Category Archives: Faith

የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት

seen by men.jpg

ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 17፡5-6

እምነት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት አይቻልም፡፡ ካለእምነት ከእግዚአብሄር መቀበል አይቻልም፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር ጋር ሰርቶ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡ በአጠቃላይ ያለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

ኢየሱስ እምነት ጨምርልን ለሚለው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልሰጠም፡፡ ኢየሱስ እምነትን ጨምርልን የሚለው ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ እንደሆነ አምኖ ይጨመርላችኋል አላለም፡፡ ኢየሱስ እምነት ጨምርልን ለሚለው ጥያቄ የመለሰው መልስ ሃዋሪያቱ ባላቸው እምነት ምን እያደረጉ እንደሆነ የሚፈትን ነው፡፡

ሁሉም ክርስትያን እምነት አለው፡፡  እያንዳንዱ ኢየሱስን የሚከተል ሰው የእምነትን መጠን ተካፍሏል፡፡

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡3

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሰማ ሰው ሁሉ እምነት አለው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17

ልዩነት የሚያመጣው የምንሰማውን ቃል እንደት እንደምንሰማ ፣ በምንሰማው ቃል እንዴት እርምጃ እንደምወስድና በቃሉ እርምጃ ወሰድን በፅናት እንዴት እንደምንቀበል ነው፡፡

የሃዋሪያቱ ችግር የእምነት ትንሽነት ችግር አይደለም፡፡ እምነት እምነት ነው፡፡ እምነት የሚሰራ ነው፡፡ ለመስራት የማይበቃ እምነት የለም፡፡ እምነት ከሆነ ይሰራል፡፡

የሰውም ጥያቄ የእምነት ጭማሬ ጥያቄ አይደለም፡፡ ያለንን እምነት በሚገባ ከተጠቀምንበት በህይወታችን ስኬታማ እንሆናለን፡፡

በመፅሃፍ ቅዱስ የነቢይ ሚስት የነበረችው እዳ የነበረባት ሴት ወደኤልሳ እንዲረዳት ስትጮህ ኤልሳ ያላት በቤትሽ ምን አለ? ነው፡፡

ከነቢያትም ወገን ሚስቶች አንዲት ሴት፦ ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን ይፈራ እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች። ኤልሳዕም። አደርግልሽ ዘንድ ምን ትሻለሽ? በቤትሽ ያለውን ንገሪኝ አላት። እርስዋም፦ ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም አለች። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 4፡1-2

እግዚአብሄር ተአምር የሰራው በቤትዋ ባለው በራስዋ ነገር ተጠቅሞ ነው፡፡

አሁንም እግዚአብሄር በህይወታችን ታእምር የሚሰራው ባለን እምነት ተጠቅሞ ነው፡፡

ብዙ ሰው ግን እግዚአብሄር በተአምር እምነቴን ቢጨምር እኮ ብሎ በከንቱ ይመኛል፡፡ ችግርህ የመጣው በቂ እምነት ስለሌለህ አይደለም፡፡ ችግርህን የሚፈታው ተጨማሪ እምነት በማግኘት ላይ አይደለም፡፡ ችግርህ የመጣው ያለህን እምነት ባለመጠቀም ነው፡፡ ችግርህ የሚፈታው ያለህን አምነት ተጠቅመህ እንዴት ፍሬያማ እንደምትሆን በማወቅ ነው፡፡

ተጨማሪ እምነት ሳያስፈልገን ያለንን እምነት ወደውጤት የምናደርስበት 5 መንገዶች

 1. እምነት አስፈላጊ እንደሆነ ተረዳ

ከእግዚአብሄር በአጋጣሚ የምታገኘው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር እንደ ልጅ ከሰው አምነትን ይጠብቃል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት እምነት ይጠይቃል፡፡ በህይወትህ እምነት እንደሚያስፈልግህ እወቅ፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት እንደማትችል አጥብቀህ ተረዳ፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

 1. እምነትን ለመጠበቅ ትጋ

እምነት የልብ ነው፡፡ ልብህን ከጥርጥር ካልጠበቅክ እምነትንም ልትጠብቅ አትችልም፡፡ ካልተጠነቀቅክ ጥርጥር እምነትን ከልብህ ያጠፋዋል፡፡ ጥርጥርን በልብህ ካስተናገደከው እመነትህ ሊሰራ አይችልም፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። የማርቆስ ወንጌል 11፡23

አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡23

በመንገድ ዳርም ያሉት የሚሰሙ ናቸው፤ ከዚህ በኋላም ዲያብሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል። የሉቃስ ወንጌል 8፡12

 1. በእምነት ነገር ሰነፍ አትሁን

እምነት የሰነፎች አይደለም፡፡ አምነት ትጋትን ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ሰው እግዚአብሄርን በእምነት ለመፈለግ ስንፍና ስላለበት በቀላሉ እግዚአብሄር የለም በማለት እግዚአብሄርን ከመፈለግ ይጋት ያቋርጣል፡፡

ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።መዝሙረ ዳዊት 14፡1

 1. እምነት የግፈኞች ነው

እምነት ገድል ስለሚጠይቅ የለስላሳ ሰዎች አይደለም፡፡ እምነት የግፈኞች ነው፡፡ እምነት ያነሰን ነገር የማይቀበሉ ሰዎች ነው፡፡

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። የማቴዎስ ወንጌል 11፡12

እምነት ምንም ምክንያት አይቀበልም፡፡ እምነት የሚፈልገውን እስከሚያገኝ የሙጥኝ የሚል ነው፡፡

እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት። እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ። እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች። የማቴዎስ ወንጌል 15፡25-28

እምነት በቃሉ ወደኋላ አያፈገፍግም፡፡

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። ወደ ዕብራውያን 10፡38

 1. እምነት መፅናትን ይጠይቃል

የሚታየው ሁሉ ከማይታየው የተገኘ ነው፡፡ ሰው በእርሻው ደክሞ መልካምን ዘር ዘርቶ ለፍሬ መጠበቅ አለበት፡፡ እንዲሁ እግዚአብሄርን በቃሉ ያመንንበት ነገር ከማይታየው ወደሚታየው አለም አስከሚመጣ ድረስ መፅናት ይገባናል፡፡ ሁሉንም እንደ እግዚአብሄር ቃል ካደረግን በኋላ እምነት መፅናትን ይጠይቃል፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ወደ ዕብራውያን 10፡36

በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። ወደ ዕብራውያን 6፡11-12

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የሰናፍጭቅንጣት #መፅናት #ትጋት #እምነት #መናገር #ግፈኞች #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ጥርጥር #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ሰውን ማስደሰት ይቻላል

ethiopia-girls-laughing-dfid.jpg

ሰው የሚደሰትበት የተለያየ መንገድ አለ፡፡ ሰው ጥሩ ነገር ሲበላ ይደሰታል፡፡ ሰው ጥሩ ሲለብስ ደስ ይለዋል፡፡ ሰው ጥሩ መኪና ሲነዳ ደስ ይለዋል፡፡ ሰው ገንዘብ ከፍሎ አንድም የሚፈልገውን ነገር ማደረግ ሲችል ደስ ይለዋል፡፡

ሰውን ብዙ ነገሮች ያስደንቁታል፡፡ ሰው ያልጠበቅው መልካም ነገር ሲያገኝ ይደነቃል፡፡ ሰው የማይችለውን ነገር ሲችል ይደነቃል፡፡

እግዚአብሄርን የሚያስደንቀው ሰውን የሚያስደንቁ ነገሮች ሁሉ አይደሉም፡፡ ሰውን የሚያስደንቀው እግዚአብሄርን የማያስደንቀው ብዙ ነገር አለ፡፡

 1. እግዚአብሄር በገንዘባችን አይደነቅም

እግዚአብሄር የሰው ገንዘብ አያስደንቀውም፡፡ የማንም ቢሊየነር ሃብት እግዚአብሄርን አያስደንቀውም፡፡

የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። መዝሙረ ዳዊት 50፡10

 1. እግዚአብሄር በውበታችን አይደነቅም

የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ ውበትን ስናይ የምንደነቀው እኛ ነን፡፡ እግዚአብሄር ውበታችንን አይቶ ይገርማል ውበቱ አይልም፡፡ እግዚአብሄር ውበታችንን አያይም፡፡ የመንፈስ እንጂ የስጋ ውበታችን ለእግዚአብሄር አይታየውም፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡4

 1. እግዚአብሄር በዝናችን አይደነቅም

እኛ እንደሰው ዝነኛ የሆነ ሰው ጋር ስንቀርብ እንለያለን፡፡ ሰው ዝነኛ ሰው ጋር ሲቀርብ ፈጥኖ ለማስታወሻ የሚሆን ፊርማ ያስፈርማል፡፡ ሰው ዝነኛ ሰው ጋር በአጋጣሚ ከተገናኘ አብሮ ፎቶ ለመነሳት ይቸኩላል፡፡ እግዚአብሄር ይሄስ ዝነኛ ነው ብሎ ሁለተኛ ዞር ብሎ አያየውም፡፡ እግዚአብሄር ዝናችን አይገርመውም፡፡

 1. እግዚአብሄር በጥበባችን አይደነቅም

ማስተዋሉ የማይመረመር እግዚአብሄር ጥበበኛ ሰው አያስደንቀው፡፡ እንደሰው አዋቂ የሆነ ሰው ጋር ስንቀርብ የምንናገረውን ነገር ይበልጥ እንጠነቀቃለን፡፡ እንደ ሰው በሰው ጥበብ እንደነቃለን፡፡ ሰው ጥበበኛ ሰው ጋር ሲቀርብ ያለውን ጥበብ እንዲኖረው ይመኛል፡፡ እግዚአብሄር ግን ማንም ጥበበኛ ሰው በጥበቡ አያስደንቀውም፡፡

የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡19-20

 1. እግዚአብሄር በሃይላችን አይደነቅም

እግዚአብሄር ሃያል ነው ማንንም አይንቅም፡፡ እግዚአብሄር ልናቅ ቢል ደግሞ የሚተርፈው ማንም ሰው አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር የአሜሪካንን ፕሬዝዳንት አይቶ “ውይ ይሄን መናቅ እንዴት ይሆንልኛል?” አይልም፡፡ እግዚአብሄር አይንቅም እንጂ ቢንቅ ማንም አይተርፈውም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ማንንም አይንቅም፡፡

እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው። መጽሐፈ ኢዮብ 36፡5

እግዚአብሄር በእነዚህ ነገሮች አይደነቅም እንጂ እግዚአብሄር ከነጭራሹ አይደነቅም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ይደነቃል፡፡ ሰዎችን ብዙ የሚያስደንቃቸው ነገሮች እግዚአብሄርን ላያስደንቁት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ይደነቃል፡፡ ሰዎችን የሚያስደስቱዋቸው ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄርን ላያስደስተው ይችላል፡ሸ ነግር ግን እግዚአብሄር ይደሰታል፡፡ እግዚአብሄ የሚደሰትበት ነገር አለ፡፡

እግዚአብሄርን የሚያስደንቀው ነገር የሰው እምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚደሰተው በእምነት ነው፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄን ደስ ማሰኘት አይቻለም፡፡

ለእግዚአብሄር ገንዘባችንን ከምናሳየው ይልቅ ምንም ገንዘብ ሳይኖረን እምነታችንን ብናሳየው ይበልጥ ይደሰታል፡፡

በውበታችን ከምንመካ ይልቅ በእግዚአብሄር ሞገስ ስንመካ እግዚአብሄርን እናድስደስተዋለን፡፡

በዝናችን ደስ ከሚለን ይልቅ በእግዚአብሄር ደስ ሲለን እግዚአብሄር ይይካብናል፡፡

በጥበባችን ከምንደገፍ ይልቅ በእርሱ ብንገደፍ እግዚአብሄርን እናስደስተዋለን፡፡

በሃይላችን ከምንታመን ይልቅ በእርሱ በእግዚአብሄ ብንታመን አግዚአብሄርን እናስደስተዋለን፡፡

እግዚአብሄር ይደነቃል፡፡ ሰውን ብዙ ነገሮች ሊያስደንቁት ይችላሉ፡፡ ሰውን የሚያስደንቁት ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄርን ላያስደንቁይት ይችላሉ፡፡ በተለይ ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ ምንም ሰዎች እንዲኖራቸው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ ቢኖረን እምነት ግን ከሌለን እግዚአብሄርን አናስደስተውም፡፡ በተቃራኒ ሰዎች በምድር ላይ የሚፈልጉዋቸው ነገሮች ሁሉ ቢጎድለን ነገር ግን እምነት ካለን እግዚአብሄርን በሚገባ እናስደስተዋለን፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእምነት አለም ክብር

seen by men.jpg

እምነት ራሱን የቻለ ልዩ አለም ነው፡፡ እምነት ለየት ያለ አለም ነው፡፡

ተፈጥሯዊ አለም አለ፡፡ መንፈሳዊ አለም አለ፡፡ በተፈጥሮአዊ አምስቱ የስሜት ህዋሳቶች የሚታይ የሚዳሰስ የሚሰማ የሚቀመስ የሚሸተት አለም አለ፡፡ በተፈጥሯዊ አምስቱ የስሜት ህዋሳቶች የማይታይ የማይዳሰስ የማይሰማ የማይቀመስ የማይሸተት አለም አለ፡፡ በተፈጥሯዊው አይን የሚታይ አለም አለ፡፡ በተፈጥሯዊው አይን የማይታይ አለም አለ፡፡ በእምነት አይን የሚታይ አለም አለ፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18

ሰው ምርጫ አለው፡፡ ሰው በተፈጥሯዊው አለም እይታ ለመኖር መወሰን ይችላል፡፡ ወይም ሰው በመንፈሳዊ አለም እይታ ለመኖር መወሰን ይችላል፡፡ ሰው በሚታየው ለመመላለስ ሊወስን ይችላል፡፡ ሰው በማይታየው ለመመላለስ ሊወስን ይችላል፡፡ ሰው በሚታየው ለመኖር መወሰን ይችላል፡፡ ሰው በእምነት ለመመላለስ መወሰን ይችላል፡፡

እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡6-7

እምነት የሚመጣው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄር ቃል በመቀበል ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17

የእምነት አለም የራሱ ተግዳሮቶች ቢኖሩትም የእምነት አለም የራሱ ክብሮች አሉት፡፡

 1. የእምነት አለም የሃይል አለም ነው

ሰው እውነተኛውን ሃይል መለማመድ ከፈለገ በእምነት መኖር አለበት፡፡ እምነት የማይታየውን ማየት ይጠይቃል፡፡ የማይታየውን ማየት ደግሞ ለስጋ አይመችም፡፡ እምነት ስጋን ያናውጣል፡፡ እግዚአብሄርን መንፈስ ነው፡፡ በመንፈሳዊው አለም ከሚኖረው መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት የምንችለው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር መቀበል የምንችለው በእምነት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ሃይል የምንካፈለው በእምነት ብቻ ነው፡፡

ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ወደ ዕብራውያን 11፡11

በየእለት ህይወታችን የእግዚአብሄርን የሚያስችል ሃይልና ፀጋ የምንለማመደው በእምነት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16

 1. የእምነት አለም የሞገስ አለም ነው

ሞገስ የተቀባይነት ሃይል ማለት ነው፡፡ ሞገስ ሲኖረን ተቀባይነትና ተሰሚነት ይኖረናል፡፡ ሞገስ ሲኖረን ሰዎች እሺ ይሉናል ይቀበሉናል፡፡ ሞገስ ሲኖረን ጥያቄያችንን ለመመለስ ሰዎች ይታዘዛሉ፡፡ ሞገስ እንደጥበብ የሚታይና የሚዳሰስ ነገር አይደለም፡፡

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። የያዕቆብ መልእክት 1፡5-6

ሞገስ በእምነት ከእግዚአብሄር የምንቀበለው የማይታይ ነገር ነው፡፡ ታዲያ በእግዚአብሄር ሞገስ የምንወጣውና የምንገባው በእምነት ነው፡፡

ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ የማቴዎስ ወንጌል 6፡28-31

 1. የእምነት አለም የነፃነት አለም ነው

የሰይጣን አለም መንፈሳዊ አለም ነው፡፡ የሰይጣን እስራት መንፈሳዊ አስራት ነው፡፡ ከባርነት ነፃ መውጣት ካለብን ከባርነት መንፈሳዊ አለም ወደነፃነት መንፈሳዊ አለም እንደተሸጋገርን ማመን አለብን፡፡ የእውነተኛን ነፃነት ትርጉም የምናጣጥመው በእምነት ለመኖር ስንወስን ብቻ ነው፡፡

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14

 1. የእምነት አለም የእርካታ አለም ነው

ሰው የተፈጠረው ለእምነት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የማይታየውን ብቻ ለማየት አይደለም፡፡ ሰው የተፈጠረው የማይታየውንብ እንዲያየ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የሚታየውን እንዳያየን ነው፡፡ ሰው ምንም ቢኖረው በእምነት መኖር ካልጀመረ በስተቀር እርካታን አያየም፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡36

ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። የዮሐንስ ወንጌል 4፡13-14

 1. የእምነት አለም የደስታና የሰላም አለም ነው

ሰው የተፈጠረው በእምነት እንዲኖር በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው፡፡ እምነት ብዙ ተግዳሮቶች ያሉበት አለም ቢሆንም ነገር ግን በእምነት ውስጥ የሚገኘውን ደስታ በምንም ነገር ልናገኘው አንችልም፡፡ ሰው በእምነት ከእግዚአብሄር ጎን መሆኑን እንደማወቅ የሚያስደስተውና የሚያሳርፈው ነገር የለም፡፡ ሰው እውነተኛን ደስታ ማጣጣም ከፈለገ በሚታይ ነገር ሳይሆን በእምነት ለመኖር መወሰን አለበት፡፡

ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።  የዮሐንስ ወንጌል 14፡27

ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም፡፡ ሰው በምድራዊ ቁሳቁስ እስከኖረ ድረስ በእምነት የሚገኘውን ደስታና ሰላም ሊካፈል አይችልም፡፡ ሁለት ወዶ አይሆንም፡፡ ሰው በምድር ተስፋ ይሆነኛል ብሎ የምድር ገንዘብን እስካልናቀ ድረስ የእምነትን ደስታ ሊያጣጥም አይችልም፡፡

እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4

 1. እምነት የገድል አለም ነው

ሰው የተፈጠረው ለገድል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር ታላላቅ ፈተናዎች እንዲያልፍ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲያሸንፍ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲዋጋ እና ድል እንዲነሳ ነው፡፡ ሰው ለቀላልና ለትናንሽ ነገር አልተፈጠረም፡፡ ሰው የተፈጠረው ጥቂት ሰዎች ብቻ ለሚያገኙት የአሸናፊነት ህይወት ነው፡፡

በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። የማቴዎስ ወንጌል 7፡13

እምነት ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ በሁለት ሃሳብ ለሚወላውል ሰው እምነት አይሰራለትም፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። የያዕቆብ መልእክት 1፡6-8

የእምነት አለም ነፍስህን ለማዳን ከመያዝ ይልቅ በእግዚአብሄር እጅ ላይ የምትጥልበት የውርርድ አለም ነው፡፡

ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። የማቴዎስ ወንጌል 16፡25

 1. የእምነት አለም የክብር አለም ነው

የእምነት አለም እግዚአብሄር ትክክል ነው ብሎ ለእግዚአብሄር ቃል እውቅና መስጠት ነው፡፡ የእምነት አለም ቃሉን በመስማትና በመታዘዝ ለእግዚአብሄር እውቅና መስጠት ነው፡፡ የእምነት አለም የሚታየውን ባለማየት የማይታየውን በማየት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት ነው፡፡ የእምነት አለም እግዚአብሄርን ማክበር ነው፡፡ የእምነት አለም የተፈጠሩበትን አላማ በመፈፀም ከእግዚአብሄር ጋር የመክበር አለም ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #ደስታ #ሰላም #እርካታ #ክብር #ገድል #ነፃነት #ሞገስ #ሃይል #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእግዚአብሔር እንጂ በሁኔታ አንታመንም

silver+refining.png

ብዙ ሰዎች ሁኔታዎች እየጨለሙ ሲሄዱ እምነታቸው የሚጠፋ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን እምነት ከሁኔታ ጋር አይገናኝም፡፡ እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ እምነት የሚወሰንው በእግዚአብሄር ፈቃድ እንጂ በሁኔታ አይደለም፡፡ እምነት የሚሄደው ከእግዚአብሄር ቃል ሃሳብ እንጂ ከሁኔታ ጋር አይደለም፡፡

ሁኔታዎች እንዳመንነው ሳይሆነ ካመነንው ከእግዚአብሄር ቃል የተቃረነ ሲመስል እምነታችን ከመጥፋት ግን እየጠራ ይሄዳል እንጂ አይጠፋም፡፡ ሁኔታዎች ሁሉ ካመንነው ተቃራኒውን ሲናገሩ እምነታችን ሲፈተን እየጠራ ይሄዳል፡፡

በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡6-7

ብዙ ጊዜ ፀሎታችን ወዲያው ሲመለስ እምነታችን አያደገ ይመስለናል፡፡ የፀሎታችን መልሰ የዘገየ ሲመስለን ደግሞ እምነታቸን እየደከመ ይመስለናል፡፡ ሁኔታዎች እንደፈለግናቸው ሲሄዱ እምነታእን የሚያድግ ሁኔታዎች እንደፈለግናቸው ካለሄዱ እምነታችን የሚቀጭጭ ይመስለናል፡፡ ፀሎታችን ያልተመለሰ ሲመስለን እምነታችን ውስጥ ወስጡን እምነታችን ያድጋል፡፡ ሁኔታዎች ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ እምነታችን እየጠራ ይሄዳል፡፡

ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ሲሸፍን የእምነታችን ብርሃን እየጨመረ ይደምቃል፡፡ ስለዚህ ፀሎታችን ያልተመለሰ ሲመስለን እምነታችን ግን እየጨመረ እየደመቀ ይበራል፡፡

ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። ትንቢተ ኢሳይያስ 60፡1-3

እንዲያውም ሁኔታዎች ከእግዚአብሄር ቃል በተቃራኒ እንደመሄድ እምነትን የሚያጠራውና ይበልጥ እግዚአብሄር ላይ እንድንደገፍ የሚያደርግ ሌላ ነገር የለም፡፡ እንደ ሁኔታዎች አለመከናወን እምነትን የሚያጠራው ነገር የለም፡፡ እንደ እምነት ፈተና እምነትን የከበረ አድርጎ የሚያጠራው ነገር የለም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መፈተን #መጥራት #ጨለማ #ብርሃን #እሳት ##መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል

your will

እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ነው የፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር አልሰሰተም ቁርጥ እርሱን አስመስሎ ነው የፈጠረው፡፡ እንደ አንዳንድ ሰዎች ከሆነ ሰውን በመልኩና በአምሳሉ መፍጠሩ ትክክል አልሰራም፡፡ በግልፅ ባይሆንም ሰው በመልኩና በአምሳሉ መፈጠሩን ባገኙት አጋጣሚ ይቃወማሉ፡፡ እነርሱ ቢሆኑ እንደማያደርጉት እርግጥ ነው፡፡

እንዲሁም ለሚያምን ሁሉ ይቻላል የሚለው አባባል የሚያስደነግጣቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነግር ግን ምንም ማድርግ አይቻልም፡፡

ሰው ለእግዚአብሄር ሁሉ ይቻላል ሲባል ይሻለዋል፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል ሲባል ያስፈራዋል፡፡

ነግር ግን እውነቱ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስብና የሚያስላስል ሰው እንደ እግዚአብሄር ያስባል ይባላል፡፡ እውነት ነው

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡

ስለአለበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ቃል የሚሰማ ሰው ሁሉ እምነት ከእግዚአብሄር ቃል ይመጣለታል፡፡

ለሚያምን ሰው ቃሉ ይቻላል የሚለው ነገር ሁሉ ይቻለዋል፡፡

ለእግዚአብሄ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ሁሉ ለሚያምን ሰው የሚሳነው ነገር አይኖርም፡፡

ለሚያም ሁሉ ይቻለዋል፡፡

ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። የማርቆስ ወንጌል 9፡23

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል !

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ብታምኚስ

1 (4).jpg

ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው። ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። የዮሐንስ ወንጌል 11፡39-40

የእግዚአብሄርን ክብር ማየት የማይፈልግ ሰው የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት መመዘኛ አለው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር በህይወታችን ለመለማመድ መመዘኛው ደግሞ ሊደረስበት የማይችል ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት የሚጠይቀው እምነት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለማስደሰትና የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ የለውም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ ቢኖር ኖሮ ያንን መንገድ እንከተል ነበር፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ሌላ መንገድ የለውም፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ብቸኛው መንገድ እምነት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ለማርታ አልነገርሁሽምን? የሚላት በፊትም የእግዚአብሄርን ክብር የምታይው ስታምኚ እንደሆነ ነግሬሻለሁ ዛሬም አልተለወጠም የእግዚአብሄን ክብር ማየት ከፈለግሽ ማመን ወሳኝ ነው እያላት ነው፡፡

የእግዚአብሄን ክብር እንድናይ የሚያስችለን እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17

የእግዚአብሄር ክብር ከሰዎች የራቀ እጅግ ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ቸር አምላክ ነው፡፡ ምድር በእግዚአብሄር ከብር ተሞልታለች፡፡

ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።  ኦሪት ዘኍልቍ 14፡21

የእግዚአብሄር ክብር የሚያይ ሰው በእግዚአብሄር ቃል መስማት እምነትን ያገኘ ሰው ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር በህይወቱ የሚለማመድ ሰው በእግዚአብሄር ቃል እምነትን ያገኘ ሰው ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብርና ሃይል በህይወቱ የሚለማድ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል የሚያምን ሰው ነው፡፡

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፡9

የእግዚአብሄርን ቃል የሰማ ሰው የእግዚአብሄርን ክብርና በጎነት በህይወቱ ይለማመዳል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት ይቻላል፡፡ የሞተ ሲነሳ ማየት ይቻላል፡፡ የደከመ ሲበረታ ማየት ይቻላል፡፡ የሌለን ወደመኖር ሲመጣ ማየት ይቻላል፡፡

ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡16-17

በእምነት የእግዚአብሄርን ክብር ማየት ይቻላል፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፡፡ ለማያምን የእግዚአብሄርን ክብር ሃይልና በጎነት ማየት ይቻለዋል፡፡

ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው። ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት። የዮሐንስ ወንጌል 11፡39-40

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ክብር #መልክ #አምሳል #ሃይል #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #በጎነት #መጠማት #መራብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በሰው የሚታመን

conscious.jpg

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። ትንቢተ ኤርምያስ 17፡5-6

እግዚአብሄር የፈጠረን በእርሱ እንድንደገፍ ነው፡፡ በእርሱ ስንደገፍ እግዚአብሄር ደስ ያሰኘዋል፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሄር መታመን ትተን በሰዎች መታመን ስንጀምር እግዚአብሄር ያዝናል፡፡ የተፈጠርነው በእግዚአብሄር እንድንደገፍ ስለሆነ በሰው ስንደገፍ አይሳካልንም፡፡

እንኳን ለሌላ ሰው መገደፊያ ሊሆን ይቅርና ሰው ራሱ በእግዚአብሄር ላይ መገደፍ አለበት፡፡ ሰው ለሌላ ለማንም ሰው መደፊያ ሊሆን አይችልም፡፡

ብዙ ሰዎች በእግዚአብሄር መታመን ይጀምራሉ፡፡ በእግዚአብሄር በመታመን እንድንጀምር ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር በመታመን እንድንጨርስ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡

በአስቸጋሪ ጊዜ እምነቱን ከእግዚአብሄር ላይ የማያነሳ ሰው ምስጉን ነው፡፡ በክፉ ጊዜ እምነቱን ከእግዚአብሄር ላይ የሚያነሳ ሰው እርጉም ነው፡፡

በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 24፡10

አስቸጋሪ ጊዜ አልፎ ደግሞ መልካም ዘመን ሲመጣ እምነቱ ከእግዚአብሄር ላይ ያነሳውና በሰው ላየ ያደረገው ሰው ይፀፀታል፡፡ መልካም ጊዜ መጥቶ የማይለወጥ የሚመስለው ነገር ሲለወጥ እምነቱን ከእግዚአብሄር ላይ እንስቶ ወደሰው ላይ ያደረገው ሰው ለሚያልፍ ነገር ምነው በእግዚአብሄር በታመንኩኝ ኖሮ ብሎ ይቆጫል፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ እምነቱን እግዚአብሄርን በሰው የለወጠ ሰው የእምነትን ገድል ደስታ አያገኘውም፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ እምነቱን ከእግዚአብሄር ላይ እንስቶ በሰው ላይ ያደረገ ሰው ለማይረባ ነገር እግዚአብሄርን ስለለወጠው ያፍራል፡፡

በአስቸጋሪ ጊዜ ሁሉ ከእግዚአብሄር ጋር የሙጥኝ ያለ ሰው በእግዚአብሄር በመታመኑና በማለፉ ብቻ እምነቱ ይጨምራል፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ እግዚአብሄርና ያመነና የጠበቀ ሰው እምነቱ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ጠርቶና ከብሮ ይወጣል፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ እምነቱን በሰው ያልለወጠው ሰው ደስታው ይበዛል፡፡

በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡6-7

እምነቱን ሲፈተን የወደቀ ሰው መልካም በመጣ ጊዜ አያይም፡፡ በሰው መደገፍን ያልናቀ ሰው በእግዚአብሄር በመደገፍ ያለውን ደስታ አያይም፡፡ በሰው በመደገፍ ክፉን ጊዜ ያሳለፈ ሰው ላነሰ ጥቅም ራሱን ስለሰጠ እውነተኛውን የእግዚአብሄርን በረከት አያየውም፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። ትንቢተ ኤርምያስ 17፡5-6

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ስጋለባሽ #መታመን #መደገፍ #ልብ #የሚመልስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ክንዱ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእምነትም ያልሆነ ሁሉ

8ccb4ec4225b290726ae9be975220ff4.jpg

የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23

ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናከብረው ቃሉን በመጠበቅና በቃሉ በመኖር ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሄርን የምናከብረውና የምናስደስተው በቃሉ በመኖር ፍሬ በማፍራት ብቻ ነው፡፡

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7-8

ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6

እግዚአብሄርን የምናስደስተው ከቃሉ በሆነ እምነት ኑሮ ብቻ ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17

ሰው የተፈጠረው ከቃሉ በሚገኝ እምነት እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእምነት ከእግዚአብሄር ጋር እንዲራመድ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእምነት በሚወስደው እርምጃ እግዚአብሄርን እንዲያስደስት ነው፡፡ ሰው በእምነት ሲኖር የተፈጠረበትን አላማ ግቡን ይመታል፡፡ ሰው ከእምነት ውጭ ሲኖር የተፈጠረበትን አላማ ይስተዋል፡፡ ከቃሉ በሚመጣ እምነት እንጂ በጥርጥር እግዚአብሄር አይከብርም፡፡ ጥርጥር የተፈጠሩበትን አላማን መሳት ነው፡፡ ጥርጥር አላማን መሳት ወይም ሃጢያት ነው፡፡

ስለዚህ ነው እምነት የሚገኝበትን የእግዚአብሄር ቃል ላይ የሙጥኝ ማለት ያለብንና በእምነት እርምጃን መውሰድ ያለብን፡፡

የሚጠራጠረው ግን ቢበላ በእምነት ስላልሆነ ተኮንኖአል፤ በእምነትም ያልሆነ ሁሉ ኃጢአት ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፡23

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ያለእምነት #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አላማ #መሳት #ሃጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

“Love Everyone Trust No One”

your will.jpgWe hear this kind of saying from time to time. And we sometimes say it or are tempted to say it, especially after we are betrayed by a very good friend, we fear to trust any other person again. We lose the confidence of trusting anyone for fear of hurt that comes from the past history of the unfaithfulness of others.

Nobody pretends that a trust issue is an easy subject of black and white. Trust isn’t an easy subject at all.

Human beings are created to be social beings. Humans are created to work together. Humans need a relationship with each other.

To relate to other trust is a must. Without trust, no one operates in life leave alone to be successful.

Actually, the success rate is determined in the art of trusting others. Successful people know who to trust and the amount of trust they have on different people. The more we trust others the more we relate to others. The more we relate to others, we extend our influence. The more we relate with others, we work together for a better achievement.

IT is obvious that we sometimes miss estimating others to trust heavily on them. But it is ok. We learn from that. If we fear to trust others we are stopped to live.

With all the risks attached to trusting others, trusting others is a must. We need an amount of trust to live and achieve in life. It is better to trust others and betrayed by them than not to trust anyone.

We have to have a room for betrayal. We have to be vulnerable.

The sayings love everyone and trust no one is opposed to each other as love always trusts.

It always protects, always trusts, always hopes, always perseveres. 1 Corinthians 13:7

We trust others in trusting God. The more we trust God, the more we trust people.

Jesus lived and ministered with Judas knowing that he was the one who betrays him.

For he knew who was going to betray him, and that was why he said not every one was clean. John 13:11

Trust must always be held with caution. But we have to train ourselves to trust others.

Abiy Wakuma Dinsa

For More Articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#Jesus #God #Trust #praise #livelife #betrayal #blessed #rejoice #faith #enjoylife #faithfulness #church #achievement #celebration #preaching #salvation #bible #countingthecost #abiy #facebook #abiywakuma #abiywakumadinsa

የእምነት ማጣት አስራ አንዱ ምልክቶች

conscious.jpgየእግዚአብሄር መንግስት የመንፈስ መንግስት ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምናደርገውን ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም፡፡ ለክርስትና ህይወት እምነት ወሳኝ ነው፡፡

እግዚአብሄር የሚሰራው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚጠቀመው እምነት ያለውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ለመስራት እምነት ያለውን ሰው ይፈልጋል፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን  ማስደሰት አይቻለም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ ምንም ታላቅ ሃይል ቢኖረውም ሰዎችን ለመርዳት ቢፈልግም እምነት ላልነበራቸው ሰዎች ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡

በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም። ማቴዎስ 13፡58

እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ ስለ ምን ትፈራላችሁ? ማቴዎስ 8:26

ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ማቴዎስ 17፡17

ሰው እግዚአብሄርን አላምንም ብሎ ላይናገር ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ስራው ይናገራል፡፡ እምነት ያለው ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች እንዳሉ ሁሉ የማያምን ሰው የሚያሳያቸው ምልከቶች አሉ፡፡

 1. የማያምን ሰው ጠማማ ነው

የማያምን ሰው ቅን ሊሆን አይችልም፡፡ የማያምን ሰው የዋህ ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን መንገድ ስለማይከተል የራሱን የጠማማነትን መንገድ ይከተላል፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ማቴዎስ 17፡17

 1. የማያምን ሰው ኩራተኛ ሰው ነው

የሚያምን ሰው የሚታወቀው በትህትናው ሲሆን የማያምን ሰው የሚታወቀው በትእቢቱ ነው፡፡ የማያምን ሰው በእግዚአብሄር ሳይሆን በራሱ ይተማመናል፡፡ የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ላይ ይደገፋል፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

 1. የማያምን ሰው ፈሪ ነው

የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ይደፍራል የማያምን ሰው ግን ፍርሃት አለበት፡፡ በእግዚአብሄር የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ልቡ ስለሚጠበቅ ያርፋል፡፡ የማያምን ሰው ግን ልቡ በምንም ላይ ስለማያርፍ ይፈራል፡፡ የማያምን ሰው የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ የሚያደርገው ከፍቅር ድፍረት ሳይሆን ከፍርሃት ነው፡፡ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ ስለ ምን ትፈራላችሁ? ማቴዎስ 8:26

 1. የማያምን ሰው ፍቅር ይጎድለዋል

የሚያምን ሰው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሄርን ስለሚያምን በፍቅር ለመኖር አይፈራም፡፡ የማምን ሰው ግን የእግዚአብሄርን ፍቅር ስለማያምን እና ስለማይቀበል ራሱም በፍቅር ለመኖር ራሱን አይሰጥም፡፡ የማምን ሰው ከፍቅር ይልቅ ሌላ የራሱን መንገድ ይፈልጋል፡፡

እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13

 1. የማያምን ሰው በምድር ጥበብ ይመላለሳል

ከእግዚአብሄር የሆነው ንፅህ ጥበብ የሚገኘው በእምነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ይህን ንፁህ ጥበብ በምድራዊ ተንኮል ይለውጠዋል፡፡

ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ያዕቆብ 3፡14-16

 1. የማያምን ሰው ይቸኩላል

የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ጊዜ ይተማመናል፡፡ የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን እርምጃ ይታገሳል፡፡ የማያምን ሰው ግን የእግዚአብሄርን ጊዜ ስለማያምነው ይቸኩላል፡፡

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።ምሳሌ 28፡20

 1. የማያምን ሰው ከሰው ጋር ይጣላል፡፡

የማያምን ሰው በረከቱን የያዘው ሰው ስለሚመስለው ከሰው ጋር ይጣላል፡፡ የማያምን ሰው ከሰው ስለሚጠብቅ በሰው ይሰናከላል፡፡ የመያምን ሰው መንፈሳዊውን አለም በእምነት ስለማያይ የጦር እቃው ስጋዊ ብቻ ነው፡፡ የሚያምን ሰው ግን ከእግዚአብሄር ስለሚጠብቅ በሰው አይሰናከልም፡፡ የሚያምን ሰው ከሰው ባሻገር መንፈሳዊውን አለም ስለሚያይ የጦር መሳሪያው ስጋዊ አይደለም፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡1-3

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡3-4

 1. የማያምን ሰው በጥበቡ በሃይሉና በብልጥግናው ይመካል

የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር ይመካል፡፡ የማያምን ሰው ግን የእግዚአብሄር ሃብት የእኔ ሃብት ነው ስለማይል መሰብሰብ ማከማቸት ይፈልጋል፡፡ የሚያምን ሰው እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም ስለሚል ማግበስበስ አያስፈልገውም፡፡ የማያምን ሰው ግን እረኛውን ስለማያምን እረኛ የሚያደርገው ጥበቡን ሃይሉንና ባለጠግነቱን ነው፡፡ የሚያምን ሰው የነገሮች ሁሉ ቁልፍ እግዚአብሄር ጋር እንጂ ጥበብ ፣ ሃይልና ባለጠግነት ጋር እንዳይደለ ያውቃል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 9፡23-24

 1. የማያምን ሰው ይጨነቃል

የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቅን ሲፈልግ እግዚአብሄር በምድር የሚያስፈልገው እንደሚያሟላለት ስለሚያምን አይጨነቅም፡፡ እግዚአብሄርን የማያምን ሰው ግን ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ በመጨነቅ እግዚአብሄር ይጨመርላችኋል ያለውን በመፈልግ ህይወቱን ያባክናል፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33

 1. የማያምን ሰው ያጉረመርማል

የሚያምን ሰው በእግዚአብሄር መልካምነት ስለሚተማመን ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡ የማያምን ሰው ደስታው በሁኔታዎች ብቻ ስለሆነ ያጉረመርማል፡፡ የሚያምን ሰው እግዚአብሄርን መልካምነት ስለሚያይ በእግዚአብሄር ላይ ጥያቄ የለውም፡፡

ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10

 1. የማያምን ሰው ይመኛል

የሚያምን ሰው ምንም እንዳልጎደለው ራሱን ያማጥናል፡፡ የሚያምን ሰው ጉድለቱን በሚሸፍን ድካምን በሚሞላ የእግዚአብሄር ፀጋ ስለሚተማመን አይመኝም፡፡ የማያምን ሰው ግን ሁሌ እግዚአብሄር ያልሰጠውን ነገር ይመኛል፡፡ የሚያምን ሰው ራሱን በሁኔታዎች ሁሉ ራሱን ያማጥናል፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጭንቀት #ፍርሃት #ፍቅር #ተንኮል #ጠማማነት #ኩራት #ቅን #እምነት #ተንኮል #ምኞት #ሰላም #ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በእምነቱ በሕይወት

conscious.jpgእነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

መፅሃፍ ቅዱስ በእምነት ስለሚኖር ሰውና በእምነት ስለማይኖር ሰው እያነፃፀረ ያስተምራል፡፡ ሰዎች በምድር ላይ ወይ በእምነት ነው የሚኖሩት ወይም ደግሞ በእምነት አይደለም የሚኖሩት፡፡

በእምንት ስለመኖር ጥቅም ሲናገር በህይወት ያኖራል ይላል፡፡ በህይወት መኖር ማለት በሁሉ ነገር ህያው መሆን ማለት እንጂ በስጋ አለመሞት ማለት ብቻ አይደለም፡፡

ለምሳሌ ኢየሱስ ያለው ህይወት አለው ሲል የዘላለም ህይወትን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ህይወትን ስለማጣጣም ይናገራል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በእርሱ የማያምን ህይወትን አያይም ሲል በስጋ ይሞታል ማለት ሳይሆን የእግዚአብሄርን ህይወት አላማ ይስተዋል ማለት ነው፡፡ ህይወትን አያይም ማለት እግዚአብሄር በህይወት ውስጥ ያስቀመጠውን በረከት አያገኘውም ማለት ነው፡፡ ህይወትን አያይም ማለት የህይወትን እውነተኛ መልክና ጣእም አያገኘውም ማለት ነው፡፡

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በደስታ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች ለመደሰት የሆነ ነገር አይጠብቁም፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች እነርሱን ለማስደሰት ጌታ ብቻውን በቂ ነው፡፡ በእምነት የሚኖሩ ሰዎች ለመደሰት ሌላ ሌላ ነገር መጨመር የለባቸውም፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡4

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከጭንቀት በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖር ሰው ለእርሱ የሚያስብለት እንዳለ ስለሚያምን ጭንቀት ከህይወቱ ይሞታል፡፡

እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በሃይል ይኖራል ማለት ነው፡፡

ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ዕብራውያን 11፡11

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በሃይል ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖረ ሰው እግዚአብሄር እንዲሰራው የሰጠውን ስራ ለመስራት ምንም ሃይል አይጎድልበትም፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ስኬት ይኖራል ማለት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ በእግዚአብሄ ቃል እምነት የሚኖር ሰው በስራው ሁሉ ፍሬያማ ይሆናል፡፡

ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡2-3

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል ማለት ነው፡፡

ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል” ዮሐንስ 10፡1

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከጠላት ጥቃት በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8-9

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በክንውን ደስታ ይኖራል ማለት ነው፡፡

እኔም መልሼ፦። የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው። ነህምያ 2፡20

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በነፃነት ይኖራል ማለት ነው፡፡

በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃነት አወጣን እንግዲህ ፀንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ! ገላትያ 5:1

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከሁኔታዎች በላይ ይኖራል ማለት ነው፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በእርካታ ይኖራል ማለት ነው፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡11-12

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በድፍረት ይኖራል ማለት ነው፡፡

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም። ዕብራውያን 10፡38-39

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በፍሬያማነት ይኖራል ማለት ነው፡፡ በእምነት የሚኖር ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በየዋህነት በማድረግ ፍሬን ያፈራል፡፡

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሃንስ 15፡15

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ ከመቋጠር ይወጣል ፣ ረጋ ብሎ በስፋት ካለስጋት ይኖራል ማለት ነው፡፡

ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ። መዝሙር 18፡19

አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። መዝሙር 18፡36

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ አያፍርም አይዋረድም በእረፍት ይኖራል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም። ኢሳያስ 28፡16

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል ሲል ጻድቅ ግን በእምነቱ በአሸናፊነት ይኖራል ማለት ነው፡፡

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ስፋት #እርካታ #ፍሬያማነት #ክንውን #አሸናፊነት #በጎነት #ቅን #እምነት #ፅድቅ #ደስታ #ሰላም #ኢየሱስ #ጌታ #ሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ

conscious.jpgእምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡19

እምነት ታላቅ የክርስትና ሃይል ነው፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፡፡ እምነት እጅግ ታላቅ ሃየለን ይሰጠናል፡፡ እምነት የማያስችለን ነገር የለም፡፡

ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23

ነገር ግን ሃይል ካልመቆጣጠሪያው መንገድ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ካለመቆጣጠሪያ መሳሪያው ብቻውን አደገኛ ነው፡፡ እምነትና በጎ ህሊና ይኑርህ የሚለው ለዚህም ነው፡፡

ምክኒያቱም እምነት እንደ መርከብ ግዙፍና ብዙ ስራዎችን ሊሰራ የሚችል ነገር ነው፡፡ በጎ ህሊና ደግሞ ያንን ታላቅ መርከብ ሊቆጣጠር የሚችልና ወደሚፈለግበት ቦታ ሊያደርስ የሚችል መሪው ነው፡፡

ታላቅ መርከብ መሪ ባይኖረው እጅግ አደገኛ እንደሆነ ሁሉ እምነት ያለበጎ ህሊና አደገኛ ነው፡፡

በታላቅ እምነቱ የታወቀው ሃዋሪያው ጳውሎስ በእምነቱ ብቻ ሳይሆን በህሊናውም ንፅህና ይታወቅ ነበር፡፡ ሃዋሪያው እምነቱን በእምነቱ መልካም ገድልን መጋደል ብቻ ሳይሆን ህሊናውን ንጹህ ለማድረግ ይተጋ ነበር፡፡

ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡3

የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡5

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ህሊና #ተጋድሎ #ንፅህና #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ

trust.jpgበእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። ኤርምያስ 17፡7-8

በእግዚአብሄር የታመኑ ሰዎች አይታወኩም፡፡

በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። መዝሙር 125፡1

በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው አያፍርም፡፡

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም። ኢሳያስ 28፡16

እግዚአብሄርን የሚያውቁት በእርሱ ይታመናሉ፡፡

ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። መዝሙር 9፡10

ስለዚህ በእግዚአብሄር ታመኑ እርሱ ረዳት ነው፡፡

የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው። መዝሙር 62፡8

በእግዚአብሄር የሚታመን ምስጉን ነው፡፡

የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው። መዝሙር 84፡12

በእግዚአብሄር የታመነ ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ የሚያስፈነድቀውም የሚያስፈራውም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር በሁሉ ፍሬያማ እንደሆነ በእግዚአብሄር የታመነ በምንም ሁኔታ ውስጥ ፍሬያማ ነው፡፡ በእግዚአብሄር እንደሚታመን ሰው ፍሬያማ የተሳካለትና የተከናወነለት ሰው የለም፡፡

በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። ኤርምያስ 17፡7-8

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ

grace teaching.jpgበልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። መዝሙር 91፡1

በዚህ ለህይወታችን ምንም ማስተማመኛ በሌለው አለም በአግዚአብሄር ጥበቃ እንደመታመን የሚያሳርፍ ነገር የለም፡፡ አለ ያልነው ሰው በድንገት ሲወሰድ ደጋግመን አይተናል፡፡ ይሞታል ብለን በአእምሮዋችን ያላሰብነው ሰው ሲሞት አይተናል፡፡

ያልታሰቡ አደጋዎችን ስናይ እኔስ መድህኔ ምንድነው ብለን እንጠይቃለን፡፡ ለህይወታችን ብቸኛ ጥበቃ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እስካሁንም ችለን ራሳችንን አልጠበቅንም፡፡ እስካሁንም የጠበቀን እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡

ካላየነውና ካየነው ክፋት እስጥሎና ከልሎ እዚህ አድርሶናል፡፡ እግዚአብሄር ሳናየው ያስመለጠንን አደጋ ሁሉ ብናይ ከማሰብና ከመያዝ አቅማችን በላይ ስለሆነ አእምሮዋችን ጤነኛ የሚሆን አይመስለኝም፡፡

ከክፉ አደጋ ተጠብቀን በህይወት በመኖራችን ብቻ እግዚአብሄር ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን ህያው መሆናችን መተንፈሳችን ብቻ ይበቃል፡፡

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ። መዝሙር 150፡6

አንዳንድ አደጋዎችን ስንሰማ ከአልጋችን ተነሰተን እንደገና ህይወትን መጋፈጥ ይፈታተነናል፡፡ ስለ ደህንነታችን ስናስብ እንደገና መኖር እንፈራለን፡፡ እግዚአብሄርን ካላሰብን በስተቀር እንደገና ለመኖር አቅም እናጣለን፡፡

በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ። እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። መዝሙር 91፡1-8

የትኛውም ብልጠታችን ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አይጠብቀንም፡፡ የትኛውም እውቀታችን ከአዳኝ ወጥመድና ከሚያስደነገጥ ነገር አያድነንም፡፡

ያለው ብቸኛ አማራጭ እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ያለው አማራጭ በልኡል መጠጊያ መኖር ነው፡፡ አንዱና ብቻኛው አማራጭ ከላባዎቹ በታች በጋረደን በእግዚአብሄር ክንፎች መተማመን ነው፡፡

በእግዚአብሄር ካልታመንን የምንታመንበት ምንም ነገር አይቀርልንም፡፡ ሁሉን በሚችል አምላክ መታመን አማራጭ አይደለም፡፡ በምድር ላይ ስለደህንነታችን ሁሉን በሚችል በእግዚአብሄር መታመን ግዴታ ነው፡፡

ትእዛዙ በፍፁም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን ነው፡፡ በፍፁም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን። ምሳሌ 3፡5

ትእዛዙ በእግዚአብሄር ታመን በምድር ተቀመጥ ታምነህ ተሰማራ ነው፡፡

በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። መዝሙር 37፡3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነትና ጥርጥር

fear vs faith 22.jpgኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

ለእግዚአብሄር አንድን ነገር ማድረግ ከፈለግን በእምነት መሆን አለበት፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንገናኘው በእምነት ነው፡፡ ከእግዚአብሄር የምንቀበለው በእምነት ነው፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ጥርጥር ደግሞ እግዚአብሄርን አለማመን ነው፡፡ ጥርጥር የእምነት ተቃራኒ ነው፡፡ ጥርጥር የእምነት ጠላት ነው፡፡ ጥርጥር እጃችንን ዘርግተን አንድን ነገር ከእግዚአብሄር በእምነት እንዳንቀበል እጃችንን እንድንሰበስብ ይፈታተነናል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲያምን የእምነት ጠላት የሆነውን ጥርጥርን መዋጋት አለበት፡፡

እምነት የሚመጣው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ሰው አንድን ነገር ሲያምን ያመነው ነገር እስኪሆን ደርስ በእምነቱ ፀንቶ መጠበቅ አለበት፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

የሚታየው ነገር ሁሉ የሚመጣው ከማይታየው አለም ነው፡፡ ሰው በማይታየው አለም ውስጥ በእምነት ያየው ነገር ወደሚታየው ግኡዙ አለም እስኪመጣ መታገስ አለበት፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡1፣3

ሰው አንድን ነገር ሲያምን ያመነው ነገር ወደ ገሃዱ አለም አሰኪገለጥ ድረስ በጥርጥር ይፈተናል፡፡ ሰው ያመነው ነገር ትክክል እንዳይደለና እንዲተወው ጥርጥር ይፈትነዋል፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የሚከፍለው በእምነቱ ብቻ ነው፡፡ የሚጠራጠር ሰው ከእግዚአብሄር አይቀበለም፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

መጠራጠር የለብንም ማለት ግን የጥርጥር ሃሳብ ወደ አእመሮዋችን አይመጣም ማለት አይደለም፡፡ ሰው ያመነው ነገር እንደማይሆን ሰይጣን የጥርጥርን ሃሳብ ይልካል፡፡ ሰው የጥርጥርን ሃሳብ ከተቃወመው በእምነቱ ከእግዚአብሄር ብድራትን ይቀበላል፡፡ ሰው ግን የጥርጥርን ሃሳብ ከተቀበለው እምነቱ ያለፍሬ ይቀራል፡፡

ሰው መጀመሪያ ማመኑ ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰው ሲያምን ጥርጥርን በሚገባ መቃወም አለበት፡፡

ጴጥሮስ የጌታን ቃል እምኖ በውሃ ላይ መራመድ ጀምሮ ነበር ፡፡ ነገር ግን ጥርጥር በውሃ ላይ መራመድ የጀመረውን ጴጥሮስን አሰመጠው፡፡ ጴጥሮስ አይኑን ና ከሚለው ከኢየሱስ ቃል ላይ እንስቶ ወደወጀቡ ላይ ሲያደርግ መስመጥ ጀመረ፡፡

እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ማቴዎስ 14፡29-30

ጥርጥርን የምንዋጋው የእግዚአብሄርን ቃል በቀጣይነት በመስማት በማሰላሰልና በመናገር ነው፡፡ ጥርጥርን የምንዋጋው ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ የሆነን ነገር ባለመስማትና ባለመከተል ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነትና ፍርሃት

fear vs faith 22.jpgከእግዚአብሄር ጋር ላለን የሰመረ ግንኙነት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

አንዱ የእምነት ጠላት ደግሞ ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው ከእምነት ጉዞ ልናቋርጥ እንችላለን፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ሳናከናውን እንቀራለን፡፡

እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እንድንሰማና እንድንከተል ያደርጋል፡፡ ፍርሃት ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳንሰማና እንዳንከተል ያደርጋል፡፡

እምነት አለን ማለት ግን ከፍርሃት ስሜት ነፃ እንሆናለን ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት የማይኖረን ወደሰማይ ስንሄድ ብቻ ነው፡፡ በምድር ላይ ይብዛም ይነስም የፍርሃት ስሜት አለ፡፡

የፍርሃት ስሜት አለን ማለት ግን እምነት የለንም ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም የማመን እድሉ አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም እምነት አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት  እምነታችንን ፍርሃት እየተፈታተነው ነው ማለት ነው፡፡ ፍርሃት የሚመጣው የሚያምንን ሰው ለማስቆም ነው፡፡

ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ በከንቱ ይደክማል፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ ስኬታማ አይደለም፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ አይከናወንለትም፡፡

የፍርሃትን ስሜት ካልተከተልነው በእምነታችን አሸናፊ እንሆናለን፡፡ ደፋር የሚባለው ሰው ምንም የፍርሃት ስሜት የማይሰማው ሰው አይደለም፡፡ ደፋር የሚባለው እንዲያውም በጣም የሚያስፈራ ነገር ውስጥ የሚያልፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር የፍርሃት ስሜት እንዳይገዛው የሚያደርግ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው በፍርሃት ስሜት የማይሸነፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር ስው የፍርሃት ስሜት የማይወሰደ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው ፍርሃትን ሰምቶ ከእምነት ጊዞ የማይቆም ነው፡፡

እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡35

ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡36

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ፍርሃት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት

የእምነት ክህደት

walk by faith 22.jpgበአለም ላይ የተለያዩ ድምፆች አሉ፡፡ በአለም ላይ መስማት ያለብንና መስማት የሌለብን ድምፆች አሉ፡፡ በአለም ላይ ልንከተለው የሚገባና ልንከተለው የማይገባ ሁኔታ አለ፡፡

ከእግዚአብሄር ቃል የሚገኝ የእግዚአብሄር ድምፅ አለ፡፡ ሰው ያንን የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ እምነት ይመጣለታል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ወደ እግዚአብሄር ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ሊቀበል ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር ሊረዳ ይችላል፡፡ ሰው የማይታየውን ማየት የሚችለው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡

በአለም ላይ የእግዚአብሄርን ቃል የሚቃረን ሌላ ድምፅ ደግሞ አለ፡፡

ሰይጣን የውሸት አባት ነው፡፡ ሰይጣን በልባችን ያለውን በእግዚአብሄር ቃል በኩል ያገኘነውን እውነት ለመስረቅ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሄር ቃል ያገኘነውን እውነት በውሸት ሊያስጥለን ይመጣል፡፡ ሰይጣን እውነቱን ትተን ውሸቱን እንድናምን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን የማይታየውን ማየት ትተን የሚታየውን በማየት ከእግዚአብሄር በረከት እንድንወድቅ ይፈልጋል፡፡

ሁኔታ የእግዚአብሄርን ቃል ሊቃረን ይችላል፡፡ የሚታየው ነገር ከማይታየው ነገር ተቃራኒ ሊሆን ይችላል፡፡ የአካባቢያችን ሁኔታ ከምናውቀው ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ ሊሆን ይችላል፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ስለዚህ ነው የሚታየው ከማይታየው ከእግዚአብሄር ፈቃድ ሲቃረን የሚታየውን ማየት ትትን የማይታየው የእግዚአብሄ ቃል ላይ ማተኮር ያለብን፡፡

የሚታየው የሚመጣው ከማይታየው ነው፡፡ የሚታየውን የሚገዛው የማይታየው ነው፡፡ የሚታየው ለማይታየውን ይገዛል፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

የሚታየው ቋሚ አይደለም፡፡ የሚታየው ተለዋዋጭ ነው፡፡ የሚታየው ጊዜያዊ ነው፡፡ የሚታየው ይለወጣል፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የሚታየው ለማይታየው ፈቃድ ይገዛል፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ስኬታማ ለመሆን የማይታየውን እንጂ የሚታየውን አንመልከት፡፡ በእግዚአብሄር ስራ ፍሬያማ ለመሆን በማይታየውን ላይ እንጂ የሚታየው ላይ አናተኩር፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት በማይታየው እንጂ በሚታየው ነገር አንወሰድ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሰምር የሚታየውን ትተን የማይታየውን እንመልከት፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ማየት #መስማት #የሚታየው #የማይታየው #እንመልከት #አንመልከት #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስም

walk by faith 11.jpg

እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7

እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ መቀበል ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን እንደቃሉ መጠበቅ ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን እንደቃሉ መያዝ ነው፡፡ እምነት እንደቃሉ ማሰብ እንደቃሉ መናገርና እንደቃሉ ማድረግ ነው፡፡

እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በአይን አይታይም፡፡ በአይን የማይታየውን እግዚአብሄርን ለማየት እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን የማየታየውን የእግዚአብሄርን መንግስት ለማየት እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን የማይታየው የእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ለመግባት እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን በማይታየው በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ለመስራት እምነት ይጠይቃል፡፡

ወደ ማይታየው እግዚአብሄር ለመቅረብ እምነት ይጠይቃል፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቀርበን እንድን ነገር ለማስፈፀም እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን ከማይታየው ከእግዚአብሄር ለመቀበል እምነት ይጠይቃል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ እግዞአብሄን የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡

የማይታየውን አለም እይታ የምናገኘው በእግዚአብሄር ቃል በኩል ነው፡፡ የማይታየውን አለም ለማየት ብርሃን የምናገኘው እግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

እምነት በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ያለውን ማየት ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለው ሁኔታ አለማየት ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ያለውን እውነት መከተል ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለውን ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ የሚናገረውን ሁኔታን አለመከተል ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ያለውን እውነት መቀበል ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለውን ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ የሚናገረውን ሁኔታን አለመቀበል ነው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማየት ###ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም

faith vs pride.jpgእምነትና ቅንነት አብረው የሚሄዱ ተመሳሳይ ነገሮች ናቸው፡፡ እምነትና ኩራት አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

እምነትና ኩራት አብረው የሚሄዱ ነገሮች አይደሉም፡፡ እምነት ካለ ትምክህት አይኖርም፡፡ ትምክህት ካለ እምነት አይኖርም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካመነ በምንም ነገር አይመካም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ለማመን በራስ መተማመንን መጣል አለበት፡፡ ሰው በራሱ ከተማመነ እግዚአብሄርን ሊያምን አይችልም፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ለማመን ለእግዚአብሄር ቃል ቅን መሆን አለበት፡፡ ሰው በእግዚአብሄርን ለማመን የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ በየዋህነት መቀበል አለበት፡፡

ሄዋን ቅንነትዋ ሲበላሽ እምነትዋን አጣች፡፡ ሄዋን ቅንነትዋን እስከጠበቀች ድረስ እምነትዋን ጠብቃ ነበር፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ይጠራጠራል፡፡ ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ማቴዎስ 25፡24

እምነት ትህትናን ይጠይቃል፡፡ ትሁት የሆነና ራሱን የሚያዋርድ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን አምኖ የሚጠብቀው፡፡ ትእቢተኛ የሆነና በራሱ የሚመካ ሰው እግዚአብሄርን መጠበቅ አይችልም፡፡ በራሱ ለሚመካ ሰው እግዚአብሄርን ማመን ሞኝነት ነው፡፡ እኔ አውቃለሁ የሚል ሰው እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡

ሰው እምነቱን ለመጠበቅ ለእግዚአብሄር ያለውን ቅንነት መጠበቅ አለበት፡፡ ሰው እምነቱን ላለማጣት ለእግዚአብሄር ቃል ያለውን ቅናት ማጣት የለበትም፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ እግዚአብሄርን ይጠራጠራል፡፡ የሰው ነፍሱ ከኮራ እግዚአብሄርን ማመን ያቅተዋል፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ በእግዚአብሄር ሳይሆን በራሱ መደገፍ ይጀምራል፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ቅንነት #ኰርታለች #ቅን #እምነት #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በልቡ ሳይጠራጠር

doubt.jpgእውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23

ጥርጥር የክርስትና የእምነት ጉዞ ህይወት ጠር ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል መጠራጠር ከጀመረና እስከ መጨረሻው በእምነት ውስጥ የተዘጋጀለትን በረከት ያጣዋል፡፡

ሰው ስለ እምነቱ ከእግዚአብሄር ዘንድ ሽልማት ይቀበላል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ሰው ወይ ያምናል ወይ ይጠራጠራል፡፡ 50% አምኗል ተብሎ 50% ሽልማት የሚሸለም ሰው የለም፡፡ ከተጠራጠረ ተጠራጠረ 0% ሽልማት ያገኛል ካመነ አመነ 100% ሽልማት ያገኛል፡፡ ስለዚህ ነው ልባችንን ከየትኛውም አይነት ጥርጥር አጥብቀን መጠበቅ ያለብን፡፡

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

ሰው ካመነ በኋላ ጥርጥርን ላለማስተናገድ መጋደል አለበት፡፡ ሰው ጥርጥርምን ለማስተናገድ ቸልተኛ ከሆነና መንገድ ከከፈተ ሳያውቅው በእምነት ምክኒያት ያገኘውን ወይም ማግኘት የሚገባውን በረከት ያጣዋል፡፡

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል እንደመሆኑ መጠን ጥርጥር የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ የሆነን ነገር በመስማት  ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ የሚናገረውን ሁኔታን ከሰማን እንጠራጠራለን፡፡

ጴጥሮስ ና የሚለውን ቃል ሰምቶ በውሃ ላይ መራመድ ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የነፋሱን ሃይል አይቶ ተጠራጠረ እምነቱን አጣው፡፡

ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው። ማቴዎስ 14፡30-31

ሰው የሰማውንም የእግዚአብሄርን ቃል ትቶ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ የሚናገሩትን የሰዎችን ቃል ከሰማ ጥርጥርን ያስተናግዳል፡፡

የምኵራብ አለቃው ስለልጁ ፈውስ ከአዚየሱስ ጋረ እየሄደ ሰዎች ከፈውስ ተቃራኒ ነገር ነገሩት፡፡ ኢየሱስን እምነቱ እንዳይጠፋ መስማት ያለበትን የእርሱን ቃልና መስማት የሌለበትን የጥርጥር ቃል እንደገና አስታወሰው፡፡

እርሱም ገና ሲናገር ከምኵራብ አለቃው ቤት ዘንድ የመጡት፦ ልጅህ ሞታለች፤ ስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ? አሉት። ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡35-36

እምነታችን እንዲሰራ በሰማነው በእግዚአብሄር ቃል ላይ መቆም አለብን፡፡ ሁኔታዎች ባይመሰክሩ እንኳን በሰማነው በእግዚአብሄር ቃል ላይ መቆም አለብን፡፡ ሰዎች የተለየ ሃሳብ ቢኖራቸው እንኳን  መጀመሪያ በሰማነው በእግዚአብሄር ቃል ላይ መቆማችን እግዚአብሄር በእምነት ውስጥ ያስቀመጠውን ሽልማታችንን መውሰድ ያስችለናል፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእምነት ያለህ አትበል

faith comes.jpgእግዚአብሄር ከሰው ጋር ግንኙነት ማድረግ ስለፈለገ ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ ሰው በሃጢያት ምክንያት ከእግዚአብሄር ከተለያየም በኋላ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲገናኝ በዘመናት ሁሉ እግዚአብሄር ሁኔታዎችን ሲያመቻች ቆይቷል፡፡

እግዚአብሄር አሁንም ከሰው ጋር ግንኙነት ማድረግ ስለሚፈልግ ከእርሱ ጋር የሚገናኝበትን መንገድ አዘጋጅቷል፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት የሚችለው በእምነት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚደርሰው በእምነት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚያገኘው በእምነት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጠይቆ የሚቀበለው በእምነት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ተግባብቶ የሚኖረው በእምነት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የሚሰማውና የሚታዘዘው በእምነት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚራመደው በእምነት ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነትን ለማግኘት ሰው እጅግ የተመረቀ ሰው መሆን የለበትም፡፡ እምነትን እንዲኖረው ሰው ቅዱስ መሆን አይጠበቅበትም፡፡ ሰው እምነት እንዲኖረው ሰማእት መሆን የለበትም፡፡

እምነት እጅግ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ አይደለም፡፡ እምነት አንዳንድ ሰዎች ብቻ በድንገት የሚያገኙት እድል አይደለም፡፡ እምነት ለጥቂት ለተመረጡ ሰዎች የሚመጣ ገጠመኝ አይደለም፡፡ እምነት እጅግ ጥቂት ሰዎች ተመራምረው የሚደርሱበት ረቂቅ ነገር አይደለም፡፡

እምነት የሚመጣው ከመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል መስማት የሚችል ሰው ሁሉ እምነት ሊኖረው ይችላል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያነብ ሰው ሁሉ እምነት ሊመጣለት ይችላል፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሚሰማ ማንኛውም ሰው እምነት ይመጣለታል፡፡

ሰው ዝም ብሎ እምነትን መመኘት የለበትም፡፡ ሰው እምነት እንዲኖረው ቁጭ ብሎ መጓጓት የለበትም፡፡ ሰው እምነት ያላቸውን ሰዎች ተመልክቶ በተስፋ መቁረጥ መቋመጥ የለበትም፡፡ ሰው እኔ እንግዲህ እምነትን ከየት አመጣዋለሁ ማለት የለበትም፡፡

ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ሮሜ 10፡6-8

እምነት ቀርቧል፡፡ እምነት በማንም ሰው ይገኛል፡፡ እምነት ለማንም ሰው የተሰወረ አይደለም፡፡ እምነት ከማንም ሰው ሩቅ አይደለም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን የማገኝበት እምነት ከየት ይገኛል ማለት አይችልም፡፡ ሰው የእምነት ያለህ እንዳይል እምነት እንዴት እንደሚገኝ በመፅሃፍ ቅዱስ ተፅፏል፡፡

እምነት የሚገኘው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል አንብብ እምነት ይሆንልሃል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስማ የእምነት ሰው ትሆናለህ፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነት ተስፋ አይደለም!

Dollarphotoclub_67194567-600x300.jpgእምነት በተፈጥሮአዊው አለም የማይታየውን ማየት ነው፡፡ እምነት መንፈሳዊውን አለም ማየት መቻል ነው፡፡ እምነት ልእለ-ተፈጥሮአዊውን አለም ማየት ነው፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር የሚያስረግጥ ነገር ነው፡፡ እምነት የተስፋ ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት ተስፋችን እንደሚፈጸም ማረጋጫ ነው፡፡

እምነት ተስፋ ማድረግ ብቻ አይደለም፡፡ እምነት ተስፋ የምናደርገውን ነገር ማስረጃ ነው፡፡ እምነት ተስፋችን እንደሚፈፀም ማረጋገጫው ነው፡፡

እምነትና ተስፋ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ እውነት ነው ለእምነት ተስፋ ያስፈልጋል፡፡ ተስፋ ብቻ ግን አምነት አይደለም፡፡ ተስፋ እና የተስፋ ማረጋገጫው በአንድነት እምነት ይባላል፡፡

ተስፋ አንድ ነገር ወደፊት እንደሚሆን መጠበቅ ነው፡፡

በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ሮሜ 8፡24-25

ተስፋ አስፈላጊ ነው፡፡ ካለ ተስፋ እምነት አይኖርም፡፡ ተስፋ አለን ማለት ግን እምነት አለን ማለት አይደለም፡፡ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ይላል፡፡ . . . በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24

አንድ ሰው ወደፊት እንደሚፈወስ ተስፋ አለኝ ካለ ተስፋ አለው ማለት ብቻ ነው፡፡ ተስፋ ብቻ ለመፈወስ አይበቃም፡፡ ተስፋና የተስፋው ማረጋገጫ የሆነው እምነት ሲኖረን እንፈውሳለን፡፡ ለመፈወስ ተስፋ ብቻ ሳይሆን እምነት ይጠይቃል፡፡

ሰው እምነት ሲኖረው ይፈወሳል፡፡ ሰው ግን በተስፋ ብቻ አይፈወስም፡፡ ተስፋው ማረጋገጫ ካለው ይፈወሳል፡፡ ተስፋ ማረጋገጫው እምነት ከሌለው አይፈውስም፡፡

ሰው እግዚአብሄር በኢየሱስ የሰራለትን ለፈውሱ የተከፈለለትን ክፍያ ከእግዚአብሄር ቃል ሲረዳ ይፈወሳል፡፡ ሰው በኢየሱስ መገረፍ ቁስል እንደተፈወሰ ሲያምን ተስፋ አያደርግም፡፡ ሰው በኢየሱስ መገረፍ ቁስል እንደተፈወሰ ሲያምን እምነቱን ይቀበላል፡፡

ሰው እንደተፈወሰ ሲያምን ተስፋ ማድረጉን ያቆማል፡፡ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ይላል መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ የሚያየውን ተስፋ የሚያደርግ ሰው የለም፡፡ የሚያየውን ያመሰግንበታል ይጠቀምበታል እንጂ የሚያየውን ማንም ተስፋ አያደርገውም፡፡

እንደዚሁ በመገረፉ ቁስል እንደተፈወሰ ያመነ ሰው ተስፋ አያደርግም፡፡ ምክኒያቱ ተስፋ ሊመጣም ላይመጣም ይችላል፡፡ በመገረፉ ቁስል የተፈወሰ ሰው እግዚአብሄርን ስለፈውሱ ያመሰግናል እንደተፈወሰ ሰው ይኖራል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

መጽናት ለምን

Perseverance-781x520.jpgየእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ዕብራውያን 10፡36

የምናየው ነገር ሁሉ የመጣው ከማይታየው ነገር ነው፡፡ የምናየው ነገር ሁሉ የማይታየው አለም ውስጥ የነበረ ነው፡፡ እምነትም የማይታየው አለም ውስጥ ያለውን ነገር አይቶ ወደሚታየው አለም እስኪመጣ መጠበቅ ነው፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

የእግዚአብሄ ፈቃድ ከመንፈሳዊው አለም ወደሚታየው አለም ከመምጣቱ በፊት የእኛን እምነትና ትግስት ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ነው ስትፀልዩ እንደተቀበላችሁ እመኑ ይሆንላችኋል የሚለው፡፡ የሚታየው አለም ላይ ከመሆኑ በፊት ማመን ይጠይቃል፡፡

ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ሉቃስ 11፡24

የእግዚአብሄር ፈቃድ ከማይታየው አለም ወደሚታየው አለም እስኪመጣ መጽናት ይጠይቃል፡፡ የእምነትን እርምጃ ከተራመድን በኋላ ውጤት እስከምናገኝ ድረስ መታገስ ወሳኝ ነው፡፡

በእምነት ጉዞ በተፈጥሮአዊ አይን የሚታየውን ባለማየት በመንፈሳዊ አይን የሚታየውን ደግሞ በማየት እንደሚቀበሉት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17

እግዚአብሄር ተናገረን የእግዚአብሄን ፈቃድ አገኘን ማለት አካባቢ ሁሉ ከዚያ ቃል ጋር ከመቀጽበት ይስማማል ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውን የአካባቢ ሁኔታ ተቃራኒውን ሊናገር ይችላል፡፡ ስሜታችን ከእግዚአብሄር ፈቃድ ተቃራኒውን ሊያሰማን ይችላል፡፡

ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። መዝሙር 43፡5

እግዚአብሄር የተናገረንና የምናልፍበት ነገር እጅግ ሊለያይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ነው ሁኔታዎች እንዳያጠራጥሩን በልቡ ሳይጠራጠር ብሎ መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡ ስሜታችንን ከተከተልን እንጠራጠራለን፡፡ ሁኔታውን ካየን እንጠራጠራለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሰምቶ በውሃ ላይ ይራመድ የጀመረው ጴጥሮስ መስመጥ የጀመረው የአካባቢውን ሁኔታ አይቶ ስለተቀበለው እና ስለፈራ ነው፡፡

ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ማቴዎስ 14፡30

ሁኔታም ሆነ ስሜታችን ሁለቱም ድንበራቸው የሚታየው አለም ብቻ ስለሆነና አቅማቸው ስለማይፈቅድ ስለእምነት እና ስለ እግዚአብሄር ፈቃድ ሊመሰክሩ አይችሉም፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23

የአካባቢያችን ሁኔታዎችና ስሜታችን ስለእግዚአብሄር ፈቃድ ሊመሰክሩ ብቁ አይደሉም፡፡ የአካባቢያችን ሁኔታዎችና ስሜታችን የምንታገሳቸው እንጂ ስለእምነት ነገር እውነተኛ ምስክሮች አይደሉም፡፡

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና የሚለው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነትና ስሜት

feeling_free.jpgእምነት በክርስትያን ህይወት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እንዲያውም ያለእምነት ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት አይቻልም፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻለም፡፡ ያለእምነት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገባ መኖር አይቻልም፡፡

ስሜት ደግሞ የአካባቢያችንን ሁኔታ የሚያሳውቀን የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡ ስሜት በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቻችን የምንረዳውን ነገር ያሳውቀናል፡፡ ስሜት ከአምስቱ የስሜት ህዋሳታችን በማየት ፣ በመስማት ፣ በመቅመስ ፣ በመዳደስና በማሽተት ከምንረዳው ነገር በላይ መሄድ አይችልም፡፡ ስሜት ድንበሩ ተፈጥሮአዊ አለም ብቻ ነው፡፡ ከተፈጥሮአዊ ወይም ከቁሳዊ አለም ያለፈን ነገር ስሜት መረዳት አይችልም፡፡

እምነት ደግሞ በእነዚህ የስሜት ህዋሳቶቻችን ከምንረዳው ያለፈ በመንፈሳዊ አለም ያለውን ነገር ያያል ፣ ይሰማል ፣ ይቀምሳል ፣ ይዳስሳል እንዲሁም ያሸታል፡፡

የእምነት ክልል መንፈሳዊው አለም ፣ በአይን የማይታየው አለምና ልእለ ተፈጥሮአዊው አለም ነው፡፡ እምነት የሚያየው በተፈጥሮ አይን የማይታየውን ነው፡፡ እምነት የሚያየው በውስጠኛው በልቦና በመንፈስ አይን የሚታየውን ነው፡፡

ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19

እምነት የሚደርሰው መንፈሳዊውን አለምን ነው፡፡ እምነት የሚደርሰው እና የሚይዘው በተፈጥሮአዊ እጃችን መያዝ የማንችለውን በመንፈሳዊ አለም ያለውን ነገር ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

የእምነት ክልል ከስሜት ክልል ያለፈ ስለሆነ የእምነትን ነገር ፣ የእግዚአብሄርን ነገር ፣ የመንፈስን ነገር በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቻችን ልንረዳው አንችልም፡፡

ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14

እምነት የሚያየውን ነገር ስሜት በፍፁም አይረዳውም፡፡ ስሜት የሚረዳበት ክልል ተፈጥሮአዊው አለም ነው፡፡ እምነት ደግሞ የሚረዳበት ክልል መንፈሳዊው አለም ነው፡፡

ስለዚህ  በእግዚአብሄር ቃል በእምነት የተረዳነው ነገር ከስሜታችን ጋር ሊቃረን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ አሸናፊ ነህ ሲል ስሜታችን የእግዚአብሄርን ቃል በእምነት መረዳት ስለማይችል የአካባቢውን ሁኔታ ብቻ ይናገራል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ዕብራዊያን 10፡17

ስለዚህ ነው በእምነት የስሜትን ነገር መመልከት እና መከተል እንደሌለብን መጽሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡ በእንደ ጊዜ የማይታየውን በእምነት አይተንም የዙሪያችንን ሁኔታም አይተንም አይሆንም፡፡ ስለዚህ ነው በእምነት ስንኖር አካባቢያችንን የሚነግረንን ስሜታችንን መስማት እንደሌለብን መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . .  የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

feeling_free.jpg

እምነት ይጠይቃል

faith please god.jpgከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሰምር እምነት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ማንኛውም ግንኙነት መንፈሳዊውን አለም የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ይጠይቃል፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ለመኖር በመካከላችን ያለችውን በአይን የማትታየውን መንፈሳዊውን አለም ማየት ይጠይቃል፡፡

ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡21

መንፈሳውን አለም ማየት የማይችል ሰው ከእግዚአብሄርም ጋር ይሁን በአጠቃላይ ከመንፈሳዊ አለም ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችልም፡፡ በተፈጥሯዊ አይንህ የሚታየውን ነገር ብቻ የሚያይ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሊግባባ ፣ አብሮ ሊሰራና ውጤት ሊያገኝ አይችልም፡፡ ለመንፈሳዊ አለም አይኑ የታወረ ሰው እግዚአብሄርን ሊያየው እና ሊከተለው አይችልም፡፡

ስለዚህ ነው ካለእምነት አግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት የማይቻለው፡፡ እግዚአብሄርን ለማሰደስት እምነት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሄር እኛን በሚያስደንቁን ብዙ ነገሮች አይደነቅም፡፡ እኛን የሚያስደስቱን ነገሮች ሁሉ እግዚአብሄርን ላያስደስቱት ይችላሉ፡፡ እምነት ግን በእርግጥ እግዚአሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡

ሰው በምድር የሚፈለጉት ጥበብ ፣ ሃይልና ባለጠግነት ሁሉ ቢኖረው እምነት ግን ከሌለው እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡ ጠቢብ ይሁን ያልተማረ ፣ ሃያልም ይሁን ደካማ ፣ ባለጠጋም ይሁን ደሃ እግዚአብሄርን የሚያሰደስተው ጠብቡ ሃይሉ ባለጠግነቱ ሳይሆን እምነቱ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሰው ጥበብ አያበረታታውም ፣ እግዚአብሄርን የሰው አለማወቅ ተስፋ አያስቆርጨውም ፣ የሰው ሃይል አያስገርመውም የሰው ድካም አያስደነግጠውም ፣ የሰው ባለጠግነት አያስገርመውም የሰው ድህነት አይከብደውም፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

የሰው ጥበብ ምንም እንደማያመጣ ፣ የሰው አለማወቅ ምንም እንደማይቀንስ ፣ የሰው ሃይል ከቁጥር እንደማይገባ ፣ የሰው ድካም ነገሩን እንደማይለውጥ ፣ የሰው ባለጠግነት ምንም እንደማይጨምር ፣ የሰው ድህነት ምንም እንደማይቀንስ ማወቅና ሁሉን በሚችል በእግዚአብሄር መታመን እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11

የሰው ፈጣንነት እግዚአብሄርን አያንቀሳቅሰውም፡፡ እግዚአብሄርን የሚያንቀሳቅሰው እምነት ነው፡፡

ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡ ወደእግዚአብሄርን በእምነት የሚደርስ ሰው ከእግዚአብሄር ዋጋን ይቀበላል፡፡ በእምነት ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝ ሰው በእግዚአብሄር ጥበብ ፣ ሃይልና ባለጠግነት ይኖራል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዋጋ #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን

how to overcome fear of failure in sports.pngከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

እግዚአብሄር የዘላለም ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር አሸናፊ ነው፡፡

አለም በመንፈሳዊ አለም በጦርነት የተሞላች ነች፡፡ በዚህ ምክኒያት ብዙ ሰዎች በአለም ተሸንፈው ቀርተዋል፡፡

አለምን የምናሸንፈው በእድል አይደለም፡፡ አለምን የምናሸንፈው በእውቀት አይደለም፡፡ አለምን የምናሸንፈው በሃይል አይደለም፡፡ አለምን የምናሸንፈው በብልጥግና አይደለም፡፡ የአለም አሸናፊነት የምድራዊ አሸናፊነት ጉዳይ አይደለም፡፡ አለም ከእግዚአብሄር ያልተወለዱትን አዋቂዎች ፣ ሃያላን እና ባለጠጎች ሁሉ አሸንፋ ከንቱ አድርጋለች፡፡

በአለም ላይ አሸናፊ ለመሆን ብቸኛው መንገድ ከእግዚአብሄር መወለድ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር የተወለደ ሁሉ ደግሞ አለምን ያሸንፋል፡፡

ሰው በእምነት መንፈሳዊውን አለም ካላየና ከእግዚአብሄር ጋር በእምነት ካልተገናኘ አለምን መሸነፍ በፍፁም አይችልም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ቃል ዳግመኛ በመወለድ ብቻ የእግዚአብሄርን መንግስት ማየትና ከንጉሱም ጋር መገናኘት ይችላል፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3

ሰው በእምነት የዘላለሙንና የማይታየውን ካላየ በስተቀር አለምን ማሸነፍ አይችልም፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ሰው በእግዚአብሄር ቃል ጉልበት ካልሆነ አለምን ማሸነፍ አይችልም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት በእምነት አይን ካላየ አለምን ማሸነፍ አይችልም፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ሰው ግን የሁሉ ነገር ምንጭ የሆነውን መንፈሳዊውን አለም ማየት ከቻለ አለምን ማሸነፍ ይችላል፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #ድልነሺ #ዳግመኛመወለድ #የእግዚአብሄርልጅ #መንፈስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #አሸናፊ #አለቅነት #ስልጣናት #ስልጣን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

how to overcome fear of failure in sports.png

የእምነት አቡጊዳ

hot-lentil-vegan-plate.jpgከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ ካለእምነት ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ካለእምነት ከእግዚአብሄር ጋር መኖር አይቻልም፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው የመጀመሪያው እምነት ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ ለእኔ ነው ብሎ  ማመን እና መቀበል ነው፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ማመን የእምነት የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ እምነት መንፈሳዊውን አለም ማየት ነው፡፡ ኢየሱስን ያላመነ ሰው የእግዚአብሄር መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3

ኢየሱስን ከማመን ቀጥሎ ለእግዚአብሄር ለመኖርና እግዚአብሄርን ለማገልገል የመጀመሪያውና ወሳኙ እምነት ስለ መሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ማመን ነው፡፡ ስለ መሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ማመን ቀላል እምነት ይመስላል ፡፡ ነገር ግን ብዙዎችን ከህይወትና ከአገልግሎት ያሰናከለው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን አለማመን ነው፡፡ ለእግዚአብሄር እንድንኖርና እግዚአብሄርን እንድናገለግል የሚያስችለን የእግዚአብሄር ቃል እንዳይሰራብን የሚያገደው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን አለማመን ነው፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19

ሰው ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ካላመነ ስለሌላ ስለምንም አምናለሁ ቢል ውሸት ነው፡፡ ሰው ስለሌላ ነገር ከማመኑ በፊት የሚቀድመው እርሱ ለእግዚአብሄር ሲኖር እግዚአብሄር መሰረታዊ ፍላጎቱን እንደሚያሟላ ማመን ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33

ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ማመን ከደህንነት ቀጥሎ የእምነት መሰረት ነው፡፡ ሰው ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ካመነ ስለሌላ ስለምንም ነገር ማመን አይቸግረውም፡፡ ሰው ስለመሰረታዊ ፍሎጎቱ ካላመነ ደግሞ አንደኛ ደረጃን ሳይጨርስ ሁለተኛ ደረጃን ለማለፍ እንደመሞከር ነው፡፡

ስለመሰረታዊ ፍላጎት እምነት ያለው ሰው እግዚአብሄርን በወደደው አቅጣጫ ሊያገለግለው ይችላል፡፡ የመሰረታዊ ፍላጎት ጥያቄ ሙሉ ዜን የሚጠይቅ ስለሆነ ስለመሰረታዊ ፍላጎት የማያምን ሰው ግን እግዚአብሄርን ማገልገል ያቅተዋል፡፡

እግዚአብሄርን ማገልገል የምንችለው ስለመሰረታዊ ፍላጎታችን እግዚአብሄርን በምናምንበት መጠን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎታችን በማናምንበት መጠን ህይወታችንን እናባክነዋለን፡፡

አህዛብ መሰረታዊ ፍላጎትን ከማሟላት ያለፈ ስራ የላቸውም፡፡ አህዛብ እግዚአብሄር እንደልጅ እንደሚንከባከባቸው አያምኑም፡፡ አህዛብ አንዱና ብቸኛው የህይወት አላማቸው የሚበላና የሚጠጣ የሚለበስ መፈለግ ነው፡፡ አህዛብ የሚበላ ፣ የሚጠጣና የሚለበስ በመፈለግ ብቻ እግዚአብሄርን የሚያገለግሉበትን ክቡር ህይወት ያባክናሉ፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ማቴዎስ 6፡31-32

ስለቤት ኪራይ ፣ ስለልጆች ትምህርት ቤት ፣ ስለመጓጓዣ በአጠቃላይ ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ሳያምኑ እግዚአብሄርን እናገለግላለን ማለት ዘበት ነው፡፡

አሁን በክርስትያን ህይወት ውስጥ የሚታዩ ብዙ ችግሮችን ወደኋላ ሄደን ብንፈትሽ እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎት ያለማመን ችግር ውጤት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የሚጣሉት ስለመሰረታዊ ፍላት እግዚአብሄርን ካለማመን ነው፡፡ ሰዎች በክርስትና ህይወታቸው ጌታን እንደልባቸው የማገልገል ችግር የመነጨው እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎት ካለማመን ነው፡፡ ሰዎች ለስልጣን የሚዋጉት በተዘዋሪ ስለመሰረታዊ ፍላጎት ካለማመን ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሄርን በማገልገል ላይ ከማተኮር ይልቅ በሌሎች ነገሮች ላይ የሚያተኩሩት ስር መሰረቱ ቢታይ የመሰረታዊ ፍላጎት ጥያቄ ነው፡፡

ሳይሰስት ተሰጥቶ እግዚአብሄርን የሚያገለግል ሰውን ብናይ ደግሞ እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ እንዳመነው እርግህጠኛ መሆን እንችላለን፡፡ ስለ ስልጣንና ስለማእረግ ግድ የማይለው አገልጋይ ብናይ ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ በጌታ ላይ የተደገፈ ሰው ስለሆነ ነው፡፡ ስለአገልግሎቱ ስፋትና ስለዝናው ሌት ተቀን የማይጨነቅ ሰው ካየን ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ በእግዚአብሄር ላይ ያረፈ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ህዝብ መጥቀም ፣ ማገልገል ፣ ማንሳትና ማሻገር ላይ የሚያተኩር አገልጋይ ካየን እርሱ ለእግዚአብሄር ህዝብ ሲሰራ እግዚአብሄር የእርሱን ቤት እንደሚሰራ ስለተማመነ ነው፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ባመነበት መጠን ብቻ ነው ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር ነፃ የሚሆነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ስለሚበላው ፣ ስለሚጠጣውና ስለሚለብሰው በአጠቃላይ ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ካመነ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን ለማገልገል የሚለቀቀው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር

በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ሚልክያስ 3፡10

እግዚአብሄር እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር መልኩ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር አይለወጥም፡፡ እግዚአብሄር አይዋሽም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈራው የለም፡፡ እግዚአብሄ ቅዱስ ነው፡ሸ እግዚአብሄ ንፁህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሊደብቀው የሚፈልገው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር አውነትን ይናገራል፡፡

የእግዚአብሄ ቃል እውነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የተፈተነ ነው፡፡ የእግዚአብሄ ቃል ተፈትኖ ያለፈ አስተማማኝ ማነም ሰው ሊደገፍበት የሚችል ነው፡፡

በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው። መዝሙር 12፡6

ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ፈትኑኝ የሚለው፡፡ ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ያልፈፀምኩት ቃል የት አለ? ኑና እንዋቀስ የሚለው፡፡ እግዚአብሄ ቃሉን ሁልጊዜ ስለሚጠብቅ ከማንም ጋር ለመዋቀስ አይፈራም፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን ሙሉ ለሙሉ ስለሚጠብቅ ኑና እንዋቀስ ይላል፡፡ እግዚአብሄር የማንም ባለእዳ አይደለም፡፡

ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። ኢሳያስ 1፡18

እግዚአብሄር መጠየቅን አይፈራም፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ መፈተንን ይወደዋል፡፡ እግዚአብሄር እውነተኛ ስለሆነ ሁልጊዜ በቃሉ እንድንፈትነው ይጋብዘናል፡፡

በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ሚልክያስ 3፡10

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነት ጨምርልን

faith_ann.jpgሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6

ለስጋችንና ለምስኪን እኔ አስተሳሰባችንን የሚመቹ ነገር ግን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የፀሎት ርእሶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል እምነትን ጨምርልን የሚለው አንዱ ነው፡፡

ሃዋሪያት ኢየሱስን እምነትን ጨርልን ሲሉት “እሺ ተቀበሉ እምነትን እየጨመርኩላችሁ ነው” አላላቸውም፡፡ ኢየሱስ ያለው ያላችሁን ትንሽ የምትመስለውን እምነት ተጠቀሙ ስራ ስሩባት ለውጥን ታመጣለች ነው፡፡ ኢየሱስ የሚለው ነገራችሁን ለመለወጥ የሚያስፈልጋችሁ ያላችሁ ትንሽ የምትመስለው እምነት ብቻ ነች፡፡ ኢየሱስ የሚለው የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል የሆነችውን እምነት መጠቀም አለባችሁ ለውጥ የሚመጣው በእርሱ ነው፡፡

የእምነት ትንሽ የለውም፡፡ እምነት ሁሉ ይሰራል፡፡ ያላችሁን እምነት ብትጠቀሙ ለውጥ ይመጣል፡፡ እምነት ጥቅም ላይ ሲውል ሁልጊዜ ታላቅን ስራን ይሰራል፡፡ የእምነት እርምጃን በመውሰድ ለውጥን ታያላችሁ፡፡

አንዳንድ ሰው የሚረካው በመለመን ብቻ ነው ፡፡ ባለው እምነት መጠቀም ፣ እርምጃ መውሰድ ፣ ስራ መስራትና ፍሬ ማፍራት አያውቅም፡፡ ስለዚህ በህይወቱ ለውጥን አያይም፡፡ ሰው የሚያስፈልገው አሁን ባለው እምነት መጠቀም ነው፡፡

ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ጥርጥር #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት የማይቻልበት 7 ምክኒያቶች

church-Leaders.jpgያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

 1. የሚታየው ሁሉ ከማይታየው ስለሆነ ነው፡፡

ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት የማንችለው የሚታየው ነገር ሁሉ ምንጩ የማይታየው አለም መሆኑን ማመን ስለሆነ ነው፡፡ እምነት የሁሉም ነገር ምንጭ የሆነው የማይታየው ነገር ላይ ማተኮር  ነው፡፡ እምነት የማይታየው ነገር ላይ ለማተኮር የሚታየው ነገር ላይ አለማተኮት ነው፡፡ እምነት የሚታየውን አለመመልከት የማይታየውን መመልከት ስለሆነ ነው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

 1. አስፈላጊና ጉዳዬ ልንለው የሚገባው የማይታየውን ስለሆነ ነው

ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት የማይቻለው የማይታየውን ባንመለከት ሁሉን ነገር ስለምናጣ ነው፡፡ የሚታየውን ባንመለከት ምንም የምናጣው ነገር የለም፡፡ አስፈላጊው ነገር የማይታየው ነገር ነው፡፡ ህይወትን የሚሰጠው የማይታየው መንፈስ ነው፡፡ የህይወት ቁልፋችን ያለው በማይታየው ነገር ውስጥ ነው፡፡ የማንኛውም የህይወት ጥያቄያችንን የሚመልሰው የማይታየው ህይወትና መንፈስ የሆነው የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡

ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ዮሃንስ 6፡63

 1. የማይታየው ወደሚታየው ለመምጣት ትግስት ስለሚጠይቅ ነው፡፡

ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት የማይቻለው የእምነት ውጤት ቅፅበታዊ ስላይደለ ነው፡፡ በመንፈሳዊ አለም ያለው ነገር ወደ ተፈጥሮአዊ አለም እንዲመጣ ትግስት ይጠይቃል፡፡ ትግስት ደግሞ ራስን መካድና ትህትናን ይጠይቃል፡፡

በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ። ዕብራውያን 6፡11-12፣15

 1. የሚታየውን ማንም ሰው ማየት ስለሚችል ነው ፡፡

ያለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት የማይቻለው እምነት የማይታየውን በማየት በማይታየው ላይ ማተኮር ስለሆነ ነው፡፡ የሚታየውን ለማየት ጥረት አያስፈልግም፡፡ የማይታየውን ለማየት ግን በመጀመሪያ ኢየሱስን አዳኝ አድርጎ በመቀበል ከእግዚአብሄር መወለድ በመቀጠልም እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፈቃድ ከቃሉ ፈልጎ ማግኘት እንዲሁም በፈቃዱ ላይ መቆም ይጠይቃል፡፡

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

 1. የእግዚአብሄርን ተስፋ ብቻ በመያዝ ስለሆነ ነው፡፡

ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት የማይቻለው እምነት በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ብቻ መቆም ስለሆነ ነው፡፡ እምነት ሌሎች ተስፋዎች አያስፈልጉትም፡፡ እምነት የእግዚአብሄር የተስፋ ቃል በቂው ነው፡፡ እምነት ዝናብና ንፋስ አይደግፉትም፡፡

ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። ሮሜ 4፡18

ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ሮሜ 4፡20-21

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። 2ኛ ነገሥት 3፡17

 1. እምነት ትጋትን ስለሚጠይቅ ነው

ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት የማይቻለው እምነት ትጋትን ስለሚጠይቅ ነው፡፡ እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ስለሆነ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል መፈለግ ማሰላሰል መናገርና ማድረግ አድርጎም መታገስ ስለሚጠይቅ ነው፡፡ እምነት ሰነፎች እንደ እድል እጄ ይገባ ይሆናል ብለው የሚመኙት ነገር አይደለም፡፡ እምነት ተጋድሎ ነው፡፡

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ዕብራውያን 10፡36

 1. የእምነት ምስክርነት እውነተኛ ምስክርነት ስለሆነ ነው፡፡

ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት የማይቻልበት ምክኒያት ሰው በእምነቱ ካልተመሰከረለት በምንም ነገር ሊመሰከርለት ስለማይችል ነው፡፡ በእምነቱ የተመሰከረለት ሰው ደግሞ በሁሉም ነገሩ ይመሰከርለታል፡፡ ምንም ነገር ብናደርግ ካለእምነት ከሆነ ሃጢያት ስለሆነ ነው፡፡(ሮሜ 14፡23) የሰው እውነተኛ ምስክርነት የእምነት ምስክርነት ነው፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዕብራውያን 11፡1-2

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነት ሲገለጥ

faith.jpgእምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

የሚታይ አለምን አለ የማይታይ አለም አለ፡፡ እምነት የማይታየው አለም ውስጥ ምን እየተሰራ እንደሆነ የምናይበትና መንገድ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮአዊ አይናችን የማይታየው አለም ውስጥ ምን እንዳለ በመንፈሳዊ አይናችን አይተን የምናረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡

ይህ የምንኖርበት አለም ያልነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህ የምንኖርበት አለም እንኳን የመጣው ከማይታየው አለም ነው፡፡ አለም የተፈጠረው በማይታየው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

ሰው ካላየ ማረጋገጥ አይችልም፡፡ የምናየውን እንዳለ እርግጠኛ እንሆናለን፡፡ እምነት የሚያስረግጥ ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር በመንፈሳዊ አለም እንዳለ የሚያረጋገጥልን ማረጋገጫ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር የምናይበት መንገድ ነው፡፡ እምነት በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን የማንደርስበትን አለም የሚያይና ምን እንዳለ የሚያረጋግጥልን ነገር ነው፡፡

እምነት ከሚታየው አለም አልፎ የማይታየውን ዘላለማዊውን አለም የምናይበትና የምናረጋግጥበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ . . . የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17

አሁን ያለን ማንኛውም እውቀት ሁሉ የመጣው ካስረዳን ሰው ነው፡፡ እምነት የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ እምነት የሚታየው አለም ሁሉ ምንጭ በሆነው በመንፈሳዊ አለም ያለውን ነገር አይቶ የሚያስተምረን የሚያስረዳን አስረጂ ነው፡፡ እምነት የመንፈሳዊውን አለም እውቀት የሚሰጠን አስተማሪ ነው፡፡

የማይታየውን አለም የምናይበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንረዳ መንፈሳዊውን አለም እንረዳለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ የማይታየውን አለም እንሰማለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናይ የማይታየውን አለም እናያለን፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ተስፋ #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

40 የእምነት ጥቅሞች (ክፍል አንድ) ዕብራውያን 11፡1-20

faith benefites.jpgእምነት በተፈጥሮአዊ አይናችን የማናየውን ተስፋ ለማስረገጥ ይጠቅማል፡፡ እምነት በተፈጥሮ አይናችን የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

እምነት እውነተኛ የእግዚአብሄር ምስክርነት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዕብራውያን 11፡2

የአለምን አጀማመር አፈጣጠር የምንረዳው በእምነት ብቻ ነው ፡፡ የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው መንፈሳዊ አለም እንደመጣ ለመረዳት እምነት ወሳኝ ነው፡፡

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።ዕብራውያን 11፡3

እግዚአብሄር የሚቀበለውን መስዋእት የምናቀርበው በእምነት ነው፡፡

አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።ዕብራውያን 11፡4

ከተፈጥሮአዊ ነገር በላይ ከፍ ብለን በተፈጥሮአዊ ነገር ሳንያዝና ሳንወሰን እንድንኖር የሚያደርገን እምነት ብቻ ነው፡፡

ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ዕብራውያን 11፡5

እምነት ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሰምርና ጌታን ለማስደሰት ይጠቅማል፡፡ እምነት ከእግዚአብሄር ዋጋን ያሰጠናል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።ዕብራውያን 11፡6

እምነት በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነትን ይሰጠናል፡፡

ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። ዕብራውያን 11፡7

በምንም ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሄርን እንድንታዘዝ እምነት ይጠቅማል፡፡

አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ዕብራውያን 11፡8

እምነት የተስፋ ቃላችንን በመመልከት የዛሬን መከራ እንድንንቅና እንድንታገስ ያደርገናል፡፡

ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ ዕብራውያን 11፡9

እምነት የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል በትግስት እንድንጠብቅ ጉልበት ይሆነናል፡፡

መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።ዕብራውያን 11፡10

እምነት የማይቻል ነገር እንድናደርግ ከተፈጥሮ በላይ የሆነን አቅምን ይሰጠናል፡፡

ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ዕብራውያን 11፡11

እምነት ከሞተ ነገር ውስጥ ህይወት እንዲወጣና እንዲበዛ ያስችላል፡፡

ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። ዕብራውያን 11፡12

እምነት በዚህ አለም እንግዳ ሆነን እንድንኖር ያስችለናል፡፡

እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። ዕብራውያን 11፡13

እምነት ከእግዚአብሄር የሆነውን እውነተኛውን ነገር እንድንፈልግ ያፀናናል፡፡

እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤  ዕብራውያን 11፡14-15

እምነት ልባችን መዝገባችን ባለበት በሰማይ እንዲሆን ያስችላል፡፡

አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ዕብራውያን 11፡16

እምነት ከእኛ ችሎታ ያለፈ መስዋእትን እንድናቀርብና ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡

አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤ ዕብራውያን 11፡17-18

እምነት እግዚአብሄር ለሞተው ህይወትን እንደሚሰጥ በማመን ከሞት በላይ እንድናስብ ይጠቅመናል፡፡

እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው።ዕብራውያን 11፡19

እምነት የእግዚአብሄርን በረከት በሌሎች ላይ እንድናስተላልፍ ያስችለናል፡፡

ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው። ዕብራውያን 11፡20

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የአባቶች እምነት ምስክርነት በ40 ጥቅሶች

by faith.png1.jpgዕብራውያን 11፡1-40

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና። ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤ እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው። ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው። ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸው ባረካቸው፥ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ። ዮሴፍ ወደ ሞት ቀርቦ ሳለ በእምነት ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት አስታወሰ፥ ስለ አጥንቱም አዘዛቸው። ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ ያማረ ሕፃን መሆኑን አይተው በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት የንጉሥንም አዋጅ አልፈሩም። ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና። አጥፊው የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ። በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባሕር በእምነት ተሻገሩ፥ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ተዋጡ። የኢያሪኮ ቅጥር ሰባት ቀን ከዞሩበት በኋላ በእምነት ወደቀ። ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም። እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።

የእምነት ጋሻ

shield7.jpgየዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ ኤፌሶን 6፡11-12፣16

ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ ጠላት ደግሞ ይህንን አይፈልግም፡፡ ጠላታችን ዲያቢሎስ የሚፈልገው የእግዚአብሄርን ሃሳብ እንድንጥል የእግዚአብሔርን ቃል እንዳንከተልና የተፈጠርንበትን አላማ በመሳት ከንቱ እንድንሆን ነው፡፡

የጠላት ግቡ መስረቅ ማረድ ማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ አላማ የለውም፡፡

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10

የሰው ልጆችን ህይወት የሚሰርቅበት ፣ የሚያርደበትና የሚያጠፋበት መንገዱ በእግዚአብሄር ቃል እንዳይኖሩ ጥርጥርን ወደልባቸውና መላክ ነው፡፡ ዲያቢሎስ የመስረቅ የማረድ የማጥፋት አላማውን ለማሳካት የክፉ ሃሳብ ፍላፃዎችን ወደ እኛ ካለማሰለስ ይልካል፡፡ ይህ የክፋት ሃሳብ ህይወታችንን ለማቃጠልና ለማጥፋት የታለመ ነው፡፡

ኢየሱስ በዲያቢሎስ ሲፈተን የዲያቢሎስን የጥርጥር ቀስት በሙሉ የመለሰው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ (ማቴዎስ 4፡1-11) የእግዚአብሄርን ቃል የማያውቅና  የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት በሚመጣው እምነት ያልታጠቀ ክርስትያን ጋሻ ሳይዝ በጠላት ቀስት መካከል እንደተገኘ ሰው ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

የጠላት ዲያቢሎስን የክፋት እሳት ማጥፋት የምንችለው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ራሳችንን ከዚህ የጥርጥር ቀስት መጠበቅ የምንችለው ራሳችንን በእምነት ምንጭ ቃል በመመገብ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በቀጣይነት የማይሰማና እምነቱን የማይመግብ ሰው ለዚህ የጥርጥር ቀስት የተጋለጠ ይሆናል፡፡

ሰው በቀጣይነትና በትጋት የእግዚአብሄርን ቃል ካልመገበና ራሱን በእምነት ጋሻ ካላስታጠቀ ልቡ በፍላፃ ይወጋል፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀን ልባችንን እንድንጠብቅ የሚያዘን፡፡

አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 4፡23

በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ ኤፌሶን 6፡16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ፍላጻ #ጋሻ #መስማት #እቃጦር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በፍቅር የሚሠራ እምነት

faith works in love.jpgበክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ገላትያ 5፡6

እምነት እንዲሰራ የሚያደርገው ፍቅር ነው፡፡ እምነት የሚያስፈልገውም የፍቅርን ህይወት እንድንኖር ነው፡፡ እምነት ከፍቅር ተለይቶ አይሰራም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ያለው ያው ጌታ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገው ውደድ ብሏል፡፡

ሰው እምነት ቢኖረው እንዲሰራ የሚያደርገው ፍቅር ግን ከሌለው ከንቱ ነው፡፡ ሰው እምነት ቢኖረው የእምነቱ ሃይል ትክክለኛ ቦታ ላይ እንዲውል የሚያደርገው ፍቅር ከሌለው ከንቱ ነው፡፡ እምነትን ወደ ትክክለኛ ቦታ የሚመራው ፍቅር ነው፡፡

ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-2

በእምነት ስለምናደርገው ማንኛውም ነገር መነሻ ዝንባሌው ፍቅር መሆን አለበት፡፡ በፍቅር ባህሪ ያልተገራ የእምነት ሃይል አይሰራም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ

የስህተት ገድል

rome-swordfighing-NINA-CAPLAN-large.jpgበህይወታችን በፍፁም መሳተፍ የሌለብን መልካም ያልሆኑ የገድል አይነቶች አሉ፡፡ እንደ እነዚህ አይነት የገድል አይነቶች ውስጥ መሳተፍ አላስፈላጊ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ በተሳሳተ ገድል ላይ መካተት ህይወታችን ፍሬ ቢስ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ መልካሙን ገድል እንድንጋደል እንጂ መልካም ያልሆነውን ገድል አንዳንጋደል መፅሃፍ ቀዱስ በብርቱ ያስጠነቅቀናል፡፡ ለመልካም ገድል በቂ ፀጋና ሃይል ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን መልካም ያልሆነውን ተጋድሎ ስናደርግ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር አይሆንም እንዲሁ እንደክማለን እንጂ ምንም ውጤተ አናገኝም፡፡

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

 1. ስለደረሰብን በደል ራስ የመበቀል ገድል

እግዚአብሄር የሁላችን ፈራጅ ነው፡፡ ሰው ግን እራሱን በእግዚአብሄር ቦታ ከፍ አድርጎ እንደፈራጅ ሲሆን እግዚአብሄር አብሮት አይሆንም፡፡ የእግዚአብሄርን ቦታ ወስዶ ፈራጅ ለመሆን መሞከር ብክነትና ፍሬ ቢስነት ነው፡፡ ሰው ምንም ቢበደል ለእግዚአብሄር ፈራጅነት ስፍራ መስጠት አለበት እንጂ ራሱ የመበቀል ተጋድሎ ውስጥ መግባት የለበትም፡፡

ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ሮሜ 12፡17፣19

ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? ያዕቆብ 4፡12

 1. ሰውን እንደምንጭ የመመልከትና ተስፋ የማድረግ ገድል

የበጎ ነገር ሁሉ ምንጭ እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ግን ስለ መልካም ነገርና እድገት ስለማግኘት ወደ እግዚአብሄር ማየት ትቶ ወደ ሰው ካየና ሰውን ተስፋ ካደረገ ስለዚህ ስህተቱ አላስፈላጊ ዋጋ ይከፍላል፡፡ የሰው በረከት በእግዚአብሄር እጅ ነው፡፡ የእርሱን እጣ ፈንታ የያዘው ሰው እንደሆነ አድርጎ ከሰው ጋር ከተጋደለ ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤  ያዕቆብ 4፡1-2

 1. ሰውን የመጥላት ገድል

እግዚአብሄር የፈጠረንና ዲዛይን ያደረገን ለፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ፀጋ ሰውን ለመውደድ በቂ ነው እንጂ ሰውን ለመጥላት አይተርፍም፡፡ ሰውን የምንጠላውና በሰው ላይ ክፋትን ለማድረግ የምንተጋው በራሳችን ወጭ ነው፡፡ ሰውን ለመጥላት የምናደርገው ማንኛውም ተጋድሎ ውጤት የሌለውና የአቅም ብክነት ብቻ ነው፡፡

ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡9

 1. በቅንጦት ለመኖር የሚደረግ ተጋድሎ

እግዚአብሄር እረኛችን ነው የሚያሳጣን አንድም ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ከመሰረታዊ ፍላጎት አልፈን የምንፈልገውንና በምቾትና በቅንጦት ለመኖር በምናደርገው ተጋድሎ ጉዞ እግዚአብሄር አብሮን ስለማይሆን ከባድ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ነገር ሳይበቃን ሲቀር እጃችንን ዘርግተን እግዚአብሄር ያልሰጠንን ከወሰድን እግዚአብሄር አብሮን አይቆምም፡፡ ይህ ለቅንጦት ኑሮ እና ለኑሮ ትምክት የሚደረግ ተጋድሎ እግዚአብሄር የሌለበትና እኛው በራሳችን የምናደርገው ስለሆነ ውጤት የሌለው ድካም ነው፡፡

ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡3

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥

አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

 1. እግዚአብሄር ያላለንን ለማድረግ ያለ ተጋድሎ

እግዚአብሄር በስራ ላይ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር የአገልግሎት ሃሳብ አንሰጠውም፡፡ እግዚአብሄር ነገሮች እንዴት መሆን እንደለባቸው ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ዘወትር በስራ ላይ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት እግዚአብሄር በህይወታችን ያሰበውን በነገር ማግኘት አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት አስቀድሞ ያዘጋጀልንን ስራ ከእርሱ ከራሱ ፈልገን ማግኘትና መረዳት አለብን፡፡ ሰው ግን በራሱ አነሳኝነት እግዚአብሄር እንደዚህ ሳይፈልግ አይቀርም ብሎ መልካም የመሰለውን ነገር ለእግዚአብሄር ለማድረግ የሚያደርገው ተጋድሎ እግዚአብሄር ጎሽ የማይለው ከንቱ ተጋድሎ ነው፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። ዮሃንስ 5፡19፣30

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት  #ቃል #የሰውበቀል #ቅንጦት #ጥላቻ #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ማስተዋል #ማሰላሰል #መናገር #መፅናት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የምንቀበለው ብቸኛው ገድል

fist-fight-shutterstock-crop-1200x480.jpgመልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

በምድር ላይ ብዙ አይነት ተጋድሎዎች አሉ፡፡ ሰዎች ብዙ ነገር ለማድረግ ፣ ብዙ ነገር ለማግኘትና ብዙ ነገር ለመሆን ይጋደላሉ፡፡

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እንድንጋደለው የተሰጠን አንዱ  ተጋድሎ የእምነት ተጋድሎ ብቻ ነው፡፡

የሰው ልጆች የህይወት ጥያቄ ሁሉ በክርስቶስ የመስቀል ስራ ተመልሷል፡፡ አሁን ያለው ብቸኛ ተጋድሎ በዚያ በክርስቶስ በተሰራው ስራ ላይ የመቆም የእምነት ተጋድሎ ብቻ ነው፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ስራ ውጭ አሁን አንደ አዲስ የምንቆረቁረው ስራ የለም፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ካሸነፈው ተጋድሎ ውጭ የምንጋደለው አዲስ ጠላት የለም፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከጨረሰው ስራ ውጭ አዲስ የምንሰራው አዲስ ስራ የለም፡፡

አሁን ያለው ተጋድሎ የእምነት ተጋድሎ ብቻ ነው፡፡ አሁን ያለው ተጋድሎ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ፣ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመረዳት ፣ በእግዚአብሄር ቃል አካባቢ ውስጥ ለመቆየት ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ለመጠበቅ ፣ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ለመቆምና በእግዚአብሄር ቃል ላይ ለመጽፅናት ያለ ተጋድሎ ብቻ ነው፡፡

የእምነት ተጋድሎ አይነቶች

 1. እምነት የሚመጣው እግዚአብሄር ስለ እኛ ያለውን ፈቃድ ከመረዳት በመሆኑ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመረዳት የእግዚአብሄርን ቃል መፈለግ ማጥናት መስማት የእምነት ተጋድሎ ክፍል ነው፡፡

 

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

 

 1. የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ በሙሉ ልብ በማስተዋል መስማት ሌላው የእምነት ተጋድሎ አካል ነው፡፡

 

የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። ማቴዎስ 13፡18-19

 

 1. በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተሰራልንን መብታችንንና ጥቅማችንን ከመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልገን ማግኘትና መረዳት የእምነት እርምጃ ነው፡፡

 

የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤ ፊልሞና 1፡6

 

 1. ራሳችንን በቃሉ እውነት ከባቢ ውስጥ ለመጠበቅ ቃሉን ማሰላለስ የእምነት አንዱ ተጋድሎ ነው፡፡

 

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8

 

 1. የእግዚአብሄርን ቃል በነገራችን ላይ መናገር ነው፡፡ የአመንነውን የእግዚአብሄር ቃል መናገር በእምነት ውጤት የማግኛ መንገዱ ነው፡፡

 

ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡13

 

 1. ልባችንን ከጥርጥር መጠበቅ ሌላው የእመነት እርምጃ ነው፡፡ በልባችን ያለው የእምነት ቃል በጥርጥር ሃሳብ እንዳይበረዝ ፍርሃትንና ጥርጥርን የሚያመጡትን ነገሮች አለማስተናገድ የእምነት ተጋድሎ ክፍል ነው፡፡

 

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23

 

ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። ሉቃስ 8፡50

 

 1. የእግዚአብሄርን ቃል ካደረግን በኋላ መፅናት የእምነት ተጋድሎ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በማድረግ መፅናት መቀጠል የእምነት ገድል የሚጠይቀው ወሳኝ ነገር ነው፡፡

 

እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ዕብራውያን 10፡35-36

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት  #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ማስተዋል #ማሰላሰል #መናገር #መፅናት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነት ይመጣል

faith comes.jpgካለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ እንደሰው ብዙ የሚያስደስቱንና የሚማርኩን ነገሮች አሉ፡፡

እግዚአብሄር በመልኩና በአምሳሉ ስለፈጠረን እንደ እኛ ስሜት አለው የሚወደውና የማይወደው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄርን የሚስቡትና የማይስቡት ነገሮች አሉ፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄር የሚማርኩትና የማይማርኩት ነገሮች አሉ፡፡

እግዚአብሄር እኛን የሚማርኩን ነገሮች ሁሉ አይማርኩትም፡፡ እግዚአብሄርን እንደሚያስደስተው በግልፅ የተፃፈልን ነገር እምነት ነው፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ስለሆነና ከእግዚአብሄር ጋር የምንገኛኘው በእምነት ስለሆነ ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አንችልም፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት ሊሰምር በፍፁም አይችልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

አንዳንድ ሰዎች ስለ እምነት ሲያስቡ ጭንቅ ይላቸዋል፡፡ እምነት እጅግ ርቆ የተሰቀለ ሩቅ ነገር ይመስላቸዋል፡፡ እምነት እንደ ምትሃት ከባድ ነገር እንደሆነ ያስባሉ፡፡ እምነት ለጥቂት እድለኛ ሰዎች የሚመጣ አድረገው ያያሉ፡፡

ነገር ግን ካለ እምነት እግዚአብሄር ደስ ማሰኘት እንደማችል የሚያስተምረው መፅሃፍ ቅዱስ እምነት እንዴት እንደሚመጣም አስተምሮዋል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

እምነት እግዚአብሄር በቃሉ የተናገረው ነገርን መቀበል ሲሆን እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በሰማን መጠን እምነት ይመጣልናል፡፡

የእግዚአብሄር ቃል የተሰጠው ለሁላችንም እንደመሆኑ መጠን ቃሉን በመስማት የሚመጣው እምነትም የተሰጠው ለሁላችንም ነው፡፡ እምነት የሚመጣላቸው በጣት ለሚቆጠሩ ጥቂት ሰዎች ሳይሆን ቃሉን ሰምተው ለተቀበሉ ሁሉ ነው፡፡

ቃሉን ከሰማን እምነት መምጣቱ ግድ ነው፡፡ ቃሉን የሚሰማ ሰው ሁሉ እምነት ይመጣለታል፡፡ በእምነት ላለመኖር ምንም ምክኒያት እስከማይኖረን ድረስ እግዚአብሄር እምነት የሚገኝበትን የእምነት ቃል ሰጥቶናል፡፡

ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ሮሜ 10፡6-8

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ቃል #መስማት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ማንም ያለው ነገር

mountain moving1.jpgእውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ማርቆስ  11፡23-24

የእግዚአብሄር ልጅነት ክብር ታላቅ ክብር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ንግግር ታላቅ ሃይል ያለው ንግግር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የእምነት ቃል ሃያል ቃል ነው፡፡

ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን ይሆንለታል፡፡

የምንለው ነገር ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር ልጅነታችንን ስልጣን የምንገልፀው በመናገር ነው፡፡ በንግግራችን ውስጥ ታላቅ ስልጣን  አለ፡፡

ለንግግራችን ሃይል የሚሰጠው እምነታችን ነው፡፡

በንግግር የሚገለፅ እምነት ነገሮችን ይለውጣል፡፡ አምነን የምንናገረው ነገር ይሆናል፡፡ አምነን የምናዘው ተራራ ይታዘዛል፡፡

እምነትን የሚያመጣው ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል መረዳታችን ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ መቀበል ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመቀበል ነው፡፡

እምነትን የሚያጠፋውን ጥርጥርን ደግሞ መዋጋት አለብን፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ የሆነን ነገር ከሰማን እና ትኩረታችንን ከሰጠነው ጥርጥር ወደልባችን ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ከሰማንና ከተቀበልን በኋላ ልባችንን ለተቃራኒ ነገር መዝጋት አለብን፡፡

ለእግዚአብሄር ቃል ልባችንን እንደከፈተን ሁሉ እንደ እግዚአብሄር ቃል ላልሆነ ሃሳብ ደግሞ ልባችንን መዝጋት አለብን፡፡ የጥርጥር ሃሳብ ወደ አእምሮዋችን ሲመጣ በፍጥነት አውጥተን መጣል አለብን፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነ የጥርጥር ሃሳብ ለጥቂት ጊዜ እንኳን በአእምሮዋችን እንዲቆይ መፍቀድ የለብንም፡፡

ስለ አለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ቃል ከፈለግህንና ካገኘንም በኋላ በቃሉ ላይ መቆም አለብን፡፡ ቃሉን በእምነት መናገር አለብን፡፡ ቃላችን ከእግዚአብሄ ቃል ጋር መስማማት አለበት፡፡ የምንናገረውን የእግዚአብሄ ቃል ካለጥርጥር መናገር ማለት ይገባናል፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ማርቆስ  11፡23-24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ጥርጥር #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የማያወላዳ የእምነት ምልክት

prayer kneel.jpgሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? ሉቃስ 18፡8

የማይፀልይ ሰው የማይፀልየው ከእግዚአብሄር የሚፈልገው ነገር ስለሌለ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሄር የማይፈልገው ነገር የለም፡፡  የማይፀልይ ሰው አብዛኛውን ጊዜ ሰው የማይፀልየው እግዚአብሄር ስለማያስፈልገው አይደለም፡፡ ሰው ምንም ነገር ባያስፈልገው እግዚአብሄር ያስፈልገዋል፡፡

ሰው ፀልዮ ከእግዚአብሄር የማይቀበለው ፀሎት እምነት ስለሚጠይቅ ነው፡፡ ሰው ባለጠጋ አባት እያለው በጉድለት የሚኖረው ለመፀለይ ሲሰንፍ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለምኑ ፀልዩ እያለ ደጋግሞ እያስተማረ ሰው ወደ እግዚአብሄር ፀልዮ የማይቀበለው ስለማያምን ነው፡፡

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8

የፀሎት መልስ ለትጉሆች እንጂ ለሰነፎች አይደለም፡፡ የፀሎት መልስ ለአማኞች እንጂ ለተጠራጣሪዎች አይደለም፡፡ የፀሎት መልስ  ለሚያቋርጡና ለሚረሱት ሳይሆን ሳያቋርጡ ለሚፀልዩ ነው፡፡

ጥያቄው እምነት አለ ወይ ነው፡፡ እምነት ካለ የፀሎት ጥያቄ ይመለሳል፡፡ ድል ሳያቋርጡ ለሚፀልዩ ነው፡፡

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ማርቆስ 11፡22-24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፀሎት #ፅናት #ትግስት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር

እግዚአብሄርን የሚያስደስቱ ሰባት አይነት ሰዎች

fear vs faith.jpgእግዚአብሄር በተፈጥሮአዊ አይን አይታይም፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ በተፈጥሮ ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት እንችልም፡፡  ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ማንኛውም ግንኙነት መደረግ የሚቻለው በእምነት ነው፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር ጋር ልንገናኝ የእግዚአብሄርን ነገር ማድረግ እንችልም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ (ዕብራዊያን 11፡6)

በእምነት በመኖር እግዚአብሄርን ማስደሰታችንን ማወቅ ይገባናል፡፡ በእምነት መኖራችንን የሚመሰክሩ ነገሮች፡፡

 1. የልቡን ሰላም የሚከተል

የልብ ሰላም ያለው ሰው በእምምነት እየኖረ መሆኑ ማረጋገጫው ነው፡፡ በእምነት የሚኖር ሰው አካባቢው ሊታወክ ይችላል፡፡ የአእምሮም ሰላም በእምነት እንደምንኖር ላይመሰክር ይችላል፡፡ ምክኒያቱም አእምሮ ብዙ አይነት ሃሳቦች የሚስተናገዱበት ስለሆነ በአእምሮዋችንን ጥርጥር ሊመጣ ይችላል፡፡ በአእምሮዋችን፻ጥርጥር መጣ ማለት እምነት የለንም ማለት አይደለም፡፡ በአካባቢያችን ያለውን ሁኔታን ወይም በአእምሮዋችን ያለውን የተለያየ ሃሳብ ሳይሆን የልባችንን ፀጥታና ዝምታ ከተከተልን በእግዚአብሄር እንደተደገፍን እናውቃለን፡፡

በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። ቆላስይስ 3፡15

 1. በእግዚአብሄር የሚደሰት

እግዚአብሄር ደስ የሚልህ ከሆነ በእምነት እየኖርክ ነው፡፡ ይህን ካላገኘህ በደስታ አተኖርም፡፡ ደስታ ያለው በእኔ ውስጥ ነው፡፡ እኔን ካላገኘህ አለቀልህ ማለት ነው የሚሉ ብዙ ነገሮች ባሉበት አለም ውስጥ በእግዚአብሄርና በቃሉ ብቻ ደስ ካለህ በእምነት እየኖርክ መሆኑን ማረጋገጫው ነው፡፡

ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ጌታ ቅርብ ነው። ፊልጵስዩስ 4፡4

 1. የማይናወጥና የማይቸኩል

እግዚአብሄር አለምን እንደሚያስተዳድራትና እግዚአብሄር ለአንተ የሚያስባትን ሃሳብ የሚያውቅና በትጋትንም እየሰራበት መሆኑን ካወቅክ አትቸኩልም፡፡ እግዚአብሄርን የሚቀድመው ሰው እንደሌለ አንተን የሚቀድምህ ሰው እንደማይኖር ካለፍርሃት በመረጋጋት ከኖርክ ታምነሃል፡፡

የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐንስ 14፡1

 1. የእንግድነት ስሜት የሚሰማው

በእንግድነት በምድር ላይ እንደምትኖር የሚሰማህ ከሆነ በእመነት እየኖርክ ነው፡፡ የሚታየው ሁሉ ሃላፊ እንደሆነ ካወቅክ በእመነት እየኖርክ ነው፡፡ ምድርን ጊዜያዊ የእንግድነትና የስደት ቤትህ እድርገህ ካየሃት በእምነት እየኖርክ ነው፡፡ እንደእንግዳ ሰው ነፍስን ከሚያረክስ ነገር ራስህን ከጠበቅክ በእምነት እየኖርክ ነው፡፡

እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ ታምነናል 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-8

 1. የአለምን ውድድር ውስጥ የማይገባ

በአለም ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቁንም የመፈለግ አላማ ስለሌላቸው ትልቁ አላማቸው በልብስና በመኪና ብራንድ መወዳደርና ማሸነፍ ነው፡፡ በምድር ላይ ካለው የአለም ፉክክር በፈቃዳችን ራሳችንን ካገለልን ፅድቁንና መንግስቱን በመፈለግ እንኖራለን በዚያም በእምነታችን እግዚአብሄርን ደስ እናሰኛለን፡፡ ሰው እግዚአብሄንና መንግስቱን ሲያይ የዚህን አለም ውድድር ይንቃል፡፡ ሃዋሪያው አለም ለእኔ ሙት ነች አትስበኝም ይላል፡፡

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ገላትያ 2፡20

 1. የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቅ የሚፈልግ

ስለኑሮው የማይጨነቅ ይልቁንም የእግዚአብሄን ፅድቅና መንግስት ለመፈለግ የሚያስብ ሰው በእምነት የሚኖር ሰው ነው፡፡ የእኔን የህይወት ፍላጎት እግዚአብሄር ነው የሚያሟላው የእኔ ሃላፊነት የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው ብሎ የሚያምን ሰው በእምነት የሚኖር ሰው ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

 1. ባለው ነገር እግዚአብሄርን የሚያመሰግን

ባለው ነገርና በደረሰበት ደረጃ ረክቶ የሚያመሰግን ሰው እግዚአብሄርን በእምነት ያስደስተዋል፡፡ ስላለው ነገር የሚያመሰግንና ለዚህ መልካም ጌታ ምን ላድርግለት ምኔን ልስጠው ብሎ በእግዚአብሄር ስራ ላይ የተጠመደ ሰው የእምነት ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ የለም (መዝሙር 23፡1) የሚለው ቃል ከእምነት ሰው የሚወጣ ነው፡፡

በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡17-18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ሁሉን የሚችል አማኝ!

eag.jpgቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም አለው። ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

ሁሉ? አዎ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

ተመልከቱ ለእኔ ለኢየሱስ ሁሉ ይቻላል አይደለም ያለው ኢየሱስ፡፡ ኢየሱስ ትሁት በመሆኑ ራሱን ከሁላችን ጋር አስተባብሮ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ይላል፡፡

በእምነት ውስጥ ያለው እምቅ ጉልበት ይህ ነው የሚባል አይደለም፡፡ካመንክ ለአንተ ሁሉ ይቻላል፡፡ ከአምንሽ ለአንቺ ሁሉ ይቻላል፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለሚያምን እንዲሁ ሁሉ ይቻለዋል፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአበሄርን ፈቃድ ከመረዳት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለተረዳና እንደ ፈቃዱ ለሚኖር ሰው ሁሉ ይቻለዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ ተረድቶ እንደ እግዚአብሄር ሃሳብ ለኖረ ሰው ሁሉ ይቻላል፡፡ በሚያምነውን ሰው አንደበት የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡ በሚያምነው ሰው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡

ለሚያምን ሰው ሁሉን ቻዩ የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉን ይቻላል፡፡ ለሚያምን ሰው ሰማይና ምድርን የፈጠረውን የእግዚአብሄርን ቃል ሁሉ ያስችለዋል፡፡ በእግዚአብሄን ቃል የሚደገፍ ሰው አይወድቅም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሊቋቋም የሚችል እንደሌለ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያምነውን ሰው ሊቋቋም የሚችል ሃይል ከሰማይ በታች የለም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል!

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የአብርሃም እምነት

abraham-promise.jpgእርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ሮሜ 4፡16-21

እግዚአብሄር ለአብርሃም በእርጅናው ወራት ልጅን እሰጥሃለሁ አለው፡፡ አብርሃምም እግዚአብሄርን አመነ፡፡ አብርሃም የእግዚአብሄርን ቃል እንዳለ ተቀበለው፡፡

እግዚአብሄር ለሙታን ህይወትን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር የሌለውን እንዳለ አድርጎ ይጠራል፡፡ እግዚአብሄር ልጅን እሰጥሃለሁ ሲለው አብርሃም ለሙታን ህይወትን በሚሰጥ የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራ በእግዚአብሄር ይህንንም ማድረግ እንደሚችል ተማመነበት፡፡

አንድም ልጅ የሌለውን አብርሃምን ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት ይበዛል የተባለውን ቃል አመነ፡፡ ሳራም እርሱም ምንም ቢያረጁም በተፈጥሮአዊ ተስፋ የሌለው ቢሆንም የእግዚአብሄርን ቃል ተስፋ አድርጎ አመነ፡፡ በተፈጥሮ ያጣውን ተስፋ በእግዚአብሄር ቃልኪዳን ተስፋ አገኘ፡፡

የመቶ አመት ሽማግሌ ሆኖ የእግዚአብሄርን ቃል እንጂ ሙት የሆነውን የራሱን ስጋና የሳራን ማህፀን አልተመለከተም፡፡ እንደሙት በሆነው በእርሱ ስጋና በሳራ ማህፀን ላይ አላተኮረም፡፡ ሙት ከሆነው ከራሱ ስጋና ከሳራ ማህፀን በስቲያ የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል ላይ አተኮረ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ተስፋ በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፡፡

እግዚአብሄር የሰጠው የተስፋ ቃል እንደሚፈፀም በመተማመን ለእግዚአብሄር ክብርን ይሰጥ ነበር፡፡ እግዚአብሄር የሰጠውን ተስፋ ሊፈፅመው እንደሚችል ተረድቶ አርፎ ነበር፡፡

አብርሃም በእምነት በረታ እንጂ ጥርጥር በህይወቱ እንዲገባ አልፈቀደለትም፡፡ አብርሃም ለእምነት እንጂ ለጥርጥር ሃሳቡን አይሰጥም ነበር፡፡

እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ሮሜ 4፡16-21

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #ተስፋ #አለማመን #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ጥርጥር #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ብቸኛ መልካም ገድል

fight-of-faith-logo.jpgመልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

ብዙ አይነት ገድሎች አሉ፡፡ ሰዎች ስለ ብዙ ነገሮች ከብዙ ነገር ጋር ይጋደላሉ፡፡ መልካም ገድል አለ መልካም ያልሆነ ገድል ደግሞ አለ፡፡

ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን የተጠራንለት አንድ ገድል ነው፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስ በማያሻማ አባባል በግልፅ የተቀመጠው መልካም ገድል አንድ ገድል ነው፡፡ ፍሬ ያለው የሚገባ ገድል አለ፡፡ ጊዜያችንን ጉልበታችንን እውቀታችንን ልናፈስበት የሚገባ ገድል አለ፡፡

ይህ ልንጋደልለት የሚገባው ፣ ህይወታችንን ልናሳልፍበት የሚገባውና ልንተጋለት የሚገባው መልካም ገድል የእምነት ገድል ነው፡፡ ምክኒያቱም እኛ ምንም ማድረግ ባልቻልንበት ጊዜና ደካሞች በነበረን ጊዜ ክርስቶስ ስለእኛ ሞቷል፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ ሃጢያችን ሙሉ ለሙሉ ዋጋ ከፍሏል፡፡  ክርስቶስ ስለእኛ ጠላታችንን ዲያለቢሎስን አዋርዶታል፡፡ አሁን እንደ አዲስ የምንሰራው ምንም ስራ የለም፡፡ እኛ ለመጀመሪያ ጊዜ የምንረታው ሃጢያት የለም፡፡ እኛ አሁን እንደ አዲስ የምናሸንፈው ጠላት የለም፡፡ በክርስቶስ ሃጢያት ድል ተነስቷል፡፡ ኢየሱስ የሰይጣንን ስልጣን በመስቀል ላይ ሽሮታል፡፡

አሁን ከእኛ የሚጠበቅብን ነገር ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ድል ላይ መቆም ብቻ ነው፡፡ በክርስቶስ የተሰራልንን ድል ከቃሉ በመመልከት በዚያ ላይ መቆም ብቻ ነው የሚያስፈልገን፡፡ አሁን የሚጠበቅብን ብቸኛ ገድል በቃሉ ላይ በእምነት የመቆም ገድል ነው፡፡ አሁን የሚጠበቅብን ብቸኛ ገድል በቃሉ ላይ እርምጃ መውሰድ ነው፡፡ አሁን የሚጠበቅብን ተጋድሎ በስፍራችን ላይ በእምነት የመቆም ተጋድሎ ነው፡፡

ገድሉንም መልካም የሚያደርገው ተሰርቶ ባለቀ ስራ ላይ ስለምንቆም ነው፡፡ ገድሉን መልካም የሚያደርገው በእምነት ከቆምን ድሉ ሁልጊዜ የእኛ እንደሆነ የተረጋገጠለት ተጋድሎ ስለሆነ ነው፡፡ ገድሉን መልካ የሚያደርገው ውጤቱ የታወቀ ተጋድሎን ስለምናደርግ ነው፡፡

አሁን የሚያስፈልገን ነገር  በተከፈለልን ዋጋ በእምነት መመላለስ ነው፡፡ አሁን የሚጠበቅብን ቃሉን መፈለግ ፣ ቃሉን ማሰላሰል ፣ በቃሉ ከባቢ ውስጥ መቆየት ፣ ቃሉን መናገር ፣ ቃሉን ማድረግና በቃሉ ላይ የመቆም የእምነት ገድል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተሻለ ልናደርግ የምንችለው ተፈፀመ ባለው በኢየሱስ የመስቀል ስራ ላይ በእምነት መቆም ብቻ ነው፡፡

መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእምነትተጋድሎ #የእግዚአብሄርቃል #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሔር እንዳለ

god is.jpgያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እግዚአብሄር በተፈጥሮ አይናችን የማይታይ መንፈስ ነው፡፡ የእግዚአብሄርም መንግስት እንዲሁ በአይን የማይታይ መንፈስ ነው፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ የሚፈልግ ሰው ማድረግ የሚችለው በእምነት ነው፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን ማየት አይቻልም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ማግኘት አይቻልም፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን መድረስ አይቻልም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን መንካት አይቻልም፡፡ ካለ እምነት ከእግዚአብሄር መቀበል በፍፁም አይቻልም፡፡

ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ሰው በመጀመሪያ እግዚአብሄር እንዳለ ማመን አለበት፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው ከእግዚአብሄር ሊቀበል በፍፁም አይችልም፡፡  እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው ከእግዚአብሄር የሚቀበልበት ሁኔታ ላይ ሊገኝ አይችልም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው እግዚአብሄርን ሊነካው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር እንዳለ የማያምን ሰው የእምነት እጆቹን ዘርግቶ ከእግዚአብሄር መቀበል ይሳነዋል፡፡

ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ሰው እግዚአብሄር በትጋት ለሚፈልጉት ዋጋ እንደሚሰጥ ሊያምን ይገባዋል፡፡ ወደእግዚአብሄር የሚመጣ እግዚአብሄር ቸርና ርህሩህ በመሆኑ ብቻ ለሚፈልጉት ዋጋ እንደሚሰጥ ያመነ ዘንድ ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄር ለሚፈልጉት ዋጋን የሚሰጥ ልዩ ከፋይ እንደሆነ ሊያምን ይገባል፡፡ ወደእግዚአብሄ የሚደርስ እግዚአብሄርን መፈለግ እጅግ አትራፊ ስራ እንደሆነ ሊረዳ ያስፈልገዋል፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ ጥበበኛ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚደርሰው ሰው እግዚአብሄርን በመፈለግ ላይ ጊዜንና ጉልበትን ማፍሰስ እጅግ አትራፊ ስራ መሆኑን ሊረዳ ይገባዋል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የእምነት ብቸኛው መንገድ

waking.jpgበአይን ከማይታየው መንፈስ ከሆነው ከእግዚአብሄር ጋር ላለን ግንኙነት እምነት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለመድረስና ከእግዚአብሄር ለመቀበል የእምነት እጅ ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሄርን ለማየት የእምነት እይታ ይጠይቃል፡፡ በአጠቃላይ እግዚአብሄርን ለማስደሰትና ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነታችን እንዲሰምር እምነት ይጠይቃል፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ታዲያ እምነትን የምናገኘው እንዴት ነው? እምነት እንዴት ይመጣል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ብልህነት ነው፡፡

ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ እምነት የማይታሰብ ነው፡፡ እምነት ይኖረን ዘንድ መጀመሪያ ስለ ሁኔታችን የእግዚአብሄር ቃል የሚለውን ማግኘት ግዴታ ነው፡፡ እምነት የሚገኘው የእግዚአብሄር ፈቃድ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ እምነት የሚመጣው በእግዚአብሄር ቃል መረዳት ብቻ ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ከእምነት ጉዞ የሚቀድመው ዋንኛው ነገር የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከቃሉ ፈልጎ ማግኘት ነው፡፡ እምነት የሚያመጣውን ቃሉን መስማትና መረዳት ነው፡፡

በእምነት ለመኖር በእግዚአብሄር ቃል መኖር አለብን፡፡ እግዚአብሄርን ለመስማትና ለማመን ቃሉን መስማት አለብን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እምነት እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝበት ምክኒያት

konjo-smile.jpgእምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክኒያቱም እግዚአብሄርን ማስደሰተ የምንችለው በእምነት ስንኖር ብቻ ነው፡፡ እምነታችን እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ ካለ እምነት ደግሞ እግዚአብሄርን ለማስደሰት መሞከር ሞኝነት ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው ነገር ምንድነው? እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘበት የእምነት ባህሪ መረዳት እግዚአብሄርን በምንም ሁኔታ ውስጥ ለማመን ይረዳናል፡፡

እምነት በተስፋ ስለሚኖር ነው

ሁሉም ሰው በአይን በሚታይ ነገር ሲኖር እምነት ግን የሚኖረው በአይን ከሚታይ ነገር ከፍ ብሎ ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያት እምነት በተስፋ እንጂ የሚኖረው በአይን በሚታይ ነገር አይደለም፡፡ እምነት የሚኖረው በአይን ከሚታየው ክልል አልፎ ነው፡፡  እምነት የሚኖረው በተስፋ ነው፡፡ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ተስፋ አድርጎ ይኖራል፡፡

በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ሮሜ 8፡24-25

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያቱ እምነት የማይታይን ነገር የሚያይ ስለሆነ ነው፡፡ እምነት የሚያየው የማይታየውን የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ነው፡፡ እምነት የሚሰማይ የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ነው፡፡ እምነት የሚያምነው የማይታየውን እግዚአብሄርን ነው፡፡

በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡21

እምነት ከሚታየው ይልቅ የማይታየውን ስለሚያስበልጥ ነው

እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ሌላው ምክኒያት እምነት የሚታየውን ስለማያይ የማይታየውን ስለሚያይ ነው፡፡ እምነት የሚያየው እግዚአብሄር በቃሉ ያለውን የማይታየውን ነው፡፡ እምነት ልቡን የሚጥለው እግዚአብሄር በተናገረው ነገር ላይ ነው፡፡ እምነት የሚከተለው ቃሉን ነው፡፡

እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7

እምነት የሚታየውን ስለማያይ ነው

እምነት እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት ምክኒያቱ እምነት ከቃሉ ጋር የማይስማማውንም ማንኛውም ሁኔታ አለማየቱ ነው፡፡ እምነት በአካባበው ያሉትን ጊዜያዊ ሁኔዎች አያይም፡፡ እምነት በዙሪያው የከበቡትን ገጠመኞች አያይም፡፡ እምነት በአካባቢው ከሚጮኸው ሁኔታ በላይ በልቡ የሚያሾከሽከውን የእግዚአብሄርን ቃል ያምናል፡፡ እምነት የሚታየውን ሁኔታ አይከተለም፡፡ እምነት እንደሁኔታው እና እነደጊዜው አይራመድም፡፡

ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ሮሜ 4፡18-19

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ተስፋ #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የልጅነት ክብር ናሙና

sonship_toga_virilus.jpgቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14

አንድ የእግዚአብሄር ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብር ያየነው በኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ልጆቹን እንዴት እንደሚያያቸው ያየነው በኢየሱስ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች በእግዚአብሄር ዘንድ ያላቸውን የክብር ቦታ ያየነው በክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች በአባታቸው በእግዚአብሄር ዘንድ ያላቸውን ስልጣን ያየነው በክርስቶስ ነው፡፡ አባታቸው ልጆቹን እንዴት እንደሚወዳቸው ያየነው በኢየሱስ ነው፡፡

ኢየሱስ የእግዚአብሄ ልጅነት ናሙና ነው፡፡ ኢየሱስ የኢየሱስ ልጅነት ክብር ሞዴል ነው፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስን እንድንመስል የተጠራነው፡፡ ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ሁሉ ተሰጥቶናል፡፡

እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡1

የእግዚአብሄር ውሳኔ የእግዚአብሄር ልጆች ሁሉ ኢየሱስን እንዲመስሉ ነው፡፡

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ሮሜ 8፡29

ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው፡፡ ኢየሱስ የእኛን ስጋ ለብሶ በመምጣት ስጋ የለበሰ ሰው እንዴት ከሃጢያት በላይ መኖር እንደሚችል አሳይቶናል፡፡ ከሃጢያት በላይ ሆነን እንዳንኖር ምንም ሰበብ የለንም፡፡

ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ ዕብራውያን 4፡15

ኢየሱስ በምድር ላይ እንዳሸነፈ እኛም በሁሉ ነገር እንድናሸንፍ ኢየሱስን የምንመስልበት ሁሉም ነገር ተሰጥቶናል፡፡

የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡2-3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የልጅነትክብር #ናሙና #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ሞዴል #መምሰል #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

የዘላለም አምላክ

 

psalm 31 9.pngአላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡28

አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሄ ፊት የምናገራቸው ነገሮች እግዚአብሄርን የማያከብሩ አላዋቂነታችንን የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ያወቅን ይመስለናል፡፡ ለእግዚአብሄር ምክር መለገስ የምንችል ይመስለናል፡፡ ስንደክም እግዚአብሄርም አብሮን የሚደክም የቆሎ ጓደኛችን ይመስለናል፡፡ እግዚአብሄር አባታችንም ቢሆን የቆሎ ጓደኛችን ግን አይደለም፡፡

ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነት በጥንቃቄ ልናደርገው ይገባል፡፡ አክብሮት የጎደላቸውና ንግግሮችና ዝንባሌዎች ከህይወታችን ልናስወግድና በትህትና ከእግዚአብሄር ጋር ልንኖር ይገባል፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? . . . ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ሚክያስ 6፡8

ልትሰማና ልታውቅ ይገባል ይላል እግዚአብሄር፡፡ የዚህ ሁሉ ንግግር ምንጩ አለማወቅ ነው፡፡

እግዚአብሄ የዘላለም አምላክ ነው

አግዚአብሄር ተለማማጅ መሪ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር አንተን እንዴት እንደሚመራ ፣ አንተን እንዴት እንደሚይዝህና እንደሚንከባከብህ ፣ አንተን እንዴት እንደሚያስተዳድርህ ከጊዜ ወደጊዜ ልምድን እያካበተ የሚሄድ መሪ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ከዘላለም የነበረ መሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከዘመናት ጀምሮ ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር የዘላለም አምላክ ነው፡፡

እግዚአብሄር እንዴት ሊይዝህ እንደሚገባው ለመምከር ከዳዳህ እባክህ አፍህን አታበላሽ፡፡ እግዚአብሄርን አትመክረውም፡፡

የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው? ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ሮሜ 11፡34-35

እግዚአብሄር የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው

እግዚአብሄር ሃያል ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለውን የሃይል መጠን ተረድተን አንጨርሰውም፡፡ እግዚአብሄር በምድር ውስጥ እንዳንድ ነገሮችን ያገኘ ሳይንቲስት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር በቀናት የፈጠራቸውን ነገሮች የአለም ምርጥ ሳይንቲስቶች በክፍለ ዘመናት ሁሉ ተማራምረው ተመራምረው ተመራምረው አልጨረሱትም፡፡

የእግዚአብሄር ማስተዋል አይመረመርም

እግዚአብሄርን ተረድተን ለመጨረስ መሞከር የውድቀት መጀመሪያ ነው፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለው ነገር በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ ማረፍ ብልህነት ነው፡፡ በእግዚአብሄር በጎነት ላይ መደገፍ ጥበብ ነው፡፡ የሚያስጨንቀንን በእርሱ ላይ መጣል የአባት ነው፡፡

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርምያስ 29፡11-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄር #የዘላለምአምላክ #የምድርዳርቻ #መታመን #መደገፍ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በገድል አምናለሁ!

rome-swordfighing-NINA-CAPLAN-large.jpgመልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

የምንኖረው ጠላት ዲያቢሎስ በሚሰራበት አለም ውስጥ ነው፡፡ ኢየሱስን ለመከተል ስንወስን በቅፅበት የሰይጣን ጠላቶች ሆነናል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በምድር የሰጠንን ሃላፊነት ሰርቶ ለማለፍ ተጋድሎ ይጠይቃል፡፡

ይህ የእምነት ተጋድሎ እግዚአብሄ የሰጠን ተጋድሎ ስለሆነ መልካም ተጋድሎ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያልሰጠን ተጋድሎዎች በሙሉ መልካም ተጋድሎዎች አይደሉም ውጤትና ፍሬም የላቸውም፡፡ ሰው በራስ አነሳሽነት የሚታገላቸው ተጋድሎዎች ውጤት አልባና የብክነት ተጋድሎዎች ናቸው፡፡

ለምሳሌ ሰው ከሰው ጋር ያለው ተጋድሎ ፣ ከሰው ጋር ያለ ፉክክርና ከንቱ ውድድር መልካም ያልሆነ ተጋድሎ ነው፡፡ ከሰው ጋር የምናደርገው የጦርና የጠብ ተጋድሎ እግዚአብሄር የሰጠን መልካም ተጋድሎ አይደለም፡፡

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡2-3

ሰው በራሱ መንገድ እግዚአበሄርን ለማስደሰት የሚያደርገው ተጋድሎ መልካም ተጋድሎ አይደለም፡፡ መልካም ተጋድሎ እግዚአብሄር ለሰው ልጅ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ኢየሱስን አዳኝና ጌታ አድርጎ መቀበል ነው፡፡ ሰው ግንብ ይህንን ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለለትን የሃጢያት እዳ ክፍያ ትቶ በራሱ መንገድ እግዚአብሄርን ለማስደሰት መሞከር መልካም ተጋድሎ አይደለም፡፡  ሰው በግብረገብ ለመዳን መሞከርና መፍጨርጨር ኢየሱስ የከፈለውን መስዋእት ከንቱ ስለሚያደርገው መልካም ተጋድሎ አይደለም፡፡ ሰው በራሱ ህግን ለመፈፀም መሞከር እግዚአብሄር የሚፈልገው ውጤታማ ተጋድሎ አይደለም፡፡ ህግን ጠብቆ ለመዳን መሞከር ከነፃ የእግዚአብሄር ስጦታ ከደህንነት ፀጋ መንገድ መውደቅ ነው፡፡

በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ገላትያ 5፡4

ስለሚበላና ስለሚጠጣ የምንጨነቀው ጭንቀትና ተጋድሎ እግዚአብሄር ጎሽ የሚለው ተጋድሎ አይደለም፡፡ ሰው አስቀድሞ የእግዚአብሄርን መንግስት መፈለግ ነው ያለበት፡፡ ሰው ግን የእግዚአብሄርን መንግስት ከመፈለግ ይልቅ ስለሚበላና ስለሚጠጣ ላይ ታች ማለቱ መልካም ተጋድሎ አይደለም፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ማቴዎስ 6፡31

ይህን ተጋድሎ ልዩ የሚያደርገውና መልካም ያሰኘው እግዚአብሄር ከእኛ የሚጠብቀው ብቸኛ ተጋድሎ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ተጋድሎ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው ብቸኛው ተጋድሎ ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህ ተጋድሎ እግዚአብሄር አብሮት የሚሰራ ተጋድሎ ነው፡፡ ይህ ተጋድሎ ብክነት የሌለበት ፍሬያማ ተጋድሎ ነው፡፡ ይህ ተጋድሎ ውጤቱ ሁልጊዜ ድል የሆነ ተጋድሎ ነው፡፡

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4

የእምነት ገድል እግዚአብሄር ቃል ላይ በመቆምና በመፅናት የምንጋደለው ተጋድሎ ነው፡፡ የእምነት ገድል ኢየሱስ በመስቀል ላይ የፈፀመልንን ድል የእኛ ድል አድርገን መኖር ነው፡፡ የእምነት ገድል እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠንን አላማ እስከመጨረሻው ማስፈፀም ነው፡፡ የእምነት ገድል እግዚአብሄር የሰጠንን አገልግሎት መምድር ላይ ፈጽመን እግዚአብሄን ማስከበር ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ተጋድሎ #አላማ #ቃል #ውጤት #ድል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእግዚአብሔር እመኑ

duck_on_water_by_miku.jpgልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐንስ 14፡1

ኢየሱስ አለ “በእግዚአብሄር እመኑ”፡፡ በእግዚአብሄር የማያምን ሰው አለ ወይ የሚል ጥያቄ ይጠየቅ ይሆናል፡፡ ምክኒያቱም ሁሉም ሰው በእግዘኢአብሄር እንደሚያመን ይናገራል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያምን ሰው አለ፡፡ እግዚአብሄርን የማያምን ሰው አለ፡፡ ሁሉም ሰው እግዚአብሄርን አያምንም፡፡

እምነት የሚለካው በስራ ነው፡፡ ሰው አግዚአብሄርን አምናለሁ እያለ እግዚአብሄርን የሚያምን ሰው ስራን ካልሰራ ወይም እግዚአብሄርን እንደሚያምን ሰው ካልኖረ እግዚአብሄርን እንደማያምን ግልፅ ነው፡፡

እምነት በአይን የሚታይ ነገር አይደለም እምነት ግን በድርጊት ይገለፃል፡፡ በእግዚአብሄር የሚያምን ሰው የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ በእግዚአብሄር የማያምን ሰው የሚያደርገው ነገር ደግሞ አለ፡፡ በእግዚአብሄር የሚያምን ሰው የማያደርገው ነገር አለ፡፡ በእግዚአብሄር የማያምን ሰው የማያደርገው ነገር አለ፡፡

እግዚአብሄርን ማመናችንና አለማመናችን የሚያሳዩ ምልክቶች

በእግዚአብሄር የሚያምን ያርፋል

ሰው በእግዚአብሄር አምናለሁ እያለ ካላረፈ በእግዚአብሄር አላመነም፡፡ ያመነ ሰው ልቡ አይታወክም፡፡ ያመነ ሰው ሰላሙን አያጣም፡፡

ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። መዝሙር 46፡2

ሰው የራሱን ደረጃ በራሱ ከፍ አድርጎ ከሰቀለ በእግዚአብሄር አያምንም፡፡ የሰውን ክብር የሚፈልግ ሰው እግዚአብሄርን አላመነም፡፡

እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? ዮሐንስ 5፡44

ያመነ ሰው ራሱን ለማዋረድ አይከብደውም

ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ዮሐንስ 13፡3-5

ሰው በሁኔታዎች ሰላሙን ካጣ በእግዚአብሄር አላመነም፡፡

ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። ዮሐንስ 14፡27

በአንዳንደ ነገሮች እግዚአብሄር እንደማያስፈልገው የሚያስብ ሰው በእግዚአብሄር አልታመነም፡፡

እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መዝሙር 105፡4

ሰው ከሰው እድገትን ከጠበቀ በእግዚአብሄር አላመነም፡፡ ሰው ሰውን እንዲያነሳው ተስፋ ካደረገ እግዚአብሄርን አልታመነም፡፡ ሰው በአንድ ጊዜ በሰውም ላይ በእግዚአብሄር ላይ ሊታመን አይችልም፡፡

ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤ መዝሙር 75፡6

ሰው ስለስኬቱ በሰው ላይ ልቡን የሚጥል ሰው በእግዚአብሄርን አላመነም፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። ኤርምያስ 17፡5

ሰው ለእግዚአብሄር ላለመስራት ከሰሰተ በእግዚአብሄር አላመነም፡፡ ሰው ሲያምን ለእግዚአብሄር ሁሉን ነገሩን ይሰጣል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ከመስጠት የሚሰስተው ነገር ካለ አልታመነም ማለት ነው፡፡

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ። ማቴዎስ 25፡24-25

ያመነ ሰው ጌታን በትግስት ይጠብቃል

ሰው እግዚአብሄርን ለመጠበቅ ትግስት ካጣ በእግዚአብሄር አላመነም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን አመጣጥ ካልታገሰ እምነት ጎድሎታል፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20

እጦትን የሚፈራ ሰው በእግዚአብሄር አልታመነም

የታመነ ሰው እጦትን አይፈራም፡፡ የታመነ ሰው እጦት እንዳይደርስበት የማይገባውን አያደርግም፡፡ የታመነ ሰው እጦትን ይንቃል፡፡ የታመነ ሰው እጦት ምንም እንደማያመጣና ሁሉን የሚችለው ኃይልን በሚሰጠው በክርስቶስ እንደሆነ ያምናል፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12-13

ስለህይወቱ የሚጨነቅ ሰው እግዚአብሄርን አልታመነም

እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ማቴዎስ 6፡30-31

ባለጠግነት ጥበብና ሃይል ሀይወቴን ያቃኑታል ብሎ የሚያስብ ሰው በእግዚአብሄር አልታመነም፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐንስ 14፡1

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል

walking-on-water-prank.jpgኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡  በእግዚአብሄር ፊት ያለን ቦታ እንዴት ልዩ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን ክብር እንዴት ድንቅ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለን ስልጣን እንዴት ታላቅ ነው፡፡

ለሚያም ሁሉ ይቻላል፡፡ ለሚያምን የማይቻል ነገር የለም፡፡ እምነት የማይፈታው ቁልፍ የለም፡፡ ለሚያምን የሚያቅተው ነገር የለም፡፡ እምነት የማይደርስበት ከፍታ የለም፡፡ እምነት የማይሻገረው ርቀት የለም፡፡ እምነት የማደርስበት ስፍራ የለም፡፡

እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ የእምነት ሃይል ለሁሉም የተሰጠ ነው – ለሚያምን ሁሉ፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡፡ ሁሉን መቻል እምነት ላለው ሁሉ የተሰጠ መብት ነው፡፡

እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ስለህይወታችን ክፍል እግዚአብሄር የሚለውን መስማት እምነትን ያመጣል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 1፡17

የእግዚአብሄርን ቃል ሲመጣልን ለቃሉ የመጀመሪያ ስፍራ በህይወታችን በመስጠት ቃሉን ማሰላሰል አለብን፡፡

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። ኢያሱ 1፡8

የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከቃሉ ስናገኝ ንግግራችን ሁሉ እንደቃሉ መቃኘት ይኖርበታል፡፡ ቃሉን መናገር ይኖርብናል፡፡

ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡13

እንዲሁም ቃሉን ማድረግ አለብን፡፡ ቃሉን ካላደረገን በቃሉ የተባለልን በህይወታችን ሳይሆን ይቀራል፡፡

ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ያዕቆብ 1፡22

ለሚያምን ሁሉ ይቻላል !

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእለት እንጀራችንን እለት እለት ስጠን

publication11የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ ማቴዎስ 6፡11

ለአብዛኞቻችን መሰረታዊ ፍላጎት ዋና የህይወት ጥያቄ አይመሰለንም፡፡ ነገር ግን ዋናው የህይወት ጥያቄ የእለት እንጀራ ነው፡፡ የእለት እንጀራ ለኑሮ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ፍላጎትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

በህይወት ስለብዙ “ትልልቅ” ነገሮች ጌታን ማመን ያለብን ይመስለናል፡፡ ሰው ለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ካመነ አረፈ ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም በህይወት የሚያስፈልገው ዋና ነገር መሰረታዊ ፍላጎትን አማልቶ ጌታን መከተል ነው፡፡

የመኖር አላማችን ጌታን መከተል ፣ ለጌታ መኖርና ኢየሱስን በህይወታችን ማክበር ነው፡፡ የምንኖረው ለመኖር ብቻ አይደለም፡፡ የምንኖረው ኢየሱስን በመምሰል ስለ ኢየሱስ አዳኝነትና ጌትነት በምድር ላይ ለመመስከር ነው፡፡

ስለ ኢየሱስ አዳኝነትና ጌትነት በምድር ላይ ለመመስከር የሚያስፈልገን መሰረታዊ ፍላጎታችን መሟላቱና ነው፡፡

ብዙ ሰው ስለብዙ ነገር ታላቅ እምነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ሰው ኢየሱስ ስለ እርሱ ሃጢያት በመስቀል ላይ እንደሞተ ከማመን ቀጥሎ የመጀመሪያውና መሰረታዊው እምነት ስለ እለት እንጀራው ወይም ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ማመን ነው፡፡

ስው ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ካላመነ ስለምንም ሌላ ነገር አምናለሁ ሊል ይዋሻል፡፡ ሰው ስለመሰረታዊው ፍላጎቱ ካላመነ ስለ ትልልቅ ነገር ጌታን አምናለሁ ቢል ምንም አይጠቅመውም፡፡

ሰው ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ስለሚበላው ፣ የቤት ኪራይ ስለሚከፍለው ፣ ስለ ልጆቹ ትምህርት ቤት ፣ ስለ መኪናው ነዳጅ ጌታን ካመነ እግዚአብሄርን በነፃነት ማገልገል ይችላል፡፡ የኑሮ ጭንቀት ፊት ከሰጠነው ማናችንንም በቁማችን ሊውጠን ስለሚችል ሰው ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ካላመነ ጌታን ለማገልገል ነፃነት ሊኖረው አይችልም፡፡

ሰው ብዙ አላስፈላጊ እርምጃ ሲወስድ የሚየታየው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ባለማመኑ ነው፡፡ ሰው የሚዋሸው ፣ የሚያጭበረብረው ፣ ሌላውን የሚጠላው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ስለማያምን ነው፡፡

ስለመሰረታዊ ፍሎጎቱ ጌታን ያመነ ሰው ጌታ የእለት እንጀራውን በእለቱ እንደሚሰጠው አጥብቆ የተረዳ ሰው ፀጥና ዝግ ብሎ በመኖር ጌታን ሲያሳይ ለብዙዎች ምሳሌ ሊሆንና በሚቀናበት የክርስትና ህይወት ጌታን በምድር ቆይታው ሲያስከብ እናያለን፡፡

የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ ማቴዎስ 6፡11

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እኔ ኤልሻዳይ ነኝ

Talking from the heart Blog

%e1%8a%a0%e1%8a%a4%e1%88%8d%e1%88%b8%e1%88%bb%e1%8b%b0%e1%8b%b3%e1%8b%adአብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ዘፍጥረት 17፡1
ሰዎች ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር ለእነርሱ ስለሚያደርገግላቸው ነገር በጣም ሲጨነቁ ይታያል፡፡ ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ስለእግዚአብሄ ድርሻ በመጨነቅ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ትኩረታቸው እግዚአብሄር እንዴት ቃሉን እንደሚፈፅመው በማውጣትና በማውረድ ነው፡፡እግዚአብሄርን ማንም አያስተምረውም፡፡ እንዴት እንደሚፈፅመው ያውቅበታል፡፡
እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28
የእግዚአብሄርን ድርሻ ለመስራት ስንሞክር የራሳችንን ድርሻ እንረሳለን፡፡ የራሳችን ድርሻ ላይ ብቻ ብናተኩር የእግዚአብሄር ፈቃድ በሙላት በህይወታችን ይፈፀማል፡፡ ወራሽ የለኝም ብሎ እግዚአብሄር ቃል ኪዳኑን እንዴት እንደሚፈፅም ላልተረዳ አብርሃም እግዚአብሄር እንዲህ አለው፡፡
እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
እግዚአብሔር ስለእኔ አታስብ፡፡ እኔ ሁሉን ቻይ ነኝ፡፡ ከእኔ ጋር ስትነጋገር ውስን ከሆነ ከሰው ጋር እንደምትነጋገር ማሰብ የለብህም፡፡ እኔ ሁሉን እችላለሁ እያለው ነው፡፡ ካንተ የሚጠበቀው ግን በፊቴ መመላለስ ነው፡፡ በፊቴ እንደምትኖር ኑር፡፡
በፊቴ ውጣ በፊቴ ግባ፡፡ እኔ የምታደርገውን ሁሉ ልይልህ፡፡ በምታደርገው ነገር ሁሉ ልምራህ፡፡ በዚህም ፍፁም ሁን፡፡ በዚህም ታዘዘኝ፡፡…

View original post 61 more words

ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን

mountainኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ ወንጌል 11፡22-23
መፅሃፍ ቅዱሳችንን ስናጠና በጣም የሚያስደንቀንና የሚያስገርመን ነገር በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን ቦታ እጅግ የከበረ እንደሆና እኛ ራሳችንን እንደምናየው እግዚአብሄር እኛን እነደማያየን ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለንን ቦታ በትክክል የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ዘንድ ያለንን ስልጣን የምንጠቀምበት በመናገር እንደሆነ ኢየሱስ ያስተምራል፡፡ በክርስቶስ የዳነ ሰው ቃል ስልጣን አለው፡፡ በክርስቶስ ያለ ሰው በቃሉ ያለው ስልጣን አስደናቂ ነው፡፡
ማንም ያለው እንዲደረግለት በማለት በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን የልጅነት ስልጣንና ቦታ እጅግ ልዩ እንደሆነና መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ ማንኛውም ነገር ንግግራችንን እንደሚያከብርና ለቃላችን እንደሚገዛ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ ያስተምራል፡፡ ንግግራችን ግን የእምነት ንግግር መሆን እንዳለበት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ የእምነት ንግግራችን ተራራን መንቀል የሚችል ጉልበት አለው፡፡
ንግግራችን ሁኔታችንን የመለወጥ ውጤት እንዳያመጣ የሚያደርገው የልብ ጥርጥር እንደሆነም ይነግረናል፡፡ ንግግራችን በልብ ጥርጥር ከሆነ አይሰራም፡፡ ቃላችን ግን በልብ በእምነትና ጥርጥር የሌለበት ከሆነ ንግግራችን ነገራችንን ይለውጣል፡፡ ነገራችን ቃላችንን ከመታዘዝ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡
ስለ ሁኔታችን የማንጠራጠረው ደግሞ እምነት ሲኖረን ነው፡፡ እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሄር ቃል ከመስማት ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
ስለምናገረውን ነገር እምነት የሚኖረን የእግዚአብሄር ቃል ስለሁኔታው ምን እንደሚል ፈልገን ስናገኝ ነው፡፡ ስለሁኔታችን ከእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄርን ፈቃድ ካገኘን እምነት ይኖረናል፡፡ በእምነት የምንናገረው ነገር ደግሞ ሁኔታችንን ይለውጣል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነው

huge-9-47943ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። 1ኛ ዮሐንስ 4፡4
አለም በክፉ ተይዞዋል፡፡ አለም እንዲደግፈንና እንዲያበረታታን አንጠብቅም፡፡ አለም ጎሽ እንዲለንና እንዲረዳን አንጠብቅም፡፡ አለም በቻለው አቅም ይቃወመናል፡፡ አለም በቻለው አቅም ታላቅነቱን ሊያሳየን ይሞክራል፡፡ አለም በቻለው አቅም እኛ ትንሽ እነደሆንን ሊያሳየን ይሞክራል፡፡ በአለም ያለው የሚያስፈራራ ነው፡፡ በአለም ያለው የሚንቅና ዝቅ ዝቅ የሚያደረግ ነው፡፡ በአለም ያለው በፍርሃት አስሮ ለማስቀመጥ የሚጥር ነው፡፡ ከአለም የምንጠብቀው ተግዳሮትና መቋቋምን ብቻ ነው፡፡
የአለም ስርአት ከፈቀድንለት ለእግዚአብሄ እንዳንኖር አሳስሮ ሊያስቀምጠን ነው የሚጥረው፡፡ እህህ ብለን ከሰማነው እንደጠፋን እንደማይከናወንልን ነው አለም በጩኸት የሚነግረን፡፡ አለም ከሰማንና ከተቀበልነው እግዚአብሄር በህይወታችን ያለው አላማ እንደማይፈፀም ነው የሚነግረን፡፡ ምክኒያቱም አለም በክፉ ተይዟል፡፡
ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን። 1ኛ ዮሐንስ 5፡19
አለም ምን ያህል ደካማና ለምንም የማንበቃ እንደሆንን ሊያሳየን ነው የሚፈልገው፡፡ የአለም ስርአት እኛ ምንም እንዳይደለንና ለምንም እንደማንበቃ ሊያስፈራራን ነው የሚመጣው፡፡ አለም በክፉ የተያዘ ነው፡፡ አለም ውሸትን የተሞላ ነው፡፡ እውነት የሆነው መፅሃፍ ቅዱስ ግን በእኛ ውስጥ ስላለው ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡
በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። ምክኒያቱም ከእግዚአብሄር ናችሁ ፡፡ ያሸነፋችሁበት ምክኒያት በእናንተ ያለው ከአለም ካለው ታላቅ ስለሆነ ነው፡፡ በውስጣችን የሚኖረው ኢየሱስ አለምን ያሸነፈ ነው፡፡
በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። . . . ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። ዮሃንስ 16፡33
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #አለም #ታላቅ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #በረከት #ትግስት #መሪ

ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ

covenantአብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ዘፍጥረት 14፡22-24
እግዚአብሄር አብርሃምን ጠራውና ከእርሱ ጋር ቃልኪዳንን ገባ፡፡
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። ዘፍጥረት 12፡1-3
አብርሃምም አምኖ እግዚአብሄርን ታዘዘ፡፡ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ እግዚአብሄርን ተከተለው፡፡
እግዚአብሄር እንደሚባርከው አብርሃም ቅንጣት ጥርጥር አልነበረውም፡፡ አብርሃም ይጠነቀቅ የነበረው የእግዚአብሄር በረከትና የሰው በረከት በህይወቱ እንዳይቀላቀል ብቻ ነበር፡፡
ሰዎች ስጦታ ሊሰጡት ሲመጡ አመጣጣቸውን አይቶ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት የሚሉ አይነት ከሆነ ስጦታቸውን አይቀበልም ነበር፡፡ ምክኒያቱም አብርሃም እግዚአብሄር እንደሚባርከው ምንም ጥርጥር አልነበረውም፡፡ አብርሃም ይጠነቀቅ የነበረው የእግዚአብሄር ቃልኪዳን ሲፈፀም ከሰው ስጦታ ጋር እንዳይቀላቀልበት ነበር፡፡
የአብርሃምን የመበልፀጉን ምስጋና ሰው እንዳይወስድ ይጠነቀቅ ነበር፡፡
አብርሃምን የሚያሳስበው እግዚአብሄር ቃል ኪዳኑን ጠብቆ መባረኩ በፍፁም አልነበረም፡፡ እግዚአብሄር እንደሚባርከው ምንም ጥርጥር አልነበረውም፡፡ አብርሃምን የሚያሳስበው እግዚአብሄር ሲያበለፅገው ሰዎች ክብሩን እንዳይወስዱ ብቻ ነበር፡፡
ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤
አብርሃም ከእግዚአብሄር ጋር የቃልኪዳን አጋር ነውና በአብርሃም መበልፀግ ማንም ምስጋናውንና ክብሩን መውሰድ የለበትም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
#ኢየሱስ #ጌታ #ልብ #መዳን #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #አብርሃም #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

ምኑ ነው አዲስ?

7013647-new-plant-growth-wallpaperስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17
ስለሃጢያቱ በመስቀል ላይ ዋጋ የከፈለውን ኢየሱስን የተቀበለ ሰው ሁሉ አዲስ ፍጥረት ነው፡፡ አዲሱ ሰው እርጅናና ድካም የማያውቀው አዲስ ፍጥረት ነው፡፡ ኢየሱስን እንደ አዳኙና የህይወቱ ጌታው አድርጎ የተቀበለ ሰው አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል፡፡ ግን አዲስ የሆነው ምንድነው ?
 • ልጅነቱ አዲስ ነው፡፡ ሰው በሃጢያት እስራት እያለ የእግዚአብሄር ልጅ አልነበረም፡፡ እውነት ነው የእግዚአብሄር ፍጥረት ነው የእግዚአብሄር ልጅ ግብን አልነበረም፡፡ ሰው በአመፅ ሲኖር የዲያቢሎስ ልጅ ነው፡፡
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሃንስ 8፡44
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። 1ኛ ዮሃንስ 3፡2
 • ወዳጅነታችን አዲስ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ወዳጅ አልነበረም፡፡ ሰው የእግዚአብሄር ጠላት ነበረ፡፡ አሁን ግን ሰው በክርስቶስ የእግዚአብሄር ወዳጅ መሆን ይችላል፡፡
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ሮሜ 5፡10
ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና። ዮሃንስ 15፡15
 • ህያውነታችን አዲስ ነው፡፡ ሰው ቆሞ ይሂድ እንጂ በእግዚአብሄር እይታ ሙት ነበረ፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒያት ለዘላለም ከእግዚአብሄ ተለይቶ ነበረ፡፡ ሰው ክርስቶስን በመቀበል እግዚአብሄር ይቀበለዋል፡፡ ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር ይኖራል፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ ኤፌሶን 2፡1
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡5
 • የሰይጣን መጠቀሚያ ነበርን፡፡ የምንኖረው በሰይጣን ፈቃድ ነበር፡፡ አሁን ግን ከሰይጣን ግዛት ወጥተናል፡፡ እኛ ስፍራ ሰጥተነው ካልሆነ ሰይጣን በእኛ ላይ ምንም ስልዕጣን የለውም፡፡
በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ኤፌሶን 2፡2
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሉቃስ 10፡19
 • ሰላማችንና መታረቃችን አዲስ ነው፡፡ የቁጣ ልጆች ነበርን፡፡ እግዚአብሄር በሃጢያታችንና በአመፃችን ደስተኛ አልነበረም፡፡ አሁን እግዚአበሄ ተቀብሎናን ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ስራ እግዚአብሄር በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ረክቷል፡፡
በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ኤፌሶን 2፡3
እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ 2ኛ ቆሮንጦስ 5፡14-15
 • ተስፋችን አምላካችን አዲስ ነው፡፡ ካለ እግዚአብሄር ካለተስፋ ነበርን፡፡ አሁን ግን አምላክ አለን፡፡ አሁን ግን ተስፋችን ሙሉ ነው፡፡
በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። ኤፌሶን 2፡12
መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። ኤፌሶን 2፡17-19
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ

የሰው ፍቅር

%e1%8d%8d%e1%89%85%e1%88%adበሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡1

ሰው የሚያከብረውም ሆነ የሚያዋርደው ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ያለው ሰው የከበረ ሰው ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ደግሞ የተዋረደ ነው፡፡

ሰው የተሰራው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው የተሰራበት አላማ ከጎደለው ባዶ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በመጀመሪያ እግዚአብሄርን እንዲወድ እንዲሁም ሰውን እንዲወድ ነው ፡፡

አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። ማርቆስ 12፡30-31

ሰውን የሚያከብረው የፍቅር ድርጊት ነው፡፡ ሰው ምንም ችሎታ ቢኖረው በፍቅር ልብ ካላደረገው ምንም አይጠቅመውም፡፡ ሰው ለእግዚአብሄርም ሆነ ለሰው ምንም ስጦታ ቢሰጥ ከፍቅር ልብ የመነጨ ስጦታ ካልሆነ ከንቱ ነው፡፡

በፍቅር ያልሆነ የሰው ተሰጥኦ ከንቱ ነው፡፡ ሰው ታላቅ የመናገር ስጦታ ቢኖረው እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽልና እንደሚጮኽ ናስ ትርጉም የሌለው ረባሽ ነው፡፡

ሰው ፍቅር ከሌለው ለማንም አይጠቅምም፡፡ ፍቅር የሌለው ሰው ለራሱም ምንም አይጠቅመውም፡፡

ሰውን የሚያከብረው ፍቅር ስለሆነ ሰው በአለም ላይ አለ የሚባለው እውቀት ቢኖረው ፍቅር ግን ከሌለው ከንቱ ነው፡፡

የሰውን መስዋዕትነት የሚያከብረው ከፍቅር ልብ መምጣቱ ነው፡፡ ሰው ድሆችን ለመመገብ ታላቅ መስዋዕትነት ቢከፍል ከፍቅር ልብ የመነጨ ግን ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ፍቅር ሁሉን ያምናል

ጥላቻ ከእግዚአብሄር አይደለም

የፍቅር ጀብደኛ

Love Adventure

ፍቅር ምርጫ ነው

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

እምነት አሁን ነው

downloadስለእምነት አስፈላጊነት ተናግረን አናበቃም፡፡ ምክኒያቱም ምንም ምንም ብናደርግ የምናደርገው ሁሉ በእምነት መሆን አለበት፡፡ ያለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የተሳካ ግንኙነት እንዲኖረን እምነት ወሳኝ ነው፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነትን ደግሞ የምንለማመደው አሁን ነው፡፡

እምነት ረስተን ረስተን አስቸጋሪ ነገር ሲመጣ የምንመዘው መጠባበቂያ መሳሪያ አይደለም፡፡ እምነት በቀን ተቀን ህይወታችን የምንለማመደውና የምናዳብረው ነገር ነው፡፡

በሰውነት እንቅስቃሴ ልምምድ ሰውነታችንን እንደምናስለምደው ሁሉ ራስን ለመንፈሳዊነት ነገር ማስለመድ ጊዜንና የሚጠይቅ ነገር ነው፡፡ ማስለመድ የአንድ ቀን ስራ አይደለም፡፡ ይበልጥ ቶሎ ቶሎ እንደልምድ ካደረግነውና የህይወት ዘይቤያችን ከሆነ ይበልጥ ለከባድም ነገር ለመጠቀም እየቀለለ ይሄዳል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ፈተና ሳይመጣ በፊት አስቀድመን ራሳችንን  ለፈተና በፀሎት መገንባት እንዳለብን ይናገራል፡፡

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። ማቴዎስ 26፡41

በህይወትም በመጀመሪያ በወጣትነታችን እግዚአብሄርን እንድንፈራና ህይወታችንን በእግዚአብሄር ሃሳብ እንድንገነባ መፅሃፍ ያስተምራል፡፡

የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤መክብብ 12፡1

መፅሃፍ በክርስትና አዲስ የተወለዱ ህፃናት ለስጋና ለጠንካራ ምግብ ራሳቸውን ለማዳበር በታማኝነት ለወተት ታማኝ መሆን እንዳለባቸው ያስተምራል፡፡

ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡2-3

እንዲሁም እምነት የምንለማመደው ከምናውቀው ከትንሹ ነገር ነው፡፡ በተረዳነው ከእግዚአብሄር ቃል የእምነትን እርምጃ መውሰድ እንጀምር፡፡ ይህ ቀላል ነገር ነው ከምንለው ጀምረን አግዚአብሄርን እንታዘዝ፡፡

ይህ የዛሬ ቀላል የእምነት እርምጃ ለነገው ከባዱ የእምነት እርምጃ መንፈሳዊ ጡንቻችንን ያሳድገዋል፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!

ለተጨማሪ ፅሁፎች

ታመን

እመን ብቻ እንጂ አትፍራ!

 

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ከሐዲ ልብ

9-22-cc-guardyourheart_566029787-1አንድን ሰው አይታችሁዋል፡፡ እግዚአብሄርን ሲያመልክ የነበረ ሰው ፣ ጌታን አገልግሎ የማይጠግብ የነበረ ሰው ፣ እግዚአብሄርን በቀላሉ ያምን የነበረ ሰው ነገር ግን ሁሉም ነገር ጠፍቶበት እግዚአብሄርን ለቀላል ነገር ማመን ሲያቅተው ፣ የእግዚአብሄርን ሃይል ሲክድና ባለማመን ሲሞላ እግዚአብሄርን ማገልገል ሞኝነት ሲመስለው አይታችኋል?
መጠንቀቅ እንጂ እኔ እንደዚያ ልሆን አልችልም ማለት አያስፈልግም፡፡ ያም ሰው አንድ ቀን “እኔን አይመለከተኝም እኔ ልወድቅ አልችልም በጣም ሩቅ መጥቻለሁ” ሲል የነበረ ከመጠን ያለፈ መተማመን በራሱ የነበረው ሰው ነበር፡፡
እንደዚህ አይነት ሰው የወደቀበትን ውድቀት ስናይ ከዚህ በፊት ጌታን ተረድቶት እንደነበር እንጠራጠራለን፡፡ እውነቱ ግን ማንም ሰው ሊወድቅ ይችላል፡፡ ከዚህ ውድቀት አልፌያለሁ እኔን አይነካኝም ሊል የሚችል ሰው የለም፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ “ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ” የሚለው፡፡ሮሜ 11:20
የልብ ችግር ከባድ ችግር ቢሆንም ነገር ግን መፍትሄ የሌለው ችግር አይደለም፡፡ ለዚህ የልብ ክፋት ችግር መፅሃፍ ቅዱስ ፍቱን መድሃኒት አለው፡፡
በመጀመሪያ ሰው እግዚአብሄርን የሚያስክደው ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ሊጠነቀቅ ይገባዋል፡፡ የሚወድቀው የማይጠነቀቅና “እኔ ከመውደቅ አልፌያለሁ” የሚል ሰው ነው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ልባችን በጥንቃቄ የምንከታተለው እንደሆነ ያስተምራል፡፡ ልባችንን በቸልታ ከያዝነው ሊያስተን የሚችል ትልቅ ሃይል ያለው ነው፡፡
ጌታን ብዙ ዓመት ከተከተልንና ካገለገልን በኋላ አንዳንዴ በልባችን የምናገኘው ክፉ ሃሳብ እኛን ራሳችንን ያስደነግጠናል፡፡እንደዚህ አይነት ሃሳብ ከእኔ ልብ ነው የወጣው ብለን አንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡
ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ማቴዎስ 15፡19
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? ኤርምያስ 17፡9
ልብን በጥንቃቄ መያዝ የሚበጀው ክፋት ሁሉ የሚወጣው ከልብ ስለሆነ ነው፡፡ ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ዕብራውያን 3፡12
የሰውን ልብ የሚያውቅውና ሊገራው የሚችለው የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው ወደ ልባችን ሊደርስ የሚችለው፡፡ በልባችን ያለውን ነገር ሁሉ እንደ እንደእግዚአብሄር ፈቃድ የሚያሳየንና የሚያስተካክለው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ፊት ሁሉ ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡12-13
ስለዚህ ነው ከምንም ነገር በላይ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት መትጋት ያለብን፡፡ ስለዚህ ነው ልባችንን በንፅህና ለመጠበቅ ማድረግ ያለብንን ነገር ሁሉ ማድረግ ያለብን፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፣ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና” የሚለው፡፡ ምሳሌ 4፡23
ስለዚህ ነው የእግዚአብሄር ቃልን ከሚያስቡና ከሚናገሩ ሰዎች ጋር በየእለቱ ህብረት ማድረግና መመካከር ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረን መፍትሄ እንደሆነ የሚናገረው፡፡ ስለዚህ ነው ህይወታችን የእግዚአብሄርን ቃል በሚረዱ ሰዎች ፊት መፈተን ያለበት፡፡
የእግዚአብሄርን ቃል የሚረዱ እህቶችና ወንድሞች ናቸው እኛ ያላየነውን የልባችንን ክፋት የሚነግሩንና ልብህ ንፁህ አይደለም ብለው የሚገስፁን፡፡
ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ ዕብራውያን 3፡13
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ተመካከሩ #ከሃዲ #እልከኛ #ልብ #ቃል #ምስጉን #ሃሳብ #ማሰላሰል #ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #ፌስቡክ #አዋጅ

አካባቢያችንን እንጠብቅ

%e1%8a%a0%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%89%a0ሰው አካባቢውን ከአየርና ከውሃ ብክለት ለመጠበቅ ታላቅ እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ ሰዎች የአለምን አረንጓዴነትና ለጤና ተስማሚነት ለመጠበቅ ማንኛውም ነገር ያደርጋሉ፡፡
ምድርን የሚበክልን ነገር ለምሳሌ የከታላላቅ ፋብሪካዎች የሚወጣውን የተበከለ ጭስ እንዲቀነስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ምክኒያቱም በቀጣይነት በቆሻሻ አካባቢ ውስጥ የሚኖር ሰው ከመታመምና ከመሞት ሊያመልጥ አይችልም፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን አለማችንን የሚበክለው እግዚአብሄርን ባለማመንና ጥርጣሬ ነው፡፡ ሰው አካባቢውን በእግዚአብሄር ቃል ካልሞላ እግዚአብሄርን ካላመነ በስተቀር እግዚአብሄርን ደስ ሊያሰኝ ከእግዚአብሄር የሆነውንም ነገር ሊቀበል አይችልም፡፡ ከባቢው ተበላሽቶ እግዚአብሄርን ማመን ካቃተው ሰው የሚበልጥ ምስኪን ሰው የለም፡፡
ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን የአስተሳሰብ አካባቢያችንን በመበከል መንፈሳዊ ጤንነታችንን የሚጎዱ ነገሮችን ሊያስፋፋ ይመጣል፡፡
የሰይጣን የመስረቂያ የማረጃና የማጥፊያ አካባቢዎች አለማመን ፍርሃትና ጥርጣሬ ናቸው፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አካባቢያችንን በእግዚአብሄር ቃል እንድንሞላና ንፅህናውን ከአለማመን እንድንጠብቅ የሚያስተምረን፡፡ አካባቢያችን በእግዚአብሄር ቃል ስንሞላና የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ ንፁህ መንፈሳዊ አየርን መተንፈስ እንችላለን፡፡
የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ በፍጹምም ነፍስ በፍጹምም ኃይል ለመውደድ አካባቢያቸውን በእግዚአብሄር ቃል እንዲሞሉና ከብክለት እንዲጠብቁና እንዲያፀዱ ተመክረዋል፡፡
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9
የእግዚአብሄር ህዝብ መሪ የነበረው ኢያሱ የእግዚአብሄርን ቃል ለመፈፀም እንዲያስችለው ቃሉን በቀንና በሌሊት እንዲያሰላስልና በቃሉ አካባቢ ውስጥ እንዲኖር ታዟል፡፡
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። እያሱ 1፡8
እግዚአብሄር እንደልቤ ያለው መዝሙረኛው ዳዊት መዝሙሩን የጀመረው አካባቢውን ከክፋት ሃሳብ ብክለት ስለሚጠብቅና በእግዚአብሄር ቃል ከባቢ ውስጥ ስለሚኖረው ሰው ምስጉንነትና የዘወትር ክንውን በመናገር ነው፡፡
ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። መዝሙር 1፡1-3
ሃዋሪያው ሰው አለምን የማይመስልበትን ብቸኛው መንገድ የሃሳብን አካባቢ በእግዚአብሄር ቃል በማፅዳትና በመጠበቅ እንደሆነ ያስተምራል፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
መንፈሳዊ ህይወታችንን ከብክለት ለመጠበቅ በአስተሳሰብ አካባቢያችን የሚፈቀድላቸውና የማይፈቀድላቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደሚገቡ መፅሃፍ ቅዱስ በአፅንኦት ያስተምራል፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊሊጲስዮስ 4፡8
ስለዚህ ነው ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ምን እንደምትሰሙ ተጠበቁ ያላቸው፡፡
አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። ማርቆስ 4፡24
ስለዚህ ነው የእግዚአበሄር ቃል በቤታችን በስልኮቻችን በመኪናችን ልንሰማና ልናነብ የሚገባን፡፡ ለዚህ ነው ባገኘነው አጋጣሚ የእግዚአብሄርን ቃል ከባቢ መፍጠር ያለብን፡፡ ለዚህ ነው የእግዚአብሄርን ቃል ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መጫወት ያለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ለመረዳትና ለመጠበቅ የእግዚአብሄርን ቃል አካባቢ መፍጠርና በከባቢው ውስጥ መኖር አለብን፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ አጥብቀህ አካባቢህን ጠብቅ ያለው፡፡
ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 4፡20 ፣ 22-23
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። ዘዳግም 6፡5-9
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ኢየሱስ ጌታ ነው

jesus-is-lordክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው በሚለው የሶስት ቃላት አረፍተ ነገር ውስጥ እጅግ የተጠቀጠቁ ትርጉሞች ይገኙበታል፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ሲባል
1. ኢየሱስ በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሃያል ነው ማለት ነው፡፡
በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡9-11
2. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት በሞት ላይ ስልጣን ያለውን በሞቱ የሻረ ብቸኛ የነገስታት ንጉስ ነው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ እስኪመጣ ድርስ ሞት ሃያል ጌታ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ሞትን ያሸነፈ ማንም አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ሲመጣ ግን በሞት ላይ ስልጣን ያለውን ሰይጣንን በሞቱ መሻሩን ያሳያል፡፡
እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ ዕብራውያን 2፡14-15
3. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ሃይላትንና ስልጣናትን የገፈፈ የመጨረሻው ባለስልጣን ነው ማለት ነው ፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ቆላስይስ 2፡15
ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ኤፌሶን 1፡20-21
4. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ላይ መሪና ወሳኝ ነው ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በልባችን የመጀመሪያው ስፍራ የእርሱ ነው ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ከእርሱ ጋር የምናወዳድረው ምንም ነገር የለም ማለታችን ነው፡፡ በልባችን ዙፋን ላይ የተቀመጠው ኢየሱስ ነው ማለታችን ነው፡፡
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15 ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል እርሱን ከሁሉም በላይ እንወደዋለን ማለታችን ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል ከእርሱ ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር የለም ማለታችን ነው፡፡ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። ሮሜ 8፡38-39
5. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል ከእጁ የሚነጥቀን ማንም ሃይል የለም በማለት እየተመካን ነው፡፡ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሐንስ 10፡29
6. ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል በህይወታችን ላይ ጌታ ሊሆን የሚችለውን ነገር ሁሉ ላይ ጌታ ነው ማለታችን ነው፡፡
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 8፡38፣37
7. ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት የዳነው በኢየሱስ ጌትነት ነው ማለታችን ነው፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
8. የምንሰብከው እንኳን ጌታ ክርስቶስ ነው፡፡
ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።
9. በቃልም ሆነ በስራ የምናደርገውን ሁሉ በጌታ ኢየሱስ ስም የምናደርገው ስለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ቆላስይስ 3፡17
10. በመጨረሻም የምንነግሰው የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር ነው፡፡
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ። ራእይ 7፡14 ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ንጉስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ክብራችን አይፈቅድም !

bada-kaun-hindi-story-1ልጅነታችን ክብር አለው ልጅነታችን የእግዚአብሄር የቤተሰብነት አባል ታላቅ ክብር አለው፡፡ እንደ ልጅነታችን ክብር የማይስማማ ምንም ነገር ለማድረግ እንፈልግም፡፡ ከልጅነት ክብራችን ጋር የማይሄድ ማንኛውም ጥቅም እንንቀዋለን፡፡ ክብራችን ተነክቶ የምናገኘውን ጥቅም ከምናገኝ ሞት ይሻለናል፡፡
እኔ ግን ከእነዚህ ሁሉ ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡15
አንዳንድ ሰዎች ሃዋሪያው ጳውሎስ ጌታን የሚያገለግለው ስለሚጠቀም ነው ጥቅሙ ቢቀርነት አገልግሎቱን ያቆማል የሚል አመለካከት ለነበራቸው ሰዎች ለማሳየት ሰዎች የሚሰጡትን ስጦታ አልተቀበለም፡፡ ምክኒያም ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡3-4
 • ለመዋሸት ክብራችን እይፈቅድም
ውሸት ከፍርሃት ይመነጫል፡፡ እኛ ደግሞ በፍቅር የምንኖር ስለሆንንና ፍፁም ፍቅርም ፍርሃትን አውጥቶ ስለሚጥል አንዋሽም፡፡ ከምንዋሽ በውሸት የሚመጣው ጥቅምን ቢቀርብን ይሻለናል፡፡ የልጅነትን ክብራችንን እንዲነካ ለምንም ነገር አንፈቅድም፡፡ እውነትን የማንናገርለት ነገር የእኛ እንዳልሆነ እናምናለን፡፡
እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም። ኢሳይያስ 52፥12
 • ለመለማመጥ ክብራችን አይፈቅድም በመሃላ በመለማመጥ በብዙ ቃልና በብዙ ጭንቅ ሰዎችን ልናሳምን አንጥርም፡፡ በእግዚአብሄር እንታመናለን፡፡ እግዚአብሄር ያላደረግልንን ነገር አንወስድም፡፡ የራሳችንን ሃይል ጨምረን የምናመጣው ነገር በእውነት የእኛ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ያላደረገልንን ነገር ሁሉ የእኛ እንዳልሆነ ነው የምንቆጥረው፡፡
በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። ማቴዎስ 5፡36-37
 • ክብራችን ነውረኛን ረብ አይፈቅድም የቤተሰቡ ደረጃ ክብር የሌለበትን ጥቅም ያስንቃል፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ ነው የምናምነው፡፡ በነውር በወስላታነት በታማኝነት ያልሆነ ጥቅምን እንንቃለን፡፡ እግዚአብሄር በክብር እንደሚባርክ እናምናለን፡፡
ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡9
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
 • ለጥቅም ጌታን ማገልገል ክብራችን አይፈቅድም ፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ መስራት ሲችል እራሱ እየሰራ የሚያስፈልገውን ያሟላ ነበር፡፡
ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም። 2ኛ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡8
 • ከስስታም ሰው ለመቀበል ክብራችን አይፈቅድም፡፡
ሰው የሚያደርግልንና የሚሰጠን ደስ ብሎት ከልቡ ካልሆነ እየሰሰተ ከሚሰጠን ሰው ለመቀበል ክብራችን እይፈቅድም፡፡ ሰው በልቡ ባይበላ እያለ ከሚሰጠን መራብ ይሻለናል፡፡
የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፤ በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ። ምሳሌ 23፡6-8
 • ወንጌልን ዝቅ አድርጎ ለሚያይ ሰው ጋር መከራከር ክብራችን እይፈቅድም፡፡ የወንጌልን ክብር ከማይረዳ እንዲያውም ልንጎዳው እንደመጣን ከሚያስብ ሰው ጋር በክርክር ጊዜያችንንና ጉልበታችንን መጨረስ ክብራችን አይፈቅደውም፡፡
በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ። ማቴዎስ 7፡6
 • ከሰነፍ ጋር ለመመላስ ክብራችን አይፈቅድም፡፡ እውነትን ለማወቅ ፈልጎ ከሆነ እንረዳዋለን፡፡ እኛን ለማዋረድ ፈልጎ ከሆነ ለክርክር ጊዜ የለንም፡፡ አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት። ምሳሌ 26፡4
በክርክርና በጭቅጭቅ የሚገኘውን ጥቅም ለማግኘት ክብራችን አይፈቅድም፡፡ ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል። ምሳሌ 20፡3
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ . . . የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡3
 • መስራት እየቻልን የሌላን ሰው እርዳታ አንጠብቅም፡፡
ለለበጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡11-12
 • ቃልኪዳናችን ከእግዚአብሄር ጋር ስለሆነ ስለመባረካችን ስለማደጋችንና ስለመለወጣችን ማንም ስጋ የለበሰ ክብሩን አንዲወስድ አንፈቅድም፡፡ ስለስኬታችን ክብሩን ከጌታ ጋር የሚሻማ ከሆነ ጥቅሙን እንተዋለን፡፡ ሰው እኔ አነሳሁት ከሚለን የሚያደርግልን ይቅርብን፡፡
አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ዘፍጥረት 14፡22-24
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#እግዚአብሔር #አምላክ #ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ፍቅር ሁሉን ያምናል

sprout
ፍቅር አስደናቂ ነው፡፡ በተለይ ፍቅር ሁሉን ያምናል የሚለውን ቃል ሳሰላስል ነበር ያመሸሁት፡፡ ይህን ቃል ሳሰላስል ጌታ የሰጠኝን መረዳት አብሬያችሁ ልካፈል ወደድኩ፡፡
ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ቆሮንጦስ 13፡7
ፍቅር ከሁኔታዎች ያለፈ የማየት ችሎታ አለው፡፡ ፍቅር በጊዜያዊ ሁኔታዎች ላይ አያተኩርም፡፡ከጊዜያዊ ሁኔታ ባለፈ በእግዚአብሔር እቅድ ላይ ስለሚያተኩር ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡
ፍቅር የጊዜያዊውን ብቻ ሳይሆን የሩቁንም ጭምር ያያል፡፡ ፍቅርን ለየት የሚያደርገው የሩቁን እንዲያውም ዘላለማዊውን ጭምር በርቀት ስለሚያይ ሁሉን ያምናል፡፡ ፍቅር በሰው ድካም ላይ አያተኩርም፡፡ ፍቅር ከሰው ድካም ባለፈ በሰው እምቅ ጉልበትና ችሎታ /Potential/ ላይ ያተኩራል፡፡ ፍቅር በድካም መካከል ብርታት የማየት ችሎታ አለው፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡
ፍቅር ስለሰው መነሳት ስለሰው ማደግ ስለሰው መለወጥ ያምናል፡፡ ፍቅር እምነት አለው፡፡ ፍቅር ልቡ ሙሉ ነው፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ ፍቅር አይሆንም ብሎ ፍርሃትና ጥርጣሬ የለበትም፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ እንደሚጥል ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡
ፍፁም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም። 1ኛ ዮሀንስ 4፡18
ፍቅር የማይለወጠውን የእግዚአብሔርን ምንጭ ያምናል፡፡ ፍቅር እግዚአብሔርን በማመን ሁሉን ያምናል፡፡ ፍቅር ማስተዋሉ በማይመረመር እግዚአብሄር ስለሚያምን ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡
እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28
ፍቅር እግዚአብሔር ሁኔታውን እንደተቆጣጠረው በማመን በሰዎች ያምናል፡፡ ፍቅር በእግዚአብሔር ሰዎችን የመምራት ችሎታ ላይ ስለሚደገፍና ስለሚተማመን ሁሉን ያምናል፡፡
ፍቅር እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚለውጥ በማመን በሰዎች መለወጥ ያምናል፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ሉቃስ 1:37
ፍቅር ለሚያምን ሁሉ እንደሚቻል ስለሚረዳ ሁሉን ያምናል፡፡ ሔ ፍቅር በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ስለሚያምን በሁሉ ያምናል፡፡
ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡1-2
ፍቅር እግዚአብሔር ብርሃን ይሁን የማይለው ጨለማ እንደሌለ ስለሚረዳ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡
#እግዚአብሔር #አምላክ #ፍቅር #እምነት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Are You in Relationship?

Father-and-SonMany people claim to be Christians. Yes, there are Christians but some of them are not Christians anything, more than they inherit religious rituals from their parents. A real Christian is identified by the personal relationship with God.
But because of sin, our relationship had been married by sin. We are dead towards God because of sin. We were actually enemies of God and the wrath of God lived upon us. As for you, you were dead in your transgressions and sins, Ephesians 2:1
Whoever believes in the Son has eternal life, but whoever rejects the Son will not see life, for God’s wrath remains on them. John 3:36
Jesus came to this earth to restore our broken relationship with God. We had been created for relationship. We have been created in his image and after his likeness for a relationship. When one receives Christ who paid the full debt of our sin as a savior God receives the person as daughter and son into his family
But how can we check we have a personal relationship with God. These points can help to judge to know whether we have a personal relationship with God.
1. Founded on the word of God.
In the life of the person who has a personal relationship with God, the word of God comes first in whatever he thinks, says and does in his life. His life principles are based on the word and not on any traditional teachings. The word of God has a final authority in his life and not any religion leader.
For the word of God is living and powerful, and sharper than any two-edged sword, piercing even to the division of soul and spirit, and of joints and marrow, and is a discerner of the thoughts and intents of the heart. Hebrews 4:122
2. Knowing God not just about him.
Many people know about God. They heard how God works and they heard a lot about him. They don’t have a firsthand knowledge of God. They haven’t tasted God’s fatherhood in their daily lives. They don’t see God at work in their lives. They don’t have a personal encounter with him.
That which was from the beginning, which we have heard, which we have seen with our eyes, which we have looked upon, and our hands have handled, concerning the Word of life— the life was manifested, and we have seen, and bear witness, and declare to you that eternal life which was with the Father and was manifested to us—1 John 1:1-2
3. Fellowship with God daily.
When we have a personal relationship with God, we hunger and thirst for his presence in our lives. We want to be with Him all the time. We want to talk to Him. We want to listen to what he has to say every moment of our lives. We have a father-son relationship with him. We call him father and he answers to us.
Yet to all who did receive him, to those who believed in his name, he gave the right to become children of God— John 1:12
4. We follow Jesus. In whatever we do, we want to live according to his teachings. We obey him at any cost. We actually live for him and for Him only.
Therefore go and make disciples of all nations, baptizing them in the name of the Father and of the Son and of the Holy Spirit, and teaching them to obey everything I have commanded you. Matthew 28:19-20
5. Jesus lives in us
We know Him working in us. We know His presence. We know His power because of His abiding presence in us. We are guided by him from within us. He lives and walks in us. I have been crucified with Christ and I no longer live, but Christ lives in me. The life I now live in the body, I live by faith in the Son of God, who loved me and gave himself for me. Galatians 2:20
#relationship #personal #knowledge #son #daughter #grace #salvation #church #testimony #rejoice #preaching #Bible #theword #Abiydinsa #scriptures #abiywakumadinsa

በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ!

fireየእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በመንፈስ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት እውነተኛ አገልግሎት ለማገልገል መቀጣጠሉና ግለቱ ወሳኝ ነው፡፡
ሰው ሁሉ ነገር ቢኖረው ነገር ግን ምንም መነሳሳትና መቀጣጠል ከሌለውና ልቡ ከቀዘቀዘ ምንም አይጠቅምም፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ሁሌ እንድንቀጣጠል የሚያዘን፡፡
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ ሮሜ 10፡11
ሰው ምንም ያህል የመውረስ የመውጣት የማገልገል እድሉም ቢኖረው እሳቱ ከተዳፈነና ልቡ ከሞተ ምንም ማድረግ ያቅተዋል፡፡
ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ፤ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፤ ኢያሱ 13:1
ኢያሱ እንኳን እድሜው አርጅቶ ነው ነገር ግን እድሜያቸው ሳያረጅ በውስጣቸው የታመቀ ሃይል እያለ ልባቸው ያረጀ ሰዎች ለእግዚአብሄር መንግስት ያላቸው ጠቀሜታ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ለመንግስቱ ስራ ያላቸው ምንም የማይጠቅሙ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ ይህንን የሚያወርሰንን እሳት የሚበሉትን ነገሮችን ካወቅን እሳታችንን በሚገባ እንጠብቃለን፡፡
ቀድሞ የነበረንን እሳትን መቀጣጠልን ግለትን የሚያጠፉት አራት ነገሮችን ተግተን ከጠበቅን እግዚአብሄር እስከመጨረሻው የምንጠቅም ውድ እቃዎች እንሆናለን፡፡
 1. የኑሮ ሃሳብን መቀበል
የህይወት ዘመን ሃሳብ ፊት ከሰጠነው አሽመድምዶ ሽባ ሊያደርገን የሚችል አፍራሽ ሃይል ነው፡፡ ስለአቅርቦታችን እግዚአብሄርን በማመን መንግስቱንና ፅድቁን በመፈለግ ላይ ካላተኮርን የአለም ሃሳብ መቀጣጠላችንን ለመብላትና ከአገልግሎት ውጭ ለማድርግ የማይናቅ ሃይል አለው፡፡
የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19
በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። ሉቃስ 8፡14
2. የአመለካከታችን መበላሸት
አመለካከታችን በእግዚአብሄር ቃል በየጊዜው ካልታደሰ ሊበላሽና ለክርስቶስ ካለን ቅንነት ሊለወጥ ይችላል፡፡ ሳናስበው ለጌታ የነበረንን እሳት ለጌታ ስራ መስዋእት ለማድርግ የነበረንን ግለት ከቦታው ልናጣው ልንቀዘቅዝ እንችላለን፡፡
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3
ለእግዚአብሄር ያለን ቅንነት ሲለወጥና በመንፈስ መቀጣጠላችን ሲቀንስ ራሳችንን ከእግዚአብሄር መጠበቅ እንጀምራለን፡፡ ጊዜያችንን ጉልበታችንን እቅውቀታችንን ከእግዚአብሄር ስራ መሰሰት እንጀምራለን፡፡ እኔ የእርሱን ቤት ስሰራ እግዚአብሄር የኔን ቤት ይሰራል የሚለውን የዋህነታችንን ጥለን እኛ ለራሳችን መስራት እንጀምራለን፡፡
አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ማቴዎስ 25፡24
3. ከንቱ ውድድር
ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀለትን ስራ ትቶ ለሌላ ስራ ለከተጠራው ከጎረቤቱ ጋር መወዳደር ሲጀምር እሳቱን ያጣዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን ስራ ለመፈፀም አይኑን ጌታ ላይ ካደረገ ብቻ ነው እሳቱን በልቡ የሚጠብቀው፡፡ ስለውድድር ብሎ እግዚአብሄር ያልጠራው ቦታ ላይ ሲገኝ እሳቱና ግለቱ አብሮት አይሆንም፡፡ ስለዚህ የባሰ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ ሰው ግን ከውድድር በራሱ ፈቃድ ተሰናብቶ እግዚአብሄር በሰጠው የአገልግሎት ስራ ላይ ካተኮረ እሳቱ እይጨመረ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
4. የሰዎች አመለካከት
በክርስቶስ ማን እንደሆንን በደንብ ካልተረዳንና የሰዎች አመለካከት እኛን ዝቅ አድርጎ መመልከታቸውን ከተቀበልነው እሳቱ ይዳፈናል፡፡ ሰዎች ከተለያየ ነገር ተነስተው አንተ ምንም ማድረግ አትችልም ያሉንን ካመንንና እንደዛው መኖር ከጀመርን ለእግዚአብሄ ስራ ለመሮጥ ወሳኝ የሆነውን እሳቱን እናዳፍነዋለን፡፡ ራሳችንን በክርስቶስ ማየት ካቃተን እሳቱ እየደበዘዘ ለእግዚአብሄር ለመትጋት ጉልበት እያጠረን ይሄዳል፡፡
በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡11-12
እሳቱን የመጠበቅ ጉዳይ እኔን አይመለከተኝም የሚል ሰው የለም፡፡ ጌታን ለማገልገል እሳቱ ሙሉ የነበረው ኤልያስ የኤልዛቤልን ዛቻ ሰምቶ ወደልቡ ስለከተተው ከአባቶቼ አልበልጥም ብሎ ተስፋ ቆረጠ፡፡ የእግዚአብሔር ነቢይ የልቡ እሳት ተዳፈነ፡፡
እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ፤ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና፦ ይበቃኛል አሁንም፥ አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንዲሞት ለመነ። 1ኛ ነገሥት 19:4
ስለዚህ ነው መፅሃፍ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የህይወት መውጫ ከእርሱ ነውና የሚለው፡፡ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፣ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና ምሳሌ 4:23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

በፈቃዱ ውስጥ እንዳለው በምን አውቃለው?

leading-questions-800x400በእየሱስ የመስቀል ስራ ከእግዚአብሄ ጋር ከታረቅን በኋላ የመጀመሪያው በህይወታችን የምንፈልገው ነገር የእግዚአብሄርን ፈቃድ ነው፡፡ በህይወታችን የምንጠላውና የማንፈልገው ነገር ደግሞ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጭ መገኘትን ነው፡፡
አብዛኛው ክርስትያን በህይወቱ የሚፈልገው ዋና ነገር ምን እንደሆነ ቢጠየቅ የሚመልሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማድረግና እግዚአብሄርን በህይወቱ ማክበር ነው፡፡
ግን አንዴት ነው የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስጥ መሆኔንና አለመሆኔን የማውቀው የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስጥ መሆናችንን ለማወቅ የሚረዱ ሰባት ነጥቦች፡፡
1.የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ከምንጠማው በላይ እግዚአብሄር ፈቃዱን እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ እንዲያውም ሲጀመር የፈጠረን ፈቃዱን እንድናደርግ ለክብሩ ነው ፡፡ ፈቃዱን አንድንረዳና እንድናደርግ ሙሉ ለሙሉ አብሮን ይሰራል፡፡
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳይያስ 43፡7
2. የእግዚአብሄርን ፈቃድ መረዳት ለሁላችን የተሰጠ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድን መረዳት ለጥቂት ሰዎች የተሰጠ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አማኝ የተሰጠ ዕድል ነው፡፡ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ዮሃንስ 10፡4-5
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ዮሃንስ 10፡14
3. የእግዚአብሄር ፈቃድ ውስብስብና ለመረዳት የሚያስቸግር አይደለም፡፡ ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3
4. የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንረዳው ከተናጋሪው ችሎታ እንጂ ከሰሚው ችሎታ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ፈቃዱን የሚያሳውቀን በመስማት ደረጃችን ወርዶ በሚገባን መንገድ ነው፡፡ ፈቃዱን ለማወቅ እስከፈለግን ድረስ እስኪገባን ድረስ ይናገረናል፡፡
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል። ዮሃንስ 7፡17
5. በጣም አስደናቂ በሆነ በደመናና በታላቅ ድምፅ አልተናገረንም ማለት እየመራን አይደለም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር አብዛኛውን ጊዜ በልባችን በለሆሳስ ነው የሚናገረን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሄርን ምሪት እንዲሁ እንረዳዋለን እንጂ ማስረዳት ከባድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር ግን እናውቀዋለን፡፡
እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። 1ኛ ነገስት 19፡11-12
6. በአጠቃላይ እግዚአብሄር በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ ደስተኛ ካልሆነ ይናገረናል፡፡ እግዚአብሄር ተበሳጭቶብን ኖሮ ኖሮ ድንገት ሲደሰትብን አይደለም የሚናገረን፡፡ እግዚአብሄር በእኛ በደረስንበት ደረጃ ባለንበት ሁኔታ ደስተኛ ነው፡፡ ያልተደሰተበት ነገር ካለ ያሳየናል፡፡ እኛ ራሳችንን ከምንረዳው በላይ እርሱ እኛን ይረዳናል፡፡
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። ሮሜ 8:1
7. ፈቃዱን ለማድርግ መፈለግንና መነሳሳትን በምህረቱ የሚሰጠን አግዚአብሄር ነው፡፡ ስለ መልካምነቱ እንዲሁ ማድረግን የሚሰራው እርሱ ራሱ ነው፡፡
ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ፊልጵስዩስ 2፡10

We can Live Beyond our Generation

 
600_top_baby_namesWe are a part of generations. We build a foundation for the next generation and we actually shape it in what we say and do. We contribute to the success or failure of the next generation of believers. We can set a practical example for the Christian generation to come.
We desire that the generation coming obey the king of Glory we happily submit to. Our concern is how we influence the next generation while we are living in ours. We want to know how we effectively influence the next generation to facilitate for their lives of following Jesus. We want to be a role model for the people around us now and to leave foot-prints for the next generation.
We don’t just live for ourselves only. We also have the responsibility of the next generation to come. Our daily godly lives give a fuel to the next generation to be on fire for God. How we behave in this will encourage or discourage next. The way we worship God and serve him will be used as a measuring tool for the generation to come.
What we say and do in our generation actually influence the next one. We have the great opportunity of being a role model in what we say and do. But you have carefully followed my doctrine, manner of life, purpose, faith, longsuffering, love, and perseverance 2 Timothy 3:10
We can be real models of following Jesus wholeheartedly for the next generation to look up to. We can be good examples in the high regard we give to the word of God in our daily lives for the next generation.
We can be examples of faith-living. We can facilitate for their rising. We sacrifice for their comfort. We encourage the next to sacrifice more by what we sacrifice now.
A generation that will see us as fathers and mothers of faith is coming. We are here to contribute for the advancement of the Kingdome and presence of God in our generation and the generation to come.
We want as many as of our children, grandchildren and great grandchildren will follow Jesus if he tarries. We want as many of them minister the gospel. We want them to follow the pure teaching of Jesus without compromise.
It is only by living for God and for him only that we can give the next generation a practical example how to follow Jesus.
I am reminded of your sincere faith, which first lived in your grandmother Lois and in your mother Eunice and, I am persuaded, now lives in you also. 2 Timothy 1:5
#generation #model #example #church #legacy #Christian #Jesus #God #Abiywakuma #Abiywakumadinsa #salvation #abiydinsa #Facebook

እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ

girls_beautyful_girls_listening_to_music_022763_29ሰዎችን የሚማርኳቸውና የሚደሰቱባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ካለ እምነት ግን እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራዊያን 11፡6

እምነት ደግሞ መንፈሳዊውን አለም ማየትና በዚያው መመላለስ ነው፡፡ እምነት በተፈጥሮአዊ አይን ከሚታየው አለም ባለፈ የመንፈሳዊውን አለም ማየትና ከመንፈሳዊ አለም ጋር አብሮ መራመድ ነው፡፡ እምነት በአካባቢያችን ከምናየው ነገር በላይ የእግዚአብሄርን ቃል ማየትና እንደ እግዚአብሄር ቃል መመላለስ ነው፡፡

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ዕብራውያን 11፡1

 • እምነትም የሚመጣበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት እንደሆነ አውቀን የእግዚአብሄርን ቃል በጥንቃቄ መስማት ይገባናል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

የእግዚአብሄርን ቃል አሰማማችን በውስጣችን እምነት እንዲፈጠር ወይም እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ሰው ቃል ካለሰማነው የእግዚአብሄር ቃል እንደእግዚአበሄ ቃል በእምነትና በየዋህነት ከተቀበልነው በውስጣችን እምነትን ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ነው እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ የሚለው፡፡ /ሉቃስ 8:18/

 • ቃሉን አሰማማችን ፍሬ እስከምናገኝበት ድረስ በቃሉ ለመፅናት መሆን አለበት፡፡

በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። ሉቃስ 8፡15

በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል። ማቴዎስ 13፡23

 • ቃሉን አማራጭ የሌለው ብቸኛ መፍትሄ እንደሆነ በማመን ወደቃሉ መምጣትና ቃሉን መስማት አለብን፡፡

ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ። ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ ዮሃንስ 6፡67-68

 • የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ ለመፈወስና ለመለወጥ ተዘጋጅተን በመጠባበቅ መሆን አለበት፡፡

ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ሉቃስ 6፡17

 • የእግዚአብሄር ቃል ህያው እንደሆነና ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ውስጣችንን ሊለውጥ እንደሚችል በማወቅ በአክብሮት ልንሰማው ይገባናል

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ሮሜ 4፡12

የእግዚአብሄርን ቃል እንደሚሰራና እንደሚለውጥ ቃል ካልተቀበልነው በህይወታችን ሊሰራናየምንፈልገውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡

ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ዕብራውያን 4፡2

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

#ቃል  #እምነት #መንፈስ #መፅሃፍቅዱስ #ነፍስ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት#አማርኛ #ስብከት #መዳን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

አምስቱ የግንኙነት መመዘኛዎች

Father-and-Sonክርስቲያን ነኝ ያለ ሰው ሁሉ ክርስቲያን አይደለም፡፡ ክርስቲያን ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ያለው ሰው ብቻ ነው፡፡
ሰው ሁሉ ሃጢያትን ሰርቶ ከእግዚአብሄር ክብር ስለወደቀ ንስሃ ገብቶ ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ አለበት፡፡ እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያቱ የሰራውን ስራ ለእኔ ነው ኢየሱስ የሞተው በእኔ ምትክ ነው ብሎ የሚቀበል ሰው እግዚአብሄር ይቀበለዋል በቤተሰቡ ውስጥ ልጅ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት ይኖረዋል እግዚአብሄርን በግሉ ያውቀዋል፡፡
የኢየሱስ ከሃጢያት አዳኝነት የምስራች ሲበሰርላቸው ብዙ ሰዎች እኔ ክርስቲያን ነኝ ብለው ስለሚያስቡ ብቻ ኢየሱስን ለመቀበል ፈቃደኛ አይሆኑም፡፡ ነገር ግን ክርስትናን እንደማንኛውም ሃይማኖት ሃይማኖቴ ነው ብሎ የያዘ ሰው ሁሉ ድኗል ማለት አይቻልም፡፡ እየሱስ ወደምድር የመጣው አንድ ተጨማሪ ሃይማኖት ለመመስረት ሳይሆን ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁና የአባትና የልጅ ግንኙነት አንዲኖራቸው ነው፡፡
ክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጋር የግል ግንኙነት መመስረት ነው፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት እንዳለንና እንደሌለን 5 መመዘኛዎች
 • ህይወታችን በእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን የመጨረሻው ስልጣን ይሆናል፡፡ የእግዚአብሄ ቃል አድርጉ የሚለንን እናደርጋለን አታድርጉ የሚለንን አናደርግም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ዕብራውያን 4፡12
 • እግዚአብሄርን በሰሚ ሰሚ ሳይሆን በግላችን እናውቀዋለን፡፡ እግዚአብሄርን በእለት ተእለት ህይወታችን እንፈልገዋለን በህይወታችን በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላችን ሲሰራ እናውቀዋለን፡፡
ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-2
 • ከእግዚአብሄር ጋር በየእለቱ እንነጋገራለን፡፡ እግዚአብሄርን የምናውቀው በታሪክ ወይም በሰዎች ልምምድ ሳይሆን የእግዚአብሄርን አባትነት በህይወታችን እንለማመዳለን፡፡ እንደ አባት እንጠራዋለን እንደ ልጅ ይሰማናል ይናገረናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
 • በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከማንም ከምንም አብልጠን ኢየሱስን እንከተላለን:: የኢየሱስን አስተምሮዎች ሁሉ እንታዘዛለን፡፡

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ማቴዎስ 28፡19-20

 • ኢየሱስ በልባችን ይኖራል፡፡ ክርስትና ሃይማኖታዊ ወግና ስርአት መፈፀም ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሄር መኖርና በእግዚአብሄር ሃይል ማገልገል ነው፡፡ ኢየሱስን የምናውቀው በልባችን ሲኖርና ከልባችን ሲመራንና በልባችን በመኖር ሃይል ሲሰጠን ነው እንዲያውም ኢየሱስ በእኛ ሲወጣና ሲገባ ስራውን ሲሰራ ነው፡፡
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ገላትያ 2፡20
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ

Gentleness Defined

gentleness (1)God created man in his image, after his likeness. One of the most important characters God wants to see in us in gentleness. Gentleness comes when we glorify the word of God in our lives. It is the character that is developed through time.

Gentleness is one of the most coveted character and personality by men and women. It is our real beauty in the sight of God.

Rather, it should be that of your inner self, the unfading beauty of a gentle and quiet spirit, which is of great worth in God’s sight. 1 Peter 3:4

Defining the word gentle in a single word or sentence is very difficult.

A gentle person is not quarrelsome, not greedy for gain, not self-centered, quiet, calm, modest, prudent, balanced, trusting in God, kind, compassionate, merciful, patient, moderate, contented, temperate, sober-minded, and compassionate person. Gentle person restrains himself not to use his power for evil. He is bridled person.

 • A Gentle person is respectful who does not want to abuse and manipulate others. He is kind, intelligent and balanced person.

And the servant of the Lord must not strive; but be gentle unto all men, apt to teach, patient, 2 Timothy

2:24

 • A Gentle person is not greedy for money, decent, contented, considerate, not quarrelsome.

. . . not given to wine, not violent, not greedy for money, but gentle, not quarrelsome, not covetous; 1 Timothy 3: 3

 • Gentleness is the acid test to differentiate between the wisdom from above and wisdom from below.

But the wisdom that is from above is first pure, then peaceable, gentle, willing to yield, full of mercy and good fruits, without partiality and without hypocrisy. James 3:17

 • Gentleness is the way we communicate with others especially the unbelievers. They understand gentleness.

But in your hearts revere Christ as Lord. Always be prepared to give an answer to everyone who asks you to give the reason for the hope that you have. But do this with gentleness and respect, 1 Peter 3: 15

 • One of the leadership qualities exhibited by Apostle Paul

Now I, Paul, myself am pleading with you by the meekness and gentleness of Christ—who in presence am lowly among you, but being absent am bold toward you. 2 Corinthians 10: 1

 • One of the most powerful tools of our testimony is to show forth the character of gentleness in our daily lives.

Let your gentleness be evident to all. The Lord is near. Philippians 4:5

To share this article

For more articles https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#quiet #gentle #decent #contented #considerate  #kind #modest #moderate #calm #compassionate #balanced #Jesus #Lord #Church #character  #testimony #sermon #bible #christ #facebook #abiywakumadinsa #abiydinsa #abiywakuma

Persecution Blessings

Persecution_0.jpg 2Blessed are those who are persecuted because of righteousness, for theirs is the kingdom of heaven. Matthew 5:10
The whole world is under the control of the evil one. When one follows Jesus he is will be spotted and will stand out from the rest. We sacrifice many things for the sake of following Jesus.
Many people are deceived that they not to live for God is the right way to live and they are deceived and their minds are darkened to believe that we are on the wrong track. When the Christian understands the will of God for his life a, thinks different, comes out from among them and is completely different by his actions.
His uniqueness will not make the others comfortable. They try hard to make him the same like them again or they make his life hard to follow Jesus. His uniqueness will make them uncomfortable and they oppose him for whatever reasons they can get.
A person in dirty clothing isn’t comfortable in the midst of the people in clean cloth. The people who practice sin will never be comfortable in the presence of the person who is disciplined to follow Jesus. The people who are reckless will never stand in the presence of the person who fears God. He frightens them all.
He may not use any word but his pure life will condemn them that they are not going to heaven. His uniqueness will destruct their worldly lives. His holy living of light will expose their darkness.
We automatically reject the devil when we chose to follow Jesus and make him our savor and Lord. So the Devil will attack us using any available weapon at his disposal. He will use others ignorance to persecute us. He will do whatever to stop us from living for God and for Him only. If He doesn’t succeed, he wants to make our Christian life miserable.
In fact, everyone who wants to live a godly life in Christ Jesus will be persecuted, 2 Timothy 3:12
We lose our status in society, we lose our friendship, we lose our comfort, and we lose our freedom. We lose our good names. The followers of Jesus sacrifice their benefits for the sake of the Gospel.
We may even be demoted or sacked from our work. We can be imprisoned. We can be displaced. We can be beaten or we can even be killed.
Blessed are those who are persecuted because of righteousness, for theirs is the kingdom of heaven. Matthew 5:10
Blessed, praiseworthy, happy and favored are those who are persecuted because of righteousness.

Designed to Serve

wash_feetGod created man to solve problems. Every man is created with built-in talent to contribute to the advancement of others. We are born on earth for a purpose greater than us. We are not just born to eat, drink and die. We are born for others. we are born to serve others and add value in their lives.
Man is designed and created to serve others. Man is only satisfied in adding value in others. If man follows selfishness, he will be miserable as his design doesn’t allow that. Even if man gets everything under the sun, he will never be satisfied unless. He is only satisfied and a life well-lived when he serves others and live for them.
All things are wearisome, more than one can say. The eye never has enough of seeing, nor the ear its fill of hearing. Ecclesiastes 1:8
If a man is promised to be provided with everything and is prevented from working and serving others, it will be like killing the person. Only provision can’t satisfy the person, unless he works and contribute to the wellbeing of others. That is the design of man. For the person who serve others, provision isn’t a question at all.
If a person has a poor-me mentality he will never have the confidence to serve others. He will die in trying to be satisfied by gathering things thinking that satisfaction is found in accumulating material things.
But those who understand the glory of serving and benefiting others will live to serve others. They are confidence in what they can do in the lives of others beyond themselves.
It is said that the legacy of the person who lives for himself will end at his funeral but the legacy of the person who live for others will echo long after the burial through the persons served by him. Jesus answered I am the way and the truth and the life.(John 14:6) encourages us to serve other following his examples.
just as the Son of Man did not come to be served, but to serve, and to give his life as a ransom for many. Matthew 20:28
Click to share this article with others
#serve #design #service #addvalue #benefitothers #church #legacy #Christian #Jesus #God #Abiywakuma #Abiywakumadinsa #salvation #abiydinsa #Facebook

ለሚጠሩትም ባለ ጠጋ ነው

View of smiling man raising his hands standing in the fieldበአለም ላይ የሃብት ችግር የለም፡፡ በአለም ላይ ለሁሉም ሰው የሚበቃ ምንጭ አለ፡፡ እግዚአብሄር የአቅርቦች ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ በአለም ላይ ያለው ችግር እግዚአብሄርን ያለመፈለግና እግዚአብሄርን ያለመጥራት ችግር ነው፡፡ በምድር ላይ ያለው ችግር ወደ እግዚአብሄር ያለመፀለይ ችግር ነው፡፡
እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ባለጠግነት የሚጠቀሙበት የሚጠሩት ናቸው፡፡ የሚጠሩት የእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡ የሚጠሩት በእግዚአብሄር ባለጠግነት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ከባለጠግነቱ ተካፋዮች የሚሆኑት ሃብታሞች ብቻ አይደሉም ፡፡ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚጠቀሙት የሚሆኑት ሃያላን ብቻ አይደሉም፡፡ ወይም ደግሞ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚካፈሉት ጠቢባብን ብቻ አይደሉም፡፡ የሚጠሩት ሁሉ ከባለጠግነቱ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ፤ ሮሜ 10፡12
እግዚአብሄርን ያየው አንድስ እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው የተባለለት እየሱስ ስለእግዚአብሄር ልብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ማቴዎስ 7፡7
ለምኑ እንጂ ያለው በንግዳችሁ ልክ ለምኑ አላለም፡፡ ፈልጉ እንጂ ያለው በደሞዛችሁ ልክ ፍለጋችሁን ወስኑት አላለም፡፡ አንኳኩ እንጂ ባላችሁ ካፒታል ልክ አንኳኩ አአላለም፡፡
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡8
የእግዚአብሄር ባለጠግነት ከሃብቱ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ነው፡፡ ልመናችሁን በገቢያችሁ አትወስኑት ፡፡ ፀሎታችሁን በሃብታችሁ አትወስኑት፡፡ እግዚአብሄርን በኑሮዋችሁ ደረጃ አትወስኑት፡፡
እግዚአብሄርን ካልጠራነው ግን የባለጠግነቱ ተካፋይ ልንሆን አንችልም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ለምኑ #ባለጠግነት #አንኳኩ #ሃብት #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሃይል አያስመካም ማስተዋል እንጂ

boast 2.png 3.jpgሁሉም ሰው በምድር ላይ እንዲከናወን ይፈልጋል ከክንውንም መጉደል የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ ሰውም የክንውን መንገዶች የሚባሉትን ሁሉ ማጥናት መከተል ይፈልጋል፡፡
በዚህ ረገድ ሰዎች እነዚህ የህይወት ቁልፍ ናቸው ብለው ካለማወቅ የሚሳሳቱባቸው ሶስት ነገሮች አሉ፡፡
በየዘመኑ የኖሩ ሰዎች የህይወት ዘመናቸውን እነዚህን በመፈለግ ቢፈጁም በኋላ ግን የጠበቁት ስለማይሆን ያዝናሉ ይሰናከላሉ፡፡
ለማይጠቅም ለከንቱ ነገር ጊዜያቸውን ስለፈጁ ይፀፀታሉ፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ስለ እነዚህ ሰዎች በስህተት ስለሚመኩባቸው ሶስት ነገሮች በየጊዜው በተለያለ መልኩ የሚናገረው፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስ ሰው በጥበቡ በሃይሉና በባለጠግነቱ እንዳይመካ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ኤርሚያስ 9፡23
እግዚአብሄር እንዲህ እያለ ነው ፡፡ የሰው ጥበብ እንደ ህይወት ቁልፍ የሚያስመካ ነገር አይደለም፡፡ የሰው ጥበብ እንደ ስኬት ምንጭ ወሳኝ አይደለም፡፡ ጥበብ የሚያደርጋቸው ውስን ነገሮች አሉ ነገር ግን የሰው ጥበብ የህይወት መንገድ አይደለም፡፡
በሌላ አነጋገር ጥበብ የሌለው ሰው ከህይወት መንገድ እንደጎደለ ሊሰማው አያስፈልግም፡፡ ጥበብ የሌለው ሰው የህይወት ቁልፉን እንዳጣ አይዋረድ፡፡ ጥበብ የሌለው ሰው ህይወት እንደጎደለው አይሰማው፡፡ ጥበብ ጉድለት ምንም ችግር የለውም እያለ ነው፡፡
ሃያልም በሃይሉ አይመካ ማለት ሃያል በሃይሉ ምንም አያመጣም ማለት ነው፡፡ ሃያል ሃይሉ አያስጥለውም ማለት ነው፡፡ ሃያል ሃይሉ በር አይከፍትለትም ማለት ነው፡፡ ሰው በሃይሉ ጠብ የሚል ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ሰው በሃይሉ መመካቱ አያዋጣውም፡፡
በሌላ አነጋገር ደካማው ከህይወት መንገድ ተጥያለሁ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ አይዘን ማለቱ ነው፡፡ ደካማው ድካ ብቻ ከህየወት ሩጫ ሊያሰወጣው የሚችል በቂ ምክኒያት አይደለም ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ ማለት የህይወት ስኬት ቁልፍ በባለጠግነት ውስጥ አይደለም ማለት ነው፡፡ ባለጠጋ ስለሆነ ብቻ ህይወትን ያገኘ አይምሰለው ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት የሚያስመካ ምንም ነገር የለውም ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማድረግ የማይችላቸው በጣም ብዙ ነገሮች አሉ እያለ ነው፡፡
የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው። ሉቃስ 12፡15
እንዲሁም ደግሞ ደሃ የህይወት ቁልፉን እንዳጣ አይሰማው ማለት ነው፡፡ ደሃ ምንም እንደጎደለበት አይሰማው፡፡ ድሃ በድህነቱ አይዋረድ፡፡
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24
የህይወት ቁልፍ ሃይል ሃብትና ጥበብ ውስጥ አይደለም፡፡ የስኬት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር እጅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ሃያልነትና ድካም ፣ የሰውን ባለጠግነትና ድህነት ፣ የሰውን ጥበብና የጥበብ ጉድለት ተከትሎ ምንም የሚሰራው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ምድርን የሚያስተዳድረው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በማድረግ ነው፡፡
በጥበቡ የሚመካ ሰው ሞኝ ነው፡፡ በሃይሉ የሚመካ ሰው ደካማ ነው ፡፡በባለጠግነቱ የሚመካ ሰው ድሃ ነው፡፡
ስለዚህ የሰው ስኬት ምንጩ በምድር እንደሌለ የሰው ስኬት ምንጩ እግዚአብሄር እጅ እንዳለ የተረዳ ሰው ይህ መረዳቱ ሊያስፈነድቀውና ሊያስመካው ይችላል፡፡ ምክኒያቱም ሊመኩበት የሚገባ እግዚአብሄ ብቻ ነውና፡፡
በእግዚአብሄር ብቻ መመካት እውነተኛ ባለጠግነት ነው ፣ በእግዚአብሄር መመካት እውነተኛ ሃያልነት ነው ፣ እውነተኛ ጠቢብነት በእግዚአብሄር መመካት ነው፡፡
የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ !
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ተዝቆ የማያልቅ የብልፅግና እድል

shake.jpgእግዚአብሄር እጅግ ባለፀጋ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ያየው አንድስ እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው የተባለው እየሱስ ስለእግዚአብሄር ተዝቆ የማያልቅ ብልፅግና ይናገራል፡፡
እየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ ሞቷል የሃጢያት እዳችንንም ሙሉ ለሙሉ ከፍሏል፡፡ እየሱስን አንደአዳኝና ጌታችን የተቀበልን ሁላችን ከዚህ የማያልቅ በረከት ተካፋዮች ለመሆን ተጋብዘናል፡፡ እየሱስ በራሱ አንደበት የሚያስተላልፈውን የግብዣ ጥሪ እንስማ፡፡ በመጨረሻ ህይወታችንን መለስ አድርገን ስናይ ከዚህ የማያልቅ በረከት በሚገባ ባለመጠቀማችን እንዳንቆጭ ግብዣውን ለሁላችን ያስተላልፋል፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
ይህን የማያልቅ የእግዚአብሄር ሃብት የምንካፈልበትና በዚህ ሃብት የምንኖርበትን መንገድ በቃሉ እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ ታላቅ ከሆነውና ባለጠግነቱ ከማይነገረው እግዚአብሄር ጋር የምንገናኘውና የምንያያዘው በቃሉ አማካኝነት ነው፡፡
ይህ የእግዚአብሄር ባለጠግነት ወደ እኛ የሚፈስበት መንገዱ ቃሉ በእኛ ውስጥ መኖሩ ነው፡፡ ካለንበት ውስን ከሆነው ሃብት ወጥተን ከያዙል ከውስንነታችንና ከገደባችን ተሻግተረን የዚህ የእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋይ የምንሆነው በቃሉ አማካኝነት ነው፡፡
ቃሉ በእኛ ውስጥ በበዛ ቁጥር የብልፅግና እድላችን ይበዛል፡፡ በቃሉ ስንኖር አስበን የማናውቀው ብልፅግና በቃሉ ውስጥ ተጠውቅልሎ እናገኛለን፡፡
ይህ ሁሉ አርነት በክርስቶስ ውስጥ አለ እንዴ ብለን እስከምንገረም ድረስ አስበን ከምናውቀው ሁሉ በላይ ሰፊ የሆነውን የእግዚአብሄርን ባለጠግነት እንለማመዳለን፡፡
ይህን ባለጠግነት የምናረጋገጥበትን መንገድ ሲናገር ቃሎቼ በእናንተ ቢኖሩ ይለናል፡፡ ቃሎቹ በእኛ ሲበዙ ይበልጥ የእግዚአብሄር የማያልቅ ብልጥግና ተካፋዮች እንሆናለን፡፡
የሚገርመው በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ ብሎ ውጤቱ ምን እንደሚሆን የሚገርምና የሚደንቅ ነገርን ይናገራል፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል ይላል፡፡ ይህ ማለት ፡-
ለቃሌ የዋህ ስትሆኑና ስታደርጉት ለቃላችሁና ለፀሎታችሁ የዋህ እሆናለሁ እፈፅመዋለሁ እያለ ነው፡፡ እናንተ ራሳችሁን ስትሰጡኝ እኔ ራሴን እሰጣችሁዋለሁ እያለ ነው፡፡
የእኔ ቃል የእናንተ ሲሆን የእኔ ሃብት የእናንተ ይሆናል እያለ ነው፡፡ ቃሎቼን ስታደርጉ ቃላችሁን አደርጋለሁ እያለ ነው፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
#ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ