Category Archives: Contentment

ራሳችንን እናማጥናለን

contentment.jpgጌታን የምናገለግለው በሚታይ ነገር ስለደላንና ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ስለሆነልን አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው ጌታን ማገልገል ስላለብን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው የምንፈልገው ነገር ሁሉ ተሟልቶልን አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው ጉድለታችን በእግዚአብሄር ፀጋ እየተሸፈነ ነው፡፡

ጌታን የምናገለግለው የተሻለ የሙያ መስክ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለገልው በእግዚአብሄር ስለተጠራን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው ከዚህ የተሻለ የምንሰራው ስራ ስለሌለ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግልው በህይወታችን ያለውን የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመፈፀም ነው፡፡

ጌታን የምናገለግለው ከግል ጥቅም አንፃር አትራፊ ስራ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው እግዚአብሄር ለዚህ አገልግሎት እንደፈጠረን ስለምናምን ነው፡፡ ጌታን የምናገለግለው መብቱና ስልጣኑ ብዙ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታን የምናገለግለው መብታችንንና ጥቅማችንን እየተውን ነው፡፡

ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ ይልቁን እንዴታ? ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ በዚህ መብት አልተጠቀምንም። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡12

እግዚአብሄርን የምናገለግለው ሁሉ ሰው ተቀብሎን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው እግዚአብሄር ስለላከን ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግልው የምናገለግላቸው ሁልጊዜ እያስደሰቱን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግልው በጌታ ደስ በመሰኘት ብቻ ነው፡፡

ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ዕብራውያን 13፡17

ስለዚህ የተሻለ ስለሚከፈለው ነው ይህ ደሞዝ አንድ ቀን ሲቆም አገልግሎት ያቆማል ለሚሉት መሰናከያ መሆን አንፈልግም፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ቢከፈለንም ባይከፈለንም እናገለግላለን፡፡ ቢመቸንም ባይመቸንም እናገለግላለን፡፡ በጊዜውም አለጊዜውም እንፀናለን፡፡

እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡15

ስለዚህ በከፍታና በዝቅታ ራሳችንን እናማጥናለን፡፡ ከሰው ምንም ሳንጠብቅ እግዚአብሄርን ማገልገል ትምክታችን ነው፡፡ እግዚአብሄርን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ማገልገላችን ሃብታችን ትምክታችን ነው፡፡ ትምክታችንን ማንም ከንቱ ከሚያደርግብን ሞት ይሻለናል፡፡

አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡3-8

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #እውቀት #ምስጋና #ትህትና #ልብ #እምነት #ፀሎት #ማማጠን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በዘፈንና በስካር አይሁን

Ethiopia_4.jpgክርስትና ከሚታወቅበት ልዩ ባህሪዎች አንዱ ሚዛናዊ የሆነንን ህይወት መምራት ነው፡፡ክርስትያን በደስታም የሚያከብረው እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን በደስታም ከልክ አያልፍም፡፡ ክርስትያን ደስታውና ዘና ማለቱ ሃጢያት እስኪያሰራው አያደርሰውም፡፡ ክርስትያን በነገሮች ያለመጠን አይፈነጥዝም ደስታውን ሁሉ በልክ ያደርጋል፡፡

ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29-31

ክርስትያን በሃዘንም እግዚአብሔርን ነው የሚያየውም የሚያከብረውም እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን ሃዘኑም ለሞት የሚያደርስ ራስን የሚያስጥል ከመጠን ያለፈ አይደለም፡፡

የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10

ክርስትያን አገኘሁ ብሎ ብዙ አይበላም ራስን በመግዛት ራሱን ያዝ ያደርገዋል፡፡ ክርስትያን አገኘሁ አገኘሁ ብሎ ብዙ አይጠጣም፡፡ ክርስትያን ለመንቃት የሚያደክመውን ካለልክ እንዲዝናና የሚያደርገውን ኑሮ ይሸሻል፡፡ ክርስትያን ለመንቃትና ሳያቋርጥ ለመፀለይ ስለሚፈልግ እንቅልፍ እንቅልፍ የሚያስብለውን የሚያደክመውን ከመጠን ያለፈ ኑሮ አይኖርም፡፡

ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ሮሜ 13፡11-13

በመጠኑ መኖር በመንፈስ ለመንቃት ይጠቅማል፡፡ መንቃት ደግሞ ለመፀለይና ይጠቅማል፡፡ በመጠኑ መኖር ላለመዘናጋት ነቅቶ ለመፀለይ ይጠቅማል፡፡

በመጠኑ ኑሩ ንቁም፥ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያጋሳ አንበሳ ይዞራልና፤1ኛ ጴጥሮስ 5፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: