መኖርን የረሳው ሽማግሌ ታሪክ

forget to live.jpgመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡

ከዚያ ደግሞ ኮሌጅን ለመጨረስ እና ሥራ ለመጀመር እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡

ከዚያም ለማግባት እና ልጆች ለመውለድ እስከሞት ድረስ እጓጓ  ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ ወደ ሥራዬ መመለስ እንድችል ልጆቼን ለትምህርት የሚያበቃ ዕድሜዬ እንኪደርሱ እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ ጡረታ ለመውጣት እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡

እና አሁን ለመሞት ተቃርቤያለሁ . . . .

በድንገት የተረዳሁት ነገር በህይወቴ ዘመን ሁሉ የሚቀጥለው ደረጃ ላይ ለመድረስ እጅግ ስጓጓ ነገር ግን መኖርን ረስቼ እንደነበር ነው፡፡

የምድር ህይወት አጭር ነው፡፡ ለስኬታማነት ጊዜ እንደምትሰጥ ሁሉ ስኬትህን ለማጣጣም ጊዜ ስጥ፡፡ ለመከናወን እንደምትጥር ሁሉ በክንውንህን ለመደሰት ጊዜ ውሰድ፡፡

አንዳንድ ሰው ገንዘብ ማከማቸቱን እንጂ ገንዘብ ለምን እንዳከማቸ እንኳን እስኪረሳው ድረስ በገንዘቡ የሚያስፈልገውን ማድረግ ያቅዋል፡፡ ሰው ገንዘብን ለማከማቸት ተምሮ ገንዘቡን መጠቀም ካልተማረ ምን ይጠቅመዋል?

ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፤ እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድር ነው? ዘመኑን ሁሉ በጨለማ በኀዘን በብስጭት በደዌና በቍጣ ነው። መክብብ 5፡16-17

ሰው ስኬታማ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን ስኬቱን እንዲደሰትበት ጌታ ይፈልጋል፡፡ ሰው እንዲከናወንለት ብቻ ሳይሆን ክንውኑን ጊዜ ወስዶ አንዲያጥመው ጌታ ይጠብቃል፡፡ ሰውን ለስኬት ብቻ ሳይሆን ስኬቱን እንዲጠቀምበት ጌታ ያሰለጥነዋል፡፡

እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ እድል ፈንታው ነውና። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መክብብ 5፡18-19

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #መደሰት #ስኬት #ህይወት #ስጦታ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on February 6, 2018, in enjoy life, rejoice. Bookmark the permalink. Comments Off on መኖርን የረሳው ሽማግሌ ታሪክ.

Comments are closed.

%d bloggers like this: