Blog Archives

በምድር ላይ ያለንበት ዋነኛው አላማ

evangelism8.jpgኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20

ብዙ ጊዜ የሚባል አባባል አለ፡፡ በምድር ላይ የምንፈፅመው የወንጌል አላማ ባይኖረው ልክ በክርስቶስ እንደዳንን እግዚአብሄር ወደ ራሱ ይሰበስበን ነበር፡፡ እውነት ነው ከምንም ነገር በላይ በምድር ላይ የወንጌል አደራ አለብን፡፡ በምድር ያለነው እግዚአብሄርን በሚመስል ኑሯችን ለአለም የመዳንን መንገድ ለማሳየት ነው፡፡

እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ሐዋርያት ሥራ 16፡17

በምድር ያለንው ብርሃን ልንሆን ነው፡፡ በምድር ያለነው የምድር ጨው ለመሆን ነው፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። ማቴዎስ 5፡13-14

በምድር ያለነው በስራችን የእግዚአብሄርን መልካምነት ለማንፀባረቅ ነው፡፡ በምድር ያለነው የእግዚአብሄርን መንግስት ለመግለጥ ነው፡፡

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። ማቴዎስ 5፡16

በየእለት ነፍሳችንን የምንክደው በኑሮና በቃል ወንጌልን ለመሰበክ ነው፡፡

ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን፥ እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌልን መመስከር በሃሴት እፈጽም ዘንድ፥ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፡፡ ሐዋሪያት ሥራ 20:24

በምድር ያለነው ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ ነው፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-19

በምድር ያለነው የክርስቶስ አምባሳደሮች በመሆን ነው፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20

በምድር ላይ ሌሎች ሌሎች የምናደርጋቸው አላማዎች ቢኖሩንም ወንጌልን ስንኖርና ስንሰብክ እግረ መንገዳችን የምናደርጋቸው ነገሮች እንጂ ዋና ነገሮች አይደሉም፡፡ በምድር ላይ ያለንበት ዋናው ምክኒያት ወንጌልን መስበክ ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሰራዊት ጌታ እንደዚህ ይላል

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡ ትታመኑብኝ አልነበረምን? ሁሉን ጥላችሁ ተከትላችሁኝ አልነበረምን? ከእኔ ውጭ መተማመኛ ሳትፈልጉ አላገለገላችሁኝምን?

ታዲያ እኔን ታምናችሁ በወጣችሁ ጊዜ ምን ጎደለባችሁ ? ታዲያ በላክኋችሁ ጊዜ ምን አጎደልኩባችሁ ይላል እግዚአብሄር? ያላደረግኩላችሁ ነገር ነበርን ይላል የሰራት ጌታ እግዚአብሄር?

ታዲያ አሁን ከእኔ ውጭ ደህንነትን ለምን ፈለጋችሁ? ታዲያ በቁሳቁስና በገንዘብ ደህንነትን ለምን ፈለጋችሁ ይላል እግዚአብሄር? ቦዶ እጃችሁን እንዳልተከተላችሁኝ ያላችሁ ለምን አልበቃ አላችሁ ይላል እግዚአብሄር? እኔ አልለወጥም ይላል እግዚአብሄር፡፡

ስትደገፉብኝ ፣ ፊቴን ስትፈልጉ ፣ ጌታ ጌታ ስትሉኝ ያረካኛል ይላል እግዚአብሄር፡፡ በእኔ ተደገፉብኝ ፣ እኔ ብቻ ደህንነታችሁ ልሁን ይላል እግዚአብሄር፡፡ ያላችሁ ምንም ነገራችሁ ደህንነት አይሁናችሁ ይላል እግዚአብሄር፡፡

አሁንም ተመለሱ ይላል እግዚአብሄር፡፡ ቁሳቁስን ገንዘብን ከመፈለግ እኔን ፈልጉ ይላል እግዚአብሄር፡፡ በእኔ ውስጥ የህይወታችሁ ጥያቄ ሁሉ መልስ አለ ይላል እግዚአብሄር፡፡ የምትፈልጉት ሁሉ እኔ ውስጥ አለ ይላል እግዚአብሄር፡፡

እኔ አልለወጥም፡፡ እስከ ሽምግልና የምሸከምህ እኔ ነኝ ይላል እግዚአብሄር፡፡

ባላችሁ ነገር ሳይሆን በእኔ ላይ ስትደገፉ ደስ ይለኛል ይላል እግዚአብሄር፡፡ በእኔ ላይ ስትደገፉ ብቻ ያረካኛል ይላል እግዚአብሄር፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

%d bloggers like this: