Category Archives: Reward

ዋጋ እንዲሰጥ

32584-praying-hands-3-1200.1200w.tn.jpgወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ሰዎች አሰሪን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ስራን ሰርተውለት ጥሩ የሚከፍላቸውን አሰሪ ተግተው ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ዝነኛ ስም ያለው የተከበረ መስሪያ ቤት ሲሰሩ ይበልጥ ደስ ይላቸዋል፡፡

ሰራተኛንና አሰሪን የሚያገናኝ የሰው ሃይል አስተዳደር ኢንዱስትሪ ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ ትልልቅ ድርጅት ያላቸው ሰዎች ለድርጅታቸው በቋሚነት ሰራተኛ የሚመለምሉበትና የሚቀጥሩበት ትላልቅ መምሪያ አላቸው፡፡

ድርጅቶቹ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ የሚሰራላቸው ብቁ የሆነው ሰው ለመመልመል ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ሁሉም ግን የሚሰራላቸውን ሰው ነው የሚፈልጉት፡፡

ፈልጉኝና ዋጋን እሰጣችኋለሁ ያለ ሰው ሰምቼ አላውቅም፡፡ ስለፈለግነው ብቻ ዋጋን የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ዋጋን ይሰጣል፡፡

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ ሰው መሆን ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡26-28

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በእምነት መፈለግ ነው፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በፍፁም ልብ መፈለግ ነው፡፡

እግዚአብሔር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኩሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንም ባጣ ቆየኝ እንዲያደርገው አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔርን በሁለት ሃሳብ እንድንፈልገው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔርን ፈልገን እንደባለጠግነቱ መጠን ዋጋ እንዲሰጠን ካስፈለገ በፍፁም ልባችን ልንፈልገው ይገባል፡፡

እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርሚያስ 29፡13

ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ  1፡7-8

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህ አዲስ ዓመት እግዚአብሔርን በመፈለግ እንደባለጠግነቱ መጠን ከእግዚአብሔር ዋጋ የምንቀበልበት ዓመት ይሁን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #እግዚአብሔርንመፈለግ #መፀለይ #ፍፁምልብ #አዲስአመት #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አክሊል ተዘጋጅቷል

crown.jpgየኢየሱስን አዳኝነት አምነን የተቀበልን ሁላችን ወደጌታ ስንሄድ ወይም ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ በእግዚአብሄር የፍርድ ፊት ቀርበን ሽልማታችንን እንቀበላለን፡፡

ነገር ግን ሁሉም ሁሉን አይነት ሽልማት አይቀበልም፡፡ እውነት ነው ደህንነት በነኛ ነው፡፡ ደሀንነት ኢየሱስ በሰራው መስዋእትነበት በማመን ብቻ የምንቀበለው ስለሆነ ለሁሉም ነው፡፡ ሰው ለመዳን ኢየሱስ በሰራው የመስቀል ስራ ከማመን ውጭ ምንም አይነት ስራ መስራት የለበትም፡፡

በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡13-15

ነገር ግን ሽልማቱ ለሁሉም አይደለም፡፡ እንደሚገባ ለሚታገሉ ፣ የመታገያውን ህግ ለሚጠብቁ ፣ ረሳቸውን ለሚገዙ ፣ ምንም ይሁን ምን በፍቅር ለመኖር ለሚወስኑ ፣ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ዋጋ ለሚከፍሉ ፣ ራሳቸውን ለሚክዱ ፣ ባላቸው ነገር ሁሉ ቤተክርስትያንን ለሚያገለግሉ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት መስፋፋት ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ገንዘባቸውን ፣ እውቀታቸው ሳይሰስቱ ለሚሰጡ ሰዎች ብቻ ነው፡፡

ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5

የሚያሳዝነው ግን እንዳንድ ሰዎች ያደረጉትን መልካም ነገር ሁሉ ዋጋ በምድር ላይ ይቀበሉታል፡፡

ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና። ሉቃስ 6፡22-24

በምድር ስንኖር መከራ አለ፡፡ የጠላት የዲያቢሎስ መንግስት ይሰራል፡፡ በምድር ላይ ለእግዚአብሄር ስንኖር ፣ የእግዚአብሄርን መንግስት ስናስፋፋና እግዚአብሄር በህይወታቸን ያስቀመጠውን የመንግስቱን አላማ ስናስፈፅም ሊያስቆመን መከራን ያመጣብናል፡፡ ነገር ግን የታመንን ከሆንን የህይወት አክሊል ለእኛ ይሆናል፡፡

ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ። ራእይ 2፥10

በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና። ያዕቆብ 1፥12

በምድር እንኳን ሰው ለምድራዊ ሽልማት ተግቶ ይሰራል፡፡ የምድራዊውን ለመሸለም ሰው ራሱን ይገዛል፡፡ የሚያምረውን አይበላም ፣ የሚያምረውን አይለብስም የሚያምረውንም አይጠጣም፡፡ ለምድራዊ ሽልማት ሰው እንደዚህ ራሱን ካስገዛ እኛማ ለዘላለማዊው ለማይጠፋው ሽልማት እንዴት ሌት ተቀን አንሰራም፡፡

የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል #ሽልማት #ትንሳኤ #ሰማይ #የማይጠፋአከሊል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

%d bloggers like this: