የመታዘዝ ስልጣን

5930198_orig.jpg

ሰው የተፈጠረው እንዲገዛ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን ወክሎ ምድርን እንዲያስተዳደር ነው፡፡

ሰው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠረው ከሙሉ ስልጣን ጋር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በስልጣን ነው፡፡

ሰው እግዚአብሄርን መታዘዝ ሲያቆም ስልጣኑን አጣው፡፡ ሰው እግዚአብሄር ላይ ሲያምፅ ክብሩን አጣው፡፡ ሰው እግዚአብሄር ላይ ሲያምፅ ንግስናውን አጣው፡፡  ለእግዚአብሄር የማዘዝ ስልጣን እምቢ ሲል ሰው የራሱን ስልጣኑን አጣው፡፡ ሰው በአመፅ ስልጣኑን አሳልፎ ሰጠ፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ሲታዝዝ የሚታዘዙለት ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ሲያምፅ አመፁበት፡፡ ሰው ሲያምፅ እግዚአብሄን ሲታዝዝ የነበረውን ስልጣን አጣው፡፡

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡27-28

መታዝዝ ያነግሳል፡፡ መታዘዝ ያከብራል፡፡ መታዘዝ ስልጣንን ይሰጣል፡፡

ማመፅ ስልጣንን ይሽራል፡፡ አለመታዘዝ ያዋርዳል፡፡ አለመታዘዝ ያስንቃል፡፡

ለእግዚአብሄር ስርአት መታዘዝ ክብር እንጂ ውርደት አይደለም፡፡ ለእግዚአብሄር ስልጣን መታዝዝ ሃይል እንጂ ድካም እይደለም፡፡ እግዚአብሄር ላስቀመጣቸው ባለስልጣናት መታዘዝ ድል እንጂ ሽንፈት አይደለም፡፡

ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡1-2

ሰው ስልጣኑን የሚያገኘው በትህትና ነው፡፡ ሰው ሃይሉን የሚያገኘው በመታዝዝ ነው፡፡

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መታዝዝ #ስልጣን #ትህትና #ክብር #ውርደት #አመፅ #ሃይል #ተገዙ #ተቃወሙት #አለመታዘዝ #ታማኝ #ትጉህ #መክሊት #ትውልድ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ሃሳብ #ገንዘብ #ጊዜ #ትግስት #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on September 26, 2018, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Comments Off on የመታዘዝ ስልጣን.

Comments are closed.

%d bloggers like this: