Category Archives: Heart Matters

እግዚአብሔርን የሚያስክደን ክፉና የማያምን ልብ 8 ምልክቶች

your will.jpg

ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ወደ ዕብራውያን 3፡12

አማኝ የነበረ ሰው ካልተጠነቀቀ በስተቀር አንድ ቀን ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክደው ክፉና የማያምን ልብ ሊኖረው ይችላል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አመልካች ምልክቶች ሰው በአፉ ምንም ቢልም እንኳን ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክደው ክፉና የማያምን ልብ እንዳለው ያመለክታል፡፡

 1. በህይወታችን ለቁሳቁስ የመጀመሪያውን ስፍራ ስንሰጥ

ሰው እግዚአብሄርን ተስፋ ካላደረገ ተስፋ የሚሆነውን ነገር ይፈልጋል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ማመን ሲያቆም በቁሳቁስ ማመን ይጀምራል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ማመን ሲያቆም በገንዘብ  ማመን ይጀምራል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር መገዛት ሲያቆም ለገንዘብ ይገዛል፡፡ ሰው ገንዘብን ሲወስድ እግዚአብሄርን ይጠላል፡፡

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። የማቴዎስ ወንጌል 6፡24

 1. ስለዘላለም ህይወት ማሰብ ስናቆም

ሰው የሚያሳስበው የምድር ህይወት ብቻ ከሆነ ልቡ እግዚአብሄርን አስክዶታል ማለት ነው፡፡ ሰው በአፉ ምንም ቢናገር ነገር ግን ለዘላለም ህይወት አክብሮት ካጣ በእግዚአብሄር የፍርድ ወንበር ፊት እንደሚቀርብ ማሰብ ከተወ እግዚአብሄርን እንደካደ የሚያሳይ ጥሩ ምልክት ነው፡፡

እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡32

 1. ስለ እግዚአብሄር ፈቃድ ግድ ሳይኖረን ሲቀር

እግዚአብሄርን የሚያምን ሰው ምልክቱ ለእግዚአብሄር ክብር መኖር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያምን ሰው የመጀመሪያው ፍላጎቱ እግዚአብሄር በህይወቱ ያለውን አላማ ለመፈፀም የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግ ነው፡፡ ሰው ግን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈለግ ፍላጎቱን ካጣና ለእግዚአብሄር ፈቃድ ግድ ከሌለው እግዚአብሄርን እንደካደ አመልካች ነው፡፡

ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42

 1. ለቤተክርስትያን የቤተሰብነት ስሜት ስናጣ

ሰው እግዚአብሄርን ሲያምን በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሄር ቤተሰብ አባል እንደሆነ የቤተሰብነት ስሜት ይሰማዋል፡፡ ሰው ግን ለቤተክርስትያን የቤተሰብነት ስሜት ካጣ በቤተክርስትያን ላይ እንደፈለገ የሚናገርና የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሄርን እንደካደ አመልካች ነው፡፡

አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል። እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡26-27

 1. ለእግዚአብሄር ቃል የነበረንን ክብደት ስናጣ

ሰው ለእግዚአብሄር ቃል ያለውን የመጀመሪያ ስፍራ ካጣ እና የእግዚአብሄርን ቃል እንደሰው ቃል ማየት ከጀመረ በአፉ ምንም ይበል ምን እግዚአብሄርን እየካደ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ሰው ሃሳቡን እንደ እግዚአብሄር ቃል መመዘኛ መመርመር ካቆመ እግዚአብሄርን እየካደ ነው፡፡

ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ የዮሐንስ ወንጌል 6፡68

 1. እግዚአብሄርን መፍራት ስናቆም

ሰው እግዚአብሄርን መፍራት ካቆመና እግዚአብሄር እንደሚያይ እንደሚሰማና በሁላችን ላይ ዳኛ እንደሆነ ከረሳ እግዚአብሄርን  ክዶዋል፡፡ ሰው የዘራወን ያንኑ ደግሞ እንደሚያጭድ ካላወቀ እግዚአብሄርን የሚያስክድ ክፉ ልብ አለው ማለት ነው፡፡

አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7

 1. መፀለይ ስናቆም

እግዚአብሄርን የሚያምን ሰው እግዚአብሄርን በመፈለግና በመፀለይ ይታወቃል፡፡ ሰው ግን መፀለይን ካቆመና ሁሉንም ነገር በራሱ ጉልበት ለመፍታት ከፈለገ እግዚአብሄርን የሚያስክድ ክፉና የማያምን ልብ እንዳለው ራሱን ይመርምር፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤የያዕቆብ መልእክት 4፡1-2

 1. እግዚአብሄርን መከተልና ማገልገል ከንቱ ነው ብለን ስናስንብ

ሰው በአፉ ላይናገረው ይችላል ነገር ግን እግዚአብሄርን ማገልገል ከንቱ ነው ብሎ ካሰበ እግዚአብሄርን የሚያስክድ ክፉና የማያምን ልብ እንዳለው አውቆ በንስሃ ይመለስ ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የሚያስክድ #ክፉልብ #የማያምን #ትግስት #መሪ

Advertisements

እንደልቤ የተባለው ዳዊት 7 የልብ ውበቶች

conscious.jpgዳዊት እግዚአብሄር እንደልቤ ያለው ሰው ነው፡፡

እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም፦ እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ። የሐዋርያት ሥራ 13፡22

ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ ተብሎ የተመሰከረለት የተባረከ ሰው ነው፡፡

ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤የሐዋርያት ሥራ 13፡36

የዳዊትን የልብ ባህሪያት ማጥናት እኛም በዘመናችን የእግዚአብሄርን ልብ ተረድተን የእግዚአብሄርን ፈቃድ አገልግለን እንድናልፍ ያስታጥቀናል፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡4

 1. ዳዊት የምስጋናን መስዋእት ያቀርባል

ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው ሲመቸው ብቻ አይደለም፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው የሚፈልገው ነገር ሁሉ እንደተሟላለት ካረጋገጠ በኋላ አይደለም፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው ሁልጊዜ ነው፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው በችግር ጊዜም ነው፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው ማጉረምረም በሚያምረው ጊዜ ነው፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው ከማመስገን ይልቅ ማጉረምረም በሚቀልበት ጊዜ ነው፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን የሚየመሰግነው ለማጉረምረም ብዙ ምክኒያቶች እያሉ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ መዝሙረ ዳዊት 50፡14

ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። መዝሙረ ዳዊት 42፡11

ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡17-18

 1. ዳዊት ለእግዚአብሄር ስርአት አክብሮት አለው

ዳዊት የመርህ ሰው ነው፡፡ ዳዊት ስሜታዊ ሰው አይደለም፡፡ ዳት የእግዚአብሄን ስርአት ያውቃል ያከብራል፡፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን ስርአት ለመጠበቅ ይጠነቀቃል፡፡ ዳዊት ሳኦል በሚያሳድደው ጊዜ ሊገድለው ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር በተቀባው ላይ እጄን አላነሳም አለ፡፡

ሰዎቹንም፦ እግዚአብሔር የቀባው ነውና እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር አደርግ ዘንድ እጄንም እጥልበት ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው አላቸው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 24፡6

ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1-2

 1. ዳዊት ሲሳሳት ለንስሃ ፈጣን ነው

ዳዊት ጥማቱና ረሃቡ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሆኖ መገኘት ነው፡፡ ዳዊት ሲሳሳት ይመለሳል፡፡ ዳዊት ሲሳሳት ራሱን ያዋርዳል፡፡ ዳዊት ከሃጢያቱ በፍጥነት ይመለስም ነበር፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄርን በሰውም ፊት ለመዋረድ ዝግጁ ነበር፡፡

ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ። መዝሙረ ዳዊት 51፡2-5

 1. ዳዊት ለሰው ፍቅር አለው

ዳዊት ለሰው ፍቅር እና አክብሮት አለው፡፡ ዳዊት ሰዎችን በማገልገል ይረካል፡፡ ዳዊት በሰዎች በመጠቀም ላይ አያተኩርም፡፡ ዳዊትን የተከተሉት ሰዎች የተጨነቁ ብድር ያለባቸው እና የተከፉ ሰዎች ነበሩ፡፡

የተጨነቀውም ሁሉ፥ ብድርም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተከማቸ፤ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 22፡2

ዳዊት እነርሱን በመምራትና በማገልገል ሃያላን አደረጋቸው፡፡ /መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 23፡8-39/

ዳዊት አንድ ጊዜ የሚጠጣው ውሃ በፈለገ ጊዜ ሃያላኑ በህይወታቸው ተወራርደው የፍልስጤምን ሰራዊት ሰንጥቀው የሚጠጣውን ውሃ አመጡለት፡፡ እርሱ ግን ለእነዚያ ሰዎች ከነበረው ክብር አንጻር በመሬት ላይ ደገፋው፡፡

ዳዊትም፦ በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ? ብሎ ተመኘ። ሦስቱም ኃያላን የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፥ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦ አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ በነፍሳቸው ደፍረው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን? ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው። መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 23፡15-17

 1. ዳዊት ለቃሉ የመጀመሪያውንም ስፍራ ይሰጣል

ዳዊት በክፋት ላለመሄድ ይጠነቀቃል፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን እንዳይበድል የእግዚአብሄርን ቃል በልቡ ይሰውራል፡፡

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።

መዝሙረ ዳዊት 1፡1-3

አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። መዝሙረ ዳዊት 119፡11-12

ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ። መዝሙረ ዳዊት 119፡127

 1. ዳዊት የእግዚአብሄርን ቤት ይወዳል

ዳዊት የእግዚአብሄርን ቤት ይወዳል፡፡ ዳዊት ለእግዚአብሄር ቤት የማያደርገው ነገር የለም፡፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን ቤት ለማገልገል ቀን ከሌሊት በትጋት ይሰራል፡፡

አቤቱ፥ ዳዊትን ገርነቱንም ሁሉ አስብ፤ ለእግዚአብሔር እንደ ማለ፥ ለያዕቆብም አምላክ እንደ ተሳለ፦ በእውነት ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥ ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም፥ ለዓይኖቼም መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ፥ ለጕንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም፥ ለእግዚአብሔር ስፍራ፥ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ። እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥ በዱር ውስጥም አገኘነው። መዝሙረ ዳዊት 132፡1-6

 1. ዳዊት የእግዚአብሄርን ምሪት ያስቀድማል፡፡

ዳዊት እግዚአብሄር እንዳለበት ያላረጋገጠውን ነገር ላለማድርግ ይጠነቀቃል፡ሸ ዳዊት በራሱ ማስተዋል አየደገፍም፡፡ ዳት በመንገዱ ሁሉ ለእግዚአብሄር ምሪት እውቅና ይሰጣል፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5-6

ዳዊት ጠላቶች መጥተው በዘረፉት ጊዜ እንኳን ለምንም ነገር አይቸኩልም ነገር ግን ልውጣባቸውን አሳልፈህ ትሰጠኛለህን ብሎ የእግዚአብሄርን ምሪት ይጠይቃል፡፡

ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 30፡8

ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበትነው ሰፈሩ። ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 5፡18-19

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡4

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፀጋ #ምህረት #ቃል #መባረክ #አገልግሎት #መዋረድ #ምስጋና #ምሪት #ፀጋ #ንስሃ #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #ዳዊት #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ልብ #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Motives are Weighed

heart 1.jpgA motive is a reason for doing something. When we do something we have a reason to do it. When we do something we always have a purpose to do when we do. We have a goal to achieve.

Many people think that God is concerned with what we do only. It isn’t true. God is concerned about what we do and in why we do them.

Some of our motives are open and the others are hidden. Some of our motives may be pure and some of them are not so pure.

We may hide our motives from people but God knows all the motives. One may argue that isn’t my motive. But God knows the motive of people. God sees the motive of acting or reacting in a manner.

All a person’s ways seem pure to them, but motives are weighed by the LORD. Proverbs 16:2

God only rewards a pure motive, not a disguised one.

The most important Biblical practice can be done in a wrong motive that nullifies its rewards from God.

For instance, the Pharisees and Sadducees were giving alms in a movie of being seen by men as religious. Their motives were not to see the poor helped. Their motives are centered on themselves, not on the person they are helping.

That is why Jesus warned us not be unfruitful in our walk with God.

Be careful not to practice your righteousness in front of others to be seen by them. If you do, you will have no reward from your Father in heaven. Matthew 6:1

Jesus encourages us to purify our motives. Jesus talks about those who don’t search their hearts and purify their motives. He said that they receive their rewards on earth in fully.  God only rewards those things that are done out of pure motives. It doesn’t really matter whether or not they are religious or not. There is nothing scary to receive all your rewards on earth working for God for years.

So when you give to the needy, do not announce it with trumpets, as the hypocrites do in the synagogues and on the streets, to be honored by others. Truly I tell you, they have received their reward in full. Matthew 6:2

Let’s search our hearts. Let’s allow the word of God that searches our heart through and through.

For the word of God is alive and active. Sharper than any double-edged sword, it penetrates even to dividing soul and spirit, joints and marrow; it judges the thoughts and attitudes of the heart. 13 Nothing in all creation is hidden from God’s sight. Everything is uncovered and laid bare before the eyes of him to whom we must give account. Hebrews 4:12-13

Not only God is concerned what we do he is also concerned why we do them.

A person may think their own ways are right, but the LORD weighs the heart. Proverbs 21:2

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#Jesus #God #holyspirit #hidden #motive #value #respecter #heart #relationship #personal #knowledge #son #daughter #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

ራሳችንን አንሰብክም

me i.jpgክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡5

ክርስቶስ አዳኝ ነው፡፡ ክርስቶስ ጌታ ነው፡፡ ክርስቶስ ሊያድነን ወደምድር የመጣ ነው፡፡ ክርስቶስ አዳኝ ነው፡፡

እኛ በእርሱ ዳንን እንጂ አዳኝ አይደለንም፡፡ ከእርሱ በቀር እኛ በጎነት የለንም፡፡ እኛ ምንም በጎነት ቢታይብን ምንጩ ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡

እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙር 16፡2

ክርስቶስ በምደር ላይ ያለነው የኢየሰስ ስንም ልንሸከም ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ኢየሱስ ከፍ አድርገን ልናሳይ ነው፡፡

ክርስቶስ ከፍ ብሎ እንዲታይ እኛ ዘቅ እንላለን፡፡ ክርስቶስን እንዳንሸፍን ራሳችንን እናዋርዳለን፡፡

ሰዎች ከሆነው በላይ እንደሆንን እንዳያስቡ በነገር ሁሉ እንጠነቀቃለን፡፡

ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡6

ሰዎች በህይወታችን ስለተገለጠው ፀጋ ሲያነሱ እኛ ደግሞ ሰጪውን እግዚአብሄርን እናነሳለን፡፡ ሰዎች ስለአገልግሎታችን ሲያመሰግኑን እኛ ደግሞ የዚህን ሁሉ ምንጭ ጌታን እናመሰግናለን፡፡

ሰው ራሱን ከሰበከ በምድር ላይ ሊጠቀም ይችላል ነገር ግን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋውን በምድር ተቀብሎዋልና በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ የለውም፡፡

ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። ማቴዎስ 6፡1-2

ክርስቶስን እንዲወክል ተልኮ ራስን እንደመስበክ መሳሳት የለም፡፡ ክርስቶስን ሊሰብክ ተልኮ ራስን እንደመስበክ ኪሳራ የለም፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20

የእኛ የስኬታችን መጨረሻ ሰዎችን ከጌታ ጋር ማገናኘት ነው፡፡ የመጨረሻው ስኬታችን በሰዎች ውስጥ ክርስቶስን መሳል ነው፡፡

በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ገላትያ 3፡1

ለህይወት ሙሉ መፍትሄ ያለው ክርስቶስ በሰዎች ልብ ውስጥ ሲሳል ብቻ ነው የምናርፈው፡፡

ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል። ገላትያ 4፡19

ክርስቶስ በሰዎች ውስጥ መሳሉ የክርስትና ህይወት ግባችን ነው፡፡ ክርስቶስ ነው መፍትሄ ያለው፡፡ ስለዚህ ነው ክርስቶስን እንጂ ራሳችንን የማንሰብከው፡፡

በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ

peace of god.jpgበአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

በምድር ብዙ ድምፅና ማስፈራራት አለ፡፡ አለም አይሆንም አትችልም አይሳካልህም በሚሉ ድምፆች የተሞላች ነች፡፡

አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም ጎሽ ቀጥሉ የእግዚአብሄርን ስራ እየሰራችሁ ነው፡፡ በትክክለኛ መንገድ ላይ ናችሁ ሰላም ነው እንድትለን መጠበቅ የለብንም፡፡ አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም በእኛ ላየ ነው የሚሰራው አንጂ ለእኛ አይደለም የሚሰራው፡፡ ከአለም እንደዚህ አይነትን ማረጋገጫ መጠበቅ ሃዘን ውስጥ ይከታል፡፡

ትክክልኛውንና እውነተኛውን ነገር የምንረዳው ከመንፈሳዊው አለም ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ነገር የምናውቀው በመንፈሳዊው አለም ብቻ ነው፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27

የእግዚአብሄርን ነገር የምንሰማው በልፀባችን ነው፡፡ ከግርግሩ ወጣ ብለን ወደልባችን መልስ ብለንብ ልባችንን የምንሰማበት ጊዜ ሊኖረን ይገባል፡፡ በዚህ መድር ላይ ትክክለኛውን ማረጋገጫ ሎሰጠን የሚችል ብቸኛው ነገር ልባቸነ ነው፡፡

አካባቢያችን በታላቅ ረብሻ ቢሞላም እንኳን ልባችን ሰላም ነው ካለ ሰላም ነው፡፡ አእምሮዋችን በጭንቀት ሃሳብ ቢወጠር እንኳን ልባችን ሰላም ከሆነ ሰላም ነው፡፡

ልባችን ሰላም ከሆነ ሁሉ ሰላም ስለሆነ እርፍ ልንል ይገባናል፡፡ የሚመራን የአለም ጩኸትና ማስፈራራት ሳይሆን ሂዱ ቁሙ እያል የሚመራን የክርስቶስ ሰላም ይሁን፡፡

ስለዚህ ነው ዘማሪ ተከስተ ጌትነት

ውስጤ ስሰማው ሳደምጠው

ሁሉ ሰላም ሰላም ነው

ውጭውን አይቶ ልቤ እንዳይሰጋ

እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ

በማለት የዘመረው፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አእምሮ #መንፈስ #ሰላም #ልብ #አይታወክ #አይፍራ #ጭንቀት #ቅባት #ይግዛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ልብ ይጠይቃል !

insomnia_01_img0053.jpg

 1. ከእኛ የተለየውን ሰው ለመቀበል ልብ ይጠይቃል
  1. ማንም መንገደኛ የሚመስለውንና የሚስማማውን ብቻ ይቀበላል፡፡ የሚወደውን ለመውደድ የሚጠላውን ደግሞ ለመጥላት ብዙ ጥረት አይጠይቅም፡፡ ከእርሱ የተለየውን ሰው ለመጣል ራስ ወዳድነት በቂ ነው፡፡ ከእኛ የተለየውን እንደ አካለ ብልት ለመቁጠርና ከማይመስለን ሰው ጋር ለአንድ ግብ ለመስራት እና እና ሌላውን ለመታገስ ልብ ይጠይቃል፡፡ ደካማ ሰዎች ሁሉንም እሺ የሚሉዋቸውን ፣ የማይጋፈጡዋቸውን ፣ የሚፈሩዋቸውንና እንዲለወጡ የማይገዳደሩዋቸውን ሰዎች በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፡፡ እውነተኛ ሰዎች ሌላ የተደበቀ የስስት አላማ ስለሌላቸው ለመታረም ለመለወጥ ክፍት በመሆናቸው የሚያርሙዋቸውን ከእነርሱ የተለየተ ሃሳብ ያላቸውን እንዲያድጉና እንዲዘረጉ የሚያበረታቱዋቸውን ሰዎች ያከብራሉ፡፡  ሌሎችን የማያምን ራሱን ብቻ የሚያምን ሰው በህይወት እያነሰና እየቆረቆዘ ይሄዳል፡፡ ሁሉንም እንደሚያውቅ ሌላው የተሻለ እንደሚያውቅ የማያስብ ሰው እያነሰ ይሄዳል፡፡ ከእርሱ የተለየውን ሰው ውበት ማየት የሚችልና ሳያሻሽል የሚቀበለው ሰው ግን እየበዛ እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ ከሰው ድካም ባሻገር ጥንካሬንና ውበትን ማየት መቻል ልብ ይጠይቃል፡፡

   የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3

   ዓይን እጅን፦ አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፦ አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡21

   1. ለሌላው ቅድሚያ መስጠትና ለራስ ብቻ አለማሰብ ልብ ይጠይቃል

   ለሌላው ቅድሚያ መስጠት ክብር መሆኑን ማወቅ ትልቅነት ነው፡፡ ለራሱ ብቻ የሚያስብ ሰው ፣ ራሱ ላይ ብቻ የሚሰራ ሰው ፣ ለራሱ ብቻ የሚያከማች ሰው የተፈጠረበትን አላማ ስቶዋል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር መወደዱን ሲያውቅ ሰዎችን ይወዳል ለሰዎች ቅድሚያን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በፍቅር እና በርህራሄ እንደሚያየው የሚያውቅ ስው ሌሎችን በፍቅር ያያል፡፡ እግዚአብሄር አባቱ እንደሆነ የተረዳ ሰው ለሌሎች አባት ይሆናል፡፡ በእግዚአብሄር አባትነት የማይተማመን ሰው ግን የራሱን ፍሎጎት ብቻ ለማሙዋላት ሲደሳክር ዘመኑን ይፈጃል፡፡ የተፈጠረው ለሌላው ሰው በጎነት እንደሆነ ያለተረዳ ሰው ሳያካፋል ያለውን ነገር ሁሉ ራሱ ላይ ብቻ አፍስሶ ህይወቱን በከንቱ ያሳልፋል፡፡

   ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። ፊልጵስዩስ 2፡3-4

   1. በምድር ከፉክክር ነፅቶ እንደ እንግዳ መኖርና በዘላለም እይታ መኖር ልብ ይጠይቃል

   የምድር ፉክክር የአላማ ጠላት ነው፡፡ የምድር ፉክክር በተንኮል ወደህይወታቸን እየገባ ከመንገዳችን የሚያስወጣ የህይወት አላማ ጠር ነው፡፡ የምድር ፉክክር ለእግዚአብሄር ሳይሆን ለሰው እንድንኖር የሚያታለል ክፉ በሽታ ነው፡፡ ይህን የምድር ፉክክር ጥሎ መውጣትና እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን በሰጠን ሃላፊነት ላይ ማተኮር ድፍረት ይጠይቃል፡፡ ማንም ሰው በምድር ፉክክር ውስጥ ገብቶ እንደሰው መሆን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ግን እንደ እግዚአብሄር ልጆች የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን እንድንፈልግ ጠርቶናል፡፡ ሰው ከምድር ፉክክር በራሱ ፈቃድ ካላቋረጠ እግዚአብሄር በህይወቱ ያስቀመጠውን አላማ መፈፀም አይችልም፡፡

   ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ ገላትያ 6፡4

   1. ከራስ አልፎ ለሚቀጥለው ትውልድ ማሰብ ልብ ይጠይቃል

   ማንም ሰው ለዛሬ መኖር ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን የዛሬን ደስታ አዘግይቶ ለሚመጣው ትውልድ መሰረት መጣል የተለየ መንፈስ ይጠይቃል፡፡ ዛሬ እንብላ ነገ እንሞታለን ማለት ቀላል ነው፡፡ የሚመጣው ትውልድ ሸክም በእኔ ትከሻ ላይ ነው ብሎ ለሚመጣው ትውልድ መልካም ምሳሌ ሆኖ ማለፍ ልብ ይጠይቃል፡፡ ከራስ ትውልድ አልፎ የእግዚአብሄርን ቃል ምሳሌነት ለሚመጣው ትውልድ ማድረስ የየእለት ጥረት ይጠይቃል፡፡

   እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡32

   1. አለመጨነቅ ልብ ይጠይቃል፡፡

   መጨነቅ ውጤት የሌለው ነገር ግን ከውጤት የሚያሰናክል ነገር ነው፡፡ እንድንጨነቅ የሚገፋፋ ብዙ ምክኒያቶች እያሉ አለመጨነቅ እምነት ይጠይቃል፡፡ ብዙ ሰዎች ሲጨነቁ ስራ የሰሩ ይመስላቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች መጨነቅ መብታቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች የጭንቀትን ጉዳት አይረዱትይም፡፡ ጭንቀት ማቀድ ይመስላቸዋል፡፡ ጭንቀት ግን ማቀድ አይደለም፡፡ ጭንቀት ማለት ማድረግ የማንችለውን ነገር ለማድረግ መፍጨርጨር ነው፡፡ ጭንቀት ማለት የማናውቅውን ነገር አሁኑኑ ለማወቅ መላላጥ ነው፡፡ ጭንቀት ማለት ቆይተን የምንረዳውን ነገር አሁኑኑ ለመረዳት አእምሮን ማጣበብ ነው፡፡ ጭንቀት ማለት ወደፊታችን ምን እንደሚሆነ ካሁኑ አውቆ ለመጨረስ የመሞከር ከንቱ ድካም ነው፡፡ የሚያስጨንቀንን ነገር ለእኛ በሚያስበው በጌታ ላይ መጣል ልብ ይጠይቃል፡፡

   እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7

   1. አለመፍረድ ልብ ይጠይቃል፡፡

   ማንም መንገደኛ በማንም ላይ ሊፈርድ ይችላል፡፡ አለመፍረድና ይልቁንም ሌላውን መርዳት ልብ ይጠይቃል፡፡ አለመፍረድ ይልቁንም ራስን በሌላ ሰው ቦታ አድርጎ መመልከትና ለሌላው መራራት ልብ ይጠይቃል፡፡ አለመፍረድና ይልቁንም የሰዎችን ስሜት መረዳት ጥረት ይጠይቃል፡፡ አለመፍረድ ይልቁንም ወደሰዎች ደረጃ ወርዶ ማገዝ ምሳሌ መሆን ልብ ይጠይቃል፡፡

   ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ገላትያ 6፡1

   ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ያዕቆብ 4፡11

   1. ጠላትን መውደድ የሚረግሙንን መባረክ ልብ ይጠይቃል፡፡

   በራሱ ሃይል የማይታመን በእግዚአብሄር ብቻ የሚታመን ሰው ነው ጠላቱን የሚወድ፡፡  በእግዚአብሄር ፈራጅነት የሚታመን ሰው ብቻ ነው እራሱ የማይፈርደው፡፡ እግዚአብሄር እንደሚባርክ የተረዳ ሰው ብቻ ነው የሰውን እርግማን ተከትሎ የማይራገም፡፡ አስቀድሞ እንደተባረከ የሚያምን ብቻ ነው ሰውን የማይረግመው፡፡ ለእርሱ መባረክ የሌላው መረገም አንደማያስፈልግ የሚያምን ሰው ብቻ ነው ሰውን የማይራገም፡፡

   ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡9

   እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ማቴዎስ 5፡44-45

   1. ነገሮች ሁሉ በተቃራኒው ሲሰሩ እግዚአብሄርን ማመን ልብ ይጠይቃል፡፡

   በሁኔታዎች ውስጥ ማረጋገጫ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን በሁኔታዎች ውስጥ ማረጋገጫ ሲጠፋና የሚታየው ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ከተናገረን ተቃራኒ ሲሆን እግዚአብሄርን ለማመን ልብ ይጠይቃል፡፡ ሌላው ሰው ሁኔታውን አይቶ እጅ ሲሰጥ ለመቀጠል ልብ ይጠይቃል፡፡

   ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ሮሜ 4፡18-19

   ሰዎች  በፊታቸው እንበጣ ነን ሲል እንደ እንጀራ ይሆኑልናል ማለት ልብ ይጠይቃል፡፡

   ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። ዘኍልቍ 14፡9

   1. ምንም ነገር የማይበቃ በሚመስልበት ያለኝ ይበቃኛል ማለት ልብ ይጠይቃል

   የሰው ፍላጎት አያልቅም፡፡ እኛ ለፍላጎታቸን ገደብ ካላበጀንና በመሰረታዊ ፍላጎታችን ላይ ብቻ ካላተኮርን የማያልቅ ፈላጎታችንን ከማሙዋላት አልፈን እግዚአብሄርን ማገልገል አንችልም፡፡ ሰው ለመሰረታዊ ፍላጎቱ እግዚአብሄርን ካልታመነና ያለኝ ይበቃኛል ካላለ የማያባራውን የሰውን ፍላጎት ማሙዋላት ብቻ የህይወት ዘመን ይጠይቃል፡፡ አህዛብ ሌላ የህይወት አላማ ስለሌላቸው የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ፍላጎታቸው የሚበላና የሚለበስ ነው፡፡ ሰው ያለኝ ይበቃኛል ባለ መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የሚችለው፡፡ ያለኝ አይበቃኝም ባለ መጠን ሁሉ ህይወቱ ይባክናል፡፡

   ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። ፊልጵስዩስ 4፡11

   ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33

   ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

   ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

   #ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፀጋ #ምህረት #ቃል #መባረክ #አገልግሎት #መዋረድ #ፉክክር #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሔር ለምን? የሚለው ጥያቄ ግድ ይለዋል

motives weigh.jpg

እግዚአብሔር ምን እንደምናደርግ ብቻ ሳይሆን ለምን እንደምናደረገው ምክኒያታችንን ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የምንሰራውን ነገር ብቻ ሳይሆን ለምን እንደምንሰራው ግድ ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ንግግራችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ይመዝናል፡፡ እግዚአብሔር ድርጊታችንን ብቻ ሳይሆን ለድርጊቱ ያነሳሳንን ነገር ያያል፡፡

አንድን ነገር ስናደርግ በትህትና ይሁን በትእቢት እንዳደረግነው እግዚአብሔር የልባችንን ሃሳብ ይመዝናል፡፡ ስለዚህ ነው ሰዎች ትእቢተኛ ያሉትን ኢየሱስን እግዚአብሔር በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ እርሱ ነው እርሱን ነው እርሱን ስሙት ያለው፡፡ (ማቴዎስ 3፡17) ለዚህም ነው መልካም የመሰለን የሰው ሃሳብ ያመጣው ጴጥሮስ አንተ ሰይጣን ተብሎ በኢየሱስ የተገሰፀው፡፡ (ማቴዎስ 16፡23)

ገንዘባችንን ስንሰጥ ለምን እንደሰጠን አግዚአብሔር ልባችንን ይመዝናል፡፡ ገንዘባቸውን ለታይታ ፣ ሰዎችን ጉድ ለማሰኘትና ከሰው ክብርን ለማግኘት የሚሰጡትን ፈሪሳዊያን ልባቸውን እንዲያጠሩ ኢየሱስ አስተምሮዋልል፡፡

ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። ማቴዎስ 6፡1

በሰዎች ፊት ቅዱስ ሃሳብ የሚባል ሃይማኖታዊ ነገር እንኳን ስናደርግ እግዚአብሔር ግን ለምን እንዳደረግነው ልባችንን ይመዝናል፡፡

ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። ማቴዎስ 23፡5-7

ለእግዚአብሔር ብለን የምናደርገውን ነገር እግዚአብሔር ይመዝነዋል፡፡ ለታይታ ወይም በፉክክር ያደረግነው ነገር እግዚአብሔር በእሺታ አይቀበለውም፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ኤፌሶን 6፡6-7

ምንም ያህል መልካም ነገር ቢሆን በፍቅር ያልተደረገ ነገር ከንቱ ነው ምንም አይጠቅመንም፡፡ ከፍቅር ውጭ ያለ መነሻ ሃሳብ ከንቱ ነው፡፡ በጥላቻ በፉክክር በትእቢት ከማን አንሼ በማለት የተደረገ ምንም መልካም ነገር ፍሬ ቢስ ከንቱ ድካም ነው፡፡

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡1-3

በመጨረሻም ምን ሰራን ብቻ ሳይሆን ለምን ሰራነው የሚለውም ይፈተናል፡፡ እግዚአብሔር ምን ሰራን ከሚለው ያለነሰ ለምን ሰራነው የሚለው ግድ ይለዋል፡፡

ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡12-15

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ሃሳብ #መነሻሃሳብ #ልብ #ንፁህ #ፍቅር #ፉክክር #ቃል #ክብር #የእግዚአብሔርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የልብ ስፋት ጥቅሞች

medications-shouldn-t-taken-enlarged-heart_af7ec0871b39cb3.jpgእግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። 1ኛ ነገሥት 4፡29

በህይወቴ እንዲኖረኝና ይበልጥ እንዲኖረኝ የምፈልገው የልብ ስፋት ነው፡፡

የልብ ስፋት ግን ለምን አስፈለገ

 1. ከልባችን ስፋት በላይ በምንም ነገር መስፋት ስለማንችል ነው፡፡

አገልግሎታችን እንዲበዛ ያለንን አገልግሎት የሚይዝ ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡ ሃብታችን እንዲበዛ ያንን ማስተዳደር ብቃት ያለው ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡ አሁን የደረስንበት ደረጃ የልባችን ስፋት ደረጃ ነው፡፡ ምንም ብንመኝ ከልባችን ስፋት ደረጃ በላይ አናድግም፡፡ እያንዳንዱን ሰው እንደ አቅሙ ይዘን ከእያንዳንዱ ውስጥ የተሻለ ነገር ለማውጣት ሰፊ ልብ ይጠይቃል፡፡ ሃላፊነታቸን መብዛት ካለበት ልባችን መጀመሪያ መስፋት አለበት፡፡

ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ማቴዎስ 25፡15

 1. ሰዎች የተለያዩ ስለሆኑ ነው፡፡

ሰዎች ሁሉ እኛን አይመስሉም፡፡ እኛን ደረጃ መዳቢ አድርገንም ሌላው ሰው ሁሉ ራሱን ትቶ እኛን እንዲመስል ከፈለግን አይቻልም፡፡ ይልቁንም ሁሉንም ሰው እንደ ደረጃውና እንደዝንባሌው መረዳትና መቀበል የሚችል ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡

ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡30-31

 1. ሰፊ ልብ የሚጠይቀው ሁኔታዎች ስለሚለዋወጡ ነው፡፡

ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡ አሁን እናገኛለን ሌላ ጊዜ አናገኝም፡፡ አሁን እናተርፋለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ልንከስር እንችላለን፡፡ ይህ እኔ ላይ አይሆንም ያለነው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን አንወጣለን ሌላ ጊዜ ደግሞ እንወርዳለን፡፡ ይህንን ተለዋዋጭ አለም ተቋቁመን ማለፍ የምንችለው በሰፊ ልብ ብቻ ነው፡፡ ሰፊ ልብ ከሌለን ከደረሰበን ነገር አንፃር እንደገና መኖር ሊያስፈራን ይችላል፡፡

ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡4-6

 1. ሰፊ ልብ ያስፈለገው ሰዎች ስለሚለወጡ ነው፡፡

ሰዎች በተለያየ ምክኒያት ይለወጣሉ፡፡ አይክዱንም ያልናቸው ሰዎች ሊክዱን ይችላሉ፡፡ ሰፊ ልብ ከሌለን ተመልሰን ሌላ ሰውን ማመን ያቅተናል፡፡ ሰውን ካላመንን ደግሞ ውስን እንሆናለን፡፡ የሌሎችን ህይወት መቆጣጠር አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለ ነገር ልባችንን ማስፋት ብቻ ነው፡፡

ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ? ኤርምያስ 12፡5

 1. ሰፊ ልብ ያስፈለገው እውቀት ሁሉ ስለሌለን ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የምናውቀውን እውቀት ሁሉ ወደጎን አድርገን ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ላይ መታመን ይገባናል፡፡ በሚያውቁት እውቀት ለመሄድ ሰፊ አእምሮ ሲጠይቅ በማይገባንና በማንረዳው መንገድ ለመሄድ ሰፊ ልብ ይጠይቃል፡፡

አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ዕብራውያን 11፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ልብ #ዋጋ # #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሄር ልብን አይቶ ያደላል

heart.jpgእግዚአብሄር የሰውን ፊትን አይቶ አያዳላም፡፡ የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት እግዚአብሄር ሰውን በውጫዊ ነገር በአነጋገሩንና በአለባበሱ አይመዝንም ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ንጉስን ሊመርጥ ሲል ለንጉስነት የሚቀባው ነቢይ የሰውን ፊት ያይ ስለነበረ ቁመታቸው ዘለግ ያለውን ሰዎች ለንጉስንት ሊቀባ ነበር፡፡

እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 16፡6-7

እግዚአብሄር ሰው እንደሚያይ አያይም ፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ በውጭ በሚያየው ውስን ይሆናል፡፡ ሰው ማየት የሚችለው ፊትን ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችልው የውጫዊውን ገፅታ ነው፡፡ ሰው ማየት የሚችለው የሰውን ልብስ እና የሚነዳውን መኪና ነው፡፡ ሰው ሰውን የሚመዝነው በውጫዊ ማየት በሚችልው በውጫዊ ነገር ብቻ ነው፡፡

ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ። ሐዋርያት 10፡34-35

ሰው እንደሚያይ እግዚአብሄር አያይም፡፡ እግዚአብሄር የሰው መመዘኛ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ከልብስና ከውጫዊ ገፅታ ባሻገር የሰውን ዋናውን ነገር ልብን ማየት ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰው ያከበረውን እግዚአብሄር ሊንቀው ይችላል፡፡ ሰው የናቀውን ደግሞ እግዚአብሄር ሊያከብረው ይችላል፡፡

እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና። ሮሜ 2፡11

እውነት ነው እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ ይህ ማለት ግን እግዚአብሄር አይመዝንም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም ማለት ግን እግዚአብሄር መመዘኛ የለውም ማለት አይደለም፡፡

እግዚአብሄር የራሱ መመዘኛ አለው፡፡ የእግዚአብሄር መመዘኛ እንደ ሰው መመዘኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፊትን እይቶ አያዳላም እንጂ እግዚአብሄር ግን የራሱ ምርጫ አለው፡፡ እግዚአብሄር ይመርጣል፡፡ እግዚአብሄር የሚመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር የማይመርጠው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው ስው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የማያስደስተው ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያዘነብላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው አያዘነብልም፡፡ እግዚአብሄር ወደ አንዱ ያደላል እግዚአብሄር ወደ ሌላው ደግሞ አያደላም፡፡ እግዚአብሄር ግን ያደላል፡፡

እግዚአብሄር ፊትን አይቶ አያዳላም እንጂ ልብን አይቶ ግን ያደላል፡፡ እግዚአብሄር የሰው ልብ ይማርከዋል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ልብ ይመዝናል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የልብ አይነት አለ፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4

እግዚአብሄር ልብን አይቶ ማድላት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፍፁም ልብ ባለው ሰው ህይወት ሃይሉን ለመግለጥ ፈልጎ አይኖቹ በምድር ላይ ይመላለሳሉ፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። 2ኛ ዜና 16፡9

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሚለው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 3፡5፣ 4፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ልብ #ዋጋ # #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ታላቅ ሊሆን የሚወድ

jesus 2.jpgሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል። ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።  ማቴዎስ 23፡10-12

ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ማቴዎስ 20፡25-26

በወደቀው አለም ስርአት ስልጣን መጠቀሚያ መንገድ ነው፡፡ ስልጣን መያዝ መታደል ነው፡፡ ስልጣን ጥቅም ነው፡፡ ስልጣን ያለውን ሰው ሰዎች ያገለግሉታል፡፡ ሰው ስልጣኑ ሲበዛ የሚያገለግሉት ይበዛሉ፡፡ ሰው ስልጣኑ ከፍ ሲል ጥቅሙም ከፍ ይላል፡፡

ስለዚህ ሰው የሚጋደለው ያለውን ሁሉ ተጠቅሞ ስልጣኑን ፣ ዝናውንና ተሰሚነቱን ለመጨመር ነው፡፡ ዝናው በጨመረ ቁጥር በቀላሉ መጠቀም ይችላል፡፡ ተሰሚነቱ በጨመረ ቁጥር የሰዎችን አእምሮ አላግባብ በመቆጣጠር ጥቅሙን ያበዛል፡፡ መፈራቱ በጨመረ ቁጥር ሰዎች ይንበረከኩለታል፡፡ መፈራቱ በጨመረ ቁጥረ የሚከራከረው ሳይኖር ሰዎች ይነጠቁለታል፡፡ መፈራቱ በጨመረ ቁጥር የሰዎችን አእምሮ በመቆጣጠር የፈለገውን ያስወጣቸዋል፡፡ መፈራቱ በጨመረ ቁጥር ሰዎችን በማዋከብ ይነጥቃቸዋል፡፡

ስለዚህ ነው በአለም ስርአት ተናጋሪ ሰው ይጠቀማል፡፡ ተናጋሪ ሰው ሰዎችን ወደፈለገበት መንገድ ይመራል፡፡ ተናጋሪ ሰው ሰዎችን ያስከትላል፡፡ ተናጋሪ ሰው በሰዎች ይጠቀማል፡፡ በመናገር ችሎታው ሰዎችን መጠቀሚያ ያደርጋቸዋል፡፡

በአለም ስርአት ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ከሰዎች የስልጣናቸውን ደረጃ ለማሳየት የሚነዱትን መኪና ደረጃ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ከሰዎች እንደ አንዱ አለመሆናቸውን ለማፅናት ብቻ የማያስፈልጋቸው ትልልቅ ቤት ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከሰዎች እጅግ ከፍ ብለው ለመታየት ታላላቅ ስም ለራሳቸው ይሰጣሉ፡፡ ከሰው እጅግ ከፍ ማለታቸውን ለማሳየት እጅግ ውድ ልብስ ይለብሳሉ፡፡ ታላቅ የሆነውን የስልጣን ክንዳቸውን ለማሳየት በታላላቅ ሰዎች ይከበባሉ፡፡ ከሰዎች ጋር ላለመቀላቀል የሚቀመጡበትን ቦታ እንኳን ይለያሉ፡፡

ይህ ሁሉ መልክት አለው፡፡ መልዕክቱ እኔ እጅግ ከፍ ያልኩ ሰው በመሆኔ አንደሌላ ሰው አትዩኝ ነው፡፡ መልክቱ እኔ እጅግ የከበርኩ በመሆኔ እንደሌላ ሰው አትስጡኝ ነው፡፡ መልክቱ እኔ እጅግ የከበርኩ ስለሆንከ እንደሌላ ሰው አትያዙኝ ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች የመበለቶችን ቤት ለመበዝበዝ ፀሎታቸውን ያስረዝማሉ፡፡ ፀሎታቸው በረዘመ ቁጥር “አንቺ መበለት ሆይ መንፈሳዊ ነገር ከባድ ነው፡፡ እኔ እንዴት እየደከምኩ እንደሆነ ተመልከቺ፡፡ ስጦታዬ እንዴት እንደከበረ ማየት ትችያለሽ፡፡ እኔ እንዴት እጅግ የከበርኩ ታላቅ ሰው እንደሆንኩ ተመልከቺ፡፡ ጌታ ጋር ለመግባት ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀብኝ ተመልከቺ፡፡ ስለዚህ ያሰብሸውን ያንን ስጦታ ወዲያ በዪና አራት እጥፍ አድርጊው፡፡ ” የሚል መልክት በፀሎታቸው ርዝማኔ ያስተላልፋሉ፡፡ አንዳንዶቹ በንግግራቸው ልቀት ይህንንኑ መለክት ያስተላልፋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የኑሮ ዘይቤያቸው ያንንኑ ይናገራል፡፡

ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ አለ። ሉቃስ 20፡46-47

ኢየሱስ ግን የሚያስተምረው ያለን ነገር ሁሉ ሰዎችን ለማገልገል የተሰጠን ነገር እንደሆነ ነው፡፡ እንዲያውም ክብራችን የተፈጠርንበትን አላማ አገልግሎትን ሰዎችን መጥቀም ሰዎችን ማንሳት ለሰዎች ማድረግ ነው፡፡ ጥሪያችን ሰዎችን የማገልገል ሃላፊነታችንን መወጣት ነው፡፡ ጥሪያችን በስልጣናችን ተጠቅመን ሰዎችን ማራቆት ሳይሆን ለሰዎች በጎነት መስራት ነው፡፡ ጥሪያችን በአንደበተ ርቱእነታችን ተጠቅመን ለደሃ መሟገት ነው፡፡ ጥሪያችን ዝናችንን ተጠቅመን ሰዎችን መፈወስ ነው፡፡ ጥሪያችን ስልጣናችንን ተጠቅመን ሰዎችን መባረክ ነው፡፡ ክብራችን ከእግዚአብሄር ብቻ እየጠበቅን ሰዎች ላይ ጫና ሳንፈጥር ማገልገል ነው፡፡

ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡10

በክርስትና ያለው ውድድር የስልጣን ፣ የዝናና የሃብት ሳይሆን የአገልግሎት ውደድር ነው፡፡ አንዱ ካንዱ እንደሚበልጥ የሚያሳየው ከህዝብ ጥቅምን ሳይጠብቅ ለሰዎች በመድከሙ ፣ በመልፋቱና በመጥቀሙ ነው፡፡ በክርስትና ውድድሩ እንደፈሪሳዊያን ዋጋን በምድር ሳይቀበሉ በቸርነት ለእግዚአብሄር ህዝብ መኖር ፣ ያለንን ለህዝቡ ማካፈል ፣ ህዝቡን በትህትና መጥቀም መባረከ ነው፡፡ ስልጣን ሰዎችን የማገልገል የመጥቀም የማንሳት ሃላፊነት እንጂ በሰዎች የመጠቀሚያ መሳሪያ አይደለም፡፡

 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: