የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል

The-Walk-to-the-cross-1600x768.jpgየሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው። የማርቆስ ወንጌል 14፡21

የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል፥ ነገር ግን አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት። የሉቃስ ወንጌል 22፡22

እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ሰው በምድር ላይ የሚያደርግለት ነገር የተወሰነ ነገር ነበር፡፡ እግዚአብሄር መጀመሪያ ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ሰው በምድር ላይ ለምን አላማ እንደሚፈጠር ያውቅ ነበር፡፡ ሰው በምድር ላይ የተፈጠረውም ያንን እግዚአብሄር በልቡ የነበረውን አላማ እንዲፈፅም ነበር፡፡

እያንዳንዳችን ደግሞ ወደ ምድር ከመፈጠራችን በፊት በምድር ላይ እንድንፈፅመው የተዘጋጀ መልካም ስራ ነበር፡፡ በምድር ላይ መወለዳችን የሚያሳየው ልንሰራ ያለነው ልዩ ስራ እንዳለ ነው፡፡ በምድር ላይ የምንሰራው ስራ ባይኖር ኖሮ በምድር ላይ ባልተወለድን ነበር፡፡

በምድር ላይ የተወለድንበትን ስራ ስንሰራ በብዙ ነገሮች ውስጥ እናልፋለን፡፡ በምን ውስጥ አልፈን የእግዚአብሄርን ስራ እንደምንሰራ አስቀድሞ በእግዚአብሄር ተወስኗል፡፡

በምድር ላይ የምናልፍበትን ነገር ሊያስጥል የሚችል ማንም ሰው የለም፡፡ በእግዚአብሄር ከተወሰነውና በእግዚአብሄ ልብ ካለው ውጭ የሚሆንብን ምንም ነገር የለም፡፡

ኢየሱስ ሊሰቀል በሚወሰድበት ጊዜ ስለእርሱ የሚያለቅሱ ሴቶችን ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፦ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ አላቸው።

ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት። ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፦ እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፦ መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ። የሉቃስ ወንጌል 23፡27-29

ኢየሱስ መሲህ ስለሆነና ሰዎች ሁሉ ሊቀበለኩት ስለተገባ ኢየሱስ የሚያልፍናቸው ነገሮች ሁሉ አስቀድመው በእግዚአብሄ ይታወቃሉ እንዲሁም በመፅሃፍ ቅዱስ ተፅፈውልናል፡፡ ኢየሱስ ስለሚያልፍባቸው መንገዶች ሁሉ እንደተፃፈ ሁሉ እያንዳንዳችን ስለምናልፍባቸው መንገዶች በእግዚአብሄር ዘንድ የታወቀ ነው፡፡

በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል። ዕብራውያን 10፡7

ኢየሱስ በምድር ላይ ስለእርሱ በመፅሃፍ ቅዱስ የተፃፈውን ሊያደርግ እንደመጣ ሁሉ እኛም በምድር ላይ ልንፈፅመው የተወሰነልንን ነገር ልናደርግ ነው ወደምድር የመጣነው፡፡

የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ማቴዎስ 26፡24

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #እንደተፃፈ #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 9, 2018, in Vision and Leading. Bookmark the permalink. Comments Off on የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: