላይ ለእግዚአብሄር ያለንን ፍቅር ማስበለጥ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ሙሉ ትኩረታችንን ለእግዚአብሄር መስጠት ማለት ነው፡፡

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ማርቆስ 12፡29-30

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መታመን ማለት ነው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ ምሳሌ 3፡5

 1. በእግዚአብሄር ደስ መሰኘት ማለት ነው፡፡ አግዚአብሄርን ማምለክ ማለት በእግዚአብሄር መመካት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምልክ ማለት በእግዚአብሄር ከፍ ከፍ ማልት ነማለት ነው፡፡

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። መዝሙር 105፡3

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ብቻ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው፡፡

አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው። መዝሙር 39፡7

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሄርን መፈለግ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት ምንንም ነገር ከእግዚአብሄር አለማስተካከል ማለት ነው፡፡

ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም። መዝሙር 34፡10

 1. እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ከሌሎች ነገሮች ለይቶ ማየት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማምለክ ማለት እግዚአብሄርን ከሌሎች ነገሮች ጋር አለመቀላቀል ማለት ነው፡፡

ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡14-15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #አምላክ #ኢየሱስ #ቃል #መገዛት #አምልኮ #መስማት #መታዘዝ #መውደድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መከተል #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም!

46879143-amazing-pictures.jpgይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።  ዘዳግም 33፡26

እግዚአብሄር በሰማይ ላይ ያለው ህዝቡን ሊረዳ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስራው ለክብሩ የፈጠረውን ህዝብ መርዳርትት ነው፡፡ እግዚአብሄር ስራው እኛን መከታተል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስራ እኛ ልጆቹ ምንም እንደማይጎድልብን እርግጠኛ መሆን ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰማያት ላይ የሚሄደው ሊረዳህ ነው፡፡

እግዚአብሄር በሰማያት ላይ ያለው እኛን ሊረዳን ነው፡፡ እግዚአብሄር ከፍ ብሎ ያለው እኛን በትክክል ለማስተዳደር ነው፡፡ እግዚአብሄር በጥበብ በሃይልና በፍቅር አለምን ሊገዛ በደመናት ላይ አለ፡፡ ከእግዚአብሄር ቁጥጥር ውጭ የሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር የማያውቀው ነገር በምድር ላይ አይፈፀምም፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደንቀው ነገር “እንዴ!” የሚያሰኘው ነገር የለም፡፡ የእግዚአብሄር ማስተዋል አይመረመርም፡፡

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28

ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? 2ኛ ሳሙኤል 7፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄርታላቅ #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የዝምታ አምልኮ

የዝምታ አምልኮ

silence-is-golden.jpgከእግዚአብሄር ጋር ላለን ግንኙነት መጠናከር ጠቃሚ ከሆኑ የተለያዩ የጥሞና መንገዶች አንዱ ዝምታ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት ስምረት የሚለካበት አንዱ መንገድ ዝምታ ነው፡፡
ስጋ ሁል ጊዜ መናገር ይፈልጋል፡፡ ስጋ የሚረካው በመናገር ነው፡፡ ስጋ በህይወት የመጡትን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚሞክረው በመናገር ብዛት ነው፡፡ ስለዚህ ነው አንዳንድ ጊዜ አልናገርም ብለን ስንወስን ስጋ ከውስጣችን ሲጮህና ሲቃወም የምንሰማው፡፡ ስጋ ራሱን የሚያረካው በመናገር ነው፡፡
ስጋ ዝም ማለትና ማረፍ አይፈልግም፡፡ ስጋ ነገሮችን በንግግር መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ስጋ ለእግዚአብሄር ጊዜ መስጠት አይፈልግም፡፡ ስጋ ለእግዚአብሄር ስፍራን በመስጠት በዝምታ መጠበቅ አይፈልግም፡፡ ስጋ ዝምታን እንደ ሽንፈትና እንደ አቅመቢስነት ነው የሚያየው፡፡ አንደበቱን መግታት የማይችል ብዙ የሚለፈልፍ ሰው ካያችሁ በስጋው የተሸነፈ ሰው ነው፡፡
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ሮሜ 12፡19
ፀጥታ የመታመን ምልክት ነው፡፡ ፀጥ የሚለው እግዚአብሄር የልብን ጩኸት ይሰማል የሚል ሰው ነው፡፡ ፀጥ የሚል ሰው የህይወት ቁልፉ እግዚአብሄር ጋር እንጂ ሰው ጋር እንደሌለ የሚያምን ሰው ነው፡፡ ፀጥ የሚል ሰው የሰው ቁጣ የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንደማይሰራ (ያዕቆብ 1፡20) የተረዳ ሰው ነው፡፡ ያልታመነ ሰው ይናወጣል፡፡ ያላመነ ሰው በፀጥታ መቀመጥ አይችልም፡፡
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15
ሳንናወጥ በዝምታ እግዚአብሄርን መጠበቅ በእግዚአብሄር ላይ መደገፋችንን ያሳያል፡፡ በፀጥታ እግዚአብሄርን መጠበቃችን ለእግዚአብሄር ስፍራን መስጠታችንን ያሳያል፡፡ በፀጥታ መቀመጣችን “ካለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና” (ዮሐንስ 15፡5) ያለውን ቃል በማመን በእርሱ ላይ እርፍ ማለታችንን ያሳያል፡፡ ፀጥታችን እግዚአብሄር ምድርን እንደሚገዛ ማመናችንን ያሳያል፡፡
ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙር 46፡10
በዝምታ የሚኖር ሰው ሃይሉን ባላስፈላጊ መናወጥ አያባክንም፡፡ በእርግጥም በዝምታ እግዚአብሄርን የሚጠብቅ ሰው ሃይሉን እንደንስር ያድሳል፡፡
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ኢሳይያስ 40፡31
የምናድርበት መንገድ ነው፡፡ ዝምታ ለእግዚአብሄር የምናመልክበት መንገድ ነው፡፡ ዝምታ ለእግዚአብሄር የምንገዛበት መንገድ ነው፡፡
ከሁሉም በላይ ልንከተለው ስለሚገባው ስለኢየሱስ ዝምታ መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡
እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ማቴዎስ 12፡18-19
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ዝምታ #ማረፍ #መታመን #መደገፍ #ፀጥታ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መንገድ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
%d bloggers like this: