Category Archives: glory

ብታምኚስ

1 (4).jpg

ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው። ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። የዮሐንስ ወንጌል 11፡39-40

የእግዚአብሄርን ክብር ማየት የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት መመዘኛ አለው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር በህይወታችን ለመለማመድ መመዘኛው ደግሞ ሊደረስበት የማይችል ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት የሚጠይቀው እምነት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለማስደሰትና የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ የለውም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ ቢኖር ኖሮ ያንን መንገድ እንከተል ነበር፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ የለውም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ብቸኛው መንገድ እምነት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ለማርታ አልነገርሁሽምን? የሚላት በፊትም የእግዚአብሄርን ክብር የምታይው ስታምኚ እንደሆነ ነግሬሻለሁ ዛሬም አልተለወጠም የእግዚአብሄን ክብር ማየት ከፈለግሽ ማመን ወሳኝ ነው እያላት ነው፡፡

የእግዚአብሄን ክብር እንድናይ የሚያስችለን እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17

የእግዚአብሄር ክብር ከሰዎች የራቀ እጅግ ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ቸር አምላክ ነው፡፡ ምድር በእግዚአብሄር ከብር ተሞልታለች፡፡

ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።  ኦሪት ዘኍልቍ 14፡21

የእግዚአብሄር ክብር የሚያይ ሰው በእግዚአብሄር ቃል መስማት እምነትን ያገኘ ሰው ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር በህይወቱ የሚለማመድ ሰው በእግዚአብሄር ቃል እምነትን ያገኘ ሰው ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብርና ሃይል በህይወቱ የሚለማድ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል የሚያምን ሰው ነው፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፡9

የእግዚአብሄርን ቃል የሰማ ሰው የእግዚአብሄርን ክብርና በጎነት በህይወቱ ይለማመዳል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት ይቻላል፡፡ የሞተ ሲነሳ ማየት ይቻላል፡፡ የደከመ ሲበረታ ማየት ይቻላል፡፡ የሌለን ወደመኖር ሲመጣ ማየት ይቻላል፡፡

ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡16-17

በእምነት የእግዚአብሄርን ክብር ማየት ይቻላል፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፡፡ ለማያምን የእግዚአብሄርን ክብር ሃይልና በጎነት ማየት ይቻለዋል፡፡

ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው። ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። የዮሐንስ ወንጌል 11፡39-40

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ክብር #መልክ #አምሳል #ሃይል #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #በጎነት #መጠማት #መራብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ

3d-hd-wallpaper-0453-1024x768.jpgእኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከአርሱ ጋር ህብረት እንዲያደርግ ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ብቻ እንዲረካ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ ምንም እርካታ የሌለው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችል ክፍተት በህይወቱ ያለው፡፡

መዝሙረኛው የሚለው ይህንን ነው፡፡

ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል ብለው ወደ ብዙ ነገሮች ይሮጣሉ ብዙ ነገሮችን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ያረካናል የሚሉትን ብዙ ነገሮችን ይሰበስባሉ ነገር ግን ሲያገኙዋቸው አይረኩም፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ለመርካት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

ለእኔ ግን ይላል መዝሙረኛው ሰዎች የሚፈልጉት ነገር ሁሉ አያረካኝም፡፡ እኔን የሚያረካኝ ግን ይህ ሁሉ ነገር አይደለም ይላል፡፡ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው አንተን እግዚአብሄርን ነው እያለው ነው መዝሙረኛው፡፡

እኔ ግን ትክክለኛነቴን ላለመተው ዋጋ እከፍላለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን የሚያሳዝን ነገር ላለማድረግ እጠነቀቃለሁ፡፡ እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን አድረጋለሁ፡፡  እኔ ግን አንተን ለማክበር ሁሉን እንቃለሁ፡፡ እኔ ግን በእውነት ወደአንተ እቀርባለሁ፡፡

እኔን የሚያረካኝ ክብርህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ መገኘትህ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ የአንተ አብሮነት ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተ ነህ፡፡ እኔን የሚያረካኝ አንተን መፈለግ ነው፡፡ እኔን የሚያረካኝ ክብርህን ማየት ነው፡፡

እኔን ሊያጠግበኝ የሚችል ከአንተ ውጭ ከሰማይ በታች ምንም ነገር የለም፡፡ ሰዎች ለመርካት የሚፈልጉበት ነገር ሁሉ እኔን አያረካኝም፡፡ ሰዎች ለመጥገብ የሚጋደሉለት ነገር ሁሉ አያጠግበኝም፡፡

እኔን የምረካው ክብርህን ሳይ ብቻ ነው፡፡

እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ክብር #መልክ #አምሳል #ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #መፈለግ #መጠማት #መራብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ኤልሻዳይ ነኝ

800px-Ethiopian_highlands_01_mod.jpgአብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ዘፍጥረት 17፡1

ብዙ ጊዜ ሰዎችን የሚያስጨንቃቸው የማያስጨንቅ ነገር ነው፡፡ መንፈሳዊ ነገር የእግዚአብሄርና የሰው ስራ ውጤት ነው፡፡ ሰው የማይሰራው የእግዚአብሄር ስራ አለ፡፡ እግዚአብሄር የማይሰራው የሰው ደግሞ ስራ አለ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የራሳቸው ድርሻ ላይ አያተኩሩም፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ድርሻ ትተው የእግዚአብሄር ድርሻ ላይ ሲያተኩሩ ይጨነቃሉ በክርስትና ህይወታቸው መደሰት ያቅታቸዋል፡፡

ሰዎች በህይወት ያላቸውን ሃላፊነት ሳይረዱ ሲቀሩ በእግዚአብሄር ስራ ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ስራ ሰርተው ካላረፉ የእግዚአብሄርን ድርሻ ለመስራት ሲሞክሩ ህይወታችውን ያባክናሉ፡፡

እግዚአብሄር ለአብርሃም ልጅን እሰጥሃለሁ ብሎታል፡፡ እግዚአብሄር ካለ ሆነም ነው፡፡ አብርሃም ማድረግ ያለበት በእምነት ተቀብሎ መኖር ብቻ ነው፡፡ አብርሃም ማድረግ ያለበት እግዚአብሄር ከእርሱ የሚፈልገውን ነገር በትጋት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከአብርሃም የሚፈልገው ነገር አብርሃም እግዚአብሄርን እንዲከተል ብቻ ነው፡፡

አብርሃም እግዚአብሄር የሰጠውን የራሱን ሃላፊነት ትቶ ግን እግዚአብሄር ቃሉን እንዴት ሊፈጽመው ነው እያለ ቢጨቅ የሚያመጣው ነገር የለም፡፡ አብርሃም እግዚአብሄር እንዴት ቃሉን እንደሚያደርገው ቢያወጣና ቢያወርድ ለራሱ የተሰጠውን ሃላፊነት መወጣት ያቅተዋል፡፡

በአዲስ ኪዳንን ኢየሱስ ያለው ይህንኑ ነው፡፡ የሰው ድርሻ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ ሁል ጊዜ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሆኖ መገኘት ነው፡፡ የሰው ድርሻ ኢየሱስን ፈፅሞ መከተል ነው፡፡ የሰው ድርሻ የእግዚአብሄር መንግስትን ጥቅም መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ ለእግዚአብሄርን መንግስት በጎነትና ማሸነፍ በትጋት መስራት ነው፡፡

የእግዚአብሄር ድርሻ ሰው ለኑሮ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለሰው ማሟላት ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

ብዙ ሰው ማድረግ የሚፈልገው ግን የራሱን ድርሻ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ከመፈለግ ይልቅ እግዚአብሄር  ይጨመርላችኋል ያለውን ስለሚበላላና ስለሚጠጣ መጨነቅ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲተላለፍ የሚያደርገው እግዚአብሄር አድርግ ያለውን የራሱን ድርሻ ትቶ ይህ የእኔ ድርሻ ነው አትሞክረው ያለውን የእግዚአብሄን ድርሻ ለማድረግ መሞከሩ ነው፡፡

እግዚአብሄር አብርሃምን ያለውም የአንተ ድርሻ በፊቴ መመላለስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው ተከተለኝ ስማኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው ህይወትህን ጠብቅ ንፅህናህን ጠብቅ ቅድስናህን ጠብቅ ነው፡፡

ከዚያ ውጭ ምንም የሚያሳስብህ ነገር የለም፡፡ ነገርህ በእኔ እጅ ነው፡፡ ሌላው የእኔ ሃላፊነት ነው፡፡ ቃሌን መፈፀም የእኔ ስራ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ሁሉ እችላለሁ፡፡ እኔ የማደርገው አያሳስብህ፡፡ ለማድረግ ብቃቱ አለኝ እያለው ነው፡፡

አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ዘፍጥረት 17፡1

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍፁም #ተመላለስ #ኤልሻዳይ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የናቁኝም ይናቃሉ

pride.jpgአሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

እግዚአብሄር መናቅ በፅንሰ ሃሳብ ደረጀ ብቻ ያለ በተግባር ግን የሌለ ነገር አይደለም፡፡ በየእለት ተእለት ኑሮዋቸው እግዚአብሄርንእግዚአብሄርን የሚንቁ፡ በአስተሳሰባቸው ለእግዚአብሄር ክብር የሌላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በአነጋገራቸው እግዚአብሄርን የማይፈሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በአደራረጋቸው እግዚአብሄርን የማያከብሩ ሰዎች አሉ፡፡

ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርህ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

ከእግዚአብሄር ይልቅ ታዋቂነታቸውን የሚያከብሩ ሰዎች እግዚአብሄርን ደስ አያሰኙትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ፍላጎታቸውን የሚያስቀድሙትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብሩትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ገንዘብን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አይደሰትባቸውም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ስለኑሮ የሚጨነቁት ሰዎች እግዚአብሄርን አያስከብሩትም፡፡

ከእግዚአብሄር በላይ ማጣትን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብርም፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12

ከእግዚአብሄር በላይ የሰዎችን ፍላጎት የሚያርጉትን እግዚአብሄር አያከብርም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ሰውንም ደስ ለማሰኘት የሚኖሩት እግዚአብሄርን አያከብሩትም፡፡

ወደ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ገላትያ 1፡10

የናቁትን ማክበር ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡ ያከበሩትን መናቅ ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡

የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። መዝሙር 51፡17

ያከበሩትን ያከብራል የናቁት ይናቃሉ፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2

አዳም እግዚአብሄርን ባላከበረ እና ባልታዘዘ ጊዜ ምድር እንኳን ለገመች እንደ ሃይሉዋ መጠንም መስጠት አቆመች፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ማክበር ሲያቆም እና ሲንቅ በተፈጥሮ ሁሉ ይናቃል፡፡

ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ። ዘፍጥረት 4፡12

አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የናቁኝም #ይናቃሉ #መልስ #ቁጣ #ፍርሃት #ናፍቆት #ቅንዓት #በቀል #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ተአምራት ነን

miracles.jpgእነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን። ኢሳያስ 8፡18

ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሄርን እንወክላለን፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር ላይ እናስፈጽማለን፡፡

ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ ማቴዎስ 6፡10

ኑሮዋችን በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው፡፡

እግዚአብሄር ይረዳናል፡፡

ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33፡26

የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ ከምድር አይደለንም፡፡ በምድር ላይ በእግዚአብሄር ልጅነት ስልጣን እንኖራለን፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12

ሃይማኖት ሃይማኖት ጫወታ እየተጫወትን አይደለም፡፡ ኢየሱስ በልባችን ይኖራል፡፡ ብቃታችን ኢየሱስ ራሱ ነው፡፡ የምንኖረው በእርሱ ነው፡፡

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5

በምድር ላይ በእግዚአብሄር ሃይል እንኖራለን፡፡ በምድር ላይ በእግዚአብሄር ስልጣን እንኖራለን፡፡

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና . . . እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20

ለምድር ሰዎች እንግዳ ነን፡፡ ለምድር ሰዎች እግዚአብሄር እንደሚሰራ ምልክቶች ነን፡፡ ለምድር ሰዎች ድንቅና ተአምራት ነን፡፡

ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ። ማቴዎስ 9፡8

እነሆ፥ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን። ኢሳያስ 8፡18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #ተአምር #የሚያስችልሃይል #ድንቅ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #የእግዚአብሄርችሎታ #እግዚአብሄርንሃያል #ራስንመግዛት #ልብ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ

Paving-Your-Road-to-Success.jpgየአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ኢሳይያስ 40፡3-6

እግዚአብሄር በእያንዳንዱ የህይወት አቅጣጫችን ሁልጊዜ መገለጥ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ፋንታ ሃይሉን መግለጥ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በድካማችን ሊቆም ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ሊታይ ይፈልጋል፡፡ በህይወታችን አስበን የማናውቀውን ድንቅ ነገር ማድረግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታች ሃይሉን ሊያሳይ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ክብሩን እንዲገልጥ ልባችን እንዲዘጋጅ ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ግን ጨዋ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደ ልጆች ለእኛ ክብር አለው፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፈቃድ ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ፈቃደኝነትና መተባበር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ኩሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ክብሩን ማወቃችንን ማየት ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄርን እንድንፈልገው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ክብሩን እንዲገልጥ ለእግዚአብሄር መምጫ መንገድን ልንጠርግ ያስፈልጋል፡፡

የአንዳንዱ ሰው ህይወት ለእግዚአብሄር ስራ እንደ አውራ ጎዳና ነው፡፡ የሌላው ደግሞ ህይወት እንደ ተራራና ሸለቆ የማይመችና የማይጋብዝ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ክብሩን እንዲገልጥ መንገድን እንድንጠርግለት ይፈልጋል፡፡ እኛ ማድረግ የማንችለው ነገር እርሱ እንዲያደርግ እኛ ማድረግ የምንችለውን ነገር መጀመሪያ እንድናደርግ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ የእግዚአብሄር ክብርና በጎነት እንዲገለጥ የእኛ ትህትናና የዋህነት ይጠይቃል፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችን እንዲገለጥ እግዚአብሄር ከእኛ የሚጠብቃቸው ነገሮች አሉ፡፡

  1. እግዚአብሄር በእኛ ክብሩን ለመግለጥ በህይወታችን ያለው ሸለቆ እንዲሞላ ይፈልጋል፡፡

አልችልም አልበቃም አይገባኝም የምንለውና ሃሞት ቢስነታችንን እምነት ማጣታችንን በእምነት መለወጥ አለብን፡፡ በክርስቶስ በመስቀል ላይ በተከፈለልን የሃጢያት ዋጋ ምክኒያት ማንኛውም የእግዚአብሄር በጎነት ይገባናል፡፡ እግዚአብሄርን ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡ እግዚአብሄን መጠበቅ አለብን፡፡ የማይቻለውን ነገር ይችላል ብለን ማመን አለብን፡፡ እኛ የማንችለውን ነገር ካላደረገ ምኑን አምላካችን ሆነ፡፡ እኛ የማንችለውን ታእምር ካላደረገ የአምላክ አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው፡፡ ከተፈጥሮ በላይ የሆነውን ነገር ካላደረገ እምነት ምንድነው፡፡ የማናየውን ነገር ካላደረግ እምነታችን የት አለን፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። ዮሃንስ 11፡40

  1. እግዚአብሄር በድካማችን ሃይሉን እንዲያሳይ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችን በበጎነቱ እንዲገለጥ ከፍ ያለው ነገር የራስ ጉልበትና ችሎታ ትእቢት እና ትምክት እንዲዋረድ ያስፈልጋል፡፡ ትሁት እንድንሆን ራሳችንን በፊቱ እንድናዋርድ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ የማላውቀው ነገር አለ ስለእኔ ከእኔ በላይ እግዚአብሄር ያውቃል ማለት ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡6

  1. ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል

ጥርጥራችንንና አለማመናችንን ማስወገድ አለብን፡፡ የዋሆች መሆን ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሄር እንዲሚክሰን በማመን ለመጎዳት ለመበለጥ መዘጋጀት አለብን፡፡ ክፉን በክፉ ላለመመለስ ሃይላችን ለክፋት ላለመጠቀም መወሰን ለክፋት ሞኝ መሆን አለብን፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል የዋህ መሆን ይጠበቅብናል፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7

የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ማቴዎስ 5፡5

እኛ የእግዚአብሄን ክብር ከምንፈልገው ባለይ እግዚአብሄር በህይወታችን ክብሩን ማሳየት ይፈልጋል፡፡ እኛ ከተዘጋጀን እግዚአብሄር በህይወታችን ይታያል ክብሩንና በጎነቱን በህይወታችን ይገልጻል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ሃይል #ዘላለም #ጥበብ #የእግዚአብሄርመንግስት #ንጉስ #እርሾ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች

glory-of-god.jpgቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች ኢሳያስ 6፡3

የእግዚአብሄርን አሰራር በተረዳን መጠን እናርፋለን፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር በተረዳን መጠን በስራው መተባበር እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር በተረዳን መጠን በምንሰራው ሁሉ ፍሬያማ እንሆናለን፡፡

እግዚአብሄር የምድር ፈጣሪና ባለቤት ነው፡፡ እግዚአብሄር ምድርንና ሰውን የፈጠረው ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ምድርን አያስተዳደረ ነው፡፡

እግዚአብሄር አንዳንዴ ከምናስበው በላይ በትጋት እየሰራ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስለጥቃቅኑም ነገር ግድ ይለዋል፡፡

ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። ማቴዎስ 10፡29-30

እግዚአብሄር ሰዎችን ፍቃድ ያላቸው አድርጎ ቢፈጥራቸውም እግዚአብሄር ምድርግን በፈለገው መንገድ ምድርን እያስኬደ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ንጉስ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል። መዝሙር 47፡7-8

እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ምን መስራት እንደሚፈልግ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር በእያንዳንዱ ነገር ላይ አላማ አለው፡፡ እግዚአብሄር አላማውን ለማሳካት በትጋር እየሰራ ነው፡፡ እግዚአብሄር በስራ ላይ ነው፡፡

ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17

ለእግዚአብሄር ሃሳብ አንሰጠውም፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ያውቃል፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11

የተሻለ ነገር ብናደርግ ቀድሞውኑ በስራ ላይ ካለው ከእግዚአብሄር ጋር መተባበር ነው፡፡ የሚሳካልን ምድር ሁሉ ከክብሩ እንደተሞላች አስተውለን ከእገዚአብሄር ጋረ አብረን ስንሰራ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር አብረን ሰራተኛ ነን፡፡ ምክኒያቱም ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለችና፡፡

የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡9

የእግዚአብሄር መንግስት በሃይል እየሰራች ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት እየሰራች መሆኑን በአይናችን አላየንም ማለይት ስራዋን አቁማለች ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በምድር ላይ በሃይልና በትጋት እየሰራች ነው፡፡

ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡20-21

የእግዚአብሄር አሰራር እንደ እርሾ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፈጥኖ ሲሰራ አይታይም ግን እየለወጠ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ሊያደናቅፍና በፊቱ ሊቆም የሚችል ምንም ሃይል የለም፡፡

ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች። ማቴዎስ 13፡33

በፍጥረት ወቅት የእግዚአብሄር መንፈስ በጥልቁ ላይ እንደነበረ ሁሉ ምድር በእግዚአብሄር ክብር ተሞልታለች፡፡ /ዘፍጥረት 1፡3/ ከእግዚአብሄር እውቀትና ሃይል የሚያመልጥ ምንም ነገር የለም፡፡

ስንፀልይ እንኳን ምድር ሁሉ ከክብሩ እንደተሞላችና ከእግዚአብሄር ክብር የሚያመልጥ ነገር እንደሌለ በማመን በእረፍት ነው፡፡

መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ማቴዎስ 6፡13

ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች፡፡ ኢሳያስ 6፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ሃይል #ዘላለም #ጥበብ #የእግዚአብሄርመንግስት #ንጉስ #እርሾ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: