እኔ ግን አልረሳሽም

14064233_1313270928691015_8507530893785444500_n.jpgጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። ኢሳይያስ 49፡14-15

እግዚአብሄር ስለራሱ አዛኝና ርሁርሁነት ሲናገር የእርሱን አዛኝነት ከእናት አዛኝነት ጋር ያመሳሰልዋል፡፡

እናት አዛኝ ርህሩህ ተንከባካቢ ይቅር ባይ መሃሪ ነች፡፡ እግዚአብሄር ታጋሽ ፣ ደግና ቸር ነው፡፡

እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። መዝሙር 149፡8-9

ሰው ደግሞ እግዚአብሄር ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲደገፍ ስለተፈጠረ የእግዚአብሄርን የቅርብ ክትትል ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡

እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ዕብራውያን 4፡13

እግዚአብሄር የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም አይታክትም ማስተዋሉም አይመረመርም፡፡

ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡27-28

እግዚአብሄር ስለእርሱ እናትነት ደረጃ ሲናገር ከምድር እናትነት እጅግ የላቀ መሆኑን ይናገራል፡፡ እናት የወለደችውን ልጅ ትረሳለችን እያለ ይጠይቃል፡፡ እናተ ብትረሳ እንኳን እርሱ ግን እንደሚራራልንና እንደማይረሳን ይነግረናል፡፡

ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። ኢሳይያስ 49፡14-15

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እግዚአብሔር #ሴት #እናትነት #ጌታ #መከተል #ፍቅር #ርህራሄ #ይቅርታ  #ቃል #ደግነት #ቸርነት #አልረሳሽም #እግዚአብሔርንመምሰል #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት  #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on May 12, 2018, in mother. Bookmark the permalink. Comments Off on እኔ ግን አልረሳሽም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: