እንደ እንጀራ ይሆኑልናል

seen by men.jpg

ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት። እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። ኦሪት ዘኍልቍ 14፡7-9

የእስራኤል ህዝብ ወደከንአን ሊገቡ ሲሉ ኢያሱ ምድሪቱን እንዲሰልሉ 12 ሰላዮችን ላከ፡፡ ከኢያሱና ከካሌብ በስተቀር ሁሉም ሰላዮች ስለምድሪቱ ክፉን ነገር ለእስራኤል ህዝብ አወሩ፡፡

ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። ኦሪት ዘኍልቍ 14፡32

እነዚያ ሰላዮች እንዲያውም እኛ በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣ ነን ብለው ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ አደረጉ፡፡

በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን፤ እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ። ኦሪት ዘኍልቍ 14፡33

እነዚህ አስሩ ሰላዮች ራሳቸውን እንጂ አብሮዋቸው የሚወጣውን የሰራዊት ጌታ ማየት አልቻሉ፡፡ ሊዋጉ የፈለጉት እንደዳዊት በእግዚአብሄር ስም ሳይሆን በራሳቸው ስም ነው፡፡

ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17፡45

ዳዊት ሁልጊዜ የሚያስበው ጦርነቱን በየእለቱ የሚዋጋለት እግዚአብሄር ነው፡፡

አንድ ጊዜም እንዲህ ሆነ፡፡ በመጽሃፍ ቅዱስ የኤልሳ ባሪያ አንድ ጊዜ የጠላትን ሰራዊት ብዛት ተመልክቶ ልቡ ተሸበረ፡፡

የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡15

ሲሸበር ኤልሳም እግዚአብሄር የብላቴናውን አይን እንዲከፍት ፀለየ፡፡

ኤልሳዕም፦ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡17

እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፡16

አስሩ ሰላዮች ስለምድሪቱ ክፉ ወሬን አስወሩ፡፡ አስሩ ሰላዮች የጠላታቸውነ በዛት እነጂ የእግዚአብሄርን ትልቅነት አላስተዋሉም፡፡ አስሩ ሰላዮች የጠላታቸውን ሃያልነት እንጂ የእግዚአብሄርን ሃያልነት ረሱ፡፡

ሁለቱ ሰላዮች ግን የጠላታቸውን ብዛት ሳይክዱ የእግዚአብሄርን ታላቅነት ተመለከቱ፡፡

ስለዚህ እንዳውም ጠላት ሲበዛ ድል ይበዛል፡፡ እንደ እንጀራ ይሆኑልናል በማለት እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ስላለ ምንም እንደማያቅታቸውና እነርሱን ማሸነፍ ለእግዚአብሄር ቀላል እንደሆነ ተናገሩ፡፡

ጠላት ሲገዝፍ ድላችን ይገዝፋል፡፡

ጨለማው በጨለመ መጠን ብርሃናችን ይደምቃል፡፡

ጠላት ሲተልቅ እንጀራው ይተልቃል፡፡

የጠላታችን ግዙፍነት የድላችንን መጠን ያገዝፈዋል፡፡

እኛ የምናሸንፈው ተሸናፊዎችን አይደለም፡፡ እኛ የምናሸንፈው አሸናፊዎችን ነው፡፡ እኛ የምናሸንፈው ብዙዎችን ያሸነፉትን ነው፡፡ እኛ የምናሸንፈው ብዙዎችን ያንበረከኩትን ነው፡፡ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመሆን አሸናፊውን ማሸነፍ ግዴታ ነው፡፡

በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡37

ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። ኦሪት ዘኍልቍ 14፡7-9

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ራዕይ #ምሪት #ድል #አሸናፊ #የእግዚአብሄርአላማ #የእግዚአብሄርምክር #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተግዳሮት #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አይን #እይታ #አጥርቶ #ራእይ #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on July 13, 2018, in warfare. Bookmark the permalink. Comments Off on እንደ እንጀራ ይሆኑልናል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: