እግዚአብሄር ከሐዘናችን ምን ይጠቀማል

58926.jpgእነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል በመካከላችሁ አደረገ። በዚህ ነገር ንጹሐን እንደ ሆናችሁ በሁሉ አስረድታችኋል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡11

ሃዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ በላከው በመጀመሪያው መልእክቱ በቤተክርስትያን ውስጥ የነበረውን የቅድስና ማጣት አስረድቶ ገስጿቸው ነበር፡፡ የቆሮንጦስ ሰዎችም በተከሰሱበት ሃጢያት አዝነው ነበር፡፡

ሃዘናቸውን የተመለከተው ሃዋሪያው ሁለተኛውን መልእክት ሲፅፍላቸው በመጀመሪያው መልእክቱ በማዘናቸው ደስ እንዳለው ደስ ያለው በሃዘናቸው ሳይሆን ሃዘናቸው ባመጣው ውጤት እንደሆነ ይናገራል፡፡

በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤ በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡8-9

በሁለተኛው መልዕክቱ ግን ሃዘናቸው ያመጣውን ውጤት እየዘረዘረ ሃዘናቸው ፍሬያማ እንደነበረ ይፅፍላቸዋል፡፡

እግዚአብሄር በሰው ውደቀት አይጠቀምም፡፡ እግዚአብሄር በሰው ማዘን ብቻ አይከብርም፡፡ እግዚአብሄር በሰው መዋረድ አይጠቀምም፡፡

እግዚአብሄር የሚጠቀመው ሃዘኑ በሚያመጣው ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚከብረው በመዋረዳችን በሚበዛልን ፀጋ ነው፡፡

በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ። ሮሜ 5፡20-21

እግዚአብሄር የሚጠቀመው ውድቀታችን በሚያስተምረን ወሳኝ የትህትና ትምህርት ነው፡፡

እግዚአብሄር በእኛ ሃዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ካገኘ ስኬታማ ነው፡፡

እግዚአብሄ በእኛ መዋረድ እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ካመጣለት ደስተኛ ነው፡፡

እግዚአብሄር በእኛ ውድቀት እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል ከተገኘ እግዚአብሄር ይከብራል፡፡

የቆሮንጦስ ሰዎች ከውድቀታቸው በፊት ከነበራቸው ትጋት ፥ መልስ ፥ ቁጣ ፥ ፍርሃት ፥ ናፍቆት ፥ ቅንዓት ፥ በቀል በላይ ከወደቁ በኋላ የነበራቸው ትጋት ፥ መልስ ፥ ቁጣ ፥ ፍርሃት ፥ ናፍቆት ፥ ቅንዓት ፥ በቀል ጨምሮዋል፡፡

የቆሮንጦስ ሰዎች ለእግዚአብሄር ስራ እጅግ የሚበልጥ ትጋትን አሳይተዋል ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ለመታዘዝ ያላቸው መልስ ይበልጥ ፈጣን ሆኖዋል ፣ በሰይጣንና በክፋት ላይ ያላቸው ቁጣ ጨምሮዋል ፥ እግዚአብሄርን ይበልጥ ፈርተዋል እግዚአብሄርን የመፍራት መንፈስ ጨምሮላቸዋል ፣ ለእግዚአብሄር ነገር ያላቸው መጠበቅ እጅግ ጨምሯል ፣ ፅድቅን መራባቸውና መጠማታቸው ጨምሮዋል ፣ ለእግዚአብሄር ስራ በቅንዓት ተነስተዋል ፥ የክፋትን ስራ ለመበቀል ይበልጥ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡

እግዚአብሄር የሚከብረው ከሃዘናቸው ሳይሆን ሃዘናቸው ካመጣው የመንፈስ መነቃቃት ነው፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የሚያዝኑ #ትጋት #መልስ #ቁጣ #ፍርሃት #ናፍቆት #ቅንዓት #በቀል #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on May 21, 2018, in Righeousness. Bookmark the permalink. Comments Off on እግዚአብሄር ከሐዘናችን ምን ይጠቀማል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: