የሰው ችግር የእግዚአብሔር ችግር ነው

$_57.png

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ተፈልጎና ታቅዶ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በድንገት አይደለም፡፡ ሰው ሲፈጠር የሚያስፈልገው ሁሉ ከተሟላ በኋላ ነው፡፡ ሰው ፍፁም ተደርጎ ነው የተፈጠረው፡፡ ሰው ሲፈጠር ምንም አይነት ችግር አልነበረበትም፡፡

ሰው እግዚአብሄር አትብላ ያለውን በበላ ጊዜ ችግር ተፈጠረ፡፡ ሰው እግዚአብሄር ላይ ባመፀ ጊዜ ሃጢያት ወደ አለም ገባ፡፡ የሰው ችግር የጀመረው በሰውና በእግዚአብሄር መካከል ነው፡፡ የሰው ችግር የጀመረው ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ባለው ግንኙነት ነው፡፡

ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ችግር ሲፈጠር ሰው ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ችግር ውስጥ ወደቀ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ችግር ሲፈጠር ሰው ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ችግር ውስጥ ወደቀ፡፡

ሰው እግዚአብሄርን ባለመታዘዙና እግዚአብሄር ላይ በማመፁ የተፈጠረበትን አላማ ስቷል፡፡ የሰው ችግር ሁሉ የመነጨው ከእግዚአብሄር ጋር በፈጠረው ችግር ነው፡፡ የሰው ችግር ሁሉ የእግዚአብሄር ችግር ነው የሚባለው ስለዚህ ነው፡፡

የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡20-21

አሁንም የሰው ችግር መፍትሄው እግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው ከራሱ ጋር ፣ ሰው ከሰው ጋር ፣ ሰው ከተለያዩ ነገሮች ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ከእግዚአብሄር ውጭ ሌላ ቦታ መሄድ የለበትም፡፡ ሰው መጀመሪያ ለችግሮቹ ሁሉ ምንጭ የሆነውን ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ችግር ካልተፈታ ችግሮቹን በዘላቂነት መፍታት አይችልም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ችግር ከተፈታ ደግሞ የማይፈታ ምንም ችግር አይኖርም፡፡

ሰው እንደተፈጠረበት አላማ ከእግዚአብሄር ጋር በትህትና መሄድ ሲጀምር ከሰዎች ጋር እና ከራሱ ጋር በትህትና መኖር ይጀምራል፡፡

ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? ትንቢተ ሚክያስ 6፡8

ሰው ከጥንት እንተፈጠረበት አላማ እግዚአብሄርን እየፈራ ከኖረ ከሌላ ከሁሉም ነገር ጋር ያለው ግንኙነት ይሰምራል፡፡

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡13-14

ሰው የተፈጠረበትን ለእግዚአብሄር እንደእግዚአብሄርነቱ መጠን ክብርን የመስጠት አላማ ከፈፀመ ሌሎች ግንኙነቶቹ ሁሉ የተሳኩ ይሆናሉ፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #እግዚአብሔርንመፍራት #ጥበብ #ክፉ #መልካም #ፍርድ #እውቅና #ፍፁም #ችግር #መፍትሄ #አላማ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on July 19, 2018, in SIN. Bookmark the permalink. Comments Off on የሰው ችግር የእግዚአብሔር ችግር ነው.

Comments are closed.

%d bloggers like this: