Author Archives: AbiyWakumaDinsa

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው

DsuOreL.jpgበምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ። እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ። መዝሙር 66፡ 1-3

አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው። መዝሙር 92፡4-5

አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ። መዝሙር 40፡5

የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። ሮሜ 11፡33

በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ። ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፤ ከሰው ልጆች ይልቅ በምክር ግሩም ነው። መዝሙር 66፡4-5

አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች። መዝሙር 104፡24

አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና። መዝሙር 86፡10

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #ታላቅ #ድንቅ #ልዩ #ግሩም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

Advertisements

አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን

your will.jpgጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ። ማቴዎስ 26፡39

ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃስ 22፡42

አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ። ማርቆስ 14፡36

እኛ ለእግዚአብሄር ክብር ለመኖር የተጠራን ሁላችን ለእግዚአብሄር መኖር እንፈልጋላን፡፡ ኢየሱስን ስንከተል ለክብሩ ለመኖር ወስነን ነው፡፡ ኢየሱስን የተከተልነው ለሞተልንና ለተነሳው ለኢየሱስ እንጂ ወደፊት ለራሳችን ላለመኖር ነው፡፡

በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።  2ኛ ቆሮንቶስ 5፡15

በተለያየ ጊዜያት በህይወታችን የተለያዩ ምርጫዎች ይቀርቡልናል፡፡ በተለይ ኢየሱስን በሁለንተናችን ለመከተል የወሰንንእኛ ክርስትያኖች በየጊዜው የእኛ ፍላጎትና የእግዚአብሄር ፍላጎት ሲለያይ እንመለከታለን፡፡ በህይወት ጉዞዋችን እኛ የምንፈቅደውና እግዚአብሄር የሚፈቅደው በፊታችን እንደምርጫ ሲቀርብልን እናገኛለን፡፡፡ እኛ በህይወታችን እንዲሆን የምንወደው ነገር እግዚአብሄር የማይወደው ነገር ይሆንና እጅግ እንጨነቃለን፡፡ ወይም እኛ የማንወደው ነገርን እግዚአብሄር ይህንን እወዳለሁ ሲለን የእግዚአብሄርን ወይም የእኛን ለመምረጥ በውሳኔ መካከል ራሳችንን እናገኛለን፡፡

የራሳችንን ፈቃድ መከተል ለጊዜው ደስ ይል ይሆናል እንጂ ዘለቄታዊነት የለውም፡፡ የራሳችንን ፍላጎት መከተል እኛን ከእግዚአብሄር ፈቃድ በረከቶች ውጭ ያደርገናል፡፡ የራሳችን ፈቃድ መከተል በምድር ላይ ያለንን አንድ የህይወት እድል እንድናባክነው ያደርገናል፡፡  የራሳችንን ፍላጎት መከተል የእግዚአብሄር አብሮነት ያሳጣናል፡፡ የራሳችን ፍላጎት መከተል ክስረት ያመጣብናል፡፡ የራሳችንን ፍላጎት መከተል በእግዚአብሄር ፊት ያለንን ድፍረት ያሳጣናል፡፡

የእኛ ምርጫ ችግር አለበት፡፡ የእኛ ምርጫ ሁሉን የማያውቅ ሰው ምርጫ ነው፡፡ የእኛ ምርጫ እውቀት የጎደለው ሰው ምርጫ ነው፡፡ የእኛ መርጫ እንከን አያጣውም፡፡ በአለም ላይ የእጅግ ጥበበኛው ሰው ምርጫ ፍፁም አይደለም ጉድለት አለበት፡፡

የእግዚአብሄር ምርጫ ሁሉ የሚችል አምላክ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ የቅዱስ አምላክ ምርጫ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ የፍቅር አምላክ ምርጫ ነው፡፡

ስለዚህ ነው በራሳችን ፈቃድና በእግዚአብሄር ፈቃድ መካካል የምንጨነቀው፡፡ የእኛ ምርጫ ምን ያህን እንከን እንዳበት ስለምናውቅ በራሳችን መንገድ ላመሄድ ከራሳችን ጋር እንከራከራለን፡፡ በራሳችን ማስተዋል መደገፍ ስለማንፈልግ ነው ሁልጊዜ የእግዚአብሄርን ምርጫ መከተል የምንፈልገው፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ምሳሌ 3፡5

የእግዚአብሄር ምርጫ የተሳሳተና የማይመስል ብዙዎች የማይደግፉት ቢሆን እንኳን የእርሱ ምርጫ ከየትኛውም መርጫችን የተሻለ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ምርጫ ሞኝነት ቢመስል እንኳን የእግዚአብሄር ሞኝነት ከሰው ጥበብ ይጠበባል፡፡

ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡25

ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ሉቃስ 22፡42

ፀሎት

እግዚአብሄር ሆይ ስለተናገርከኝ ስለዚህ ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በሁለንተናዬ ለአንተ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ የአንተን ፈቃድ ብቻ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ፈቃድህን ስለምትገልጥልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ፈቃድህን እንድከተል ሃይል ስለምትሆነኝ ፀጋህን ስለምታበዛልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተን በሁለንተናዬ እስከመጨረሻው ተከትዬህ ስለማልፍ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለ ሁሉም ተመስገን ፡፡ በኢየሱስ ስም ፡፡ አሜን

ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት

church leader.jpgእነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። ማቴዎስ 18፡17

የእግዚአብሄር ቃል ከጊዜ ጋር አይለወጥም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንደዘመኑ አይለዋወጠም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በዘመናት የፀና ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል አያረጅም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል አያልፍም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፉ ይቀላል፡፡

የእግዚአብሄር ቃል ስለቤተክርስያን የሚለውን ማወቅ ከብዙ ስህተት ያድናል፡፡

ሰውን ክርስትያን አይደለህም እስከማለት ትልቅ ስልጣን ያላት ቤተክርስትያን ብቻ ነች፡፡ ቤተክርስትያን በምድር ላይ የእግዚአብሄርን መንግስት የምትወክል እንደ መሆንዋ መጠን በመሪዎችዋ አማካኝነት የምታስተላልፈው ውሳኔ የፀና ነው፡፡

ቤተክርስትያን በምድር የእግዚአብሄር መንግስት ተወካይ ነች፡፡ ቤተክርስታን የምትኖረው በክርስቶ ኢየሱስ ሙሉ ክብር ነው፡፡ ቤተክርስትያን ያላት ስልጣን ራስዋ ኢየሱስ ያው ስልጣን ነው፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ ስልጣኑን የሚለማመደው በቤተክርስትያን በኩል ነው፡፡

ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። ኤፌሶን ሰዎች 1፡22-23

ቤተክርስትያን በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፡፡ ቤተክርስትያን በምድር የምትፈታው በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል። ማቴዎስ 18፡18

ቤተክርስትያን ጉባኤ ወይም በተወካይ መሪዎችዋ በኩል የምትወስነውን ውሳኔ እግዚአብሄር ይፈፅመዋል፡፡

እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡3-5

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #መሪ #ሽማግሌ #ሰይጣን #ፍርድ #ውሳኔ #በምድርየምታስሩት #በሰማይየታሰረ #በምድርምየምትፈቱት #በሰማይየተፈታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት

ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ

rebuke.jpgየጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ምሳሌ 1፡7

ነፍስ ያለእውቀት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፡፡ ጥበብና እውቀት ከሚገኝበት መንገድ አንዱ ተግሳፅ ነው፡፡ ተግሳፅ የሰው ሃብት ነው፡፡ ተግሳፅን የሚሰማ ሰው ደግሞ ተግሳፅ ከክፉ ይጠብቀዋል፡፡

ተግሳፅን የማይሰማ ሰው ግን ያንኑ ስንፍና ሲደግመው ሳያድግና ሳይለወጥ እንደተፀፀተ ይኖራል፡፡ ሰነፍ ሰው በተግሳፅ ለመታረም ከመትጋተ ይልቅ ስንፍናው በህይወት ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍል ያደርገዋል፡፡

እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም። ምሳሌ 23፡23

ሰው ስለዘለፋ እና ተግሳፅ ጥቅም እውቀት ከሌለው ዘለፋንና ተግሳፅን ይንቃል፡፡ ዘለፋና ተግሳፅ ያላቸውን ዋጋ የተረዳ ሰው ያከብራቸዋል፡፡ የተግሳፅን አስፈላጊነት የተረዳ ሰው ለተግሳፅ ሙሉ ልቡን ይሰጣል፡፡ የዘለፋን ጥቅም ያወቀ ሰው የዘለፋን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ እስከሚጠቀምበት ድረስ ዘለፋን አያልፈውም፡፡

ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፤ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።ምሳሌ 4፡13

የዘለፋን ጥቅም የማያውቅ ሰው ግን የገሰፀው ሰው ጠላቱ ይመስለዋል፡፡ የተግሳፅን አስፈላጊነት ያልተረዳ ሰው ግን የሚገስፀው ሰው ያለአግባብ የሚጠቀምበት ይመስለዋል፡፡

በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ። ማቴዎስ 7፡6

ሰው ከተግሳፅ ምን እጠቀማለሁ ማለቱ ግን ወሳኝ ነው፡፡ ተግሳፅ ራሳችንን እንድናይ ያደርገናል፡፡ ተግሳፅ እኔ ሃላፊነት የመወስደው ስለየቱ ጥፋት ነው ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ተግሳፅ ራሳችንን እንድናነፃ እድልን ይሰጠናል፡፡ ተግሳፅ ትክክል ብንሆን እንኳን ትክክል መሆናችንን ያፀናልናል፡፡

ብልህ ሰው ህይወት ከሚገስፀው ሰው ቢገስፀው ይሻለዋል፡፡ ብልህ ሰው ውድቀት ከሚያዋርደው ዘለፋ ቢያዋርደው ይቀለዋል፡፡ ጠቢብ ሰው መከራ ከሚመክረው ሰው ቢመክረው ይሻለዋል፡፡

ዘለፋን የሚጠላ ገንዘቡ የማያደርግ ሰው ዘለፋን የሚንቅ ቸልተኛ ሰው በፍፃሜው እንዴት እንደሚፀፀት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ አትናገሩኝ የሚል ሰው በትእቢቱ ይፀፀታል፡፡

በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥ ትላለህም፦ እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ! የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም። ምሳሌ 5፡11-13

ዘለፋን የሚታገስ ፡ በተግሳፅ ራሱን የሚያይ በተግሳፅ ተጠቅሞ ራሱን የሚያሻሻል ሰው እየለመለመ ፣ እያበበና እያፈራ ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #ተግሳፅ #ዘለፋ #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ሙሉ ቀን እስኪሆንም እየተጨመረ ይበራል

THE WAY OF THE RIGHEOUS.jpgየጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4:18

በጌታ ኢየሱስ አምኖ ጌታን የሚከተል ሰው ሁሉ ተስፋው ብሩህ ነው፡፡ ጌታን የሚከተል ሰው ሁሉ እየተነሳ ያለ ኮከብ ነው፡፡ ጌታን ለመከተል የወሰነ ሰው ሁሉ መጨረሻው የሚያምር ነው፡፡

እርግጥ ነው ክርስትያን በብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ያልፋል፡፡ በነገሮች ወስጥ ሁሉ ግን ክርስትያን እያደገ ፣ እያሸነፈና እየለመለመ ይሄዳል፡፡

ክርስትያን የሚያልፍባቸውን አስቸጋሪ ነገሮችን ልዩ የሚያደርጋቸው እግዚአብሄር አብሮት ስላለ ነው፡፡ አስቸጋሪውን ነገር እግዚአብሄር አብሮት ይጋፈጠዋል፡፡ እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያልፈው ጥበብን ይሰጠዋል፡፡

ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ያዕቆብ 1፡5

ጌታን የሚከተል ሰው በራሱ ሲደክም እግዚአብሄር ያስችለዋል፡፡ እግዚአብሄር በድካሙ እየገባ በፀጋው ሃይል ያስችለዋል፡፡

እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9

በክርስቶስ የመስቀል ስራ የፀደቀ ሰው መንገዱ እንደንጋት ብርሀን ነው፡፡ የንጋት ብርሃን ከትንሽ ወገግታ ብርሃን አንስቶ እየደመቀ እየደመቀ እንደሚሄድ ሁሉ የክርስትያን መንገስ እንደዚያው ነው፡፡

የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20

የክርስትያን ሙሉ የህይወት ለውጥ ድንገተኛ አይደለም፡፡ የክርስትያን መንገድ የሚሄደው ቀስ በቀስ  እየጨመረ ይበልጥ እየበራ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አስተዳደግ በፍጥነት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር አስተዳደግ በሂደት ነው፡፡

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11

ጌታን የሚከተል ሰው ፍፃሜው ያማረ ነው፡፡

የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። ምሳሌ 4:18

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጻድቃን #የታመነ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #እየተጨመረ #በረከት #ትግስት #መሪ

ኤልሻዳይ ነኝ

800px-Ethiopian_highlands_01_mod.jpgአብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ዘፍጥረት 17፡1

ብዙ ጊዜ ሰዎችን የሚያስጨንቃቸው የማያስጨንቅ ነገር ነው፡፡ መንፈሳዊ ነገር የእግዚአብሄርና የሰው ስራ ውጤት ነው፡፡ ሰው የማይሰራው የእግዚአብሄር ስራ አለ፡፡ እግዚአብሄር የማይሰራው የሰው ደግሞ ስራ አለ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የራሳቸው ድርሻ ላይ አያተኩሩም፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ድርሻ ትተው የእግዚአብሄር ድርሻ ላይ ሲያተኩሩ ይጨነቃሉ በክርስትና ህይወታቸው መደሰት ያቅታቸዋል፡፡

ሰዎች በህይወት ያላቸውን ሃላፊነት ሳይረዱ ሲቀሩ በእግዚአብሄር ስራ ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ስራ ሰርተው ካላረፉ የእግዚአብሄርን ድርሻ ለመስራት ሲሞክሩ ህይወታችውን ያባክናሉ፡፡

እግዚአብሄር ለአብርሃም ልጅን እሰጥሃለሁ ብሎታል፡፡ እግዚአብሄር ካለ ሆነም ነው፡፡ አብርሃም ማድረግ ያለበት በእምነት ተቀብሎ መኖር ብቻ ነው፡፡ አብርሃም ማድረግ ያለበት እግዚአብሄር ከእርሱ የሚፈልገውን ነገር በትጋት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከአብርሃም የሚፈልገው ነገር አብርሃም እግዚአብሄርን እንዲከተል ብቻ ነው፡፡

አብርሃም እግዚአብሄር የሰጠውን የራሱን ሃላፊነት ትቶ ግን እግዚአብሄር ቃሉን እንዴት ሊፈጽመው ነው እያለ ቢጨቅ የሚያመጣው ነገር የለም፡፡ አብርሃም እግዚአብሄር እንዴት ቃሉን እንደሚያደርገው ቢያወጣና ቢያወርድ ለራሱ የተሰጠውን ሃላፊነት መወጣት ያቅተዋል፡፡

በአዲስ ኪዳንን ኢየሱስ ያለው ይህንኑ ነው፡፡ የሰው ድርሻ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ ሁል ጊዜ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሆኖ መገኘት ነው፡፡ የሰው ድርሻ ኢየሱስን ፈፅሞ መከተል ነው፡፡ የሰው ድርሻ የእግዚአብሄር መንግስትን ጥቅም መፈለግ ነው፡፡ የሰው ድርሻ ለእግዚአብሄርን መንግስት በጎነትና ማሸነፍ በትጋት መስራት ነው፡፡

የእግዚአብሄር ድርሻ ሰው ለኑሮ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለሰው ማሟላት ነው፡፡

እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33

ብዙ ሰው ማድረግ የሚፈልገው ግን የራሱን ድርሻ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ከመፈለግ ይልቅ እግዚአብሄር  ይጨመርላችኋል ያለውን ስለሚበላላና ስለሚጠጣ መጨነቅ ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲተላለፍ የሚያደርገው እግዚአብሄር አድርግ ያለውን የራሱን ድርሻ ትቶ ይህ የእኔ ድርሻ ነው አትሞክረው ያለውን የእግዚአብሄን ድርሻ ለማድረግ መሞከሩ ነው፡፡

እግዚአብሄር አብርሃምን ያለውም የአንተ ድርሻ በፊቴ መመላለስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው ተከተለኝ ስማኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያለው ህይወትህን ጠብቅ ንፅህናህን ጠብቅ ቅድስናህን ጠብቅ ነው፡፡

ከዚያ ውጭ ምንም የሚያሳስብህ ነገር የለም፡፡ ነገርህ በእኔ እጅ ነው፡፡ ሌላው የእኔ ሃላፊነት ነው፡፡ ቃሌን መፈፀም የእኔ ስራ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ሁሉ እችላለሁ፡፡ እኔ የማደርገው አያሳስብህ፡፡ ለማድረግ ብቃቱ አለኝ እያለው ነው፡፡

አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤ ዘፍጥረት 17፡1

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍፁም #ተመላለስ #ኤልሻዳይ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

የናቁኝም ይናቃሉ

pride.jpgአሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

እግዚአብሄር መናቅ በፅንሰ ሃሳብ ደረጀ ብቻ ያለ በተግባር ግን የሌለ ነገር አይደለም፡፡ በየእለት ተእለት ኑሮዋቸው እግዚአብሄርንእግዚአብሄርን የሚንቁ፡ በአስተሳሰባቸው ለእግዚአብሄር ክብር የሌላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በአነጋገራቸው እግዚአብሄርን የማይፈሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በአደራረጋቸው እግዚአብሄርን የማያከብሩ ሰዎች አሉ፡፡

ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርህ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

ከእግዚአብሄር ይልቅ ታዋቂነታቸውን የሚያከብሩ ሰዎች እግዚአብሄርን ደስ አያሰኙትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ፍላጎታቸውን የሚያስቀድሙትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብሩትም፡፡ ከእግዚአብሄር ይልቅ ገንዘብን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አይደሰትባቸውም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ስለኑሮ የሚጨነቁት ሰዎች እግዚአብሄርን አያስከብሩትም፡፡

ከእግዚአብሄር በላይ ማጣትን የሚያከብሩትን ሰዎች እግዚአብሄር አያከብርም፡፡

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡12

ከእግዚአብሄር በላይ የሰዎችን ፍላጎት የሚያርጉትን እግዚአብሄር አያከብርም፡፡ ከእግዚአብሄር በላይ ሰውንም ደስ ለማሰኘት የሚኖሩት እግዚአብሄርን አያከብሩትም፡፡

ወደ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ገላትያ 1፡10

የናቁትን ማክበር ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡ ያከበሩትን መናቅ ለእግዚአብሄር አይሆንለትም፡፡

የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። መዝሙር 51፡17

ያከበሩትን ያከብራል የናቁት ይናቃሉ፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2

አዳም እግዚአብሄርን ባላከበረ እና ባልታዘዘ ጊዜ ምድር እንኳን ለገመች እንደ ሃይሉዋ መጠንም መስጠት አቆመች፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ማክበር ሲያቆም እና ሲንቅ በተፈጥሮ ሁሉ ይናቃል፡፡

ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ። ዘፍጥረት 4፡12

አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። 1ኛ ሳሙኤል 2፡30

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የናቁኝም #ይናቃሉ #መልስ #ቁጣ #ፍርሃት #ናፍቆት #ቅንዓት #በቀል #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

እግዚአብሄር ከሐዘናችን ምን ይጠቀማል

58926.jpgእነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል በመካከላችሁ አደረገ። በዚህ ነገር ንጹሐን እንደ ሆናችሁ በሁሉ አስረድታችኋል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡11

ሃዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ በላከው በመጀመሪያው መልእክቱ በቤተክርስትያን ውስጥ የነበረውን የቅድስና ማጣት አስረድቶ ገስጿቸው ነበር፡፡ የቆሮንጦስ ሰዎችም በተከሰሱበት ሃጢያት አዝነው ነበር፡፡

ሃዘናቸውን የተመለከተው ሃዋሪያው ሁለተኛውን መልእክት ሲፅፍላቸው በመጀመሪያው መልእክቱ በማዘናቸው ደስ እንዳለው ደስ ያለው በሃዘናቸው ሳይሆን ሃዘናቸው ባመጣው ውጤት እንደሆነ ይናገራል፡፡

በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤ በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡8-9

በሁለተኛው መልዕክቱ ግን ሃዘናቸው ያመጣውን ውጤት እየዘረዘረ ሃዘናቸው ፍሬያማ እንደነበረ ይፅፍላቸዋል፡፡

እግዚአብሄር በሰው ውደቀት አይጠቀምም፡፡ እግዚአብሄር በሰው ማዘን ብቻ አይከብርም፡፡ እግዚአብሄር በሰው መዋረድ አይጠቀምም፡፡

እግዚአብሄር የሚጠቀመው ሃዘኑ በሚያመጣው ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚከብረው በመዋረዳችን በሚበዛልን ፀጋ ነው፡፡

በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ። ሮሜ 5፡20-21

እግዚአብሄር የሚጠቀመው ውድቀታችን በሚያስተምረን ወሳኝ የትህትና ትምህርት ነው፡፡

እግዚአብሄር በእኛ ሃዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ካገኘ ስኬታማ ነው፡፡

እግዚአብሄ በእኛ መዋረድ እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ካመጣለት ደስተኛ ነው፡፡

እግዚአብሄር በእኛ ውድቀት እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ከተገኘ እግዚአብሄር ይከብራል፡፡

የቆሮንጦስ ሰዎች ከውድቀታቸው በፊት ከነበራቸው ትጋት ፥ መልስ ፥ ቁጣ ፥ ፍርሃት ፥ ናፍቆት ፥ ቅንዓት ፥ በቀል በላይ ከወደቁ በኋላ የነበራቸው ትጋት ፥ መልስ ፥ ቁጣ ፥ ፍርሃት ፥ ናፍቆት ፥ ቅንዓት ፥ በቀል ጨምሮዋል፡፡

የቆሮንጦስ ሰዎች ለእግዚአብሄር ስራ እጅግ የሚበልጥ ትጋትን አሳይተዋል ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ለመታዘዝ ያላቸው መልስ ይበልጥ ፈጣን ሆኖዋል ፣ በሰይጣንና በክፋት ላይ ያላቸው ቁጣ ጨምሮዋል ፥ እግዚአብሄርን ይበልጥ ፈርተዋል እግዚአብሄርን የመፍራት መንፈስ ጨምሮላቸዋል ፣ ለእግዚአብሄር ነገር ያላቸው መጠበቅ እጅግ ጨምሯል ፣ ፅድቅን መራባቸውና መጠማታቸው ጨምሮዋል ፣ ለእግዚአብሄር ስራ በቅንዓት ተነስተዋል ፥ የክፋትን ስራ ለመበቀል ይበልጥ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡

እግዚአብሄር የሚከብረው ከሃዘናቸው ሳይሆን ሃዘናቸው ካመጣው የመንፈስ መነቃቃት ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የሚያዝኑ #ትጋት #መልስ #ቁጣ #ፍርሃት #ናፍቆት #ቅንዓት #በቀል #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ

tahoepurewater-slide-2.jpgበውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።  ሕዝቅኤል 28፡17

ሰይጣን እግዚአብሄር ላይ በማመፅ ከመውደቁ በፊት በእግዚአብሄር ጥበብ ነበር የሚኖረው፡፡ ሰይጣን ከክብሩ ሲወድቅ ግን የሰይጣን ጥበብ ረከሰ፡፡

ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚታለሉት ጥበበኛ የሆኑ እየመሰላቸው ነው፡፡ ጥበበሦች የሆኑ ሲመስላቸው የማያስተውሉ ይሆናሉ፡፡

ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ ሮሜ 1፡22

ሰዎች ጥበብ አለን ይላሉ ነገር ግን ያላቸው ጥበብ ምን አይነት ጥበብ እንደሆነ አያስተውሉም፡፡ ሰዎች በጥበብ እየኖሩ ይመስላቸዋል ነገር ግን ያላቸውን የጥበብ አይነት ለይተው አያውቁትም፡፡

ሰዎች በአግዚአብሄር ጥበብ እየኖሩ እየመሰላቸው በሰይጣን ጥበብ ይኖራሉ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ጥበብ ሁሉ እውነተኛ ጥበብ እንዳይደለ ያስተምራል፡፡ ጥበብ ሁሉ ንፁህ ጥበብ እንዳይደለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ ንፁህ ጥበብ እንዳለ ሁሉ የረከሰ ጥብብ እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ በግልፅ ያስተምረናል፡፡

ሰይጣን ጥበብ አለው፡፡ ነገር ግን የሰይጣን ጥበብና የእግዚአብሄር ጥበብ አንድ አይደሉም፡፡ የሰይጣን ጥበብ የረከሰ ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥብብ ቅዱስ ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የየዋህነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የተንኮል ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የይቅርታ ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የመራርነት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የፍቅር ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የቅንአት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የአንደነት ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የአድመኝነትና የመከፋፈል ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ የሰላም ጥበብ ነው፡፡ የሰይጣን ጥበብ የጥል ጥበብ ነው፡፡

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡13-17

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #መራራ #ቅንዓትና #አድመኛነት #ንጽሕት #በኋላም #ታራቂ #ገር #እሺባይ #ጥርጥር #ግብዝነት  ##አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

በእንጀራ ብቻ አይኖርም

1_Nk_BLgJCCRa3GL9WE5i0cA.jpegፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስ 4፡3-4

ፈታኙ ሰይጣን ኢየሱስን የፈተነው ኢየሱስ በምድራዊ ነገር ላይ ብቻ በማተኮር ሰው የሚኖርበትን የእግዚአብሄርን ቃል እንዲረሳ ነው፡፡

የሰይጣን አላማ አይናችንን ከመንፈሳዊው ነገር ላይ አንስተን በስጋዊው ነገር ላይ ብቻ እንድናተኩር ማድረግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በምድራዊ ነገር ሁሉ ባተሌ ሆነን መንፈሳዊ ነገርን በመርሳት ህይወታችንን ማባከን ነው፡፡ የሰይጣን አላማ አይናችንን ቁሳቁስ ላይ በማድረግ ከተጠራንበት ከፍ ካለው መንፈሳዊ አላማ ማስተጓጎል ነው፡፡

የሰይጣን አላማው ለስጋችን የሚያስፈልገው ነገር ላይ ብቻ አተኩረን መንፈሳዊውን ምግብ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳናስታውስ በዚያም ፍሬ ቢስ እንድንሆን ነው፡፡ የሰይጣን አላማ ለስጋችን የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እያደረግን ለመንፈሳችን የሚሆነውን ነገር እንዳናደርግ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ እየኖረን በመንፈስ እንድንሞት ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ ሰብተን በመንፈስ አንድንጫጭ ነው፡፡ የሰይጣን አላማ በስጋ እየኖርን መንፈሳችንን በህይወት የሚያኖረውን በእግዚአብሄር ቃል እንዳንኖር ነው፡፡

ሰይጣን የሚፈልገው በስጋ ነገር ባተሌ ሆነን በመንፈስ ነገር እንድንከስር ነው፡፡ ሰይጣን የሚፈትነው ስለሚበላና ስለሚጠጣ እየተጨነቅን የእግዚአብሄርን መንግስት ፅድቁንም እንዳንፈልግ ነው፡፡

እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 4፡31-33

ሰይጣን የሚፈልገው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት የእግዚአብሄር ቃል የሚገባውን ስፍራ በህይወታችን እንዳይኖረውና ሙሉ ፍሬ አንዳያፈራ ማድረግ ነው፡፡

በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። ሉቃስ 8፡14

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ስኬት #ክንውን #ቃል #መንፈስ #ስጋ #እንጀራ #የእግዚአብሔርቃል ##ማሰላሰል #አእምሮ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

%d bloggers like this: