መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው

Manhã-de-oração1-1140x712.jpgያቤጽም፦ እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው። 1ኛ ዜና 4፡10

ያለንበት ደረጃ ፍፃሜያችን አይደለም፡፡ ስለዚህ ነው እንደያቤጽ አይነት ስሜት የሚሰማን፡፡ ልባችን ለመስፋት የሚጮኸው፡፡ የመጥበብ ስሜት ይሰማናል፡፡ የእግዚአብሄር በረከት ይህ ብቻ እንዳይደለ ይሰማናል፡፡ ባሁኑ ደረጃችን ረክተን እልተቀመጥንም፡፡ የእግዚአብሄርን እጅና ሃይል ይበልጥ እንፈልጋለን፡፡

ወደ እግዚአብሄር መቅረብ መፀለይ መማለድ እግዚአብሄር እንዲመልስ ያደርጋል፡፡

ታእምር ቅርባችን ነው ያለው፡፡ በክርስቶስ ያልተሰጠን ነገር የለም፡፡ ሁሉ በክርስቶስ ተዘጋጅቶልናል፡፡ አይናችን ግን ሊከፈት ይገባዋል፡፡ አጥርተን ማየት ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሄር ድንበራችንን ከማስፋቱ በፊት እይታችንን ነው የሚያሰፋው፡፡ ይበልጥ ባየን ቁጥር በተሰጠን በረከት ውስጥ እንገባለን፡፡

ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ። መዝሙር 119፡18

ቃሉ ተኣምር የታጨቀ ነው፡፡ የምንፈልገው ነገር ሁሉ በቃሉ ውስጥ አለ፡፡ የእግዚአብሄርን ተኣምር በቃሉ ውስጥ ፈልገው፡፡ የልብህን ጩኸት መልስ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ፈልግ፡፡ የእግዚአብሄር ተኣምር በቃሉ ውስጥ ነው፡፡

ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፦ ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። ዘፍጥረት 13፡14-15

ባየን መጠን ነው በረከት ውስጥ መግባት የምንችለው፡፡ ያየነውን መጠን ብቻ መውሰድ የምንችለው፡፡ ባየነው መጠን ብቻ ነው ተጠቃሚ መሆን የምንችለው፡፡ እግዚአብሄን የሚለው አይንህን አንሳና ተመልከት፡፡

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡17-19

በህይወታችን ካየነው አሉታዊ ሁኔታዎች የተነሳ እንዳንዘረጋ የሚያስፈራሩ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አትችልም ፣ አትበቃም ፣ አትመጥንም ፣ ይቅርብህ ይሉናል፡፡ በህይወታችን ያሳለፍነው አሉታዊ ልምድ እንዲሁ ዋ! እንዳትዘረጋ እያለ ያስጠነቅቅናል፡፡ እግዚአብሄር ግን እንዲህ ይላል፡- የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ አትቆጥቢ፡፡

የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና። ኢሳይያስ 54፡2-3

እንዳየን ደግሞ እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡ እጃችንን ዘርግተን መውሰድ አለብን፡፡ የሰጠንን ነገር መርገጥ አለብን፡፡ እግዚአብሄርን በመታዘዝ እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡

ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ። ኢያሱ 1፡3

የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። ዘዳግም 11፡24

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #ፀሎት #እግዚአብሄርንመፈለግ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #መርገጥ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መቃተት #መንበርከክ #መጠበቅ #ትግስት #መሪ

About apostle AbiyWakumaDinsa

The fear of the Lord is the beginning of knowledge, but fools[a] despise wisdom and instruction. Proverbs 1:7 The fear of the Lord is the beginning of wisdom, and knowledge of the Holy One is understanding. Proverbs 9:10

Posted on March 16, 2017, in Prayer. Bookmark the permalink. Comments Off on መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው.

Comments are closed.