በህይወታችን ዘመን መለወጡን የምናውቅባቸው አምስት መንገዶች

4 season.jpg

ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ መጽሐፈ መክብብ 3፡1-8፣11

እግዚአብሄር ነገሮችን የሚሰራው በዘመን ውስጥ ነው፡፡ እያንዳንዳችን የተወሰነልን የምናልፈበት ዘመንና ጊዜ አለ፡፡ አንድ ዘመን ተፈጽሞ ሌላው ሲጀመር ማወቅ ራሳችንን ከሚመጣው ዘመን ጋር አስተካክለን እንድናሰለፍና እንድናስተካከል ያዘጋጀናል፡፡ አንዱ የህይወት ምእራፋችን መዘጋቱና የተወሰነው ዘመን እንዳለቀ ማወቅ ባለፈው ዘመን ላይ እንዳንቆይ እና ባለቀና በተለወጠ ዘመን ላይ ጉልበታችንን እንዳናባክን ይረዳናል፡፡ አዲስ የህይወት ምእራፍ መከፈቱን ማወቅ ከአዲሱ የህይወት ምእራፍ ጋር ራሳችንን በትክክል አስተካክለን እንድናሰልፍ ያስችለናል፡፡

ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ የማቴዎስ ወንጌል 24፡32

በህይወታችን ዘመን ሲለወጥ እግዚአብሄር በቀንና በሰአት ባይመራንም ዘመን መለወጡን የምናውቅባቸውን መንገዶች እንመልከት

  1. በጣም ለምንወደው እና አድርገን ለማንጠግበው ነገር ፍላጎት ስናጣ
  2. ህይወታችን በተለየ ሁኔታ ለሌላ ነገር ሲጠማና ሲራብ
  3. ለነበረን የህይወት ሃላፊነት ሸክም እና ትእግስት ስናጣ
  4. አሁን በምናደርገው ላይ ልባችን ሳይኖር ሲቀር ልባችን ከነገሩ ላይ ሲነሳ
  5. የምናደርገው ነገር ከባድ ተራራ መግፋት ሲሆን

እነዚህና እንዚህን የመሳሰሉ ምልክቶች በህይወታችን ካየን በህይወታችን ዘመን እየተለወጠ መሆኑን አመላካቾች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የመንፈስ የውስጥ ምስክርነት እና ምሪት ማረጋገጫ የሆኑትን እነዚህን ምልክቶች ካየን ለሚቀጥለው የህይወት ምእራፋችን መዘጋጀት ግድ ይላል፡፡

ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ። አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ። በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡10-13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጊዜ #ዘመን #ውብ #ፀጋ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መጐብኘትሽ #አላወቅሽም #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #ወንጌል #ዛሬ #ነገ #ትላንት #መሪ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on October 12, 2018, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Comments Off on በህይወታችን ዘመን መለወጡን የምናውቅባቸው አምስት መንገዶች.

Comments are closed.

%d bloggers like this: