Category Archives: New Year

ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ

new year1.jpgይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ዘጸአት 12፡2

የእግዚአብሄርና የሰው አቆጣጠር ይለያያል፡፡ እግዚአብሄር ዘመን ተለወጠ የሚለውና ሰው ዘመን ተለወጠ የሚለለው ሁለት የተለያዩ ጊዜያትን ነው፡፡ እግዚአብሄር በመለወጡ የሚደሰትበትና ዘመንና ሰው በመለወጡ የሚደሰትበት ዘመን ይለያያል፡፡ የእግዚአብሄር አቆጣርና የሰው አቆጣጠር ለየቅል ነው፡፡

እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡8

ሰው እንደሚያይ እግዚአብሄር አያይም፡፡ ሰው ውጭን ያያል እግዚአብሄር ግን የውስጥን ልብን ያያል፡፡ ሰው ውጪው ሲለወጥ ደስ ይለዋል እግዚአብሄር ደግሞ ውስጡ ሲለወጥ ደስ ይለዋል፡፡

እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 16፡7

ሰው ዘመኑ ተለወጠ የሚለውና እግዚአብሄር ዘመኑ ተለወጠ የሚለው ይለያያል፡፡ ሰው የቀንና የወር መለዋወጥን ያያል፡፡ እግዚአብሄር ግን የህይወት ለውጥን ያያል፡፡ ሰው ውጫዊ ለውጥን ያያል እግዚአብሄር ግን የልብ እውነተኛ ለውጥን ያያል፡፡

እግዚአብሄር ዘመንን ብቻ አይቆጥርም፡፡ እግዚአብሄር የህይወት ለውጥን ያያል፡፡ እግዚአብሄር ጊዜ አያስደንቀውም የህይወት ለውጥን ግን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ነው ብዙ አዲስ አመት ያሳለፉትን ነገር ግን ህይወታቸው በዚያው መጠን ያልታደሰውና ያልተለወጡትን ሰዎች እንዲህ በማለት የሚወቅሳቸው፡፡

ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ዕብራዊያን 5፡12

እግዚአብሄር የሰው ዘመን ተለወጠ የሚለው ሰው እግዚአብሄርን ታዝዞ ነፃ ሲወጣ ብቻ ነው፡፡ የሰው ዘመን በእውነት የሚለወጠውቅ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲታዘዝ ብቻ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በታዘዘ ጊዜ ጳጉሜ 5 ቢሆን ህይወቱ ይለወጣል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በታዘዘ ጊዜ አዲስ ቀንና ወር ይኖረዋል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ካልታዘዘ ግን መስከረም አንድም ቢሆን ለማይታዘዝ ሰው አዲስ አመት አይሆንለትም፡፡

ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡31-32

የእስራኤል ህዝብ ዘመናቸው በእውነት የተለወጠው እግዚአብሄርን ታዝዘው ነፃ የሚያወጣቸውን የእግዚአብሄርን ቃል ትእዛዝ ባደረጉ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡

እግዚአብሄርም አለ ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፡፡ ዘጸአት 12፡2

ህይወታችን እንዲለወጥ አዲስ አመት መጠበቅ የለብንም፡፡ ህይወታችን እንዲታደስና አዲስ ቀን እንዲኖረን የእግዚአብሄርን ቃል በሰማን ጊዜ መታዘዝ ይኖርብናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በታዘዝን ጊዜ ህይወታችንና ዘመናችን ይለወጣል፡፡

መልካም የመታዘዝና የለውጥ አዲስ አመት!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #እውቀት #ቃል #ወር #መዳን #አዲስአመት #መልካም #መታዘዝ #የህይወትለውጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #አመት #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #መናገር #አእምሮ #ነፍስ #ቃል #ልጅ

የአዲስ ዓመት ምኞት ወይስ ፀሎት?

large_what-if-i-don-t-want-to-pray-nryzc7wj (1).jpgበአዲስ አመት አብዛኛው ሰው ለሌላው መልካም ነገርን ይመኛል፡፡ በጎን ፈቃድ መግለፅና ለሌላው በጎውን መመኘት መልካም ነው፡፡ መልካም መመኘት ለሌላው ያለንን መልካም ፈቃድ ለማሳየት እጅግ ይጠቅማል፡፡

እንደ መንፈሳዊ ሰው ደግሞ መልካም እንደምንመኝላቸው ሁሉ ጊዜ ወስደን እንፀልይላቸዋለን ወይ?  የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ይገባናል፡፡

የምንወዳቸውን የምናከብራቸውን ወዳጆቻችንን መልካም ልንመኝላቸው ብቻ ሳይሆን ልንፀልይላቸው ይገባል፡፡

የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16

በአዲስ አመት ልንፀልይላቸው የሚገባ

  1. ለወንድሞችና ለእህቶች

ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16

  1. ለቤተክርስትያን መሪዎች

ወንድሞች ሆይ፥ ስለ እኛ ጸልዩ። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡25

አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ የሚችል የለምና። 2ኛ ዜና መዋዕል 1፡10

  1. ጌታን ለማያውቁ ሰዎች

ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2-4

  1. ለወንጌል ሰራተኞችና ለሚሽነሪዎች

ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ ኤፌሶን 6፡19

በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ቆላስይስ 4፡3

  1. ለመንግስት ባለስልጣናት

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #ተቃውሞ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: