Category Archives: humility

በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው?

43475115_123001652004607_3267491658576429056_n.jpg

በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው?

እንዲህም አላቸው፦ የአሕዛብ ነገሥታት ይገዙአቸዋል፥ በላያቸውም የሚሠለጥኑት ቸርነት አድራጊዎች ይባላሉ። እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ፤ ነገር ግን ከእናንተ ታላቅ የሆነ በመካከላችሁ እንደ ታናሽ፥ የሚገዛም እንደሚያገለግል ይሁን። በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ። የሉቃስ ወንጌል 22፡25-27

ስልጣን መበለጥ መሆኑን ብናውቅ ኖሮ ብዙዎቻችን አንፈልገውም ነበር፡፡ ስልጣን ማገልገል ነው፡፡ ስልጣም መጥቀም ነው፡፡ ስልጣን መባረክ ነው፡፡

ባለስልጣን ህዝቡን ማገልግል ግዴታው ነው፡፡ ባለስልጣን ህዝቡን በማገልግል ውለታ እየሰራላቸው አይደልም፡፡

ከባለስልጣን ይልቅ ህዝብ ይበልጣል፡፡ ከሚያገለግለው ይልቅ የሚገለገለው ይበልጣል፡፡ የሚያገለግለው ባለስልጣን ለሚገለገለው ህዝብ ተዘጋጀ እንጂ የሚገለገለው ህዝብ ለሚያገለግለው ባለስልጣን አልተዘጋጀም፡፡

ባለስልጣንነት በውሳኔ ሌሎችን ማገልገል ነው፡፡ ባለስልጣንነት ፊት በመቅደም ሌሎችን መንገድ ማሳየት ነው፡፡ ባለስልጣንነት ፊት ቀድሞ ለሌሎች መጋፈጥ ነው፡፡

ባለስልጣንንት ደስ የማይል ውሳኔ መወሰን ነው፡፡ ባለስልጣንነት በሌሎች መተቸት ነው፡፡ ባለስልጣንንት ወቀሳን መቀበል ነው፡፡ ባለስልጣንንት የህዝብን ሸክም መሸከም ነው፡፡ ባለስልጣንነት ለህዝብ እድገት ሃላፊነት መውሰድ ነው፡፡

በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል ማናቸው ታላቅ ነው? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ። የሉቃስ ወንጌል 22፡27

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል

pride.jpgትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። ምሳሌ 16፡18

ሰው ጥፋትን ቢያጠፋም ተስፋ አለው፡፡ ሰው ቢስትም የሚማር ልብ እስካለው ድረስ ይመለሳል፡፡ ሰው መንገድን ቢስት እስከሰማ ድረስ ይድናል፡፡

ትእቢተኛ ሰው ግን ሰውን የማይሰማ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ከእርሱ ውጭ አዋቂ እንደሌለ የሚያስብ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ካለእርሱ መንገድ ሌላው መንገድ ሁሉ የተሳሳተ የሚመስለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ራሱን ያለአግባብ የሰቀለ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ካለ እኔ ሰው የለም የሚል ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ማንንም የማይሰማ ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው የሚማር ልብ የሌለው ሰው ነው፡፡ ትእቢተኛ ሰው ከሁሉም በላይ እውቀት ያለው የሚመስለው ሰው ነው፡፡

ደሃ እርዳታ ይገባዋል፡፡ ያዘነ መፅናናትን ይረዳል፡፡ ትእቢተኛ ግን የሚረዳው አንድን ነገር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን የሚገናኘው በሚረዳበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ ትእቢተኛ የሚረዳው ተቃውሞን ብቻ ነው፡፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ይቃወማል፡፡

እግዚአብሄር የተቸገረን ይረዳል፡፡ እግዚአብሄር የወደቀን ያነሳል፡፡ እግዚአብሄር ያዘንን ያፅናናል፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ግን የሚያሻሽልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ግን ይቃወመዋል፡፡

ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። ያዕቆብ መልእክት 4፡6

ትእቢተኛ ከእግዚአብሄር ተቃውሞ ውጭ ለማንም እድልን አይሰጥም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አይመክረውም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አያስተምረውም፡፡ ትእቢተኛ ሁለኩንም ዝቅ አድርጎ ነው የሚያየው፡፡ ትእቢተኛ ሊሰማው የሚገባው ምንም ሰው የለም፡፡ ትእቢተኛን ማንም አይመልሰውም፡፡ ትእቢተኛ ከእግዚአብሄር ተቃውሞ ውጭ ተስፋ የለውም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ትእቢተኛን ሌላ ምንም ማድረግ ስለማይችል ይቃወመዋል፡፡ ትእቢተኛ ማነንም ስለማይሰማ እግዚአብሄር  በትእቢተኛ ፊት ይቆማል፡፡

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

ትእቢተኛ ከሁሉ በላይ ራሱን አዋቂ ስለሚያደርግ ትእቢተኛ ከማንም ሊማር አይችልም፡፡ ትእቢተኛ የሚማረው በመስማት አይደለም፡፡ ትእቢተኛ የሚማረው በጥፋት ብቻ ነው፡፡ ሌላ የሚመለስበት ምንም መንገድ ስለሌለው ትእቢተኛ የሚመለሰው በውድቀት ብቻ ነው፡፡

ከትእቢት በኋላ ጥፋት ተከትላ እንደምትመጣ እርግጥ ነው፡፡ ኩሩ መንፈስን ካየህ ውድቀት ተከትላ እንድምትመጣ መጠበቅ ትችላለህ፡፡

ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። ምሳሌ 16፡18

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ጥፋት #ውድቀት #ኩሩ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም

faith vs pride.jpgእምነትና ቅንነት አብረው የሚሄዱ ተመሳሳይ ነገሮች ናቸው፡፡ እምነትና ኩራት አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

እምነትና ኩራት አብረው የሚሄዱ ነገሮች አይደሉም፡፡ እምነት ካለ ትምክህት አይኖርም፡፡ ትምክህት ካለ እምነት አይኖርም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካመነ በምንም ነገር አይመካም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ለማመን በራስ መተማመንን መጣል አለበት፡፡ ሰው በራሱ ከተማመነ እግዚአብሄርን ሊያምን አይችልም፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ለማመን ለእግዚአብሄር ቃል ቅን መሆን አለበት፡፡ ሰው በእግዚአብሄርን ለማመን የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ በየዋህነት መቀበል አለበት፡፡

ሄዋን ቅንነትዋ ሲበላሽ እምነትዋን አጣች፡፡ ሄዋን ቅንነትዋን እስከጠበቀች ድረስ እምነትዋን ጠብቃ ነበር፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3

ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ይጠራጠራል፡፡ ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ማቴዎስ 25፡24

እምነት ትህትናን ይጠይቃል፡፡ ትሁት የሆነና ራሱን የሚያዋርድ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን አምኖ የሚጠብቀው፡፡ ትእቢተኛ የሆነና በራሱ የሚመካ ሰው እግዚአብሄርን መጠበቅ አይችልም፡፡ በራሱ ለሚመካ ሰው እግዚአብሄርን ማመን ሞኝነት ነው፡፡ እኔ አውቃለሁ የሚል ሰው እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡

ሰው እምነቱን ለመጠበቅ ለእግዚአብሄር ያለውን ቅንነት መጠበቅ አለበት፡፡ ሰው እምነቱን ላለማጣት ለእግዚአብሄር ቃል ያለውን ቅናት ማጣት የለበትም፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ እግዚአብሄርን ይጠራጠራል፡፡ የሰው ነፍሱ ከኮራ እግዚአብሄርን ማመን ያቅተዋል፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ በእግዚአብሄር ሳይሆን በራሱ መደገፍ ይጀምራል፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ቅንነት #ኰርታለች #ቅን #እምነት #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የእግዚአብሔር የምድር መሠረቶች

reign of god image.jpgአትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር ይውጣ። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3 እና 8

እግዚአብሄር ምድርን ፈጥሮ አልተወውም፡፡ እግዚአብሄር በትጋት ምድርን እያስተዳደረ ነው፡፡ እግዚአብሄር በጥበቡና በሃይሉ በፍቅር እንደ እርሱ ነፃ ፈቃድ ያለው ሰው እየመራ ነው፡፡ ሁሉን ነገር ሞክረን መጨረሻ ላይ የሚሆነው የእግዚአብሄር ሃሳብ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገውን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል፡፡ ቁልፉ ያለው በእግዚአብሄር እጅ ነው፡፡

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11

እግዚአብሄር ምስኪኑን ፣ ጉልበት የሌለውንና አቅም ያነሰውን ከመሬት በማንሳት ይታወቃል፡፡

በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21

እግዚአብሄር የምድር ባለቤት ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ጉዳይ ጣልቃ ይገባል፡፡ እግዚአብሄር ምንም የሆነውን ሰው ከፍ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር ችግረኛውን ከመሬት አንስቶ የክብር ዙፋን ያወርሰዋል፡፡

ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው። ዳንኤል 4፡17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባለቤት #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ ####ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

reign of god image.jpg

እግዚአብሔር አዋቂ ነውና

silent.jpegአትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3

እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው ነገር ብዙ ነገር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ከሰው ኩራትን አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ሰው በእርሱ አሰራር እንዲታመን ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሄር በፍትህ ምድርን እያስተዳደር እንዳይደለ ያክል ሰው እንዲናገር አይፈልግም፡፡ የምድር ነገር ከእግዚአብሄር ቁጥጥር ውጭ እንደወጣ አድርጎ ሰው እንዲናገር እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ሚክያስ 6፡8

ሰው ቢያንስ ምድርን እያስተዳደር ያለው እግዚአብሄር አዋቂ ነው ብሎ ነገሮችን በእግዚአብሄር ካልተወ ነገሮች ትክክል አይሆኑም፡፡  እኔ ሁሉን አላውቅም እግዚአብሄር ግን ሁሉን ያውቃል ብሎ በእግዚአብሄር ካልተደገፈ ምንም ቢወጣና ቢወርድ ሰው አይሳካለትም፡፡

የእግዚአብሄርን ክንድ በህይወትዋ ያየችው ሃና ትመክራለች፡፡ እግዚአብሄር በፍትህ ምድርን ያስተዳደራል፡፡ እግዚአብሄር ስራውን ይመዝናል፡፡ እግዚአብሄር የተጎዳን እንዴት እንደሚክስ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር የደከመን እንዴት እንደሚግደግፍ ያውቃል እግዚአብሄር ያጣን እንዴት እንደሚሞላ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር የተዋረደን አንዴት እንደሚያነሳ ያውቃል፡፡ በዚህ የተጎዳውን በዚያ እንዴት እንደሚክሰው እግዚአብሄር ያውቃል፡፡

ሰው ሁሉን የሚያይ ምድርን በፍትህ የሚያስተዳደር እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ እንዲቆጣ እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ነው የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና። የሚለው፡፡ ያዕቆብ 1፡20 ሰው እግዚአብሄር እንደሌለ አድርጎ የህይወትን አቅጣጫ ሁሉ ሊጣጠር ከሞከረ በከንቱ ይደክማል፡፡ መዝሙር 127፡1

አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ ####ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ገና አላወቀም

learner-view-homepage-banner.jpgአውቃለሁ እንደሚል ሰው የሚያስፈራ ሰው የለም፡፡ አውቃለሁ የሚል ሰው ለመማር ምንም ስፍራ የለውም፡፡ አውቃለሁ የሚል ሰው ለመማር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ አውቃለሁ የሚል ሰው ለመሻሻል ምንም ቦታ የለውም፡፡ አውቃለሁ የሚል ሰው ማደግ አቁሟል፡፡ ሁሉንም አውቃለሁ የሚል ሰው ለመለወጥ ተስፋ የለውም፡፡

ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኸውን? ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው። ምሳሌ 26፡12

ሁሉን አውቃለሁ ማለት የሚችል እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም እየተማርን ነው፡፡ ለመማር እስከተዘጋጀን ድረስ ሁል ጊዜ እንማራለን፡፡ ለመማር እስከፈቀድን ድረስ የምንማራቸው እጅግ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በእውቀት ይበልጠናል፡፡ ከማንም ሰው ለመማር ፈቃደኛ ከሆንን ማንም ሰው ሊያስተምረንና በህይወታችን ላይ ዋጋን ሊጨምር ይችላል፡፡ ሁልጊዜ የሚማር ልብ ካለን በማንም ሰው አማካኝነት ለህይወታችን መለወጥ የሚጠቅም ቁልፍ ነገር ልንማር እንችላለን፡፡

ሰው ባወቀ መጠን የሚያውቀው ማወቅ የሚገባውን ያህል አንደማያውቅ ነው፡፡

ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡2

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #እውቀት #የሚማርልብ #የዋሃት #ትህትና #ልብ #እምነት #ሰነፍ #ተስፋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የኢየሱስ ትህትና

a4a645a0237a505ac98f74a044004180_puyallup-united-methodist-clipart-jesus-on-donkey_281-299.jpegኢየሱስ ለእኛ ሰው ሆኖ ወደምርድ ስለመጣ ፍፁም ምሳሌያችን ነው፡፡ ማንንም ባንከተል ኢየሱስን መከተል አለብን፡፡ ማንም ምንም የሚጎድለው ባህሪ ቢኖር ኢየሱስ በባህሪው ፍፁም ነው፡፡ ኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ ልንከተለው የምንችለው አስተማማኝ ምሳሌያችን ነው፡፡

እኛም እንድንከተለው ከታዘዝነው የኢየሱስ ባህሪያት አንዱ ትህትናው ነው፡፡ ኢየሱስ ትሁት ነው፡፡ ከኢየሱስ ትህትና ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡

 1. የኢየሱስ ትህትና የመነጨው ራሱን ከማወቁ ነው፡፡ ሰው ትሁት መሆን ካቃተው የበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው ማለት ነው፡፡ ሰው የበታችነት ስሜት ካለበት ያንን ለማካካስ ራሱን ይኮፍሳል ትእቢተኛም ይሆናል፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለውን የክብር ቦታ የተረዳ ሰው ግን እርሱን ሊያዋርደው የሚችል ምንም ዝቅታ እንደሌለ ስለሚያምን ራሱን ማዋረድ አይቸግረውም፡፡ ስለማንነቱ እርግጠኛ ካልሆነ ሁልጊዜ በትእቢት ይነፋል፡፡

ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ዮሐንስ 13፡3-5

 1. ትህትና ከላይ ከላይ የምናሳየው ሳይሆን የልብ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው በልቡ ትእቢተኛ ሆኖ በአንደበቱ የትህትና ቃሎችን ተለማምዶ ሊናገራቸው ይችላል፡፡ ሰው በልቡ ትእቢተኛ ሆኖ በአካሄዱ ትሁት ሊመስል ይችላል፡፡ እውነተኛው ትህትና የልብ ትህትና ነው፡፡ እወነተኛው ትህትና ማንም ሳይሰማን በምንናገረው ነገር ይታወቃል፡፡ የልብ ትህትና ማንም በማያየን ጊዜ በምናደርገው ነገር ይታያል፡፡

ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ማቴዎስ 11፡29

 1. ትሁት ሰው ስለ ደህንነቱና ስለ ማግኘቱ በእግዚአብሄር ይታመናል፡፡ ትሁት ሰው ለመተው ለመልቀቅ ዝግጁ ነው፡፡ ትሁት ሰው የራሱ ክብር ሳይሆን የሌላውን ጥቅም ያስቀድማል፡፡ ትሁት በሚሰጠው በእግዚአብሄር ስለሚታመን ለማጣት ዝግጁ ነው፡፡ ትህትና የማይገባንን ሳይሆን የሚገባንን መተው ነው፡፡ ትህትና ንጉስ በአህያ ውርንጭላ ሲሄድ ነው፡፡

ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ማቴዎስ 21፡4-5

ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ኢሳይያስ 53፡7

 1. ትህትና እግዚአብሄርን ብቸኛ ምንጭ ከማድረግ ይመጣል፡፡ ትህትና በስሜት አለመመራት ነው፡፡ ትህትና ሃያልነት እንጂ ሽንፈት አይደለም፡፡ ትህትና ሃይልን ለክፋት ላለመጠቀም ከመወሰን ጥበብ ይመጣል፡፡

አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። ማቴዎስ 12፡19-20

 1. ትህትና ሰዎችን አንድናከብር እንደ እግዚአብሄር ለሰዎች ታላቅ ዋጋ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ትህትና ሰዎችን ከመናቅ ትእቢት ነፃ ያወጣናል፡፡

ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ፊልጵስዩስ 2፡3

 1. ትሁት ሰው ልታይ ልታይ አይልም፡፡ ትሁት ሰው ራሱን ይደብቃል፡፡ ትሁት ሰው ለስሙ አይጋደልም፡፡ ኢየሱስ ሰዎችን ከፈወሰ በኋላ ለማንም አትንገሩ ይል ነበር፡፡ የኢየሱስ ትኩረት የሰዎች መጠቀም እንጂ የራሱ ስም ዝና አልነበረም፡፡

ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው። ማቴዎስ 17፡9

 1. ትሁት ሰው እግዚአብሄር በሌላው እንደሚጠቀም ያምናል፡፡ ትሁት ሰው ራሱን አንድ ለእናቱ (ሱፐር ስታር) አድርጎ አያይም፡፡ ትሁት ሰው ሌሎችን በማገልገል በማንሳትና በመጥቀም ይረካል፡፡

እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ማቴዎስ 8፡26

 1. ትሁት ሰው ያለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሄር እንደሆነ ስለሚያምን ስለማጣት ምንም አይሰጋም፡፡ ትሁት ሰው ቀድሞ ራሱን ስላዋረደ ማንም ሊያዋርደው አይችልም፡፡ ትሁት ሰው ህይወቱን ቀለል ስላደረገና ውስብስብ የቅንጦትን ህይወት ስለሚሸሽ ለእግዚአብሄር የሚመች አገልጋይ ይሆናል፡፡

ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው። ሉቃስ 9፡58

 1. ትህትና ገመናን ይሸፍናል፡፡ ትህትና ከውድ ልብስ በላይ ሞገስ የሚሰጥ ልብስ ነው፡፡

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5

 1. ትሁትና የእግዚአብሄርን መንፈስ ይስባል፡፡ ካለን ምንም ነገር በላይ ትህትናችን እግዚአብሄርን ይማርከዋል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2

 1. እንደ ትህትና የተሻለ አስተማማኝ ዋስትና የለም፡፡ እግዚአብሄር ከትሁቱ ጋር ይወግናል፡፡ እግዚአብሄር ለተዋረደው ይዋጋል፡፡ እግዚአብሄር ለትሁታን ፀጋን ይሰጣል፡፡

ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው። ምሳሌ 22፡4

በፌዘኞች እርሱ ያፌዛል፥ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል። ምሳሌ 3፡34

 1. ትህትና ከእግዚአብሄር የሆነን ክብር መቀበያ ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ ትህትና በህይወታችን እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር መጠየቂያ መንገድ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ፊልጵስዩስ 2፡9

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

ጥሩ ትምክተኛ

boast boy.jpgእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፡፡ ጠቢብ ጥበቡ የሆነ ነገር እንደሚያደርግለት አያስብ፡፡ ጠቢብ ጥበቡን አያጋንነው፡፡ ጠቢብ ጥበቡ ማድረግ የማይችለውን ብዙ ነገር እንዳለ ይረዳ፡፡ ጠቢብ የጥበቡን ውስንነት ይረዳ፡፡ ጠቢብ በጥበቡ ተስፋ አያድርግ፡፡

በተቃራኒው ደግሞ ሞኝ ከህይወት ጎድያለሁ አይበል፡፡ ሞኝ ጥበበፃ ስላልሆነ ብቻ ምንም እንደጎደለው አያስብ፡፡ ሞኝ የህይወት ቁልፉ እንደሌለው ተስፋ አይቁረጥ፡፡ ሞኝ በሞኝነቱ አይሰማው፡፡

እግዚአብሄ እንዲህ ይላል፡፡ ሃያል በሃይሉ አይመካ፡፡ ሃያል በሃይሉ ደስ አይበለው፡፡ ሃያል በሃይሉ አይኩራራ፡፡ ሃያል የሃይሉን ውስንነት ይወቅ፡፡ ሃያል ሃይሉ የማያደርግለትን ብዙ ነገሮች ይረዳ፡፡ ሃያል በሃይሉ ውስጥ መልስ እንዳለ አያስብ፡፡ ሃያል በሃይሉ ላይ ልቡን አይጣል፡፡

በተቃራኒው ደካማው ከህይወት እንደተቆረጠ አይምሰለው፡፡ ደካማው በድካሙ አይዘን፡፡ ደካማው በድካሙ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ የሚያጣው እንዳለ አይምሰለው፡፡ ደካማው በድካሙ ድፍረቱን አይጣ፡፡

ባለጠጋም ባለጠግነቱ ውስጥ የህይወት መልስ ያለ አይምሰለው፡፡ ባለጠጋም ባለጠግነቱን አያጋነው፡፡ ባለጠጋም በባለጠግነቱ ከፍ ከፍ አይበል፡፡ ባለጋም ብልጥግናውን አያመሰግን፡፡ ባለጠጋ የብልጥግናውን ውስንነት ይረዳ፡፡ ባለጠጋ ብልጥግናው ማድረግ የማይችለውን ነገር ይወቅ፡፡ ባለጠጋው በብልጥግናው አይታመን፡፡

እንዲሁም በተቃራኒው ደሃ ከህይወት ድርሻ ወድቄያለሁ አይበል፡፡ ድሃ በድህነቱ ብቻ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ድሃ በድህነቱ የሚያጣው መልካምነት ነገር እንዳለ አይምሰለው፡፡ ድሃ በድህነት የህይወት ቁልፍ እንደሌለው አይሰማው፡፡ ደሃ በድህነቱ አይዘን፡፡

በጥበብ ውስጥ የህይወት መልስ የለም፡፡ ህይወት በጥበብ አትሰራም፡፡ ጥበብ የህይወት ቁልፍ አይደለም፡፡ ሃያልነት ምንም አያመጣም፡፡ ህይወት በሃያልነት አይደለም፡፡ ሃያልነት ህይወትን አይሰራም፡፡ ሃያል የህይወት ቁልፍ የለውም፡፡ ለህይወት ሃያልነት ወሳኝ አይደለም፡፡ ለህይወት ስኬት ባለጠግነት መልስ አይደለም፡፡ ባለጠግነት ህይወትን አያከናውንም፡፡ ባለጠጋ የህይወት ቁልፍ የለውም፡፡

የህይወት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር ጋር ብቻ ነው፡፡ ለሰው ህይወትን የሚያሳካው ጥበብ ፣ ሃይል ወይም ባለጠግነት ሳይሆን እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ካላለ ሃያል ሰው ሃይሉ ህይወትን ሊያሰምርለት አይችልም፡፡ የህይወት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር ጋር እንጂ ባለጠጋ ጋር አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ካላለ በጥበብ ፣ በሃይል ወይም በባለጠግነት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡

አለምን የሚመራው እግዚአብሄር ነው፡፡ ለሰው ምህረትን የሚያደርገው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ነው ለሰው የማይገባውን መልካምነት የሚሰጠው፡፡ እግዚአብሄር ነው የሚፈርደው፡፡ቁልፉ እግዚአብሄር ጋር ነው፡፡ የህይወት ቀልፍ ጠቢብም ጋር ፣ ሃያልም ጋር ባለጠጋም ጋር ሳትሆን እግዚአብሄር እጅ ነች፡፡ የሰውን ሃብት ፣ የሰውን ጥበብ ፣ የሰውን ባለጠግነት ሳያይ የሰውን ሳያዳላ በፅድቅ አለምን የሚያስተዳድረው እግዚአብሄር ነው፡፡

ይህን ያወቀ ሰው በጥበብ ላይ ልቡን አይጥልም፡፡ ይህን ያወቀ ሰው በሃይሉ አይመካም፡፡ ይህን የተረዳ ሰው በባለጠግነት ላይ ተስፋ አያደርግም፡፡ ይህን ያወቀ ሰው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ በሚያደርግ በእግዚአብሄር ይመካል፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጥበብ #ማስተዋል #መረዳት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የየዋህነት ክብር

decent.jpgየጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም። ደግሞም፦ ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡24-26

የዋህነት የመንፈስ ፍሬ እንደሆነና መንፈሳዊ ውጤታችንና ፍሬያማነታችነ የሚለካበት ወሳኝ ባህሪ እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። ገላትያ 5፡22

በነገር ሁሉ ምሳሌያችን የሆነው ኢየሱስ የዋህ ነበረ፡፡ ከእኔም ተማሩ ብሎ ያስተምረናል፡፡

ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤  ማቴዎስ 11፡29

የዋህነት የጥሪያችን ደረጃ ነው፡፡ ከየዋህነት ያነሰ ኑሮ እንድንኖር አልተጠራንም፡፡  ለጥሪያችን እንደሚገባ መኖር በየዋህነት መኖር ነው፡፡

እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ ኤፌሶን 4፡1-2

ስለየዋህነት መፅሃፍ ቅዱስ ብዙ ያስተምራል፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህን ያህል ስለ የዋህነት አስፈላጊነት ካየን የየዋህነትን ትርጉም እንመልከት፡፡

ግን የዋህነት ምንድነው?

የዋህነት በብዙ ቃላት ሊተረጎም የሚችል ቃል ነው፡፡ የየዋህነትን ትርጉም እንመልከት፡-

ቸር

መልካምና ርህሩህ አዛኝ ስለሌላው ግድ የሚለው

ክፉና ግፈኛ ያልሆነ

ለሰው የሚጠነቀቅ ፣ ግዴለሽ ያልሆነ ፣ ራስ ወዳድ ያልሆነ ፣ የሰውን ፍላጎት የሚያከብር

ልከኛ

ለጥቅም የማይስገበገብ ፣ በቃኝ የሚል ፣ ለመኖር ብዙ ነገር የማይጠይቅ

የተከበረ

ሰዎች የሚያከብሩት ፣ ክብሩን ጠብቆ የሚኖር ፣ የሚያዋርደውንና የሚያስንቀውን ክፉ ነገር የማያደርግ

ጨዋ

የተገራ ፣ ለጥቅም የማይጣላ ፣ በራስ ወዳድነት የማይከራከር

ሰላማዊ

ሰላም ያለው ፣ ለሌላም ሰላም የሚሰጥ ፣ አስጊ ያልሆነ

አክባሪ

ሰውን አክባሪ ፣ ሰውን የማይንቅ ፣ ለሰው ትልቅ ስፍራ ያለው

ጭምት

ረጋ ያለ ፣ የማይቸኩል ፣ ቁጥብ ፣ ስሜቱን የሚገዛ

በተራ ነገር ላይ የማይገኝ

በትክክለኛው መንገድ የማይመጣን ጥቅም የሚንቅ ፣ ነውረኛ ረብ የማይወድ

ደረጃው ከፍ ያለ

መልካም ባህሪ ያለው በሚሉት ቃላት ሊገለፅ ይችላል፡፡

በጣም ልቤን የነካኝ ይህን ሁሉ ሃሳብ ይበልጥ ሊገልፅ የሚችል የሚርያም ዌብስተር የመዝገበ ቃላት ትርጉምን ላካፍላችሁ፡፡

Gentleman a :  a man of noble or gentle birth d :  a man of independent means who does not engage in any occupation or profession for gain

https://www.merriam-webster.com/dictionary/gentleman

Gentleman የዋህ ፡- የነገስታት ቤተሰብ አባል የሆነ ጥቅም ለማግኘት ማንኛውንም ሥራ ወይም ሙያ ለመሰማራት የማይፈልግ ነፃ ሰው ማለት ነው፡፡

እኛ ኢየሱስን አንደአዳኝና ጌታ የተቀበልን ክርስቲያኖች ይህ መግለጫ በትክክል ይገልጠናል፡፡ አሁን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነናል፡፡ የምንሰራው ለመኖር አይደለም፡፡ ለመኖር አንጨነቅም፡፡ ለኑሮዋችን የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ የሚያዘጋጀው አባታችን እግዚአብሄር ነው፡፡

እኛ የምንሰራው ከፍ ላለ ነገር ነው፡፡እኛ የምንሰራው ለመንግስቱ ነው፡፡ እኛ የምንፈልገው የእግዚአብሄርን ፅድቅ ነው፡፡ ሌላ ሁሉ በእግዚአብሄር የሚጨመርልን የእግዚአብሄር ቤተሰብ አባላት ነን፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ገርነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #የዋህነት #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱ

 

All things were made by him.jpgሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36

ሁሉ ከእርሱ

መልካምነት ሁሉ ከእርሱ ነው፡፡ እኛም ከእርሱ ነን፡፡ የሚያቀርበው እርሱ ነው፡፡ መልካንም ነገር ለማድረግ የሚያስፈልገውን መነሳሳት እንኳን የሚሰጠን እርሱ ነው፡፡ ድፍረትን የሚሰጠን ራሱ ነው፡፡ የሚያበረታን እርሱ ነው፡፡ ሁሉ ከእረሱ ነው፡፡

ሁሉ በእርሱ ነው

ከእግዚአብሄር ጋር አብረን የምንሰራ ነን፡፡ እርሱ ሲሰራ እንተባበረዋለን፡፡ እርሱ እየሰራ ነው፡፡ በእድል የሆነ ነገር የለም፡፡ ሁሉንም የነደፈው እርሱ ነው፡፡ የሚጀምረውና የሚመራንና እርሱ ነው፡፡ እርሱ የሚሰራበትን ፈልገን እንተባበረዋለን፡፡ በእኛ ሃይል ለእግዚአብሄር አንኖርም እግዚአብሄርንም በራሳችን ሃይል አናገለግልም፡፡ ሁሉ በእርሱ ነው፡፡

የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9

ሁሉ ለእርሱ ነው

ሁሉንም እንዴት ለራሱ ክብርና ለእኛ ጥቅም እንደሚለውጠው ያውቃል፡፡ ሁሉ ለእርሱ ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማንም መጠቀሚያ ሊያደርገው አይችልም፡፡ እንዴት የሁሉንም ነገር መጨረሻ ለራሱ አላማ እንደሚለውጠው ያውቃል፡፡ ክብሩንም ሁሉ መውሰድ ያለበት እግዚአብሄር ነው፡፡

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28

ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#በእርሱ #ለእርሱ #ከእርሱ #ክብር #አላማ #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: