Category Archives: maturity

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

seen by men.jpg

በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ

ክፉን በክፉ ላለመመለስ ህፃናተ ሁኑ እንጂ ስለህይወታችሁ እወቁ፡፡ ህይወታችሁን እንዳመጣላችሁ አትምሩት፡፡ ህይወታቸሁን ለመምራት አስቡ አቅዱ በእግዚአብሄር ቃል የታደሰ አእምሮዋችሁን ተጠቀሙ፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20

መውጫ መግቢያውን የምትቃኙ ንቁዎችና ብልሆች ሁኑ እንጂ ወደ ወሰዷችሁ የምትጎተቱ ሞኞች አትሁኑ፡፡

እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 10፡16

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

በእእምሮው ህፃን የሆነ ሰው የራሱ የህይወት መርህ የለውም የመጣው ነገር ሁሉ ይወስደዋል፡፡

ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡11

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡14

በአእምሮው የበሰለ ሰው የሰው የግል መጠቀሚያ አይሆንም፡፡ በአእምሮ የበሰለ ሰው ዘሎ ውሳኔን አይወስንም በአእመሮ ህፃን ያልሆነ ሰው አካሄድን ይመለከታል ይመዝናል፡፡

በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17

የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል። መጽሐፈ ምሳሌ 14፡15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #ህፃንነት #ብስለት #ጥበብ #ማስተዋል #አላማ #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አንድነት #ትህትና #አክብሮት #ስልጣን #መሪ

የህፃንነት ልዩ ምልክቶች

tongue.jpg

ብዙ ጊዜ የምናተኩረው በክርስቶስ ስለተደረገልን ነገር ነው፡፡ በክርስቶስ የተደረገልን ነገር ሁሉ ያልለፋንበት ስጦታ ነው፡፡ በክርስቶስ ይህ ሁሉ ነገር ተፈደርጎልንም ለሃላፊነት የማንበቃ ህፃናት ልንሆን እንችላለን፡፡

ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡1-2

እግዚአብሄር ለብዙ ነገሮች ያምነን ዘንድ ከህጻንነት መውጣት አለብን፡፡

የህፃንነት ምልክቶች

 1. ትግስት ማጣት

ህጻን የሚያውቅው አሁንን ነው፡፡ ህጻን እቅድን አያውቅም፡፡ ህፃን ተስፋን አይረዳም፡፡ ህፃን የወደፊቱን ብዙም አያየም፡፡ ህጻን የሚያየውና የሚያውቀው አሁንን ነው፡፡ እንዲሁ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው የቅርቡን ብቻ ያያል የሩቁን ማይት ተስኖታል፡፡

እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡9

በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው ወደፊቱን አያየም፡፡ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው አሁን የሚያደርገው ነገር ነገር ስለሚያስከትልበት ችግር አይረዳም፡፡ በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰወ ስለሚዘራው ክፉ ዘአዘር አይጠነቀቅም፡፡

አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡7-8

በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው መታገሉን እንጂ በሚገባ በህጉ መሰረት መታገሉን አያረጋግጥም፡፡

የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡4-5

 1. ሁሉንም ለመስራት መሞከር

ህፃን ለራሱ ያው አመለካከት የተዛባ ነው፡፡ ህፃን የማይችለውን የሚችለው ይመስለዋል፡፡ ህፃን በቀላሉ ይታለላል፡፡ ህጻን እርሱ ብቻ የሚችል ይመስለዋል፡፡ ህፃን ውስን እንደሆነ አይረዳም፡፡ ህፃን ሌላው የአካል ብልት የሚያደርገውን አይረዳም፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡20

 1. ራስን ከሌላ ጋር ማስተያየት

ህፃን የሆነ ሰው በመወዳር በቅናትና በፉክክር ህይወቱን ለማባከን አይፈራም፡፡

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡12

 1. ጥልና ክርክር

እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤

ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡1-3

 1. ክፍፍል እና አድመኝነት

በክርስቶስ ህፃን የሆነ ሰው ጥበብ ሁሉ አንድ አይነት ይመስለዋል፡፡ በክርስቶስ ያልበሰለ ሰው በምድርና በሰማይ ጥበብ መካከል ያለውን ልዩነት አያውቅም፡፡

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።

ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። የያዕቆብ መልእክት 3፡13-17

 1. ተምሮ ወደ እውቀት አለመድረስ

ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፥6-7

 1. የመንፈሳዊ መረዳት ጉድለት

መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡13

ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።

ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። ወደ ዕብራውያን 5፡12-14

 1. በፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት አለመረዳት

ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መክብብ 10፡16-17

 1. ቶሎ ሆድ ይብሰዋል

ህጻን ቶሎ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ህጻን በአንድ ቦታ አይጸናም፡፡ ህጻን መከራን ከመታገስ ይልቅ መሸሽን ይመርጣል፡፡ ህፃን ወረተኛ ነው፡፡ በክርስቶስ ህፃንም የሆነ እንዲሁ ያገኘውን ነገር ወዲያው ያጋንነዋል ወዲያውም ያጣጥለዋል፡፡ ህፃን ጠንካራን ነገር ዋጥ አድርጎ የማለፍ ጉልበት የለውም፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #መሰረታዊፍላጎት #ቅንጦት #ማማጠን #ህፃን #ንጉስ #መኳንንት #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የክርስቶስም ሙላቱ ልክ እስክንደርስ

church leader.jpgሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። ኤፌሶን 4፡12-13

የክርስትና ጉዞ የእድገት ጉዞ ነው፡፡ የክርስትና ጉዞ መነሻ ያለው መድረሻም ያለው ጉዞ ነው፡፡

የክርስትና ጉዞ ሲጀመር የሚታወቅ ግቡም የሚታወቅ ጉዞ ነው፡፡ ክርስትና መነሻውም መድረሻውም የማይታወቅ የግምት ረቂቅ ጉዞ አይደለም፡፡ ክርስትና መነሻውም መድረሻውም የሚገመት ባዶ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና መነሻውም መድረሻውም የማይታወቅ የወግና የስርአት ብዛት አይደለም፡፡

ክርስትና የሚጀመረው በንስሃ ከአሮጌ ኑሮ ፍጹም ወደኋላ በመመለስ ነው፡፡ ክርስትና የሚጀመረው ዳግም ከመወለድ ነው፡፡ ዳግም የተወለደ ሰው ደግሞ ያድጋል፡፡

የክርስትና እድገት ወግና ስርአት መፈፀም አይደለም፡፡ የክርስትና እድገት የውጫዊ ስርአትን መጠበቅ አይደለም፡፡

ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ። እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡18-19

የክርስትና እድገት ጣራው የክርስቶስ ሙላት ልክ ነው፡፡ የክርስትና መጨረሻው ክርስቶስን መምሰል ነው፡፡ የክርስትና መጨረሻው የክርስቶስ ሙላት ልክ ነው፡፡ የክርስትና ግቡ ክርስቶስን ሙሉ ለሙሉ መከተልና መምሰል ነው፡፡

ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡12-13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ጌታ #መከተል #ክርስቶስእስኪሳል #መምሰል #ክርስቶስንመምሰል #ቃል #ተማሪ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #ተከታይ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አስሩ የብስለት መለኪያዎች

matured2.jpgነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ገላትያ 4፡1-2

 • ከውጭው ይልቅ ስለ ውስጡ ስለልባችን ማሰብ

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4

 • ለሰው ያለ ትልቅ ክብር

ሰው ማደጉ የሚታወቀው ለሰው ያለው ክብር ሲጨምር ነው፡፡ በተለይ ሰውን ስላለው ነገርና ስለሆነውስ ነገር ሳይሆን ስለሰውነቱ ብቻ መናክበር ከቻለ በሳል ሰው ነው ይባላል፡፡

ዝቅተኛ ኑሮ ወይም ዝቅተኛ ሥራ ለመሥራት ፍቀዱ ውስጥ ካሉ ጋር አብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ሮሜ 12፡16

 • ሰዎችንና ነገሮችን የመተው ችሎታ

የበደሉንን ለመተው ይቅር የማለት ችሎታ ክርስያናዊ ብስለትን ይጠይቃል፡፡ የስኬት ምንጭ እግዚአብሄር መሆኑን አውቆ ለእድገት ከሰው ጋር አለመከራከር አለመጣላት፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ዕብራውያን 10፡34

 • ቁሳቁስን ቀለል አድርጎ መመልከትና ለምድራዊ ነገር አለመንገብገብ

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

 • በዝቅታ በእግዚአብሄር መታመንና በምድር ራስን እንደ እንግዳ መቁጠር

ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ ዕብራውያን 11፡9

በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7

 • የዘላለም ህይወት እይታ

በጌታ ያደገ ሰው ማንኛውንም ውሳኔ የሚወስነው ለዘላለም መንግስት ካለው ጥቅም አንጻር ነው፡፡ በሳል ሰው ምንም ነገርን የሚመዝነው በዘላለም እይታ ነው፡፡

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2

መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ፊልጵስዩስ 3፡19-20

 • ከከንቱ ውድድር እና ፉክክር እስራት ነፃ መውጣት

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡12

 • ከምንም ነገር ስለ አላማ ማሰብ

በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡14

የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡28

 • ካለ እግዚአብሄር ምሪት ለመሄድ አለመቸኮል

እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27

 • ሌላውን በትህትና መመልከት

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ፊልጵስዩስ 2፡3፣5

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ትህትና #ባህሪ #ምሪት #ዘላለም #መተው #ልብ #ፉክክር #ቁሳቁስ #መታመን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: