Category Archives: Uncategorized

ሁልጊዜ የፀሎት መልሳችንን የምንቀበልባቸው አምስቱ ጥበቦች

your will11.jpg

ከልባችን የፀለይናቸው ፀሎቶች ሁሉ ተመልሰዋል፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7

የሚለምነውም ሁሉ ይቀበላል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር መንገድ እንጂ በእኛ መንገድ አንቀበልም፡፡ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ጊዜ እንጂ በእኛ ጊዜ አናገኝም፡፡ ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትልን በእኛ ሁኔታ ሳይሆን በእግዚአብሄር ሁኔታ ነው፡፡

የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡8

 1. እግዚአብሄር የፀሎት መልሳችንን በእርግጥ ይመልሳል፡፡ እግዚአብሄር የፀሎት መልሳችንን በችኮላ አይመልስም፡፡ እግዚአብሄር ፀሎታችንን በጊዜው እንጂ በችኮላ አይመስለስም፡፡ እግዚአብሄር ማንም አይቀድመውም፡፡ እግዚአብሄር ጊዜ አያልፍበትም፡፡ እግዚአብሄር ከአላማው ጋር እንጂ ከጊዜ ጋር አይሮጥም፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን ነገር ስለሚያይ እኛ እንደምንቸኩል አይቸኩልም፡፡ እግዚአብሄር እኛ በቸኮልንበት ጊዜ የፀሎት መልሳችንን በችኮላ ስላልመለሰ ያልተመለሰ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን የሚለምነው ሁሉ በጊዜውና በሰአቱ በእግዚአብሄር መንገድ ይቀበላል፡፡

ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? የሉቃስ ወንጌል 18፡1፣7፣8

 1. የፀሎት ምለሳችን ሁሉ ይመጣል፡፡ ነገር ግን የፀሎት መልሳችን በጣም በጓጓን ጊዜ ላይመለስ ይችላል፡፡ ለፀሎት መልሳችን በጣም መጓጓት አይናችንን ከእግዚአብሄር ላይ አንስተን የፀሎት መልሳችን ላይ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ ለፀሎት መልሳችን በጣም መጓጓት የፀሎት መልሳችንን ጣኦት እንድናደርገው ያደርገናል፡፡ ለእግዚአብሄር የፀሎት መልሳችንን ለመመለስ ትክክለኛው ጊዜ ከመጠን ያለፈ መጓጓታችን ሲበርድልን ነው፡፡ እግዚአብሄር አንዳንዴ ፀሎታችንን የሚመልሰው ከመጠን ያለፈ ጉጉታችንን ከጨረስን በኃላ ነው፡፡ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላል ነገር ግን የለመንነውን ሁሉ ከመጠን በላይ በጓጓን ጊዜ አንቀበልም፡፡ ከመጠን በላይ መጓጓት የፀሎት መልሳችንን እንደሚገባ እንዳንይዘው ያደርገናል፡፡ ለፀሎት መልሳችን ከመጠን ያለፈ መጓጓት የፀሎት መልሳችንን እንድናመልከው ይፈትነናል፡፡
 2. የፀሎት መልሳችን በቅንጦት አይመለስም፡፡ እግዚአብሄር የሚያቀርበው እንደፍላጎታችን መጠን ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ፍላጎት ባለብን የህይታችን ክፍል በብዙ እንቀበላለን፡፡ ብዙ ፍላጎት በሌለን በህይወታችን ክፍል በብዙ አንቀበልምን፡፡ ብዙ ፍላጎት ላለበት ሰው እግዚአብሄር በብዙ ያቀርብለታል፡፡ ጥቂት ፍላጎት ላለለው ሰው በብዙ አያቀርብም፡፡ እግዚአብሄር በብዙ ካቀረበለን አሁንም ባይሆን ወደፊት ብዙ ፍላጎት እየመጣ ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከላቀረበ ፍላጎት የለብንም ማለት ነው ብለን ማመን እና እግዚአብሄርን ማመስገን አለብን፡፡ ቀድሞ እንኳን ብዙ ካቀረበ ብዙ ፍላጎት እየመጣ ነው ብለን ለወደፊት ማስቀመጥ እንጂ ሁሉንም አቅርቦት በምቾቶቻችን መክፈል ወይም በቅንጦት ላይ ማዋል የለብንም፡፡

ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። የያዕቆብ መልእክት 4፡3

 1. የፀሎት መልሳችን ሞቲቫችን ሲጣራ ይመልሳል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንፀልይ በሁለት መነሻ ሃሳቦች እንፀልያለን፡፡ አንዱ በፀሎት መልሳችን እግዚአብሄርን የማክበር ንፁህ የልብ መነሻ ሃሳብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ከሌላው ሰው መብለጥ ታዋቂ መሆን ባለጠጋ መሆን ወይም ደግሞ ከሰው ሁሉ በልጦ ሃያል መሆን ነው፡፡ እግዚአብሄር የፀሎት መልሳችንን በእኛ ጊዜ ሳይሆን በራሱ ጊዜ ሲመልስ ንፁህ ያልሆነው የልባችን መነሻ ሃሳብ ከቀነሰ በኃላ ነው፡፡ ስጋችን የፀሎት መልሳችን እንዲመልስ የሚፈልገው ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም ሳይሆን ለራሱ ምቾት ነው፡፡ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል ነገር ግን ብዙ ጊዜ የፈለግነውን ሁሉ እንዳለገኘን የሚሰማን የስጋ መነሻ ሃሳባችን ከጠፋ በኃላ የጸሎት መልሳችን ስለሚመለስ ነው፡፡

ሃና ልጅ የምትፈልገው የልብዋ መነሻ ሃሳብ ለእግዚአብሄር መልሳ ለመስጠት ሲሆን እግዚአብሄር መለሰላት፡፡

እርስዋም፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1፡11

 1. የፀሎት መልሳችን ካደግን በኃላ ይመለሳል፡፡ ክርስቶስን የምንከተል ሁላችንም በየቀኑ እያደግን ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፀሎት መልሳችን እንዳልተመለሰ የሚሰማን ከፀሎት ጥያቄው አልፈን ወደሌላ የፀሎት ጥያቄ ውስጥ ከገባን በኃላ ስለሚመለስ ነው፡፡ እኛ ህይወታችን አድጎና የፀሎት ጥያቄያችን አድጎ ወደሌላ ከፍ ወዳለ የፀሎት ጥያቄ ውስጥ ከገባን በኃላ የበፊቱ የፀሎት መልሳችን ስለሚመጣ ያልተመለሰ ይመስለናል፡፡ የሚፈልገውም ያገኛል፡፡ የቀድሞውን የፀሎት ርእሳችንን አልፈን ሌላ ነገር በመፈለግ ላይ ስለተጠመድን የመጀመሪያውን የፀሎት መልስ ያገኘን አይመስለንም፡፡

አብዝተን እንድንቀበል አብዝተን እንለምን፡፡ መቼ እንደምናገኝ ሳናስብ አብዝተን እንፈልግ፡፡ እንዴት እንደሚከፈት ሳንጨነቅው አብዝተን አናንኳኳ፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ለምኑ #ፈልጉ #አንኳኩ #ይቀበላል #ያገኛል #ይከፈትለታል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

ህይወታችን እንዳልተለወጠ ሲሰማን ማድረግ ያለብን 5 ነገሮች

plant-growing-v2 (2).png

ሁላችንን በየጊዜው ህይወታችን እንደቆመ እንደሚገባው እንዳልተራመድን እያደግን እየተለወጥን እንዳይደለ ይሰማናል፡፡ የእስራኤል ህዝብ በእግዚአብሄር ላይ እልከኛ በመሆንና ባለመታዘዝ አርባ አመት ሙሉ አንድን ተራራ ሲዞሩ ኖረዋል፡፡ እኛም በተለያየ ጊዜ እንደ እስራኤላዊያን የሴይርን ተራራ እንደምንዞር ፣ ህይወታችን ለውጥ አልባ እንደሆነና ህይወታችን እርምጃ እንደሌለው ሲሰማን ማድረግ ያለብን 5 ነገሮች

 1. በጌታ ፊት ጊዜ መውሰድ

እርምጃችን በእውነት መቆሙን ለማረጋገጥ በጌታ ፊት ጊዜ መውሰድ ይጠይቃል፡፡ እርምጃችን እንደቆመ መሰማቱ ብቻ እርምጃችን በእውነትም መቆምሙን ሊያረጋጋጥ አይችልም፡፡ እርምጃችን እንደቆመ መሰማቱ መቆማችንን ሊያሳይ ወይም ደግሞ ላያሳይ ይችላል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን እርምጃ ማጣት ሲሰማን እውነት እድገቴ ቆሟል ወይስ አልቆመመ ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ያለመራመድ ፣ ያለማደግና ያለመለወጥ ስሜት በሚሰማን ጊዜ የእግዚአብሄርን ፊት መፈለግፍ ወርቃማ አጋጣሚ ነው፡፡ እርምጃችን እንደቆመ ሲሰማን እግዚአብሄር ትኩረታችን ፈልጎና ከእኛ ጋር ህብረትን ለማድረግ ናፍቆን ሊሆን ይችላል፡፡ እርምጃችን እንደቆመ ሲሰማን እርሱን በግል እንድንፈልገው ፈልጎ ሊሆን ይችላል፡፡ እርምጃችን እንደቆመ ሲሰማን እግዚአብሄር ወደሚቀጥለው የህይወታችን ምእራፍ ሊያሻግረን መለወጥ ያለብንን ነገር እንድንለውጥ ፈልጎ ሊሆን ይችላል፡፡ እርምጃችን እንደቆመ ሲሰማን እግዚአብሄር የነበርንበት የህይወት ምእራፍ በመዝጋት ስለሚቀጥለው የህይወት ምእራፍ እርሱን እንድንፈልገውና ምሪትን እንድንቀበል ምልክት እየሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11-13

 1. በእግዚአብሄር ቃል ራሳችንን ማየት

መራመድ እንዳቆምን የተሰማን እውነትም እድገታችን ቆሞ ሊሆን ይችላል፡፡ እድገትን ሊያቆም የሚችለውና ከእግዚአብሄር ጋር ያለንንን ግንኙነት እና ህብረት የሚያበላሸው ሃጢያት እና አለመታዘዘ ነው፡፡ እግዚአብሄር የመራንን መሪት ሳንከተል ሌላ ምሪትይ እንዲሰጠን መፈለግ አንችልም፡፡ እግዚአብሄር ያዘዝንን ትእዛዘ በእምነት ሳንፈፅጽም ህይወታችን እንዲለወጥ መጠበቅ የለብንም፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክለውን እምነታችንን ሳንጠቀም እምነት እንዲጨምርልን መፀለይና እምነት እንዳልጨመርን ሊሰማን አይገባም፡፡

ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 17፡5-6

እግዚአብሄር ያስረዳንን የእግዚአብሄርን ቃል ወተት መረዳት ሳንታዘዝ ጠንካራ ምግብ ለመመገብ መሞከር አይቻልም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ልባችንን በመፈተሽና እርምጃችንን በእግዚአብሄር ቃል በመመርመር እየተራመድን ከሆነ ቆመን ከሆነ እግዚአብሄርን በማመስገን በዚያው መቀጠል ይገባናል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ራሳችንን ስንፈትሽ የሳትነው ነገር ካለ በእግዚአብሄር ፊት ሃሳባችንን ለውጠን የእግዚአብሄርን ቃል ለመታዘዝ መወሰን አለብን፡፡

ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። የያዕቆብ መልእክት 1፡22

 1. የእግዚአብሄርን እርምጃ መታገስ

እርምጃችን እንደቆመ እና ህይወታችን እንዳልተለወጠ ሲሰማን ስለእግዚአብሄር አሰራር ያለንን አመለካከት መፈተሽ አለብን፡፡ እግዚአብሄር አይቸኩልም፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። መጽሐፈ ምሳሌ 28፡20

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። መጽሐፈ ምሳሌ 13፡11

እግዚአብሄር ነገሮችን የሚያደርገው በራሱ ጊዜ እንጂ በእኛ ጊዜ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ነገሮችን ውብ የሚያደርገው በጊዜው ነው፡፡

ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ መጽሐፈ መክብብ 3፡1፣11

ከእኛ የሚጠበቀው በጊዜው መልካም ማድረግ ፣ መልካምን በማድረግ አለመታከትና እንዲሁም መታገስና መጠበቅ ነው፡፡

ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡9

የእግዚአብሄር ፈቃድን ካደረግን በኃላ እንኳን የተሰጠንን የተስፋ ቃል እስክናገኝ መፅናት አለብን፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድን ስላደረግን ብቻ እግዚአብሄር ነገሮች ከመቀፅበት ይሆኑልናል ብለን ካሰብን እንሳሳታለን፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ወደ ዕብራውያን 10፡36

 1. ስለደረስንበት ደረጃ እግዚአብሄርን ማመስገን

ብዙ ጊዜ ህይወታችን እድገት እንደሌለው የሚሰማን ልንሄድበት የምንፈልገውንና ያለንበትን ደረጃ ስናነፃፅር ብቻ ነው፡፡ እውነት ነው የምንሄድበትንና ያለንበትን ማነፃፀር መልካም እና አስፈላጊም ነው፡፡  ነገር ግን የመጣንበትንና ያለንበትን ስናስተያይ ደግሞ ምን ያህል ህይወታችን እንደተለወጠ እናስተውላለን፡፡ ቀድሞ የነበርንበትንና አሁን ያለንበትን ስናስተያይ አሁን እየኖርነው ያለነው ህልማችንን እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ የነበርንበትንና ያለንበትን ደረጃ ስናነፃፅር አሁን ያለንበትን ደረጃ ከጊዜ በፊት ሊደረስበት የማይችል የመሰለን እንደተራራ የገዘፈብን የህይወት ደረጃ እንደነበረ እናስተውላለን፡፡

ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡17-18

 1. እየታዘዝነው ያለውን የእግዚአብሄርን ቃል በመታዘዝ መቀጠል

ህይወታችን ካለ እድገት እንደቆመ ሲሰማን እየታዘዝነው ያለውን የእግዚአብሄርን ቃል በመታዘዝ መቀጠል ይኖርብናል፡፡ እድገት የሚመጣው ጥቃቅን የሚመስሉ የእለት ተእለት ተደጋጋሚ ነገሮችን በፅናት በማድረግ ነው፡፡ እውነተኛ እድገት የሚመጣው ከውስጥ ወደ ውጭ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ከሰማን ከታዘዝንና ከፀናንበት እድገትና ለውጥ የማይቀር ነገር ነው፡፡

በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። የሉቃስ ወንጌል 8፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ፅናት #መጠበቅ #ምስጋና ##ሃሳብ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ንስሃ #መለወጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አእምሮ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

It is complicated

your will11.jpg

Life isn’t always black and white. If life is black and white, we wouldn’t have to fight to succeed.

Life isn’t simple. It is foolish to try to give a simple answer to complicated life questions. It is not possible to give a simple solution to a complex life situation.

Life takes a lot of wisdom and understanding solving its problems.

The reason we have been equipped with the manifold wisdom of God is that life problems take a pearl of variety wisdom to solve them.

His intent was that now, through the church, the manifold wisdom of God should be made known to the rulers and authorities in the heavenly realms, Ephesians 3:10

That was the exact reason that Jesus was not only having wisdom but also grew in having more wisdom. Jesus had to become wiser to solve more complicated problems.

And Jesus grew in wisdom and stature, and in favor with God and man. Luke 2:52

That is the reason that we don’t just need wisdom but wisdom abundantly.

If any of you lacks wisdom, you should ask God, who gives generously to all without finding fault, and it will be given to you. James 1:5

Some of the life’s problem is solved by prayer, the others by being patience, the other by loving others, the others by forgiveness, and the others by being contented etc.

There is no one size fits all solution to every life problems. Life isn’t a single battlefield. Life has many battlefields. Wining in one and losing on the other isn’t really wining. It takes to win in each and every life battlefields to win.

Any challenge that isn’t be dealt with one kind of wisdom will be dealt with the other kind of wisdom. But there is wisdom somewhere that can solve the problem we are facing.

The LORD said to him, “Go, return on your way to the wilderness of Damascus, and when you have arrived, you shall anoint Hazael king over Aram; 16and Jehu the son of Nimshi you shall anoint king over Israel; and Elisha the son of Shaphat of Abel-meholah you shall anoint as prophet in your place. “It shall come about, the one who escapes from the sword of Hazael, Jehu shall put to death, and the one who escapes from the sword of Jehu, Elisha shall put to death. 1 Kings 19:15-17

Les’t come to the Lord in prayer to have manifold wisdom of God.

That is the reason that we don’t just need wisdom but abundant wisdom.

If any of you lacks wisdom, you should ask God, who gives generously to all without finding fault, and it will be given to you. James 1:5

For more articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#Christian #prayer #wisdom #Jesus #Church #Lord # inspired #Amharic # sermon #steward of the # bible # Faith # Hope # Love # #peace #abiywakuma #abiywakumadinsa #Politics

19ኙ የጥበብ ጉድለት አደጋዎች

jacar1.jpg

የህይወት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ አላቸው፡፡ መልስ የሌለው ጥያቄ መፍትሄ የሌለው ችግር መውጫ የሌለው ፈተና የለም፡፡ የሚያስፈልገን ጥበብ ነው፡፡ ጥበበ ከጎደለን ግን በህይወታችን ለእነዚህ አደጋዎች እንጋለጣለን፡፡

ጥበብ በጎደለን መጠን የህይወት አደጋችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። የያዕቆብ መልእክት 1፡5

 1. የጥበብ ጉድለት ያለንን ነገር ሁሉ ለማይረባና ለማያጠግብ እንጀራ እንድናውለው ያደርገናል፡፡ ጥበብ ሲጎድለን የዋጋ አሰጣጣችን ይዛባል፡፡ ጥበብ ሲጎድለን የከበረውን ከተዋረደው መለየት ያቅተናል፡፡ ጥበብ ሲጎድለን ዋጋ ለሌለው ዋጋ እንሰጣለን ለከበረው የሚገባውን ክብር እንሰጥም፡፡

ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡2

 1. የጥበብ መጉደል ከእኛ የተለዩ ሰዎችን ባለመቀበልና በመግፋት የአካላችንን አንዱን እንድንጥል ያደርገናል፡፡

እግዚአብሄር ወደ አየልን የህይወት አላማ እንድንደርስ የሚረዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡ የህይወታችን መፍትሄ ሁሉ እኛ ውስጥ የለም፡፡ እግዚአብሄር ለህይወታችን የሚያስፈልገውን እኛ ውስጥ ግን የሌለውን ነገር ሁሉ ያስቀመጠው በሌሎች ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በሌሎች ውስጥ ለእኛ ያስቀመጠውን በረከት መጠቀንም የምንችለው ከእኛ የተለዩትን ሰዎች ለመለወጥ ባለመሞከር ነው፡፡ እግዚአብሄር በሌሎች ውስጥ ለእኛ ያስቀመጠውን በረከት መጠቀንም የምንችለው ሌሎችን በጥበብ መያዝ ስንችል ብቻ ነው፡፡

አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡17-18

 1. ጥበብ መጉደል ሁሉንም ሰው በአንድ አይን እንድንመለከትና የሰውን ልዩነት ተረድተን እንደ እያንዳንዳንዱ ሰው ጥንካሬ እና ድካም እንዳንይዘው እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ ከሁሉም ሰው ተመሳሳይ ነገር ከጠበቅን እንሳሳታለን፡፡ ሁሉንም ሰው ተመሳሳይ ለማድረግ ከሞከርን እኛ ውስጥ የሌለውን የሰዎችን ልዩ ስጦታ እንገድላለን፡፡

እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡7

 1. የጥበብ ጉድለት ለፈጠረን ለእግዚአብሄር የሚገባውን የክብር ስፍራ እንዳንሰጥ ያደርገናል፡፡ የጥበብ መጉደል ከፈጠረን ከእግዚአብሄር ጋር እንዴት እንድምንኖር እንዳናውቅ ያደርገናል፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡7

 1. ጥበብ ሲጎድለን ለህጉ ዋና ነገር የሚገባውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያደርገናል፡፡ ጥበብ ሲጎድለን ህይወት የሚሰጠውን የህጉን መንፈስ ትተን የህጉን ፊደል እንድንከተል ያደርገናል፡፡

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር። የማቴዎስ ወንጌል 23፡23

 1. የጥበብ መጉደል ለገንዘብና ለቁሳቁስ የማይገባውን ክብር እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ የጥበብ መጉደል ለገንዘብ ካለአቅሙ ከፍተኛ ግምት እንድንሰጥና ለገንዘብ እንድንጎመጅ ያደርገናል፡፡

የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው። የሉቃስ ወንጌል 12፡15

 1. የጥበብ መጉደል የህይወት ቁልፍ ያለው ሃያል ባለጠጋ እና ጥበበኛ ጋር እንደሆነ በማሳመን ያሳስተናል፡፡ የጥበብ መጉደል ትኩረታችንን ከእግዚአብሄር ላይ እንድናነሳ እና ሃይል ባለጠግናትና ጥበብ ላይ እንድናደርግ ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24

 1. የጥበብ መጉደል መናገር በሌለብን ጊዜ እንድንናገር ዝም ማለት ባለብን ጊዜ እንድንናገር ያደርገናል፡፡ ጠቢብ መቼ እንደሚናገር መቼ ዝም እንደሚል ማስተዋል ይመራዋል፡፡

ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል። ትንቢተ አሞጽ 5፡13

 1. የጥበብ መጉደል ነገራችንን በልክ እንዳናደርግ ይፈታነናል፡፡ ከራሳችን አልፈን ለሌላው የምንተርፈው ነገራችንን በልክ ስናደርግ ያለኝ ይበቃኛል ስንል ብቻ ነው ፡፡

አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡5

 1. የጥበብ መጉደል በቅንጦትና በመሰረታዊ ፍላጎት መካከል እንዳንለይ ያደርገናል፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ነው የሚያሳጣን የሚያስፈልገን ነገር የለም፡፡ ሰው በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን መለየት ካልቻለ ህይወቱ አያርፍም፡፡ ሰው በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ካልቻለ ሞልቶ የማይሞላውን ቅንጦት በማሟላት ሩጫ ህይወቱን ያባክናል፡፡ ሰው በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ካልቻለ በጭንቀት ታስሮ እግዚአብሄር ያስቀመጠለትን የህይወት አላማ ከግብ ማድረስ አይችልም፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ . . . አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡6-9

 1. ጥበብ ማጣት እውነተኛውን የህይወት ምንጭ ትተን ውሃ የማይዝ ጉድጉዋድ እንድንቆፍር ያደረገናል፡፡ ጥበብ እውነተኛውን የህይወት ምንጭ እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ያስተምረናል፡፡

ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥ የተቀደዱትንም ጕድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል። ትንቢተ ኤርምያስ 2፡13

 1. የጥበብ ጉድለት እኛን ለማይመስሉ እና ከእኛ ለተለዩ ሰዎች ልባችን እንዲጠብ ያደርገናል፡፡ የጥበብ ጉድለት እኛን የማይመስሉንን ሰዎች በጥበብ ከመያዝ ይልቅ ጨፍልቀን እኛን እንዲመስሉ በምናደርገው ሙከራ እንድንጥላቸው ያደርገናል፡፡ የጥበብ ጉድለት ከእኛ ለየት ያሉት ሰዎች ውስጥ እግዚአብሄር ያስቀመጠልንን በረከት በመጣል በእጦት እና በሽንፈት እንድንኖር ያደርገናል፡፡

እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 4፡29

 1. የጥበብ መጉደል ያለንን ውስን ጉልበት ባላስፈላጊ ነገር ላይ እንድናባክን ያደርጋል፡፡ የጥበብ ጉድለት ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገር ቅድሚያ እንዳንሰጥ ስለሚያደርገን ብዙ ዘርተን ትንሽ እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተቃራኒው ጥበብን ማግኘት ማስተዋል ባለበት በትንሽ ስራ ብዙ ውጤት እንድናገኝ ይረዳናል፡፡

የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና። መጽሐፈ መክብብ 10፡15

 1. የጥበብ መጉደል ሰው ዝም ብሎ መስራትና መጣር ብቻ እንጂ በውጤቱና በግኝቱ እንዳይሰደሰት ማስተዋል ይነሳዋል፡፡ ጥበብ መጉደል ህይወታችንን እንደልጅ በሚገባ እንዳንደሰትበት ያደርገናል፡፡ ህይወት ሃላፊነትና ሸክም ብቻ ሳይሆን እንድንደሰትበት የተሰጠ ስጦታ እንደሆነ ጥበብ ያስተምረናል፡፡ ጥበብ በሰራነው ነገር ፣ ባገኘነው ነገርና በደረስንበት ደረጃ እንድንደሰት ያስተምረናል፡፡

እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መጽሐፈ መክብብ 5፡18-19

 1. የጥበብ መጉደል ባላስፈላጊ ፉክክርና ውድድር ውስጥ ህይወታችንን እንድናባክን ያደርጋል፡፡

ጠቢብ ሰው ስኬቱን የሚለካው እግዚአብሄር በሰጠው የስራ ሃላፊነት ብቻ ነው፡፡ ጠቢብ ሰው ጎረቤቱ በሆነ ነገር በምንም ነገር ከጎረቤቱ ማነሱም ሆነ መብለጡ ስለስኬቱ ወይም ስለውድቀቱ አይነግረውም፡፡

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡12

 1. የጥበብ መጉደል ትክክለኛውን ጊዜ እንዳንለይ ያደርገናል፡፡ በትክክለኛው ጊዜ ውስጥ የሚለቀቅ ልዩ ሃይልና ስኬት አለ፡፡ ልክ ከጊዜው በፊት ልክ እንደጊዜው ነገሮች ውብ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። መጽሐፈ መክብብ 3፡1

 1. ጥበብ ከጎደለን ውብና ድንቅ ተደርገን ለልዩ አላማ እንደተፈጠረን ስለማንረዳ ሌላውን ለመምሰል በመጣጣር አንዷን ልዩ ህይወታችንን በከንቱ እናባክናታለን፡፡

ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። መዝሙረ ዳዊት 139፡14

 1. የጥበብ ጉድለት የእግዚአብሄርን እርምጃ እና ፍጥነት እንዳንታገሰው ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር አይቸኩልም፡፡ የእግዚአብሄርን እርምጃ ፍጥነት ከታገስን ፀፀትን በማትጨምረው እውነተኛ በረከት ውስጥ እንገባለን፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። መጽሐፈ ምሳሌ 28፡20

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። መጽሐፈ ምሳሌ 13፡11

 1. የጥበብ ጉድለት ከፍቅር ውጭ በመኖር ህይወታችን ዋጋ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡2-3

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሌለኝ ሁሉ የማያስፈልገኝ ነው

your will11.jpg

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙረ ዳዊት 23፡1

የሌለኝ የማያስፈልገኝ እንደሆነ በትክክል ለመረዳት አመታት ሊፈጅብኝ ይችላል፡፡ የሌለኝ የማያስፈልገኝ እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት ጌታ መጥቶ አሁን በድንግዝግዝ የማየውን በግልፅ ላየው ይገባ ይሆናል፡፡ እውነቱ ግን የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው፡፡

እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም እያልኩ የሚያስፈልገኝን አጣሁ ማለት አልችልም፡፡ የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው፡፡

የሌለኝ የማያስፈልገኝ እንደሆነ ለአእምሮዬ ሊከብድ ይችላል፡፡ እውነቱ ግን የሚያስፈልገኝን ሁሉ የሰጠኝ እግዚአብሄር ያልሰጠኝን ያልሰጠኝ ስለማያስፈልግኝ ብቻ ነው፡፡

እኔ ራሴን አልፈጠርኩትም፡፡ የፈጠረኝ እግዚአብሄር ነው፡፡ የሰራኝ እርሱ ነው፡፡ እርሱ ሁለንተናዬን ያውቃል፡፡ እርሱ እንደ መልካም እረኛ ያልሰጠኝ ነገር ካለ የማያስፈልገኝ ነገር መሆን አለበት፡፡

አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም። አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ። ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥ መዝሙረ ዳዊት 139፡1-3

እግዚአብሄር ምን እንደሚያስፈለገን ያውቃል፡፡ ከእኛ በላይ እግዚአብሄር ለእኛ ያውቃል፡፡ እፃ የሚያስፈልገንን ለማግኘት ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ለማሟላት ይፈልጋል፡፡

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡32

የሚያስፈልገኝን አጣሁ ከማለት ይልቅ የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው ማለት ይቀላል፡፡

እግዚአብሄ እረኛዬ ሆኖ የሚያስፈልገኝን አሳጣኝ ከምል ይልቅ የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው ብል አልሳሳትም፡፡

ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? የማቴዎስ ወንጌል 7፡9-11

እግዚአብሄር መልካም ሆኖ በትእቢት የሚያስፈልገኝን አሳጣኝ ከምል የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው ብል እውነተኛ ትህትና ነው፡፡

እግዚአብሄር እረኛዬ ሆኖ የሚያስፈልገኝን አሳጣኝ ብዬ ከምጠራጠር የሌለኝ የማያስፈልገኝ ነው ብዬ ማመን ይሻለኛል፡፡ እግዚአብሄር ከፍቅሩ የተነሳ ኢየሱስን እንዲሞትልኝ አሳልፎ እስኪሰጠኝ ወዶኝ ሌላውን ጥቃቅኑን ያነሰውን ነገርማ እንዴት አይሰጠፅም ብዬ ልመን?  የሚያስፈልገኝ ጎድሎብኛል ብዬ ከማመን አንድ ልጁን ሳይሳሳ የሰጠኝ እግዚአብሄር ሌላውንማ አብልጦ ይሰጠኛል ብዬ ማመን ይቀርበኛል፡፡

ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡32

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እረኛ #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው

your will1.jpg

በመጀመሪያ ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፥ በአንድ በኩልም አምናለሁ። በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት እንዲገለጡ በመካከላችሁ ወገኖች ደግሞ ሊሆኑ ግድ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡18-19

ከሁሉ አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያን በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ ሰምቻለሁ፤ ይህም ሊሆን እንደሚችል በከፊል አምናለሁ። ከእናንተ መካከል እውነተኞቹ ተለይተው ይታወቁ ዘንድ፣ ይህ መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው። (አዲሱ መደበኛው ትርጉም) 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡18-19

ሃዋርያው ጳውሎስ በቤተክርስትያን ውስጥ ስለተነሳው መከፋፈልና እና መለያየት ሲናገር መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው ይላል፡፡

ቤተክርስትያን ከእውነት ቃል ስታ ካለመለያየት በአንድነት ልትቀጥል ትችላለች፡፡ ቤተክርስትያን ከእውነት ቃል መሳትዋ ለእግዚአብሄርም ለእግዚአብሄርም ህዝብ አይጠቅምም፡፡

ቤተክርስትያን እውነትን በማመቻመች ካለመከፋፈል በአንድነት መቀጠልዋ ለቤተክርስትያን ተልእኮ መሳካት እንቅፋት ነው፡፡

ቤተክርስትያን በባህል እና በወግ ተጠላልፋ እግዚአብሄር በምድር ላይ ያስቀመጣትን የወንጌል ስብከት አላማ ዘንግታ ካለመለያየት በአንድነት መኖርዋ የቤተክርስትያንን ንፅህና አያሳይም፡፡

ቤተክርስትያን እውነትን ጥላ በሃይማኖት መልክ ብቻ ባለመከፋፈልና በውሸት አንድነት ልትቀጥል መቻልዋ ይህ ከመለያየት የከፋ ውድቀት እንጂ የቤተክርስትያንን ስኬት አያሳይም፡፡

በቤተክርስትያን ውስጥ ውዝብ ከተነሳ ውዝግቡ ቤተክርስትያን በትጋት መፍታት ያለባትን ችግር እንዳለ ያሳያል፡፡ በቤተክርስትያን ውዝግብ ተነሳ ማለት የተሳሳቱት መሪዎች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ወይም በቤተክርስትያን ወዝግብ እና መለያየት ተነሳ ማለት ለውዝግቡ መነሳት ጥፋተኞቹ ተከታዮች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ የተሳሳቱት የቤተክርስትያን ችግር መንስኤ የሆኑት የቤተክርስትያን መሪዎች ወይም ተከታዮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የቤተክርስትያን መሪዎች ወይም ተከታዮች ለውዝግቡ እና ለመለያየቱ ሁለቱም ያደረጉት አስተዋፅኦ ሊኖር ይችላል፡፡ የቤተክርስትያን መሪዎችም ይሁን ተከታዮች ይብዛም ይነስም ውዝግቡን በያዙበት መንገድ ሁለቱም ጥፋተኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በቤተክርስትያን ውዝግብ በሚነሳ ጊዜ መሪዎችም ሆነ ተከታዮች ሰይጣን ስፍራን እንዳያገኝ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ መሪዎችም ሆነ ተከታዮች ስለእውነት ብለው ችግሩን ከማባባስ ይልቅ ይልቅ ለመፍትሄው አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።  ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡27

ከመሪዎችም ይሁን ከተከታዮች ወገን ቅን ልብ ይጠይቃል፡፡ ጥያቄውን የሚጠይቁት ተከታዮች ጥያቄ የምጠይቀው በእውነት ነው? ብለው ራቸውን ደጋግመው ሊጠይቁ ይገባል፡፡

እግዚአብሄር ከመሪዎችም ይሁን ከተከታዮችም ወገን ለመቆም እውነትን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሃይል ካለው ፣ ገንዘብ ካለው ፣ ዝና ካለው ወይም ደግሞ ተሰሚነት ካለው ወገን ጋር ሳይሆን እውነት ያለው ሰው ከእርሱ ጋር ይሆናል፡፡ ምንም ዝነኛ ባለጠጋ ታዋቂ ብንሆን ከእውነት ጋር መወገን እንጂ ከእውነት ተቃራኒ ሆነን ምንም ልናደርግ አንችለም፡፡ እውነት የሌለው ሰው ደግሞ መሪም ይሁን ተከታይ እግዚአብሄር አብሮት አይሆንም፡፡ መሪዎችም ይሁን ተከታዮች እውነት የያዙ ሰዎች ተቃውመው አይቀጥሉም፡፡ እውነት የያዙ ሰዎች እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ይሆናል፡፡

ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8

በአጠቃላይ ከእኛ የተለየውን ሰው ለመረዳት ቅንነት ይጠይቃል፡፡

ተከታዮች የምንጠይቀውን ጥያቄ በቅንነት መጠየቃችንን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር ከማንም ጋር አይወግንም፡፡ እግዚአብሄር ከቅኖች ጋር ግን ይወግናል፡፡ የምንጠይቀውን ጥያቄ ስንጠይቅ ሌላ የተደበቀ አላማ አለን ወይስ የለንም? ብሎ ራስን መፈተሽ ይጠይቃል፡፡ የተደበቀ ምክኒያት ካለን ያንን ድብቅ አላማችንን መተው መመለስ ይጠበቅብናል፡፡ ልባችንን ፈትሸን የተደበቀ አጀንዳ እንደሌለን ካረጋገጥን ደግሞ ከእውነት ጋር መወገን ይጠበቅብናል፡፡

በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ። ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22፡24-26

እንደ መሪ ተከታዮች የሚጠይቁትን ጥያቄ በቅንነት ካየነው እና ለእውነተኛው ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከሰራን ሃላፊነታችንነ ሁሉ እንወጣለን፡፡ እንደ መሪ ተከታዮች የሚጠይቁትን ጥያቄ በቅንነት ካየነው ሌላው ጥያቄ እግዚአብሄር የሚመልሰው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚጠየቅን ጥያቄ ካለምንም ቅድመ ግምት በቅንነት ካላየንና እንደዚህ ያሉት እንዲህ ሊያደርጉ ፈልገው ነው በማለት እውነተኛውን ጥያቄ ለመመለስ ቸል ካልን ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡ መሪዎች እውነተኛውን ጥያቄ በቅንነት ካላዩት እና በእውነተኝነት መመለስ ካልፈለጉ መሪዎቹ ተከታዮችን ተከታዮች ደግሞ መሪዎቹን ያጣሉ፡፡

በዚህ ወሳኝ ጊዜ የቤተክርስትያን መሪዎች ብስለት የሚለካው ከቁጣና ከእልህ ነፃ ሆነው እውነተኛ እንደሆነ የሚያምኑበትን ጥያቄ እንደ እግዚአብሄር ቃል በመመለሳቸው ነው፡፡

ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። የያዕቆብ መልእክት 1፡19-20

ቅንነት ካለ ፍቅር ካለ እውነተኝነት ካለ ተቀራርቦ መነጋገር ብዙ ችግሮችን ይፈታል፡፡ ነገር ግን ቅንንት ከጎደለ ፍቅር ከሌለና እውነተኝነት ከጠፋ ሊፈታ የሚችለው ችግር ሁሉ ገዝፎ መበታተንን ያመጣል፡፡ እግዚአብሄርን በቅንነት ማገልገል የሚፈልግ ሰው እና ድብቅ አጀንዳ የሌለው ሰው በመቀራረበ በመነጋገር የሚያጣው ምንም ነገር የለም፡፡

አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡5

እግዚአብሄርን በቅንነት ማገልገል የሚፈልግ ሰው እና ድብቅ አጀንዳ የሌለው ሰው ከእርሱ የተለየውን የሌላውን ወገን ሃሳብ ለመረዳት በትህትና ይቀርባል፡፡ እግዚአብሄርን በቅንነት ማገልገል የሚፈልግ ሰው እና ድብቅ አጀንዳ የሌለው ሰው ባልንጀራው ከእርሱ እንዲሻል አስቦ በትህትና ይቆጥራል፡፡ እግዚአብሄርን በቅንነት ማገልገል የሚፈልግ ሰው እና ድብቅ አጀንዳ የሌለው ሰው ሌላውን ለማስደሰት የሌላውን እውነተኛ ጥያቄ ለመመለስ ይሰራል፡፡

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡3

የቤተክርስትያን መሪዎች ተቀራርበው ለመነጋገር ትህትና ከጎደላቸው ራሳቸው መሸከም የሚገባቸውን የቤተክርስትያንን አስተዳደር ሸክም በከንቱ ለተከታዮች ያሸክማሉ፡፡ የቤተክርስትያን መሪዎች ተቀራርበው ለመነጋገር ትህትና ከጎደላቸው አንዱ ስለሌላው ክፋትን እየተናገሩ ተከታዮቻቸውን የራሳቸው ለማደረገ በሚያደርጉት ክፉ ዘመቻ ተከታዮች መስማት የሌላባቸውን የቤተክርስትያን ሚስጥር በመስማትና መሸከም የሌለባቸውን ሸክም ካላቅማቸው በመሸከም ይበተናሉ፡፡ ራሳቸው መሸከም የሚገባቸውን የቤተክርስትያንን አስተዳደር ሸክም በከንቱ ለተከታዮች ያሸክማሉ፡፡

በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት እንዲገለጡ በመካከላችሁ ወገኖች ደግሞ ሊሆኑ ግድ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡19

አሁን ፈተናው ማነው ቅን በቅንነት ጥያቄን የጠየቀ ወይም በቅንንት መልስን የመለሰ የሚለው ነው፡፡ እግዚአብሄር በደፈናው የሚቆመው ከመሪም ሆነ ከተከታይ ጋር ሳይሆን ከቅኖች ጋር ነው፡፡

አሁን ፈተናው ማነው እውነተኛ እውነትን የያዘ ተከታይ እውነትን የያዘ መሪ የሚለው ነው፡፡ እግዚአብሄር ከመሪም ሆነ ከተከታይ ጋር ሳይሆን ከእውነተኛ መሪም ሆነ ተከታይ ጋር ይቆማል፡፡

አሁን ጥያቄው በእርጋታና በፍቅር ውዝግቡን ሊፈታ የሚችል እውነተኛው ማነው የሚለው ነው፡፡

አሁን ፈተናው ማነው በፍቅር የሚመላለሰው ተከታይ በፍቅር የሚመላለስ መሪ የሚለው ነው፡፡ አሁን ፈተናው ማነው ከጥላቻ ራሱን የሚጠብቅ መሪና እና ተከታይ የሚለው ነው፡፡ ፍቅር የሌለበት ነገር ምንም አይጠቅምም፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሄር ይኖራል፡፡ እግዚአብሄር ከፍቅር ሃሳብ ጋር ይወግናል፡፡ እግዚአብሄር በጭፍኑ ከመሪም ሆነ ከተከታይ ጋር ሳይሆን ከእውነተኛ ወገን ጋር ይቆማል፡፡

አሁን ፈተናው ለወገኔ ይጠቅማል በማለት የሚመላለሰው መሪው ነው ተከታዪ የሚለው ነው፡፡ አሁን ፈተናው ማነው በወገንተኝነት እና በራስ ወዳድነት የሚኖረው የሚለው ነው፡፡

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡3-4

እውነተኛውን ጥያቄ ጥያቄ ከመጠየቅና እውነተኛውን መልስ ከመመለስ ይልቅ በቡድን ተካፋፍሎ ድንጋይን መወርወር ቤተክርስትያንን ያዳክማል እንጂ ለማንም አይጠቅምም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎችhttps://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶችhttps://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መለያየት #አዲስ #መዋጀት #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #አቁማዳ #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ

የስኬት ጣሪያ

0_rblj0p_tomzAaXPr 1.jpg

እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡10-11

እግዚአብሄር የፈጠረን በመልኩ እና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር እርሱን እንድንመስል ሳይሰስት ፈጥሮናል፡፡

እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27

የእግዚአብሄር አላማ ራሱን በሰው ልጆች ውስጥ ማብዛት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ባህሪውን በሰው ልጆች ውስጥ ማየት ነው፡፡ የሰው ልጅ የህይወት አላማ እርሱን መምሰል ስለሆነ እግዚአብሄር እርሱን እንድንመስል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሳይሰስት ሰጥቶናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡2-3

የእግዚአብሄር አላማ መልኩን በእኛ ውስጥ ራሱን ማየት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አለካማ ባህሪው በእኛ ውስጥ ሲበዛ ማየት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ የመልካምነቱ ሁሉ ባህሪ በእኛ ውስጥ ሲበዛና ሲሰፋ ማየት ነው፡፡

እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡1

ሃዋሪያው ጳውሎስ በሞቱ እንኳንም እርሱን መምሰል ይመኝ ነበር፡፡

የክርስትና ስኬት የሚለካው ምን ያህል ክርስቶስን መስለሃል መልክህ ወደ ክርስቶስ ተጠግቷል በሚል ነው፡፡

ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡15

በክርስትናቸው ስላለተሳካላቸው ሰዎች መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እንዳላደጉና ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ እንዳልተጠጉ ይናገራል፡፡

እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፥19

የአለምና የእግዚአብሄር የስኬት መልኪያ ይለያያል፡፡ በህይወታችን በኑሮዋችን በአነጋገራችን በአካሄዳችን በአስተሳሰባችን ክርስቶስን መምሰል የስኬታችን መለኪያ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuam Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ስኬት #ወንጌል #ፍቅር #በክርስቶስ #የጌታፈቃድ #የጌታአላማ #ባለጠጋ #ጠቢባን #ሃያላን #ሞገስ #ክንውን #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ባሪያህ ይሰማልና ተናገር የማለት 10 ምክኒያቶች

listen.jpg

እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 3፡10

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን እግዚአብሄር በህይወታችን እየሰራ ያለውን ነገር አናውቅም ልንተባበረውም አብረነው ልንሰራም ልናገለግለውም አንችልም፡፡

ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 5፡17

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን እንስታለን

በእግዚአብሄር ምሪት ካልሆነ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የምናውቅበት ሌላ ምንም መንገድ የለም፡፡ ክፉና ደጉን ለመለየት በራሳችን ማስተዋል ለመደገፍ ብቁ አይደለንም፡፡ መንገዳችን የሚቀናው ለእርሱ ምሪት እውቅና ሰጥተን ድምፁን ስንሰማ ብቻ ነው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5-7

 • እግዚአብሄርን መስማት ከምንም ድንቅ መስዋእት ይበልጣል፡፡

ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን ውጤታማ አንሆንም፡፡ የተፈጠርነው እግዚአብሄርን በመስማት እና በመታዘዝ ውጤታማ እንድንሆን ዲዛይን ተደርገን ነው፡፡ እግዚአብሄርን አለመስማት ከተፈጠርንበት ዲዛይን ውጭ በመኖር ፍሬ የማፍራት ከንቱ ሙከራ ነው፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7-8

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን የእስራኤል ህዝብ የሴይርን ተራራ 40 አመት እንደዞረ እንዞራለን እንጂ ህይወታችን አይለወጥም፡፡

ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። ወደ ዕብራውያን 3፡8-9

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን ልናስደስተው አንችልም፡፡

 

እግዚአብሄርን የምናስደስተው በራሳችን መንገድ አይደለም በእርሱ በራሱ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናስደስተው ራሳችን የምንፈልገውን በማድር አይደለም እርሱ የሚፈልገውን በማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናስደስተው በራሳችን ህግ አይደለም በእርሱ ህግ ነው፡፡ እርሱ ንጉስ ነው፡፡ እርሱ ህግ አውጪ ነው፡፡ እርሱ እውነተኛ ነው፡፡ እርሱ ትክክል ነው፡፡ እርሱን መስማት እንድናስደስተው ያስችለናል፡፡ እርሱን አለመስማት ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነታችንን ያበላሻል፡፡

 

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

 

 • እግዚአብሄርን አለመስማትና በእግዚአብሄር ላይ ማመፅ ጣኦትን እንደማምለክ ነው

ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15:23

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን አናርፍም

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡33

 • እግዚአብሄርን ካልሰማን የህይወት አላማችንን እንስታለን፡፡

 

በምድር ላይ ያለነው ለልዩ አላማ ነው፡፡ ያንን አላማ በህይወታችን የሚሰራውን እግዚአብሄርን ለመስማት ጊዜ ካልሰጠንና ካልታዘዝነው አላማ ቢስ ሆንን ህይወታችንን እናባክናለን፡፡

 

 • ጠላት ዲያቢሎስ እያለ የበላይ ሆነን በድል የምናሸንፈው እግዚአብሄርን ለመስማት እና ለመታዘዝ ስንቀርብ ብቻ ነው፡፡

 

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡16-17

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ምሪት #ጆሮ #ትህትና #ቃል #ድምፅ #አእምሮ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #መታዝዝ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና

67121134_2406544886293761_6950157164044353536_o.jpg

ምሕረቱ ለዘላለም ነውና

መዝሙረ ዳዊት 136
1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
4 እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5 ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6 ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
7 ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
8 ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
9 ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
10 ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
12 በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
18 ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
22 ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
24 ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና
25 ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ

your will11.jpg

እኛ እያንዳንዳችን በተለያየም ምክኒያት ወደዚህ ምድር መጥተናል፡፡ አንዳንዶች በፖለቲካ ተሰደው መጥተዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህይወትን ለመለወጥ በሚል ምክኒያት በዚህ አገር ይኖራሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ እህት ወንድም ተከትለው መጥተዋል፡፡ ሌሎቹ በጋብቻ የመጡ ብዙ አሉ፡፡

መልካምን ነገር የሚሰጠው እግዚአብሄር ነው፡፡ እያንዳንዳችን የመጣነው እግዚአብሄር በርን ከፍቶልን ነው፡፡ እግዚአብሄር በርን ካልከፈተ ማናችንም እዚህ አገር አንመጣም ነበር፡፡

ብዙዎች እዚህ አገር ለመምጣት እየተመኙና እየፀለዩ ያልተሳካላቸው አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከእኛ እዚህ አገር ለመምጣት ከነበረን እድል በላይ በላይ የተሻለ እድል ኖሮዋቸው ያልመጡ አሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ሌሎች አውሮፓ አገሮችና አሜሪካ የመሄድ እድል አዘይነበራቸው እግዚአብሄር እዚህ ስለከፈተላቸው ብቻ ልባቸው ተነሳስቶ መጥተዋል፡፡

ብዙዎቻችን ባለታሰበ መልኩ በሮች ተከፍቶልን የመጣነው እግዚአብሄር ስለፈቀደ ነው፡፡

ይህን አገር የሰጠን ሰው አይደለም፡፡ ይህን አገር የሰጠን እግዚአብሄር ነው፡፡ እንደሰው ቢሆን አልቆልን ነበር፡፡ እግዚአብሄር እንደሰው አይደለም፡፡

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥ ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤ በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር። ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ። መዝሙረ ዳዊት 124፡1-6

እዚህ አገር ያለነው በሰው ችሮታ አይደለም፡፡ እዚህ አገር ያለነው የእግዚአብሄር ፈቃድ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ እዚህ አገር ያለነው እግዚአብሄር ሰዎችን ስለተጠቀመ ነው፡፡ እዚህ ምድር ላይ ያለነው እግዚአብሄር ሰዎችን ስለያዘልን ነው፡፡ በዚህ ምድር ያለነው እግዚአብሄር ላባን ለያቆብ በህልም እንደገሰፀው በእግዚአብሄር ገስፀው ነው፡፡

የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ድካም አየ፥ ትናንትም ገሠጸህ። ኦሪት ዘፍጥረት 31፡42

እዚህ አገር ያሉ አንዳንድ ሰዎች እኛ እዚህ አገር መኖራችን አይፈልጉም፡፡ አንዳንዶቹ በህይወታቸው ስላለው ችግር ሁሉ ተጠያቂ እንደሆንን የሰይጣንን ውሸት ያምናሉ፡፡ አንዳንዶቹ እኛ ብቻ ሳይሆን ከሌላ አገር የመጡት የውጭ ዜጎች ሁሉ ቢወጡላቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ችግራቸውን አይፈታም፡፡

እኛን ለማስወጣት ብዙም ጊዜ ሞክረዋል፡፡ በፊት በፊት ሊያስወጡን ቢፈልጉ በቀላሉ እንደሚያስወጡን ያስቡ ነበር፡፡ አሁን ግን ብዙ ሙከራቸው ብዙ ጊዜ ከሸፈ በኃላ እኛን ማስወጣት እንደማይችሉ ተረድተውታል፡፡ አሁን ያላቸው አንድ መሳሪያ ማስፈራራት ነው፡፡ እኛን ለማስፈራራት ብዙ አጭር የስልክ የፅሁፍ መልክቶች በዋትስአፕ በመሳሰሉት ለአመታት ሲሰራጩ ቆይተዋል፡፡ እኛ ፈርተን እንድንወጣ ብዙ ማስፈራሪያዎች ተደርገዋል፡፡ ፍርሃት ከሰይጣን ነው፡፡ ፍርሃትን የሚጠቀመው ሰይጣን ነው፡፡ የፍርሃት አላማ ደግሞ እኛን ከመኖር ከመስራትና ከመውጣት ከመግባት ማገድ ነው፡፡ ፍርሃትን ሰምተን መኖርን ከቆምን ሰይጣን ባለድል ይሆናል፡፡ ፍርሃትን ሳንሰማ በጥንቃቄ ከኖርን ሰይጣን የመስረቅ ግቡን አይመታም፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

ልንፈራው የሚገባው አግዚአብሄርን ብቻ ነው፡፡ ልናመልከውና ልንቀድሰው የሚገባው እግዚአብሄርን ብቻ ነው፡፡ ክፉ በማድረግ የሃገሪቱን ህግ በመጣስ መከራን አንቀበል እንጂ ከዚያ ውጭ ያለውን ፈርተን መቆም የለብንም፡፡ በሚጠብቀን በእግዚአብሄር ታማኝነት ታምነን መጠንቀቅ እንጂ መቆም አይገባንም፡፡

ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3

ለአመታትም በተነሱት ጥቃቶች እግዚአብሄር ከልሎናል፡፡ እግዚአብሄር ከብዙዎቹ ጥቃቶች አስመልጦናል፡፡ ከጥቃቱ እቅድ አንፃር ምልክቱን ብቻ ነው ያየነው፡፡ ሰዎች የፈለጉትን አላደረጉብንም፡፡ እግዚአብሄር ታማኝነቱን በተደጋጋሚ አሳይቶናል፡፡ እግዚአብሄር አብዝቶናል አስፍቶንማል፡፡

እንደማንኛውም ህዝብ በድህነትና በስራ አጥነት የሚሰቃይ ህዝብ ቢሆንም በአጠቃላይ ህዝቡ መልካም ህዝብ ነው፡፡ ካልወጣችሁ እንዲህ እናደርጋችሁዋለን የሚለው ማስፈራሪያ በጥቂት በቅናተኞችና በክፉ ሰዎች የሚጠቀመው የሰይጣን ምኞት ነው፡፡ ሰይጣን ደግሞ የተሸነፈ ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የተፈረደበት ጠላት ነው፡፡

ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 16፡11

እዚህ አገር ያለነው ሰይጣን አስኮናኞች ኑሩ ስላለን አይደለም፡፡ እዚህ አገር ያለነው በሰይጣን ምህረት አይደለም፡፡ እዚህ አገር ያለነው በሰይጣን በጎ ፈቃድ አይደለም፡፡ እዚህ አገር ያለነው በእግዚአብሄር ምህረት ነው፡፡

ዜጎቹ በዚህ ምድር እንዲወለዱ ያደረገው እግዚአብሄር እኛንም እዚህ ምድር እንድንገባና እንድንኖር በሮችን ከፍቶዋል፡፡ ይህን ምድር እንደ ትውልድ አገር ለዜጎቹ የሰጣቸው እግዚአብሄር እኛንም ይህንን ምድር እንድንሰራበት እና እግዚአብሄርን እንድናመልክ ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምድር እንዲወለዱ የፈቀደላቸው እግዚአብሄር እኛም እዚህ ምድር መጥተን በህይወትም በቃልም ወንጌልን እንድንሰብክ የእግዚአብሄርን በጎነት እንድንናገር ልኮናል፡፡

በእግዚአብሄር እይታ እነርሱ ለመኖር መብት እንዳላቸው ሁሉ እኛም ለመኖር መብት አለን፡፡

ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝሙረ ዳዊት 24፡1

እዚሁ ምድር ካልቀጠልንና በዚህ ምድር መኖሪያ ጊዜያችን ሲያበቃ ደግሞ እግዚአብሄር ወደምድራችን ይመልሰናል ወይም ደግሞ ሌሎች ምድሮችን ይከፍትልናል፡፡ እዚህ ምድር ኑሮዋችንን አገልግሎታቸንን እስክንጨርስ የትም አንሄድም፡፡ በችኮላና በፍርሀት ምንም አናደርግም፡፡

እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም። ትንቢተ ኢሳይያስ 52፡12

እንዲያውም በሚቀጥሉት ዘመናት ልጆቻቸን አድገው ተምረው ሰርተው አገሪትዋን ያሳድጋሉ፡፡ በሚቀጥሉት ዘመናት ልጆቻችን በፖለቲካ በኢኮኖሚ በትምህርት በጤና ሃገሪቱንም ራሳቸውንም ያድጋሉ ይሰፋሉ፡፡

በዚህ አገር የህንድ ማህበረሰብ እንዳለው ሁሉ በሚመጡት ዘመናት የኢትዮጲያ ማህበረስብ እየበዛ እየሰፋ እያየለ ይሄዳል፡፡ ከሌሎች አገሮች መጥተው በዚህ እንደሚኖሩ ሌሎች ትልልቅ ማህበረሰቦች ሁሉ የኢትዮጲያ ማህበረሰብ ይሰፋል ይበዛል ያብባል፡፡

በሃገሪቱ ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንረዳለን፡፡ የፖለቲካ መሪዎች ለህዝቡ እንደ አባት መሆን ነበረባቸው፡፡ ህዝቡን በቅንንነት ማገልገል ትተው ራሳቸውን በሚያበለፅጉ በአንድንድ የፖለቲካ መሪዎች እናዝናለን፡፡ እግዚአብሄር በጥበብ የሚያስተዳድሩዋትን በጎ መሪዎችን እንዲሰጣት ስለምድሪቱ እንፀልያለን፡፡

የስደተኛ ችግር የደቡብ አፍሪካ ብቻ ችግር አደለም፡፡ ከአሜሪካ እስከአውስትራሊያ ከኖርዌይ እስከ ጃፓን የስደተኝነት ችግር የአለም ችግር ነው፡፡

በምድራቸው ያለውን የዜጋውንም ሆነ የስደተኛውን ህዝብ ደህንነት መጠበቅ የአሩ መሪዎች ሃላፊነት ነው፡፡ በምድራቸው የሚኖረውን ህዝብ ስኬታማ ማድረግ አገሪትዋን ስኬታማ ማድረግ ነው፡፡ በምድራቸው እስከኖርን ድረስ የአገሪቱ የሰው ሃብት ነን፡፡ እኛን መቀበልና በሚገባ በፍትህና በሰላም ማስተዳደር ክብራቸው ነው፡፡

በምድሪቱ ላይ እንድንኖር የተቀበሉንን ሰዎች እናመሰግናለን፡፡ ከሁሉም በላይ በምድሪቱ ላይ እንምድንኖር ሞገስን የተሰጠንን እግዚአብሄርን ከልባችን አናመሰግናለን፡፡

በዚህም ምድር ላይ ያለነው ሌላ ምድር ስለሌለ አይደለም፡፡ የተሳካልን በዚህ መድር ላይ ስላለን አይደለም፡፡ የተሳካልን እግዚአብሄር ስላሳካልን ነው፡፡ በምድሪቱ ላይ የምንኖረው የሚበላና የሚጠጣ ፈልገን አይደለም፡፡ በዚህ ምድር ላይ ያለነው እግዚአብሄር በምድሪቱ ላይ የመኖራችን ልዩ አላማ እንዳለው ስለምናንም ነው፡፡ በምድሪቱ ላይ ያለነው ሌሎችን ለማገልገል እኛም ለመጠቀም ነው፡፡

የትኛውም አገር የራሱ ጥቅም እና የራሱ ተግዳሮት እንዳለው ሁሉ ደቡብ አፍሪካም የራሱ በጎ ጎኖችና ተግዳሮቶች አሉት፡፡ ተግዳሮቶቹን በትግስት አልፈን እግዚአብሄር በህይወታችን ያየውን አላማ ከመፈፀም የሚያግደን የለም፡፡ ይህን የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም ምንም የሚያግደን ነገር አይኖርም፡፡ ይህን የእግዚአብሄር ፈቃድ ለመፈፀም በፊታችን የሚቆም ማንም ሰው አይኖርም፡፡

በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡5

በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። መዝሙረ ዳዊት 37፡3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #አትፍራ #ታመን #መሪ

ከማገልገልህ በፊት ማረጋገጥ ያለብህ ወሳኝ ነገር

your will11.jpg

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡25፣31-33

አገልግሎት ከስጦታ አይጀምርም፡፡ ምንም ያህል መንፈሳዊ ስጦታ ቢኖርህ ስለመሰረታዊ ፍላጎትህ እግዚአብሄርን እስካላመንከው ድረስ አገልግሎት አልጀመርክም፡፡ እግዚአብሄርን ስለምግብህ ስለልብስህ ስለቤት ኪራይህ ስለልጆችህ ትምህርት ቤት ክፍያ ስለመሳሰሉት እግዚአብሄርን ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማድረግ ትችላለህ ነገር ግን እግዚአብሄርን ማገልግል አትችልም፡፡

ሌላውን የምታገለግለው የእግዚአብሄር ቃል በህይወትህ ፍሬ ባፈራ መጠን ብቻ ነው፡፡ ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ካላመንከው በስተቀር  የእግዚአብሄር ቃል እንደሚገባው በህይወትህ ፍሬ አያፈራም፡፡ ስለኑሮ የምትጨነቅ ከሆንክ የእግዚአብሄር ቃል በህይወትህ ሙሉ ፍሬ አያፈራም፡፡ አገልግሎት ከህይወት ይመነጫል፡፡ ፍሬ ባላፈራህበት የህይወትህ ዘርፍ ማገልገል አትችልም፡፡

በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። የሉቃስ ወንጌል 8፡14

አገልግሎት የሚመነጨው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ አገልግሎት የሚመነጨው በእግዚአብሄር ከመገልገል ነው፡፡ አገልግሎት የሚመነጨው በእግዚአብሄር በመሰረታዊ ፍላጎት ከመገልገል ነው፡፡ እግዚአብሄር አንተን እንደሚያገለግልህ ሳታምንና እርግጠኛ ሳትሆን አገልግሎት አትጀምር፡፡ በእግዚአብሄር ሳይገለገሉ ማገልገል ውሸት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ሳያምኑ ማገልገል የሃይማኖት መልክ እንጂ እውነተኛ አገልግሎት አይደለም፡፡

አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ወደ እግዚአብሄር ቅረብ፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ከእግዚአብሄር ጋር ያለህን ግንኙነት ፈትሽ፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎትህ ማመንህን እርግጠኛ ሁን፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ማመን ተማር፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ማመን ተለማመድ፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን እንደ አባት ፣ እንደ አቅራቢና እንደ ምንጭ እወቀው፡፡

አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። የማቴዎስ ወንጌል 23፡9-10

እግዚአብሄርን እንደ አባት ካላወቅከው በስተቀር ሌላውን ሰው አባት ታደርግና ከማገልገል ይልቅ በእግዚአብሄር ሳይሆን በሌላው ሰው  በመገልገል ህይወትህን ታባክናለህ፡፡ እግዚአብሄርን እንደ መሰረታዊ ፍላጎትህ ምንጭ ካላወቅከው ሌሎችን የምታገለግላቸውን ሰዎች እንደ ምንጭ ትይዝና ህይወትህ በእረፍት ሳይሆን በረብሻ ይሞላል፡፡ እግዚአብሄርን እንደ አቅራቢ ካላወቅከው ሌላውን አቅራቢ ታደርግና ከማገልገል ይልቅ በምስኪንነት አስተሳሰብ ከሌላው ሰው ጠባቂ ሆነህ ሳታገለግል ህይወትህን ትፈጃለህ፡፡

ስለመሰረታዊ ፍላጎትህ እግዚአብሄርን ማመን ከአገልግሎት ይቀድማል፡፡ እግዚአብሄር እንደሚንከባከብህ ሳትረዳ ከአንተ አልፈህ ሰውን በእውነት መንከባከብ አትችልም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መሰረታዊፍላጎት #ጭንቀት #አገልጋይ #እረፍት #ድካም #ጥረት #ባለጠግነት #በረከት #አላማ #ልፋት #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልግሎት #ፉክክር #ዋጋ

ዓለም አቀፋዊው የአገልግሎት ህግ

1426857.jpg

ሁላችንም እግዚአብሄር በምድር ያስቀመጠንን አላማ ፈፅመን ማለፍ እንፈልጋለን፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄርን አገልግለን ማለፍ እንፈልጋለን፡፡ የሁላችንም ህልምና ጥማት ሰዎችን በማገልገል ጌታን እንደሚገባው ማገልገል ነው፡፡ የሁላችንም ቅናት በዘመናችን የእግዚአብሄርን ፈቃድ አገልግለን ማለፍ ነው፡፡

ባልረካንበትና ባልጠገብንበት ዘርፍ ሌላውን ማርካትና ማጥገብ አንችልም፡፡ ባልተገለገልንበትና ባልተጠቀምንበት ዘርፍ ሌላውን መጥቀም አንችልም፡፡ ባልረካንትና በቃኝ ባላልንበት የህይወት ክፍል ሌላውን ማገልገል አንችልም፡፡

የሰው ፍላጎት አያልቅም፡፡ ፍላጎታችንን የምንገታው እኛው ነን፡፡ ራሳችንን የምግዛው እኛ ነን እንጂ አንድ ቀን ፍላጎታችን አያልቅም፡፡ አንድ ቀን ፍላጎታችን ያበቃል ብለን ካሰብን ጌታን ሳናገልግል እናልፋለን፡፡ ፍላጎት አያልቅም፡፡ ፍላጎት አያበቃም፡፡ ለፍላጎት ገደብን የምናበጀው እኛ ነን፡፡ የሰው ፍላጎት በራሱ ገደብ የለውም፡፡ ለፍላጎታችን ገደብ የሚኖረው እኛ ገደብ ባበጀንለት መጠን ብቻ ነው ፡፡

ያለኝ ይበቃኛል ማለት ያለብን እኛ ነን፡፡ እኛ ነን ከዚህ በላይ አያስፈልገኝም ማለት ያለብን፡፡ ከዚህ በላይ ምን ይሰራልኛል ብለን ተጨማሪን ነገር ከመከተል መመለስ ያለብን እኛ ነን፡፡ እኛ ነን እኔ በቃኝ ላለው ደግሞ ላካፍል ማለት ያለብን፡፡ ከዚህ በላይ አያስፈልገኝንም በማለት ፍላጎታችንን መግታት ያለብን እኛ ነን፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

ሌላውን ማገልገል የምንችለው በቃኝ ባልን መጠን ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም አገልግሎታችን ያለኝ ይበቃኛል ከሚለው አስተሳሰባችን ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡ አገልግሎታችን በቃኝ ካልንበት መጠን በላይ ሊሆን አይችልም፡፡ በህይወታችን 10 በመቶ ያለኝ ይበቃኛል ካለን ማገልገል የምንችለው 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በህይወታችን 50 በመቶ ያለኝ ይበቃኛል እያልን ከዚያ በላይ ማገልገል የማይታሰብን ነው፡፡ አይበቃኝም ብለን በምስኪንነት አስተሳሰብ የዋጥነውን ለሌላው ማካፈል አንችልም፡፡ ለሌላው ማካፈል የምችለው በቃኝ ብለን ያስተረፍነውን ብቻ ነው፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11

ራሱን ያማጠነ ሰው ብቻ ነው ለሌላው መትረፍ የሚችለው፡፡ ሌላውን የምንጠቅመውና የምንባርከው ራሳችንን ባማጠንንበት መጠን ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡4

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ይበቃኛል #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የምስራች በእግዚአብሄር የተመረጠ ሞኝ ደካማ ምናምንቴ የተናቀ ያልሆነ

1_j9PVBK7YEBgPAArVMeeEGQ.jpeg

እግዚአብሄር አላማውን ለመፈፀም በማንም ሰው ላይ አይደገፍም፡፡ እግዚአብሄር ለመስራት ጥበበኛን አይፈልግም፡፡ ጥበበኛውን ለማሳፈር እግዚአብሄር በእግዚአብሄር ፊት ሞኝ የሆነውን ሰው ይጠቀማል፡፡

ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን። የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡18-20

እግዚአብሄር ሊጠቀምብን መሰጠትን ብቻ እንጂ ሌላ ምንም መመዘኛ አልጠበቀብንም፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡26-28

ብዙ ጊዜ ሰው በሃይሉ የሚበረታ እና እግዚአብሄር እንደማያስፈልገው ያስባል፡፡ ነገር ግን ሰው በሃይሉ አይበረታም፡፡ የሰው ሃይል ምንም አያመጣም፡፡

እግዚአብሄር ለመርዳት የማንንም እርዳታ አይጠይቅም፡፡

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8

እግዚአብሄር አቤት እርሱ ተብሎ በተደነቀለት በብዙ ሃያል ዝነኛና ጥበበኛ ከማዳን ይልቅ በጥቂት ማዳንን ይመርጣል፡፡ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውም፡፡

ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ጭፍራ እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 14፡6

እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ መዝሙረ ዳዊት 136፡4

በሃይሉ እንደማይበረታ የሚያስተውል ሰው ሲያገኝ እግዚአብሄር ሃይሉን ይገልጥበታል፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፡9

የህይወት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር ጋር እንጂ ሃያል ጥበበኛና ባለጠጋ ጋር እንዳልሆነ የሚያስተውል ደካማ ሰው ሲያገኝ እእግዚአብሄር ለታላላቅ ነገር ይጠቀምበታል፡፡ እግዚአብሄር ህይወታችን ሊለውጥ ሃይላችንን ጥበባችንና ብልጥግናችንን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር ሃይል ፣ ጥበብና ብልጥግና የሌላቸውን ደካማ ሰዎች ህይወት በመለወጥ የተካነ ነው፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጥበብ #ማስተዋል #ሞኝ #ደካማ #ምናምንቴ #የተናቀ #ያልሆነ #መረዳት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #ውርደቱ #ይመካ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ስኬት ውስጤ ነው

15895351_1013263932112615_4905316888275387628_n.jpg

እግዚአብሄር በሁሉም አቅጣጫ ስኬታማ ነው፡፡ ሰውን የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ስስታም አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ቁርጥ እርሱን አስመስሎ በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡27-28

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እንደእርሱ ሙሉ ለሙሉ ስኬታማ እንዲሆን ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው ለስኬት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ በውስጡ አስቀምጦ ነው፡፡

ሰው ለስኬቱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ በውስጡ አለ፡፡ የሰው ስኬት በሌላ ሰው በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ሌላው ሰው እንዲሳካልን ቢፈልግም ባይፈልግም ለስኬት የሚያስፈልገው ነገር በውስህ አለ፡፡ ስኬት በገንዘብ ወስጥ የለም ስኬት በዝና ውስጥ የለም ስኬት በሃይል ውስጥ የለም፡፡ ስኬት ያለው በአንተ ውስጥ ነው፡፡ ስኬት በውስጥህ ስላለ እና ለስኬታማነት ስለተቀረፅክ እና ስለተነደፍክ ገንዘብ ፣ ዝና እና ስልጣን በሌለበት ቦታ ብትጣል ይሳካልሃል፡፡ የሚያሳካለህ እግዚአብሄር ከአንተ ጋር መኖሩ ብቻ ነው፡፡

በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡5

ሁኔታዎች አይሳካልህም ቢሉም ለስኬት ከሚያስፈልገው ማንኛውም ነገር ጋር ተፈጥረናል፡፡ ሊሳካልህ አይችልም ብሎ ያሳመነህ ካለህ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ብቻ የሚመጣው የሰይጣን ድምፅ ብቻ ነው፡፡

ሰው በውስጡ ያለውን የስኬት ንጥረ ነገር በታማኝነት ካወጣው እና ከሰራበት ስኬትን የሚወስድበት ማንም የለም፡፡ ሰው በውስጡ ያለውን የስኬት ንጥረ ነገር በትጋት ከሰራበት ሰይጣነም ሆነ ሰው ከስኬት ሊያቆመው አይችልም፡፡

ሰው እንኳን ለመኖር የሚያስፈልገው ይቅርና ሌሎችን ሊያገለግልበትና ሊባርክበት የሚችልበት ትልቅ የተጠራቀመ ጉልበት በውስጡ አለ፡፡ እንዲያውም ሰው የተፈጠረው ለራሱ እንዲሳካለት አይደለም፡፡ ሰው የሚሳካለት እግረመንገዱን በነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከራሱ አልፎ ሌሎችን ለስኬት ለመርዳት ነው፡፡

የስኬታማ ሰዎችና ያልተሳካለቻው ሰዎች የሚለዩት በውስጣቸው ባለው የስኬት ዘር ሳይሆን የስኬት ዘሩን አውጥተው በመጠቀማቸውና ባለመጠቀማቸው ብቻ ነው፡፡ አንዳንዱ እዲሳካለትና አንዳንዱ እንዳይሳካለት ታቅዶ አልተፈጠረም፡፡ ህሊናውን ጠብቆ የሚኖር ሰው ሁሉ እንዲሳካለት ለስኬት ከሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ጋር ተፈጥሮአል፡፡

የሰው ስኬት የሚለካው በጎረቤቱ የስኬት መመዘኛ አይደለም፡፡ የሰው ስኬት የሚለካው በልቡ በተቀመጠው ክህሎት ነው፡፡ ምንም ከሌሎች የተለየ ቢሆን በልቡ የተቀመጠውን የስኬት ዘር አውጥቶ ከዘራው ፣ ከኮተኮተውና ከተንከባከበው ሰው ሁሉ በራሱ መንገድ ስኬታማ መሆን ይችላል፡፡

ሰው አግዚአብሄር ለምን እንደፈጠረው እግዚአብሄር የፈጠረበትን አላማ ከእግዚአብሄር ቃል ፈልጎ ካገኘውና የህይወት አላማ እና እቅድ  በትጋት ከተከተለ የማይሳካለት ምንም ምክኒያት የለም፡፡

አንተ ስኬትን ከምትፈልገው በላይ እግዚአብሄር እንዲሳካልህ ይፈልጋል፡፡ እንዲሳካልህ መፈለግና ውድቀትን መጥላትን በውስጥህ ያስቀመጠው በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህ የሚፈልገው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡

ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። 3ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፡2

እንዲሳካልህ የሚያስፈልገውን ቁልፍ ነገር በየጊዜው የሚያስታውስህ እንዲሳካልህ የእግዚአብሄር በጎ ፈቃድ ስለሆነ ነው፡፡

በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡7-8

የስኬትን መንገድ የሚያስተምርህ እውነተኛ ስኬት እንዲኖርህ የሚያስፈልገውን ሁሉ ስለሰጠህና ለስኬትህ አብሮ መስራት ስለሚፈልግ ነው፡፡

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙረ ዳዊት 1፡1-3

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ስኬት #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ደስታ #እርካታ #ሰላም #ምሪት #ፍቅር #እምነት #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት

የፍሬ ፍሬ

AAG4idI.jpg

ለፍሬያማነት መተከልና ስር መስደድ ወሳኝ ነው፡፡ የትኛውም ዘር ስር ሳይሰድ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡ ዘር ፍሬ ለማፍራት መጀመሪያ ከምንጩ ጋር መገናኘት ይኖርበታል፡፡ ዘር አድጎ ፍሬ ከማፍራቱ በፊት ፍሬ ሊያፈራ ከሚያስችለው አቅራቦት ጋር በሚገባ መገናኘት አይችልም፡፡

እድገቱ አስተማማኝ እንዲሆን ተክል ስር መስደድ አለበት፡፡ ተክል እንዲያድግና እንዲፈራ ክር መስደድ ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ተክል ሊያድግና ፍሬ ሊያፈራ የሚችለውስር በሰደደው መጠን ብቻ ነው፡፡

በክርስትናም ለማደግና ፍሬ ለማፍራት ለማደግ ከሚያስፈልገው ከእግዚአብሄር ቃል ጋር በሚገባ መገናኘት ይጠይቃል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሳይዙ ለማደግ እና በህይወት ፍሬ ለማፍራተ መሞከር መሰረት ሳይሰሩ ቤት ለመስራት እንደመሞከር ከንቱ ድካም ነው፡፡

ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ። የማቴዎስ ወንጌል 7፡26-27

ስር ካልሰደደ ተክል እድገትና ፍያማነት መጠበቅ ከንቱ እንደሆነው ሁሉ በእግዚአብሄር ቃል ልምምድ ስር ካልሰደደ ክርስትያን መንፈሳዊ እድገትና ፍሬያማነት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡

ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፥7

ስርና መሰረታቸው በእግዚአብሄር ቃል በጌታ ያልፀኑ ሰዎች የማይያዙ የማይጨበጡ በጠንካራ መሰረት ላይ ያልታነፁ ሰዎች ናቸው፡፡

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

በአንዴ የሚያፈራ ተክል እንደሌለ ሁሉ ለማፍራት መቆየት እና መኖር ይጠይቃል፡፡ ለማፍራት ራስን በመስጠት መጠበቅ ይጠይቃል፡፡ ለማፍራት ራስን በመስጠት መቆየት መኖር ይጠይቃል፡፡

በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። የዮሐንስ ወንጌል 15፡4

በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። የሉቃስ ወንጌል 8፡15

ምንም ግንኙነት ካለመቆየት ፍሬ አይሰጥም፡፡ የተክሉና ለተክሉ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ በስሩ አማካኝነት ካልተገናኘ ተክሉ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡ በየጊዜው አዳዲስ ቦታ የሚተከል ችግኝ መጠውለጉና ለፍሬ ሳይበቃ መድረቁ አይርም፡፡

በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፥16-17

እግዚአብሄርን የምናስከብረው በፍሬ ብቻ ነው፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7-8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍሬያማነት #ፍሬ #ስር #መሰረት #ማፍራት #ስኬት #በእኔኑሩ #ቃል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መመዘኛ #መስፈርት #ፅናት #ትግስት #መሪ

ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?

raise-hand.png

እግዚአብሄር ምንም ያህል መንገዱን እንድንከተል ቢፈልግም ነገር ግን የእግዚአብሄርን አላማ መሳት አለ፡፡ እግዚአብሄር ምንም ያህል እንዳንስት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ቢያዘጋጅም ነገር ግን መሳት በህይወታችን ይከሰታል፡፡ መሳት የማይያዝ የማይጨበጥ ሃይማኖታዊ ሃሳብ ሳይሆን እውን በእለት ተእለት ህይወታችን ሊከሰት የሚችል ክስተት ነው፡፡

በህይወታቸው የእግዚአብሄርን መንገድ የሚጠብቁ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በህይወታቸው የእግዚአብሄርን መንገድን የሚስቱ ሰዎች አሉ፡፡ በህይወታቸው መሄድ የማይፈልጉበት ቦታ ራሳቸውን የሚያገኙ ሰዎች አሉ፡፡

እኛ የእግዚአብሄርን መንገድ መሳት ከማንፈልገው በላይ እግዚአብሄር እንዳንስት ቢፈልግም ነገር ግን መሳት በሰው ልጆች ህይወት ላይ የሚከሰት ያለ ነገር ነው፡፡ መንገዱን እንዳንስት እግዚአብሄር የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ቢያዘጋጅም እንኳን መሳት እውን ነው፡፡ መንገዱን እንዳንስት እግዚአብሄር ካዘጋጃቸው እጅግ ብዙ ነገሮች አንፃር መሳት ከባድ ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሄርን መንገድ ልንስት አንችለም ማለት ግን በፍፁም አይደለም፡፡ ከእግዚአብሄር ፍቅር አንፃር ለሰው ከመሳት ይልቅ አለመሳት ቢቀለውም ነገር ግን መሳት የለም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን እየፈለግን መሳት ከባድ ቢሆንም ነገር ግን ካልተጠነቀቅን ሊሆን የሚችል ነገር ነው፡፡

ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል። የዮሐንስ ወንጌል 7፡17

ልስት አልችልም ብለን ስላሰብን ብቻ አንስትም ማለት አይደለም፡፡ ከሚስቱ ሰዎች አብዛኛዎቹ ከመሳሳታቸው በፊት መሳት የሚባለው ነገር እኔ ላይ ላይ አይደርስም ብለው አስበዋል፡፡ የማይጠነቀቀውና የሚስተው ልስት አልችልም ብሎ የሚይስብ ሰው ብቻ ነው፡፡

ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋልም ይጋርድሃል፣ ከክፉ መንገድ” ያድንሃል። መጽሐፈ ምሳሌ 2:11

እኛም ብዙ ጊዜ ለዚህ አሳልፈ አልሰጥም ብለን ላሰብንለት ነገር ተሰጥተን ራሳችንን አግኝተነዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ በእኔ ላይ አይሆንም ብለን ያሰብነው ነገር ሆኖብን አይተናል፡፡

ምንም ያህል ነገሮች የምናይና የምናውቅ ብንሆን የማናያቸው ነገሮች አሉ ብለን ማሰብ እና የእግዚአብሄርን እርዳታ በቀጣይነት መፈለግ ጥበብ ነው፡፡

የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። መጽሐፈ ምሳሌ 21፡2

ጌታ  ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል ባለ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እኔ እሆንን? ይሉ ጀመር፡፡

ሲበሉም፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል አለ። እጅግም አዝነው እያንዳንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን? ይሉት ጀመር። የማቴዎስ ወንጌል 26፡21-22

ማነው እርሱ አሳልፎ የሚሰጥህ ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እኔ እሆንን ማለት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ እርሱ ማነው የሚለው ብቻ ሳይሆን እኔ እሆንን ማለት ትህትና ነው፡፡ አንተ አይደለህም ብሎ ሊመሰክር የሚችል የእግዚአብሄር ቃልና የእግዚአብሄር መንፈስ ብቻ እንጂ እኛ ራሳችን አይደለንም፡፡  ወደድንም ጠላንም አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ ውስጥ ያለው ስጋ እኛም ውስጥ ይኖራል፡፡ ይሁዳን ያሳሳተው ሰይጣን እኔን ሊያሳስተኝ አይችልም ብሎ አለመጠንቀቅ በእርግጥ መሳትን ያስከትላል፡፡

ስለዚህ ነው ሃዋርያው ፍራ እንጂ የትቢትን ነገር አታስብ ያለው ለዚህ ነው፡፡ የሚወድቁት ልወድቅ አልችልም ብለው የማይጠነቀቁ ሰዎች ናቸው፡፡ የሚወድቅ ሰው ምልክቱ ልወድቅ አልችልም ብሎ ማሰቡ ነው፡፡ አንተ ልትወድቅ እስከማትችል ድረስ መጠንቀቅ የለብህም ብሎ ካሳመናችሁ ሰይጣን እንጂ እግዚአብሄር ሊሆን ፈፅሞ አይችልም፡፡

መልካም፤ እነርሱ ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ አንተም ከእምነት የተነሣ ቆመሃል። ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ። ወደ ሮሜ ሰዎች 11፡20

ታላቁ ሃዋርያው ጳውሎስ እንዳይስትና እስከመጨረሻው ፀንቶ ለመቆም የሚያደርገውን ጥንቃቄ እያየን እኔ አልስትም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡

ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #መንገድ #ድምፅ #ጌታ #መሳት #ስህተት #ትእቢት #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥንቃቄ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መንገድህን እባክህ አሳየኝ

your will11.jpg

አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው። ኦሪት ዘጸአት 33፡13

መንገድህን እባክህ አሳየኝ ልመና ከእግዚአብሄር መንገድ ውጭ ያለው መንገድ ሁሉ አደገኛ የሆነ የብክነት ህይወት እንደሆነ የተረዳ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡

አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ። መዝሙረ ዳዊት 25፡4

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት ህይወቱን ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ ላማባከን የማይፈልግ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡

አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል።  መዝሙረ ዳዊት 86፡11

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት በእግዚአብሄር መንገድ ብቻ እውነተኛ ስኬት ፍሬማነትና ውጤት እንደሚገኝ የተረዳ ሰው የልብ ጩሸት ነው፡፡

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት ለእያንዳንዳችን የተወሰነ የተለየ መንገድ እንዳለ ሰው ስለሄደበት ብቻ በግርታ መሄድ እንደሌለበት የተረዳ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት እኛ እንዲመራን ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር ሊመራን እንደሚፈልግ የተረዳ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት ከእግዚአብሄር መንገድ ውጭ የሆነው የእኛ መንገድ የትም የማያደረስ የድካምና እና የከንቱነት መንገድ እንደሆነ የተረዳ ሰው ጩኸት ነው፡፡

መንገድህን እባክህ አሳየኝ የሚለው ጩኸት ለመሄድ ብቻ ብሎ እግዚአብሄር በሌለበት መንገድ ከመሄድ አለመሄድ መቅረት እንደሚሻል የተረዳ ሰው የልብ ጩኸት ነው፡፡

እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #መንገድ #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ

fb367b1c6fa2d27c08a54213ee39e436 (1).jpg

በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16

ክርስትና የሚቻለው በእግዚአብሄር እርዳታ ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር እርዳታ ውጭ እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻለም፡፡ እግዚአብሄር በሚያስችል ፀጋው ካላስቻለን ፈቃዱን አድርገን እግዚአብሄርን የሚያስደስት ህይወት ሊኖረን አይችልም፡፡

ለእግዚአብሄር መኖር እየፈለግን አንዳንድ ጊዜ አቅም እናጣለን ይደክመናል፡፡ ለእግዚአብሄር እንዴት መኖር እንዳለብን እናውቃለን ነገር ግን ጉልበት እንደከዳን ይሰማናል፡፡ በየት መንገድ መሄድ እንዳለብን እናውቃለን ነገር ግን ተጨማሪ እርምጃ ለመራመድ ጉልበት እንዳነሰን  ይሰማናል፡፡ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ እንፈልጋለን ነገር ግን ከተለያየ ምክኒያት የተነሳ ይታክተናል እርዳታን እንፈልጋለን፡፡

ለጌታ ለመኖር ፈቃዱን ለማድረግና በነገር ሁሉ እርሱን ለማስደሰት ያለን ብቸኛ አማራጭ ወደ እርሱ መሮጥ ነው፡፡ በኑሮዋችን እርሱን ማስደሰት የምንችልበትን በሚያስፈልገን በትክለኛው ጉልበት የምናገኘው ከፀጋው ዙፋን ነው፡፡

የእግዚአብሄር ዙፋን የፀጋው ዙፋን የተባለበት ምክኒያት እርሱ ሁልጊዜ ሊረዳ ሊደግፍ ፈቃደኛና የተዘጋጀ መልካም አምላክ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ዙፋን የፀጋው ዙፋን የተባለበት ምክኒያት እርሱ እርዳታውን የሚፈልጉትን በመርዳት የተካነ አምላክ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ዙፋን የፀጋው ዙፋን የተባለበት ምክኒያት በህይወታችን የሚገጥመንን ማንኛውንም ተግዳሮት ለማለፍ የሚያስችል ብቃትን የምናገኘው ከእርሱ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ዙፋን የፀጋው ዙፋን የተባለበት ምክኒያት እርሱ ከልባቸው እርዳታውን የሚፈልጉትን ለመርዳት አይኖቹ በምድር ላይ ስለሚመላለሱ ነው፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፡9

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ላለማድረግ ምንም ሰበብ የለንም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ የሚያስችለንን ፀጋ እንድንቀበል ወደፀጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ፡፡ ይበልጥ ወደ ፀጋው ዙፋን በቀረብን መጠን ይበልጥ የእግዚአብሄር ፀጋ በህይወታችን ይገለጣል፡፡ ይበልጥ ወደፀጋው ዙፋን በቀረብን መጠን ይበልጥ በድካማችን ላይ የእግዚአብሄር ፀጋ ብርታት ይገለጥበታል፡፡ ይበልጥ ወደፀጋው ዙፋን በቀረብን መጠን ይበልጥ የእግዚአብሄር ፀጋ ድካማችንን ይሸፍናል፡፡ ይበልጥ ወደ ፀጋው ዙፋን በቀረብን መጠን ይበልጥ ድካማችን በብርታት ይለወጣል ለእግዚአብሄርም ለመኖር አቅም እናገኛለን፡፡

ወደ ፀጋው ዙፋን መቅረብ ያለብን ደግሞ በእምነት ነው፡፡ ስለአንድ የህይወታችን ጥያቄ ወደፀጋው ዙፋን ከቀረብን በኃላ እግዚአብሄር የሚያስችለውን ፀጋ እንደሰጠን አምነን መሰማራት አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ፀጋ እንደተቀበልን የምናውቀው በእምነት እንጂ ወደ ፀጋው ዙፋን እንደቀረብን እየበረረ መጥቶ የሚገባብን በተፈጥሮአዊ አይን የሚታየ ፀጋ የለም፡፡ እግዚአብሄር ሊደግፈን እንደሚፈልግ በማመን ወደፀጋው ዙፋን ከቀረብን በኃላ ታምነን መሰማራት አለብን፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ . . . ታምነህም ተሰማራ። የዳዊት መዝሙር። 37፡3

እንደፈቃዱ እንደፀለይን ካመንን እንደተቀበልን እናውቃለን፡፡

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #የሚረዳንን #ፀሎት #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ABDII (HOPE) Fenan Befikadu Dawit Getachew & Meron Alemu New Ethiopian Music Official Video

መታዘዝ እንጂ መሥዋዕት እግዚአብሄርን ደስ አያሰኘውም

b2a3bbacdc0f411f2bff504c4251f5c7.jpg

መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም። የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። መዝሙረ ዳዊት 51፡16-17

እውነተኛ አምልኮት በራስ ግምት እግዚአብሄርን ለማምለክ ከመሞከር ተስፋ መቁረጥ ነው፡፡ እውነተኛ አምልኮት በራስ መስዋእት ተስፋ ከመቁረጥ ይጀመራል፡፡ እውነተኛ አምልኮ መስዋእትን ማቅረብ ሳይሆን እግዚአብሄር የጠየቀንን ነገር ለመታዘዝ መስዋእት መሆን ነው፡፡

መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም፤ ሥጋን አዘጋጀህልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻህም። በዚያን ጊዜ አልሁ፦ እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። መዝሙረ ዳዊት 40፡6-8

እውነተኛ አምልኮ እግዚአብሄር ይህን ባቀርብለት መልካም ነው በማለት መስዋእትን ማቅረብ ሳይሆን እግዚአብሄር እንድናደርግ ያዘዘንን ያንን ብቻ መታዘዝ ነው፡፡ እውነተኛ አምልኮ የእግዚአብሄር ፈቃድ መሆኑን በልባችን የሰማነውን ነገር ማድረግ ነው፡፡

ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15፡22

የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው እግዚአብሄርን አያውቅም አይከተልም፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው ምህረትን አያውቅም አይከተልም፡፡ የአምልኮት መልክ ያለው ሰው እግዚአብሄርን መታዘዝን በራስ ግምት እግዚአብሄርን በስጦታ ለማስደሰት በመሞከር ይለውጠዋል፡፡ የአምልኮት መልክ የእውነተኛ መንፈሳዊነት ማስመሰያ ፌክ ነው፡፡

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡5

የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው የሃይማኖት ወጎችንና ስርአቶችን አይፈፅምም ማለት አይደለም፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው እንደ ማንኛውም አምላኪ የሃይማኖት ወጎችንና ስርአቶችን ይፈፅማል፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው በራሱ ግምት እግዚአብሄር ይሄን ሊፈልግ ይችላል እያለ በግምት መስዋእትን ያቀርባል፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ከማድረግ ውጭ ሃይማኖታዊ ወጎችንና ስርአቶችን ሁሉ ይፈፅማል፡፡

ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወድዳለሁና። ትንቢተ ሆሴዕ 6፡6

የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው መንገዱ በፊቱ የቀናች ትመስለዋለች፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው እግዚአብሄርን እያገለገለ ይመስለዋል፡፡ የአምልኮት መልክ ብቻ ያለው ሰው ስርአትና ወግ ስለፈፀመ ብቻ እግዚአብሄርን የሚያስደስት ይመስለዋል፡፡

እግዚአብሄር ግን ሰው እግዚአብሄርን አስደስትበታለሁ ብሎ በሚገምተው የግምት መስዋእት አይደሰትም፡፡

የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። እግዚአብሔር ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል። መጽሐፈ ምሳሌ 21፡2-3

እግዚአብሄር የሚፈልገውን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው ከእግዚአብሄር ጋር መቆምን እግዚአብሄርን በቃሉ መታዘዝን ነው፡፡ እግዚአብሄር እውነተኛ መስዋእት የሚለው እርሱን ሰምቶ መታዘዝን እንጂ መልካም የሚመስልን ነገር ለእግዚአብሄር ማድረግን አይደለም፡፡ ለእግዚአብሄር ከምናደርግለት ብዙ መስዋእት ይልቅ ድምፁን በመታዘዛችን ይደሰታል፡፡

መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም፤ ሥጋን አዘጋጀህልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻህም። በዚያን ጊዜ አልሁ፦ እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። መዝሙረ ዳዊት 40፡6-8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiydinsa7/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #እንደተፃፈ #ማታዘዝ #መባ #መሥዋዕት ##እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሰው መጠቀሚያ የመሆን ስሜት

644735-1024x768-[DesktopNexus.com].jpg

እውነትም እያንዳንዳችን አንዳንዴ ሌላው ሰው ካላግባብ እንደተጠቀመብን ይሰማናል::

ከሰው ጋር እየኖረና እየሰራ ይህ አይነት ስሜት በየጊዜው የማይሰማው ሰው አይገኝም:: አንዳንዴ መሪው ተመሪው እንደተጠቀመበት ይሰማዋል:: ተመሪው  መሪው እንደተጠቀመበት ይሰማዋል:: አንዳንዴ ፓስተሩ ምእመኑ እንደተጠቀመበት ይሰማዋል:: ምእመኑ ፓስተሩ እንደተጠቀመበት ይሰማዋል:: አንዳንዴ አሰሪው ሰራትኛው እንደተጠቀመበት ይሰማዋል:: ሰራተኛው አሰሪው እንደተጠቀመበት ይሰማዋል::

አንዳንዴ እጅግ ቅርብ በሆኑት በባልና በሚስት ላይ እንኳን እንደዚህ አይነት ሌላው ተጠቀመበኝ ስሜት ይንፀባረቃል:: አንዳንዴ ሚስት ባልዋ እንደተጠቀመባት ይሰማታል:: ባል ሚስቱ እንደተጠቀምችበት ይሰማዋል::

እንዳንዴ ሌላው ተጠቀምብኝ የሚለውን ሁሉ ስንሰማ ይህ ሁሉ ጥቅም የት ገባ ብለን እንጠይቃለን::

እውነት ነው ድንበራችንን ካላወቅንና ካላሳወቅ ድንበራቸውን የማያውቁ እና ካላግባብ ሊጠቀሙብን የሚፈልጉ ሰዎች ይኖራሉ:: ነገር ግን ሌላው ሰው ተጠቀመብን የሚለውን ስሜታችንን ሁሉ ካመንነው ደግሞ ሰላማችንን እናጣለን::

ሌላው ተጠቀመብን የሚለው ስሜት ሁሌም ባይሆንም አንዳንዴ ከራስ ወዳድነትና ከስስት ይመጣል፡፡ እኛ ይበልጥ እንደለፋን ስናስብ መነጫነጭ እንጀምራለን፡፡ በማንኛውም አጋርነት አንተ ሃምሳ በመቶ እኔ ሃምሳ በመቶ እናዋጣለን ተብሎ የሚሰመርበት ሁኔታ የለም፡፡ በቃል ደረጃ እንለዋለን እንጂ አንዱ አንዳንድ ጊዜ ሰባ በመቶ የሚያዋጣበት ለዔላው ሃምሳ በመቶ የሚያዋጣበት ሁኔተ ይፈጠራል፡፡ በሌላ ጊዜ ድግሞ ሰላሳ በመቶ ያዋጣው ስልሳ በመቶ የሚያዋጣበትና ሌላው አርበና በመቲ የሚያዋጣበት ሁኔታ ደግሞ ይፈጠራል፡፡

የሰው ብድራት ያለው በእግዚአብሄር ዘንድ እንደሆነ የሚያምን ሰው ብዙ በማዋጣቱ እንደተጠቀመ ደስ እያለው ይሄዳል እንጂ አይነጫነጭም፡፡

ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡8

ሰዎች ቢጠቀሙብን ብንበደል እንኳን የሚክሰን እግዚአብሄር አለ፡፡ ከመበደል መበደል ይሻላል፡፡

እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡7

የሚያፅናናን ነገር ግን ሰው ሊጠቀምብን የሚፈልገው ጠቃሚ ስለሆንን ነው:: ከሌላ ሰው ጥቅም ያልፈለገው ሰው ከእኛ ጥቅም ቢፈልግ ሰውን መጥቀም መቻላችን በራሱ ክብራችን ነው፡፡

እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፡— የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፡ በሉ። የሉቃስ ወንጌል 17:10

ሰው ሊጠቀምብን የሚፈልገውም እንዳንጠቀምበት ፈርቶ ከስጋት ከመነጨ ስሜት ሊሆን ይችላል:: እንዳልተጠቀምንበት ስጋቱን የምንቀንሰው ገፋ አድርገን እንዲጠቀምብን ስንፈቅድለት ነው::

ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡41

እግዚአብሄር በሰጠን ፀጋ ከሌላው ሰው እንደተሻልን የምናሳየውና በእግዚአብሄር የሚያስችል ሃይል የምንኩራራው ተጨማሪውን ምእራፍ በራሳችን ፈቃድ ስንሄድ ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ተጠቀምክበትና ተጠቀመብህ የሚለው ጥያቄና ስሜት ቀላል መልስ ያለው  ጥያቄ አይደለም:: ሰውን እናንተ እንዳልተጠቀማችሁበት ወይም ሌላው እንደተጠቀመባቹ በንግግር ከማሳመን ይልቅ ክርክር ያስነሳውን ጥቅማችሁ የተባለውን ነገር መተው ይቀላል::

መፍቀድ የሌለባችሁ ግልፅ የሆነ አላግባበ መጠቀም ካልሆነ በስተቀር አግባብና አላግባብ የሆነውን መጠቀም ለመለየት ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህ ሰውን እናንተ እንዳልተጠቀማችሁበት ወይም ሌላው እንዳልተጠቀምባቹ በንግግር ከማሳመን ይልቅ ክርክር ያስነሳውን ጥቅማችሁ የተባለውን ነገር መተው ውጥረት ይቀንሳል ሰላምን ይሰጣል::

ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። ወደ ሮሜ 12:18

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእግዚአብሔርን ባለጠግነት የምንካፈልበት ስልት

67018703_10214529962544437_589549553468833792_o.jpg

እግዚአብሄር ባለጠጋ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነ የሚጎድለው የሌለ ባለጠጋ አምላክ ነው፡፡

እርሱ ባጠጋ ሆኖ ልጆቹ እንዲያጡና እንዲጎድላቸው የሚፈልግ አባት እንደሌለ ሁሉ እግዚአብሄር ልጆቹም ያጡትንና የጎደላቸውን ነገር ይው እንዲልምኑት ይፈልጋል፡፡ ልጆቹ ከእርሱ ባለጠግነት ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ አባት ሁሉ እግዚአብሄርም በፀሎት ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋይ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡

ልጆቹ ከእርሱ ባለጠግነት እንዲካፈሉ የሚፈልግ ጌታ የሰው ልጆች እንዲፀልዩ በብዙ ቦታዎች ያበረታታል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄርን ያየው አንዳች እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው እንደሚል ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ልብ ሲተርከው ሰዎች መፀለይ እንዳለባቸው በብዙ ቦታዎች በምሳና ካለ ምሳሌ በተደጋጋሚ ሲያስተምር እንመለከታለን፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7

ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? የሉቃስ ወንጌል 18፡1፣7-8

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡23-24

ኢየሱስ ስለፀሎት ያስተማረበትን ስንመለከት እግዚአብሄር ለልጆቹ ያልውን ቅናት እንመለከታለን፡፡ ልጆቹ ምን የመሰለ አባት በሰማይ እያላቸው ባለመለመናቸው ብቻ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋዮች አለመሆናቸውን አይቶ ይቀናል፡፡ ኢየሱስ ስለፀሎት ያስተማረውን ስንመለከት ልጆቹ ቶሎ ስለፀሎት ተረድተው እንዲፀልዩና ከእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋይ እንዲሆኑ የቀናላቸውን የእግዚአብሄርን ቅናት እናስተውላለን፡፡

እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ የዮሐንስ ወንጌል 16፡24

እንደ እውነቱ ከሆነ መፀለይና መቀበል የሚገባንን ያህል አልተቀበልንም፡፡ የእግዚአብሄር ግምጃ ቤት ሙሉ ነው፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8

ብዙ ክርስትያኖች እግዚአብሄር አባታቸው ባለጠጋ ሆኖ እነርሱ ግን በጉድለት የሚኖሩበት ምክኒያት ለመፀለይ በመጀመሪያ ራሳቸውን ስለሚያዩ ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ እንደ ደሞዛችሁ መጠል ለምኑ ፣ እንደ ገቢያቹ መጠን ለምኑ ፣ እንደ ባንክ ሂሳባችሁ መጠን ለምኑ ያለ ይመስላቸዋል፡፡

እግዚአብሄር ግን ያው ለምኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያበረታን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድንለምን ነው፡፡

ሲጀመር የሚለምን ሰው የሚለመነው ነገር ያለው ሰው አይደለም፡፡ የሚለምን ሰው የጎደለው የሌለው ሰው ነው፡፡ የሚለምን ሰው እንዲኖረው የሚፈልግ እንጂ ያለው ሰው አይደለም፡፡

ያለመቀበላችን ምክኒያት አለመለመናችን ነው፡፡

ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡2

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ለምኑ #ፈልጉ #አንኳኩ #ይቀበላል #ያገኛል #ይከፈትለታል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በጣም የጓጓንለት ነገር ያሳፍረናል

your will.jpg

ለአንድ ነገር በጣም መጓጓት ለነገሩ ያለንን የእውቀት ማነስ ሊያሳይ ይችላል:: ለአንድ ነገር ያለን መጓጓት ግምት አሰጣጣችን መዛባቱን ከማሳየቱም በላይ ይፍጠንም ይዘግይም እንደሚያሳዝነን እርግጥ ነው::

ከሰማይ በታች የሚያጓጓ ነገር የለም:: ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም:: አዲሱ ነገር ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው:: አዲሱ ነገር በፍቅር መኖር ነው:: አዲሱ ነገር ጌታንና ሰውን መውደድ ነው:: አዲሱ ነገር ጌታን መከተልና ማምለክ ነው::

ከጌታ ውጭ በጣም የሚያጓጓ ምንም ነገር የለም::

የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም። መጽሐፈ መክብብ 1:9

ሰው ሰውን የማገልገል ሀላፊነቱን ከተረዳው ስለ ስልጣን በጣም አይጓጓም::

ሰው ከዝነኝነት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሀላፊነት ከተረዳ የዝነኝነት ጥቅም ያን ያህል አያጓጓውም::

ሰው ሀይሉን በሚገባው ቦታ ላይ ብቻ የማዋል ከፍተኛ ሀላፊነት እንደተጫነበት የሚርዳ ሰው ሃይል እና ስልጣን ለማግኘት አይቸኩልም:: ስልጣን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የማገልገል ሃላፊነትም እንደሆነ የተረዳ ሰው ስልጣንን ያን ያህል አይመኝም፡፡

የትዳርን ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን ሃላፊነቱንም በሚገባ የተረዳ ሰው ተግዳሮቱን እንዳልተረዳው ሰው የብቸኝነት ጊዜውን ሳያጣጥል አክብሮ በሚገባ ይጠቀምበታል::

ከሚጠብቀው ነገር ውስጥ ጥቅም ብቻ የሚጠብቅና ሃላፊነቱን የማይረዳ ሰው በራሱ ይሰናከላል:: እያንዳንዱ ጥቅም ከሃላፊነት ጋር ይመጣል::

እያንዳንዱ አገር የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የማይረዳ ሰው አገር በመለውጥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከተግዳሮት ለማረፍ እጅግ ይጓጓል::

ለነገ ከመጠን በላይ የሚጓጓው እያንዳንዱ ቀን ከራሱ ጭንቀት ጋር አብሮ እንደሚመጣ የማያውቅ ሰው ብቻ ነው::

ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6:34፤

ከእግዚአብሄር ውጭ ሙሉ ትኩረታችንን ሊወስድ የሚገባው ምንም ነገር ሊኖር አይገባውም፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ በጣም የምንጓጓለት ነገር ከመጠን በላይ ስላጋነንነው ያስቀይመናል፡፡

ለእግዚአብሄር ብቻ መስጠት ያለብንን ትኩረት ለሌላ ለምንም ነገር በመስጠት እግዚአብሄርን አንስቀናው::

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ዘላለማዊ #አዲስ #ልብ #ሰማይ #ዘላለም #ጌታ #ከፀሐይበታች #ያልፋሉ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ዛሬ ካልሆነ መቼ?

0 (1).jpg

ህይወት ደስ ይላል፡፡ ህይወት ምን ያህል እንደሚጣፍጥ የምናውቅው ልናጣው ስንል ነው፡፡ የህይወትን ክብር ይበልጥ የምንረዳው ከሞላ ጎደል አጥተነው ስናገኘው ነው፡፡

እግዚአብሄርን አሁን ካላመሰገነው መቼ እናመሰግነዋለን፡፡

ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል። ትንቢተ ኢሳይያስ 38፡18-19

አንድ የእግዚአብሄር ሰው ሲናገር ለስኬት የሚያስፈልገው ቤት ብቻ ነው ይላል፡፡ ሲቀጥልም ለስኬት የሚያስፈልገው በስጋ ውስጥ መኖር ህያው መሆን በህይወት መኖር ብቻ ነው፡፡ በህይወት የሚኖር ሰው ለስኬት ተስፋ አለው፡፡ ሰው በምድር ላይ ለስኬት ተስፋው የሚያከትመው ከስጋ ከወጣ ብቻ ነው፡፡

አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥ ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፤ እኛ ሕያዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔርን እንባርካለን፡፡ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 115፡17-18

እግዚአብሄርን ለማመስገን የሚያስፈልጉት ነገሮች ህያው መሆንና ህያው መሆን ብቻ ናቸው፡፡

ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት። በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት። በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት። በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 150፡1-6

እግዚአብሄርን ለማመስገን ቀን መቅጠር አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን አንዱና ብቸኛው ቅድመ ሁኔታ ህያው መሆን በህይወት መኖር ነው፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ።

ነገ ያንተ አይደለም፡፡ ዛሬን በህይወት የጠበቀህን ነገን ሊሰጥህ የሚችለውን እስትንፋስህን በእጁ የያዘውን እግዚአብሄርን ዛሬ አመስግን፡፡

አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። የያዕቆብ መልእክት 4፡13-16

እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት። ዕብራውያን 13፡15

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙረ ዳዊት 150፡6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች

your will1.jpg

ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28

እስራኤል ህይወቱ ቅርፅ አልባ ስለሆነበት መንገዴ ከእግዚአብሄር ተሰውራለች ሲል እንመለከተዋለን፡፡ እስራኤል ህይወቱ የተበታተነ እና የተወሳሰበ ስለሆነ ከዚህ ቅርፅ አልባ ህይወቱ ሊወጣ እንደማይችል አስቧል፡፡ እስራኤል ጥያቄው ውስብስብ በመሆኑ ሊፈታ እንደማይችል ተስፋ ቆርጧል፡፡ እስራኤል በህይወቱ ካሉ መልሶች ይልቅ ጥያቄዎቹ በዝተዋል፡፡

አሁንም እያንዳንዳችን አንዳንዴ ህይወታችን እንደተበታተነ ቅርፅ አልባ እንደሆነና የህይወታችንን መንገድ ማንበብ እንደማንችእል ይሰማናል፡፡ አንዳንዴ የህይወታችን ክር እንደተበተበና ውሉ እንደጠፋ እንደተወሳሰበ ይሰማናል፡፡

አንዳንዴ የህይወታችንን መንገድ ጫፉ እንደማይያዝ መጀመሪያውና መጨረሻው እንደማይታወቅ ይሆናል፡፡ የህይወታችንን እንቆቅልሽ መጀመሪያውንና መጨረሻ ማገናኘት ያቅተናል፡፡

ይህ ስሜት መርገም አይደለም፡፡ ይህ ስሜት ለእርዳታ እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ትሁት የሚያደርግን ተፈጥሮአዊ ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ህይወታችንን በራሳችን እንደማንወጣው የሚያስታውሰን ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ህይወታችን በእግዚአብሄር እንጂ በእኛ እንዳልተያዝ የሚያስታውስን ስሜት ነው፡፡

የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት። መጽሐፈ ኢዮብ 12፡10

ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም። ትንቢተ ዳንኤል 5፡23

ህይወታችንን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ማወቅ የለብንም፡፡ የምናውቃቸው ነገሮች አሉ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ ሁሉንም ካወቅን እግዚአብሄር እንጂ ሰው ልንሆን አንችልም፡፡ ሁሉንም ነገር ካወቅን በእግዚአብሄር ላይ መታመን አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ነገር ማድረግ ከቻልን የእግዚአብሄር እርዳታ አያስፈልግም፡፡

ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ኦሪት ዘዳግም 29፡29

ሁሉን በሚያውቅ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ያለብን እኛ እውቀት ሁሉ ስለሌለን ነው፡፡

የእግዚአብሄር አምላካዊ መልስ ግን እንዲህ ይላል፡፡

እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡27-28

አንተ አላወቅክም ማለት እግዚአብሄር አላወቀም ማለት አይደለም፡፡ አንተ የህይወትህ ንድፍ ዲዛይን የለህም ማለት እርሱ የለውም ማለት አይደለም፡፡

አንተ የሚያስፈልግህ አንድ ነገር በምታውቅው እርምጃ እየወሰድክ በማታውቅው በሚያውቀውና ማስተዋሉ በማይመረመረው እግዚአብሄር ላይ መደገፍ ነው፡፡ እንደ እርሱ እንድትበረታ ፣ እንደ እርሱ እንድታስተውል ፣ እንደ እርሱ እንድታውቅና እንደ እርሱ እንድትራመድ የሚያስፈልግህ እርሱን በመተማመን መጠበቅ ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡31

እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡

እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና። ትንቢተ ኢሳይያስ 41፡13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበት #መተማመን #እምነት #ያድሳሉ #ይወጣሉ #አይደክሙም #አይታክቱም #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ፍቅር አይወድቅም

maison-du-monde-fleche-nouveau-la-flc2a8che-maison-d-enfants-reine-marie-henriette-asbl-don-of-maison-du-monde-fleche1.jpg

ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8

ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡

ፍቅር የእግዚአብሄር ባህሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደማይወድቅ ሁሉ ከእግዚአብሄር የሚገኘውና በእግዚአብሄር የሚደገፈው ፍቅር አይወድቅም፡፡ እግዚአብሄር ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጊዜው እንደማያልፍበት ሁሉ ፍቅር ጊዜው አያልፍበትም፡፡ እግዚአብሄር ጊዜ እንደማይሽረው ሁሉ ፍቅር ጊዜ አይሽረውም፡፡

ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡7-8

ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡

ፍቅር የአንድ ሰሞን አይደለም፡፡ ፍቅር ወረት አያውቅም፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡

ፍቅር ሃያል ነው፡፡

ፍቅር የሚያሸንፈው የለም፡፡ ፍቅር ምንም ህግ አይገዛውም፡፡ ፍቅርንብ የሚከለክል ህግ የለም፡፡ ፍቅርን የሚረታ ስልጣን የለም፡፡

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23

ፍቅር ደካማ አይደለም፡፡

ፍቅር በሁኔታዎች የሚደገፍ ደካማ አይደልም፡፡ ፍቅር አሸናፊ ነው፡፡ ፍቅር ሁሉን ይረታል፡፡ ፍቅር እንደሁኔተው ይሚለዋወጥ አይደለም፡፡ ፍቅር የራሱ የማይለወጥ መርህ ያለው ባህሪ ነው፡፡

ፍቅር ቋሚ እና ዘላቂ ነው፡፡

ፍቅር ዘላቂ ነው፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡ ፍቅር አይቆምም፡፡

ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡

ፍቅር የውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር የመረዳት ነገር ነው፡፡ ፍቅር ስሜታዊ አይደለም፡፡ ፍቅር ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ አይደለም፡፡ ፍቅር እስከ መጨረሻው ይሄዳል፡፡

ፍቅር ያሸንፋል፡፡ በብዙ ነገር የማይረቱ አሉ፡፡ ፍቅር የማይረታው ሰው ግን ማንም የለም፡፡ የየሰው መረዳት እንደሰው አይነት ይለያያል፡፡ ብዙ ነገርን ሊረዳ የማይችል ብዙ ሰው አለ፡፡ ፍቅርን ሊረዳ የማይችል ሰው ግን የለም፡፡ ብዙ ነገር የማይማረከው ሰው አለ፡፡ ፍቅር የማይማረከው ሰው ግን የለም፡፡

እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። የዮሐንስ ወንጌል 13፡35

ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ፍቅር አይወድቅም

maison-du-monde-fleche-nouveau-la-flc2a8che-maison-d-enfants-reine-marie-henriette-asbl-don-of-maison-du-monde-fleche.jpg

ፍቅር አይወድቅም

ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8

ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡

ፍቅር የእግዚአብሄር ባህሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደማይወድቅ ሁሉ ከእግዚአብሄር የሚገኘውና በእግዚአብሄር የሚደገፈው ፍቅር አይወድቅም፡፡ እግዚአብሄር ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ፍቅር ዘላለማዊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጊዜው እንደማያልፍበት ሁሉ ፍቅር ጊዜው አያልፍበትም፡፡ እግዚአብሄር ጊዜ እንደማይሽረው ሁሉ ፍቅር ጊዜ አይሽረውም፡፡

ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡7-8

ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡

ፍቅር የአንድ ሰሞን አይደለም፡፡ ፍቅር ወረት አያውቅም፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡

ፍቅር ሃያል ነው፡፡

ፍቅር የሚያሸንፈው የለም፡፡ ፍቅር ምንም ህግ አይገዛውም፡፡ ፍቅርንብ የሚከለክል ህግ የለም፡፡ ፍቅርን የሚረታ ስልጣን የለም፡፡

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23

ፍቅር ደካማ አይደለም፡፡

ፍቅር በሁኔታዎች የሚደገፍ ደካማ አይደልም፡፡ ፍቅር አሸናፊ ነው፡፡ ፍቅር ሁሉን ይረታል፡፡ ፍቅር እንደሁኔተው ይሚለዋወጥ አይደለም፡፡ ፍቅር የራሱ የማይለወጥ መርህ ያለው ባህሪ ነው፡፡

ፍቅር ቋሚ እና ዘላቂ ነው፡፡

ፍቅር ዘላቂ ነው፡፡ ፍቅር አይለወጥም፡፡ ፍቅር አይቆምም፡፡

ፍቅር ጊዜያዊ አይደለም፡፡

ፍቅር የውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር የመረዳት ነገር ነው፡፡ ፍቅር ስሜታዊ አይደለም፡፡ ፍቅር ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ አይደለም፡፡ ፍቅር እስከ መጨረሻው ይሄዳል፡፡

ፍቅር ያሸንፋል፡፡ በብዙ ነገር የማይረቱ አሉ፡፡ ፍቅር የማይረታው ሰው ግን ማንም የለም፡፡ የየሰው መረዳት እንደሰው አይነት ይለያያል፡፡ ብዙ ነገርን ሊረዳ የማይችል ብዙ ሰው አለ፡፡ ፍቅርን ሊረዳ የማይችል ሰው ግን የለም፡፡ ብዙ ነገር የማይማረከው ሰው አለ፡፡ ፍቅር የማይማረከው ሰው ግን የለም፡፡

እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። የዮሐንስ ወንጌል 13፡35

ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው

36389cde-7781-4f1e-be1d-1bb3eaa8c89a.jpg

እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 3:16-18

ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡

ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄርን ክንድ አይተናል ነገር ግን አሁን ስላለንበት ሁኔታ ደግሞ ይህንንም ሊያደርግ ይችላል ብለን እናስባለን፡፡ መልሱ ግን ያ አላልፍም ብለህ ግን ያለፍክበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡ ያንን አለልፍም ብለህ ያለፍክበት ሁኔታን እንደለወጠ ሁሉ ይህንንም ሊለውጥ ይችላል፡፡ ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል፡፡

እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ። የሉቃስ ወንጌል 18፡27

ብዙ ጊዜ ተስፋ እንድንቆርጥና ወደኋላ እንድንመለስ የሚፈትነንም በአካባቢያችን ስለሁኔታው እውነተኝነት የሚመሰክሩ ምልክቶች አለመኖራቸው ነው፡፡

እግዚአብሄር ለዚህም መልስ አለው፡፡ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችሁ ምልክቱ ስለሁኔታው እውነተኝነት የሚመሰክሩ ምልክቶች አለማየታችሁ ነው፡፡

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፡፡

የፈራችሁትም ውድቀት አይደርስባችሁም፡፡

እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።

ውድቀት አይደርስባችሁም ብቻ ሳይሆን በህይወታችሁ እውነተኛውን ድል ታገኛላችሁ፡፡ በዚህም እግዚአብሄር የልባችሁ መሻት ይሞላል፡፡

ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል።

ምክንያቱም ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፡፡

እግዚአብሄርን የሚያሳስበው ሰውን የሚያሳስበ አይደለም፡፡ ሰውን የሚያሳስብው ውሃ አለመምጣቱ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያሳስበው ነገር በእግዚአብሄር አይን ቀላል የሆነውን ነገር እግዚአብሄር ሲያደርግ ሰው ለታእምሩ አለመዘጋጀቱ ነው፡፡ የሰው ትኩረት ታእምሩ እንዴት እንደሚሆን ነው፡፡ የእግዚአብሄር ትኩረት ሰው ተአምሩን እንዴት በሚገባ እንደሚጠቀምበት ነው፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ።

እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድጓድ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 3:16-18

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

 

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

 

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የህይወት ከፍተኛው የእርካታ ደረጃ

E9CDEE7E-FE0C-4AD7-94ED-57ED91D9E698.jpeg

የህይወትከፍተኛውየእርካታደረጃ

ሰውበእግዚአብሔርመልክእናአምሳልበእግዚአብሔርክብርተፈጥሯል::

እንደዝናገንዘብስልጣንያሉተራነገሮችበራሳቸውበእግዚአብሔርመልክናአምሳልበእግዚአብሔርክብርለተፈጠረውሰውእውነተኛናዘላቂየእርካታስሜትሊሰውን  አይችሉም::

እንደዝናገንዘብስልጣንያሉነገሮችሰውየተፈጠረበትሌሎችንበፍቅርየማገልገልአላማለማሳካትየሚጠቅሙመሳሪያዎችእንጂበራሳቸውየህይወትግብአይደሉም::

ሰውየሚረካውየተፈጠረበትንየእግዚአብሄርአላማሲፈፅምብቻነው::

ሰውየሚረካውየተፈጠረበትንሌሎችንየማገልገልአላማከግብሲያደርስብቻነው::

ሰውየሚረካውየተፈጠረበትንሌሎችንበፍቅርየማገልገልአላማከግብሲያደርስብቻነው::

በሚያደርገውነገርሁሉየተሳካለትሰውየተፈጠረበትየእግዚአብሔርንአላማከሳተውውጤቱሁሉምነገርበዜሮእንደሚባዛውጤቱዜሮነው::

በሰዎችናበመላእክትልሳንብናገርፍቅርግንከሌለኝእንደሚጮኽናስወይምእንደሚንሽዋሽዋጸናጽልሆኜአለሁ።ትንቢትምቢኖረኝምሥጢርንምሁሉናእውቀትንሁሉባውቅ፥ተራሮችንምእስካፈልስድረስእምነትሁሉቢኖረኝፍቅርግንከሌለኝከንቱነኝ።ድሆችንምልመግብያለኝንሁሉባካፍል፥ሥጋዬንምለእሳትመቃጠልአሳልፌብሰጥፍቅርግንከሌለኝምንምአይጠቅመኝም።1ቆሮንቶስ13:1-3

ሰውብዙዝናገንዘብናስልጣንባይኖረውምባለውነገርሁሉተጠቅሞሌላውንበፍቅርየሚያገለግልሰውከእርሱበላይየተሳካለትሰውየሌለየመጨረሻየተባረከሰውነው::

ወንድሙንም ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል

life-insurance-for-dummies.jpg

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። የማቴዎስ ወንጌል 5፡22

እግዚአብሄር አንድ ላይ እንድንኖር ማህበራዊ ፍጥረቶች አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያለው ፍላጎት የሚያሟላው አጠገባችን ባለው ሰው ስጦታ ተጠቅሞ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው በስጦታችን የሌላውን ሰው ፍላጎት ለማሟላት ነው፡፡

እግዚአብሄር ሲፈጥረን የተለያን አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ ሁላችንም የተለያየ አስተሳሰብ ፣ አመለካከት ፣ ስጦታ ፣ ዝንባሌና  ፍላጎት ያለን ሰዎች ነን፡፡  ስላለን ትክክል ነው ብለን ስለምናምነው አስተሳሰብ ፣ አመለካከት ፣ ስጦታ ፣ ዝንባሌና  ፍላጎት ንስሃ እንደማንገባ ሁሉ ሌላውም ሰው ማንንም ይቅርታ ባይጠይቅ መገረም የለብንም፡፡ እኔ እስከ ልዩነቴ ሰዎች እንዲቀበሉኝ ወይም እንዲታገሱኝ እንደምፈልገው ሁሉ ሌላውም ሰው እንድንታገሰው ይፈልጋል፡፡

ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው። የሉቃስ ወንጌል 6፡31

በምድር ላይ ስኬታማ ለመሆን ልዩነታችንን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እንዲያውም በምድር ላይ ፍሬያማ ለመሆን ልዩነታችንን ተረድቶ እንደ ልዩነታችን መኖር ግዴታ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንኳን ያላደረገውን ሁሉንም ሰው አንድ አይነት ለማድረግ በሞከር ህይወትን ከማባከን የሰውን ልዩነት ለመቀበል ልብን ማስፋት ጥቅም አለው፡፡ የሰዎችን ልዩነት የማይረዳ ሰው በህይወቱ ስኬትንና ፍሬያማነትን ሳያይ ያልፋል፡፡

ከእኛ የተለዩ ብዙ ሰዎች ባሉበት ምድር ውስጥ መኖር ትህትናን ይጠይቃል፡፡ በፍፁም የማንረዳቸው ሰዎች ባሉበት ምድር ውስጥ ለመኖር ራስን ማዋረድ ይጠይቃል፡፡ በፍፁም የማይረዱን ሰዎች ባሉበት ምድር ውስጥ በሰላም መኖር መረዳትን ይጠይቃል፡፡ በፍጩም የማንረዳቸው ሰዎች ባሉነት መድር ወስጥ መኖር ራሰን መግዛት ይጠይቃል፡፡

ማናችንም ራሳችንን አልፈጠረንም፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄር ለራሱ የፈጠረን የእግዚአብሄር ባሪያዎች ነን፡፡ የፈጠራቸው እግዚአብሄር አለ እንጂ ማናችንም ሌላውን ሰው አልፈጠርንም፡፡ ሰውም በመጨረሻ ተጠሪነቱ ለፈጠረው ለእግዚአብሄር እንጂ ለእርስ በእርሳችን አይደለም፡፡

እኛ የእግዚአብሄር ፍጥረት እንደሆንን ሁሉ ወደድንም ጠላንም የማይመቸን ሰው የእግዚአብሄር ፍጥረት ነው፡፡ እኛን እግዚአብሄር እንደሚወደን ሁሉ ወደድንም ጠላንም በፍጹም የማይረዳንን ሰው ወዶታል፡፡ የእኛ ድርሻ እግዚአብሄር ከፈጠራቸው ሰዎች ጋር በትህትና መኖር ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋረ በትህትና መሄዳችን የሚታየው ከፈጠራቸው ጋር በትህትና በመኖር ነው፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8

ሌላውን መጣል የራስን አንድ የሰውነት ክፍል እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሌላውን መጣል አንዱን በረከታችንን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሌላው ላይ መፍረድ ትእቢት ነው፡፡ ሌላው ላይ መፍረድ የእግዚአብሄርን ቦታ መውሰድ ነው፡፡ ሌላው ላይ መፍረድ ከእግዚአብሄር በላይ አውቃለሁ ማለት ነው፡፡ ሌላው ላይ መፍረድ አለም የምትተዳረው እንደ እግዚአብሄር ሳይሆን እንደ እኔ ህግ ነው ማለት ነው፡፡ ሌላው ላይ መፍረድ ማለት አለም ሰው መተዳደር ያለበት እንደእኔ መረዳት እንጂ እንደ እግዚአብሄር መረዳት አይደለም ማለት ነው፡፡

በመፅሃፍ ቅዱስ ሌላውን መጣል እንደሚያስፈርድ የሚያስተምረው ስለዚህ ነው፡፡

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። የማቴዎስ ወንጌል 5፡22

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #ደንቆሮ #የሚቆጣ #ፍርድ #ጨርቃም #ትህትና #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ቸሩ እግዚአብሔር

balloon-flower.jpg

እግዚአብሄር አይለወጥም የእግዚአብሄር መልካምነት አይለወጥም

እግዚአብሄር ሁሌ መልካም ነው፡፡ የእግዚአብሄር መልካምነት ባህሪው ነው፡፡ እግዚአብሄርን ብታገላብጡት መልካም እንጂ ክፉ ሊሆን አይችልም፡፡

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።  የያዕቆብ መልእክት 1፡16-17

እግዚአብሄር ከምድር አባት ሁሉ የሚበልጥ ልዩ አባት ነው

አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣል፡፡

ይህ ከምድር ኣበቶች ሁሉ በአባትነቱ መልካምነት የሚበልጠው እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት ላመንን ሁላችን አባታችን ሆኖዋል፡፡

ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? የማቴዎስ ወንጌል 7፡9-11

እግዚአብሄር የመልካምነት ማጣቀሻ ነው፡፡

ስለአንድ መልካምነት ክርክር ከተነሳ ውሳኔውን የሚሰጥ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ መልካም የሚባለው እግዚአብሄር መልካም ካለው ነው፡፡ ክፉ የሚባለው እግዚአብሄር  በቃሉ ክፉ ካለው ብቻ ነው፡፡ የመልካምነት ደረጃ መዳቢ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መልካምነት በወሳኝ ጊዜ ይታያል

ብዙ መልካም ሊያደርጉልን የሚፈልጉ በመካከላችን አሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም በማይችሉበት ጊዜ ምላምን ከሊያደርግልን የሚችል እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። ትንቢተ ናሆም 1፡7

የትኛውም መልካምነት የሚመነጨው ከእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

እናንትም ምንም መልካም ማድረግ ብትፈልጉ እግዚአብሄር ካልተጠቀመባችሁ ለማንም አትጠቅሙም፡፡

እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙረ ዳዊት 16፡2

ሰው ምንም ቢያዝናችሁ ሃዘናችሁን ይካፈላል እንጂ እግዚአብሄር ካልተጠቀመበት ምንም መልካምነት ሊያደርግላችሁ አይችልም፡፡

ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 18፡19

እግዚአብሄር ለእኛ የሚያስብ ፍፁም አሳብ ያለው መልካም አባት ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

ስለዚህ እግዚአብሄርን ማመስገን መልካም ነው፡፡ እግዚአብሄርን ባለማመስገን እንጂ እግዚአብሄርን አመስግኖ የሚሳሳት ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄር መልካም ነው፡፡

ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ መዝሙረ ዳዊት 107፡1

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

እግዚአብሄር ያሳፍራል

wallpaper.wiki-Peaceful-Pictures-PIC-WPE004376.jpg

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። ነገር ግን፡— የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ፡ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 1:26-31

 • ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤

እግዚአብሔር ጥበበኛን ቢመርጥ የሚረዳው ፈልጎ ነው ይባላል:: እግዚአብሔር እኛን ይረዳል እንጂ በማናችንም አይረዳም :: እግዚአብሔር ክብሩን ለማንም ስለማይሰጥ ሞኝን ነገር መረጠ:: እግዚአብሔር ሞኝን ጠቢብ ቢያደርግ ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው ይባላል::

ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የሐዋርያት ሥራ 4:13

 • ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤

እግዚአብሄር ከሰው ጋር አይወዳደርም:: እግዝአብሄር እኛን የሚያዋርደው ያንሰኛል እበልጠዋለሁ በምንለው ሰው ነው:: እግዚአብሔር ደካማውን ያበረታና የምንመካበት የእኛ ብርታት ምንም እንዳይደለ ያሳየናል::

እርሱም፡— ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና፡ አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። . . . ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12:9-10

 • እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥

እግዚአብሔር ይህ የትም አይደርስም የተባለውን አስነስቶ እርሱ ብቻ ክብሩን መውሰድ ይፈልጋል::

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2:8

እግዚአብሄር በተናቀው ተጠቅሞ የናቀውን ትእቢተኛውን ያስቀናል::

ነገር ግን፡— እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ፡— እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኋለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኋለሁ፥ ብሎአል። ወደ ሮሜ 10:19

ሰው በእግዚአብሔር ፊት የሚያስመካው አንዳች ነገር የለም:: ምንም እንድንበልጥ ያደረገን ነገር ቢኖረን ከእርሱ የተቀበልነው ብቻ ነው፡፡

አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡7

ሰው መመካት የሚችለውና የሚገባው እስትንፋሳችንን በእጁ በያዘው በጌታ ብቻ ነው::

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ተጠማው እልውናህን መገኘትህን ጌታ ድምጽህን መዓዛ ግርማህን አልፈልግም ኖረ ኖረ ኖረ ሞተ አልፈልግም መሆን በምድር የታመነ መንፈስክን ይዞ ይዞ ሚገሰግስ ለተጠማው ደርሶ የልብህን የሚያደርስ ንፋስክህን በላዬ በላዬ አንፍስ የሞተውን ደርሶ ተነስ ተነስ ብሎ ሚቀሰቅስ ውረድ በላዬ ላይ መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ዝናብ አትምቀኝ በመንፈስ እንደገና እውስጥ አስገባኝ መለኪያ የሌለው ያንተ ማንነትህ ውዴ ይምጣ በኔ እይወቴ ጌታ ሆይ ድንቅህ ታምራትህ እያየሁ እየሰማሁ እየያዝኩህ እየዳሰስኩ እንዳመልክህ እፈልጋልሁ መንፈስ ቅዱስ ተጠምቻልሁ እሱ አባት ነው እሱ አይጥልም እሱ ያደርሳል እሱ ይረዳል እሱ ይሰማል እሱ ይመልሳል እሱ ልዩ ነው ከሁሉም ይበልጣል ተጠማው ተጠማው ተጠምቻለው

ተጠማው እልውናህን መገኘትህን ጌታ ድምጽህን መዓዛ ግርማህን አልፈልግም ኖረ ኖረ ኖረ ሞተ አልፈልግም መሆን በምድር የታመነ መንፈስክን ይዞ ይዞ ሚገሰግስ ለተጠማው ደርሶ የልብህን የሚያደርስ ንፋስክህን በላዬ በላዬ አንፍስ የሞተውን ደርሶ ተነስ ተነስ ብሎ ሚቀሰቅስ ውረድ በላዬ ላይ መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ዝናብ አትምቀኝ በመንፈስ እንደገና እውስጥ አስገባኝ መለኪያ የሌለው ያንተ ማንነትህ ውዴ ይምጣ በኔ እይወቴ ጌታ ሆይ ድንቅህ ታምራትህ እያየሁ እየሰማሁ እየያዝኩህ እየዳሰስኩ እንዳመልክህ እፈልጋልሁ መንፈስ ቅዱስ ተጠምቻልሁ እሱ አባት ነው እሱ አይጥልም እሱ ያደርሳል እሱ ይረዳል እሱ ይሰማል እሱ ይመልሳል እሱ ልዩ ነው ከሁሉም ይበልጣል ተጠማው ተጠማው ተጠምቻለው

ተጠማው

እልውናህን መገኘትህን

ጌታ ድምጽህን መዓዛ ግርማህን

 

አልፈልግም ኖረ ኖረ ኖረ ሞተ

አልፈልግም መሆን በምድር የታመነ

መንፈስክን ይዞ ይዞ ሚገሰግስ

ለተጠማው ደርሶ የልብህን የሚያደርስ

ንፋስክህን በላዬ በላዬ አንፍስ

የሞተውን ደርሶ ተነስ ተነስ ብሎ ሚቀሰቅስ

 

ውረድ በላዬ ላይ መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደ ዝናብ

አትምቀኝ በመንፈስ እንደገና እውስጥ አስገባኝ

መለኪያ የሌለው ያንተ ማንነትህ

ውዴ ይምጣ በኔ እይወቴ

ጌታ ሆይ ድንቅህ ታምራትህ

 

እያየሁ እየሰማሁ እየያዝኩህ

እየዳሰስኩ እንዳመልክህ እፈልጋልሁ

መንፈስ ቅዱስ ተጠምቻልሁ

 

እሱ አባት ነው እሱ አይጥልም

እሱ ያደርሳል እሱ ይረዳል

እሱ ይሰማል እሱ ይመልሳል

እሱ ልዩ ነው ከሁሉም ይበልጣል

ተጠማው ተጠማው ተጠምቻለው

 

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን?

62459044_10157181161106411_6857141448156905472_n.jpg

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ወደ ገላትያ 1:10

ብዙ የሰውና የእግዚአብሔር ፍላጎት ጊዜ ይለያያሉ::

እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 16፡23

በሰው ወርቅ የሆነው ሃሳብ በእግዚአብሄር ግን የተሳሳተ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፡፡

ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍላጎት ጥቁርና ነጭን ቀለም እንደ መለየት ቀላል ይመስለናል:: አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሄር አሰራር የምናዝነው ወይም የምንሰናከለው እንደጠበቅነው ስለማይሆ ነው፡፡ እግዚአብሔር መልካምን ነገር እንዳገኝ ይፈልጋል እንላለን ነገር ግን  ከማን አንፃር መልካም የሆነውን እግዚአብሄር እንደሚፈልግ አንርዳውም::

ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍላጎት ምንድነው ብለን ከመጠየቅና ከመፈለግ ይልቅ እግዚአብሔር ይህ እንዲሆንልኝ ሳይፈልግ አይቀርም ብለን በግምት በስንፍና እግዚአብሔርን በራሳችን ትንሽ አእሮምሮ ልንወስነው እንፈልጋለን::

ክርስትና የሚጀምረው የአንተ እና የእኔ ሀሳብ የተለያየ ነው ብሎ ከማመን ነው:: ክርስትና ፍሬያማ የሚሆነው በትህትናና በየዋህነት የራሳችንን ሀሳብ እየጣልን የእርሱን ሃሳብ በተቀበልን መጠን ብቻ ነው:: ክርስትና የሚደመደመው ብእርሱ ሀስብ እርሱን ስንመስለው ነው:: ክርስትና የሚጣፍጠው አእምሮዋችንን በእግዚአብሄር ቃል አና በእግዚአብሄር ሀሳብ ካደስን ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2

የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመቀበልና ለመተግበር የራሳችንንና የሌላውን ሰው ሀሳብ መተው ይጠይቃል::

ከምንስበው በላይ ብዙ ጊዜ የሰው ሃሳብና የእግዚአብሔር ሃሳብ በፊታችን እንደምርጫ ይቀርብልናል:: ክርስቶስን በመከተል ፍሬያማ ለመሆን ለእግዚአብሄር ቃል አዎ ለሰው ሃሳብ ደግሞ አይ ማለትን መማር አለብን፡፡

ከምናስበው በላይ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርና የሰው ህሳብ ይራራቃሉ:: የሰውንና የእግዚአብሄርን ሀሳብ አንድ ላይ ማስኬድ ደግሞ በፍፁም አይቻልም::

ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ። አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡7-9

ብዙ ጊዜ ሰውን ደስ ለማሰኘት የእግዚአብሔርን ሃሳብ መጣል ይጠይቃል:: ብዙ ጊዜ እግዚአብሄርን ደስ ለማሰኘት የሰውን ሃሳብ መተው  ይጠይቃል::

ሰው ሊከበር ይገባዋል፡፡ ሰው ግን እንደ እግዚአብሄር ሊፈራ አይገባውም፡፡ ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፡፡

ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል። መጽሐፈ ምሳሌ 29፡25

አንዳንደ ጊዜ የእግዚአብሄርን ሃሳብ መርጠን የሰውን ቅያሜ ለመቀበል መዘጋጀት አለብን፡፡ የሰውን አስተያየት ሳንፈራ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለማድረግ ግንባራችንን የቡላድ ድንጋይ ማድረግ አለብን፡፡

ከቡላድ ድንጋይ ይልቅ እንዳለ አልማዝ ግምባርህን አጠንክሬአለሁ፤ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ቢሆኑ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ። ትንቢተ ሕዝቅኤል 3፡9

የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለማድረግ ሰዎች ነውር ነው የሚሉትን ነገር እንኳን ለማድረግ መዘጋጀት አለብን፡፡ እንደ ኢየሱስ እንደ ወንበዴ ተይዞ መሰቀል በብዙዎች ሰዎች ዘንድ ነውር ነው፡፡ ብዙዎች እንደወንበዴ ተይዘው ከሚሰቀሉ በእግዚአብሄር ሃሳብ ላይ ቢያመቻምቹ ይሻላቸዋል፡፡ ምሳሌያችን ኢየሱስ ግን ነውርን ናቀው እንጂ ከእግዚአብሄር ፈቃድ በላይ ነውርን አላከበረውም፡፡

እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ወደ ዕብራውያን 12፡2

የብዛት ጉዳይ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር አብሮ የሚቆም አንድ ሰው አብላጫ ነው፡፡

ይህ ሕዝብ፦ ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፦ ዱለት ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። ትንቢተ ኢሳይያስ 8፡12

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ፍቅር #ፍርሃት #ሃይል #ራስንመግዛት #አላማ #መዳን #ነፃነት #ቅድስና #ሰላም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ

ስምንቱ የአባቶች ቀን ውሳኔዎች

father_son_hd.jpg

 1. ልጆቼን ልመክርና ልገስፅ ግን ላላቆጣ እወስናለሁ

እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡4

 1. ለልጆቼ በእግዚአብሄር ቃል ምሳሌ ለመሆን እወስናለሁ

ባገኘሁት ጊዜ ሁሉ የስጋ ልጆቼ ላልሆኑት የአባትነትን ምክርና እንክብካቤ እሰጣለሁ፡፡

 1. ልጆቼን የእግዚአብሄርን መንገድ ለማሳየት ለማስተማር እወስናለሁ፡፡

ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። መጽሐፈ ምሳሌ 22፡6

 1. ለቤተሰቤ የሚያስፈልገውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል በመትጋት ለማቅረብ እወስናለሁ፡፡

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5፡8

 1. አባት ለሌለው ለድሃ አደጉ የመፍረድና የመከራከር መልካም ስራ በትጋት ለመስራት እወስናለሁ፡፡

መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ። ትንቢተ ኢሳይያስ 1፡17

 1. የቤተሰቡን ችግር ከፊት ሆኜ ልጋፈጥ ችግሩ ወደ ቤተሰቤ እንዳይመጣ ቤተሰቤን ልከላከልና ጥላ ልሆናቸው እውስናለሁ፡፡

አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ መዝሙረ ዳዊት 103፡13

 1. በማንኛውም ሁኔታ ቤተሰቤን ላፅናና እና ላበረታታ እወስናለሁ፡፡

የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡3

 1. በስጋ ልጄ ላልሆነ በተለይ ይህ የአባትነት እድል ለማያገኘው በየትም ስፍራ ለማገኘው ልጅ በቻልኩት መጠን ሁሉ የአባትነት ተምሳሌ ልሆነው በህይወቱ ላይ አንድ የማበረታቻ ቃል አንኳን ቢሆን የአባትነትን አስተዋፅኦ ለማድረግ እወስናለሁ፡፡

 

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

መልካም የአባቶች ቀን!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #ጥንካሬ #ራእይ #ደረጃመስጠት #ጥላ #ማበረታታት #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ልናጣው የማንችለው ነገር ሁሉ የእኛ አይደለም በህይወታችን ዘመን ብዙ በረከቶች ወደ ህይወታችን ይመጣሉ:: እኛን ለመባረክና እና ለመጥቀም እግዚአብሔር ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማል:: በህይወታችን ያለውን አላማውን ለመፈጸም እግዚአብሄር በብዙ አይነት እና በብዙ መንገድ የሚጠቀምባቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜው ናቸው እንጂ ለዘላለም አይደሉም:: ከእግዚአብሔር ውጭ ምንም ቋሚ ነገር የለም:: ከእግዚአብሔር ውጭ የሚታየው ነገር ሁሉ ሃላፊ ነው:: ቋሚ ያልሆነን ነገር እንደ ጊዜያዊነቱ በትክክል መያዝ ከብዙ ጭንቀት ያድናል:: ከእግዚአብሔር ውጭ ይህን ካላገኘሁ አልኖርም የምንለው ምንም ነገር መኖር የለበትም:: እግዚአብሔር የሚሰጠንን ነገሮች ጨምሮ አንድ ቀን እንደማንለያቸው አድርገን ውስጣችን ማስገባት ችግርን መጋበዝ ነው:: የራሳችንን ማንነትና ነፃነት እስከምናጣ ድረስ ሁኔታዎችን ውስጣችን መክተት ጊዜያዊዉን ነገር ስንለየው ስቃይ ውስጥ መግባት ያስገባናል:: የነገሮችን ጊዜያዊነትና ልካቸውን ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ የሚለውን ቃል መከትል ጥበብ ነው:: አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:5 ለዘላለም ከሚኖረው ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ ሁኔታዎችን ወደ ውስጣችን አለማስገባትና በውጭ መጠበቅ ስንለይ ከሚመጣ የመለያየት ስቃይ ይጠብቀናል:: የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4:17-18 ብዙ ጊዜ ሰይጣን የሚያስፈራራንና እስራት ውስጥ የሚከተን ይህን ነገር ብታጣውስ ብሎ በማስፈራራት ነው:: እግዚአብሔርን አልጣው እንጂ ካለእርሱ መኖር የማልችለው ምንም ነገር የለም ካልን ለሰይጣን እድል ፈንታ አንሰጠውም:: ከእግዚአብሔር ውጭ ካለእርሱ መኖር አልችልም የምንለው ነገር ካለ በዘመናችን ሁሉ በፍርሃት ባርነት ውስጥ እንቆያለን :: ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡27 በምንም ነገር በእውነት ተጠቃሚ የምንሆነው ላጣው አልችልም ብለን የምናስበውን ነገር ከሌለና ማንኛውንም ነገር ለማጣት ከተዘጋጀን ብቻ ነው:: ይህን ካጣኽው መኖር አትችልም የሚለው በፅኑ ልንቃወመው የሚገባ የሰይጣን ድምፅ ነው:: ልንይዘውና ልንጠቀምብት እንጂ ምንም ነገር ሊይዘን እና ሊቆጣጠረን አይገባም:: ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29-31 አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos #ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

C6138DB9-FC68-4AA9-A84C-D8A890B5063D.jpeg

ልናጣው የማንችለው ነገር ሁሉ የእኛ አይደለም
በህይወታችን ዘመን ብዙ በረከቶች ወደ ህይወታችን ይመጣሉ:: እኛን ለመባረክና እና ለመጥቀም እግዚአብሔር ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማል:: በህይወታችን ያለውን አላማውን ለመፈጸም እግዚአብሄር በብዙ አይነት እና በብዙ መንገድ የሚጠቀምባቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜው ናቸው እንጂ ለዘላለም አይደሉም::
ከእግዚአብሔር ውጭ ምንም ቋሚ ነገር የለም:: ከእግዚአብሔር ውጭ የሚታየው ነገር ሁሉ ሃላፊ ነው::
ቋሚ ያልሆነን ነገር እንደ ጊዜያዊነቱ በትክክል መያዝ ከብዙ ጭንቀት ያድናል::
ከእግዚአብሔር ውጭ ይህን ካላገኘሁ አልኖርም የምንለው ምንም ነገር መኖር የለበትም::
እግዚአብሔር የሚሰጠንን ነገሮች ጨምሮ አንድ ቀን እንደማንለያቸው አድርገን ውስጣችን ማስገባት ችግርን መጋበዝ ነው:: የራሳችንን ማንነትና ነፃነት እስከምናጣ ድረስ ሁኔታዎችን ውስጣችን መክተት ጊዜያዊዉን ነገር ስንለየው ስቃይ ውስጥ መግባት ያስገባናል:: የነገሮችን ጊዜያዊነትና ልካቸውን ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ የሚለውን ቃል መከትል ጥበብ ነው::
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:5
ለዘላለም ከሚኖረው ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ ሁኔታዎችን ወደ ውስጣችን አለማስገባትና በውጭ መጠበቅ ስንለይ ከሚመጣ የመለያየት ስቃይ ይጠብቀናል::
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4:17-18
ብዙ ጊዜ ሰይጣን የሚያስፈራራንና እስራት ውስጥ የሚከተን ይህን ነገር ብታጣውስ ብሎ በማስፈራራት ነው:: እግዚአብሔርን አልጣው እንጂ ካለእርሱ መኖር የማልችለው ምንም ነገር የለም ካልን ለሰይጣን እድል ፈንታ አንሰጠውም:: ከእግዚአብሔር ውጭ ካለእርሱ መኖር አልችልም የምንለው ነገር ካለ በዘመናችን ሁሉ በፍርሃት ባርነት ውስጥ እንቆያለን ::
ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡27
በምንም ነገር በእውነት ተጠቃሚ የምንሆነው ላጣው አልችልም ብለን የምናስበውን ነገር ከሌለና ማንኛውንም ነገር ለማጣት ከተዘጋጀን ብቻ ነው::
ይህን ካጣኽው መኖር አትችልም የሚለው በፅኑ ልንቃወመው የሚገባ የሰይጣን ድምፅ ነው::
ልንይዘውና ልንጠቀምብት እንጂ ምንም ነገር ሊይዘን እና ሊቆጣጠረን አይገባም::
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29-31
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እንደ ህፃናት ካልሆናችሁ

your will1.jpg

ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። የማቴዎስ ወንጌል 18፡2-3

ሰው የተፈጠረው እንደ ህፃን የዋህ ተደርጎ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን በሰይጣን ተንኮል አእምሮዋቸው ከመበላሸቱ በፊት እንደህፃን እግዚአብሄርን ሙሉ ለሙሉ ያምኑት ነበር፡፡ ከውድቀታቸው በፊት ለአዳምና እና ለሄዋን እግዚአብሄር አንድን ነገር አለ ማለት ሆነ ተደረገ ማለት ነበር፡፡ ከሃጢያት በኋላ ግን ሰው የህጻንነት የዋህነቱንና ገርነቱ አጥቷል፡፡

በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡2-3

ህፃናት ከአዋቂዎች የተለየ ባህሪ አላቸው፡፡ ይህ ባህሪ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ በጣም የሚፈልግ ባህሪ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ስርአት እንደ ህፃናት የሆኑ ሰዎች ብቻ እንዲከናወኑበት የተሰራ ስርአት ነው፡፡ እንደ ህፃን ለማይሆኑ ሰዎች የእግዚአብሄር መንግስት ለማደግና ለማፍራት ተስማሚ ስፍራ አይደለም፡፡ የህፃንነት ባህሪ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሁኔታዎችን ተቋቁመን እንድናልፍ የሚያደርግ ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡ የህጻንነት ባህሪ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሙሉ ተጠቃሚ የሚያደርገን እግዚአብሄር ወዳየልን የህይወት ከፍታ የምንወጣበት ባህሪ ነው፡፡

አንድ አዋቂ ሰው የልጆች አለም ውስጥ ገብቶ እንደ ልጆቹ መጫወቻውን ቦታ ሊደሰትበት ፣ ሊዝናናበት እና ሊጠቀምበት እንደማይችል ሁሉ እንደህፃን የማይሆን ሰው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ደስተኛ ሊሆን ፣ በሚገባ ሊኖርና ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡ ከዋህነትና ከገርነት ጉድለት በአጠቃላይ እንደህፃናት ካለመሆን እንድንመለስና እንደ ህፃናት እንድንሆን እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆነው የህፃናት ባህሪ ምን እንደሆነ ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡፡

 1. ህፃናት ቀጥተኛ ናቸው

ህፃናት በልባቸው የሚያስቡትና በአፋቸው የሚናገሩት የተለያየ አይደለም፡፡ ህፃናት በልባቸው አንድ ነገር በአፋቸው ሌላ ነገር የለም፡፡ ህፃናት አንድ ናቸው፡፡ ህፃናት በተንኮል ወይም በድብቅ ሃሳብ አእምሮዋቸው አልተበላሸም፡፡ ህፃናት ቀጥተኛና ንፁህ ናቸው፡፡ ህፃናት ቅን ናቸው፡፡

በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡2-3

 1. ህፃናት ለማመን ፈጣን ናቸው

ህፃናት ለማመን ይፈጥናሉ፡፡ ህፃናት በቀላሉ ራሳቸውን ይሰጣሉ፡፡ እኛም በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ቃሉን እንድናምን እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ በተስፋ ቃሉ ሙሉ ለሙሉ እንድንደገፍ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ለቃሉ ህጻናት እንድንሆንና በቃሉ የተናገረውን ነገር ሳንጠራጠር በፍጥነት እርምጃ እንድንወስድ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ። የያዕቆብ መልእክት 1፡21

እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡1-3

 1. ህፃናት በደልን አይቆጥሩም

እስከምትደነግጡ ድረስ ህፃናት በደልን በቶሎ ይረሳሉ፡፡ ህፃናት በደልን አያጠራቅሙም፡፡ ህፃናት ክፉን በክፉ ለመመለስ አያቅዱም፡፡ ህፃናት በደልን ይተዋሉ፡፡

ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡17

የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5

 1. ህፃናት ትንሽ ስጦታ ያስደንቃቸዋል

ህግፃናት ያመሰግናሉ፡፡ ህፃናት ትንሽ ነገርን ማድነቅ ይችላሉ፡፡ ህፃናት ያላቸው ነገር ላይ እንጂ ያላገኙት ነገር ላይ አያተኩሩም፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡15

 1. ህፃናት አይጨነቁም

ህፃናት የሚኖሩት በዛሬ ውስጥ ነው፡፡ ህፃናት በትላንት ወይም በነገ ውስጥ አይኖሩም፡፡ ህፃናት የሚኖሩት እያንዳንዱን ቀን አንድ በአንድ ነው፡፡

ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡34

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ህፃንነት #ብስለት #ጥበብ #ማስተዋል #አላማ #ቅንነት #የዋህነት #አለመጨነቅ #እምነት #ማድነቅ #ማመስገን #በደልንአይቆጥርም ##መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ

እንዳለ

745816b037a32c3.jpg

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

እንደ እውነቱ ከሆነ በእግዚአብሄር የማያምኑ ብዙ ሰዎች በምድር ላይ አሉ፡፡ እርሱም ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የማያምኑ ብዙ የሃይማኖት ተከታዮች በምድር ላይ ይኖራሉ፡፡ እውነት ነው እግዚአብሄር የለም ብለው የሚያምኑ እና በግልፅ የሚናገሩ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን በልባቸው እግዚአብሄር የለም የሚሉ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል። ወደ ቲቶ 1፡16

እግዚአብሄርን የሚያውቁ እንደሆነ በአፋቸው የሚናገሩ ነገር ግን በስራቸው የሚክዱት ብዙ ሰዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል፡፡ አስተውሉ ሰነፍ በአፉ አይደለም እግዚአብሔር የለም የሚለው፡፡ የሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም አስተሳሰብ የሚገለፀው በድርጊቱ ብቻ ነው፡፡

ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። መዝሙረ ዳዊት 14፥1

በአፉ እግዚአብሄር አለ ብሎ የሚናገር ወይም እግዚአብሄር የለም ብሎ በአፉ የማይናገር ነገር ግን በልቡ እግዚአብሔር የለም የሚል የሰነፍ ሰውን ምልክቶችን እንመልከት፡፡

 1. እግዚአብሄርን እንደፈራጅ አያየውም

ሰው የፈለገውን ክፉ ነገር አድርጎ ከእርሱ በላይ ፈራጅ እንደሌለ እንደሚሄድ ካሰበ እግዚአብሄር እንዳለ አያምንም፡፡

 1. እግዚአብሄርን አይፈራም

ሰው ጥበቡ የማይመረመር ሃያል አምላክ እንዳል ካላመነ በስተቀር እግዚአብሄርን እንዴት ሊፈራ ይችላል፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው እግዚአብሄርን ሳይሆን ሰውን ይፈራል፡፡ በፊቱ ሁሉ ነገሮች የተራቆተና የተገለጠ አምላክ እንዳለ የማያምን ሰው ነገሮቹን ሁሉ በሰው ፊት ያደርጋል፡፡ ሁሉንም የሚያይ አምላክ እንዳለ የማያምን ሰው ከሰው በመደበቁ እና ሰውን በመዋሸቱ ብቻ እንደተሳካለት ያስባል፡፡

እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ወደ ዕብራውያን 4፡13

 1. ባለው ነገር ይመካል ይታመናል

እግዚአብሄር እንዳለ የሚያምን ሰው እግዚአብሄርን ከመታመን ውጭ ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ባለው ነገር የሚታመን ሰው እግዚአብሄር እንዳለ አያምንም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ ባለማመኑ የሚመካበትና የሚደገፍነበት ቁሳቁስ ዝና እና ጥበብን ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24

 1. እግዚአብሄር የምድር ባለቤት እንደሆነ አይታመንም

ሰው እግዚአብሄር እንዳለ ካላመነ  በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሄር እንደፈጠረ እና እርሱ ባለቤት እንደሆነ አይረዳም፡፡ ሰው ምድር አንድ ባለቤት እንዳለው ሰው አስተዳዳሪ እና ባላአደራ እንጂ የምንም ነገር ባለቤት እንዳልሆነ የሚረዳው እግዚአብሄር እንዳለ ሲያመን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው በጊዜያዊነት በታማኝነት ተጠቅሞ ከማለፍ ይልቅ የምድር ነገር ባለቤት ለመሆን ሲፍጨረጨር ህይወቱን በከንቱ ይፈጃል፡፡

ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አትሳቱ

palettblad-coleus-fairway-ruby.jpg

አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡33

የእግዚአብሔርን ህግ መከተል ከህመም ያሳርፋል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ማዳማጥ እግዚአብሄርን ለህይወታችን ያለውን ፈቃዱን ከመሳት ያድናል፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል የዋህ መሆን ከብዙ ጥፋት ያድናል፡፡

ከእግዚአብሄር በላይ ያወቅን ሲመስለን ራሳችንን እንጎዳለን፡፡ ለእግዚአብሄር ትእዛዝ ቸልተኞች ስንሆን የማይገባንን ዋጋ እንከፍላለን፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ አትሳቱ ይላል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ አይምሰላችሁ ይለናል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ አትሸወዱ ብሎ በብርቱ ይመክረናል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ አትሳቱ ያለበት ምክኒያት ይህ ነገር ሰው ብዙ ሰው ብዙ ጊዜ የሚሳሳትበት ነገር ስለሆነ ነው፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ ከሆነው በላይ ጠንካራ የሆነ ይመስለዋል፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ ከሆነው በላይ ጠቢብ እንደሆነ ሲመስለው ይሸወዳል፡፡

እግዚአብሄር አዋቂ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን አድርጎ በሰላም እንደሚኖር ካሰበ ሞኝ ሆኖዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄር ተው ያለውን ሳይተው እንደማይወድቅ ካሰበ ተታሏል፡፡

እግዚአብሄር አትሳቱ ይለናል፡፡ በምን ብለን መጠየቅ እና ትእዛዙን በፍጥነት ለመጠበቅ እርምጃ መውሰድ ብልህነት ነው፡፡

እግዚአብሄር በተለይ በክፉ ባልነጀርነት አትሳቱ ብሎ ይመክረናል ያስጠነቅቀናል፡፡ ክፉ ባልንጀራ ይዞ ክፉ አልሆንም የሚል ሰው ለራሱ ከሚገባው በላይ ግምት እየሰጠ ነው፡፡ ክፉ ባልንጀነት ይዞ አልስትም ማለት በከንቱ በራስ መመካት ነው፡፡ የክፉ ባልንጀርነት ውጤት እኔን አይነካኝም ብሎ ማሰብ ትእቢት ነው፡፡

ወደድንም ጠላንም ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል፡፡ በክፉ ባልንጀርነት ቆይተን አለን ያልነው መልካም አመል  ቢጠፋ አንደነቅ፡፡ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ይበላል፡፡

ስለምድራዊ ህይወት ብቻ ከሚያስብ ሰው ጋር ያለ ወዳጅነት የሰውን የሰማያዊ አስተሳብ ያጠፋል፡፡ በቁሳቁስ ላይ ብቻ ከሚያተኩር  ሰው ጋር ያለ ባልንጀርነት ስለመንፈሳዊ ያለን ትኩረት ቢያደበዝዘው አያስገርምም፡፡ ስለሆድ ብቻ ከሚያስብ ሰው ጋር ያለ ባልንጀርነት  ይዋል ይደር እንጂ የፍቅርና የአገልግሎት ዘርን ከውስጣችን ያመክነዋል፡፡ ስለጥርጥር ከሚያስብ ሰው ጋር ያለ ግንኙነት እምነታችንን ባይጎዳው ይገርማል፡፡

መልካሙን አመል ከመጠበቅ ይልቅ ከክፉ ባልንጀርነት ራስህን መጠበቅ ይቀላል፡፡ በክፉ ባልንጀርነት መካካል መልካምን አመል ለመጠበቅ ከመሞከር ይልቅ ክፉ ባልንጀርነት ላይ መጨከንና ከክፉ ባልንጀርነት ፈጥኖ መለየት ይቀላል፡፡ በክፉ ባልንጀርነት ውስጥ መልካም አመልይ ይዞ ከመቆየት ይልቅ ክፉ ባልንጀርነትን በፍጥነት መቁረጥ በቀላሉ ከመከራ ይገላግላል፡፡

አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡33

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ወዳጅ #ጓደኛ #መታመን #ጥበብ #ፍቅር #ባልንጀርነት #መልካም #አመል #ክፉ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የህይወት ከንቱነት

videoblocks-withered-rose-flower-with-crushed-dried-petals-on-wooden-table-in-dark-room-aged-textured-wood-looks-rustic-and-old-dolly-shot_s2fedffpuq_thumbnail-full07.png

በኢየሩሳሌም የነገሠ የሰባኪው የዳዊት ልጅ ቃል። ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። መጽሐፈ መክብብ 1፡1-2

ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሮአል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በክብሩ ፈጥሮታል፡፡ የሚያሳዝነው ነገር ግን ይህን የከበረ ህይወት በክብር የሚይዘው ሁሉም ሰው አይደለም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።  ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡17

እግዚአብሔር በሰው ላይ ከፍ ያለ ዋጋ ቢያደርግም ለህይወቱ የሚገባውን ዋጋ የሚሰጠው ሰው ግን ሁሉም አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠ የከበረው ህይወት እንደ እግዚአብሔር መንገድ ካልተኖረ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ሊሆን ይችላል፡፡

ሰው የራሱ ፈቃድ አለው፡፡ ሰው ህይወቱን በፈለገው መንገድ የመምራት ሙሉ ፈቃድ ያለው ተደርጎ ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ህይወቱን አክብሮ ህይወቱን በክብር ሊመራ ወይም ሰው ህይወቱን ሊንቅ የተፈጠረበትን አላማ ሊስትና የማይገባውን ኑሮ ሊኖር ይችላል፡፡

ህይወትን ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ሊያደርጉ የሚችሉ አምስት ነገሮችን ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት

 1. አላማ ቢስ ህይወትን መኖር

ለእግዚአብሔር አላማ ተፈጥሮ እያለ ሰው ለህይወቱ የእግዚአብሄርን አላማ የማይፈልግና የማይከተል ከሆነ ህይወቱ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ሰው አላማ በእግዚአብሔር ቃል በኩል የተፈጠረለትን የእግዚአብሔርን አላማ ካልፈፀመ ህይወት ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡

ጩኽ የሚል ሰው ቃል፤ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡6-8

 1. በፍቅር አለመኖር

ሰው በፍቅር ለመኖር ተፈጥሮአል፡፡ ከፍቅር ያነሰ ምንም አይነት ህይወት ለሰው ከንቱ ነው፡፡ ህይወት ዋጋ የሚኖረው በፍቅር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰው ምንም ዝነኛ ፣ ጥበበኛ ፣ ሃያል እና ባለጠጋ ቢሆን ፍቅር ግን ከሌለው ከንቱ ነው፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡2-3

 1. በጥንቃቄ አለመኖር

ሰው ዘመኑን በጥንቃቄ ካልያዘው ያባክነዋል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ህይወት አጭርና በጥንቃቄ መኖር ያለበት ነው፡፡ ትንሽ ጥንቃቄ ጉድለት ለብዙ ክፋት ሊያጋልጠን ይችላል፡፡

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16

በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡13-14

ሰው በምድር ላይ ለዘላለም እንደሚኖር አድርጎ በጥንቃቄ ካልኖረ ህይወት ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

 1. እንደ እንግዳ አለመኖር

የምድር ህይወት አጭር ነው፡፡ የምድር ህይወት የእንግድነት ህይወት ነው፡፡ የምድር ህይወት ጊዜያዊ መተላለፊያ ህይወት ነው፡፡ አንድ ቀን በፈጠረን በጌታችን ፊት እንቀርባለን፡፡ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት ቅርቦ እንደሚጠየቅ ተደርጎ ካልተኖረ ህይወት ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡

በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15፡19፣32

 1. በእምነት አለመኖር

ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሔር ቃል ሰምቶ እንደእግዚአብሔር ቃል እና እንደፈቃዱ በእምነት እንዲኖር ነው፡፡ ሰው በእምነት ካልኖረ ከእግዚአብሔር ጋር ሊገናኝ እና በምንም መልኩ እግዚአብሔርን ሊያስደስት አይችልም፡፡ ሰው በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቹ ብቻ በሚያየውና በሚሰማው ብቻ ከተመላለሰ ከእግዚአብሄር ጋር የሚያገናኘው ምንም መስመር ስለሌለ ህይወቱን ከንቱ ያደርገዋል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

ሰው እግዚአብሔርን በቃሉ ካላመነ ሊከተለው ፣ እራሱን ለጌታ ሊሰጥና እግዚአብሔር ወደአየለት የክብር ደረጃ ሊደርስ አይችልም፡፡

ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። የማቴዎስ ወንጌል 16፡25

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ፍቅር #አላማ #እምነት #ጥንቃቄ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ፍቃዱ ከደስታ ይበልጣል

the-joy-that-Christ-gives.jpg

ሰው የተፈጠረው ለእግዚአበሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር ላይ ለመፈፅም ነው፡፡ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንዳንፈፅም ስላደረገን ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ዋጋ ሊከፍልና ከአመጽና ካለመታዘዝ ሊያድነን እና ለእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ነፃ ሊያወጣን ነው፡፡

በምድር ላይ ለነፍሳችን ደስታን ካገኘን መልካም ነው፡፡ ነገር ግን በምድር ላይ ለነፍሳችን ደስታን ማግኘት የህይወታችን ብቸኛ አላማ አይደለም፡፡

የህይወታችን ቀዳሚ ግብ የእግዚአብሄርንም ፈቃድ መፈፀም ነው፡፡ ካለእግዚአብሄር ፈቃድ በነፋስ ሁሉ እንደሚፍገመገም በውሃ ላይ ወዲያና ወዲህም እንደሚንሳፈፍ ነን፡፡

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታችን አድርገን የተቀበልን ሁላችን የራሳችን አይደለንም፡፡ ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን በሁለንተናችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድንፈፅም በዋጋ ተገዝተናል፡፡

በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20

የተጠራነው ነፍሳችንን ለማክበርና ለማስደሰት አይደለም፡፡ የተጠራነው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመፈፀም እግዚአብሄርን ለማክበር ነው፡፡

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። የሐዋሪያት ሥራ 20:24

ቅድሚያ የምንሰጠው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን መፈፀሙን እንጂ የነፍሳችንን ደስታን አይደለም፡፡ ነፍሳችንን የምናድነው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመፈፀም እንጂ ነፍሳችንን ለጊዜው በማስደሰት አይደለም፡፡

ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። የማቴዎስ ወንጌል 16፡25

የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመፈፀም ዘለቄታዊ ሰላምና ደስታ አለ፡፡ ደስታችን የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመፈፀም የሚመጣ ብቻ ነው፡፡ በምድር ላይ በእግዚአብሄር ፈቃድ የምንለውጠው ወይም ከእግዚአብሄር ፈቃድ የምናስቀድመው ምንም አይነት ደስታ የለም፡፡ ደስታችን በእምነት እግዚአብሄርን ፈቃድ በመፈፀም እግዚአብሄርን ማስደሰት ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ ፈቃድህን እፈልጋለሁ፡፡ ነፍሴ ብትጮህ ብታጉረመርምም ፣ ለጊዜው ደስ ባይልም ፣ ለጊዜው የሚስብ ባይሆንም ፣ ብዙ ሰዎች የሚመርጡት ባይሆንም ነገር ግን ለእኔ ፈቃድህ ይሻለኛል፡፡ ምንም ዋጋ ቢያስከፍል ፈቃድህ ይሻለኛል፡፡ ምንም ቢያሳምም ፈቃድህን እፈልጋለሁ፡፡ በህይወቴ ሁሉ ፈቃድህ ይሁንልኝ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ደስታ #ክብር #ነፍስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

ለአንዱ ችግር ለሌላው እድል

istockphoto-892841692-612x612.jpg

አለም በመልካም እድሎች የተሞላች ነች፡፡ የአለም ምንጭ እና ሃብት ለሁሉም ሰው ይበቃል፡፡

ምድር ለአንዱ እናት ለሌላው ጨቋኝ የእንጀራ እናት አይደለችም፡፡ እያንዳንዳችንን ከሌላችን የሚለየን አለምን የምንመለከትበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡

እያንዳንዱ ነገር የራሱ ጥቅም የራሱ ተግዳሮት አለው፡፡ ተግዳሮት የሌለው ጥቅም የለም፡፡ እድል የሌለው ተግዳሮት የለም፡፡

በችግር ላይ የሚያተኩር ሰው ከችግሩ በስተጀርባ ያለውን መልካም እድል ማየት አይችልም፡፡ ችግር በጊዜያዊነት መልስን አለማግኘት እንጂ ዘላለማዊ ተግዳሮት የለም፡፡ እያንዳንዱ የህይወት ጥያቄ መልስ አለው፡፡ መልስ የሌለው ጥያቄ የለም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ለእያንዳንዱ የህይወት ጥያቄ መልስ ይገኝለታል፡፡ መውጫ የሌለው ፈተና የለም፡፡

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13

ሁሉም ሰው የራሱ ተግዳሮቶች አሉት፡፡ ተግዳሮቶችና ድካሞች የሌሉት ሰው በአለም ላይ የለም፡፡ ሰው የሌላውን ሰው ድካም ብቻ ካየ በዚያ ሰው ውስጥ የተቀመጠውን እምቅ ጉልበት መጠቀም ያቅተዋል፡፡ ሰው የሌላው የህይወት ተግዳሮቶች ላይ ብቻ ካተኮረ እና ከተግዳሮቶቹ ባሻገር ያለውን እድል ካልተመለከተ ሰውየውን እንዳለ አውጥቶ ለመጣል ይፈተናል፡፡ ሌላውን ሰው በደፈናው በጣልን ቁጥር አንድ የሰውነት ክፍላችንን እንጥላለን፡፡

ሃዋሪያው ጳውሎስ ጌታ ከመከተሉ በፊት ክርስትያኖችን አሳዳጅ ነበር፡፡ ሰው የጳውሎስ አደጋው ላይ ሲያተኩር  ጌታ ግን ትኩረቱ አምቅ ጉልበቱ ላይ ነበር፡፡ ሰው በጳውሎስ ጎርፍነት ሲፈራ እና ሲደናገር ጌታ ግን የጳውሎስን ጎርፍ እንዴት መንገድ እንደሚሰጠውና የጎርፉን እድል እንዴት እንደሚጠቀምበት ያውቅ ነበር፡፡ ሰው የጳውሎስን የሃይማኖት እሳት እንዴት እንደሚይዘው ስለማያውቅ እንደችግር ሲያየው ጌታ ግን የጳውሎስን እሳት እንዴት እንደሚመራውና ለእውነተኛው ለእግዚአብሄርን መንግስት ጥቅም እንደሚጠቀምበት ስለሚያውቅ ጥበቡ ስላለው የጳውሎስ ገዳይ ሃይማኖተኝነት ለጌታ ስጋት አልነበረም፡፡

አሁን የምናልፍባቸው ማንኛውም ችግሮች የራሳቸው እድል አላቸው፡፡ የሚያስፈልገን አይናችን ተከፍቶ ከተግዳሮቶቹ በስተጀርባ ያለውን እድል ማየት ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ጥያቄ መልስ አለው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማንኛውምን ፈተና መውጫ አለው፡፡

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። የያዕቆብ መልእክት 1፡5

በተግዳሮት ወቅት ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገን የልባችን አይኖች መከፈትና ከከበቡን ነገሮች በላይ እጅግ የሚበልጠውን እድል መመልከት ነው፡፡ ከተግዳሮት በስተጀርባ ያለውን እድል ሳይመለከቱ ተግዳሮቱ ላይ ብቻ በማተኮር ከተግዳሮቱ በፍጥነት ለመውጣት መሞከር በተግዳሮቱ ውስጥ የተሸሸገውን እድል እንዳናይና ወርቃማውን እድል በከንቱ እንድድናባክን ያደርገናል፡፡

በእይታ ልዩነት ምክንያት ለአንዱ የማሰናከያ ድንጋይ የሆነው ድንጋይ ለሌላው ወደከፍታ የመወጣጫ ደረጃ ነው፡፡

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡17-19

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈተና #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ጥበብ #ክፉ #አሸንፍ #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እድል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ተግዳሮት #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ #ምስክርነት

የደስተኝነት ምርጫ

በህይወት ደስተኛ መሆን የእድል ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ ነው:: ሰው ሁሉ ደስተኛ መሆን ይፈልጋል:: ነገር ግን ሰው ሁሉ ደስተኛ የሚያደርገውንነገር አይመርጥም:: እንዳንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን ቢፈልግም ደስተኛ የሚያደርጉትን ሳይሆን ደስተኛ የማያደጉትን ነገሮች ስለሚመርጥ ደስተኛ ሳይሆን ጊዜውን ያባክናል::
ክፉ ሀዘን ጉልበትን ያደክማል:: ክፉ ሀዘን የኑሮ መነሳሳትን ይገድለዋል::
እርሱም፡— ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ፡ አላቸው። መጽሐፈ ነህምያ 8:10
ደስተኝነት ለመኖር ለመስራትና ወደህይወት ግባችን ለመድረስ ጉልበት ይሰጠናል::
በህይወት ደስተኛ የማያደርገንን ነገሮች እስካልመረጥን ድረስ ደስተኛ መሆናችን አይቀርም::
ደስተኛ የማያደርጉ ሀሳቦች
1. ራስን ከሌላ ሰው ጋር ማፎካከር
ደስተኛ ላለመሆን አቋራጩ መንገድ በህይወት የተለያየ የህይወት አላማና ስጦታ ያላቸውን ሰዎች ለማወዳደርና ለማበላለጥ መሞከር ነው::
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10:12
2. ያለፈን ህይወት በፀፀት ለማስተካከል መሞከር
ያለፈ ህይወት አልፎዋል:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ዛሬን መግደል ነው:: ስላለፈ ህይወት መፀፀት ከዛሬ ትላንት ይሻል ነበር ብሎ ዛሬን ማናናቅ ነው::
3. የሌለን ነገር ላይ ማተኮር
የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን ነገር በአግባቡ እንዳንጠቀምበት ያደርገናል:: የሌለን ነገር ላይ ማተኮር ያለንን እንዳናከብረውና እንዳንንቀው ያደርገናል:: የሌለን ነገር እንደማያስፈልገን ምንም ማረጋገጫ የለንም::
4. ያልደረስንበት ደረጃ ላይ ማተኮር
ሁላችንም ህልሞች አሉን:: ነገር ግን አሁን አንዳንዱ ህልማችን እውን ሆኖ እየኖርነው አይደለም ማለት አይደለም:: ከዚህ በፊት ምንም ሆኖልን እንደማያውቅ ምንም አከናውነን እንደማናውቅ የነገ ግባችን ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር ደስተኛ ላለመሆን መምረጥ ነው::
5. ከጌታ ውጭ ማተኮር
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄርና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲኖር ነው:: ሰው ግን እግዚአብሄርን ካላሰበ ደስተኛ መሆን ያቅተዋል:: ብዙ ደስ የማያሰኙ ነገሮች በዙሪያችን እያሉ በጌታ ደስ መሰኘት ይቻላል::
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ወደ ፊልጵስዩስ 4:4

የተከፈለለት ባለእዳ

46913-34686-jesus-on-cross-2-1200.1200w.tn.800w.tn.jpg

እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡1-2

የሃጢያት ደሞዝ ሞት ነው፡፡ በሃጢያታችን ባለ እዳ ነበርን፡፡ ሃጢያት ከእዳዎች ሁሉ የከፋ እዳ ነው፡፡ ሃጢያት ሸክም ነው፡፡ ሃጢያት እስራት ነው፡፡ በሃጢያታችን ለዘለዓለም ከእግዚአብሄር መለያየት ነበረብን፡፡

ስለሃጢያትን በራሳችን ዋጋ መክፈል አንችልም፡፡ የትኛውም መልካም ስራችን ስለሃጢያታችን ክፍያ በቂ አይደለም፡፡

እኛ በሃጢያታችን ምክኒያት ለዘላለም ከእግዚአብሄር እንዳንለያይ ሃጢያት የሌለበት ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እኛን ተክቶ በመስቀል ላይ ሊሞት ወደምድር መጣ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን ሙሉ ዋጋን ከፍሏል፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያቱ ሙሉ ክፍያን እንደከፈለ ያላመነ ሰው ባለእዳ ሆኖ ይኖራል፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለለትን ለእኔ ነው ብሎ የማይቀበል ሰው የእግዚአብሄር ቁጣ በእርሱ ላይ ስለሚኖር በምድር ባለእዳ ሆኖ በጉስቁልና ይኖራል፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡36

ኢየሱስ እኛን ሃጢያተኞችን ወክሎ በእኛ ፋንታ በመስቀል ላይ እንደሞተ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ በመስቀል ላይ እንደከፈለ የማያምን  ሰው ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት የሃጢያቱን እዳ በራሱ ይከፍለዋል፡፡

በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 3፡13

ኢየሱስ በመስቀል ላየ ዋጋ መክፈሉ የሚጠቅምህና ከዘላም ጥፋተ የሚያድንንህ በእምነት ስትቀበልው ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ አንተን ተክቶ  በመስቀል ላይ የከፈለውን ዋጋ በእምነት ካለተቀበልክ እና ከሃጢያት እዳ ካልዳንክ እስከ ሃጢያትህ ትኖታለህ ትሞታለህ፡፡

ይህንን ፀሎት ከልብህ በመፀለይ የእግዚአብሄር ልጅ አድርጎ እግዚአብሄር እንዲቀበልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ሃጢያተኛ ነኝ፡፡ የሃጢያት ደሞዝ ደግሞ ለዘላለም ከአንተ መለየት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሃጢያት ለመዳኛ ያዘጋጀኸውን የሃጢያት መስዋእት ኢየሱስን እቀበላለሁ፡፡ እየሱስ ስለሃጢያቴ በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለና እንደሞተ ከሞትም እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ላይ ጌታ አድርጌ እሾመዋለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ዘመን ሁሉ እከተለዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የዘላለም ህይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes

Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት  #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #አቁማዳ #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ

ወደድክም ጠላህም አመለካከትህ ይታያል

lie.jpg

ስለሰው ያለህ አመለካከት በተለያየ ምክንያት ሊለወጥና የተበላሸ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሰው ያለህ አመለካከት እንዳይበላሽና ጉዳት እንዳያደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ስለ ሰው ያለህ አመለካከት በተለያየ ምክንያት ቢበላሽም በፍጥነት ማስተካከል ግዴታ የአመለካከት መበላሸት የሚያስከትለውን ጉዳት ይቀንሳል፡፡

ሰው በሌለበት ጊዜ ስለ አንድ ሰው ስለምታስበው ነገር እጅግ መጠንቀቅ አመለካከትህ እንዳይበላሸ ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡ ስለ አመለካከትህ መጠንቀቅ ያለብህ ስለእርሱ ያለህ አመለካከትህ የተበላሸብህ ሰው አጠገብህ ስላለ ወይም ስለሌለ አይደለም፡፡ ስለ አመለካከትህ መጠንቀቅ ያለብህ ሰው አመለካከትህን ስለሚያየው ወይም ስለማያየውም አይደለም፡፡ ሰው ቢኖርም ባይኖርም አመለካከትህ መልካም ካልሆነና ከተበላሸ የሚያበላሻቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡

ሰው በሌለበት ጊዜም ቢሆን ስለሌላው ሰው ስለምታስብው ነገር መጠንቀቅ ያለብህ ይፍጠንም ይዘግይም ስለሰው ያለህ አመለካከት ስለሚገለጥ ነው፡፡ ሰው በማይሰማህ ጊዜ ለራስህ ወይም ለሌላው ሰው የምትናገረው ነገር በአንድም በሌላ መልኩ ይሰማል፡፡ ሰው በማይኖርበት ጊዜ የምታሳየው አመለካከት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ይንፀባረቃል፡፡

የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። የሉቃስ ወንጌል 8፡17

ስለሌላው ሰው ያለህን አመለካከት ማስተካከል ያለብህ በግልህ ነው፡፡ ስለሌላው ሰው ያለህን አመለካከት ማስተካከል ያለብህ ሰውየው በሌለ ጊዜ ነው፡፡ ስለሌላው ሰው ያለህን አመለካከት ማስተካል ያለብህ ብቻህን ባለህበት ጊዜ ነው፡፡ ስለሌላው ያለህን አመለካት ማቅናት ያለብህ ሰውየው አጠገብህ በሌለበት ጊዜ ስለዚያ ሰው በምታስብበት ወቅት ነው፡፡ ስለሌላው ሰው ያለህን አመለካት ማቃናት ያለብህ ከራስህ ጋር ስታወራ ነው፡፡

ምክር በሰው ልብ እንደ ጠሊቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል። መጽሐፈ ምሳሌ 20፡5

ሰው ለእርሱ ያለህን አመለካከት ያውቃል፡፡ በተለይ መንፈሳዊ ሰው ሁሉ ይመረምራል፡፡

የተበላሸ አመለካከትህ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ የምትችለው ብቸኛ ነገር አመለካከትህን ቀድሞ ማስተካከል እንጂ አመለካከትን መደበቅ አይደለም፡፡ ጠረኑን ያመጣውን ነገር በማጥፋት የአፍን መጥፎ ጠረን ማስተካከል እንጂ ጠረኑ እንዳይታወቅ መመኘት ብቻ መፍትሄ ጠረኑ እንዳይወጣ አያግደውም፡፡

ሰዎችን እግዚአብሄር እንደሚያያቸው ማየት አመለካትህን ያስተካከልዋል፡፡ ሰዎችን እግዚአብሄር እንደሚያከብራቸው ማክብር አመለካከትህን ቀና ያደርገዋል፡፡ ከሰዎች በላይ ራስን ከፍ አድርጎ በትእቢት ላለመመልከት በአስተሳሰብ ህይወትህ መጠንቀቅ አመለካከትህን ጤናማ ያደርገዋል፡፡

ሄዋን ለእግዚአብሄር ያላት አመለካከት የተበላሸው ብቻዋን በነፃነት መልካም እንዳልሆነ ስለእግዚአብሄር ማሰብ ስትጀምር ነው፡፡ ሄዋን የቅንነት አመለካከትዋ እንዳይበላሽና ከእግዚአብሄር ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳያበበላሽ ማድረግ የምትችለው የቅንነት አስተሳሰብዋን መበላሸት በእንጭጩ ብትቀጭ ነበር፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

ለሰው ያለህ ቅንነት እንዳይበላሽ አመለካከትህን የሚያበላሽን ነገር ማስተናገድ ይኖርብሃል፡፡ ስለሰው ያለህን ቅንነትን የሚያበላሽን ፍቅር የሌለበትን ነገር በነፃነት እያስብክና ግንኙነቴን አያበላሽም ብለህ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ስለሰው ያለህን አመለካከት የሚያበላሽን አክብሮት የሌለበትን ነገር በነፃነት እያሰብክ አመለካከቴ አይታወቀም ብለህ መመኘት ከንቱ ነው፡፡ ስለሰው ያለህን ቅንነትን የሚያበላሽ እንደእግዚአብሄር ቃል ያልሆነ ሃሳብን በአስተሳሰብ ህይወትህ እያስተናገድክ ይህ አመለካከቴ ሌላውን አይጎዳም ብለህ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ስለሰው ያለህን አመለካከት ተበላሽቶ ሌላው ሰው በንግግር ወይም በድርጊትህ አይረዳውም ማለት ሞኝነት ነው፡፡

ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡12-13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አመለካከት #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የውስንነት ወሰን

your will1.jpg

እግዚአብሄር ለክብሩ የፈጠረን የእግዚአብሄር ፍጥረት ነን፡፡ እግዚአብሄር አይወሰንም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ አምላክ እንደሆነ ሁሉ እኛም ልጆቹ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ እግዚአብሄር እንደማይወሰን ታላቅ ሃይሉን የሚያሳየው እኛ በልጆቹ ነው፡፡

እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን። ትንቢተ ኢሳይያስ 8፡18

የእግዚአብሄር ሙሉ ድጋፍ ያለን በምንም ነገር የማንወሰን የእግዚአብሄር ህዝቦች ነን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ሃያል በእኛ ታላቅ ስለሆነ ጠላት ሁልጊዜ ይዋሻል፡፡

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝሙረ ዳዊት 66፡3

እግዚአብሄር ለእኛ ያለው ሙላትና መትረፍረፍ ነው፡፡

እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

እግዚአብሄር በውስጣችን ያስቀመጠውን ታላቅ እምቅ ጉልበት እንዳናወጣ የጠላት ተግዳሮት አለብን፡፡ እግዚአብሄር ወደአየልን ታላቅ ደረጃ እንዳንደርስ የሚያስፈራራና የሚያናንቅ ጠላት አለብን፡፡ እግዚአብሄር ያየልንን ሁሉ እንዳንወርስ የሚያጣጥልና የሚያሳንስ ብዙ ነገር በህይወታችን ይገጥመናል፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሄር እንዲሰራ የሰጠውን ስራ እንዳይሰራ ሰይጣን ሊያሳንሰውና የሰው ልጆችን ከማዳን ከአላማው ሊያስቆመው ይገዳደረው ነበር፡፡

ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡3

አሁንም እግዚአብሄር እንድንሆን ያሰበውን ሁሉ እንዳንሆን እግዚአብሄር አላችሁ የለንን ሁሉ እንዳይኖረን እንዲሁም እግዚአብሄር ታደርጋላችሁ የሚለንን ሁሉ እንዳናደርግ ሰይጣን ሊወስነን ይሰራል፡፡

እግዚአብሄር ወደ አየልን የክብር ቦታ እንዳንሄድ ሰይጣን ሊገድበን ከዚህ ማለፍ አትችልም ብሎ ሊያሳምነን ይጥራል፡፡ የሰይጣንን ውሸት አምነን ከቆምን ከዚያ ሁሉ ብርቱ የጦር መሳሪያችን ጋር እንማረካለን፡፡ የሰይጣንን አታልፉም ግርግር ከሰማነው እግዚአብሄር ወደአለለን ደረጃ ሳንደርስ ከዚያ ሁሉ እምቅ የእግዚአብሄር ሃይል ጋር እናልፋለን፡፡

የእኛ ወሰን እግዚአብሄር ያየልን እንጂ ሰይጣን የሚለው ውሸት አይደለም፡፡ የእኛ ልክ ሰይጣን የሰፋልን የንቀት ልብስ ሳይሆን እግዚአብሄር ያየልን የክብር ልብስ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ገደብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የሚሰራው እግዚአብሄር

deep water.jpg

ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው። መጽሐፈ መክብብ 3፡11

በህይወታችን ምንም አይነት ትርጕም ያለው ነገር ከሰራን የሰራው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ በህይወታችን ትርጉም ያለው ነገር ካቀድን ያቀደው እግዚአብሄር ነው፡፡ በህይወታችን ትርጉም ያለው ነገር ካሰብን መጀመሪያ ያሰበው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡

እግዚአብሄር ጀማሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ቀዳሚ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከመጀመሪያ ያስባል፡፡ እኛ ከመወለዳችን በፊት ስለእኛ ህይወት አስቦ ጨርሷል፡፡ አለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሄር የህይወት እቅዳችንን ሰርቶት ጨርሷል፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

እኛ ወደ ምድር ከመምጣታችንና ስራችንን ከመጀመራችን በፊት እግዚአብሄር መጨረሻውን ከመጀመሪያው አይቶታል፡፡

በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 46፡10

እኛ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያደረግነው ጥሩ አሳቢዎች ስለሆንን አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን የፈፀምነው ጥሩ ተመራማሪዎች ስለሆንን አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ በህይወታችን የተፈፀመው ምርጥ እቅድ አውጪዎች ስለሆንን አይደለም፡፡

በልባችን መልካም ሃሳብ ካለ እግዚአብሄር አስቀድሞ ያሰበው የራሱ ሃሳብ ነው፡፡ በልባችን መልካም ነገርን ካቀድን እግዚአብሄር የዘላለም እቅዱን በልባችን አካፍሎን ነው፡፡

በምድር ላይ የሰራነው አንዳች ነገር ቢኖር እግዚአብሄር ሰርቶ የጨረሰውን ብቻ ነው፡፡

ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው። መጽሐፈ መክብብ 3፡11

በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21

በምድር ላይ የምንፀልየው ለእግዚአብሄር ስለህይወት እቅዳችን ሃሳብ ልናቀብለው አይደለም፡፡ የምንፀልየው እግዚአብሄር የህይወት እቅዳችንን እንዲሰራ ሃሳብን ልናካፍለው አይደለም፡፡ የምንፀልየው ስለህይወት እቅዳችን እግዚአብሄርን ልናማክረው አይደለም፡፡ የምንፀልየው ለእግዚአብሄር ሃሳብ ካልሰጠነው የሚረሳ እና የሚዘለል ነገር ስላለና የህይወት እቅዳችን ጎዶሎ ስለሚሆን አይደለም፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

ወደ እግዚአብሄር የምንፀልየው እግዚአብሄር ለህይወታችን አስቀድሞ ሰርቶ የጨረሰወን እቅድ ለመረዳትና ከእርሱ ጋር ለመተባበር አብረነው ለመስራት ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተስፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ይቻላል

pub.jpg

ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 9፡23

እግዚአብሄር ሁለን ቻይ አምላክ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ሁለል የሚችለውን እግዚአብሄርን ተከትሎ ሁሉን እንዲችል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄር በምድር ላይ እንዲፈፅም የፈለገውን አላማ ከመፈፀም ምንም ነገር እንዳያግደው ተደርጎ ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄር ቃል ታደርጋለህ የሚለውን ሁሉ ማድረግ እንዲችል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእምነት የእግዚአብሄርን ሃይል በምድር ላይ እንዲጠቀም ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን በቃሉ እየተከተል ለሰው የማይቻለውን ነገር እንዲችል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን በማመን ለሰው የማይቻለውን ነገር በእምነት እንዲችል ነው፡፡

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከማወቅ ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ፈቃድ አውቆ በመከተል ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን እንደሚችል ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የተረዳ ሰው በእምነት ፈቃዱን ለመፈፀም የማይችለው ነገር አይኖርም፡፡

ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። የሉቃስ ወንጌል 1፡37

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ሊያስቆም የሚችል ምንም ሃይል እንደሌለ ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚከተልን ሰው የሚያቆም ምንም ሃይል የለም፡፡ ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር እንደሌለ ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከቃሉ አግኝቶ ለሚከተል ሰው የሚሳነው ነገር የለም፡፡

እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን? ትንቢተ ኤርምያስ 32፡27

እግዚአብሄር ፈቃዱን ለመፈፀም የሚያቅተው ነገር እንደሌለ ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለሚፈፅም ሰው የሚያቅተው ነገር የለም፡፡

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል !

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የማሪያም አማላጅነት

Publication2.jpg

ማሪያም ታማልዳለች ወይስ አታማልድም የሚለው ጥያቄ በኢትዮጲያ ውስጥ ብዙ ክርክርን ሲያስነሳ የቆየ ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንዶች ማሪያም በምድር ላይ እያለች አማልዳለች ነገር ግን ከሞተች በኃላ ማማለድ አትችልም ብለው ያምናሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ማሪያም አሁንም ታማልዳለች ወደ እግዚአብሄር ታቀርበናለች በማለት ይደገፉባታል ወደእርሷም ይፀልያሉ፡፡

ሲጀመር ማሪያም ታማልዳለች አታማልድም የሚለው ክርክር ከመዳን አንፃር ከቁጥር የሚገባ ክርክር አይደለም፡፡ መዳናችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው የህይወት ዋጋ የተገዛ ነው፡፡ መዳናቸነ የሚመሰረተው ኢየሱስ ስለሃጢያቴ ሞቷል ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ብለን በማመናችን ነው፡፡

በበኩሌ ሰው ማሪታም ታማልዳለችም አታማልድምም ብሎ ቢያምን ደህንነቱን ቅንጣት ይለውጣል ብዬ አላምንም፡፡ የአንድ ሰው ደህንነት የሚመሰረተው ሰው ኢየሱስ ስለሃጢያቱ በመስቀል ላይ እንደሞተና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ በማመኑ ላይ ብቻ ነው፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9-10

እውነት ነው ጤናማ የመፅሃፍ ቅዱስ ትምህርትን መማራችን የምንኖረው የክርስትና ህይወት ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ሰው ከመሰረታዊው የመፅሃፍ ቅዱስ የደህንነት አስተምሮ ውጭ የሚያምነው ማንኛውም ጥቃቅን ትምህርት ደህንነቱ ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል ብዬ አላምንም፡፡ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ማርያም አታማልድም ብሎ ቢያምን አይድንም፡፡ ዳግመኛ የተወለደ ሰው ማርያም ታማልዳለች ብሎ ቢያምን ደህንነቱን አያጣም፡፡

ኢየሱስ በምድር በሚመላለስበት ጊዜ አንድ የህግ መምህር ወደ ኢየሱስ ቀርቦ እንዲህ አለው፡፡

መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። የዮሐንስ ወንጌል 3፡2

ኢየሱስ ግን ስለመፅሃፍ ቅዱስ እውቀቱ አድንቆ በጣም አስፈላጊ ስላልሆነው አስተምሮት አላዋራውም፡፡ ኢየሱስ በቀጥታ በጣም አስፈላጊ ስለሆነው የሰው ልጅ መሰረታዊ የደህንነት ፍላጎት እንዲህ ሲል ተናገረው፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 3፡3

ለሰው ለደህነነት የሚያስፈልገው ጥሩ የመፅሃፍ ቅዱስ እውቀት ሳይሆን ዳግመኛ መወለድ ነው፡፡ ለሰው ደህንነት የሚያስፈልገው በጥቃቅን አስትምሮት ላይ ተከራክሮ ማሸነፍ ሳይሆን ዳግመኛ መወለድ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለደህንታችን የሚያስፈልገውን የሃጢያት ዋጋ ሁሉ በመስቀል ላይ ከከፈለ በኃላ የሚያስፈልገን ሌላ ነገር ሳይሆን ዳግመኛ መወለድ ነው፡፡

አሁንም የሚያከራክሩን ብዙ ነገሮች የማይገቡ ክርክሮች ናቸው፡፡ አሁን ጊዜያችንንና ጉልበታችን የሚያባክኑ ክርክሮች መሰረታው ያልሆኑ ትምህርቶች ናቸው፡፡ አሁን የሚያከራክሩንና የሚያጣሉን ክርክሮች ለመዳን ምንም የማይጨምሩ ምንም የማይቀንሱ ነገሮች ናቸው፡፡ አሁን የሚያከራክሩን ነገሮች አይቶ ሰይጣን የደህንነት አላማችንን መሳታችንን ደስ እንዲለው የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው፡፡

ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር በሚያደርገው ንግግር ለደህንነት አስፈላጊ ባልሆኑ ለመዳን በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ጊዜውን አልፈጀም፡፡ ኒቆዲሞስ አንዳንድ የሃይማኖት እውቀት ቢኖረውም ለመዳን ግን ምንም አይጠቅመውም፡፡ ኒቆዲሞስንም ሆነ እኛን የሚጠቅመን ዳግመኛ መወለድ ነው፡፡

በእናቱ ማህፀን ውስጥ ያለ ህፃን አለምን ማየት እንደማይችልና ስላልተወለደበት አለም ምንም አይነት እውቀት ሊኖረው እንደማይችል ሁሉ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር ስለ እግዚአብሄር መንግስት ሊያውቅ አይችልም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት እውነተኛ እውቀት የሚጀመረው በመወለድ ብቻ ነው፡፡ ሰው ዳግመኛ ሲወለድ አይኖቹ ይከፈታሉ ነገሮችን ማየትና ማወቅ ይጀምራል፡፡ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት ነገሮችን ለማየትና  እና ለማወቅ የሚያደርገው ሙከራ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

ሰው ዳግመኛ ከተወለደና የእግዚአብሄር የቤተሰብ አባል ስለሚሆንና ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሚኖረው ስለማማለድ የሚኖረው ጥያቄ ሁሉ ይፈታል፡፡

 

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤የዮሐንስ ወንጌል 1፡12

መፅሃፍ ቅዱስ ስለዳግም መወለድና በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በእምነት ከሃጢያት ትምህርቶች የተሞላ ነው፡፡ እንዲያውም መጽሃፍ ቅዱስ እራሱ የተፃፈበት አላማ እኛ በኢየሱስ አምነን ህይወት እንዲሆንልን ነው፡፡

ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። የዮሐንስ ወንጌል 20፡31

ይህንን ፀሎት ከልብህ በመፀለይ የእግዚአብሄር ልጅ አድርጎ እግዚአብሄር እንዲቀበልህ ማድረግ ትችላለህ፡፡

እግዚአብሄር ሆይ ሃጢያተኛ ነኝ፡፡ የሃጢያት ደሞዝ ደግሞ ለዘላለም ከአንተ መለየት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሃጢያት ለመዳኛ ያዘጋጀኸውን የሃጢያት መስዋእት ኢየሱስን እቀበላለሁ፡፡ እየሱስ ስለሃጢያቴ በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለና እንደሞተ ከሞትም እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ላይ ጌታ አድርጌ እሾመዋለሁ፡፡ ኢየሱስን በህይወቴ ዘመን ሁሉ እከተለዋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የዘላለም ህይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት  #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #አቁማዳ #መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ

ሁሉም ሊፀልየው የሚገባ የፀሎት ርእስ

your will1.jpg

እግዚአብሔር ሆይ እኔ ልቀየር የማልችላቸውን ነገሮች በዝምታ እንድቀበል ፀጋን ስጠኝ፡፡ እኔ መለወጥ የሚገባኝን ነገር ለመቀየር ድፍረት ስጠኝ፡፡ ልቀይር በምችላቸውና ልቀይር በማልችላቸው በሁለቱ ነገሮች መካከል መለየት እንድችል ጥበብን ስጠኝ፡፡ ሬይንሆልድ ኑይበር

God, give me the grace to accept with serenity the things that cannot be changed, Courage to change the things which should be changed, and the Wisdom to distinguish the one from the other. Reinhold Niebuhr

በህይወት ማድረግ የምንችለቸው ነገሮች አሉ ማድረግ የማንችላቸው ነገሮች ደግሞ አሉ፡፡ ውስን እንደሆንን ሁሉን ነገር ማድረግ እንደማንችል ካልተረዳን እረፍት በህይወታችን አይመጣም፡፡ በህይወት የሚያርፉና ህይወታቸውን በሚገባ ተደስተውበት የሚያልፉ ሰዎች ማድረግ የሚችሏቸው ታላላቅ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ማድረግ የማይችሉት አንዳንድ ነገር እንዳለ በሚገባ የተረዱ ሰዎች ናቸው፡፡

ማድረግ የምንችለውን ነገር ማወቅ በጣም ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን ማድረግ የማንችለውን ነገር ማወቅ ደግሞ እንደሁ ወሳኝ ነው፡፡

በህይወት የሚለወጡና ቢያንስ ለጊዜው የማይለወጡ ነገሮች አሉ፡፡ የሚለወጡ ነገሮችን ማወቅ እንድንለውጣቸው ድፍረት ይሰጠናል፡፡ የማይለወጡ ነገሮችን ማወቅ እንድንታገስ ያስተምረናል፡፡

መለወጥ የማይችለውን ነገር የማያውቅ ሰው መለወጥ በማይችለው ነገር ላይ በከንቱ ጊዜውንና ጉልበቱን ይፈጃል፡፡ መለወጥ የሚችለንውን ነገር የማያውቅ ሰው በከንቱ ተስፋ በመቁረጥ ነገሮችን ሊለውጥ የሚችልበትን በውስጡ ያለውን የተጠራቀመ ጉልበት ሳይጠቀምበት ያባክነዋል፡፡

በወትድርና የበሰለ ወታደር የሚባለው የሚተኩስ ሳይሆን መቼ እንደሚተኩስ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ መቼ መተኮስ እንዳለበት የሚያውቅና መቼ ደግሞ መተኮስ እንደሌለበት የሚያውቅ ወታደር ውጤታማ ወታደር ነው፡፡ የበሰለ ወታደር አንዳንዴ መተኮስ እየቻለ እስከሞት ድረስ በሚያስፈራ ሁኔታ ላላመተኮስ ይታገሳል፡፡

እግዚአብሄር ነገሮችን የምንለውጥበት ጉልበትን ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሄር ግን ነገሮችን የምንለውጥበትን ጉልበት ብቻ ሳይሆን የሚሰጠን የማይለወጡትን ነገሮች የምንታገስበትን ፀጋም ይሰጠናል፡፡

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡1፣4

አንዳንዴ በህይወታችን ያለውን ተራራ ከፊታችን እንድናነሳው ድፍረትን ይሰጠናል ሌላ ጊዜ ደግሞ ተራራውን የምንወጣበት ፀጋን ያበዛልናል፡፡

በእያንዳንዱ የህይወት እርምጃችን እግዚአብሄርን መፈለግ ያለብን በእነዚህ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #ትግስት #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ

አትወደኝም? ችግር የለም!

BBVRmfN.jpg

ሰው ፍቅር በሆነው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ተፈጥሮአል፡፡ ሰው በፍቅር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ለፍቅር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ለፍቅር እንጂ ለሌላ ነገር አልተፈጠረም፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት ያመነ ማንኛውም ሰው ሌላውን ሰው የሚወድበት ሙሉ ብቃት በውስጡ አለው፡፡ ሰው ሰውን የሚወድበት ፍቅር ከእግዚአብሄር ተሰጥቶታል፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡5

የሰው ፍቅር ምንጩ ሰው አይደለም፡፡ ሰው ሰውን ለመውደድ የሰው ፍቅር አያስፈልገውም፡፡ ሰው ሰውን ለመውደድ የሚያስፈልገው የእግዚአብሄር ፍቅር ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን ምህረትና ፍቅር የተቀበለ ሰው ሌላውን መውደድ ይችላል፡፡

ከእግዚአብሄር የተቀበልነው ፍቅር አላማው ደግሞ ለሌሎች ፍቅር እንድንሰጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር የተቀበልነውን ፍቅር ለሌሎች እንድናከፋፍል በእግዚአብሄር ፍቅር ተወደናል፡፡

አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። የዮሐንስ ወንጌል 15፡9

በእግዚአብሄር ፍቅር የረካ ሰው ሌላውን በፍቅሩ ሌላውን ሰው ማርካት ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ፍቅር የተነሳ ሰው ሌላውን በፍቅሩ ማንሳት ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ፍቅር የተባረከ ሰው ሌላውን በፍቅሩ መባረክ ይችላል፡፡

ሰው ቢወድህ ጥሩ ነው፡፡ ሰው ባይወድህ ይጎዳበታል፡፡ ሰው ቢወድህ ይጠቀማል፡፡ ሰው ባይወድህም የምትኖረው በእግዚአብሄር ፍቅር ስለሆነ እንደ እግዚአብሄር ፍቅር በህይወትህ ላይ የሚጨምረውም ሆነ የሚቀንሰው ነገር የለም፡፡ በእግዚአብሄር ፍቅር ለሚኖር ሰው የሰው ፍቅር መጣም ቀረም ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡

የሰው ፍቅር በሚወደው ሰው ፍቅር መልስ ላይ መደገፍ የለበትም፡፡ የማይወድህ ሰው አለ? ችግር የለም ልትወደው ትችላለህ፡፡

ወዳጅ ወይም ባልንጀራ ማለት የሚወድ የሚጠቅም የሚባርክ ሰው ማለት ነው፡፡ ወዳጅነት የሚመሰረተው በእኛ መውደድ ላይ እንጂ ስንወደው መልሶ በሚወደን ሰው ላይ የፍቅር መልስ ላይ አይደለም፡፡

እኔ ለሰዎች መልካም አደርጋለሁ ሰዎች ግን ለመልካምነቴ ምላሽ አይሰጡም ብሎ ላሰበው የህግ አዋቂ ኢየሱስ የመለሰው መልስ ወዳጅነት የሚመሰረተው በአፍቃሪው ላይ እንጂ በተፈቃሪው መልስ ላይ እንዳልሆነ ያስተምረናል፡፡ የሉቃስ ወንጌል 10፡29-37

ኢየሱስ በምሳሌ ያስተማረው ወዳጅነት የሚመሰረተው እኛ ለሌሎች በምናደርገው መልካምነት ላይ እንጂ መልካምነታችንን አይተው በመልካምነት በሚመልሱት በሰዎች መልስ ላይ እንዳይደለ ነው፡፡

እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል? እርሱም፦ ምሕረት ያደረገለት አለ። ኢየሱስም፦ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው። የሉቃስ ወንጌል 10፡36-37

በክርስቶስ ኢየሱስ የተወደድንበት ፍቅር ታላቅ ፍቅር ስለሆነ እኛ በፍቅር እንድንኖር ሌላ ተጨማሪ የሰው ፍቅር አያስፈልገንም፡፡ የእኛን ፍቅር የሚያበረታታ የተፈቃሪ ሰው የፍቅር መልስ የለም፡፡ የእኛን ፍቅር የሚያጨልም የተፈቃሪው ሰው አሉታዊ መልስ የለም፡፡

የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡17-18

እኛ በፍቅር እንድንኖር በልባችን የፈሰሰው የእግዚአብሄር ፍቅር በቂ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ራሱን የቻለ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር የማንንም ሰው የፍቅር እርዳታ አይፈልግም፡፡

ከእግዚአብሄር የተቀበልነውን ምህረትና ፍቅር በህይወት ዘመናችን ሁሉ ሰጥተን አንጨርሰውም፡፡

ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። የማቴዎስ ወንጌል 18፡32-33

አትወደኝም? ምንም ችግር የለም፡፡ እኔ እወድሃለሁ፡፡ እኔ አንተን ለመውደድ የአንተ እኔን መውደድ ቅድመ ሁኔታ ወይም ግዴታ አይደለም፡፡ ለእኔ መልካም አታስብም? መልካም አትናገርም? መልካም አትናገርም? ምንም ችግር የለም፡፡ እኔ ግን ለአንተ እንዲሁ በነፃ  መልካም አስባለሁ መልካም እናገራለሁ መልካም አደርጋለሁ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ፍቅር #ምክንያት #ያለምክንያት #እንዲሁ #ውሳኔ #የዘላለም #ታማኝ #ምንጭ #መውደድ #ስሜት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ማስተዋል #ልብ #መሪ

የብዙ ሰዎች ፍቅር የሚቀዘቅዝባቸው ሶስቱ ዋና ዋና ምክኒያቶች

your will1.jpg

ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። የማቴዎስ ወንጌል 24፡12-13

ፍቅር ታላቅ ሃብት ነው፡፡ የፍቅር ህይወት ታላቅ ስብእና ነው፡፡ ፍቅር ክብር ነው፡፡ ፍቅር ውበት ነው፡፡

ኢየሱስን እንደ አዳኛችን የተቀበልን ሁሉ ከእግዚአብሄር በመወለዳችን የእግዚአብሄር ፍቅር በእኛ ውስጥ አለ፡፡ የመውደድ እምቅ ጉልብት ቢኖረንም ይህ በውስጣችን የተጠራቀወመውን ጊልበት አውጥቶ ለብዙዎች በረከት ለማድርግ የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡5

ፍቅር መታወቂያችንና ክብራችን ነው፡፡ ፍቅር ሃብታችንና መገለጫችን ነው፡፡ ለፍቅር ተወልደናል፡፡ ሰው ፍቅር ከሌለው የተፈጠረበተን አላማ የሳተ ከንቱ ሰው ነው፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡1

ፍቅር ምንም ያህል የከበረ ቢሆንም ፈተና አለበት፡፡ የፍቅርን ፈተና ያላለፉ ሰዎች ፍቅራቸው ትቀዘቅዛለች፡፡

ፍቅር ቅፅበታዊ አይደለም፡፡ ፍቅር ከትትልና እንክብካቤ የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ ፍቅር ዝም ብሎ ከተተወ ፍቅርን ሊያቀዘቅዙ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ስላሉ ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡

ፍቅር ግን እንዳይቀዘቅዝ እንዲያውም እየጋለና እየጨመረ እንዲሄድ ለማድረግ እነዚህን ፍቅርን የሚያቀዘቅዙትንና የወይንም ቦታችንን የሚያጠፉትን ጥቃቅን ቀበሮዎች ከህይወታችን መሰለልና ማጥፋት አለብን፡፡

ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡15

 1. ስንፍናና አለመትጋት

ፍቅርን ሊያጠፉ የሚመጡ ብዙ ውሆች ስላሉ ፍቅር እንዳይጠፋ ትጋት ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ከተተወ ይጠፋል፡፡ ፍቅር እንክብካቤ ካልተደረገለት ይበላሻል፡፡ እንደእሳት ፍቅር ካልቆሰቆሱትና ካላቀጣጠሉት ይከስማል፡፡ ፍቅር እንደችግኝ ማዳበሪያ ካላደረጉለት ውሃ ካላጠጡትና ካልኮተኮቱት ይደርቃል፡፡

ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ወደ ዕብራውያን 10፡24-25

ፍቅር ሌላውን በመረዳት ራስን ከሚወዱት ሰው ጋር ማስተባበር ነው፡፡ ፍቅር የምንወደውን ሰው ማጥናትና መረዳት ይጠይቃል፡፡ የምንወደውን ሰው ለመረዳት መነጋገር መወያየት ይጠይቃል፡፡

በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ወደ ዕብራውያን 10፡25

ፍቅር ራስን በምንወደው ሰው ቦታ አስቀምጦ ነገሮችን ካለአድልዎ ማየት ይጠይቃል፡፡ የምንወደውን ሰው ለመረዳት ጊዜ መስጠት ይጠይቃል፡፡ የምንወደውን ሰው ለመረዳት ጥረት ይጠይቃል፡፡

 1. መሰናከልና የክፋት መልስ መመለስ

ፍቅር የሚቀዘቅዝበት ምክኒያት ለፍቅራችን መልስን መጠበቅ ነው፡፡ ለፍቅር ድርጊታችን  ከምንወደው ሰው መልስ የምንጠብቅ ከሆንን አንዳንዴ መልካም መልስ ስለማናገኝ ይፍጠንም ይዘግይም ፍቅር መቀዝቀዙ አይቀሬ ነው፡፡ ፍቅር እንካ በእንካ ጉዳይ አይደለም፡፡ ፍቅር የመስጠት የመባረክ የማንሳትና የመጥቀም ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር እንዲያው ለመስጠት ብሎ የመስጠት ጉዳይ እንጂ መልስን ጠብቆ የመስጠት ጉዳይ አይደለም፡፡

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? የማቴዎስ ወንጌል 5፡46-47

ፍቅር እግዚአብሄር ለሌላው ሰው እኛ ውስጥ ያስቀመጠውን መልካምነት በታማኝነት የማስጠት ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር ደጋግ መጋቢነት ነው፡፡ ፍቅር ንግድ አይደለም፡፡ ፍቅር ስጦታ መስጠት ነው፡፡ ፍቅር ሌላውን የተመረቀ እድለኛ ማድረግ ነው፡፡

 1. ራስ ወዳድነትና የእግዚአብሄርን ፍቅር በሚገባ አለመረዳት

ፍቅር ከራስ ያለፈን ነገር ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ሌላው ላይ ማተኮርን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ሌላውን መድረስ ይጠይቃል፡፡ ፍቅር በራስ ነገር አለመያዝና አለመወሰድን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር በራስ ጉዳይ ላይ ከመጠን ያለፈ ትኩረትን አለማድረግ ይጠይቃል፡፡

ለስጋችን ፊት ከሰጠነው ለራሳችን ህይወት ብቻ ተጨንቀን ማንንም ሳንደርስ እንድንሞት ሊያደርገን ይችላል፡፡ ስጋችንን እህህ ብለን ከሰማነው በራሳችን ጉዳይ ተጠምደን ለማንም ሰው በረከት ሳንሆን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡ ለስጋችን ፊት ከሰጠነው በእኛ ውስጥ ለሌሎች የተጠራቀመውን ጉልበት አውጥተን ሳንጠቀም እንድናልፍ ያደርገናል፡፡ የስጋን ምስኪን እኔ አስተሳሰብ ከሰማነው ለራሳችን ብቻ እያዘንን እና እየተጨነቅን እግዚአብሄር ለሌሎች በእኛ ውስጥ ካስቀመጠው ስጦታ ጋር እናልፋለን፡፡ የስጋን ለአንተስ ማን አለህ የሚለውን የሽንፈት ንግግር ከሰማነው ለራሳችንም ለሌሎችም ሳንጠቅም እንድናለፍ ያደርገናል፡፡

ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡10

እግዚአብሄር እኔን ወዶኛል እኔ ሌሎችን እወዳልሁ ካልን ግን የእግዚአብሄር አላማ ፈፅመን ማለፍ እንችላል፡፡ እግዚአብሄር አስቅድሞ ወዶኛል ስወደው መልሶ የሚወደኝ ሰው አያስፈልገኝም ካልን በፍቅር ሌሎችን ማንሳት ማነፅና መባረክ እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር በወደድን ፍቅር ከረካን ሌሎችን በፍቅራችን ማርካት እንችላለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መውደድ #መወደድ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእግዚአብሄር ቢጠሩም እንኳን የማይመረጡ አስር አይነት ሰዎች

your will1.jpgየተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና። የማቴዎስ ወንጌል 22፡14

እግዚአብሄር ቅን ፈራጅ ነው፡፡ እግዚአብሄር እውነተኛ ዳኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሁሉም ሰው እኩል እድልን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር ይመርጣል እንጂ ሁሉንም አይወስድም፡፡  እግዚአብሄር የሚመርጥበት የራሱ መመዘኛ አለው እንጂ እግዚአብሄር ይመርጣል፡፡ እግዚአብሄር ቅን ፈራጅ ነው እንጂ እግዚአብሄር አይፈርድም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በቅንነት ይፈርዳል፡፡

የሰው በረከትና ስኬታማነት በሰው በራሱ መልስ ይደገፋል፡፡ እግዚአብሄር እድሎችን ሁሉ ከፈተ ማለት ሰው ሁሉ በእድሎቹ ይጠቀማል ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር እድሎችን ሁሉ ከፈተ ማለት ሰውን ሁሉ ወደ እድሎቹ ውስጥ እንዲገባ እግዚአብሄር ያስገድዳል ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ከነፃ ፈቃድ ጋር የፈጠረ እግዚአብሄር የሰውን ነፃ ፈቃድ ያከብራል፡፡ እግዚአብሄር ጨዋ አምላክ ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰው ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ቢፈልግም መዳንና አለመዳን በሰው ምርጫ ላይ ይደገፋል፡፡

ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡3-4

እግዚአብሄር ሰውን ምንም ቢወደውና ለእርሱ ያለው አላማ የፍቅር አላማ ቢሆንም ሰው ይህንን የፍቅር አላማ ለመቀበልም ላለመቀበልም ነፃ ፈቃድ አለው፡፡

እግዚአብሄር የጠራቸው ሰዎች ሁሉ የማይመረጡበት ምክኒያት እና እግዚአብሄር ቢጠራቸውም የማይመረጡትን አይነት ሰዎች ከእግዚአብሄር ቃል እንመለከት፡፡

 • ሃላፊነቱን ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሄር የሚያስተላልፉ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

ለህይወታችው ምንም ሃላፊነት የማይወስዱ ሰዎች የተጠሩም ቢሆን እንኳን አይመረጡም፡፡ ሁል ጊዜ ሃላፊነቱን በእግዚአብሄር ላይ የሚያደርጉ ሰዎች የራሳቸውን ሃላፊነትና የህይወት ድርሻ የማይወጡ ሰዎች አይመረጡም፡፡ በህይወታቸው ስለሆነው ነገር ሁሉ የአርባ ቀን እድሌ ነው በማለት ሃላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ ሰዎች አይመረጡም፡፡ ስለወደፊት ህይወታቸው ምንም ነገር የማያደርጉ ሰዎች መስራተ የሚችሉትን ነገር ከመስራት ይልቅ እጃቸውን አጣጥፈው አንድ ነገር እንዲደረግላቸው ብቻ የሚጠብቁ ሰዎች አይመረጡም፡፡

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። የማቴዎስ ወንጌል 11፡12

 • እግዚአብሄር እንደቸገረው የሚመስላቸው ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

ከእግዚአብሄር ጋር የምንጣበቀው ለራሳችን ብለን እንጂ እግዚአብሄር ስለቸገረው ልንረዳው አይደለም፡፡ ሃጢያት የማንሰራው ህይወታችንን ላለማጉደፍና የሌሎችን ህይወት ላለማበላሸት እንጂ ለእግዚአብሄር አምላክነት አንድ ነገርን ለመጨመር አይደለም፡፡

ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ? ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል? እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፤ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል። መጽሐፈ ኢዮብ 35፡6-8

 • ነፃ ፈቃድ እንዳላቸው የማያውቁ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

ሰው እንደ ሬዲዮና ቴሌቪዠን ሲከፍቱት የሚከፈት ሲዘጉት የሚዘጋ የራሱ ፈቃድ የሌለው ግኡዝ አይደለም፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረውን ሰው ፈቃድ ያከብራል፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረውን ሰው መልካሙን መንገድ ያሳየዋል እንጂ በመልካሙ መንገድ እንዲሄድ አያስገድደውም፡፡

በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ ኦሪት ዘዳግም 30፡19

 • እግዚአብሄር ኩሩ አምላክ እንደሆነ የማይረዱ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

እግዚአብሄር የሚፈልገው በፍቅር የሚገዙለትን እንጂ በግድ የሚያመልኩትን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በግድ የሙጥኝ የሚል አምላክ  አይደለም፡፡

አሳንም ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 15፡2

 • ከእግዚአብሄር ጋር አብረው ሰራተኛ እንደሆኑ የማያውቁ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን አብረነው እንድንሰራ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረን በሙሉ ፈቃደኝነት ደስ ብሎን አብረነው እንድንወጣና እንድንገባ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር አብረው ሰራተኛ እንደሆኑ የማያውቁ በራሳቸው ጉልበት ሁሉን ነገር ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ቢጠሩም አይመረጡም፡፡

የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡9

 • ነፍሳቸውን የማይክዱ ሰነፍ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

እግዚአብሄር ትጉህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስንፍና የለበትም፡፡ እግዚአብሄር አብሮ የሚሰራው ከትጉሃና ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሄር ነገር ዋጋ መክፈል ውድ እንደሆነ እና ብክነት የሚያስቡ ሰዎች አይመረጡም፡፡ ነፍሳቸውን ከእግዚአብሄር በላይ ሊያስደስቱ እንደሚገባቸው የሚያስቡ ሰዎች በእግዚአብሄር የማይመረጡ ሰዎች ናቸው፡፡

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። የማቴዎስ ወንጌል 16፡24-25

 • እግዚአብሄርን በሚገባ የማያምኑ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

የሰው ድርሻ ለእግዚአብሄርን መንግስት ስራ መስራት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ድርሻ የሰውን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የማያምኑ ሰዎች ስለምን እንበለላን ስለምን እንጠጣለን ብለው እግዚአብሄር በሚያደርግላቸው ነገር እና በእግዚአብሄር ድርሻ ላይ በመጨነቅ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሄር አገልግሉኝ ሲላቸው ሊጠቅማቸው ሳየሆን አለአግባብ ሊጠቀምባቸው የሚመስላቸው ሰዎች ሁል ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር ስለሚተላለፉ ለእግዚአብሄር ስራ ቢጠሩ እንኳን የማይመረጡ ሰዎች ናቸው፡፡

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። የማቴዎስ ወንጌል 25፡24-25

 • የሰበብ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

መስራት የሚገባቸውን ነገር ለምን መስራት እንደማይችሉ ስንኩል ምክኒያት የሚያቀርቡ ሰዎች ቢጠሩን እንኳን አይመረጡም፡፡ እግዚአብሄርን ላለማገልገል ሁላችንም ምክኒያቶች ይኖሩናል፡፡ እንዲያውም ጌታን ላለመከተል ምክኒያት የለም ብንል እንዋሻለን፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ምክኒያት ጌታን ላለመውድና ለጌታ ዋጋ ላለመክፈል በቂ ምክኒያት አይሆንም፡፡ ነገር ግን ምክኒያቶችን ጥሰው በዘመናቸው የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርጉ ሰዎች ይመረጣሉ፡፡

ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የፊተኛው፦ መሬት ገዝቼአለሁ ወጥቼም ላየው በግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። ሌላውም፦ አምስት ጥምድ በሬዎች ገዝቼአለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው። ሌላውም፦ ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው። የሉቃስ ወንጌል 14፡18-20

 • በአለም ውድድር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

ሰው በአለም ውድድር ውስጥ ገብቶ የእግዚአብሄርን ስራም ሊሰራ አይችልም፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች ሌላ ምንም የሚሰሩት በህይወታቸው የተቀመጠ አላማ ስለሌለ እርስ በእርስ በከንቱ ይወዳደራሉ ይፎካከራሉ፡፡ ክርስቶስን ሊከተል የሚወድ ሰው ግን ከአለም ፉክክር ራሱን ማግለል አለበት፡፡ በአለም ፉክክር ውስጥ መወዳር የሚፈልጉ ሰዎች ለጌታ ከመኖር ውድቅ ስለሚሆኑ የማይመረጡ ሰዎች ናቸው፡፡

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡12

 • በሁለት ሃሳብ የሚወላውሉ ራስ ወዳድ ሰዎች በእግዚአብሄር አይመረጡም

እግዚአብሄርንም መውደድ ራስ ወዳድም መሆን አይቻልም፡፡ እግዚአብሄርን የሚወድ ሰው ከራሱ ጥቅምና ፍላጎት በፊት የእግዚአብሄርን ነገር ማስቀደም አለበት፡፡

ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው። ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። የሉቃስ ወንጌል 9፡59-62

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የተጠሩ #ብዙዎች #የተመረጡ #ጥቂቶች #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ምርጫችንን እንጂ ህይወታችንን አንወስንም

piedi wiki-2.jpg

ዛሬ የምንኖረው ኑሮ የትላንት ምርጫችን ውጤት ነው፡፡ ነገ የምንኖረው ኑሮ ደግሞ የዛሬ ምርጫችን ውጤት ነው፡፡ የትላንት ምርጫችንን እንጂ የዛሬ ኑሯችንን መወሰን እንደማንችል ሁሉ የዛሬ ምርጫችንን እንጂ የነገ ኑሯችንን መወሰን አንችልም፡፡

ዛሬ የምንወስነው ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነገ የሚያመጣውን መራራ ፍሬ እንድንጋፈጠው ያስገድደናል፡፡ ዛሬ የስንፍና ውሳኔ ወስኖ ነገ የስኬትን ውጤትን ለማግኘት መመኘት ትርፉ ድካም ነው፡፡ ዛሬ የፍርሃትን ውሳኔ ወስኖ ነገ የእምነትን ስኬት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሄርን ባለመፈለግ በግብታዊነት ውሳኔ ወስኖ ነገ ህይወቴ ይከናወናል ብሎ መጠበቅ ከንቱ ነው፡፡

ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። የማቴዎስ ወንጌል 7፡16-18

ዛሬ በስጋዊ ፍላጎት ወስኖ ነገ መንፈሳዊ ነገርን ማጨድ ዘበት ነው፡፡ ዛሬ ላይ በስጋዊ ሚዛን ውሳኔን ወስኖ ነገ በመንፈሳዊ ሚዛን ውጤቱን ለመቀበል መሞከር እግዚአብሄርን ለማታለል እንደመሞከር ነው፡፡

አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7-8

ስለትላንቱ ውሳኔያችን ንስሃ ገብቶ ከመመለስ ውጭ ምንም ላናደርግ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ስለነገ ኑሯችን ዛሬ መልካምን ብቻ ለመዝራት መወሰን እንችላን፡፡

ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡10-12

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ክብር #ራእይ #ስጋ #ሃሳብ #የዘራውን #ያጭዳል #አትሳቱ #አይዘበትበትም #መበስበስ #ሰላም #ህይወት #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ነገ #ዛሬ #ውሳኔ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መንገድ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የማይለወጥ ሰው

1_yVposzI8ujkBhVJgaZYaEA.jpeg

የሰው ትክክለኛ ህይወት ከመለወጥ ይጀምራል፡፡ ሰው እውነተኛ በረከት ውስጥ የሚገባውምው በመለወጥ ብቻ ነው፡፡ ያልተለወጠ ሰው መኖር ያልጀመረ ሰው ነው፡፡

በተፈጥሮ ስንመለከት ሰው ከተወለደ ጀምሮ ይለወጣል፡፡ ለውጥ የሰው ተፈጥሮ አንድ ክፍል ነው፡፡ ሁሉም ነገር ይለወጣል፡፡ በህይወት የማይለወጥው ነገር ለውጥ ብቻ ነው፡፡ ለማደግ ለውጥ ግዴታ ነው፡፡

በመንፈሳዊውም ብንመለከት የሰው እውነተኛ ህይወት ከለውጥ ይጀምራል፡፡

ሰው ለመለወጥ ሲወስን ህይወትን ያገኛል፡፡ ሰው መንገዱን ለመለወጥ ሲወስን ህይወቱ ይታደሳል፡፡ የህይወት መታደስ ብቸኛው መንገድ ለውጥ ነው፡፡

እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። የሐዋርያት ሥራ 3፡19-20

ለውጥ መርገም አይደለም፡፡ አስፈላጊ ለውጥ የህይወት በረከት ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ለውጥን እንዲሁ ይፈሩታል፡፡ ለውጥ ለሰነፎች አይደለም፡፡ ለውጥ ለትጉ ሰዎች ነው፡፡ ለውጥን የሚወዱ ሰዎች ለመትጋት የጨከኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለውጥን የሚወዱ ሰዎች ለመለወጥ ቅናት ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለውጥን የሚወዱ እና የሚቀበሉ ሰዎች ለማደግ ልቡ ያላቸው ፣ ሃሞታቸው ያልፈሰሰና ልባቸው ያላረጀ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

ለውጥ ስራን ይጠይቃል፡፡ ለውጥ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ ለውጥ መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ ለውጥ ራስን መመርመር ይጠይቃል፡፡ ለውጥ ቅድሚያ አሰጣጥን መፈተሽና ማስተካከልን ይጠይቃል፡፡ በዘመኑ መለወጥ ተወስደን ወደኋላ እንዳንቀር መጽሃፍ ቅዱስ ይመክራል፡፡

ዘመኑ ሲለወጥ የተለወጠውን ዘመን የምንገዛበትና ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅም የምናውልበትን የእግዚአብሄር ጥበብ መፈለግ አለብን፡፡

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16

ሁኔታዎች ሲለወጡ ስለሁኔታው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈለግ መትጋት በሁኔታዎች ውስጥ አሸናፊ እንድንሆን ያደርገናል፡፡

ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-17

ለውጥ የሚለውጠው ቅድሚያ አሰጣጣችንን ነው፡፡ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ሁሉ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ ቅድሚያ አሰጣጣችን ለነበርንበት ህይወት ተስማሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ አሰጣጣችን አዲስ ለምንገባበት የህይወት ደረጃ ተስማሚ ላይሆንና ማስተካከል የሚያስፈልገው ሊሆን ይችላል፡፡ ቅድሚያ አሰጣጣችን መስተካከልና በአዲሱ የህይወት ደረጃ መቃኘት ሊኖርበት ይችላል፡፡

ለውጥ ቀላለ ነገር አይደለም፡፡ ከለመድነው እና ከተመቻቻንበት ነገር ወጥተን አካሄዳችንን መለወጥ የህይወት ፈተና ነው፡፡ የሁኔታዎች መለወጥ መልስ የሌለው ጥያቄ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን መልስ የሌለው ጥያቄ የለም፡፡ ለማንኛውም ጥያቄ መልስ የምናገኘው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ጥያቄ አስፈሪነቱ መልስን እስከምናገኝ ድረስ ብቻ ነው፡፡

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13

ለመለወጥ የሚማር ልብ ያስፈልገናል፡፡ ለመለወጥ የማላውቀው ነገር አለ ብለን ማመን ይጠይቃል፡፡ ሁሉንም አውቃለሁ ከዚህ ወዲያ የሚያስተምረኝ ሰው የለም ብለን በትእቢት ካሳብን ለውጥን በደፈናው እንቃወመዋለን፡፡ ለመለወጥ የሚማር የዋህ ልብ ይጠይቃል፡፡ ለመለወጥ አዲስ ነገርን ለመማር የተዘጋጀ ልብን ይጠይቃል፡፡

ህይወት ሁልጊዜ አንድ አይነት እንደሆነ የሚፈልጉ ሰዎች ለውጥ ያስፈራቸዋል፡፡ ህይወት አንድ አይነት እንዲሆን የሚመኙ ሰዎች ለውጥን በፀጋ መቀበል ያቅታቸዋል፡፡ ነገረ ግን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከለውጥ ጋር አብረው መኖር እንደሚችሉ የሚያምኑ ሰዎች ከለውጥ ውስጥ የተሻለ ነገርን ማውጣት ይችላሉ፡፡ የለውጥ በጎ ጎን የሚመለከቱ ሰዎች ለውጥን ለመቀበል ይዘጋጃሉ፡፡ ያለመለወጥንና ያለማደግን አስከፊነት የሚረዱ ሰዎች ለለውጥ ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ይወስናሉ፡፡

ለመለወጥ ልበ ሰፊ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ለመለወጥ ከምናውቀው የተለየ ሃሳብን ማስተናገድ ይጠይቃል፡፡ ለመለወጥ አዲስን መንገድን ለመሞከር ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡ ለመለወጥ አዲስ ነገርን በፀጋ መቀበልን ይጠይቃል፡፡

ለመለወጥ ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ ለመወሰን የሚፈራ ሰው አይለወጥም፡፡ ለመወሰን አደጋን መጋፈጥ ወይም ሪስክ መውሰድን ይጠይቃል፡፡ ላለመሳሳት ከመጠን በላይ የሚፈራ ሰው ለመወሰን ይፈራል፡፡ የማይወስን ሰው ደግሞ አይለወጥም ብሎም አያድግም፡፡ ብሳሳትም የህይወቴ መጨረሻ አይደለም ብሎ የሚያምን ሰው ውሳኔ ለመወሰን አይፈራም፡፡

የህይወት ስኬት የቀጣይ ለውጦች ድምር ውጤት ነው፡፡

በህይወታቸን አስፈላጊ ለውጦችን ባደረግን ቁጥር እንለወጣለን፡፡ በተለወጥን ቁጥር እናደርጋለን ፡፡ ባደግን ቁጥር በምድር ላይ የእግዚአብሄርን አላማ ፈፅመን ማለፍ እንችላለን፡፡

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጌታ #ኢየሱስ #ሃሳብ #ቃል #እግዚአብሄር #መንፈስቅዱስ #ንስሃ #መለወጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #አእምሮ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከእረፍት የሚጀምር ስራ

3-Tips-to-Enrich-your-Life-and-the-Lives-of-Others.jpg

ክርስትና የእግዚአሄርን ሃሳብ በምድር ላይ ማስፈፀም ነው፡፡ ነገር ግን ክርስትና ከስራ አይጀምርም ፡፡ ክርስትና የጥረትና የግረት ጉዳይ ሳይሆን የእረፍት ጉዳይ ነው፡፡ ክርስትና የሚጀምርው ከእረፍት ነው፡፡ የክርስትና ሃይል የሚመነጨው ከእረፍታችን ነው፡፡ ክርስትና የሚቀጥለውም በእረፍት ነው፡፡ ክርስትና የሚጨርሰውም በእረፍት ነው፡፡

እውነት ነው ክርስትና መመላለስ ነው፡፡ ክርስትና መኖር ቃሉን በተግባር መፈፀም ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በፍቅር እንድንኖር ያዘናል፡፡ ነገር ግን የክርስትና ህይወት የሚጀምረው በፍቅር ከመኖር ሳይሆን የእግዚአብሄርን ፍቅር ከመረዳትና ከመቀበል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር የተረዳና በእግዚአብሄር ፍቅር የረካ ሰው ብቻ ነው ሌላውን ለመውደድ ሃይል የሚያገኘው፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቅር የተካፈለ ሰው ብቻ ነው ፍቅርን ለሌሎች በእረፍት ሊያካፍል የሚችለው፡፡

ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡2

የእግዚአብሄርን ብርሃን ያላየና ያልተረዳ ሰው በብርሃን የሊመላለስ አይችልም፡፡ በብርሃን ሊመላለስ የሚችለው የእግዚአብሄርን ብርሃን ያየና የተረዳ ሰው ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፡7

ሰው የስጋን ምኞት የማይፈጽመው በነፃ የተሰጠውን ወደ እውነት ሁሉ የሚመራውን የእግዚአብሄርን መንፈስ መከተል ሲያውቅ ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡16

ክርስትና ከመመላለስ አይጀምርም፡፡ ክርስትና የሚጀምረው ከመቀመጥ ነው፡፡

በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡6-7

ክርስትና የሚጀምረው ከሃይል ሳይሆን ከስልጣን ነው፡፡ በሰማያዊ ስፍራ የተቀመጥንበትን የስልጣን ስፍራችንን ስንረዳ ስልጣንን እንረዳለን በእረፍት እንጠቀመዋለን ስራም በመስራት ፍሬም እናፈራለን፡፡

ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡20-22

መልካሙን ስራ ለማድረግ ተፈጥረናል፡፡ ባዘጋጀልን መልካም ስራ መመላለስ በራስ ጉልበትና ችሎረታ ሳይሆን ከምን ስጦታ ጋር እንተደሰራን ለምን አላማ እንደተፈጠርን ከማወቅ ይጀምራል፡፡

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡10

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ክርስቶስ #ጌታ #እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #እውቀት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው

eagle eagle.jpg

የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበት ብቸኛው መንገድ እምነት ነው፡፡ ሰው ካለ እምነት በተፈጥሮ አይን ከማይታየው ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ግንኙነት ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሰው የተፈጠረበት አላማ በእምነት ከእግዚአብሄር ጋር እንዲኖርና እንዲሰራ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእምነት እንዲኖር ነው፡፡

ሰው እምነትን ከጣለ ከእግዚአብሄር ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አይኖረውም፡፡ እምነት የሌለው ሰው ምንም የስሜት ህዋሳት እንደሌሉት ከማንም ጋር መገናኘትና መግባባት እንደማይችል ሰው ነው፡፡

ሃጢያት ማለት የተፈጠሩበትን አላማ መሳት ማለት ነው፡፡ ሰው ከእምነት ከወጣ የተፈጠረበትን አላማ ይስታል፡፡

ሰው የእግዚአብሄርን አላማ የማይስተው በተፈጥሮ አይን የማይታየውን ሲያይ ብቻ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚያስደስተው በተፈጥሮ አይን በሚታየው ነገር ላለመወሰድ ሲወስን ነው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18

ሰው የእግዚአብሄርትን አላማ የማይስተው የልቦናዎቹ አይኖች ሲበሩ ብቻ ነው፡፡

ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1፡18-19

ሰው የእግዚአብሄርን አላማ የማይስተው የእግዚአብሄርን ቃል ሲያምን እና ሲከተል ብቻ ነው፡፡

ሰው ከተፈጠረበት አላማ ዝንፍ የማይለው ሁልጊዜ ታምኖ በእምነት አንጂ በማየት ባለመመላለስ ነው፡፡

እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡6-7

በእምነት እንድንኖር ታልመን ስለተፈጠረን በእምነት ከምናደርገው ማንኛውም ነገር ውጭ እግዚአብሄርን ማስደሰት አንችልም፡፡ በእምነት የምናደርገው ማንኛውም ነገር እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ በእምነት የምናደርገው ማንኛውም ነገር የተፈጠርንበትን በእምነት የመኖር አላማ መሳት ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

ሰው በምድር ላይ ምንም ነገር ቢያደርግ በእምነት ካልሆነ የተፈጠረበትን አላማ መሳት ወይም ሃጢያት ነው፡፡

የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ያለእምነት #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አላማ #መሳት #ሃጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ስፍራህን አትልቀቅ

your will1.jpg

ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ። መጽሐፈ መክብብ 10፡4

እግዚአብሄር ሁልጊዜ ሊመራን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የመራህን ነገር እስከመጨረሻው ድረስ ማድረግ በጣም ወሳኝና ሁልጊዜ ፍሬያማ የሚያደርገን ነገር ነው፡፡

ሁኔታዎች ቢለዋወጡም እግዚአብሄር በፊት ከመራን ነገር ፈቀቅ ማለት የለብንም፡፡ እግዚአብሄር የተለየ ነገር ሲናገረን ብቻ መንገዳችንን መለወጥ ያለብን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እንድንለውጥ ሳይናገርህ መጨረሻ ላይ የመራንን ምሪት መከተል ትተን ሌላ ነገር ማድረግ ከአላማችን የሚያስተጓጉለን ነገር ነው፡፡

እግዚአብሄር እንድትለውጥ እስካልመራህ ድረስ እግዚአብሄር መጨረሻ ላይ መርቶህ ስታደርገው የነበረውን ነገር እንደማድረግ አስተማማም ምሪት የለም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል

Hawaii-Beach-Wallpaper-HD_8pA2vrZ.jpgመታዘዛችሁ ለሁሉ ተወርቶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ። የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። ወደ ሮሜ ሰዎች 16፡19-20

ሰይጣን የህይወት ጠላት ነው፡፡ የሰይጣን አላማ መስረቅ ማረድና ማጥፋት ነው፡፡ ሰመስረቅ ከማረድና ከማጥፋት ውጭ ሰይጣን ሌላ አላማ የለውም፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10

ሰይጣን ህይወታችንን ሊውጥ ዙሪያችንን ይዞራል፡፡ ሰይጣን ከአላማችን ሊያሰናክለን ይፈልጋል ይተጋል፡፡

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡8-9

ስለዚህ እኛ ደግሞ ለበጎ ነገር ጥበበኞች መሆን አለብን፡፡ እንዳመጣልን የምንኖር ሰዎች መሆን የለብንም፡፡ ህይወታችንን እንዴት እንደምንመራ ማወቅ አለብን፡፡ በጎን ነገር ለማድረግ ፈጣን መሆን አለብን፡፡

ክፉን ነገር ላለማድረግ የምንጠነቀቅ ሰዎች መሆን አለብን፡፡ ክፉን በክፉ ፋንታ ላለመመለስ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ያለንን ሃይልና  ተሰሚነት ተጠቅመን ክፋትን ላለማድረግ መወሰን አለብን፡፡ ክፉ ሰዎች እነርሱን ተከትለን ክፋትን እንድንሰራ የሚመጣውን ፈተና ክፋትን ባለማድረግ በአሸናፊነት ማለፍ አለብን፡፡ ክፋትን ተከትለን ክፉን በክፉ ላለመመለስ ክፋት በእኛ እንዲያበቃ የክፋትን ሃሳብ በውስጣችን መግደል አለብን፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡20

ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች ስንሆን የእኛን ሰላም የሚፈልገው እግዚአብሄር የሰይጣን አላማ በህይወታችን ላይ እንዳይሳካ ያደርጋል፡፡ ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች ስንሆን የሰይጣንን አሰራር ከንቱ ያደርገዋል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ሰይጣን #ዲያብሎስን #ሽንገላ #ሃሳብ #አእምሮ #ጥበበኞች #ክፉ #የዋሆች #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሄር በአብዛኛው የሚናገርበት መንገድ

img_20160229_224319.jpg

እግዚአብሄር በአብዛኛው የሚናገርበት መንገድ

እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ሊያናግረው ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ሊያናግረውና ሊሰማው ነው፡፡

እግዚአብሄር ሁልጊዜ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር አንዳንድ ጊዜ በድምፅ ይናገራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ብዙ ጊዜ በድምፅ አይናገርም፡፡

የእግዚአብሄርን ድምፅ እርሱ በወደደበት ጊዜ ብቻ ወደእኛ ይመጣል፡፡ እኛ የእግዚአብሄርን ድምፅ ማምጣት አንችልም፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ በድምፅ እንዲናገረን መፈለግ ትክክል አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ በድምፅ ስለማይናገር እግዚአብሄር ሁልጊዜ በድምፅ እንዲናገረን መፈለግ ለስህተት ያጋልጠናል፡፡

እግዚአብሄር አስፈላጊ በመሰለው ጊዜ ብቻ በድምጽ ይናገረናል፡፡

እግዚአብሄር ግን ሁልጊዜ ስለሁሉም ነገር ሊመራን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ፈቃዱን እንድንፈልግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ፈቃዱን እንድንከተል ይሻል፡፡

እግዚአብሄር ሁልጊዜ በድምፅ ካልተናገረን ሁልጊዜ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንለይበት መንገድ የውስጥ ምስክርነት ይባላል፡፡

የእግዚአብሄር ድምፅ አንድ ቃል ወይም አንድ አረፍተ ነገርን በልባችን የምንሰማበት መንገድ ነው፡፡ የውስጥ ምስክርነት ግን ስለ አንድ ነገር ስንፀልይ ፣ በእግዚአብሄር ፊት ጊዜ ስንወስድና ስንቆይ አዎ ወይም አይደለም የሚል ምስክርነት ማግኘት ነው፡፡

የውስጥ ምሰክርነት ስለአንድ ነገር ስንፀልይ እግዚአብሄር ያለውን አስተያየት የእግዚአብሄርን ደስተኛ ወይም የተኮሳተረ ፊት ማየት ነው፡፡ የውስጥ ምስክርነት ስለምንፀልይበት ወይም ስለምናስበው ነገር ልባችን ሰላም መሆኑና አለመሆኑን መለየት ነው፡፡ አይምሮዋችን ሳይሆን ልባችን ከተደሰተ እግዚአብሄር ተደሰተ ማለት ነው፡፡ በአእምሮዋችን ረብሻ እያለ ልባችን ሰላም ከሆነ እግዚአብሄር ቀጥሉ እያለን ነው ማለት ነው፡፡ የልባችን ሰላም ከአእምሮዋችን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሄርን ልብ የሚያሳይ ሰላም ነው፡፡

አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡7

የውስጥ ምስክርነት ልንወስደው ስላለው እርምጃ የደስታን ስሜት ወይም የረብሻ ስሜት በልባችን በመፈልግ እግዚአብሄር ስለእርምጃችን ያለውን ሃሳብ የማወቂያ መንገድ ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና። መዝሙረ ዳዊት 85፡8

ይህ የውስጥ ምስክርነት እኛ በልባችን ፈልገን የምናገኘው የምሪት አይነት ነው እንጂ እንደ እግዚአብሄር ድምፅ እርሱ ሲናገርን በድምፅ የምንሰማበት መንገድ አይደለም፡፡

እግዚአብሄር ስለሁሉም ነገራችን ምስክርነቱን መስጠት ይፈልጋል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የውስጥ ምስክርነትን ለማግኘት መፀልይ ምስክርነቱን ለመረዳት ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡14፣16

የእግዚአብሄር ልጅ ነህ ብሎ በድምፅ ባይናገረንም የእግዚአብሄር ልጅ መሆናችንን በውስጣችን ያለው የእግዚአብሄር መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በክርስትና ህይወታችን በሙሉ ያ መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ስለ እግዚአብሄር ፈቃድ ይመሰክርልናል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የውስጥምስክርነት #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ሆድ አምላኩ

download (80).jpg

እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 16፥18

መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፥19

ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ

your will.jpg

የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ ህይወትንና ትንፋሽን የሰጠን እግዚአብሄር ነው፡፡

አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ። መጽሐፈ መክብብ 12፡7

የእያንዳንዳችንን ትንፋሽ የያዘው እግዚአብሄር ነው፡፡

ምድርን አደራ የሰጠው ማን ነው? ዓለምንስ ሁሉ በእርሱ ላይ ያኖረ ማን ነው? እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል።  መጽሐፈ ኢዮብ 34፡13-15

በመፅሃፍ ቅዱስ በትንቢተ ዳንኤል ምእራፍ 5 ከቁጥር 18 እስከ 23 የምንመለከተው ታሪክ የንጉስ አባት የናቡከደነፆር የልጁ የብልጣሶር ታሪክን ነው፡፡

ልጁ ብልጣሶር እግዚአብሄርን ስላልፈራና ስላላከበረ እግዚአብሄር የተናገረውን ንግግር እንመለከታለን፡፡

እግዚአብሄር ለአባቱ ለንጉስ ናቡከደነፆር እንዴት ታላቅ ክብርን እንደሰጠው መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ናቡከደነፆር በምድር ላይ የነበረው ታላቅነት ሁሉ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ክብር ነበር፡፡

ንጉሥ ሆይ፥ ልዑል አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነፆር መንግሥትንና ታላቅነትን ክብርንና ግርማን ሰጠው። ስለ ሰጠው ታላቅነት ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር፤ የፈቀደውን ይገድል፥ የፈቀደውንም በሕይወት ያኖር ነበር፤ የፈቀደውንም ያነሣ፥ የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር። ትንቢተ ዳንኤል 5፡18-19

አባቱ ግን በራሱ እንዴት እንደተመካና የማይገባውን ነገር እንዳደረገ እግዚአብሄርን እንደናቀው ያስታውሰዋል፡፡

ልቡ ግን በታበየ በኵራትም ያደርግ ዘንድ መንፈሱ በጠነከረ ጊዜ፥ ከመንግሥቱ ዙፋን ተዋረደ፥ ክብሩም ተለየው። ትንቢተ ዳንኤል 5፡20

በዚህ ምክኒያት ያ አለም ሁሉ ይገዛለትና ያከብረው ንጉስ እንዴት ከንጉስነት ደረጃ ወርዶ ከሰው በታች እንደተዋረደና ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና እስሰጥ ድረስ እንደ እንስሳ ሳር እንደበላ ይናገረዋል፡፡

ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወድደውንም እንዲሾምበት እስኪያውቅ ድረስ ከሰው ልጆች ተይለቶ ተሰደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፥ መኖሪያውም ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ። ትንቢተ ዳንኤል 5፡21

ይህን ሁሉ የእግዚአብሄርን አሰራር ትእቢተኛን ማዋረዱን ያየው ልጁ ብልጣሶር ከዚያ እንዳልተማረ ፣ እግዚአብሄርን እንዳልፈራ እና እርሱም እንደታበየ ያስታውሰዋል፡፡

ብልጣሶር ሆይ፥ አንተ ልጁ ስትሆን ይህን ሁሉ እያወቅህ በሰማይ ጌታ ላይ ኰራህ እንጂ ልብህን አላዋረድህም። ትንቢተ ዳንኤል 5፡22

የመቅደሱንም ዕቃዎች በፊትህ አመጡ፥ አንተም መኳንንትህም ሚስቶችህም ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው ከብርና ከወርቅም ከናስና ከብረትም ከእንጨትና ከድንጋይም የተሠሩትን የማያዩትንም የማይሰሙትንም የማያውቁትንም አማልክት አመሰገንህ፤ ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም። ትንቢተ ዳንኤል 5፡23

መፅሃፍ ቅዱስ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው የሚለው ለዚህ ነው፡፡

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡7

ትንፋሹንና መንገዱን የያዘውን እግዚአብሄርን ከማያከብር ሰው በላይ ሞኝ የለም፡፡ እግዚአብሄር መኖርና አለመኖርህን ይወስናል፡፡ እግዚአብሄርን በምድር ላይ መንገድህን ይወስናል፡፡ መንገድህን በእጁ የያዘውን እግዚአብሄርን ከማክበር የበለጠ ጥበብ የለም፡፡

ትንፋሽህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ አላከበርኸውም ትንቢተ ዳንኤል 5፡23

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እጅግ በጣም አስተማማኝ ቦታ

your will.jpg

ሁሉም ሰው በህይወት እጅግ አስተማማኝ ቦታን ይፈልጋል፡፡ እጅግ አስተማማኝ ቦታ ደግሞ የልብ ሁኔታ እንጂ የተለየ ቦታ ፣ ከተማ ወይም አገር አይደለም፡፡ የልባችን ሁኔታ የቆምንበትን ቦታ አደገኛ ወይም አስተማማኝ ያደርገዋል፡፡ የልባችን ትእቢት ህይወታችንን አደጋ ላይ ሲጥለው የልባችን መዋረድና ትህትናችን ደግሞ የህይወታችንን ስኬታማነት አስተማማኝ ያደርገዋል፡፡

በህይወት ብዙ አደገኛ ቦታዎች ቢኖሩም እንደ ትእቢት እጅግ አደገኛ ቦታ የለም፡፡ በህይወት ብዙ አስተማማኝ ቦታአዎች ቢኖሩም እንደትህትና እጅግ በጣም አስተማማኝ ቦታ ግን የለም፡፡ ትእቢተኝነት ህይወታችንን አደጋ ላይ የሚጥል በእሳት እንደመጫወት አደገኛ ሁኔታ ነው፡፡ ራስን ማዋረድ ከማንኛውም ውድቀት የሚጠብቅ እጅግ አስተማማኝ ስፍራ ነው፡፡

ትህትና ስኬትን ሲቀድም ትእቢት ውድቀትን ይቀድማል፡፡

ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። መጽሐፈ ምሳሌ 16፡18

ትእቢት ለእግዚአብሄር ፣ ለራሳችንና ለሌሎች ሰዎች ያለንን አመለካከት ሲያዛባ ትህትና ግን ለእግዚአብሄር ፣ ለራሳችንና ለሌሎች ያለንን አመለካከት ያስተካክላል፡፡

ትእቢት በእኛ ላይ የእግዚአብሄርን ተቃውሞ ሲቀሰቅስ ትህትና የእግዚአብሄርን እርዳታ ያስገኝልናል፡፡ ትህትና አግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንዲወግን ሲያደርገው ትእቢት እግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንዲቃረነን ፣ የእኛ ተቃራኒ እንሆንና መንገዳችን ላይ እንዲቆም ያደርገዋል፡፡

ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። የያዕቆብ መልእክት 4፡6

ትህትናችን ለእግዚአብሄር ትክክለኛውን የአምላክነቱን ቦታ ሲሰጠው ትእቢታችን ግን የእግዚአብሄርን የአምላክነቱን እውቅና ይነፍገዋል፡፡

ትህትና የእግዚአብሄርንም አብሮነት ሲያመጣ ትእቢት የእግዚአብሄርን ቁጣ ይቀሰቅሳል፡፡ የልባችን ትህትና እግዚአብሄር ደስ ብሎት የሚያየውና የሚጎበኘው ሰው ሲያደርገን ትእቢት ደግሞ እግዚአብሄር ፊቱን እንዲመልስብን ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 66፡1-2

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በፍቅር ፍርሃት የለም

perfect love.jpg

ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18

ፍቅር ከእምነት ይመነጫል፡፡ ፍርሃት ደግሞ ከጥርጥር ይመነጫል፡፡

ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡

ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡7

ፍቅር እና ፍርሃት አብረው አይሄዱም፡፡ ፍቅር ካለ ፍርሃት ለቆ ይወጣል፡፡ ፍርሃት ካለ ደግሞ ፍቅር በሙላት የለም ማለት ነው፡፡ የፍርሃት መኖር የፍቅር መጉደል ትክክለኛ ማስረጃ ነው፡፡ ፍርሃት ካለ ፍቅር ሙሉ አይደለምና የፍቅር ችግር ሊፈተሽ ይገባዋል፡፡

ፍቅር ነፃነት ነው፡፡ ፍርሃት ባርነት ነው፡፡ ነፃነትና ባርነት አብረው እንደማይኖሩ ሁሉ ፍቅርና ፍርሃት አብረው ሊኖሩ አይችሉም፡፡

ፍርሃት ራሱን ይሰስታል፡፡ ፍቅር ራሱን ይሰጣል፡፡

በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ ጥርጥር አለባችሁ ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ እምነት ጎድሏችኋል ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ ስለዚያ ነገር እግዚአብሄርን አላመናችሁም ማለት ነው፡፡

በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ የሚመራችሁ ፍቅር ሳይሆን ፍርሃት ነው ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ ቅጣትን ትፈራላችሁ ማለት ነው፡፡

ፍቅር ብርሃን ነው፡፡ በፍቅር የሚያስፈራ ምንም ነገር የለም፡፡ ፍቅር ንፁህ ነው፡፡ ንፅህና ድፍረትን ይሰጣል እንጂ አያሳቅቅም አያስፈራም፡፡ ፍቅር ሙሉ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፍርሃት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

አውቆ ነው

a27c1849e768e16d7cfe74378f96e55d.jpg

በህይወት በሰዎች በደል አለመሰናከልን የመሰለ ታላቅ ችሎታ የለም፡፡ ተበድሎም ማለፍን የመሰለ ነፃነት የለም፡፡ ሰው የሚያቆስል ንግግር ሲናገርህ ሰምተህ እንዳልሰማህ ማለፍና ህይወትህን መቀጠል ሀብት ነው፡፡  የናቀህን መልሰህ ለመናቅ የሚፈትንህን ፈተና በትግስት ማለፍና የናቀህን አለመናቅን የመሰለ በረከት የለም፡፡

ይቅር አለማለት የአንዳንድ ሰዎችን እምቅ ጉልበት በመብላት ህይወታቸውን ሽባ አድርጓል፡፡ በደልን አለመተው የአንዳንድ ሰውን ሩጫ ገቷል፡፡ በደልን መቁጠር ብዙ ሰዎችን ጠላልፎ ከህይወት መንገድ ጥሏል፡፡

ይቅር አለማለት ጉልበትን ላልታለመለት አላማ በከንቱ ማባከን ነው፡፡

እግዚአብሄር ለእኛ ነው እግዚአብሔር በክፉ አይፈትነንም፡፡

እንዲያውም ከምንችለው በላይ እንድንፈተን አይፈቅድም፡፡ የበደለን ይቅር ማለት እንደምንችል ያውቃል፡፡ በህይወታችን ያለፈው ፈተና ሁሉ ያለፈው ፈተናውን ሁሉ ልናልፈው እንደምንችል እግዚአበሄር አውቆ ነው፡፡

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡13

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #የሚረዳንን #ፀሎት #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሚበድል ሰው ይታዘንለታል እንጂ አይቀናበትም

forgive-fight-anger-stubborn-1598x900.jpg

የሚበድል ሰው ያልገባው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የተሳሳተው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጎደለው እውቀት አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጠፋበት መንገድ አለ፡፡ የሚበድል ሰው የሚያደርገውን ነገር በሚገባ አያውቀውም፡፡

አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሉቃስ 23፡34

ስለዚህ የሚበድል ሰው የሚቀናበት ሰው አይደለም፡፡ የሚበድል ሰው ቢያንስ በበደለበት ነገር ሊከተሉት የሚገባ ጥሩ ሞዴል አይደለም፡፡ የሚበድል ሰው የሚፎካከሩት ጠንካራ ሰው አይደለም፡፡

የሚበድል ሰው የሚታዘንለት ሰው ነው፡፡ የሚበድል ሰው ድጋፍ የሚፈልግ የተቸገረ ሰው ነው፡፡ ሰው ካልቸገረውና መንገዱ ካልጠፋው በስተቀር ሰውን በመበደል መሳሳት አይፈልግም፡፡ የሚበድል ሰው ራሱን ማዋረድና ንስሃ መግባት የሚያስፈልጉት ብዙ ስራ የሚጠብቀው ሰው ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ እናንተ ሰውን ከምትበድሉ እናንተ ብትበደሉ ይሻላችኋል ብሎ የሚመክረው ስለዚህ ነው፡፡

እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፥7

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ይቅርታ #ምህረት #ፍርድ #ጠላት #ዲያቢሎስ #ስፍራ #ኢየሱስ #ጥላቻ #ትእቢት #መራርነት #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የጥላቻን ዜና በማስፋፋት ለጊዜው የሚጠቀሙ የተሸነፉ ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው

propaganda.jpg

ፖለቲካ የህዝብ አስተዳደር ስርአት ነው፡፡ ፖለቲካ በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሙያ በክፉ ሰዎች እንደሚበላሽ ሁሉ ግን ፖለቲካም በክፉ ሰዎች ሊበላሽ አላማውንም ሊስት ይችላል፡፡

ይህ ደግሞ በመንግስት አካላት ያሉትን ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆን በህዝብ መገናኛ ዘዴዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የራሳቸውን ትንተና የሚሰጡትንና አክቲቪስቶችን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

ፖለቲካ ወቅታዊውን የህዝብን ፍላጎት መረዳት መተንነተንና የተሻለ አማራጭን ማቅረብን ይጠይቃል፡፡ ፖለቲካ ህዝብን ወደ እረፍት ሰላም እና ብልፅግና የሚያደርስን የተሻለ ሃሳብን ማምጣት ይጠይቃል፡፡ እውነተኛ ፖለቲከኝነት ቀላል ስራ አይደለም፡፡ እውነተኛ ፖለቲከኝነት በጠለቀ እውቀት ፖሊሲ መቅረፅን በዚያ ዙሪያ ህዝብን ማንቃትና በአንድ አላማ ስር ማንቀሳስን ወደልማትና ብልፅግና መምራትን ይጠይቃል፡፡

ፖለቲከኛ ያለው ብቸኛ መሳሪያ የተሻለ ሃሳብ ነው፡፡ ፖለቲከኛ የተሻለ ሃሳብን ለማምጣት የሚተጋና በተሻለው ሃሳብ ዙሪያ ሰዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያስተምር የሚያነቃና የሚሰራ ነው፡፡

እውነተኛም የፖለቲካ ስልጣን የሚገኘው አንድን የተሻለ ሃሳብ ከተቀበለ ህዝብ ነው፡፡ የፖለቲካ ስልጣን ሃሳብ በህዝብ ተቀባይነት በማግኘት ብቻ ይመጣል፡፡ የፖለቲካ ስልጣን በረብሻ አይመጣም፡፡ የፖለቲካ ስልጣን ሰዎችን ለብጥብጥ በማነሳሳት አይመጣም፡፡ የፖለቲካ ስልጣን ጥላቻን በመንዛት አይመጣም፡፡

አገራችን ኢትዮጲያ በብዙ እውነተኛ ፖለቲከኞች የተሞላች አገር ነች፡፡ ህዝባቸውን የሚወዱና ለህዝባቸው የሚሰሩ ብዙ ፖለቲከኞችን አፍርታለች፡፡

ነገር ግን የፖለቲከኝነትን ስራውን የማይፈልጉ ነገር ግን በአቋራጭ የፖለቲካ ስልጣንን የሚፈልጉ ፖለቲከኞችም አንዳንዴ ይታያሉ፡፡ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሃሳብን ከማምጣት እና የህዝብን ልብ በተሻለ ሃሳብ ከማሸነፍ ይልቅ የሰውን አለማወቅ ተጠቅመው በውሸት ዜናዎች የራሳቸውን የግል አላማ ሊያሳኩ የሚጥሩ ፖለቲከኞችም አሉ፡፡

የአገሪቱን ሁኔታ በእውቀት በመረዳትና በመተንተን ሳይሆን የሰዎችን ችግር እየነካኩ በዚያም የፖለቲካ ነጥብ ሊያስመዘግቡ የሚፈልጉ ስነምግባር የጎደላቸው ፖለቲከኞች ከመንግስትም ከመገናኛ ብዙሃንም እንዲሁም ከአክትቪስቶችም አልጠፉም፡፡

የተሻለ ሃሳብ በማቅርብ በሃሳብ ውድድር ለማሸነፍ አቅቷቸው ጥላቻን በመዝራት የሰውን ስሜት የሚቀሰቅሱና በህዝቦች መካከል ጥርጣሬና አለመተማመን የሚፈጥሩ ይገኙበታል፡፡ የፖለቲካ እውቀታቸውን ለማሳደግ እና ለማስፋት በማንበብና በመመርመር ፋንታ ጊዜያቸውን ሁሉ ረብሻ ሊያስነሳ የሚችልን ወቅታዊ ወሬን የሚፈላለጉ የፖለቲካ ስነምግባር የጎደላቸው ይታያሉ፡፡

በተሻለ ሃሳብ የማሸነፍ አቅም ሲያጥራቸው ህብረተሰቡን ስጋቱን በማባባስ በችግረኛው ህብረተሰብ ላይ ተረማመደው የተሻለ ጥቅም ለማግኘት የሚፈልጉ የፖለቲካ ስነምግባር የማይገዳቸውንም ተመልክተናል፡፡

በተሻለ ሃሳብ ህዝቦችን ከማቀራረብና ለአንድ አገር ሰላም ልማትና አንድነት ከመስራት ይልቅ አገር በህዝቦች አለመተማመን ብትታመስ ምንም ደንታ የማይሰጣቸው የተሸነፉ ፖለቲከኞችም ይታዩባታል፡፡ የሚናገሩት የስድብ እና የንቀት ንግግር በህዝቦች መካከል ለሚያመጣው መቃቃር ግድ የሌላቸው ለጊዜያዊ ታዋቂነታቸው ብቻ የሚያስቡ ፖለቲከኞች አሉ፡፡ ህዝቡ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ድንጋርይ መወራወሩት ትቶ ድህነትን በመዋጋት ወደልማትና ብልፅግና የሚሄድበትን መንገድ ለመፈለግ የሚያስችልን ከፍ ያለን ሃሳብ ማምጣት የማይችሉ ሰዎችን በማናቆር ብቻ ፖለቲከኞች እንደሆኑ የሚሰማቸው ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ እርስ በእርሱ መፎካሩንና መወዳደሩን ትቶ ለአገር እንዲሰራ የሚያሳሙበት ሃሳብ ስለሚያጥራቸው በወቅታዊ ችግሮች ላይ ተጠምደው ጊዜያዊ ጥቅምን ያሳድዳሉ፡፡

ከራሳቸው ጥቅም በላይ የአገር እና የህዝብን ጥቅም የሚያስቀድሙ ፖለቲከኞች እንዳሉ መጠን ፖለቲካ እንደ ማንኛውም ሙያ ትምህርትና እውቀት የማይፈልግ የሚመስላቸው ይገኛሉ፡፡ እንወክለዋለን ከሚሉት ህዝብ ውጪ ላለውን ለሌላው ህዝብ የፍቅርና የርህራሄ ልብ የሌላቸው ከእነርሱ የተለየውን ህዝብ ሲሰድቡ እና የንቀትን ንግግር ሲናገሩ የሚውሉ ፖለቲከኞች ይገኛሉ፡፡

በህዝቦች መካከል መቀራረብን መደራደርን የማይፈልጉ እና የማያበረታቱ የራሴ መንገድ ብቻ የሚሉ ፖለቲከኞች ያላቸው አንድ መሳሪያ ጥላቻን ማስፋፋት እና በህዝቦች መቃቃርና መናቆር በጊዜያዊነት ተጠቃሚ መሆን ብቻ ነው፡፡ በግልፅ በአደባባይ ሊሉት የማይፈልጉትን በማህበራዊ ሚዲያዎች ጀርባ እየተደበቁ ጥላቻን የሚያስፋፉ ስርአት አልበኛ ሰዎች አልታጡም፡፡

ለጊዜው የተሳካላቸው ይመስላችው ይሆናል እንጂ ሃሰተኛ ፖለቲከኞች መጋለጣቸው አይቀርም፡፡ ህዝብን የሚያቀራረብ ፍትሃዊ የሆነ የተሻለ ሃሳብን ማቅረብ እንጂ ጥላቻን በማስፋፋት የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም ማንም ሰው አይኖርም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መንፈስ #ማንነት #መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ክብር #ብሔር #ቋንቋ #ወገን #ነገድ #አፍሪካ #ኢትዮጲያ #ነገድ #ቤተሰብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ዘረኝነት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ዘውግ

ዘረኝነት ዘር የለውም

110920181747571319853.png

ዘረኝነት እጅግ ሊኮንን የሚገባ አፀያፊ አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ ዘረኝነት የሚለውን ቃል ብዙ ሰዎች ለብዙ ነገር ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ዘረኝነት በትክክል ተርጉመው ከሁኔታው ጋር አያየዝው ጥሩ የሆነ እውቀት ለሌሎች ሲያካፍሉ ይታያሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ዘረኝነት የሚለውን ቃል የሚጠቀሙበትን መንገድ ስንመለከት በእውነት ሃሳቡን ተረድተውታል ወይ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ዘረኝነት የሚለውን ቃል በትክክል ባለመረዳት በተለያየ ንግግራቸው እና ፅሁፋቸው ውስጥ ሲጠቀሙት እና ሰዎችን ከማስተማርና ከማንቃት ይልቅ ሲያደናግሩ እናያለን፡፡ ዘረፅነት የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ቃሉ ታዋቂ ስለሆነ ብቻ እንጂ ምን ማለት እንደሆነ ተረድተውት እንዳይደለ አነጋገራቸው በግልፅ ያሳያል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የዘረኝነትን ቃሉን የሚጠቀሙት በቅጡ ተረድተውት ሳይሆን የራሳቸውን ሃሳብ ብቻ ለማስፈፀም ሲሉ ብቻ ነው፡፡

ዘረኝነት ብለው በብዛት የሚጮሁ አንዳንድ ሰዎች ዘረኛ ነው ብለው ከሚኮንኑት ወገን ይልቅ እነርሱ ራሳቸው ዘረኛ ሆነው ይገኛሉ፡፡

ሁላችንም እኩል ተደርገን ተፈጥረን ሳለ ዘረኝነት የሌላውን ዘር የመናቅ ፣ የመግፋትና የማንኳሰስ ክፉ በሽታ ነው፡፡ ከእኔ ዘር ያንሳል ብለህ የምታስብው ምንም ዘር ካለ ዘረኛ ለመፈለግ ሌላ ቦታ መሄድ አይጠበቅብህም አንተው ዘረኛ ነህ፡፡

ዘረኝነት በምንም መልኩ ሊበረታታ የማይገባው ክፉ ነው፡፡

ዘረኝነትን በሚገባ ካልተረዳነው መወገዝ የማይገባውን እያወገዝን መበረታታት የማይገባውን እያበረታታን የመፍትሄው አካል መሆን ሲገባን የችግሩ አካል ሆነን በከንቱ ጊዜያችንን እናባክናለን፡፡

ዘረኝነት ከበታችነት ስሜት ይመጣል፡፡

በራሱ መተማመን የሌለው ሰው የሰው ወይም የአንድ ወገን በራስ መተማን ያሰጋዋል፡፡ ዘረኝነት ከበታችነት ስሜት የተነሳ የበላይነት ስሜትን በማሳየት ይንፀባረቃል፡፡ ዘረኝነት ከተቻለ በሃይል ካልተቻለ ደግሞ በንግግር ሌላውን ወገን ዝቅ ዝቅ ማድረግና ራስን ከፍ በማድረግ ሌላውን ማጥቃት ነው፡፡ ዘረኛ የሆነ ሰው የራሱ ዘር ስኬት የሚደገፈው በሌላው ዘር ውድቀት ላይ ይመስለዋል፡፡ የአንተ ዘር እንዲሳካለት ሌላው ዘር መውደቅ የለበትም፡፡ ስግብግብነትና ንፉግነት ካልሆነ በስተቀር ለሁሉም ዘር የሚበቃ ስኬት አለ፡፡

ሰው ክቡር ነው፡፡ ሰው ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙ ዘር በሚኖርባት አገር ውስጥ እየኖርክ የምትቀበለው ያንተን ዘር ብቻ ከሆነ አንተ ራስህ ዘረኛ ነህ፡፡ ከአንተ የተለየ ዘር በራሱ ቋንቋ መናገር የሚያሳስብህ ከሆነ አንተው ዘረኛ ነህ፡፡

ሰውን እንደ ሀብት ሳይሆን እንደ እዳ ካየኸው መለወጥ ያለብህ የራስህን የሽንፈት አስተሳሰብህን ነው፡፡ በተለይ ከአንተ የተለየን ሰው እንደ ውበት ካላየኸው በስተቀር እያነስክ ትሄዳለህ እንጂ አትሰፋም፡፡

ኢትዮጲያ ውስጥ አንድ ዘርና እንድ ቋንቋ ብቻ ካልኖረ በስተቀር ሰላም አይኖርም ብለህ የምታስብ ከሆንክ ዘረኛው አንተው ነህ፡፡ የኢትዮጲያ ችግር የመጣው ብሄሮች በራሳቸው ቋንቋ መጠቀም ሲጀምሩ ነው ብለህ ካሰብክ ዘረኛው አንተው እንጂ በቋንቋቸው የሚማሩና ብሄሮች አይደሉም፡፡ ኢትዮጲያ ባለአንድ ቋንቋ ስትሆን ብቻ ነው ሰላም የሚመጣው ብለህ የምታስብ ከሆንክ ልብህ በዘረኝነት ክፉ በሽታ አለመያዙን መርምር፡፡ እያንዳንዱ ዘር ቋንቋውን አክብሮ ለኢትዮጲያ አንድነትና ብልፅግና መስራት አይችልም ብለህ ካመንክ ሃሳብህን መለወጥ ያለብህ አንተ ነህ፡፡

አንተ በሚመችህ  ቋንቋ እየተናገርህ ሌላው በቋንቋው ስለተናገረ ዘረኛ የሆነ ከመሰለህ ራስህን መርምር፡፡

የሌላው ብሄር ሰው ሲሰደድና ሲገፋ ምንም ካልመሰለህ ያንተ ብሄር ሲገፋና ሲሰደድ ብቻ ስለዘረኝነት አስከፊነት የምታነሳ ከሆንክ አንተ ራስህ በዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ አለመግባትህን አረጋገጥ፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን። እነሆ፥ ይህን አላወቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን? መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10-12

ዘረኝነት ዘር የለውም፡፡ ዘረኝነት የሁላችንም ፈተና ነው፡፡ ዘረኝነት ዘራችንን በመውደድና የሌላውን ዘር በመጥላት መካከል ያለ ሚዛናዊነትን ያለመጠበቅ ችግር ነው፡፡ ዘረኝነት ዘራችንን በማክበርና ሌላውን ዘር በመናቅ መካከል ያለ ሚዛናዊነትን አለመጠበቅ ችግር ነው፡፡ ዘረኛ ሰው ለአንተ ወይም ለዘርህ ያለው የንቀት አስተያየት አንተም መልሰህ የእርሱን ዘር እንድትንቅ ይፈትንሃል፡፡

ዘረኝነት በሌላ በዘረኝነት አይስተካከልም፡፡ በዘረኛ ሰው ንግግርና አካሄድ ተነሳስተህ አንተም ወደ ዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ እንዳተወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ዘረኝነት ወደ አንተም ህይወት እንዳይስፋፋ በአጭሩ የምትቀጨው ዘረኛን ዘረኛ የሚያደርገው የበታችነት ስሜት እንደሆነ አውቀህ ስታዝንለትና ስትራራለት ብቻ ነው፡፡ ዘረኛነት እንዳይስፋፋ የምታደርገው በሌሎች ዘረኝነት ንግግርና ድርጊት ተሸንፈህ አንተም በዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ ላለመውደቅ ስታመልጥ ነው፡፡

ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡21

ከዘረኛ ሰው ጋር ፉክክር ውስጥ መግባት የዘረኞችን ቁጥር ያሳድጋል እንጂ ዘረኝነትን ለመዋጋት መፍትሄ አይሆንም፡፡

ዘር በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከቤተሰብ ጀምሮ በየደረጃው በዘመድ በጎሳ በብሄር በሃገር አብሮና ተረዳድቶ በወገንተኝነት ስሜት እንዲኖር አድርጎ ነው፡፡ ማንም ሰው ስለተወለደበት ቤተሰብ ጎሳ እና ዘር መሳቀቅና መጸጸት የለበትም፡፡

ከሌሎች ሰዎች ሁሉ ይልቅ ለምን ቤተሰብህን ወደድክ የሚል ሰው እንደሌለ ሁሉ ማንም ዘርህን ለምን ወደድክና አከበርክ የሚል መኖር የለበትም፡፡ ለቤተሰብህ ማደግ ለምን ትተጋለህ የሚልህ እንደሌለ ሁሉ ለዘርህ ማደግ ለምን ትተጋለህ የሚል ሰው አይኖርም፡፡ ቤተሰብህን ስትወድና ስታከብር ዘርህ ይከብራል ያድጋል፡፡ ዘርህ ሲከብርና ሲያድግ አገር ትከብራለች ታደጋለች፡፡ ምድር ለሁላችን የሚበቃ በቂ ምንጭ አላት፡፡ እኔ ዘሬን ለመጥቀም የሌላውን ዘር መጉዳት የለብኝም፡፡ እኔ አገሪቱን ለመጥቀም ዘሬን መጉዳት የለብኝም፡፡ ሁላችንም ከቤተሰባችን ጀምረን እስከ ዘራችንና ብንሰራ አገር ታድጋለች፡፡

ዘረኝነት ዘርን መውደድ ሳይሆን ሌላውን ዘር መጥላት ነው፡፡ ዘረኝነት የራስን ዘር ማክበር ሳይሆን የሌላውን ዘር መናቅ ነው፡፡ ዘረኝነት የራስን ዘር መርዳት ሳይሆን የሌላውን ዘር መጉዳት ነው፡፡ ሌላውን ዘር እንድትጠላና እንድትንቅ የሚያደርግህ ማንኛውም ንግግር በዘረኝነት መርዙ እየመረዘህ እንደሆነ አውቀህ ሽሽ፡፡ ዘረኛ የዘረኝነቱን ንቀትና ጥላቻ ማስተላለፊያ ሊያደርግህ ሲሞክር ዘረኝነቱን ባለመከተልና ባለማስፋፋት ብለጠው፡፡

ከዘረኝነት ነፃ የወጣ ሰው ከራሱ ዘር አልፎ ሌሎችን ዘሮች በማክበርና በመውደድ ይታወቃል፡፡ ዘረኝነት የሌለበት ሰው እያንዳንዱ ዘር እኩልና እኩል እድል ሊሰጠው እንደሚገባ ያምናል፡፡ ከዘረኝነት ነፃ የሆነ ሰው ጭቆናና በደል ሲደርስ ለራሱ ዘር ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዘሮች ጥብቅና ሲቆም ይታያል፡፡ አንዱ ዘር ለሌላው ዘር ሲከራከር የምንሰማው ከዘረኝነት ነፃ በሆነ ህብረተሰብ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መንፈስ #ማንነት #መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ክብር #ብሔር #ቋንቋ #ወገን #ነገድ #አፍሪካ #ኢትዮጲያ #ነገድ #ቤተሰብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ዘረኝነት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ዘውግ

ፀሎትን ፍሬያማ የሚያደርገው  

orange-tree.jpg

ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ለቅሶዋችን አይደለም፡፡ እውነት ነው ስንፀልይ አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ እንሆንና እናለቅሳለን፡፡ ነገር ግን የፀሎት ውጤት ከለቅሶ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡

ፀሎታችንን ውጤታማ የሚያደርገው መርዘሙ አይደለም፡፡ እውነት ነው አንዳንድ ጊዜ ፀሎታችን ይረዝማል፡፡ አንዳድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ከጌታ ጋር እንነጋገራለን፡፡ ፀሎታችን መርዘሙ ብዙ የፀሎት ርእሶችን ለመፀለይ ካልሆነ በስተቀር ፀሎታችን እንዲሰማ ወይም ፀሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን የሚጠቅመው ጥቅም የለም፡፡

ፀሎታችንን ውጤታማ የሚያደርገው ነገርን መደጋገማችንም አይደለም፡፡ ተመሳሳይን ነገር በደጋገምነው መጠን ፀሎታችን ይሰማል ብለን ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ እውነት ነው ፀሎትን ስንፀልይ ልባችን እስኪያርፍ ድረስና ሸክማችን እንከሚቀል ድረስ መፀለይ አለብን፡፡ ነገር ግን የፀሎት ርእሳችንን በደጋገምነው መጠን ፀሎታችን ይሰማል ብለን ማመን የለብንም፡፡

ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ስንፀልይ በምናሳየው ሃይል አይደለም፡፡ ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው በድምፃችን ከፍታ መጠን ወይም በጣም በመወራጨታችን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የልብን ጩኸት ይሰማል፡፡

ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ስንናገረው ስላጣፈጥነው አይደልም፡፡ ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው አንደበተ ርቱእ መሆናችን አይደለም፡፡

ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው እንደ ፈቃዱ መፀለያችን ነው፡፡ እንደ ፈቃዱ ከፀለይን እግዚአብሄር ይሰማናል፡፡ እንደ ፈቃዱ ካልፀለይን እግዚአብሄር አይሰማንም፡፡

የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናገኘው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ከፀለይን እግዚአብሄር ይሰማናል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ካልፀለይን እግዚአብሄር አይሰማንም፡፡

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

 

ታቦቱን መከተል

 

the-ark-of-the-covenant--alien-device-or-divine-artifact-139001.jpgሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ክብር እግዚአብሄርን ለማክበር ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው የፈለገውን ነገር እንዲያደርግ ሳይሆን እግዚአብሄርን እንዲከተል ነው፡፡ ሰው የሚሳካለት እግዚአብሄርን በቅርበት ሲከተል ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የማይከተል ሰው በነገሮች ሊሳካለት ይችላል በእግዚአብሄር ዘንድ ግን አይሳካለትም፡፡

ስለእኛ ከሃጢያት መዳን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ የምናምን ሁላችን የእግዚአብሄር መንፈስ በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡

የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ሲወጣ የእግዚአብሄርን ታቦት ይከተል ነበር፡፡ ታቦቱ ሲቆም ይቆም ነበር ታቦቱ ሲሄድ ደግሞ ይሄድ ነበር፡፡

ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 3፡3

እንዲሳካልን ሌላ ማንንም ሰው መከተል የለብንም፡፡ እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን የተለየ የስኬት አላማ አለው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11

በብሉይ ኪዳን እስራኤላዊያን ታቦቱን እንደሚከተሉ ሁሉ አሁንም እኛ በውስጥታችን ያለውን የእግዚአብሄርን መንፈስ በመከተል  ይሳካልናል፡፡

በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡14፣16

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡20፣27

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #አማላጅ #ታቦት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ኦርቶዶክስ #ማርያም #ቅዱሳን #ተዋህዶ

የማንቂያ ደውል

seen by men

እግዚአብሄርን ለሚወዱ ሰዎች ነገር ሁሉ ለበጎ ይደረጋል፡፡

ለምሳሌ እግዚአብሄርን ስንፈልግ ሰው ቢበድለን በደሉ እኛን የሚጥለን ሳይሆን የሚያነቃን ደውላችን ነው፡፡

ሰው ሲበድለን ስለበደለን ሰው እንድናውቅ እና እንድንረዳ የማንቂያ ደውል ነው፡፡

ሰው ሲበድለን ስለበደለን ሰው እንድናዝን እንድንራራ የማንቂያ ደውል ነው፡፡

ባይበድለን እንድንፀልይለት ትዝ የማይለን ሰው ቢበድለን ስለበደለን ሰው እንድንፀልይና እንድንማልድ የማንቂያ ደውል ነው፡፡

ባይረግመን ጊዜ ወስደን የማንባርከው ሰው ቢረግመን  እንድንባርከው ስለእርሱ መልካም እንድድናስብ መልካም እንድንናገርና መልካም እንድናደርግ የማንቂያ ደውል ነው፡፡

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ የማቴዎስ ወንጌል 5፡44

ሰዎች ሲበድሉን የእግዚአብሄርን መልካምነትና ልበ ሰፊነት ስንቱን እንደቻለ እንድናስብ የሚያደርግ የማንቂያ ደውል ነው፡፡

እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የማቴዎስ ወንጌል 5፡45

ሰዎች ሲበድሉን ያሉበትን የህይወት ሁኔታ ችግር ላይ መሆናቸውን ማወቅና አንድ ነገር ማድረግ አለብን፡፡ ሰዎች ሲበድሉን የእኛን ፀሎትና በረከት እንደሚያስፈልጋቸው የማንቂያ ደውሉን መስማትና መረዳት አለብን፡፡ የበደሉንን ሰዎች መልሰን ለመበደል ስንፈተን ይልቁንም በደሉን መልካም ለማድረግ እንደማንቂያ ደውል ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡9

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #መልካም #ክፉ #አሸንፍ #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ #ምስክርነት

ከፀሎት ወደ ምስጋና ካላደረስክ እምነትህ ለውጤት አልደረሰም

gogun-incileri-deneme-salih-akin-entel-manifesto-2100x1200.png

በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ለተፈጠረ ሰው እምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር በተፈጥሮአዊ አይን ስለማይታይ ከእግዚአብሄር ጋር የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የሚደረጉት በእምነት ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮአዊ አይን ማየት የማይታየውንና የማይያዘውን ነገር ማየትና መያዝ ነው፡፡

ከለእምነት ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ነገር ማድርግ አይቻለም፡፡ ካለእምንት አግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ ወደ ዕብራውያን 11፡6

ሰው ከእግዚአብሄር እንዲደረግለት በሚፈልገው ነገር ከፀሎት ወደማመስገን ካልተሸጋገረ አላመነም ማለት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር የሚፈልገው ነገር እንደተደረገለት ማመን አለበት፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር የሚፈልገው ነገር እንደተሰራለት ማወቅ አለበት፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር የሚጠይቀው ነገር እንደተሰጠው መቁጠር አለበት፡፡

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡24

የእምነት አባታችን አብርሃም የተስፋ ቃሉን ያገኘው አምኖ ማመስገን ሲጀምር ብቻ ነው፡፡

ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡20-21

ወደማመስገን ያልደረስንበት ነገር አላመንም ማለት ነው፡፡ እንዳመንን የሚመሰክረው ወሳኙ ነገር ማመስገንና ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት መጀመራችን ነው፡፡ ከእግዚአብሄር እንዲደረግልን የፈለግነው ነገር እንዳገኘነው ደስ ደስ ካላለን አላመንንም ማለት ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ምስጋና #ክብር #ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ስድብን በስድብ

dur-brain-insult-abuse-small1.jpg

ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። የማቴዎስ ወንጌል 15፥19

አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፥8

ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፥9

ስድብ ከስጋ የሃጢያት ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ስድብ በንግግር ሌላውን ዝቅ ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ስድብ በንቀት ንግግር መናገር ነው፡፡ ስድብ ራስን ከፍ ማድረግና ሌላውን ማዋረድ ነው፡፡ ስድብ ሌላውን በማሳነስ የራስን የራስ ወዳድንት ሃሳብ ለማስፈፀም መሞከር ነው፡፡ ስድብ ሌላውን በማጣጣል የራስን ምሰል መገንባት ነው፡፡

ስድብ ከጥላቻ የሚመነጭ የምድር ፥ የሥጋና የአጋንንትም ጥበብ ነው፡፡

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። የያዕቆብ መልእክት 3፡13-16

ስድብ ሰው ሌላውን በሃሳብ ብልጫ ለማሸነፍ እንደማይችል ተስፋ የቆረጠ የተሸነፈ ሰው ስልት ነው፡፡ ስድብን የሰነፍ መሳሪያ ነው፡፡ ስድብ በአቋራጭ አላማን  የማስፈፀሚያ መንገድ ነው፡፡

የሚሳደብ ሰው የሚያሳዝን ሰው ነው፡፡ የሚሳደብ ሰው በጥላቻ እስራት ውስጥ ስላለ ሊታዘንለት የሚገባ ሰው ነው፡፡ የሚሳደብ ሰው ርህራሄ ሊደረግለት የሚገባ ግራ የገባው ሰው ነው፡፡ የሚሳደብ ሰው የበታችነት ስሜቱን በበላይነት ስሜት ሊያካክስ የሚፈልግ ምስኪን ሰው ነው፡፡ የሚሳደብ ስው እውነተኛ የሚለውጥ እና የሚሰራ ሃይልና አቅም ያጠረው ሰው ነው፡፡

በሚሳደብ ሰው ለንቀና አይገባም፡፡ ከሚሳደብ ሰው ጋር በስድብ ፉክክር ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ ለተሳዳቢው ማዘንና መራራት እንጂ ሰው የሚሰድበውን ሰው መልሶ ከሰደበ ወደሚሳደበው ሰው ደረጃ ይወርዳል፡፡ የሚሳድብ ሰው ካየን እንድንራራለት እና እንድንፀልይለት እግዚአብሄር እያስታወስን ማለት ነው፡፡ ሰው ሲሳደብ ሁኔታውን በሚገባ መያዝ እንዳቃተው እና ግራ እንደገባው ተረድተን ልናዝንለት ይገባል፡፡ ሰው ሲሳደብ ልንታገሰው መልሰን በመሳደብ ተሳዳቢው ያለው እስራት ውስጥ ላለመግባት ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፥9

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ባርኩ #ክፉ #መልካም #በረከት #ልትወርሱ #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንደበት #ከንፈር #ስድብ

የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ

evil heart.jpg

እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። ኦሪት ዘፍጥረት 6፡5

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልካም ልብና ለመልካም ልብ ነበር፡፡ ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን ያንኑ ነገር ካደረገ በኋላ ሰው ከእግዚአብሄር ክብር ወደቀ፡፡ የሰው ልቡ ተበላሸ፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረው ሰው የተፈጠረበትን አላማ ስቷል፡፡

የሰው ልብ ከእግዚአብሄር መንገድ እንደወጣና ሰው ክፉ ልብ እንዳለው የሚያሳየው ነገር ምንድነው ብለን መጠየቅ ጥበብ ነው፡፡ የሰውን ልብ ክፉ የሚያደርግውን ነገር ወይም የክፉ ልብ ምልክቶችን ከእግዚአብሄር ቃል እንመልከት፡-

 1. የሰውን ልብ ክፉ እንደሆነ የሚያሳየው ራስ ወዳድ በመሆኑ ነው

የሰው ልብ ከእግዚአብሄር ሲርቅ ራስ ወዳድ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ነገር ከራሱ ጥቅም አንፃር እንጂ ከሌላው ጥቅም አንፃር መመልከት አይችልም፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ለራሱ ሙሉውን ድርሻ ወስዶ ሌላውን ባዶውን ሲልክ አይሰማውም፡፡

ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው። የሉቃስ ወንጌል 6፡31

 1. የሰውን ልብ ክፉ እንደሆነ የሚያሳየው በአድልዎ መፍረዱ ነው

የሰው ልብ ክፉ እንደሆነ የሚያሳየው ፍርዱ በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ነገር ግን በስሜቱ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ ክፉ ሰው በተመሳሳይ ጉዳይ ለአንዱ የሚፈርደው ፍርድና ለሌላው የሚፈርደው ፍርድ ይለያያል፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው የሚፈረርደው ፊትን አይቶ ነው፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ወጥ የሆነ በመርህ ላይ የተመሰረተ ፍርድ የለውም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ተመሳሳይ ጥፋት ላጠፉ ሁለት ሰዎች ያለው ምዘና የተለያየ ነው፡፡ ፍርዱ የሚወሰነው በሰዎቹ ላይ እንጂ በመርህ ላይ አይደለም፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ሰዎቹን ሳያይ በመርህ ብቻ መፍረድ አይችልም፡፡ አንዱ ሲሰራው ትክክል ነው የሚለውን ነገር ሌላው ሲሰራው ስህተት ነው ይለዋል፡፡

 1. የሰው ልብ ክፉ እንደሆነ የሚያሳየው ለሌላው ባለው ንቀት ነው

ሌላውን የሚንቅ እና ዝቅ ዝቅ አድርጎ የሚመለከት ሰው ክፉ ልብ ያለው ሰው ነው፡፡ ሌላው ሰው ሁሉ የእርሱ ታናሽ እርሱ ብቻ ታላቅ እንደሆነ በትእቢት የሚያስብ ሰው ልቡ ክፉ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የሌላውን ችግርና መከራ እንደራሱ አድርጎ የማያይ እና የሰው መከራና ችግር የማይሰማው ሰው ክፉ ልብ ያለው ሰው ነው፡፡ ራሱን በሌሎች ቦታ የማስቀምጥ እኔ ብሆን ኖሮ ምን እሆን ነበር ብሎ የሌሎችን መጎዳት ለማየት የማይፈልግ ሰው ክፉ ልብ ያለው ሰው ነው፡፡ አላግባብ ከተጠቃ ሰው ጋር ራሱን ለማስተባበር የሚፀየፍ እና የትህትናን ነገር ለማደርግ የማይፈልግ ሰው ክፉ ልብ ያለው ሰው ነው፡፡

እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡16

 1. የሰውን ልብ ክፉ እንደሆነ የሚያሳየው ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን በሃብቱ በዝናውና በሃይሉ ሲያከብር ነው

ክፉ ልብ ያለው ሰው አክብሮቱ በሰው ሃብትና ዝና ላይ ይመሰረታል፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ሰውን የሚያከብረው ሃብቱን አይቶ በእበላ ባይነት ነው፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ዝነኛን ሰው የሚያከበርው ሃያል ስለሆነ ክፉ ሊያደርግብኝ ይችላል በሚል ፍርሃት እንጂ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ስለተፈጠረ ስለ ሰውነቱ ብቻ አይደለም፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ሰውን በሰውነቱ ስለማያከብር ድሃን ይንቃል ደካማው ላይ ይበረታል፡፡

የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ፦ አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም፦ አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን? የያዕቆብ መልእክት 2፡2-4

 1. ክፉ ልብ ያለው ሰው ወገንተኛ ነው

ክፉ ልብ ያለው ሰው የሚያዳላው ለራሱ ወይም ለእኔ ስለሚለው ሰው ነው፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው የእኔ ወገኔ  ነው ስለማይለው ሰው ምንም ግድ የለውም፡፡ ክፉ ልብ ያለው ሰው ሌላው ሲጎዳ ሲያይ አይቶ እንዳላየ ያልፋል እንጂ ለሌላው ወገን አይናገርም አይከራከርም፡፡

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #የሚፈርድ #የሚያማ #ወንጌል #መውደድ #ፍቅር #የህይወትምስክርነት #መታዘዝ #ማገልገል #መውደድ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ፍራ

pit.jpg

ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ። ወደ ሮሜ ሰዎች 11፥20

በህይወት የወደቁ ሰዎች ሁሉ ከመውደቃቸው በፊት እኔ አልወድቅም ብለው አስበው ነበር፡፡ በህይወት የወደቁ ሰዎች ሁሉ ከመውደቃቸው በፊት በኩራት አስበው ነበር፡፡ በህይወት የወደቁ ሰዎች ሁሉ ከመውደቃቸው በፊት ይህ ውድቀት በእኔ ላይ አይደርስም ብለው በኩራት አስበው ነበር፡፡ ከመውደቃቸው በፊት ይህን እንዳሰቡ ማረጋገጫው ላለመውደቅ አለመፍራታቸውና ብሎም በመጨረሻም መውደቃቸው ነው፡፡

ሰው መፍራቱን ሲተውና ሃሳቡን በእርጋታ ከመቆጣጠር ይልቅ ሃሳቡን እንደፈለገ ሲለቀው ለውድቀት ይጋለጣል፡፡ ሰው ከመጠን በላይ ሲዝናናና ሃሳቡን መቆጣጠር ሲያቅተው ይስታል፡፡

እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡3

ከሰው ውስጥ ፍርሃት ከጠፋና ሰው በትእቢት ካሰበ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው እንጂ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡

ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። መጽሐፈ ምሳሌ 16፡18

እንዳይወድቁ መፍራትና ራስን በትህትና ማዋረድ መልካም ነገር ነው፡፡ ሰው ራሱን ማዋረድ ካልቻለ ሁኔታዎች ያዋርዱታል፡፡ ሰው ክቡር ነው፡፡ ሰውን ሌላ ሰው ሲያዋርደው መልካም አይደለም፡፡ ሰውን ሁኔታ ሲያዋርደው መልካም አይደለም፡፡ የተሻለው ነገር ሰው እንዳይወድቅ መፍራቱና ራሱን ማዋረዱ ነው፡፡

ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። መጽሐፈ ምሳሌ 22፡3

ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ። ወደ ሮሜ ሰዎች 11፥20

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ትእቢት #ኩራት #እግዚአብሄር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትህትና #ራስንማዋረድ #ፅናት #ትግስት #መሪ

እግዚአብሔርም ቤት ይፈልጋል !

35348763_2028309147497855_7640228919542546432_n.jpg

ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። የዮሐንስ ወንጌል 14፡23

ሰው በተፈጥሮው ቤቴ የሚለው ማረፊያ ቦታ ይፈልጋል፡፡ ሰው ከዚያ እየተነሳ የሚሰራበት የሚማርበት የሚንቀሳቀስበት መነሻ ቤት ይፈልጋል፡፡ ሰው ሰዎች ሌሎች ሰዎች ሲፈልጉት የሚገኝበት እንግዳውን የሚቀበልበት የሚያስተናግድበት ቤት ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለእርሱ ማረፊያ መኖሪያ ቤት እንዲሆን ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው የሚናከትረብት መድረክ እንዲሆንለት ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው መልካምነቱን የሚያሳይበት ቦታ እንዲሆንለት ነው፡፡

እግዚአብሄር ሰው በሰራው ቦታ ውስጥ አይኖርንም፡፡ እግዚአብሄር ደስ ብሎት የሚያርፈው እና የሚኖረው ራሱ በሰራውና በፈጠረው ሰው ውስጥ ነው፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 66፡1-2

ሰው በተፈጥሮው ንፁህ ቤት ውስጥ መኖር እንደሚፈልግ ሁሉ እግዚአብሄርም የሚኖርበት ንፁህ ቤት ንፁህ ህይወት እንዲሆንለት ይፈልጋል፡፡

ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20

መፅሃፍ ቅዱስ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ሆናችሁ ተሰሩ በማለት ያዘናል፡፡

እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡5

ባደግን ፣ በሰፋንና በነፃን መጠን ለእግዚአብሄር ይበልጥ የሚመች መኖሪያና ማገልገያ ቤት ሆን እንሰራለን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #የእግዚአብሔርቤት #በቃሉመንቀጥቀጥ #ማረፊያ #መኖሪያ #የተሰበረልብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ማደሪያ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  #የዋህነት #ንፁህ