Category Archives: ministry

የአገልግሎት ስምረት መለኪያ

scale 1.jpgየቃል አገልጋይ ስኬት የሚለካው ክርስቶስን በመስበክ በክርስቶስ ፍፁም የሆነን ሰው በማቅረብ ነው ፡፡

እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ። ቆላስይስ 1፡28-29

የቃል አገልግሎት ስኬት የሚለካው ሰዎችን ምን ያህል ወደ ክርስቶስ እንዲያድጉ በመደረጉ ነው፡፡

ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤ ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል። ኤፌሶን 4፡15-16

የእግዚአብሄር ቃል አገልግሎት ስምረት የሚለካው ሰዎች ምን ያህል በክርስቶስ ፍቅር መኖር መማራቸው ነው፡፡

ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም። የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡4-5

የቃል አገልጋይ ስኬት የሚመዘነው የተሰቀለውን ክርስቶስን በሰዎች አይን ፊት በግልፅ መሳሉ ነው፡፡

የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?ገላትያ ሰዎች 3፡1

የእግዚአብሄር ቃል አገልጋይ የሚመዘነው በሰዎች ልብ ክርስቶስን መፃፉ ነው፡፡

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 3:1-3

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

Advertisements

አምስቱ የአገልግሎት እንቅፋቶች

stumble3.jpgእግዚአብሄርን ማገልገል ከምንም ነገር በላይ የከበረ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እንዲያመልከውና እንዲያገለግለው ነው፡፡ እግዚአብሄር የእስራእኤል ህዝብን ከግብፅ ሲያወጣ እንዲያገለግለኝ ህዝቤን ልቀቅ ነው ያለው፡፡

የተፈጠርንበትን እንዲሁም በእግዚአብሄር የዳንንበትን ዋናውን አላማ እግዚአብሄርን የማገልገል ሃላፊነታችንን እንዳንፈፅም ህይወታችንን ከንቱ ሊያደርጉ የሚመጡ የህይወት አንቅፋቶች አሉ፡፡

እግዚአብሄርን የሚያገለግል ሰው የተፈጠረበትን አላማ ይፈፅማል እግዚአብሄርም እርሱን ያከብረዋል፡፡

የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል። ዮሐንስ 12፡26

ባለን ነገር አለመርካት

ባለው የሚረካ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የሚችለው፡፡ ሰው ባለው ነገር በረካበት መጠን ብቻ ነው እግዚአብሄርን ማገልገል የሚችለው፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

ጌታን እንደምናገለግል አለማወቅ

ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። ቆላስይስ 4፡17

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላስይስ 3፡23-24

የአለም ሃሳብ

የህይወት ሃላፊነቶቻችንን ለእግዚአብሄር ካልሰጠናቸውና እግዚአብሄር በሰጠን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን የመፈለግ ሃላፊነታችን ላይ ካላተኮርን እግዚአብሄርን ማገልገል የሚባለው ነገር ዘበት ነው፡፡ ፊት ከሰጠነው የኑሮ ሃሳብ በቁማችን ሊውጠን የሚችል ብዙዎችን ከአገልግሎት አስፈራርቶ ከንቱ ያደረገ ነገር ነው፡፡

የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33

ክርስቶስን አለመመልከት

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2

የእግዚአብሄርን ፀጋ አለመረዳት

እግዚአብሄርን የምናገለግለው በእርሱ በራሱ ወጭ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው በራሱ ሃይል እንደሆና ካላወቅን እንታክታለን፡፡

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣3-4

ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡1

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #አገልግሎት #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል

glory111.jpgየሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል። ዮሐንስ 12፡26

እግዚአብሄርን ማገልገል እጅግ የከበረ ነገር ነው፡፡

እንዲያውም የሰው የመጨረሻው የክብር ደረጃ መሰረታዊ ፍላጎትን እያሟላ ጌታን መከተልና ነው፡፡ ይህ የሚቀናበት ሰው ነው የሚባለው ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን የሚወድና የሚያገለግል ሰው ነው፡፡

መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን ከማገልገል በላይ የሆነ ምንም የክብር ደረጃ የለም፡፡ በክርስትና ሚሊየነርነትና ቢሊየርነት መሰረታዊ ፍሎጎትን አሟልቶ ጌታን ተከትሎ መኖር ነው፡፡

ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8

የመጨረሻ የከበረ ሰው የሚያደርገው ጌታን መከተል ነው፡፡ በክርስትና የስኬት ጣራ ጌታን ማገልገል ነው፡፡ በክርስትና አብ የሚያከብረው ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን በማሟላት ለጌታ የሚኖር ሰው ነው፡፡ በክርስትና እጅግ የተሳካለት ሰው መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ እግዚአብሄርን መስሎ የሚኖር ሰው ነው፡፡

መሰረታዊ ፍላጎቱን አሟልቶ ጌታን የሚከተለው ሰው በክብር ከማንኛውም ባለጠጋ ፣ ዝነኛና ሃያል ሰው ይበልጣል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጌታንመከተል #ጌታንማገልገል #ጌታንመውደድ #ስኬት #ክንውን #እግዚአብሄርንመምሰል #ቃል #ማሰላሰል #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

መጋቢነትና የገቢ ምንጭ

pastor income11.jpgለቤተክርስቲያነ ከተሰጡት 5ቱ የአገልግሎትር ስጦታዎች አንዱ መጋቢነት ነው፡፡ መጋቢነት ለሰዎች ነፍስ የመትጋት ታላቅ ሃላፊነትን የሚጠይቅ አገልግሎት ነው፡፡

የመጋቢነትን አገልገሎት ዋጋ ሊከፍል የሚችል ገንዘብ የለም፡፡ መጋቢ በምድር ላይ እንደሚኖር እንደ ማንኛውም ሰው ገንዘብ በምድር ላይ ኑሮ ያስፈልገዋል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስም ስለ መጋቢ ብሎም ስለሌሎች የአገልግሎት ስጦታዎች የገቢ ምንጭ ያስተምራል፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ በኑሮ ሃሳብና በባለጠግነት ምኞት ሙሉ ፍሬ ስለማያፈሩ ሰዎች ስለሚያስተምር መጋቢም ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ ከሚያደርጉት ነገሮች ራሱን ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡(ማርቆስ 4፡19) መጋቢ የገቢ ምንጩን ከየት ያገኛል፡፡ መጋቢ ስለገቢ ምንጩ ዘወር ማለት ያለበት ወደ ማን ነው?

  1. መጋቢ ለአቅርቦቱ ወደ እግዚአብሄር ብቻ ማየት ይገባዋል

መጋቢ በመጀመሪያ የእግዚአብሄር ልጅ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነ ሰው ሁሉ ደግሞ የሚኖረው ስለሰራ ወይም ስላልሰራ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን እሰከፈለገ ድረስ እግዚአብሄር የሚያስፈልገውን የሚሰጠውና የሚንከባከበው የቤተሰቡን አባል ስለሆነ ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33

በቤት የተወለደ ልጅን አባቱ የሚንከባከበው እንደስራው መጠን ሳይሆን እንደ ቤተሰቡ ደረጃ ነው፡፡ እንዲሁም መጋቢ የመጋቢነትን ታላቅ ሃላፊነት ከመቀበሉ በፊት የልጅነት መብት የመጠቀም እምነት ያስፈልገዋል፡፡ መጋቢ ከመሆኑ በፊት በእግዚአብሄርን አባትነትና አቅራቢነት እምነት ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ወደ መጋቢነቱ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት ስለሚያስፈልገው ነገር እግዚአብሄርን ማመን ሊማር ይገባዋል፡፡

  1. መጋቢ ህዝቡን የገቢ ምንጭ ማድረግ የለበትም፡፡

 

መጋቢ የአቅርቦት ምንጩ እግዚአብሄርን ብቻ ማድረግ አለበት፡፡ መጋቢ የሚመግባቸውን ሰዎች ምንጩ ካደረገ ህይወቱ ይወሳሰባል ነፃም ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ሲቀንስና ሲጨምር ገቢው አብሮ ይጨምራል ይቀንሳል፡፡ እግዚአብሄር የሰጠውን የመጋቢነት ሃላፊነት ለመወጣት ሳይሆን ገቢውን ለመጨመር በምንም መልኩ ህዝብን ለማብዛት ይፈተናል፡፡ መጋቢ የሚመራቸውን ሰዎች የገቢ ምንጩ ካደረገ እንደ ገቢው አመጣጥ ከፍ ዝቅ እንዳይል ብዙ ገንዘብ ያላቸውን ልዩ እንክብካቤ ለማድረግ ይፈተናል፡፡ መጋቢ እግዚአብሄርን የገቢ ምንጩ ካላደረገ የሚመራቸውን ለመገሰፅ አቅም ያጣል፡፡ መጋቢ ህዝቡን የገቢ ምንጩ ካደረገ የእግዚአብሄርን ቃል ለማመቻመች ይፈተናል፡፡

 

  1. መጋቢ ስለ አቅራቦቱ የእግዚአብሄርን ቃል ማመን አለበት

 

መጋቢዎች የእግዚአብሄር ቃል የሚናገረውን ወንጌልን የሚሰራ በወንጌል ይኖር የሚለውን ቃል ለማመን ሲቸገሩ ሌላ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ይጥራሉ፡፡ ሌላ የገቢ ምንጭ መፍጠር በራሱ ችግር የለውም፡፡ አንዳንዶች መጋቢዎች ለቃሉና ለፀሎት ከመትጋት ውጭ ሌላ ስራ እየሰሩ የእግዚአብሄን ህዝብ የሚያገለግሉ የተባረኩ መጋቢዎች አሉ፡፡

 

ችግሩ መጋቢው ወንጌልን በሚሰራበት ጊዜና ጉልበት ሌላ የገቢ ምንጭ ማስገኛ ነገር ውስጥ ከገባ የሰዎችን ህይወት በትጋት የመስራት ስራው ይበደላል፡፡ መፅሃፍ ወንጌልን የሚሰራ በወንጌል ይኑር ያለው መጋቢው ለቃልና ለፀሎት እንዲተጋ ሌላ ጊዜውንና ጉልበቱን የሚከፋፈል ነገር ውስጥ እንዳይገባ ነው፡፡

 

ከዚህ አንፃር መጋቢው ያለበትን ጫና ለመቀነስ የሚማረው ከሚያስተምረው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ መከፋፈል አለበት፡፡

 

ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል። ገላትያ 6፡6

 

እንዲሁም መጋቢዎች መንፈሳዊውን ነገር ዘርተው ከሚያገለግሉዋቸው ስጋዊን ነገር ቢያጭዱ ትልቅ ነገር አይደለም፡፡

 

እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡11

 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #አቅርቦት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ገቢ #ቃል #መዝራት #ወንጌል #መጋቢ #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከአካላችን ብልቶች ምን እንማራለን ?

body.jpgበአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን። ሮሜ 12፡4-5

መንፈሳዊ እውነትን ለማስጨበጥ ተፈጥሮአዊ አካላችን በምሳሌነት ሲጠቀስ ብዙ ጊዜ እንመለከታለን፡፡ አካላችንን በመመልከት ብቻ ብዙ መንፈሳዊ ትምህርትን ልንቀስም እንችላለን፡፡

ሃዋሪያው ጳውሎስ “ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁም “1ኛ ቆሮ 11፣14 በማለት ተፈጥሮን በመመልከት ብቻ የምንማራቸው ድንቅ ትምህርቶች እንዳሉ ያስተምረናል፡፡

ለምሳሌ የእኛ የክርስትያኖች ህብረት እንደ አካል እያንዳንዳችን ደግሞ እንደ አካል ክፍል ወይም ብልቶች በምሳሌነት ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡

ከአካል ምን እንማራለን?

አካል አንድ ነው

አካል አንድ ነው፡፡ ብልቶች ብዙ ቢሆኑም አካል ግን አንድ ነው፡፡ የአካል ብልቶች የተለያዩ መሆናቸው የተለያየ አላማ እንዲኖረንና ለተለያየ መንግስት እንድንሰራ ፈቃድ አይሰጠንም፡፡ ለተለየ መንግስት ከሰራን ለእግዚአበሄር መነግስት ሳይሆን ለራሳችን መንግስት ነው እያሰታን ያለነው ማለት ነው፡፡  ስለዚህ ነው ለተለያየ አላማ የመስራት ጥሪ የሌለን፡፡ ሁላችንም የምንሰራው ለአንድ መንግስት ለአንድ ግንብ ነው፡፡

ብልቶች የተለያዩ ናቸው

የብልቶችን ልዩነት መቀበል የአካልን አንድነት እንደመቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ከእርሱ የተለየ ሰው ሁሉ ስህተት ይመስለዋል፡፡ ሌላው ጃካለእርሱ ሌላው ጌታ የሚሰራበት አይመስለው፡፡ ለዌላው ደግሞ በእርሱ መንገድ ያልገሄድ ነበትክክለፃ መንገድ እንዳልሄደ ይመስለዋል፡፡

የብልቶች ልዩነት ውበት ነው

የብልቶች ውበት በልዩነታቸው ውስጥ ነው፡፡ ብልቶች ካልተለያዩ ምንም ዋጋ የለውም፡፡ ሁሉም ነገር አንድ አይነት ቢሆን እንዴት ያለ ውድቀት ነው? ሁላችንም አንድ አይነት ከሆንን እንዴት ያለ አሰልቺ ነው፡፡

አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡17

ከእኛ ለተለየ ሰው ልባችንን ልናሰፋ ይገባል፡፡ ከእኛ የተለየ ሰው ይጠቅመናል፡፡ ከእኛ የተለየ ሰው የእኛን ጉድለት ይሞላል፡፡ ከእኛ የተለየ ሰው እኛ ማድረግ የማንችለውን መነገር ያደርግልናል፡፡ ከእኛ የተለየ ሰው ውበታችን ነው፡፡

አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12

በሁላችንም የሚሰራ አንድ እግዚአብሄር ነው

የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-6

ማንም እንዲህ ላገልግል ብሎ በራሱ የሚያገለግል የለም፡፡ የሚያገለግል ከሆነ እግዚአብሄር ነው በውስጡ ያስቀመጠው እግዚአብሄርም ነው በፀጋው የሚያስታጥቀው፡፡ አንተን እግር ያደረገህ እግዚአብሄር ነው ሌላውን አይን ያደረገው፡፡

የብልቶች ውድድር ሞኝነት ነው

ብልቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ጥሪ አላቸው፡፡ የተለያየ ጥሪ ያላቸውን ለማወዳደር እንደማይቻል ሁሉ በብልቶች መካከል ያለ ውድድር ከንቱ ነው፡፡ የሚታገል ሰውንና ሯጭን ማፎካከር እንደማይቻል ሁሉ የተለያየ ጥሪ ያለንን ማወዳደር አይቻልም፡፡ አንዱ ከሌላው ጋር ለመፎካከር የራሱን ጥሪ ጥሎ ያልተጠራበትን ጥሪ ማድረግ ይኖርበታል ፡፡ ስለዚህ ነው ፉክክር የህይወት ብክነት የሚሆነው፡፡ ሰው ከጎረቤቱ ጋር ከተፎካከረ ስቷል ማለት ነው፡፡

አንዱ አንዱን ይነካዋል

የአንዱ መደከም የሌላው መድከም ነው የአንዱ መጠንከር የሌላው መጠንከር ነው፡፡ አንዱ አንዱን እንዲያሟላው እንጂ እንዱ አንዱን እንዲፎካከረው አልተሰራም፡፡ አንዱ በሌላው ውድቀት ካልታመመ አንዱ በሌላው ስኬት ካልተደሰተ ከአካል ብልትነት ውጭ እየኖረ ነው ማለት ነው፡፡

አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡26

አንዱ አንዱን ይሞላዋል

እጅ ውስጥ የተቀመጠው ችሎታ እና በረከት ለእግር ጥቅም ነው፡፡ የአይን ፀጋ ለጆሮ ያስፈልገዋል፡፡ የአንዱ ጥንካሬ ለሌላው ድካም የታቀደና የተሰራ ነው፡፡ አካል ሙሉ የሚሆነው ሁሉም ብልቶች በትክክል ሲሰሩ ነው፡፡

ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡22-23

አንዱ ለሌላው ያስፈልጋል

ዓይን እጅን፦ አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፦ አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡21

አንዱ ብልት ለሌላው ብልት ይጠቅማል፡፡ የአንዱ ብልት መሳካት በሌላው ብልት መሳካት ላይ የተመሰረት ነው፡፡ አንዱ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ያስፈልጋል፡፡ አያስፈልግም የምንለው የአካል ብልት የለም፡፡ ከሚታየው እስከ ማይታየው ከትልቁ እስከ ትንሹ የአካል ብልት ጠቃሚ ነው፡፡ የአለማችን ሳይንቲስቶች ስለአካችን ክፍሎች ጥቅም በክፍለ ዘመናት እየተመራመሩ ይገኛሉ ግን ሁሉንም የአካል ክፍል ጥቅም አውቀው አልጨረሱትም፡፡ እንዲሁም የማይጠቅም የሚመስለን የአካል ብልት ካለ ራሳችንን ትሁት እናድርግ፡፡ ይ-ጠ-ቅ-ማ-ል፡፡

ይህን ሁሉ በስፍራው የሚያስይዘው የእኛ ትህትና ነው፡፡

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ። ሮሜ 12፡3

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልዩነት #አካል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #አንድነት #ፀጋ #ብልት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: